ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ኅዳር ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሃያ አምስተኛ ሆነው አብራው ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የቅድስት ሥላሴ ዙፍን ላጠኑበት በዓልና ለአቡነ ዜና ማርቆስ በቅዱስ ማርቆስ አብሳሪነት ለተወለዱበት (ለልደታቸው) በዓላቸው በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የቅድስት ሥላሴን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ "…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ "ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን" የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ….." ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምዕራፍ 43።
+ + +
❤ አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊ በቅዱስ ማርቆስ ብሥራት እንደተወለዱ፡- አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ሲሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ "ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻድቅ ልጅ እንደምትወልድ አበሠራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት "ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል" በማለት ብሥራቱን ነግሮታል፡፡
❤ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን ዜና ማርቆስ በዚህች ዕለት ኅዳር 24 ቀን በተወለዱ ጊዜ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎች ሁሉ ታይቷል፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ዘወገግ አባት ቅዱስ እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም አቡነ ዜና ማርቆስን ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናታቸው ሰጧቸው፣ እናታቸው ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው "አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ" ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
https://t.me/Eotcw
1 161
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
አመ ፳ወ፭ ለህዳር ለቅዱስ መርቆሬዎ ስረዓተ ማኅሌት
💠💠💠💠💠💠💠💠💠
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል
@EOTCW
@EOTCW
ገባሬ ኩሉ
@EOTCW
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም
ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም
ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCW
ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ ይቀዉሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም፤ ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ ዓለም፤ ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም፤ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲአሁ።
@EOTCW
🔸ዓዲ
፩ አብ ቅዱስ ፩ ወልድ ቅዱስ፤ ፩ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘአድኃኖሙ ለሰማዕት።
@EOTCW
✨መልከአ ሚካኤል ለሕፅንከ፦
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤
ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤
ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤
ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤
እንዘ ትሰርር ነዓ በክልዔ አክናፍ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ሚካኤል መልአክ ወረደ እምሰማይ፤ ኀበ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ወአጥፍአ ኃይለ እሳት፤ ወኢለከፎ ስጋሁ።
@EOTCW
@EOTCW
✴️ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ ወያሚሆሙ ለካህናት፤ ነያ ጽዮን መድኃኒት።
@EOTCW
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ገብረ ኢየሱስ ብኢል፤ ወለስርዕትከ ጸሊም ዘቆናዚሁ ፍቱል፤ መርቆሬዎስ ሰማእት ገባሬ ተአምር ወኃይል፤ ለዮሐንስ ፍና ድኂን ከመ መራህኮ በኀቅል፤ ምርሀኒ ለወልድከ ፍና ጽድቅ ወሣህል።
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ወሀሎ ፩ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር፤ ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል፤ ነገረ ገድሉ መዓርዒር ለተናግሮ ዕፁብ ግብር፤ ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ወሀሎ ፩ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል፤
መዓርዒር ለተናግሮ ተናግሮ ዕፁብ ግብር።
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ዘተናገረ፤ ዕበደ ዕልው ዳኬዎስ ወኀጒለ አርዳሚስ ድህረ፤ መርቆሬዎስ ሰማእት አመ አፆሩከ ፆረ፤ ተዐገስከ እስከ ለሞት እንዘ ትትዌከፍ ሐሣረ፤ በዓለመ ተስፋ ሐዳስ ከመ ትንሣእ ክቡረ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤ ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ፤
አስተምህር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ዓቢያተ ተናገረ ወርእሶ አምተረ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤
አስተምህር ለነ መርቆሬዎስ ዘሰበከ ቃለ።
@EOTCW
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለልብከ ወለኅሊናከ ዘሐለየ፤ በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትትዌከፍ ሥቃየ፤ መርቆሬዎስ ሥዕልከ ከመ ጽንዐ ኃይሉ አርአየ፤ ላዕለ ዑልያኖስ መዓምፅ አመ ባስልዮስ ጸለየ፤ ኃይለ ረድኤትከ ይርአይ ዓላዊ ፀርየ።
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል፤ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ፤ ወቀተለ ፀሮሙ።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ
@EOTCW
❣🔸ወረብ ዓዲ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ
@EOTCW
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ ድኀረ ፈጸሙት ህማመ፤ በአፈ ጕድብ ሰይፍ በሊህ አመ ክሣዳ ተገዝመ፤ መርቆሬዎስ ቅድሜከ ሶበ እግረ ልብየ ቆመ፤ ሐውፀኒ ለለጽባሑ ወጸግወኒ ሰላመ ፤እስመ ረሰይኩከ አበ ወሰናይት እመ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣደ፤ ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ መርቆሬዎስ።
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣዶ፤ ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣ/2/
ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ መርቆሬዎስ/2/
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለበድነ ስጋከ ንጹሕ ወቅዱስ፤ ወለግንዘትከ ፀዓዳ በማየ ደም ግፍዕ ርሑስ፤ መርቆሬዎስ ሰማእት መኰንነ አስሊጥ ወፋርስ፤ ላዕሌየ ይኅድር እግዚኦ በጸሎትከ ክርስቶስ፤ እስመ ማኅደሩ ውእቱ ልቦና ወነፍስ።
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ከመ ኮከብ ብሩህ፤ ወከመ ዕጣን ንፁህ፤ መርቆሬዎስ ኃያል መስተጋድል፤ ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር።
@EOTCW
@EOTCW
✨መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለመቃብሪከ ለህላዌከ መካኑ፤ ወለስጋከ ቀይጠኑ፤ መርቆሬዎስ ከማከ ኢተንስአ በበዘመኑ፤ መኑ መኑ ዝይትማስለከ መኑ፤ እንበለ ጊዮርጊስ ሰማእት ዘአዳም ስኑ።
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ጸለየ መርቆሬዎስ እንዘ ይብል ኀበ ይብል ኃበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ በረከት
@EOTCW
❄️ምልጣን
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ፤ ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ፤ ወተፈሥሑ፤ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።
@EOTCW
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
ወተፈሥሑ ባስልዮስ፤
ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።
@EOTCW
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ፤
ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።
@EOTCW
@EOTCW
🔸እስመ ለአለምዘሠንበት፦
ሠርዐ ለነ ሠንበት ለዕረፍት ዚአነ፤ ከመ ናዕበያ ወናክበራ ለእለተ ሰንበት፣መላዕክተ ሰማይኒ ወኩሉ ፍጥረት ፤እለ ውስተ ሲዖል እለ ውስተ ደይን፣ ያዕረፉ ባቲ ፤እስመ ቀደሳ አዕበያ ወአልዓላ ለዕለተ ሠንበት ፤መኑ ከማከ ስቡዕ እግዚኦ በውስተ ቅዱሳን ፤ማ፦ መንክር ስብዐቲከ፤ እግዚኦ ወትረ እሴብዐከ
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
መንክር ስብዐቲከ/2/
እግዚኦ ወትረ እሴብዐከ/4/
@EOTCW
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
1 161
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ሥርዓተ ዋዜማ ዘኅዳር ፳፭ መርቆሬዎስ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
በትግስቶሙ ለሠማእት ትድእን ሀገር፤ ወበጸሎተ ጻድቅ ትትፌሳሕ መካን፤ ዝክረ ጻድቅ በውዳሴ፤ ይትፌስሁ ገሀደ ተአሚኖሙ
@EOTCW
@EOTCW
❄️ምልጣን፦
ዝክረ ጻድቅ በውዳሴ፤ ይትፌስሁ ገሀደ ተአሚኖሙ፤ ይትፌስሁ ገሀደ ተአሚኖሙ
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
ይትፌስሁ ገሀደ ተአሚኖሙ
@EOTCW
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ሰማእት ኮኑ በሃይማኖት ወበጽንአ ትእግስት ሰማእት ኮኑ በሃይማኖት
@EOTCW
@EOTCW
💎እግዚአብሔር ነግሠ፦
ሰማእት ረከቡ ተስፋሆሙ ዘአሰፈዎሙ እስመ ቦሙ ተስፋ በዘይድኅኑ ተሣየጡ ምድረ በደሞሙ
@EOTCW
@EOTCW
💠ይትባረክ፦
ምዕዎ ለእኩይ ህሊና በእምነቶሙ እስመ ሰናየ ገድለ ተጋድሉ
@EOTCW
@EOTCW
💠ሰላም፦
በፍስሀ ወበሰላም ቦኡ ሰማእት ሀገር ቅድስት በገድሎሙ ወበትእግስቶሙ እምጸሀይ ያበርህ ገጾሙ በሠላም ቦኡ ሀገሮሙ
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
እምጸሀይ ያበርህ ገጾሙ፤
በሠላም ቦኡ ሀገሮሙ
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
1 161
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሥርዓተ ማኅሌት ዘህዳር ፳፬ ካህናተ ሰማይ ወተክለሃይማኖት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል
@EOTCW
✨መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለመታክፍቲክሙ መሠረተ ዓለም እለ ፆሩ: ኖትያተ ኖኅ ሥላሴ ወዕፀወ ዐባይ ሐመሩ: ዲበ መንበርክሙ ሰብአ ሶበ አምላክ ነጸሩ: ኪሩቤል ወሱራፌል ታህተ እገሪሁ ገረሩ: እስመ ለሊሁ አዘዘ ወእሉ ተፈጥሩ፡፡
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
እሉ ኪሩቤል ወሱራፌል የዓርጉ ሎቱ ስበሐት፤ እንዘ ይብሉ፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
@EOTCW
🔸🌱ዚቅ ዓዲ፦
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ መካነ ትጉሃን ዓፀዱ፤ ካህናተ ሰማይ ቀዉማን በዓዉዱ፤ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ፤ ቅድመ መንበሩ ይሰግዱ፤ይርዕዱ፤ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ።
💎ነግስ፦
ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል፤ ሱራፌል ወኪሩቤል ኡራኤል ወሩፋኤል ሶርያል ወፋኑኤል፤ አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል፤ ሊቃናተ ወነድ ዘሰማያዊት ማእፈድ፤ በንተ በግዑ እቀብዋ ለዛቲ አጸድ።
🌱ዚቅ፦
ሊቃናተ ነድ መላእክተ ምሕረት እለ ድልዋን ለሣህል፤ ሰአሉ አስተምህሩ ለነ፤ አስመ በጸሎት ትንብልናክሙ፤ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።
💎ነግስ
ይትባረክ ስምኪ ማርያም ለዘአውፃእከነ እምፀድፍ፤ በርኅራኄኬ ትሩፍ፤ ይዌድሱኪ ኪሩቤል በከናፍር ወአፍ፤ ሐራ ሰማይ ትጉሃን አኁዛን ሰይፍ፤ አምሳለ ደመና ይኬልሉኪ በክንፍ
🌱ዚቅ፦
ብፅእት አንቲ ማርያም ወዉድስት በአፈ ኩሉ፤ ኪሩቤል ይሴብሑኪ ወሱራፌል ይቄድሱኪ፤ መላእክት በበነገዶሙ ይትቀነዩ ለኪ፤ ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ ማርያም፤ እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም፤ ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ፤ ዕፁበ ግብረ መንግስተ ሥጋ ኢያርኃወ፤ ዕፁበ ግብረ።
💎ነግስ ዘዝክረ ቃል ፦
ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ፤ ወጻድቃኒከ ይትፌስሁ ጥቀ፤ ተክለሃይማኖት በልብሱ ኮከበ ብርሐን ሠረቀ፤ ካህናተ ሰማይ ዘይትአፀፋ መብረቀ፤ አፍቀርዎ ወኮንዎ ማእረ ወአውቀ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ለእሙንቱ ሐራ ዕበዮሙ ተዓዉቀ፤ ተክለ ሃይማኖት ዜነወ ጥዩቀ፤ በእንቲአነ ይተንብሉ ጽድቀ፤ ካህናተ ሰማይ ይሴብሑ ሊቀ፤ ተ ልቢቦሙ ዘእሳት መብረቀ።
🔸🌱 ዓዲ
ይቤ መምህርነ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ፤ ለልየ ርኢኩ መንበሮ ለሊቅ፤ ካህናት የዓጥኑ በማዕጠንት ዘወርቅ፤ እምገበዋቲሁ ይወጽእ መብረቅ።
@EOTCW
🌱🌱 ዘጣእሙ፦
ሰላም ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
🌱ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ ወያሚሆሙ ለካህናት፤ ነያ ጽዮን መድኃኒት።
🔸🌱ዚቅ አዲ፦
ሱራፌል ወኪሩቤል ይኬልልዋ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና መድሐኒት ይዕቲ፤ ንብረታ ጽሙና፤ ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት።
@EOTCW
✨መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለእንግዳከ ዘጥበብ ምዕላድ፤ ወዘመንፈስ ቅዱስ ማህፈድ፤ ተክለሃይማኖት ያእቆብ እንተ እግርከ ግሙድ፤ ያስተበጽዑከ ሰማያዊያን ነገድ፤ እለ ይገሥሡ እሳተ በዕድ።
🌱ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ብሩህ ከመ ፀሐይ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ዘቦአ ቤተ መቅደስ ሃሌ ሉያ፤ ዝኬ ውእቱ ገብርኤል መልአክ፤ ዘባጢሁ ለእሳት፤ ዘልብሱ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ አስተብዕዎ ኩሎሙ መላእክት
@EOTCW
✨መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለአዕዳዊከ ዘገስሳ ነዶ፤ ለእግዚአብሔር አምላክ ስብሐተ መላእክት ዘየዐውዶ ፤ተክለሃይማኖት አብርሃም ዘጻመውከ በተአንግዶ፤ አድኅነኒ እምቃሳሜ ወይን አመ ይሌዕል ማዕጸዶ፤ እስመ አበ ስሩዕ ከመ ያድኅን ወልዶ
🌱ዚቅ፦
ለካህናት ሰመዮሙ መረግደ፤ እደዊሆሙ ይገሣ ነደ፤ በቅድመ አቡሁ ይሠዉዑ ወልደ፤ ወማዕጠንቶሙ ይትፈቀር ፈድፋደ።
@EOTCW
✨መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለኩልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግሥት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ አበ ብርሃናት፤ ተክለሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት፤ ጸሎትከ ዘገበርክሃ እስከ ኊላቔ ምእተ አመት፤ መድኃኒት ትኩነኒ እምግሩም ቅስት።
🌱ዚቅ፦
ይሰግድ በብረኪሁ፤ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር።
@EOTCW
✨መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም እብል ለስእርተ ርእስክሙ ዘላህበሰ፤ ዘቦቶን ዕፍረት ዘመአዛሁ እጹብ፤ ዕሥራ ወርብዕ ሰማያዊያን አርባብ ፤ ምስለ አብያጺሁ እለ ይቄድሱ ኪሩብ፤ እምኔክሙ ይትአኰት ወይሴባህ አብ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
መንበረ ልዑል የዓጥኑ ቃለ ፈጣሪ ይሰምዑ፤ ብፁዓን ካህናት ጽርሐ አርያም የኃድሩ።
✨መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም ለእስትንፋስክሙ እስትንፋስ ርትዕ ወሣህል፤ ኀዋኅወ ሰማይ አንትሙ እለ ሱራፌል፤ለእግዚአብሔር ዘይነብር ዲበ መንበሩ ልኡል፤ ይቀውሙ ዓውዶ ወይኬልሁ በቃል፤ ዘነጸረክሙ ኢሳያስ ይብል
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ኢሳይያስኒ ይቤ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር፤ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዋህ ወብሩህ፤ ወምሉዕ ቤተ ስብሐቲሁ፤ መልዓ ምድር ስብሐቲሁ፤ አዕላፈ አዕላፋት መላዕክት፤ ወትዕልፊተ አዕላፋት ይቀዉሙ ዓዉደ።
@EOTCW
✨ መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም ለእመታቲክሙ መንፈሳዊያን አንጋድ፤ ዘኅብራቲክሙ አምሳለ መረግድ፤ ሊቃናት ዕሥራ ወ፬ቱ በፍቅድ፤ ረስይዎ ከመ አዘቅት ወከመ ስቁር ጽኢድ፤ ለኀጕለ ህይወትየ ዘይፈቅድ አብድ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ለካህናተ ሰማይ ኅብራቲሆሙ ከመ መረግድ፤ ወአልባሲሆሙ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ይቤ ተክለ ሃይማኖት ዘገብረ ሰማ፤ ለሥላሴ ይደሉ ስብሐት፤ እስመ ወሀቡነ ሲሳየ ዕለት፤ ኅብስተ ቅዳሴ ዘይሴሰይዎ መላእክት።
@EOTCW
✨ማህሌተ ጽጌ፦
ዓቢይ ውእቱ ተአምር ጸግዮትኪ በድንጋሌ፤ ወፈርዮትኪ በንጽሕ ቁርባነ አምልኮ መጥለሌ፤ ማዕጠንተ ሱራፌ ዘወርቅ ወጽዋዓ ኪሩብ ዕንቈ ቢረሌ፤ አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ፤እንበሌኪ ማርያም ዘየዓርግ ሉዓሌ።
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ ማርያም፤ በማዕጠንት ዘወርቅ፤ ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ካህናት ሰማያዉያን፤ እለ ይከዉኑ ጸሎተ ኩሎሙ ቅዱሳን መሐይምናን፤ እምዲበ ምድር በዉስተ ማዕጠንቶሙ፤ ከማሁ በስእለተ ስምኪ፤ የዓርጉ ስእለቶሙ ለዕጓለ እመሕያዉ፤ ዉስተ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
❄️ምልጣን፦
ሰአሉ ለነ ጻድቃን ውሉደ ብርሀን ፤ ከመ ንድኅን በጸሎትክሙ፤ ጸልዩ ለነ ካህናት አግብርት እግዚአብሔር ፤እስመ ለክሙ ይቤለክሙ፤ አማልክት አንትሙ፤ ወደቂቀ ልዑል ኩልክሙ
@EOTCW
✴️ቅንዋት፦
ለካህናት አልበሶሙ ሕይወተ ለእለ ዓቀቡ ሕጎ ተአሚኖሙ በመስቀሉ እንዘ ይጸንሑ ምድረ ሐዳሰ እንተ አሰፈዎሙ፤ወአንተ ወሀበ ለአበዊሆሙ ሀገሮሙ፤ ኢየሩሳሌም ቅድስት
https://t.me/Eotcw
1 161
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ሥርዓተ ዋዜማ ዘኅዳር ፳፬ ካህናተ ሰማይ ወተክለ ሐይማኖት
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ሃሌ ሉያ ዘይዌልጦ ለሰማይ ወይኄድሳ በምድር በበረከቱ፤ ኅሩያነ ዚአሁ የኃድሩ ውስቴታ፤ ለካህናት አልበሶሙ ህይወት፤ ጻድቃንኒ ትፍስሕት ይትፌስሑ፤ ወይትወሀውሁ በአዝማን ፤ ዘአልቦ ኁልቊ።
@EOTCW
@EOTCW
❄️ምልጣን፦
ለካህናት አልበሶሙ ህይወት፤ ጻድቃንኒ ትፍስሕት ይትፌስሑ፤ ወይትወሀውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኁልቊ፤ወይትወሀውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኁልቊ።
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
ወይትወሀውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኁልቊ/2/
ወይትወሀውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኁልቊ/4/
@EOTCW
@EOTCW
💎በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ካህናት ክብር ይደልዎሙ ለእለ ይትለአኩ ሰናየ መላእክት ካህናት ክብር ይደልዎሙ
@EOTCW
@EOTCW
💎እግዚአብሔር ነግሠ፦
ለካህናቲከ እግዚኦ ለካህናቲከ እለ አስመሩከ ትቤሎሙ ባዑ ጽርአ መቅደስከ ኃበ የኃድር ኃይለ ስብሐቲከ
@EOTCW
@EOTCW
💎ይትባረክ፦
ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቅ ወጻድቃኒከ ትፍስሕት ይትፌስሑ
@EOTCW
@EOTCW
✴️ሰላም
በ4
ካህናቲከ ወምእመኒከ ይሴብሑከ የዓርጉ ለከ መስዋዕት ንጹሐ እንበለ ኑፋቄ ወይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ንጉሰ ሰላም ሰላምከ ሀበነ
@EOTCW
🔹አመላለስ፦
ወይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር /2/
ንጉሰ ሰላም ሰላምከ ሀበነ/4/
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ ኅዳር ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው በሐዋርያው በቅዱስ ጴጥሮስ እጅ ለተጠመቀ ለመቶ አለቃ ለነበረው ለጻድቁ ቅዱስ ቆርኔሌዎስና የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለሆነ ለነቢዩ ቅዱስ አብድዩ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ መቶ አለቃው ጻድቁ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ፡- ይህም ቅዱስ የፍልስጤም ክፍል በሆነች በቂሣርያ የመቶ አለቃ ሆኖ የተሾመ ነው፡፡ እርሱም አስቀድሞ ከዋክብትን ሲያመልክ የነበረ ነው፡፡ እንደርሱ ማንም ሊአደርግ የማይቻለውን የሚያመልካቸው አማልክቶቹም ቢሆኑ በሐዋርያት እጅ የሚደረገውን የተአምራታቸውና የስብከታቸውን ዜና በሰማጊዜ ወዲያውኑ ለአማልክት መስገድን አቆመና በጾም በጸሎት ተወስኖ ለድኆችና ለችግረኞች የሚመጸውት ሆነ፡፡ ሁል ጊዜም በጸሎቱም "አቤቱ እውነተኛው አምላክ ሆይ! እኔ አንተን ከማወቅ ጎደሎ ነኝና አንተ ግን የቀናውን መንገድ ምራኝ" እያለ ይለምን ነበር፡፡ ይቅር ባይ ቸር እግዚአብሔርም ቆርኔሌዎስን ይቅር ብሎት ልመናውን ተቀብሎት መልአኩን ላከለት፡፡ እርሱም መልአኩን ባየው ጊዜ ደነገጠ፡፡ መልአኩም "ቆርኔሌዎስ ሆይ! ጸሎት ልመናህ ምጽዋትህ መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓልና ደስ ይበልህ፡፡ አሁንም በጫማ ሰፊው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ስምዖን ጴጥሮስን ይጠሩልህ ዘንድ ሰዎችን በባሕር አቅራቢያ ወዳለች ኢዮጴ ከተማ ላክ" አለው። ቆርኔሌዎስም መልአኩ እንደነገረው ቅዱስ ጴጥሮስን ከስመጣው በኋላ ከእግሩ በታች ሰገደለት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም አነሣውና "እኔም እንደ አንተ ሰው ነኝ" አለው፡፡ ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ቆርኔሌዎስም ቤት ብዙ ሰዎችን ተሰብስበው አገኘ፡፡ ቆርኔሌዎስም ቅዱስ ጴጥሮስን ያስጠራበትን ምክንያት መልአኩም ተገልጦለት የነገረውን ሁሉ በዝርዝር ከነገረው በኋላ "እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ ሁላችን በፊትህ አለን" አለው፡፡ ሐዋ10፥1-31፡፡
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም አንደበቱን ገልጦ የጌታችንን ሰው የመሆኑን ምሥጢር መከራ መስቀሉን፣
ሞቱ፣ ትንሣኤውን ፣ዕርገቱንና ዳግመኛም ለፍርድ እንደሚመጣ በግልጽ አስተማራቸው፡፡ ቆርኔሌዎስም በዚህ ጊዜ ከነቤተሰቡ በጌታችን አምኖ ተጠመቀ፡፡ ከዚያ የነበሩ ብዙ አሕዛብም አምነው ተጠመቁ፡፡ ከዚህም በኋላ ቆርኔሌዎስ ይህን ዓለም ለመግዛት የተሾመውን ሹመቱን ትቶ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነ፡፡ ሐዋርያውም ቆርኔሌዎስን እጆቹን ጭኖ በእስክንድርያ አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው፡፡
❤ ቅዱስ ቆርኔሌዎስም በእስክንድርያ ወንጌልን እየሰበከ ብዙ ጣዖታት የሚያመልኩ ሰዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው፡፡ እያስተማረ መኰንኑን ዲሜጥሮስን ጨምሮ ብዙዎችን አሕዛብ አጠመቃቸው። በፊታቸውም ብዙ ተአምራትን ያደርግ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስና ስንክሳር የኅዳር 23።
+ + +
❤ ቅዱስ አብድዩ፦ ይህም ቅዱስ ከጠፍ በረሀ አቅራቢያ ከአለች ሱሳም ከምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው። ለነቢይ ቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙሩ ሁኖ ብዙ መከራን በእርሱ ላይ መጣውን ታግሦ ከመከራውም በትዕግሥቱ ዳነ።
❤ ይህም ኤልያስን የተለማመጠና ኤልያስም አዝኖለት አብሮት ወደ ንጉሥ አክዓብ የሔደለት ሦስተኛው የሃምሣ አለቃ ነው። ከዚህም በኋላ ምድራዊ ንጉሥን ማገልገልን ትቶ ነቢይን ሆነ የትንቢቱንም ወራት አድርሶ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ አብድዩ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ስንክሳር የኅዳር23።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ብእሴ ሐዲስ መርዓ። ቆርኔሌዎስ ዋሕድ እምነ አርድእት ፸ዓ። ኀቤከአ ከመ አስተበቊዐ። ይጠይቅ አርአያከ ወአምሳሊከ ኅቡአ። ኬንያ ሥዕልከ መዊቶ ተንሥአ"።
+ + +
❤ "ሰላም ለአብድዩ መንፈስ አእምሮ ለባሲ። በውሣጤ በዓት ዘኅብአ ነቢያተ እስራኤል ይሴሲ። እንዘ ያጤይቅ ምጽአቶ በከዊነ አምላክ ወብእሲ። ይቤ በአፉሁ እግዚአብሔር ነጋሢ። ለእለ ተኀርዩ መድኃኒተ በጽዮን እሬሲ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 23።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዝኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እምኌቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 10፥23፥34። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቆርኔሌዎስና የነቢዩ የቅዱስ አብድዩ የዕረፍታቸው በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
