ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤"ሰላም ለ፬እንስሳሁ ለአብ እለ ይጸውሩ መንበሮ እለ ስሞሙ አግርሜስ ገጸ አንበሳ። አግርሜጥር ገጸ ሰብእ። ባርቲና ገጸ ላሕም። አርጣን ገጸ ንስር። ለቀዳማዊ ገጹ ከመ አንበሳ፤ በአምሳለ ፈጣሪሁ ዘውእቱ አብ። ለካልዕ ገጹ ከመ ሰብእ በአምሳለ ወልድ፤ ዘውእቱ ነሥአ ፍጹመ ስባኤ። ለሣልስ ገጹ ከመ ንስር በአምሳለ መንፈስ ቅዱስ ዘውእቱ አስተርአየ በርእየተ ርግብ በሥጋ። ወራብእ ገጹ ከመ ላሕም በአምሳለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ እስመ ፬ቱ መኣዝኒሃ"። ትርጉም፦ የአብ ዙፋኑን ለሚሸከሙና ስማቸው የአንበሳ መልክ ያለው አግርሜስ፤ የሰው መልክ ያለው አግርሜጥር፤ የላም መልክ ያለው ባርቲና፤ የንስር መልክ ያለው አርጣን ለተባሉ ለአራቱ እንስሳ ሰላምታ ይገባል፤ የመዠመርያው ፊት እንደ አንበሳ ነው፤ ያውም በፈጣሪው በአብ ምሳሌ ነው፤ የኹለተኛውም ፊቱ ያውም ፍጹም ሰውነትን ገንዘብ ባደረገ በወልድ አምሳል እንደ ሰው ነው፤ የሦስተኛውም ፊቱ ያውም አካል ባለው ርግብ አምሳል በተገለጠ መንፈስ ቅዱስ አምሳል እንደንስር ነው፤ ያራተኛውም ፊቱ እንደ ላም ነው፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ፤ መኣዝኗ አራት ናቸውና። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ቅድስ ቅፍሮንያም የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በአንዲትም ቀን ደረሰ በዚያም ታላቅ ምሥጢርን አየ ከከበሩ ቦታዎችም ተባርኮ ወደ መኖሪያው ተመልሶ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 8 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ነግሠ ደንገፁ አሕዛብ። ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል አድለቅለቃ ለምድር። እግዚአብሔር ዐቢይ በጽዮን"። መዝ98፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማር16፥14-ፍ.ም
+ + +
❤የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦"ተፅዕነ ላዕለ ኪሩቤል ወሠረረ። ወሠረረ በክነፈ ነፋስ። ወረሰየ ጽልመተ ምሥዋሮ"። መዝ 17፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 5፥21-ፍ.ም ወይም 1ኛ ቆሮ 15፥24-37፣ 1ኛ ጴጥ 3፥18-ፍ.ም ወይም ራዕ.ዮሐ 4፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 5፥29-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥10-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የአርባዕቱ እንስሳና የመላእክት አለቃ የቅዱስ አፋኒን በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን የቅድስት ሥላሴ መንበር ለሚሸከሙ ሥጋ ለሌላቸው ለአርባዕቱ እንስሳ (ለኪሩቤል) ለመታሰቢያ ዓመታዊ በዓላቸው፣ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ አፍኒን ለተሸመበት በዓል፣ ለአቡነ አምደ ሚካኤል ዘወሎ ለልደታቸው በዓል፣ ለታላቁ አባት ለአቡነ ኪሮስ ለበዓላቸው መታሰቢያና ለአረማዊ መኰንን ልጅ ለነበረ ለአባ ቅፍሮንያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሊቀ ጳጳሳት ዮሐንስ ከመታሰቢያው፣ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ መስቀል ከተገለጠለትና ከሰማዕት ኤስድሮስ ማኅበር ከሆኑ ከመቶ ሰማንያ ሁለት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሶበሰ ይወርዱ መላእክት እምሰማይ ዲበ ምድር አልቦሙ ድምጽ ወኢይሰማዕ ጽምጸ ክነፊሆሙ፤ አልቦ አሠር ለምክያዳተ እገሪሆሙ፤ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋሳት"። ትርጉም፦ መላክት ከሰማይ ወደ ምድር በሚወርዱበት ጊዜ ጽምጽ የላቸውም፤ የክንፎቻቸውን ድምጽ አይሰማም፤ ለእግሮቻቸውም አረጋገጥ ኮቴ ፍለጋ የለውም፤ ሩጫቸው ከነፋሳት ይፈጥናል"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ። እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው ስለ እርሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ "በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው። የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል። የእሊህም የአራቱ እንስሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽዑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
❤ ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ "ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት። የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸወን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋር ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ"።
❤ ነቢዩ ዳዊትም "በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ" አለ ሁለተኛም "በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት" አለ።
❤ ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ "ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእርሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል። በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊት አራት ነው ክንፉም አራት ነው። እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኰናቸው ግን እንደ ላም ሰኰና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል"።
❤ ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ "በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቊጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው። ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን ባለጸግነትን ጥበብን ጽናትን መንግሥትን ክብርን ጌትነትን ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ። በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባል" አሉ "በእውነት ይገባል"። እሊህም አራቱ እንስሶች "አሜን" ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ"።
❤ ስለ ልዕናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንስሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ "ገጸ ሰብእ ስለሰው ፍጥረት ይለምናል ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጸ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል" ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
❤ ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤"ሰላም ለራጉኤል ወለሳቁኤል፤ ለአፍኒን ወለራሙኤል እለ የዐውዱ መንበሮ ለልዑል"። ትርጉም፦ የልዑል ዙፋኑን ለሚዞሩ ለራጉኤልና ለሳቁኤል፤ ለአፍኒንና ለራሙኤል ሰላምታ ይገባል፡፡ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ አፍኒን፦ ይህም ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌቱነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው ስለርሱ ሄኖክ እንዲህ አለ "ያንን ቤት ሱራፌልና አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል" እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፉ ናቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ ቅዱስ አፍኒን አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ቅፍሮንያ፦ ይህ አባት የአረማዊ መኰንን ልጅ ነው። ከዕታትም በአንዲቱ ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል መነኰስ ከአባ ጳኲሚስ ገዳም ወደ አገሩ መጣ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገረ። ከጥቂት ወራትም በኋላ ገዳማትን ሊአጠፋ ምርኮንም ሊማርክ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወደ ግብጽ አገር ዘመተ ወደ አባ ጳኲሚስም ገዳም በደረሰ ጊዜ አበ ምኔቱ ወደርሱ ወጥቶ "እኔ ነኝ" አለው ቅፍሮንያም ሰምቶ አበ ምኔቱን ለብቻው አግልሎ እንዲአጠምቀውና የምንኲስናንም ልብስ እንዲአለብሰው ለመነው አበ ምኔቱም "እሺ በጎ" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ወደ አገራቸው በተመለሱ ጊዜ ብቻቸውን ቀረ በዚያንም ጊዜ ተጋድሎውንም በመጾምና በመጸለይ ጀመረ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ ነገረ ሠሪ አስነሣበት በመኳንንቱም ዘንድ ወነጀለው እነርሱም "አገራችንን ያጠፋ የመኰንን ልጅ ከዚህ አለ" ብለው ገዳሙን ከበቡ እግዚአብሔር ሠወረው በአጡትም ጊዜ ነገረ ሠሪውን ገደሉት።
❤ ይህም ቅዱስ በገድል ተጠምዶ ኖረ በየሰባት ቀንም ይጾማል ያለ መራራ አደንጓሬ አይመገብም። በዚያም ወራት የምድር አውሬ እንስሶቻቸውን እየገደለ በገዳሙ ላይ ጥፋትን አደረሰ አባ ቅፍሮንያም ወደርሱ መጥቶ እንደ በግ ይዞ አሠረው ዐሥር ዓመትም ቆይቶ ሞተ።
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅደሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 10:16-ፍ፡ም፡ "ወናሁ አነ እፌንወክሙz" - "እንሆ፥እኔ፡እንደ፡በጎች፡በተኵላዎች፡መካከል፡እልካችኋለሁ፤ስለዚህ፥እንደ፡እባብ፡ልባሞች፡እንደ፡ርግብም፡የዋሆች፡ሁኑ። ነገር፡ግን፥ወደ፡ሸንጎ፡አሳልፈው፡ይሰጧችኋል፥በምኵራቦቻቸውም፡ይገርፏችኋልና፥ከሰዎች፡ተጠበቁ፤ ለእነርሱና፡ለአሕዛብም፡ምስክር፡እንዲሆን፥ስለ፡እኔ፡ወደ፡ገዢዎች፡ወደ፡ነገሥታትም፡ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም፡ሲሰጧችሁ፥የምትናገሩት፡በዚያች፡ሰዓት፡ይሰጣችኋልና፥እንዴት፡ወይስ፡ምን፡እንድትናገሩ፡አትጨነቁ፤ በእናንተ፡የሚናገር፡የአባታችሁ፡መንፈስ፡ነው፡እንጂ፥የምትናገሩ፡እናንተ፡አይደላችሁምና። ወንድምም፡ወንድሙን፥አባትም፡ልጁን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ይሰጣል፥ልጆችም፡በወላጆቻቸው፡ላይ፡ይነሣሉ፡ይገድሏቸውማል። በሁሉም፡ስለ፡ስሜ፡የተጠላችሁ፡ትሆናላችሁ፤እስከ፡መጨረሻ፡የሚጸና፡ግን፡እርሱ፡ይድናል። በአንዲቱ፡ከተማም፡መከራ፡ቢያሳይዋችሁ፡ወደ፡ሌላዪቱ፡ሽሹ፤እውነት፡እላችኋለሁና፥የሰው፡ልጅ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡የእስራኤልን፡ከተማዎች፡አትዘልቁም። ደቀ፡መዝሙር፡ከመምህሩ፥ባሪያም፡ከጌታው፡አይበልጥም። ደቀ፡መዝሙር፡እንደ፡መምህሩ፥ባሪያም፡እንደ፡ጌታው፡መሆኑ፡ይበቃዋል።ባለቤቱን፡ብዔል፡ዜቡል፡ካሉት፥ቤተ፡ሰዎቹንማ፡እንዴት፡አብዝተው፡አይሏቸው! እንግዲህ፡አትፍሯቸው፤የማይገለጥ፡የተከደነ፥የማይታወቅም፡የተሰወረ፡ምንም፡የለምና። በጨለማ፡የምነግራችሁን፡በብርሃን፡ተናገሩ፤በጆሮም፡የምትሰሙትን፡በሰገነት፡ላይ፡ስበኩ። ሥጋንም፡የሚገድሉትን፡ነፍስን፡ግን፡መግደል፡የማይቻላቸውን፡አትፍሩ፤ይልቅስ፡ነፍስንም፡ሥጋንም፡በገሃነም፡ሊያጠፋ፡የሚቻለውን፡ፍሩ። ሁለት፡ድንቢጦች፡በዐምስት፡ሳንቲም፡ይሸጡ፡የለምን፧ከእነርሱም፡አንዲቱ፡ያለአባታችሁ፡ፈቃድ፡በምድር፡ላይ፡አትወድቅም። የእናንተስ፡የራሳችሁ፡ጠጕር፡ሁሉ፡እንኳ፡ተቈጥሯል። እንግዲህ፡አትፍሩ፡ከብዙ፡ድንቢጦች፡እናንተ፡ትበልጣላችሁ። ስለዚህ፥በሰው፡ፊት፡ለሚመሰክርልኝ፡ሁሉ፥እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እመሰክርለታለሁ። በሰው፡ፊትም፡የሚክደኝን፡ሁሉ፡እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እክደዋለሁ። በምድር፡ላይ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡የመጣኹ፡አይምሰላችሁ፤ሰይፍን፡እንጂ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡አልመጣሁም። ሰውን፡ከአባቱ፥ሴት፡ልጅንም፡ከእናቷ፥ምራትንም፡ከአማቷ፡እለያይ፡ዘንድ፡መጥቻለሁና፤ ለሰውም፡ቤተ፡ሰዎቹ፡ጠላቶች፡ይሆኑበታል። ከእኔ፡ይልቅ፡አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገባውም፤ከእኔ፡ይልቅም፡ወንድልጁን፡ወይም፡ሴት፡ልጁን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገባውም፤ መስቀሉንም፡የማይዝ፡በዃላዬም፡የማይከተለኝ፡ለእኔ፡ሊሆን፡አይገባውም። ነፍሱን፡የሚያገኝ፡ያጠፋታል፥ነፍሱንም፡ስለ፡እኔ፡የሚያጠፋ፡ያገኛታል። እናንተን፡የሚቀበል፡እኔን፡ይቀበላል፥እኔንም፡የሚቀበል፡የላከኝን፡ይቀበላል። ነቢይን፡በነቢይ፡ስም፡የሚቀበል፡የነቢይን፡ዋጋ፡ይወስዳል፥ጻድቅንም፡በጻድቅ፡ስም፡የሚቀበል፡የጻድቁን፡ዋጋ፡ይወስዳል። ማንም፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡ለአንዱ፡ቀዝቃዛ፡ጽዋ፡ውሃ፡ብቻ፡በደቀ፡መዝሙር፡ስም፡የሚያጠጣ፥እውነት፡እላችኋለሁ፥ ዋጋው፡አይጠፋበትም።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
7/3/2015 ዓ.ም (፯/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ።
በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ።
ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን፡፡ መዝ 78:10
🕯 ትርጉም
አሕዛብ አምላካቸው ወ ዴት ነው? እንዳይሉ።
የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል።
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ዮሐ. 14:1-13፡ "ኢይደንግጽክሙ ልብክሙ" - "ልባችሁ፡አይታወክ፤በእግዚአብሔር፡እመኑ፥በእኔም፡ደግሞ፡እመኑ። በአባቴ፡ቤት፡ብዙ፡መኖሪያ፡አለ፤እንዲህስ፡ባይሆን፡ባልኋችሁ፡ነበር፤ስፍራ፡አዘጋጅላችሁ፡ዘንድ፡እሄዳለሁና፤ ሄጄም፡ስፍራ፡ባዘጋጅላችሁ፥እኔ፡ባለሁበት፡እናንተ፡ደግሞ፡እንድትሆኑ፡ሁለተኛ፡እመጣለሁ፡ወደ፡እኔም፡እወስዳችኋለሁ። ወደምሄድበትም፡ታውቃላችኹ፥መንገዱንም፡ታውቃላችሃ። ቶማስም፦ጌታ፡ሆይ፥ወደምትሄድበት፡አናውቅም፤እንዴትስ፡መንገዱን፡እናውቃለን፧አለው። ኢየሱስም፦እኔ፡መንገድና፡እውነት፡ሕይወትም፡ነኝ፤በእኔ፡በቀር፡ወደ፡አብ፡የሚመጣ፡የለም።እኔንስ፡ብታውቁኝ፡አባቴን፡ደግሞ፡ባወቃችሁ፡ነበር።ከአሁንም፡ጀምራችሁ፡ታውቁታላችሁ፡አይታችሁትማል፡አለው። ፊልጶስ፦ጌታ፡ሆይ፥አብን፡አሳየንና፡ይበቃናል፡አለው። ኢየሱስም፡አለው፦አንተ፡ፊልጶስ፥ይህን፡ያህል፡ዘመን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ስኖር፡አታውቀኝምን፧እኔን፡ያየ፡አብን፡አይቷል፤እንዴትስ፡አንተ፦አብን፡አሳየን፡ትላለህ፧እኔ፡በአብ፡እንዳለሁ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡አታምንምን፧እኔ፡የምነግራችሁን፡ቃል፡ከራሴ፡አልናገረውም፤ነገር፡ግን፥በእኔ፡የሚኖረው፡አብ፡እርሱ፡ሥራውን፡ይሠራል። እኔ፡በአብ፡እንዳለሁ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡እመኑኝ፤ባይሆንስ፡ስለ፡ራሱ፡ስለ፡ሥራው፡እመኑኝ። እውነት፡እውነት፡እላችኋለሁ፥በእኔ፡የሚያምን፡እኔ፡የማደርገውን፡ሥራ፡ርሱ፡ደግሞ፡
ያደርጋል፤ከዚህም፡የሚበልጥ፡ያደርጋል፥ እኔ፡ወደ፡አብ፡እሄዳለሁና፤አብም፡ስለ፡ወልድ፡እንዲከበር፡በስሜ፡የምትለምኑትን፡ሁሉ፡አደርገዋለሁ። ማናቸውንም፡ነገር፡በስሜ፡ብትለምኑ፡እኔ፡አደርገዋለሁ። ብትወዱኝ፡ትእዛዜን፡ጠብቁ። እኔም፡አብን፡እለምናለሁ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
7/3/2015 ዓ.ም (፯/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ።
አምላከ እስራኤል ውእቱ ይውህብ ኃይለ ወጽንዐ ለሕዝቡ ።
ወይትባረክ እግዚአብሔር፡፡ መዝ. 67÷35
🕯 ትርጉም
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።
የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣልና።
እርሱ እግዚአብሔር ይመስገን።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
+ + +
❤የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 5፥23-28፣ 1ኛ ቆሮ 7፥25-ፍ.ም ወይም 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 28፥1-11 ወይም 27፥21-27። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ዐረፉ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሐዲስ ቅዱስ መርቆሬዎስና ወንድሙ ቅዱስ ዮሐንስ፡- እነዚህም ቅዱሳን የደጋግ ክርስቲያን ልጆች ናቸው፡፡ የታላቁ ስም ሙናሂ ነበር ሲመነኩስ ግን መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የታናሹም ስም አቡፈረዥ ነበር እርሱም ሲመነኩስ ዮሐንስ ተባለ፡፡ ሁለቱም ወንድማማቾች ወደ ሊቀ ሠራዊት ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም ገብተው ጽኑ የሆነ ተጋድሎአቸውን ጀመሩ፡፡ ለመነኰሳቱ ሁሉ የሚላላኩና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ጣዕም ካላቸው ምግቦችና መጠጦች እንዲሁም ከእንቅልፍ እርቀው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ የሚመገቡትም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ሆነ፡፡ የግብፅንና የሌላውንም ጽሕፈት ተምረው መጻሕፍትን መረመሩ፡፡ እነዚህም ወንድማማቾች አንድ ቀን አብረው ሳሉ የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ወደ ምስክርነት አደባባይ ሄደው ስለጌታችን ስለ ስሙ እንዲመሰክሩና ሰማዕትነታቸውን እንዲፈጽሙ ነገራቸው፡፡
❤ እነርሱም እንደታዘዙት በከሃዲው መኰንን ፊት ሄደው ስለ ጌታችን ክብር መሰከሩ፡፡ መኰንኑም የተለያዩ ጽኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው፡፡ ከብዙ ሥቃይም በኋላ በወህኒ ቤት ተጥለው ሳለ ሌላ መኰንን ተሹሞ እርሱም ሊተዋቸው በወደደ ጊዜ የአገሩ ሰዎች "እነርሱን ካልገደልካቸው በንጉሡ ዘንድ እንከስሃለን" አሉት፡፡ ይህም መኰንን ሕዝቡን ከመፍራቱ የተነሣ ፈቃዳቸውን ይፈጽምላቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ሕዝቡም ኅዳር 7 ቀን ሐዲስ የተባለ የቅዱስ መርቆሬዎስንና የወንድሙ የቅዱስ ዮሐንስን ራስ በሰይፍ ከቆረጧቸው በኋላ የሰማዕትነት ፍጻሜአቸው ሆነ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅድስት ዘኖብያ እና ልጇ ቅዱስ ዘኖቢስ፡- እነዚህም ቅዱሳን ተበይስ ከምትብል አገር ከታላላቅ ወገኖች የተገኙ ሰማዕታት ናቸው፡፡ እነርሱም ክርስቲያኖች እንደሆኑ በከሃዲው ንጉሥ ዘንድ ዜናቸው ተሰማ፡፡ ንጉሡም ወደ እርሱ ካስመጣቸው በኋላ እምነታቸውን መረመራቸው፡፡ እነርሱም "አገራችን ተበይስ ነው የምናመልከውም የክብርን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው" አሉት፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ እናትና ልጅን "ለአማልክት ሠው" አላቸው፡፡ ቅዱሳኑም "እኛስ ለእውነተኛው አምላክ ለክርስቶስ እንሠዋለን እንጂ ለረከሱ ጣዖታት አንሠዋም" አሉት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ ቅድስት ዘኖብያንና ልጇን ቅዱስ ዘኖቢስን ጽኑ በሆነ ሥቃይ አሠቃያቸው፡፡ ልብሳቸውን ገፈው በራሳቸው ጸጉር ተቅለው እየደበደቡ እንዲያሠቃዩአቸው አደረገ፡፡ ቅዱሳኑም ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ ማሰሪያው በተአምራት ተፈታላቸው፡፡ የብርሃን ልብሶችንም ለብሰው ሕዝቡ ሁሉ አዩአቸው፡፡ ይህንንም ባዩ ጊዜ "የእነዚህ ቀዱሳን አምላካቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመስገን እኛም በአምላካቸው አምነናል" እያሉ ጮኹ፡፡ ንጉሡም በታላቅ ቁጣ ሆኖ እናትና ልጅን እርስ በእርስ እንዲተያዩ አድርጎ በሁለት መስቀሎች ላይ እርቃናቸውን ሰቀላቸው፡፡ በዚያን ጊዜም ደመና መጥታ ሸፈነቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡
❤ ዳግመኛም ንጉሡ ቅድስት ዘኖብያንና ልጇን ቅዱስ ዘኖቢስን በብረት ወንበሮች ላይ አስሮ በማስቀመጥ ከሥር በሚነድ እሳት አቃጠላቸው፡፡ ጌታችንም ከዚህ ሥቃይ አዳናቸው፡፡ በወንበሩም ላይ ሆነው በእሳት እየተቃጠሉ ሳለ ሕዝቡን ያስተምሩ ጀመር፡፡ ንጉሡም ይህንን ባየጊዜ እጅግ ተቆጥቶ ቁመቱና ጎኑ ሃያ ሃያ ክንድ የሆነ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡም እሳትን እንዲያነዱበትና ቅዱሳኑን ከዚያ እንጨምሯቸው አደረገ፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅድስት ዘኖብያንና ልጇን ቅዱስ ዘኖቢስን ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ እሳቱ ፈጥኖ ጠፋ፡፡ ንጉሡም ከዚህ በኋላ ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ በሰይፍ አንገታቸውን ቆርጠው እንገድሏቸውና እስከ ነገ ድረስ በድናቸውን ጠብቀው በእሳት እንዲያቃጥሉአቸው በነፋስም ውስጥ እንዲበትኑአቸው አዘዘ፡፡ ቅዱሳኑንም በገደሏቸው ጊዜ ነጎድጓድ መብረቅ ንውጽውጽታ ሆነ፣ ዝናብም ዘነበ፡፡ በዚህም ታላቅ ንውጽውጽታ ምክንያት 54 ሰዎች ሞቱ፡፡ በሌሊትም ምእመናን መጥተው የቅሱሳኑን ሥጋ በሥውር ወስደው ቀበሯቸው፡፡ በማግሥቱም ንጉሡ በድናቸውን በፈለገ የሆነውን ሁሉ ተረዳ፡፡ የሆነውን ሁሉ ባስተዋለ ጊዜ ዐይነ ልቡናው በራለትና በጌታችን አምኖ ንስሓ ገብቶ ተጠመቀ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕቱ አባ ናህርው፡- ይኸውም ቅዱስ ከግብጽ አገር ከፍዩም መንደር የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ ይኸውም ቅዱስ ፈሪሃ እግዚአብሔር በእጅጉ ያደረበት ደገኛ ክርስቲያን ነው፡፡ በእስክንድርያ አገር በከሃዲያን መኳንንት የሚሠቃዩትንና የሚሞቱትን የክርስቲያኖቹን ዜና በሰማ ጊዜ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ስለ ጌታችን ስለ ስሙ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ተመኘ፣ የሰማዕትነት ክብርንም ይቀዳጅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማውና በራእይ ተገልጦለት "ወደ አንጾኪያ አገር ሂድ በዚያ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ አለህ" አለው፡፡
❤ አባ ናህርው ከዚህ በኋላ ወደዚያ እንዴት መድረስ እችላለሁ ብሎ ሲያስብ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና መልአኩ ይህንን ቅዱስ በክንፎቹ ተሸክሞ ወደ አንጾኪያ አገር አደረሰው፡፡ አንጾኪያ አገር ላይ ያለው ንጉሥ ደግሞ እጅግ ጨካኝ የሆነው የክርስቲያኖችን ደም በዓለም ዙሪያ ያፈስ የነበረው ዲዮቅልጥያኖስ ነበር፡፡ እናም አባ ናህርው በከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር መሰከረ፡፡ ንጉሡም ስሙንና አገሩን ጠየቀው፡፡ እርሱም ከግብጽ አገር እንደሆነ አስረዳው፡፡ ንጉሡም ቃሉን ከሰማ በኋላ ለጣዖታቱ ቢሠዋለት ብዙ ገንዘብና ሥልጣን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት፡፡ ነገር ግን አባ ናህርው በጌታችን ታመነ፡፡ ንጉሡም "ትእዛዜን አልሰማም ካልክ አሠቃይቼ ለሞት እዳርግሃለሁ" እያለ በተደጋጋሚ ቢናገረውም አባ ናህርው ግን ከሥቃዩ የተነሣ አልፈራም፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ቅዱስ አባ ናህርውን በብዙ ዓይነት ሥቃዮች እንዲያሠቃዩት አደረገው፡፡ በእሳት ውስጥ ቢጨምሩት ረድኤተ እግዚአብሔር ጠብቆት ምንም ሳይቃጠል ቀረ፡፡ ዳግመኛም ለተራቡ አንበሶች ቢሰጡት አንበሶቹም ምንም ሳይነኩት ቀሩ፡፡ በሌላም ጊዜ በትልቅ ወጪት አድርገው በእሳት ቀቀሉት ነገር ግን አሁንም ምንም አልሆነም፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ አባ ናህርውን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ በዚህች ዕለት አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና የቅዱስ አባታችን የሰማዕትነት ፍጻሜአቸው ሆነ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 7 ስንክሳርና መዝገበ ቅዱሳን።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ። አምላከ እስራኤል ውእቱ ይሁብ ኃይለ ወፅንዐ ለሕዝቡ። ወይትባረክ እግዚአብሔር"። መዝ67፥35 የሚነበበው ወንጌል ዮሐ1 4፥1-15።
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን ለሰማዕታት አለቃ ለታላቁ መስተጋድል ለቅዱስ ጊዮርጊስ በልዳ አገር (በዓለም ላይ) ቤተ ክርስቲያን ለከበረችበት፤ ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር፣ ሰባ ነገሥታት ከደሃይቱ መበለት ቤት አስረውት ሳለ ልጇን ለፈወሰበት፤ ታስሮ የነበረበትን ደረቅ ምሰሶ ከሃገሪቱ ቅጽር በላይ እንዲታይ ላለመለመበት፤ ዲዳ፣ ደንቆሮ፣ ዕውርና አንካሳ የነበረው ልጇን ለፈወሰበት ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ከእስክድርያ አገር ለሆነ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ከግብፅ አገር ከፍዩም መንደር ሰማዕትነት ለተቀበለ ለአባ ናህርው ለዕረፍት በዓል ከገምኑዲ አውራጃ ከአገረ ተመይ ለሆነ ኤጲስቆጶስ ለአባ ሚናስ ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ፣ ተበይስ ከምትባል አገር ከታላላቆች ወገን ለሆኑ ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለቅዱሳን ዘኖቢስና ለእናቱ ዘኖብያና ለዕረፍታቸው በዓልና ለቅዱሳን ሐዲስ መርቆሬዎስና ለወንድሙ ዮሐንስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የዕለቱ እግ ነግ አራራይ ዜማ፦ "ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ ሙታነ አንሣዕከ በሥልጣነ አቡከ ሠናየ ገድለ ተጋደልከ"። ትርጉም፦ ንዑድ ክቡር ቅዱስ ጊዮርጊስን መበለት ሴት አለችው በአባትህ ሥልጣን ሙታንን አንሣን መልካምን ገድል ተጋደልክ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ።
+ + +
❤ በዚችም ቀን የልዳ አገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
❤ ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲዪኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዲው ራስ ደረሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጎሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ አገራቸው አፍረው ተመለሱ።
❤ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ አገር ያለች ነቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 7 ስንክሳር።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘእስክንድርያ፡- አባቱ በእስክንድርያ አገር በንግድ ሥራ ይተዳደር የነበረ ሲሆን ልጅ ስላልነበረው በልዳው ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሄዶ በቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል ቀን ልጅ እንዲሰጠው ሰማዕቱን በስዕለት ጠየቀው፡፡ ስዕለቱም ተሰምቶለት ልጅ ሲወልድ ስሙን በሰማዕቱ ስም ጊዮርጊስ ብሎ ጠራው፡፡ ሚስቱም የእስክንድርያው አስተዳዳሪ የአርማንዮስ እኅት ናት፡፡ ጊዮርጊስ ከተወለደ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ እናትና አባቱ ስለሞቱ አስተዳዳሪ አጎቱ ወስዶ አሳደገው፡፡ አጎቱም ጣዖትን የሚያመልክ ነው፡፡ ነገር ግን ጊዮርጊስ እስከ 20 ዓመቱ ድረስ በሃይማኖቱም እጅግ ጠንካራ ሆነ፡፡ በጾም በጸሎት እየተጋ ነዳያንን አብዝቶ ይመግብ ነበር፡፡ የጽድቅ ሥራውንም ሰው አያውቅበትም ነበር፡፡
❤ የአስተዳዳሪው ብቸኛ ሴት ልጅ ልዩ ልዩ የተዋቡ ቦታዎችን ትጎበኝ ዘንድ ከቤት ወጥታ ወደ ደብረ ቁስቋም ስትደርስ የቤተ ክርስቲያንን የቅዳሴ ዝማሬ ሰምታ ልቧ እጅግ ደስ ተሰኘ፡፡ የአክስቷ ልጅ የሆነ ጊዮርጊስንም መነኮሳቱ ስለሚያሰሙት ዝማሬ ጠየቀችው፡፡ እርሱም ምንነቱን ካስረዳት በኋላ በዚያውም የሃይማኖትን ነገር በደንብ አስተማራት፡፡ ልጅቱም ወደ ከሃዲው አስተዳዳሪው አባቷ ዘንድ ቀርባ ስለ ጌታችን ክብር ትመሰክር ጀመር፡፡ አባቷም ሊሸነግላት ቢሞክር ነገሩን እንዳልሰማችው ሲያውቅ ብቸኛና አንድያ ልጁን አንገቷን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ልጅህን አስተምሮ ያሳታት የእኅትህ ልጅ የሆነው ጊዮርጊስ ነው" ብለው ለመኰንኑ ነገሩት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን ካሠቃየው በኋላ ኅዳር 7 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጠውና ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አቡነ ሚናስ ዘሀገረ ተመይ፡- ተመይ የምትባለው አገር ኤጲስ ቆጶስ የሆነው የአቡነ ሚናስ ወላጆቹ የመነኮሳትን ሥራ የሚሠሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ ሲያድግም ያለፈቃዱ ሚስት አጋቡት፡፡ ወደ ጫጉላ ቤትም በገባ ጊዜ ድንግልናቸውን ይጠብቁ ዘንድ ከሚስቱ ጋር ተማክሮ ሁለቱም በንጽሕናና በድንግልና ሆነው በአንድነት ሊኖሩ ተስማሙ፡፡ ሌሊቱንም ሁሉ ለጸሎት ቆመው ያድሩ ነበር፡፡ እርሱም በዓለም እየኖሩ የምንኩስናን ሥራ ከመሥራት ይልቅ መንኩሶ ገዳም መግባት እንደሚሻል ለሚስቱ ሲነግራት ሸኝታ አሰናበተችው፡፡ አቡነ ሚናስም ወደ አቡነ እንጦንስ ገዳም ገባ ነገር ግን በንጉሡ ትእዛዝ ቤተሰቦቹ ቢያስፈልጉትም ጌታችን ሰውሮታል ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄደ፡፡
❤ በዚያም ሁለቱ ብርሃን ከዋክብት አባ አብርሃምንና አባ ገዐርጊን በማገልገል ልጅ ሆናቸው፡፡ ተጋድሎአቸውንና ትምህርታቸውን በሚገባ ከተማረ በኋላ እርሱም በተጋድሎው አባ አብርሃምና አባ ገዐርጊ እስኪያደንቁትና እስኪገረሙበት ድረስ ከፍ ከፍ አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ኤጲስ ቆጶስነት ይሾም ዘንድ ጌታችን መርጦት ለሊቀ ጳጳሳቱ እንዲሾመው ነገረው፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም ጠርተው ሲያስመጡት እምቢ ቢላቸውም የእግዚአብሔር ትእዛዝ መሆኑን ነግረውት ተመይ በሚባል አገር ላይ ሾሙት፡፡ አቡነ ሚናስ ከዚህም በኋላ ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ብዙ ድውያንን የሚያድናቸው ሆነ፡፡ ሁለተኛም የተሰወረውን የማወቅ ሀብት ተሰጠውና በሰው ልቡና የታሰበውን የሚያውቅ ሆነ፡፡ አቡነ ሚናስ ለአራት ታላላቅ አባቶች አባት ሆኖ እጁን በላያቸው ላይ ጭኖ ሾሟቸዋል፡፡ እነርሱም ለእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት አባ እለእስክንድሮስ፣ አባ ቆዝሞስ፣ አባ ቴዎድሮስና አባ ሚካኤል ናቸው፡፡ አባታችን በመጨረሻም ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፍበትን ጊዜ ዐውቆ ካህናቱንና ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ በቀናች ሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ከመከሯቸው በኋላ ኅዳር 7 ቀን በሰላም
