ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
አመ ፰ ለየካቲት በዓለ ልደተ ስምዖን ስርአተ ማህሌት
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል
👉@EOTCW
👉@EOTCW
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCW
ዚቅ፦
ስብሀት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም በቤተልሔም ተወልደ፤ ወሠረፀ ፍሬ ስብሐት፤ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ለሕጻን
@EOTCW
@EOTCW
ዘጣእሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCW
ዚቅ፦
ወይቤላ ስምዖን ለማርያም ዝንቱ ወልድኪ ሥዩም ዕድቀቶሙ ወለተንስኦቶሙ ለደቂቀ እስራኤል ሐቂፎ በትፍስህት የበቦ
@EOTCW
ዚቅ(ዓዲ)፦
ወዘንተ ሰሚዓ ማርያም አስተዓፀበት ወትቤሎ፣ ኦ አረጋዊ ብሉየ መዋዕል አንተ፤ዝንቱ ሕፃን፤ ማዕዚ አሠርከ ወዕፎ ይፈትሐከ
@EOTCW
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ
@EOTCW
ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ንሰብከ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፣ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉኃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ።
@EOTCW
ዚቅ(ዓዲ)፦
ስምዖን ተወክፎ ዳዊት ዘመሮ፤ነቢያት ቀዲሙ አእምሮ ፤ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፣ሰብአ ሰገል እሙነ ኮነ ልደቱ
@EOTCW
ወረብ፦
ነቢያት ቀዲሙ አእምሮ ሐዋርያት አሠሮ ተለዉ ፣
ወስምዖን ተወክፎ ተወክፎ ዳዊት ዘመሮ
@EOTCW
@EOTCW
መልክአ ኢየሱስ፦
ሰላም ለክሣድከ ግብረ መንፈስ ቅዱስ ኬንያ፤አዳም ስና ወመንክረ ላህያ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ ወሐዋርያ፤ አመ ወጽሐ ስሙዓቲከ በአድያመ ኵሉ ሶርያ፤ ብፁዓት አዕንቲከ ኪያከ ዘርዕያ።
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
ተነበየ ስምኦን ወይቤ ኢይመውት ዘእንበለ አርአይ መሲሖ ለእግዚአብሔር ርዕዮ ባረኮ ወይቤሎ ብርሀነ ዘከሰትከ ለአህዛብ ወክብረ ለህዝብከ እስራኤል
@EOTCW
ዚቅ(ዓዲ)፦
በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ እስ ርዕያ አእይንቲየ አድኅኖተከ
@EOTCW
ወረብ፦
በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፤
እለ ርዕያ አእይንቲየ አእይንቲየ አድኅኖተከ፤
@EOTCW
መልክአ ኢየሱስ፦
እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤ ተሰብኦትከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤ ያንኮርኲር ታሕት ደይን ግዱፈ ከዊኖ።
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
ነአምን ልደቶ አስተርእዮቶ ወስምኦን ተወክፎ ውስተ ህፅኑ
@EOTCW
ወረብ፦
ነአምን ልደቶ ልደቶ አስተርእዮቶ፤ ወስምኦን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ውስተ ሕፅኑ ውስተ ሕፅኑ ለሕፃን
@EOTCW
ምልጣን፦
ስምዖን ተወክፎ ዳዊት ዘመሮ፤ነቢያት ቀዲሙ አእምሮ ፤ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፣ሰብአ ሰገል እሙነ ኮነ ልደቱ
@EOTCW
ወረብ፦
አእምሮ ቀዲሙ አሠሮ ተለዉ ሐዋርያት፤
ስምዖን ተወክፎ ዳዊት ዘመሮ ዘመሮ ዳዊት፤
@EOTCW
እስመ ለአለም፦
@EOTCW
መንክር ልደቱ ወመንክር አስተርዮቱ፤ ዝኬ ውእቱ አምላከ ፍፁም ዘተነገረ በያዕቆብ፤ዘይሰባሕ በልዑላን ወልደ ድንግል፤ ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ፤ማ፦ዘዳዊት ዘመሮ፤ለሙሴ ገሃደ ተናግሮ
@EOTCW
አመላለስ፦
ዘዳዊት ዘመሮ፤
ለሙሴ ገሃደ ተናግሮ፤
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ ዘእስመ ለአለም፦
ለሙሴ ገሃደ ለሙሴ ገሃደ ተናግሮ፤
ስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ውስተ ሕፅኑ ለሕፃን
👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@EOTCE
#Join & share
1 161
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አመ ፰ ለየካቲት ልደተ ስምዖን ስርአተ ዋዜማ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በ፩-ሀሌታ
ስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ለሕፃን፤ባረኮ ወይቤሎ ፤ብርሃነ ዘከሠትከ ለአሕዛብ፤ ወክብረ ለሕዝብከ እስራኤል፤ ዝንቱ ሕፃኑ ሥዩም፤ ለተንሥኦቶሙ፤ ለደቂቀ እስራኤል
@EOTCW
@EOTCW
አመላለስ፦
ለተንሥኦቶሙ ለደቂቀ እስራኤል፤
ለተንሥኦቶሙ ለደቂቀ እስራኤል።
@EOTCW
ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
ባረኮ ወይቤሎ ብርሃነ ዘከሠትከ ለአሕዛብ ባረኮ ወይቤሎ
@EOTCW
@EOTCW
እግዚአብሔር ነግሰ፦
በቤተልሔም ተወልደ ወበናዝሬት ተሐውፀነ ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ዳዊት ዘመሮ ወዮሐንስ አንጸሮ ለሙሴ ገሃደ ተናግሮ
@EOTCW
ይትባረክ፦
በቤተልሔም ተወልደ፤ ወሠረፀ ፍሬ ስብሐት፤ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ለሕጻን
@EOTCW
@EOTCW
ዘ፫ት ደቂቅ፦
ተነበየ ስምዖን ወይቤ፤ ኢይመውት እርአይ መሢሖ ለእግዚአብሔር፤ርእዮ ባርኮ ወይቤሎ፤ ብርሃነ ዘከሠትከ ለአሕዛብ ፤ወክብረ ለሕዝብከ እስራኤል
@EOTCW
ሰላም፦
ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ለሕጻን ወይቤሎ በሰላም እግዚአ በከመ አዘዝከ ብርሃነ ዘከሠትከ ለአሕዛብ
🇪🇹👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
🇪🇹👆👆👆👆👆🇪🇹
@EOTCW
#Join & share
1 161
😭 ዜና ዕረፍት
😭 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እንጦንዮስ የኤርትራ አገር ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 3ኛ ፖትርያርክ ከዚህ ዓለም ድካም በ92 ዓመታቸው ዐረፋ።
😭 ብፁዕነታቸው እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር 1929 ዓ.ም በሓማሴን አውራጃ ተወለደ። የብፁዕ አቡነ ያዕቆብን ዕረፍት ተከትሎ። ከሚያዝያ 23 2004 (እ.ኤ.አ) ሶስተኛ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፖትርያርክ ሆነው ማገልገል ጀመሩ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ በኢትዮ ኤርትራ በባድመ ጦርነት ካህት መስቀል ይዞ እንዴት ይዘምታል፤ የሃይማኖት አባቶችን እግልት እስራትን በመቃወማቸው የሻዕቢያ መንግሥት 2006 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለ13 ዓመታት በእስር ቤት በግዞት አቆይቷቸዋል። ከዚያም ከተፈቱ በኋላ በቁም እስራት ሕይወታቸው እስከ አለፈ ድረስ ቆይተዋል።
😭 የብፁዕ አባታችን ነፍስ እግዚአብሔር አምላክ ከደጋጎቹ ብፁዓን አባቶች ከቅዱስ አትናቴዎስ፣ ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ከቅዱስ ፍሬምናጦስ (ሰላማ ከሳቴ ብርሃን) አጠገብ ያሳርፍልን። በረከታቸው ይደርብን።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለኤፍሬም ደራሲ ዘጽሩይ ልሳኑ፤ አብያተ ክርስቲያናት ይሰርገዉ በድርሳኑ"። ትርጉም፦ አብያተ ክርስቲያናት በድርሳኑ ያጌጡ ዘንድ አንደበቱ የጠራና ደራሲ ለኾነ ለኤፍሬም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም እብል ፍልሰተ ሥጋው ማሕየዊ። ለዘሐመ ብእሲ ወለዘይደዊ። ምሉአ ጥበበ ወምክር ኤፍሬም ሶርያዊ። አመ አስተርአይከ ማዕከለ ሕዝብ ሐሳዊ። በተዋሥኦትከ ጽድቀ ተሞዐ ዐላዊ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 3።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@eotcw
1 161
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሕዝብ መካከል ወጣ እያለቀሰ ጸለየ እንዲህም አለ "አቤቱ በጌትነትህ ክብር ፊት የረከሰች አፌን እንዴት እገልጣለሁ በኃጢአት ብዛት የጠቆረ ፊቴንስ እንዴት ቀና አደርጋለሁ ነገር ግን እንደ ይቅርታህ ገናናነት እንደ ቸርነትህም ብዛት ሕዝብህን ይቅር በል አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና" በዚያንም ጊዜ ብዙ ዝናም ወረደ እርሱም ጸሎቱንና ንስሓውን እግዚአብሔር እንደ ተቀበለው ኃጢአቱንም እንደ ተወለት አወቀ።
❤ ከዚህም በኋላ አስቀድሞ እንደሚሠራው ተግቶ መጸለዩንና መስገዱን አላጐደለም ነፍሱንም "ዳግመኛ በኃጢአት ውስጥ እንዳትወድቂ ተጠበቂ" በማለት ይገሥጻት ነበር ከዚህም በኋላ ዕድሜውን አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ የካቲት3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ያዕቆብ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን የሶርያዊ ቅዱስ ኤፍሬም የሥጋው ፍልሰት ሆነ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። ምንጭ፦ የካቲት3 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለያዕቆብ በደዌ ኃጢኣት ዘሐመ። ሶበ አመንከሮ ሰይጣን እንዘ ይነብር ገዳመ። እግዚአብሔር ምክሮ ውስተ ሕሊናሁ ዓቀመ። እምቀቢጸ ተስፋ ከመ ይነስሕ ዳግመ። እስከ በጸሎቱ አውረደ እምሰማይ ዝናመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት3።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአእይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እም ዳህፅ"። መዝ 55፥13። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-17፣ ያዕ 4፥7-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥9-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 7፥12-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ኤፍሬም የሥጋ ፍልሰት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የካቲት ፫ (3) ቀን።
❤ እንኳን ለባሕታውያን አለቃ ኑሯቸውም የመላእክት ኑሮ ለሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ ለተገኘ ቅዱሳን መላእክትም ክብራቸውን ለመሰከሩላቸውና በሌላ ቦታ ያሉ ሰዎችን በቃላቸው ብቻ ይፈውሱ ለነበሩ ለከበሩ አባት ለአባ ዕብሎይ ለዕረፍት በዓል፣ ተጋዳይ ለሆነ ለመነኰስ ሰይጣን በፈተና ጥሏቸው ለነበሩና በኋላም ምግብ ሳይበሉ ሳር ብቻ እየተመገቡ 30 ዓመት ለኖሩት እግዚአብሔርም ይቅር ብሏቸው ስለእርሳቸው ብሎ በድርቅ ወቅት ዝናብ ላዘነበላቸው ለአባ ያዕቆብ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት ለሶርያዊ ቅዱስ ኤፍሬም ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ አባ ዕብሎይ፦በዕብሎይ ስም የተጠሩት ይኸኛው አባት "የባሕታዊያን አለቃ" የተባሉ ኑሯቸውም "የመላእክትን ይመስላል" የተባለላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ከስደቱ በተመለሰ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ኤጲስቆጶስ አባ ባስልዮስ ዘንድ መጥቶ አንድ ላይ አድረው በግብፅ ገዳም ስለነበሩ ቅዱሳን እየተጨዋወቱና እያወዳደሩ ሲወያዩ አደሩ፡፡ በማግስቱም ቅዱስ አትናቴዎስ ታላቅ ራእይን አየ፡፡ይኸውም እስከ ሰማይ የምትደርስ ታላቅ ዛፍ ነበረች፣ ቅርንጫፎቿ እስከ ባሕር ደርሰዋል፡፡ ብዙ ሰዎችም ከቅርንጫፎቿ በታች ተጠልለዋል፡፡ በመካከሏም መሠዊያ ታቦት አለ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለአባ አትናቴዎስ ተገለጠላቸውና "ያየኸውን ራእይ ከአባ ባስልዮስ ጋር ተነጋገር ምሥጢሩን እኔ እገልጥልሃለሁ" አለው፡፡ መልአኩም ምሥጢሩን ለሁለቱ ቅዱሳን አባቶች ተረጎመላቸው፡፡ "ዛፏ በግብፅ አውራጃ የምትሠራ ገዳም ስትሆን ቅርንጫፎቿ መነኰሳት ናቸው፡፡ መሠዊያውም መላእክት የሚጎበኙት የእግዚአብሔር ማደሪያ ርኩሳን መናፍስትን የሚሽር የሐዋርያት አለቃ የጴጥሮስ አምሳል የሆነ አባ ዕብሎይ ነው"በማለት ገልጾላቸዋል፡፡
❤ አባ ዕብሎይ እጅግ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ መልካቸው እየተለወጠ እንደሚነድ እሳት እየሆኑ ሰውነታቸው የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ፡፡በቃላቸው ብቻ ለምጻሞችን ያነጹ ነበር፡፡ በእስክንድርያ የሚኖር አንድ የመቶ አለቃ የአባ ዕብሎይን ዜና ሰምቶ በረከታቸውን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዕብሎይ እንዲልከው ሊቀ ጳጳሳቱን ቅዱስ አትናቴዎስን ለመነውና እርሱም ከሰባት መነኰሳት ጋር ላከው፡፡ የመቶ አለቃውም አባ ዕብሎይን ባገኛቸውና በተሳለማቸው ጊዜ ዕውር የነበረቸው አንድ ዐይኑ ወዲያው በራችለት፡፡ ዳግመኛም "ሚስቴ በለምጽ ደዌ ትጨነቃለችና እርሷም፡ በአስኬማህ የተማጸነች ናትና እኔ ያገኘሁትን ጸጋህን ለእርሷም ይድረሳት" እያለ ለመናቸው፡፡ አባ ዕብሎይም "በክብር ባለቤት በጌታችን ስም ፈውስ ይሁንላት" ብለው በተናገሩበት ቅጽበት የመቶ አለቃው ሚስት ባለችበት ሆና ከደዌዋ ተፈወሰች፡፡
❤ በአንዲትም ዕለት አቡነ ዕብሎይ ከመኰሳት መካከል ቁሞ "ቤተ ክርስቲያን የምሠራበትን ያስገነዝበው ዘንድ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይመጣልና አንዱ ከእናንተ አይሒድ፡ከዚህ ይኑር እንጂ" አላቸው። ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበሩ ደቀ መዛሙሩቱና ከመላእክቶቹ ጋር መጣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ የሚመሠረትበትንም አሳያቸው።
❤ እርሱም በበጎ ሥራ ሁሉ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ፍቅርንም ያጸኑ ዘንድ ልጆቹን ይመክራቸው ነበር እየመከራቸውም ፊቱ ተለውጦ እንደ እግዚአብሔርን መልአክ ፊት ሆነ ሁለመናውም እንደሚነድ እሳት ሆነ እነርሱም ፈሩ። እርሱም "ልጆቼ አትፍሩ እነሆ እኔ እሰናበታችኋለሁ" አላቸው። ይህንንም ብሎ ነፍሱ ተመሠጠች በጎ መዓዛም ሸተተ ወዲያውኑ ዐይኑ ተገለጠና "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳኝ ነፍሴንም ወዳንተ ተቀበል" አለ ይህንንም ብሎ የካቲት3 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ምንጭ፦ የየካቲት3 ስንክሳርና መዝገበ፡ቅዱሳን።
+ + +
❤ አባ ያዕቆብ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ይህን ዓለም ትቶ መነኰሰና በአንዲት ዋሻ ውስጥ የሚኖር ሆነ ያለ ማቋረጥም በቀንና በሌሊት ሁል ጊዜ ይጾማል ይጸልያል በመስገድም ይተጋ ነበር ከበዓቱም ወጥቶ ወደ መንደር አይገባም የሴት ፊትም አያይም እንዲህም ሁኖ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ዲያብሎስ ከሚከተሉት ክፉዎች ሰዎች ውስጥ ምክንያት ፈጥረው አንዲቷን አመንዝራ ሴት ወደርሱ እንድትገባ አደረጓት በገባችም ጊዜ የኃጢአትን ሥራ እያስታወሰች በፊቱ መጫወት ጀመረች ቅዱስ ያዕቆብም ገሠጻት በገሀነም እሳትም ዘላለም ሲቃጠሉ መኖርን አሳሰባት ደንግጣም ንስሐ ገባች እግዚአብሔርንም የምታገለግል ሆነች። ሰይጣንም መፈታተኑን አልተወውም ከአገር ታላላቆች በአንዱ ሰው በሴት ልጁ ላይ አደረ የሚጥላትና የሚያንከባልላት ሆነ ወደ አባ ያዕቆብም ይወስዳት ዘንድ እርሱም ሊያድናት እንደሚችል አሳበው አባቷም ወደ አባ ያዕቆብ አደረሳትና በላይዋ ይጸልይ ዘንድ ለመነው እርሱም በላይዋ ሲጸልይ ዳነች አባቷም ያ ሰይጣን እንዳይመለስባት ብሎ ከታናሽ ብላቴና ወንድሟ ጋር ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ተዋት።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሷ ጋር በኃጢአት እስከ ጣለው ድረስ እርሷን በማሳሰብ በሌሊትም በቀንም በዝሙት ጦር ሰይጣን ተዋጋው በኃጢአትም በወደቀ ጊዜ ስለ ርሷ እንዳይገድሉት ፈርቶ ኃጢአቱ እንዳገለጥ ከወንድሟ ጋር ገደላት ሰይጣንም ደግሞ ቀቢጸ ተስፋ በልቡ አሳደረበት ወደ ዓለም ሊሔድ ከበዓቱ ወጣ። የኃጢአተኛውን ሞት የማይወድ መሐሪ ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ጻድቅ የሆነ መነኰስ ወደርሱ ላከ በጐዳናም ሲጓዝ ተገናኘውና ሰላምታ ሰጠው እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ወንድሜ ሆይ ምን ሁነሃል አዝነህ ተክዘህ አይሃለሁና የደአሰብህስ ምንድን ነው?"። እርሱም የሆነውን ሁሉ ከዚያች ብላቴና ጋር በኃጢአት እንደ ወደቀና ከወንድሟ ጋር እንደገደላት ነገረው። ያ ጻድቅ መነኰስም "አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ እግዚአብሔር መሐሪ ይቅር ባይ ምሕረቱ የበዛ ነውና" አለው። ከዚህም በኋላ የጾም የጸሎት የስግደት ቀኖናን እንዲይዝ አዘዘው።
❤ እርሱም ተመልሶ ከአንድ ፍርኩታ ውስጥ ገባ በውስጡም ራሱን እሥረኛ አደረገ በታላቅ ድካምና በብዙ ችግርም ላይ ታገሠ በመጾም በመጸለይ አብዝቶ በመስገድም ሁልጊዜ ይተጋል ከምድር የሚበቅል ሣርንም የሚመገብ ሆነ አብዝቶ እያዘነ "እግዚአብሔር ይቀበለኝ ይሆን ብዙ በደሌንስ ይተውልኝ ይሆን" ይላል እንዲህም በመጸጸት እየተጋደለ ሠላሳ ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርም ንስሐውን እንደተቀበለለት ሊገልጥ ወዶ በአገር ውስጥ ረኃብን አመጣ ለዚያች አገር ኤጲስቆጶስም "በፍርኩታ ውስጥ ከሚኖር ከመነኰስ ያዕቆብ ጸሎት በቀር ይህ ረኃብ አያልፍም" አለው። በዚያንም ጊዜ ኤጲስቆጶሱ ከእርሱ ጋር ካህናቱንና የዚያችን አገር ሰዎች ይዞ ተነሣ ወደ ቅዱስ ያዕቆብም ደርሰው ስርሳቸው ይጸልይ ዘንድ ለመኑት እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸውና ዝናምንም እንዲአወርድላቸው አባ ያዕቆብም "እኔ እግዚአብሔርን በኃጢአቴ ያሳዘንሁት ኃጢአተኛና በደለኛ ሰው ነኝ" አላቸው። ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ እግዚአብሔር ያለውን ነገረው።
