fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

ች በእግዚአብሔር ጸጋና በቅድስና ፍጹማን ነበሩ። ❤ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ተአምራትን ያደርግ ነበር በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር እነርሱም ከቤተ ክርስቲያኑ የጉድጓድ ውኃ ቀድተው በሽተኞችን ያጥቧቸዋል ወዲያውም ከበሽታቸው ይድኑ ነበር። ❤ አባታቸውም የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ በዚያን ሰዓት ቀሲስ ብንያሚን ቊርባን ያሳርግ ዘንድ የቅዳሴ ልብስ ለብሶ በቤተ መቅደስ ነበረ መልክተኞችም መጥተው አባቱ ለመሞት እንደ ተቃረበ እርሱንም እንደሚፈልገው ነገሩት። ብንያሚንም "የቊርባኑን ሥርዓት ሳልፈጽም ልብሰ ተክህኖውን አላወልቅም ከመሞቱ በፊት እንደየው እግዚአብሔር ከፈቀደ ይቆየኛል ካልሆነም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ። አባቱም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ላከ አባ ብንያሚን ግን የቊርባኑን ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ አባቱ ሔደ ሙቶም አገኘው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅዱሳትም እጅግ አዘነ እነርሱ በእርሱ ዘንድ እየኖሩ ዕቃዎችን ያኖረበትን ቦታ አላመለከታቸው ነበርና። ❤ ወንድሙ ብዮክም አባታቸው ስለ አስቀመጠው ንዋየ ቅዱሳት ወደ አስቆጥስ ገዳም ወደ ቅዱሳን አረጋውያን ሒዶ እንዲጠይቅ መከረው። አባ ብያሚንም በሔደ ጊዜ የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት አባ ዳንኤልን አገኘው አባ ዳንኤልም ስርሱ የመጣበትን ሥራ ሁሉ ነገረው ነገር ግን ወደ አንድ ጻድቅ ሰው እንዲሔድ አዘዘው እርሱ ንዋየ ቅዱሳቱ ያለበትን እንደሚያስረዳው ነገረው። በሔደም ጊዜ እንደ አመለከተው ያንን ጻድቅ ሰው አገኘው። እርሱም ገልጾ አስረዳው በተመለሰም ጊዜ እንዳስረዳው አገኘው። ❤ ከዚህም በኋላ በመልካም ገድል ሁሉ ከወንድሙ ጋራ ተጠምዶ ኖረ። ለሕሙማን ነፍሳቸው ሳትወጣ ያቀብሏቸው ዘንድ ከቅዱስ ቊርባን ከፍለው በሣጥን የሚኖር ሥርዓት ነበራቸው ሰይጣንም ከይሲን አነሣሣውና ሣጥኑን ቀድዶ ከዚያ ከቅዱስ ቊርባኑ በላ። ❤ ብዮክና ብንያሚንም ይህን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዘኑ ከይሲውንም ገደሉት ከዚህም በኋላ የተቀደሰውን ቊርባን ስለ በላ ከይሲውን ይበሉት ዘንድ ተማከሩ ፈቃዱም ከሆነ እንዲያስረዳቸው እግዚአብሔርን ለመኑት የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጸላቸውና ያን ከይሲ ይበሉት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም በሉት። ከበሉትም በኋላ ዐረፉ። ❤ እግዚአብሔርም ሥራቸውንና ገድላቸውን ለአንዲት ድንግል ሴት ገለጸ እርሷም የእሊህን ቅዱሳን ገድል ለሕዝብ ተናገረች። እርሱም የአማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 1 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቅፍሮንያ አስናኒሃ ዘሰበሩ። ወመለያልያቲሃ ዘመተሩ። ወዘንተ ኲሎ እንዘ ይገብሩ። ኢክህሉ በጽንዖሙ ለዲዮቅልጥያኖስ ማኅበሩ። ከመ ይምጥዋ ለክርስቶስ እምፍቅሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ1። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ለስሒት መኑ ይሌብዋ። እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ። ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ። መዝ 18፥12። የሚበበው ወንጌል ዮሐ 20፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፩ (1) ቀን። ❤ የተባረከ የሐምሌ ወር ቀኑ ዐሥራ አራት ሰዓት ነው ከዚህም በኋላ ያንሳል። ❤ እንኳን ለሐዋርያው ለቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን ላደረገበት ቀን መታሰቢያ በዓል፣ ለሊቀ ጳጳሳቱ ለአባ አግናጥዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ፣ ሰማዕት ለሆነች ሰውነቷን ለእግዚአብሔር ለሰጠች ለቅድስት ድንግልና ለመስጋድልት ለቅፍሮንያ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓልና ለቅዱሳን መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ከክልዮስና ከበርተሎሜዎስ ከጻድቁ ከገብረ መድኅንም ከዕረፍታቸው መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሽታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ያደረገው ተአምር ይህ ነው፦ ሥራ የሚሠራ አንድ ጎልማሳ ነበር ከሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም እጅ የተባረከ እንጀራ ከሕዝብ ጋራ ተቀበለ። ወደ አፉም ሊጨምረው በወደደ ጊዜ እጆቹ ደረቁ። ያዩት ሰዎች ግን በዚህ ሰው ላይ የሆነውን ለሐዋርያው ነገሩት። ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጠራው "ልጄ ሆይ አትፈር ንገረኝ የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ ዘልፎሃልና" አለው። ያም ሰው ከሐዋርያው እግር በታች ሰገደ "መልካም ሥራ የሠራሁ መስሎኝ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁ አንዲት የጠጅ አበዛ ሴት ነበረች አስቀድሞ ወደርሷ እገባ ነበር። አንተም በንጽሕና እንድትኖር አስተማርከን ያችም ሴት ከእርሷ ጋራ እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ ስለዚህም ሰይፍ አንሥቼ አረድኳት" ሐዋርያውም "እንዴት እንዲህ ያለ ቁጣና የአውሬ ሥራን ሠራህ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላም ውኃ ያመጡ ዘንድ ሐዋርያው አዘዘና በውኃው ላይ ጸለየ ጎልማሳውንም "በእግዚአብሔር ታምነህ እጆችህን ታጠብ" አለው ሲታጠብም ዳነ። ❤ ከዚህም በኋላ "የዚያች ሴት በድን ወደ አለበት ና ምራኝ" አለው ያም ጎልማሳ መርቶ ወደ ቦታዋ አደረሰው በደረሰም ጊዜ አይቷት እጅግ አዘነ። ወደ ውጭም አውጥተው በዐልጋ ላይ ያኖሯት ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ እጁንም በላይዋ ጭኖ ጸለየ። ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጎልማሳውን "ሒድ እጇን ይዘህ እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ በላት" አለው። እርሱም እንዳዘዘው አደረገ እጇንም ይዞ ሳባት ፈጥናም ተነሣች ሐዋርያውንም አየችው ዐልጋዋንም ትታ ከሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ እግር በታች ሰገደች የልብሱንም ጫፍ ይዛ "በአንተ ዘንድ አደራ ያስጠበቀኝ ባልጀራህ ወዴት አለ" አለችው። ❤ ሐዋርያውም "ወደየት ደርሰሽ ነበር ንገሪኝ" አላት እርሷም "አንተ ከእኔ ጋራ እያለህ እንዴት ንገሪኝ ትለኛለህ" አለችው "ያየሽውን ንገሪ" አላት። "ከሥጋዬ በተለየሁ ጊዜ አንድ ልቡሱ የቆሸሸ ሽታውም የሚከረፋ ጠቋራ ተቀበለኝ የእሳት ጉድጓድና የእሳት መንኰራኵር ወደአለበት ቦታ ወሰደኝ ደግሞም እድፍንና ትልን የተመላ ጒድጓድን አየሁ ነፍሳትም በውስጡ ይንከባላሉ በዚያም ምላሳቸው የተንጠለጠሉ አሉ በጠጉራቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በእጆቻቸውም በእግሮቻቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በላያቸውም ድኝ ይጤስባቸዋል ያስጨንቋቸወልም። ያ የሚመራኝም "እኒህ ነገረ ሰሪዎች፣ ሐሰተኞች፣ አመንዝራዎችና ቀማኞች፣ ሌቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች ድኆችንና በሽተኞችን የማይጎበኙ የእግዚአብሔርንም ሕግ የማያስታውሱ ናቸው ስለዚህ እንደ ሥራቸው ይቀጣሉ አለኝ" አለች። ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ከዚያ የነበሩትን "ይቺ ሴት የምትለውን ሰማችሁን ያለው ሥቃይ ይህ ብቻ አይደለም የኃጢአትን ሥራና ክፉ አሳብን ትታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። ትሕትናን የዋህነትንና ፍቅርን ንጽሕናንም ጠብቁ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ጸጋን ትቀበላላችሁ" አላቸው። ❤ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሕዝብ አመኑ ለድኆችም ምጽዋትን ሊሰጡ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው አመጡ ለድኆች ምጽዋት መስጠት ለሐዋርያው ልማዱ ነበርና። ወሬውም በየአገሩ ሁሉ ደርሶ በሽተኞችን ሁሉ አጋንንት የያዟቸውንም አምጥተው በጎዳና ዳር አኖራአቸው ሁሉንም በእግዚአብሔር ኃይል አዳናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች ቅድስት ድንግልና መስተጋድል ቅፍሮንያ፦ እርሷም በደናግል ገዳም ቊጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች። የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው። ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት። በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት። ❤ ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር። ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች። በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ። እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ። እመ ምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች። ❤ በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኖች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም። ቅድስት ቅፍሮንያን "በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት" አለቻቸው። እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው። ❤ ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት። ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦርያናም "አንተ ከሀዲ ይችን ታናሽ ብላቴና እንዳጎስቈልሃት እግዚአብሔር ያጎሳቊልህ ዘንድ አለው" ብላ ጮኸች። ❤ መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህችን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲአሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ። ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች። ❤ ከዚህ በኋላ ደግሞ ምላሷንና ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ሕማም አስነሣት። መኰንኑም እርሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች። ❤ አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ቅፍሮንያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን፦ እሊህም ቅዱሳን በግብጽ ደቡብ በቴዎዳ አውራጃ ቱና በሚባል አገር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ነበሩ። እነርሱም ወንድማማች ነበሩ። አባታቸውም የቤተ ክርስቲያን ሹም የሆነ ደግና የዋህ ሰው ነበር እሊህም ሁለቱ ልጆ

+7
1.mp31.29 MB

🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚 አመ ሰላሳሁ ለሰኔ ዮሐንስ መጥምቅ ስርአተ ማህሌት ❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ ሥርዓተ ነግሥ:- ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCW @EOTCW መልክዐ ሥላሴ፦ ሰላም ለገብዋቲክሙ እለ ዕሩቃን እምልብሰ ወርቅ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሥርግዋነ መፍርህ መብረቅ፤ መንገለ(ኀበ) ፍኖቱ ምጽዋት ለቆርኔሌዎስ ጻድቅ፤ ይምርሐኒ ወንጌልክሙ እግዚአ ፍኖት ረቂቅ፤ ዘጸያሒሁ ዮሐንስ መጥምቅ ዚቅ፦ ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ነቢየ ልዑል/2/ እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ/2/ @EOTCW @EOTCW ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። @EOTCW @EOTCW መልክዐ ዮሐንስ መጥምቅ፦ ሰላም ለጽንሰትከ እንበለ ሀጢያት ወግማኔ፤ ወለልደትከ ሰላም አመ ሰላሳሁ ለሰኔ፤ ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ ፤ አዝንም መና አዕምሮ ወኅብስተ ጥበብ መድሀኔ፤ ኀበ ሕዝበ ልብየ ኀበሩ ወገብሩ ኩርጓዴ፤ @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ሰላም ለጽንሰትከ እንበለ ሀጢያት ወግማኔ ወለልደትከ ሰላም አመ ሰላሳሁ ለሰኔ/2/ ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ ደመና ሰማይ/2/ @EOTCW @EOTCW ዚቅ፦ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ ወአርኃወ ኆኃተ ሰማይ፤ አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ ወወሀቦሙ ኅብስተ ሰማይ ፤ወኅብስተ መላእክቲሁ በልዑ ዕጓለ አመሕያው @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ ወአርኃወ ኆኃተ ሰማይ/2/ አዝነመ ሎሙ መና መና ይብልዑ/2/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ዮሐንስ መጥምቅ፦ ሰላም ለከናፍሪከ ነቢበ ከንቱ ዘኢኀሠሣ፤ ወለአፉከ ሰላም ዘኢጥዕመ እክለ አበሳ፤ ዮሐንስ ሕጻን ለእምከ ውሣጤ ከርሳ፤ እፎ አንፈርዓጽከ እንዘ ትሰግድ ለንግሳ፤ አመ ሐወጸትከ ማርያም አምላከ ፀኒሳ @EOTCW @EOTCW ዚቅ፦ ትቤላ ኤልሳቤጥ ለማርያም፤ ሶበ ሰማዕኩ ቃልኪ፣ አንፈርዓፀ ዕጓል፤ በውስተ ከርስየ በፍስሐ @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ትቤላ ኤልሳቤጥ ለማርያም፤ ሶበ ሰማዕኩ ቃልኪ/2/ አንፈርዓፀ ዕጓል በውስተ ከርስየ በፍስሐ በውስተ ከርስየ/2/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ዮሐንስ መጥምቅ፦ አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ በጽዋዔ፤ እንዘ አስተዋድድ ቃለ መጠነ ረቡዕ ሱባዔ፤ ተወከፈኒ ዮሐንስ ምስለ በርተሎሜዎስ ቀርነ ትንሳዔ፤ ከመ ተወከፈ እግዚእከ ቅድመ ወንጌላዊት ጉባኤ፤ እምዕደ አሐቲ ብዕሲት ጸራዕቀ ክልዔ @EOTCW @EOTCW ዚቅ፦ ተወከፍ ጸሎትነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ ወውሳጤሁ ዘተናገርኮ ለዮሐንስ በደብረ ጽጌ በዓምደ ደመና @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ተወከፍ ጸሎትነ ጸሎትነ ተወከፍ/2/ ዘተናገርኮ ለዮሐንስ በደብረ ጽጌ በዓምደ ደመና/2/ @EOTCW @EOTCW ዓርኬ፦ ሰላም ለልደትከ ከመ ገብርኤልክላስስት ስድስተ አውርኃ ለልደተ ክርስቶስ እንተ ቀደሞ፤ ዮሐንስ ስኂን ወምዑዝ እምቀናንሞ፤ ለለነበብኩ በጽሒቅ ለመልክዕከ ሰላሞ፤ ከመ ክላስስት በሕጽንከ ሴሞ @EOTCW @EOTCW ዚቅ፦ በእንተ ርእሱ ይነግር መድኃኒነ ወይቤ ፤ ዘይንዕሶ የዓብዮ ሃሌ ሉያ በመንግሥተ ሰማያት ፤ስድስተ አውርኃ የዓብዮ፤ ዮሐንስ ለኢየሱስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ተጠምቀ ሰማያዊ በዕደ መሬታዊ @EOTCW @EOTCW ምልጣን፦ ስምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሉ ላዕሌሃ ወተፈሦሑ ፍስሓ ፈድፋደ ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካሪያስ ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ @EOTCW @EOTCW ወረብ፦ ስምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ ለኤልሳቤጥ/2/ እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሉ ላዕሌሃ/2/ እስመ ለአለም፦ ወፈቀዱ ይሰይምዎ በስመ አቡሁ ዘካሪያስ ወትቤ እሙዮሐንስሀ ይሰመይ ወይቤልዎ፡አልቦ ዘሰማዕነ ዘከመዝ ስም እምአዝማድኪ ወዘካርያስ ሰአለ መዝሀፈ እንዘ ይብል ዮሀንስ ስሙ ፤ማ:- እስመ ከማሁ ዮሀንስ ብሂል ፍሱህ ወልድ ብሂል በትርጓሜሁ 👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

ለሰኔ ዮሐንስ መጥምቅ ስርአተ ማህሌት እንዲመች ብለ ቀድምን የሰኔ 28 29 እና 30 ስንክሳሮች ስለ ለቀቅን ከላይ👆👆 እየተመለሳችሁ የየዕለቱን ስንክሳር እድታነቡ ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሰኔ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን ለነቢዩ ለሰማዕቱ ለካህኑ ለሐዋርያው ለመጥምቀ መለኮት ለተወለደበት (ለልደት) በዓልና በሕንደኬ ካሉ ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ ለአባ ጌራን ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ማርያና፣ ከማርታ፣ ከመነኰስ ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸውና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ሰምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ። እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ። ወተፈሥሁ ፍሥሃ ፈድፋደ። ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካርያስ። ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። ❤ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት። ❤ አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ❤ ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። ❤ "የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"። ❤ ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። ❤ ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ገድለኛው የሆነ አባ ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር። ❤ ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት። ❤ በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ። ❤ ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች። ❤ ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት። ❤ ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን። ❤ የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወተወከልኩከ እንዘ ሀሎኩ ውስተ አጥባተ እምየ። ላዕሌከ ተገደፍኩ እማኅፀን። እምከርሠ እምየ አንተ አምላኪየ"። መዝ 21፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥57-80። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/EOTCWW

photo content

photo content

❤ ቅዱስ አባ ሖርንም ከቅባትና ከተቀመመ የነዳጅ ቅመም ጋራ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት እርሱም ያለ ሕማም ሁኖ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር ይህንንም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም እጅግ አደነቀ ደነገጠም። ንጉሡ ግን ተቆጣ በእጁም ጦር እንዳያዘ ወደ ብረት ምጣዱ ሒዶ ቅዱስ ሖርን ወጋው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ❤ እንዲሁም ወንድሙ አባ ብሶይን ብዙ ሥቃይን ካሠቃዩት በኋላ ራሱን በይፍ ቆረጡት። ሁሉም በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለከ ለብሔረ አግዓዚ ንጉሣ። ቴዎድሮስ ዕጓለ አንበሳ። ተዝካረ በዓልከ ዮም በጥብሐ አባግዕ ወእንሰሳ። አኮ ዘገብረት ባሕቲታ እምከ ጽዮን ሞገሳ። ደመናትኒ አንጠብጠቡ ዓሣ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ29። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና። ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር። ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር"። መዝ146፥8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ቴዎድሮስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን። https://t.me/EOTCWW

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሰኔ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን ለንጉሥ ዳዊት ልጅ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለጻድቁ ለቅዱስ ቴዎድሮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለከበረ ለቅዱስ ዐምደ ሚካኤል ለሥጋው ፍልሰት፣ ለንጹሕ ጻድቅ ለሆነ ለሮሜ ንጉሥ ለቅዱስ ማርቆስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ከቆና ገዳም ለሆኑ ለሰባት መስተጋድላን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዐረፍታቸው በዓል መታሰቢያና ለቅዱሳን ለአባ ሖር፣ ለአባ ብሶይና ለእናታቸው ይድራ ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ ለሆነ ለአባ ሖርሳም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከክብር ባለቤት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደበት ከልደቱ (ከበዓለ ወልድ) ከወራዊ ከመታሰቢያ በዓል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የንጉሥ ዳዊት ልጅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቅዱስ ቴዎድሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ በዕውቀትና በተግሣጽ አደገ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የተማረ ደግሞም ቀስት ማፈናጠርንና ፈረስ ግልቢያን ተማረ ኃይል ያለውም ብርቱ ሰው ሆነ። ❤ ከታናሽነቱም ጀምሮ በእግዚአብሔር ፍቅር ታሠረ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር። አብያተ ክርስቲያንንም እጅ መንሻ ከመያዝ ጋራ ይጎበኝ ነበረ በጸሎቱና በጾምም ይጋደል ነበር። ካንዲት ሴት በቀር አላገባም በማንም ላይ ዐመጻና ግፍ ከቶ አልሠራም። ❤ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ በአሰበ ጊዜ አባ ማርቆስን አማከረው እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ያውቅ ነበርና "ክፍልህ አይደለም" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ባረፈ ጊዜ በክረምት ወራት በድኑን ሲወስዱ ሞልቶ የነበረው ወንዝ ወዲያና ወዲህ ተከፍሎ ተሻገሩ በቀበሩበትም ቦታ ሕይወትነት ያለው ውኃ መነጨ እስከ ዛሬም አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ንጉሥ በቅዱስ ቴዎድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን የከበረ ዐምደ ሚካኤል የሥጋው ፍልሰት ሆነ መጀመሪያ በንጉሥ እስክንድር ዘመነ መንግሥት ወደ አባቶቹ መቃብር ዳግመኛም በንጉሥ ልብነ ድንግል ዘመን በአረፈ በአርባ ዓመቱ ፈለሰ አባቶቹ ነገሥታት ወደተቀበሩበት ወደ አትሮንሰ ማርያም አፍልሰው እንዲወስዱት ንጉሡ አዝዞ ነበርና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ለሮሜ ንጉሥ ቅዱስ ማርቆስ፦ ይህም ቅዱስ ንጹሕ ጻድቅ ነበር። በድንግልናው አምስት ዓመት ነገሠ ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ። እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስቱን እንዲአገባ መኳንንቱ አስገደዱት እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቁሞ ጸለየ "እመቤቴ ሆይ ላንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደ ምሔድበት ምሪኝ" አላት። እርሷም "ወደ ቶርማቅ ተራራ ሒድ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይኑር" አለችው። ❤ ከዚህም በኋላ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕር ወደብም በደረሰ ጊዜ ያለ መርከብ ተሻግሮ ወደ ቶርማቅ ተራራ ደረሰ ያም ቦታ ደረቅ ነበረ ከአጋንት ጋራም እየተጋደለ በውስጡ ስልሳ ዓመት ኖረ። ሰኔ 29 ቀን በዐረፈ ጊዜም መላእክት በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ንጉሥ በቅዱስ ማርቆስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በቆና ገዳም የነበሩ ሰባት መስተጋድላን ሰማዕታት፦ የእሊህም ስማቸው አባ አብሲዳ፣ አባ ኮቶሎስ፣ አባ አርድማ፣ አባ ሙሴ፣ አባ እሴይ፣ አባ ኒኮላስና አባ ብሶይ ናቸው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጾ እንዲህ ብሎ "አዘዛቸው ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ግለጡ"። ❤ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ሊሔዱ ተነሡ መርከብንም አገኙ በመርከቧም ውስጥ አምስቱን መስተጋድላን አገኙአቸውና ከእነርሱ ጋር ተስማሙ ወደ መኰንኑም ደርሰው በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመኑ። መኰንኑም ከእርሳቸው አንዱን ስለ ሀገራቸው ጠየቀው እርሱም ቆና ከሚባል አገር እንደሆኑ አስረዳው መኰንኑም ያሥሩዋቸው ዘንድ አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ከእሥር ቤት አውጥተው ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩአቸው ዘንድ ደግሞም በአንገቶቻቸው ከባድ ደንጊያዎችን አንጠልጥለው እንዲአሥሩዋቸው አዘዘ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በውህኒ ቤት ውስጥ ተገለጠላቸው አጽናናቸውም ቃል ኪዳንም ገባላቸው። ❤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላካቸው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው። ከዚህም በኋላ ዝፍትና ድኝ በተመሉ ከሁለት የብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩአቸው ነበልባሉም ሃያ ክንድ ከፍ ከፍ እስሚል ድረስ ከታች እሳትን አነደዱባቸው ከምጣዶችም ውስጥ አውጥተው በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩአቸው ጌታችንም ዳግመኛ ተገልጾ ያለ ምንም ጉዳት አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው መቶ ሠላሳ ሰዎች በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ከዚህም በኋላ አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ እነርሱም አጵሎን የሚሉትን ጣዖት በወንበር እንደ ተቀመጠ አምጥቶ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው እነርሱም ግን በእግሮቻቸው ረገጡትና ከመንበሩ ወድቆ ተሰበረ። ❤ መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እግሮቻቸውንም እንዲቆርጡ አዘዘ የቅዱስ ቀሲስ አብሲዳንን ግን ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ምስክርነቱን ፈጸመ እንዲሁ ደግሞ እሊያ አምስቱንም ራሶቻቸውን ቆረጡ ቅዱስ ኮቶሎስን ግን በእሳት አቃጠሉት ሁሉም የሰማዕትነት አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰባቱ መስተጋድል ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን አባ ሖር፣ አባ ብሶይና እናታቸው ይድራ ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ የሆነ አባ ሖርሳ፦ እሊህም ወደ እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም አባ ብሶይን ይዘው ቀኝ እጁንም አሥረው በከተማዎች ሁሉ በበሬዎች እንዲጐትቱት አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ የተዘረጉ ብረቶችን በእሳት አግለው በሥጋው ውስጥ አደረጉ የግራ እጁንም ቆረጡ እርሳስም አቅልጠው በአፉ ጨመሩ ጊንጦችና እባቦች ወደ ተከማቹበት ውስጥ ጣሉት እነርሱ ግን ከቶ አልቀረቡትም። ❤ ከዚህም በኋላ በብረት በትሮች ይደበድቡት ጀመር እርሱም "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ" ብሎ ጮኸ ጌታችንም አጸናው እንደቀድሞውም ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ አስነሣው። ❤ ከዚህም በኋላ እናቱ ወደርሱ መጥታ አረጋጋቸው በመጋደሉም ደስ ተሰኘችበት። ስለ እርሷም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ወደ እርሱ አስቀርቦ እያስፈራራ "ለአማልክት ሠዊ" አላት። እርሷ ግን አልፈራችውም ትእዛዙንም አልሰማችም የብረት በትሮችንም አግለው በጎኖቿ ውስጥ እንዲአደርጉ አዘዘ ይህንም በእርስዋ ላይ በአደረጉ ጊዜ ደስ ብሏት ዘመረች ስለ ቅዱስ ስሙም መከራ እንድትቀበል ያደረጋት እግዚአብሔርን አመሰገነችው ከዚህም በኋላ ነፍሷን ሰጠች የሰማዕትነትም አክሊል ተቀዳጀች።

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሰኔ ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክድርያ (ለግብጽ) አገር ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ለሆነው ሃያ ስምንት ዓመት ሙሉ በስደትና በመከራ ላሳለፈ ለታቁ አባት ለአባ ቴዎዶስዮስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ለአባ ያዕቆብ እል-በረዲ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰብ፦ ከቅዱስ ባስልዮስና ከቢፋሞን፣ ከባሊዲስና ከኮቶሎስ፣ ከአርዳሚስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ ቴዎዶስዮስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ አገር ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ነው። በዚህም ቅዱስ በስሙ በግብጽ ምድር ውስጥ ምእመናን ቴዎዶስዮሳውያን ተብለው ተጠርተውበታል። ይህም የሆነው እንዲህ ነው ሊቀ ጵጵስና ከተሾመ በኋላ ክፉዎች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሥተው በንጉሥ ምክር ከመንበረ ሢመቱ አሳደዱት በእርሱ ፈንታም አስቀድሞ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዲያቆናት የነበረ ስሙ አቃቅያኖስ የሚባለውን አንድ ሰው ሾሙ እርሱም ለአባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ጵጵስና እንዲገባው ከፈረሙት ቁጥር ውስጥ ነበር። ❤ ይህም አባት ወደ ግርማኖስ አገር ሒዶ ሦስት ወሮች ኖረ በዚያም ወራት በግብጽ አገር ንቡረ እድ አባ ሳዊሮስ ነበር እርሱም በአባቶቻችን ሐዋርያት እንዲሁም በአትናቴዎስና በዮሐንስ አፈወርቅ የደረሰባቸውን መከራ እያስታወሰ ያጽናናቸው ነበር። ከዚያም ተነሥቶ መሊግ ወደሚባል አገር ሔደ በዚያም ሁለት ዓመት ተቀመጠ። ❤ የእስክንድርያ ከተማ ሰዎችም የጠባቂያቸው የቴዎዶስዮስ መመለስ ሺተው በእስክንድርያው መኰንን ላይ ተነሡበት መኰንኑም ወደ መንበረ ሢመቱ መለሰው አቃቅያኖስንም አባረሩት። ይህም ነገር በንጉሥ ዮስጣቲያኖስና አምላክን በምትወድ በንግሥት ታዖድራ ዘንድ ተሰማ ንግሥቲቱም አስቀድሞ የተሾመው በሹመት ወንበሩ ይቀመጥ ብላ ጻፈች። ❤ ሃምሳ ስምንት ካህናትም ጉባኤ አደረጉ "አስቀድሞ የተሾመ አባ ቴዎዶስዮስ ነው" ሲሉም ጻፉ። ያን ጊዜም አቃቅያኖስ በሕዝብ ፊት ቁሞ "ክፋዎች ሰዎች ስለ አስገደዱኝ ይህን ሥራ ለመሥራት ሕግን ተላልፌአለሁ" አለ። ከዚህም በኋላ አቃቅዮስን ከውግዘቱ እንዲፈታው ነገር ግን ክህነትም ሆነ ሊቀ ዲቁና ለዘለዓለም እንዳይኖረው ሕዝቡ አባ ቴዎዶስዮስን ለመኑት። አቃቅያኖስ "አዎ እንዲሁ ይሁን" አለ ይህም አባት ከግዝቱ ፈታው። ❤ ሃይማኖቱን ያጠፋ ንጉሡ ግን በከፋች ሃይማኖቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ጋራ የሚስማማ መስሎት በእስክንድርያ ወዳሉ መኳንንቶቹ እንዲህ ብሎ ጻፈ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ በሃይማኖት ከእኛ ጋራ የሚስማማ ከሆነ ሹመት ይጨመርለታል። ለእስክንድር ከተማ ገዥ ይሆናል። ይህ ካልሆነ ከሹመቱ ይሻር። ❤ ይህም አባት ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ ሰይጣን "በበረሀ ጌታችንን ብትሰግድልኝ የዓለም መንግሥታትንና ክብራቸውን ሁሉ እሰጥሃለሁ" አለው። ያን ጊዜም ይህ አባ ቴዎዶስዮስ ተነሥቶ ከእስክንድርያ ወጣ ወደ ላይኛው ግብጽም ሔደ በዚያም ሕዝቡን እያስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ጥቂት ቀኖች ኖረ። ንጉሥም አባ ቴዎዶስዮስ ከእስክንድርያ ከተማ እንደ ወጣ በሰማ ጊዜ እየሸነገለው ወደ እርሱ መልእክት ላከ እንዲህም አለው እኔ ከአንተ ጋራ ልነጋገር ከአንተም ልባረክ እንድትመክረኝም እሻለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ሔደ የጳጳሳት አለቆችና ሕዝቡ ሁሉ ሠራዊቱም ተቀበሉት ከፍተኛ ወንበርም ላይ አስቀመጡት። እርስ በርሳቸውም ስለ ሃይማኖት ተከራከሩ ንጉሡም አብዝቶ ሲሸነግለውና ሲአባብለው ሰነበተ ቅዱስ አባት ቴዎዶስዮስ ከቅዱሳት መጻሕፍት በመጥቀስ ይረታው ነበር። ከእርሱም ጋራ ባልተስማማ ጊዜ ከመንበረ ሢመቱ ወደ ላይኛው ግብጽ አሳደደው። በእርሱም ፈንታ ጳውሎስ የሚባለውን ሰው ሾመው። ❤ ጳውሎስም ወደ እስክንድርያ ከተማ በመጣ ጊዜ ሕዝቡ አልተቀበሉትም ዓመት ሙሉም ኖረ በእጁም ማንም ቊርባንን አልተቀበለም። ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ ለመናፍቁ ጳውሎስ እስከሚታዘዙ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ አዘዘ። ምእመናንም ከእስክንድርያ በመውጣት ወደ ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቆዝሞስና ድምያኖስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዱ ነበር ካህናቱም በዚያ እየቀደሱ ያቆርኳቸው ነበር የአገር ልጆችንም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቋቸው ነበር። ❤ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲከፍቱላቸው አዘዘ አባ ቴዎዶስዮስም ሰምቶ ንጉሡ እንዳያስታቸው ፈራ ማጽናኛ ቃልን የተመላች መልእክትም ጽፎ በቀናች ሃይማኖት እያበረታቸው ወደ ምእመናን ላካት እንዲህም አላቸው "በዚያ ከሀዲ ጳውሎስ እንዳትታዘዙ ተጠበቁ"። ❤ ይህም አባት ሃያ ስምንት ዓመት በስደት ኖረ። መላው የሹመቱ ዘመን ሠላሳ ሁለት ነበር። ይኸውም በእስክንድርያ አራት ዓመት በስደትም ሃያ ስምንት ዓመት ነው። ❤ ይህም አባት ብዙ ድርሳናትን ደርሷል ምእመናንም በያዕቆብ ዘመን ያዕቆባውያን እንደ ተባሉ በስሙ ቴዎዶስዮሳውያን እየተባሉ ሲጠሩ ኖሩ። መልካም ጉዞውንም ፈጽሞ ሰኔ 28 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 25 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቴዎዶስዮስ ዘተወክፈ ክበዶ። ለሕማም ወለተሰዶ። በቃለ ሃይማኖት እንዘ ይሜህር ውሉዶ። በእንተ ዘገብረ ለክርስቶስ ፈቃዶ። ዐስበ ሐዋርያት ሎቱ ምንተኒ ኢውሕዶ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 28። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ጸላእኩ ማኅበረ እኩያን። ወኢይነብር ምስለ ጽልሕዋን። ወአሐፅብ በንጹሕ እየውየ"። መዝ25፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ10፥23-32።የ ሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን። https://t.me/EOTCWW

              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33                         #ስንክሳር                          ዘሰኔ #ሃያ ሰባት (፳፯)                       ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ https://t.me/EOTCWW https://t.me/Eotcw

#መድሃኒአለም ማለት የአለም ሁሉ መድሃኒት ማለት ነዉ ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለኛ ሲል ህይወቱን የሰጠ ፨ አሮንና ልጆቹን ....... ለክህነት የመረጠ ፨ ኤልያስን ....... በአዉሎ ነፋስ የነጠቀ ፨ እዮብን ....... በባእድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ ፨ ሎጥን ........ ከእሳት ያወጣ ፨ ለሳምሶን ........ ሀይልን የሰጠ ፨ አዛርያን አናንያን ሚሳኤልን ....... ከእሳት የታደገ ፨ ጥበብና ማስተዋልን ....... ለሰለሞን የሰጠ ፨ ያዕቆብን ....... በመንገዱ የጠበቀ እና የባረከ ፨ እስራኤልን ....... ከግብፅ ባርነት ያወጣ ፨ ለሙሴ ....... ጽላት የሰጠ ለኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩንም የገለጠ ስጦታዉ የማያልቅበት #ቸሩ_መድሃኒአለም_ይክበር _ይመስገን_አሜን /፫/ #መድኃኒአለም _የገዢዎች ሁሉ ገዢ #መድኃኒአለም ____ የነገስታት ሁሉ ንጉስ #መድኃኒአለም ____ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነዉ ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ ቀና ቀና እንድል ታደርጋለህ መድኃኒአለም መድኃኒቴ መ ____ መሃሪ ይቅር ባይ አምላክ ድ ____ ድካሜን ተመልከት ስለዉ ተበርክኬ ኃ ____ ኃያላት የማይችሉህ የኃያላን ኃያል ነ ____ ነፍሴ ትልኃለች ጌታዬ ይረዳኛል አ ____ አለምን ለማዳን መስቀል ላይ የዋለ ለ ____ ለዘላለም ፍቅር ነህ ሁሌ የማትቀየር ም ____ ምህረትህ የበዛ #የድንግል_ማርያም_ልጅ_ቸሩ_መድኃኒአለም_አንተ_ነ ህ_አባቴ !! ቸሩ መድኃኒአለም በያላቹሁበት ይጠብቃችሁ ወጥቶ ከመቅረት ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቃችሁ አሜን/፫/ የሚያኖረን ሰዉ ሳይሆን የአለም መድኃኒት የሆነዉ ለእኛ ሲል የእሾህ አክሊል የደፈዉ ቸሩ መድኃኒአለም ነዉ። ቸሩ መድኃኒአለም ሃገራችን ይጠብቅልን የዲያብሌስ ስራ እጅግ ተስፋፍቶብን የሰዉኛ ዘይቤዉ ከእኛ ዘንድ ጠፍቶብን ምግባራችን ከፍቶ ትዛዝህን ሽረን ..... በበደል ጨቂተን ዉስጣችን ሲያነባ ካንተ ተሰዉረን ለሰዉ ልጅ ነዉና ደምህ የፈሰሰዉ በምህረት እጆችህ እንባችን አብሰዉ ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁንም ላለ ኋላም የሚኖር ስሙ የተመሰገን ይሁን አሜን ፫ Join https://t.me/EOTCWW https://t.me/Eotcw