ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ ከዚህም በኋላ አስታውሱት ከወህኒቤትም አውጥተው በንጉሡ ፊት አቆሙት ንጉሡም "አግናጥዮስ ሆይ አማልክቶቼን ብታያቸው ውበታቸው ባማረህ ነበር" አለው። ቅዱሱም "ንጉሥ ሆይ አንተ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ብታምን ሙታኖችን የምታሥነሣቸው በሽተኞችንም የምትፈውሳቸው ባደረገህ ነበር"። ንጉሡም "ለፀሐይ ከመስገድ የተሻለ የለም" አለ የከበረ አግናጥዮስም "መንግሥቱ የማያልቀውን ፈጣሪ ትተህ ለተፈጠረ ፀሐይ ትሰግዳለህን?" ብሎ መለሰ ንጉሡም "ለራስህ መልካም አልክ ግን በመተላለፍ የአንጾኪያና የሶርያን ሰዎች ስበሕ ወደ ክርስቶስ አምልኮት አስገባሃቸው እንጂ" አለው። የከበረ አግናጥዮስም ተቆጥቶ "ንጉሥ ሆይ ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው።
❤ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"።
❤ ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጠረም አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት።
❤ ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ በቅዱስ አግናጥዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የአሚናዳብ ልጅ ቅድስት አስቴር፡- የአይሁድ ወገን የሚሆን ስሙ መርዶክዮስ የሚባል የኢያኤሩ ልጅ ከብንያም ወገን የተወለደ የቄስዩ ልጅ አንድ ሰው በሱሳ አገር ነበረ፡፡ ከኢሩሳሌምም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ የተማረከ ነው፡፡ ያሳደጋት ልጅ ነበረችው፡፡ እርሷም የአባቱ ወንድም የአሚናዳብ ልጅ አስቴር ናት፡፡ ከዘመዶቿ ተለይታ በወጣች ጊዜ ልጅ ትሆነው ዘንድ አሳደጋት፡፡ እርሷም እጅግ መልከ መልካም ነበረች፡፡ በአንዲትም ዕለት ንጉሥ አርጢክስስ ብዙ ተድላ ደስታ አድርጎ መኳንንቶቹን ሁሉ ጠራ፡፡ የመኳንንቶቹንም አለቃ አማሌቃዊውን ሐማንንም ጠራው፡፡ እርሱ ከሁሉም መኳንንት የከበረ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ 7ቱን ባለሟሎቹን ጠርቶ ንግሥቲቱን አስጢንን አምጥተው የእቴጌነት ዘውድ ያቀዳጇት ዘንድ እርሷ መልከ መልካም ናትና ለአሕዛብም አለቆች ሁሉ መልኳንና ውበቷን ያሳዩ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንግሥቲቱ አስጢን ግን የንጉሡን ትእዛዝ ባለመቀበል እምቢ አለች፡፡ ከባለሟሎቿም ጋር ትመጣ ዘንድ ባለወደደች ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናዶ ከንግሥትነቷ ሻራት፡፡ ከዚህም በኋላ 127 ከሚሆኑ ከሚገዘቸው አገሮች አንድ ሺህ ቆነጃጅቶችን ይመርጡለት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ከሺህ መቶ፣ ከመቶ ዓሥር፣ ከዓሥር ሦስት መረጡ፡፡ ከሁሉም በመልክ፣ በውበት፣ በደም ግባትም አንደኛ ሆና አስቴር ተመረጠች፡፡ ንጉሡም አስቴርን አነገሣት፡፡
❤ ንጉሡም አስቴርን እጅግ አድርጎ ወደዳት፣ በሴቶቹም ሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ሾማት፡፡ ከዚህም አስቀድሞ መርዶክዮስ አገሩንና አደባባዩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ ባለሟሎች ጋር በአደባባይ ኖረ፡፡ እነርሱም ስማቸው ታራ እና ገቦታ ይባላል፡፡ እርሱም እነዚህ ሁለቱ በንጉሡ ላይ ያሰቡትን ተንኮላቸውን ሰማ፡፡ ንጉሥ አርጤክስስን ይገድሉት ዘንድ ወንጀልን እንዳዘጋጁ ባወቀ ጊዜ መርዶክዮስ ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገራቸውን መርምሮ ቀጣቸውና ይህን ነገር ታሪክና ወግ በሚጻፍበት ላይ ጻፈው፡፡ ሐማ ግን አማሌቃዊ ነበረና መርዶክዮስንና እስራኤላውያንን ይጠላቸው እጅግ ነበርና የአይሁድን ወገን ሁሉ ለማጥፋት ተነሣ፡፡ መርዶክዮስም ይህንን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፡፡ መርዶክዮስም የሀዘኑን መርዶ ለአስቴር እንዲደርሳት አደረገ፡፡ አስቴርም "እስከ ሦስት ቀን ጹሙ ጸልዩ እኔም ደንገጡሮቼም እንጾማለን" ብላ ላከችለት፡፡ ሱባኤዋንም እንደጨረሰች የማቅ ልብሷን አውልቃ ጥላ ወደ ንጉሡ አዳራሽ በገባች ጊዜ "እስከ መንግሥቴም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁና የሆንሽውን ንገሪኝ" አላት፡፡ በዓልንም አደረገና ሐማንና መኳንንቱን ሁሉ ጠራ፡፡ በበዓሉም ላይ ድጋሚ "ላደርግልሽ ፈቅጂውን ንገሪኝ" አላት፡፡
❤ ንጉሡም ለመርዶክዮስ ውለታ ያደረገለትን ሲያስብ ምንም እንዳላደረገለት ዐወቀ፡፡ ወዲያውም ሐማ መርዶክዮስን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ሊገድለው እንደሆነ ተነገረ፡፡ ንጉሡም ሐማን "ንጉሥ የወደደውን ሰው ምን ያደርግለት ዘንድ ይገባል?" አለው፡፡ ሐማም "ይህስ ለእኔ ነው" ብሎ "በክብር ይሾም ዘንድ ሹመቱም አዋጅ ይነገርለት ዘንድ ይገባዋል" አለ፡፡ ንጉሡም ለሐማ ይህን ጊዜ "መልካም ተናግረሃል፣ ለመርዶክዮስ እንዲሁ ይደረግለታል" አለው፡፡ ሐማም የንጉሡን ትእዛዝ ተቀብሎ መርዶክዮስን በፈረስ አስቀምጦ በከተማው በማዞር በክብር መሾሙን በአዋጅ አስነገረለት፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡና አስቴር ለማዕድ አብረው በተቀመጡ ጊዜ ንጉሡ "ጉዳይሽን የማትነግሪኝ ለምንድነው?" አላት፡፡ እሷም ይህን ጊዜ "ንጉሥ ሆይ ዝም ባልኩ በወደድኩ ነበር ነግር ግን ወገኖቼና እኔ ለሞት ተላልፈን ተሰጥተናል" በማለት ሐማ እስራኤላውያንን በአዋጅ ሊያጠፋ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም "ማነው ይህን በማድረግ የደፈረኝ?" አላት፡፡ እሷም ሐማ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሐማ መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው መስቀል ላይ ራሱ ሐማን እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ሐማም ተሰቅሎ ሞተ፡፡ የእስራኤል ወገኖችም ሁሉ በጻድቂቱ አስቴር መዳናቸው በእርሷ ተደርጓልና ሁሉም አመሰገኗት፡፡ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ የእስራኤል ወገኖች ሁሉ ድኅነታቸው በእርሷ ተደርጓልና ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
+++
👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTCW 👈
👉 join# join# 👈
👆👆👆👆👆👆
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለልደት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ለከበረና ለተመሰገነ ለሐዋርያው አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል ሰሎንቅያ በምትባል በምስ አገር ለሆኑ ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ላነጋገሩ ለታላቁ አባት ለአባ ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ ለአሚናዳብ ልጅ ለጻድቂቱ ለቅድስት አስቴር ለዕረፍቷ መታሰቢያና ከዘጠኙ ቅዱሳንን ከፊሎች እነ አቡነ አረጋዊን ላመነኰሱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ቴዎድሮስ ኃይለ መነኰስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከከበረ ከአባት ፊሎንጎስ ዕረፍት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከነገራቸው በከዲህ ከአሉ ጻድቃን በአንዲት ቀን ዕረፍታቸው ከሆነና ከአዝቂርም ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "አባ አቡነ አቡነ መምህርነ እምአዕላፍ ኅሩይ ሐውጽ እምሰማይ ብርሃነከ ከመ ንርአይ አማን ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ"። ትርጉም፦ ከአእላፍ የተመረጥኽ መምህራችን አባታችን ሆይ ብርሃንህን እናይ ዘንድ ከሰማይ ኾነኽ ጎብኝ፤ በእውነት ተክለ ሃይማኖት ፀሓይ ነው። ከሊቁ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ ላይ።
+ + +
❤ የአባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደት፦ ... ከዚህም ቀጥሎ ከዘጠኝ ወር በኋላ በታኅሣሥ በሃያ አራት ቀን ፍስሐ ጽዮን ተወለደ። በዚያችም ቀን በጸጋ ዘአብ ቤት ታላቅ ደስታ ተደረገ መካን የነበረች ሚስቱ እግዚእ ኃረያ ወንድ ልጅ ወልዳለችና። መልኩ እጅግ ድንቅ ነው እንደ ብርሌ እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ነው። ቅላቱም እንደ ጽጌ ረዳ ነው ለነዳያንም ግብዣ አድርገው ዋሉ። ለአገራቸውም ሰዎች እንደየማዕርጋቸው ምሳ አደረጉላቸው።
❤ በዓሉንም ካከበሩ በኋላ ለእግዚእ ኃረያና ለጸጋ ዘአብ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን በጐ ሥራውን ሁሉ እያደነቁ ወደ የቤታቸው ተመልሰው ገቡ። ይህም እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችውም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው ቀን በዕለተ ሰንበት ማለት ነው። ከቀኑ በሦስት ሰዓት ይህ ብላቴና እጆቹን አንሥተሸ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ "ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን አብ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባህሪይ በሕልውና አንድ የሚሆን ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከወልድ ጋር በባህርይ በህልውና አንድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ አመሰገነ።
❤ በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደበት ስለሚወርድ ሕፃኑም መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ አይቶ እሱ እንዳስተማረው ለፈጣሪው እየተገዛ ይህን ሦስት የምስጋና ቃል አቀረበ። እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ልዩ ምስጋና ሰምታ በልቡናዋ እያደነቀች "ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው። ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነውና"። ባሏ ጸጋ ዘአብ ተመልሶ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ልጁ የተናገረውን ነገር ሁሉ ነገረች። ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀና "ልጄ እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ። በቤተ እግዚአብሔርም እንዲህ እያልክ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለሁ" አለ።
❤ ይህንም ብላቴና መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ዘወትር ይመግቡታል። እርሱም ክንፋቸውን ሲጋርዱት ባያቸው ጊዜ ከእነሱ ጋራ ይጫወት ነበር። ሁል ጊዜ ይስቅ ነበር እንጂ ሕፃናት እንደ ሚያለቅሱ አያለቅስም ነበር ቅኖች ሰዎች ዘወትር ደስ ይላችዋልና። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ም16።
+ + +
❤ አቡነ ቴዎድሮስ ኃያል መነኰስ፦ አገራቸው ሮም ሲሆን በ27 ዓመታቸው በአባ ጳውሊ እጅ መነኰሱ። የታላቁ አባት ጳኲሚስ ረዳት የነበሩ ሲሆን መጽሐፍ ሊቀ ጳጳሳትም ይላቸዋል። የመነኰሳት ቁጥር ከጀመሠሪው ከአባ እንጦስ እስከ ቴዎድሮስን ያለው ትውልድ ይባላል። በድንቅ ተአምረሠታቸው ዓለምን ያደነቃቸው ተሰዓቱ ቅዱሳን የተነሱት በዚህ ጻድቅ መናኝ ጊዜ ስለነበር ከፊሎቹንም ያመነኰሷቸው እሳቸው ናቸው። ይለብሱት የነበረው የብረት ልብስ ነበር።
❤ እንጦስ በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል እጀሰ መነኰሱ፤ እንጦንስም መቃርስን አመነኰሱ፤ መቃርስም ጳኲሚስን አመነኰሱ፤ ጳኲሚስም እኚህን ታላቅ መነኰስ ቴዎድሮስን አመነኰሱ። እርሳቸውም እነ አቡነ አረጋወመንና ሌሎቹንመሰ ቅዱሳን አመነኰሰዋል።
❤ በዐፄ ገላውዲዮስና በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን ወደ አገራችን የገባውን ቅዱስ ገድላቸውን ፊልክሲዮስ፣ ገብረ ክርስቶስ፣ አረጋዊና መንፈሳዊና ማር ይስሐቅ ናቸው የተረጐሙት።ጻድቁ የተወለዱባትን ሮምን በከሃዲነቷ በእጅጉ ይጠሏት ነበር። ሮም የእነ ልዮንን የኑፋቄ ትምህርተሰ ተከትላ ሁለት ባሕሪይ በማለቷ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ሆነው አውግዘዋል። በስማቸው የተሠሩ ቤተ ክርስቲያኖች በጎንደር በትግራይ ሁለት አሉ። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።
+ + +
❤ ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ ይህም ቅዱስ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙሩ ነው። በስብከተ ወንጌልም በማገልገል ከእርሱ ጋር ብዙ አገሮችን ዙሮ አስተምሮአል ከዚህም በኋላ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው በውስጥዋመሰ ሕይወተሰ የሆነ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱም ልቡናቸውን አበራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ጣዖትን ለሚያመልኩ ስሕተቻተውን በገለጠላቸው ጊዜ ተቆጡ። ወደ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጠራብዮስ ሔደው ከሰሱት እንዲህም አሉት "አግናጥዮስ የአማልክቶችህን አምልከሸ ይሽራል እኮን ሰዎችንም እያስተማረ ክርስቶስን ወደ ማመን ያስገባቸዋል"። በዚያንም ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "አግናጥዮስ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ የአማልክቶቼን አምልኮስ ለምን ሻርክ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ አስገብተሃቸዋልና" አለው። አግናጥዮስም "ንጉሥ ሆይ ቢቻለኝስ ያክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ባስገባሁህ ነበር" አለው ንጉሡም "ይህን ነገር ትተህ ለአማልክቶቼ ሠዋ አለዚያ በታላቅ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። "በእኔ ላይ የምትሻውን አድርግ እኔ ግን ለረከሱ አማልክቶችህ አልሠዋም ሥቃይህንም እሳትም ቢሆን አንበሳንም ቢሆን አልፈራም ከሕያው ንጉሥ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው። ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ ተቆጣ ያሠቃዩትም ዘንድ አዘዘ በተለያዩ በብዙ ሥቃዮችም አሠቀሠዩት በእጆቹም ውስጥ እሳት አድርገው ከእጆቹ ጋር በጉጠት ይዘው አቃጠሉት።
❤ ከዚህም በኋላ በዲንና በቅባት እያነደዱ ጎኖቹን አቃጠሉ በሾተሎችም ሥጋውን ሠነጠቁ። ከማሠቃየትም በደከሙ ጊዜ የሚያደርጉበትን እስከመክሩ ድረስ ከወህኒ ቤት ጨመሩት ብዙ ቀኖችም በዚያ ኖረ።
👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTCW 👈
👉 join#join# 👈
👆👆👆👆👆👆
1 161
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ቅኔያት ዘበዓለ ቅዱስ ደቅስዮስ ዘዲያቆን የአብስራ ጌታሁን
ጉባኤ ቃና
በካህን ደቅስዮስ ዘተፅህፈ ተአምረ ማርያም ድንግል
እምነአለም አርሀቀ ፅልመተ ኑፋቄ ኃያል
ዘአምላኪየ
መርድአቅኔ ደቅስዮስ በዘላዕለኩሉ ምሑር
ተለአለ በመልእልተኩሉ ለሐዳስ መንበር
አኮኑ ረቂቅ ዘያመፅኦ ምስጢር
ዋይዜማ
ሕዝቅኤል ነቢየፅድቅ
በመንፈስ ቅዱስ ነበበ በቃለትንቢት ክቡር
ለኆኅት ዘከመነፀራ በመንክር ምስጢር
ወበውስቴታ ኢቦአ እንበለአሐዱ መምህር
ዘኩሎ ባረከ በሰማይ ወምድር
ወኢሀሎ በሊሉይ ግብር
በል ሙያዋን ሞክራታ እእእእ😌😂
በ......አገባብ ፍቺው በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ
ካህን ደቅስዮስ ምሳሌ ካህን ሰም ደቅስዮስ ወርቅ ተመስሎ የማድረጊያ ባለቤት
ዘ........አገባብ ፍቺው የ ሙያው ቅፅል ቅፅልነቱ ለተአምር
ተፅህፈ ......እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
ተአምር .........የቅኔ ባለቤት
ማርያም .......የተአምር ዘርፍ
ድንግል ...........የማርያም ቅፅል
እም ......አገባብ ፍቺው ከ ሙያው መነሻ
አለም ........የመነሻ ባለቤት
አርሀቀ ........ማሰሪያ ይስባል እንጂ አይሳብም
ፅልመት ኑፋቄ ምሳሌ ፅልመት ሰም ኑፋቄ ወርቅ ተመስሎ የፅልመት ዘርፍ
ኃያል .........የፅልመት ቅፅል😇
1 161
""የገሃድ ፆም""
***
፦በልደት ገሃድ አለ?
፦ገሃድ ወይም ጋድ ትርጉሙ ምንድነው?
፦የገናን ፆም ሳይፆሙ የመጨረሻዋን ቀን የሚፆሙ ምዕመናን በተመለከተ።
፦የዘንድሮ ገና ዓርብ ላይ ውሏልና ዓርብ ይፆማል?
፦ለእነዚና መሰል ጥያቄዎች በመጠኑ የቀረበ መልስ ነው አንብበው ያጋሩ።
ምንጭ፦ፍ/ነገሥት አን 15 ቁ 566ና 603
የኢ/ቤ/ታሪክ አባ ጎርጎሬዎስ ሊቀጳጳስ
፦በየ ዓመቱ በኦርቶዶክስ ምዕመናን ከሚነሱት ጥያቄዎች አንዱ በልደትና በጥምቀት ላይ ቀድሞ በሚገኝ ዕለት ስላለው የፆም ሁኔታ ነው።
በዕርግጥ ቤተክርስቲያን ለሁሉ መልስ ያላት ናትና ሁሉን በመልክ በመልኩ አሰናድታ በማስቀመጥ ለልጆቿ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ መልሱን ታቀርባለች።
፦ገሃድ ወይም ጋድ በጥምቀትም በልደትም አለ አገባቡ ግን ይለያል ይላሉ የቤተክርስቲያን አባቶች።
ገሃድ ወይም ጋድ ትርጉሙ መገለጥ፣መለወጥ፣ለውጥ፣ምትክ የሚሉ ስያሜዎችን ሲይዝ እንደ አገባቡ ለገናም ለጥምቀትም እንጠቀማለን።
ለገና ሲሆን ገሃድ ምትክ የሚለው ሳይሆን መገለጥ የሚለውን ትርጉም ይይዛል።
ለገና የገና ፆም እስከ በዓሉ ድረስ ስለሚፆም ፆሙ እስከ በዓሉ ዋዜማ ይፆማልና ከዚህ አንፃር በዓሉ በታህሳስ 29 ከሆነ ታህሳስ 28 መጀመሪያውኑ ፆም በመሆኑ ምዕመናን ይፆሙታል ነገር ግን ወሩን ሙሉ ሳይፆሙ የሰነበቱ ምዕመናን አንዷን ቀን ብቻ ገሃድ ነው ብለው መፆማቸው አግባብ አይደለም በማለት አባቶች ይመክራሉ ይህ ፈፅሞ ስህተት ስለሆነ ምዕመናን ሁሉ ፆሙን በመፆም ከጌታ ፍቅርና ፀጋውን እንዲያገኙ ያሳስባሉ ካልሆነ አንዷን ቀን ብቻ በመፆም ገሃድ ነች በማለት ራሳቸውን አያጃጅሉ።
የሚገርመው ሥጋ ቤቶች ጭምር ሙሉ የገናን ፆም ሲሸጡ ከርመው የመጨረሻዋን ዕለት ዘግተው በማግስቱ መክፈታቸው ስህተት ነው።
የገና ፆም ምዕመናን ሁሉ ከሰባት ዓመት ጀምሮ እንዲፆሟቸው በአዋጅ ከተደነገጉ ሰባት አፅዋማት አንዱ በመሆኑ ሙሉውን መፆም እንጂ ሲበሉ ቆይተው የመጨረሻዋን ዕለት ገሃድ ናት ማለት ስህተትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አለማወቅ ጭምር ነው ለገና ገሃድ ስንል ምትክ ማለታችን አለመሆኑን መዘንጋት ፈፅሞ የለብንም እና አንዷን ቀን ብቻ መፆም ስርዓተ ቤተክርስቲያን አይደለም።
ለገና ገሃድ ለምን ተባለ ገሃድ መገለጥ፣መታየት ነው ብለናል የክርስቶስ ሰው መሆን መገለጡ፣
አምላክ በድንግል ማህፀን ተወስኖ መገለጡ ወይም መታየቱ ለማብሰር የመጨረሻዋ ቀን ገሃድ ትባላለች ከላይ እንደ ተመለከትነው መገለጥ፣መታየት የሚለው ትርጉም እዚህ ላይ ግልፅ ይሆናል።
ልክ በአቢይ ፆም ፆመ ህርቃል እንዳለ ፆመ ህማማት እንደሚፆም ሁሉ በገና የጌታችንን ሰው መሆን የጌታን መገለጥ በማሰብ የመጨረሻዋን ቀን ገሃድ እንላታለን።
ልደት ዓርብና ረቡዕ ሲውል ዕለቱ ከጌታ ልደት በላይ ደስታ የለምና፣ከክርስቶስ መወለድ በላይ ሃሴት የለምና አርብ ረቡዕ ፆምነታቸው ይሻራል ፍስክ ይሆናል በክርስቶስ መወለድ ያዘነው ሄሮድስ እና ጭፍሮቹ እንጂ ክርስቲያኖች አያዝኑም ፆም ማዘን፣መተከዝ፣መጎሳቆል፣መራብ መጠማት፣መስገድ መድከም ማለት ነውና በጌታ ልደት እነዚህ አይኖሩም።
አባቶች እንዲህ ይላሉ
"በጌታ ልደት ማዘን እንደ ሄሮድስና ጭፍሮቹ፣በስቅለቱ መዝፈን እንደ አይሁድ ያስቆጥራል።"
ስለዚህ የገና በዓል ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነውና ዓርብ ረቡዕ ላይ ቢውል ፆምነቱ ተሽሮ ፍስክ ይሆናል ልደቱን መገለጡን በታላቅ ደስታና ሃሴት እናከብረዋለን።
ቅዳሜና እሁድ ላይ የልደት ዋዜማ ቢውል ከጥሉላት ምግቦች መፆም ግድ ሲሆን ከእህል ውሃ ግን አይፆምም።
፦የጥምቀት ጋድ
ጥምቀት ከጌታችን ዓበይት ዘጠኙ በዓላት አንዱ ሲሆን በበዓሉ ዋዜማ
1 161
የዕለቱ ምስባክ፦
ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ፤
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ፤
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ። መዝ ፸፱፥፩
የዕለቱ ምንባባት
ዕብ ፲፫፥፲፮ - ፍ፤
፩ጴጥ ፪፥፳፩ - ፍ፤
ግብ ፲፩፥፳፪ -ፍ፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፲፥፩ - ፳፪፤
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሥላሴ 'ጥር ፯
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCW
ነግሥ
ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ፤ ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ፤ ኃይልየ ሥላሴ ወጸወንየ ሥላሴ፤ በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ።
@EOTCW
ዚቅ
ዘለብሰ ስብሐተ፤ ሀሎ ሰማያተ፤ እምድንግል ቃል ሥጋ ኮነ፤ በቤተ ልሔም ተወልደ።
ወረብ፦
ዘለብሰ ስብሐተ ዘለብሰ ስብሐተ ሀሎ ሰማያተ፤
እምድንግል ቃል ሥጋ ኮነእምድንግል ቃል።
@EOTCW
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤ ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤ አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ።
@EOTCW
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ ዘበተዋሕዶ ይሤለስ፤ እምኀበ ትጉሃን ይትቄደስ፤ እሳተ ሕይወት ዘኢይትገሠሥ፤ ወዘኢይጤየቅ ለዓይን ረቂቅ መንፈስ፤ ንሰግድ ለትሥልስቱ አሐተ ስግደተ፤ ወሎቱ ናቄርብ ስብሐታተ።
@EOTCW
ማኅሌተ ጽጌ
ተፈሥሒ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ፤ ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ፤ እንዘ ትዘብጥ ከበሮ ቅድመ አዕላፈ ኤፍሬም ወምናሴ፤ ለተአምርኪ ትነግር ውዳሴ፤ ማርያም እኅቱ ለሙሴ።
@EOTCW
ዚቅ
በፈቃደ አቡሁ ወረደ ኀበ ማርያም ተአንገደ፤ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ።
@EOTCW
ወረብ፦
በፈቃደ አቡሁ ወረደ ተአንገደ በደብረ ብርሀን ፤
በድንግልናሃ ንጹሕ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ።
@EOTCW
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላውያተ፤ ለረኪበ ስሙ ኅቡዕ አመ ወጠንኩ ተምኔተ፤ እምግብርክሙ ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ፤ መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚአክሙ ገጻተ፤ እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ።
@EOTCW
ዚቅ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ፤ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ፤ ነአምን ዘንተ ሥላሴ ፩ ውእቱ አምላክ ፍጹም፤ ዘእምኔሁ ለአብ ወልድ ተወልደ፤ በአምሳለ ዚአሁ፤ ኅቡር ኅላዌሁ፤ ነአምን ንሕነ ነአምን።
@EOTCW
ወረብ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ/፪/
፩ ውእቱ አምላክ ፍጹም ፩ ውእቱ/፪/
@EOTCW
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአጻብኢክሙ እለ እምአጽፋር ኢይትሌለዩ፤ ለቤትክሙ ሥላሴ ዘኢየኃልቅ ንዋዩ፤ አመ አብዓልክሙ ሰብአ ድኅረ አንደዩ ጌጋዩ፤ ዘኢርእዩ እምቅድመ ዮም መላእክተ ሰማይ ርእዩ፤ ወአግብርተ ሰብእ መላእክት ተሰምዩ።
@EOTCW
ዚቅ
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት፤ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ።
@EOTCW
ወረብ
ርእይዎ 'ኖሎት'/፪/ ርእይዎ አእኮትዎ/፪/
ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል/፪/
@EOTCW
መልክአ ሥላሴ
ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ፤ መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ሰብዓተ፤ ህየንተ አሐዱ ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምዕተ፤ ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ፤ ወዲበ ዐሠርቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ።
@EOTCW
ወረብ
ጸግዉኒ አጋዕዝትየ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ/፪/
ወዲበ ዐሠርቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ/፪/
@EOTCW
ዚቅ
ስብሐት ለከ ስብሐት ለዘወለደከ፤ ስብሐት ለዘሠረፀ እምአቡከ፤ ዘዕሩይ ምስሌሁ ወምስሌከ፤ በከዊነ ዘሀሎ ወይሄሉ፤ ለዓለመ ዓለም።
@EOTCW
ወረብ
ስብሐት ለከ ስብሐት ለዘወለደከ ስብሐት ለዘሠረፀ እምአቡከ/፪/
ዘሀሎ ወይሄሉ ዘዕሩይ ምስሌሁ/፪/
@EOTCW
አንገርጋሪ
ኲሉ ይሰግድ ለሥላሴ፤ ወይትቀነይ ኲሉ ለመንግሥተ ሥላሴ፤ እስመ ኮነ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል፤ ወበዓይኑ ይኔጽር ቀላያተ።
@EOTCW
አመላለስ
እስመ ኮነ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል እስመ ኮነ/፪/
ወበዓይኑ 'ይኔጽር'/፪/ ቀላያተ/፪/
@EOTCW
ወረብ
ኲሉ ይሰግድ 'ለሥላሴ'/፪/ ኲሉ ይሰግድ/፪/
ወይትቀነይ ኲሉ ለመንግሥተ 'ሥላሴ'/፪/ ኲሉ ይሰግድ/፪/
@EOTCW
እስመ ለዓለም
እገኒ ለከ እግዚኦ አምላኪየ ዘዲበ ሠረገላ ኪሩቤል ትነብር፤ ኢየሐፅፅ ወልድ እምህላዌሁ ለአብ፤ እንዘ ሀሎ ምድረ ኀቤነ ነገረነ ዜናከ፤ ማርያምሰ ተንከተመ እግዚአብሔር ኮነት ለነ፤ ዛቲ ይእቲ ትምክሕትነ ሰምዓ ግዕዛንነ፤ ወተወልደ መድኃኒነ ፍሥሐነ ወክብርነ፤ ወልዶ ዘያፈቅር ፈነወ ለነ።
@EOTCW
አመላለስ፦
ወተወልደ መድኃኒነ ፍሥሐነ ወክብርነ[፪]
ወልዶ ዘያፈቅር ፈነወ ለነ።[፬]
@EOTCW
ወረብ
እገኒ ለከ አምላኪየ ዘዲበ ሠረገላ ኪሩቤል ትነብር/፪/
ኢየሐፅፅ ወልድ እምህላዌሁ ለአብ ህላዌሁ/፪/
👇👇👇👇👇
👉share# 👈
👉@EOTCW👈
🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹
@EOTCW
#Join & share#
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሥርዓተ ዋዜማ ዘሥላሴ 'ጥር ፮'
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዋዜማ
ሃሌ ሉያ
ፈቂዶ ይርዳዕ ወይቤዙ ወልደ አብ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ፤ ተኀቢዖ ለኲሉ ኃይል፤ ለእለ በሰማይ ማኅደሮሙ በኢያእምሮ ሠወሮሙ፤ መጽአ ኀቤነ ወለብሰ ሥጋነ፤ ዘምስለ ኖኅ ተካየዳ፤ ወምስለ አብርሃም ተዓረከ ወምስለ ያዕቆብ ነገደ፤ መጽአ ኀቤነ ወለብሰ ሥጋነ፤ ምስለ ሙሴ ተናገረ ወምስለ ዳዊት ዘመረ፤ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ፤ መጽአ ኀቤነ ወለብሰ ሥጋነ፤ ስምዖን ተወክፎ ወዮሐንስ አንጸሮ፤ ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፤ መጽአ ኀቤነ ወለብሰ ሥጋነ፤ ኢኃሠሠ አበ በዲበ ምድር፤ ወኢ አመ በሰማያት፤ አሀዱ ውእቱ እግዚአብሔር፤ አብ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ።
@EOTCW
አመላለስ፦
አሀዱ ውእቱ እግዚአብሔር፤
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
@EOTCW
ወቦ ዘይቤ
ይቤሎ አብ ለወልዱ፤ ነዓ ረድ እምሰማይ ዲበ ምድር፤ ከመ ትኩን በኲረ በላዕለ ብዙኃን፤ ዜናዊ ሰማያዊ፤ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ።
@EOTCW
አመላለስ፦
ዜናዊ ሰማያዊ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤
ዜናዊ ሰማያዊ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ።
@EOTCW
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
@EOTCW
ተወልደ በተድላ መለኮት፤ ብሑተ ልደት እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ተወልደ በተድላ መለኮት።
@EOTCW
እግዚአብሔር ነግሠ፦
@EOTCW
ተወልደ መድኅን ክብረ ቅዱሳን፤ እማርያም ድንግል፤ አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ ዕብን፤ ወትቤ መድኅኑ ለዓለም።
@EOTCW
ይትባረክ
ጸሎተ ፫ቱ ደቂቅ: ፱
ይቤሎ እግዚእ ለእግዚእየ፤ ንበር በየማንየ፤ አንተ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ዘሠምረት ነፍስየ።
@EOTCW
ሰላም
ይእዜኒ ንትልዋ ለሰላም፤ እስመ ተወልደ ክርስቶስ ዮም በሀገረ ዳዊት፤ አናህስዮ አበሳነ ወልዱ ለአብ፤ ቀዳሜ በኲሩ ኃይሉ ለአብ፤ መጽአ ኀቤነ ይክሥት ብርሃነ፤ ተመሲሎ ኪያነ፤ ሰብእ ዘይከውን ኲሎ ኮነ፤ ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ።
@EOTCW
አመላለስ፦
መጽአ ኀቤነ ይክሥት ብርሃነ፤[፪]
ተመሲሎ ኪያነ ሰብእ ዘይከውን ኲሎ ኮነ ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ።[፬]
👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTCW 👈
👉 join#join# 👈
👆👆👆👆👆👆
1 161
ሰላም ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በተደጋጋሚ ቀጣይ ያሉትን ስርአተ ማህሌቶችን ላኩልን የሚል ጥያቄ ደርሶናል። አሁን ተፅፎ ስላለቀ ከደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃል።
1 161
ውድ የዚህ ቻናል ተከታታዮች በሙሉ ከባለፈው ጀምሮ ብዙ ሰዎች ከታህሳስ ገብርኤል ጀምሮ ያሉትን ስርአተ ማህሌትን ይለቀቅልን እያሉ ነው ፤ምናልባት ያላያችሁት ሰዎች ካላችሁ ከላይ ሁሉም አሉ ፤ማለትም እስከ ገና ድረስ ያሉትን በአላት።
በቅርቡ ደግሞ ከጥር ጀምሮ ያሉትን በአላት እንለቃለን።
ለሎት አንድ አንድ አስተያየቶች @YHFTED584932 ላይ ያድርሱን ተቀባይ ነን!
ሌላ ደግሞ ለክርስቲያን እህት ወንድሞቻችን ይህን ቻናል ቢያንስ ከ1-5 ሰዎችን share እያደረጋችሁ ቃለ እግዚአብሔርን ከማስፋፋት አንፃር የበኩሎትን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እናመሰግናለን!!
1 161
+ + +
❤የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 1፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥30-35። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥11-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው።መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
1 161
ወረብ☘☘☘☘
በሰዋሰው ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም ለክብረ በአላት ማውጫ።
በተጨማሪም-ዋዜማ
-የእለቱን ምስባክ
-የእለቱን በአላት በስንክሳር
ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
https://t.me/Eotcw
1 161
እንደም ቆያችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፤በግሩፕ ላይ ስለ ማህሌት እየተማማርን እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህም ሁላችሁም እንድትከታተሉ እና ሁላችሁም ቢያንስ ለ10 ሰዎች ሼር እንዲሁም አድ በማድረግ የበረከቱ አካል እና ተካፋይ ይሁኑ!!
?👇👇👇👇👇👇👇👇👇
