fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1.24 KB

30/2/2015 ዓ.ም (፴/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወተጸእልኩ በኀበ ኰሎሙ ጸላእትየ። ወፈድፋደሰ በኀበ ጎርየ። ግሩመ ኮንክዎሙ ለአዝማድየ፡፡ መዝ. 30፥11 🕯 ትርጉም በጠላቶቼ ዘንድ ተነወርሁ። ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥ ለሚያውቁኝም ፍርሀት ሆንሁ በሜዳ። ያዩኝም ከእኔ ሸሹ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለማርቆስ ዜናዊ ወንጌለ ጽድቅ ሰባኪ ለእለ በግብፅ ኖላዊ"። ትርጉም፦ በግብፅ ላሉ ምእመናን ጠባቂን ለኾነ የጽድቅ ወንጌልን የሚያስተምር ለኾነው ለባለምሥራቹ ለቅዱስ ማርቆስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አንገት በግፍ በሰማዕትነት ከተቆረጠች በኋላ በግልጽ ለታየችበት ዕለት መታሰቢያ በዓል፣ መኑፍ ከሚባል አገር በገድል ለተጸመደ ለቅዱስ አባት ለባሕታዊ አባ አብርሃም ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰቡ፦ ከፋሲለደስ፣ ከቢርወካይና፣ ከመርቲስ ከማርስና ከንጉሥ ይስሐቅ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ባሕታዊ አባት አባ አብርሃም፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ናቸው በዚህም ዓለም ገንዘብ ባለጸጎች ነበሩ። ይህም ቅዱስ በአደገ ጊዜ የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ሽቶ በላዕላይ ግብጽ ወደሚገኝ ወደ አገረ አክሚም በመርከብ ተጭኖ ሔደ ወደ አባ ጳኲሚስ ደረሰ እርሱም የምንኲስና ልብስን አለበሰው በገድልም በመጸመድ ሥጋውን አደከመ በአባ ጳኲሚስም ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሃያ ሦስት ዓመት ያህል በማገልገል ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው አባ ጳኲሚስን ለመነው እርሱም ፈቀደለት ዓሣ የሚያሠግሩበትን መረብ የሚሠራ ሆነ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ሰውን አመጣለት ያም ሰው መረቡን ሽጦ ምግቡን አተር ይገዛለታል የተረፈውንም ለድኆች ይሰጣል የምግቡም መጠን ሁሉጊዜ ማታ ማታ አንዲት እፍኝ ከጨው ጋር በውኃ የራስ አተር ነው። እንዲህም እየተጋደለ በዚያች ዋሻ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ ልብሱም ከገዳም ሲወጣ የለበሰው ከዘመን ርዝመት የተነሣ አርጅቶ ተበጣጠሰ ሥጋውንም በጨርቅ የሚሸፍን ሆነ። በየሁለት ዓመትም ወደ መነኰሳቱ ገዳም በውጣት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር። ❤ በዚያችም ዋሻ መኖር በጀመረባት ዓመት ሰይጣናት ወደ ርሱ በምጣት ምትሐት እየሠሩ ተፈታተኑት እርሱ ግን ውሻን እንደሚአበር ሰው አበረራቸው። ❤ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ሕዝባዊ ሰው ልኮ የአባ ጳኲሚስን ረድእ አባ ቴዎድሮስን አስጠራው በመጣም ጊዜ ሰግዶ ሰላምታ ሰጠው እንዲጸልይለትና በጸሎቱም እንዲአስበው ለመነው። ከዚህም በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ በዚያም ጊዜ አባ አብርሃም በርከክ ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ጥቅምት 30 ቀን ሰጠ አባ ቴዎድሮስም ወደ መነኰሳቱ ላከ እነርሱም መጥተው ከሥጋው በረከትን ተቀበሉ ሥጋውንም ወሰደው ከቅዱሳን ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በባሕታዊ አባ አብርሃም ጸሎት ይማን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 30 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለአብርሃም ነዳይ። እምነ ጥሪት ማሳኒ ወእምኀላፊ ንዋይ። እንዘ ይሴፌ ረከበ መንግሥተ ሰማይ። ይከድን ሥጋሁ በጻርቅ ብሉይ። ወሕፈነ አተር ይሴሰይ ዘርሑሱ በማይ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 30። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

❤ ሌሊት ሲሆንም ይገድሉት ዘንድ እስከሚሰበሰቡ ድረስ ወደ እስር ቤት አስገቡት፡፡ መንፈቀ ሌሊት ሲሆንም በሮች ተዘግተው ጠባቂዎችም ተኝተው ሳሉ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ የእግዚአብሔር መልአክም "የግብጽን አገራት ሁሉ የምታረጋጋ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማርቆስ ሆይ ስምህ በሰማይ ባለ የሕይወት መጽሐፍ ተጽፏል ከሐዋርያት ቁጥርም ተቆጥሮአል፤ መታሰቢያህም አይረሳም፤ በምድርም ስፍር ቁጥር የሌላትን ሥልጣን፣ ጸጋ ኃይል እነሆ ሰጥቶሃልና፤ ነፍስህ በሰማይ ይሆናል ሥጋህም በመሬት አይጠፋም" አለው፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ይህን ምሳሌ በተመለከተ ጊዜ እጆቹን ወደ ሰማይ አነሣ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከፊትህ አልጣልኸኝም፣ ከቅዱሳን ማኀበርም ደምረኸኛልና አመሰግንሃለሁ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እለምንሃለሁ ነፍሴን በሰማይ ተቀበላት፤ ከፊትህም አትተወኝ" አለ፡፡ ይህን በተናገረ ጊዜ ጌታችን አዳኝ ከሆነው ከሕማሙ በፊት በመቃብርም ከመጨመሩ አስቀድሞ በሐዋርያት መካከል እንደነበረ ሆኖ ታየው፡፡ "የመረጥሁህ ማርቆስ ሆየ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሁን፤ በወንጌል አስተማርሁህ፤ እነሆም መከራን ከመቀበሌ አስቀድሞ ከጓደኞችህ ከሐዋርያት ጋር አንደሆንሁት በአርአያ ተገለጥኩልህ፤ ከእነርሱ ምንም ጉድለት እንዳይኖርብህ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከጸጋህ ታላቅነት የተነሣ አመሰግንሃለሁ፤ በሥጋህ አንደነበርህ ሁነህ አንዳይህ የተገባኝ አድርገኸኛልና" አለው "ስለተቀደሰው ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ ትዕግሥትን አድለኸኛልና" ጌታችንም ሰላምን ሰጠውና በታላቅ ምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ሲነገም የአገሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከእስር ቤትም አወጡት በሰንሰለትም አሰሩት፤ ዳግመኛም በላሞች ቦታ እንደፍየል እንጐትተው እያሉ በከተማው ጐተቱት፡፡ ❤ ብፁዕ ማርቆስም ምስጋናን አቀረበ በሰማይ ተገለጠ፡፡ በየአገሩ ከጎተቱት በኋላም ደሙ በየመንገዱና በየአደባባይዋ ሞላ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን በእጅህ ሰጠሁ" አለ፡፡ ይህን ከተናገረ በኋላም ዐረፈ፡፡ ሁሉም አረማውያን ቅዱስ ማርቆስ አንዳረፈ በተመለከቱ ጊዜም ሥጋውን በእሳት ያቃጥሉት ዘንድ አውበካልዮን በምትባል ቦታ ጽኑ እሳትን አነደዱ፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድም ጨለማና ቀዝቃዛ ነፋስ ሆነ፤ ፀሐይም ብርሃኑን ሰወረ፡፡ በዚች ዕለትም እስከ ምሽት ድረስ መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ ዝናምና ብርድም ሆነ፤ ከአገሩ ሰዎች ከሽማግሌዎች ብዙዎች ወደቁ ከእነርሱም ብዙዎቹ ሞቱ ያን ጊዜ ፈሩ ሂደወም ከአገሩ ሰዎች የቅዱሱን ሥጋ አኖሩት፤ የተዘባበቱበትም አሉ "ታላቁ አምላክ ሆይ የዚህን ሰው ነፍስ ተቀበላት በዚች ዕለት የልደቱ ዕለት ናትና" አሉ፡፡ ምዕመናን ወንዶች ደረሱና የቅዱሱን ሥጋ ከእሳቱ ወሰዱት ጸሎት ወደሚጸለይበት ቦተም አደረሱት በእርሱ ላይም ተሳሉ፣ ምስጋናንም አቀረቡ እንደ ሥርዓታቸውም እንደ አገሩ ሰዎች ገነዙት በቆፈሩለት መቃብርም ቀበሩት፡፡ መታሰቢያውንም በደስታ፣ በምሥጋና አብዝተው አደረጉ፣ አበዙ በአገሩ መሠረታዊ ቦታም አስቀመጡት፡፡ ❤ የሰማዕታት መጀመሪያ በግብጽ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰ የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ ዕረፍቱ በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሠላሳኛው ቀን ዕለቱመ ሰኞ ጠዋት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በተገለጸ 68 ዓ.ም ወደ ሰማይ ባረገ በ35 ዓ.ም በታላቋ አገር በእስክንድርያ ሆነ ፡፡ ከሐዋርያውና ከወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፡፡ በጸሎቱ ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ ገድለ ሐዋርያት ፤ ስንክሳር ፤ ክብረ ቅዱስ ማርቆስ ከሚለው መጽሐፍ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወተጽእልኩ በኀበ ኵሎሙ ጸላእትየ። ወፈድፍደሰ በኀበ ጎርየ። ግሩም ኮንክዎሙ ለአዝማድየ"። መዝ30፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 11፥1-7። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ናሁ ይእዜ አልዐለ እግዚአብሔር ርእስየ ዲበ ጸላእትየ። ዖድኩ ወሦዕኩ ውስተ ደብተራሁ መሥዋዕተ። ወየበብኩ ሎቱ"። መዝ 26፥6። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 4፥11-ፍ.ም፣ ያቆ 1፥2-6 እና የሐዋ ሥራ 10፥36-43። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ማርቆስ የልደት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ቅዱስ ማርቆስ በኢየሩሳሌም የእናቱ የማርያም ቤት የደቀ መዛሙርቱ መገናኛና መሰባሰቢያ ስለነበር ደቀመዛሙርቱን የበለጠ እንዲያውቃቸውና እንዲቀርባቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማድረጉም በላየ በተለይም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ባለው የጠበቀ ዝምድናና ቀረቤታ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሃይማኖት ልጅ በመሆንና ለአገለግሎቱም ፍጹም መንፈሳዊና እውነተኛ የክርስቶስ ምስክር ለመሆን በቅቷል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በልጅነቱ በኢየሩሳሌም ለመኖር በመታደሉ በዚያም ዘመን ይሰጥ የነበረውን ትምህርት የማግኘት ዕድል ገጥሞት ነበርና የዕብራይስጥ፣ የላቲንና የግሪክ ቋንቋዎችን ያውቅ ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌልን መስበክ የጀመረው ገና በወጣትነቱ ነበር በመጀመሪያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብሮ ያስተምር ነበር፡፡ በግብረ ሐዋርያት አንደተገለጸው ቅዱስ ማርቆስ ከቅድስ ጳውሎስና ከቅድስ በርናባስ ጋር ይሰበክ ነበር፡፡ ከዚያም በፊት ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ አስተምሮአል፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ ንጹሕና ድንግል መሆኑን መልካምነቱንና ትምህርቱን ተመልክቶ ቅዱስ ጴጥሮስ ለግብጽና ለአካባቢዋ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አድርጎ ሾመው፡፡ በግብጽ አገሮች በሎኒያ፣ በመርቅያ፣ በጣውንቄ፣ በበርቃ ለመጀመሪያ አስተማረ እርሱ ነው፡፡ ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ አዳኝ በሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንንም አስተማራቸው፡፡ ሁሉም የዚያች አገር ሰዎች ልቡናቸው የደነደነ ነበሩ በርኵሰት ሁሉ የተሞሉ አማልክትንም ያመልኩ ነበር፡፡ ሰይጣንን በማምለክም ይኖሩ ነበር፡፡ በየቦታው በየመንገዱም ሁሉ ምኩራቦችን የአማልክትን ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ መድኃኒትን፣ ዝሙትንም ያደርጉ ሕጻናትን ይገድሉ በደማቸው መድኃኒትን ያደርጉ ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሐዋርያት በሄደ ጊዜ አስቀድሞ በርቃ ደረሰ፡፡ ዘመዶቹ ከእነርሱ ወገን ናቸውና፡፡ እግዚአብሔርን ቃልም አስተማራቸው በመካከላቸው ብዙ ተአምራትን አደረገ፤ በሽተኞችን ፈወሳቸው ለምጻሞችንም አነጻቸው፤ በእርሱ ላይ በአደረው ጸጋም አጋንንትን አስወጣ፤ ብዙዎችም በትምህርቱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ አምላኮቻቸውንም (ጣዖቶቻቸውንም) ሰባበሩ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምም አጠመቃቸው፡፡ ❤ በዚያ ቦታም ወደ እስክንድርያ ይሄድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ተገለጠለት፡፡ በዚያም መልካም ተዘራባት ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ወንጌላዊው ብፁዕ ቅዱስ ማርቆስም ለጦርነት እንደተዘጋጀ ጎልማሳ ሆነ "ወንድሞቹንም ሰላም" አላቸው "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ቦታ ቅዱስ ወንጌልን አስተምር ዘንድ ወደ እስክንድርያ እንድሄድ አዝዞኛል" አላቸው፡፡ እነርሱም ሸኙት በመርከብም ተሳፍሮ ወደ እስክንድርያ ሄደ በደረሰ ጊዜም ወደ ከተማው በር ገባ የጫማው ማሠሪያም ተቆረጠ በቅንነትም መንገድ ፈጠነች አለ በዚያም ከከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበር፡፡ ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዩናኒም ቋንቋ "ኢታስታያስ" አለ ትርጓሜው አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን" አለው "እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም" አለ፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በጣቶቹ ላይ መራቅ ጨመረና አፈር ወሰደ ያን ጫማ ሰፊ ቀባው "በሕያው አግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ስም አጅህ ትፈወስ" አለው፡፡ ስለዚህም ተፈወሰች ጫማ ሰፊውም በሥልጣኑ በቃሉ ያደረገውን ድንቅ ተአምር በተመለከተ ጊዜ "የቸሩ አምላክ አገልጋይ ሆይ እለምንሃለሁ ዛሬ ውጣና በቤቴ እረፍ በአንድነትም እንመገብ መልካም ነገርን አድርገህልኛልና" አለው፡፡ ❤ ብፁዕ ቅዱስ ማርቆስም ተደሰተ፡፡ "እግዚአብሔር ሰማያዊት የምትሆን ሕይወት ኀብስትን ይስጥህም" አለው፡፡ ጫማ ሰፊውም ሐዋርያውም እየተደሰተ ወደ ቤቱ አስገባው፡፡ ሐዋርያውም እየተደሰተ ወደ ቤቱ ገባለት። "የእግዚአብሔር በረከት በዚህ ቤት ይኑር" አለ፡፡ ወንድሞች በአንድነት ጸለዩ ከጸሎት በኋላም ተቀመጡና ደስ እያላቸው ተመገቡ፡፡ ጫማ ሰፊውም ቅዱስ ማርቆስን "አባት ሆይ እለምንሃለሁ ይህንን የምትለው እንዴት ነው፤ ይህ ስምስ ምንድን ነው ይህ እንደዚህ የሚቻለው ነው" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "እኔ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ" አለው፡፡ ጫማ ሰፊውም "እኔ ላየው እሻለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "እኔ አሳይሃለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ ነው" እያለ የወንጌሉን መጀመሪያ አስተማረው፡፡ በትንቢት ስለ እርሱ የተናገሩትንም ከመጻሕፍት ተናገረ፡፡ ጫማ ሰፊውም "እኔ የምትለውን ይህን መጽሐፍ እለምንሃለሁ ከረጅም ዘመን ጀምሮ የግብጻውያን ልጆች እንደማይማሩበት አልሰማህምን" አለው ቅዱስ ማርቆስ እንዲህ በማለት የእግዚአብሔርን ነገር ይነግረው ዘንድ አስቀደመ "የዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ናት" አለው ጫማ ሰፊውም የቅዱስን ነገር በሰማ ጊዜ በእግዚአብሔር አመነ ለእርሱም አመለከተው ከእርሱም ኃይላትን ተአምራትን አየ እርሱ ቤተሰቡ፣ ከአገሩ ሰዎችም ብዙዎቹ ተጠመቁ፡፡ የጫማ ሰፊው ስምም አንያኖስ ይባላል፡፡ ያን ጊዜም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምዕመናን በዙ፡፡ የአገሩ ሰዎች በሰሙ ጊዜም "ይህ የገሊላ ሰው ከዚህ አገር ደርሷል፤ የአማልክትን እጅ መንሻ ለውጧል፤ እንዳይመለኩ ከልክሏል" አሉ ሊገሉትም ፈለጉት ይጥሉት ዘንድም በእርሱ ላይ ፍለጋን አበዙ ብፁዕ ማርቆስ ይህን በተረዳ ጊዜ አስተማራቸውና አንኖስንም ኤጲስ ቆጾስነት ሾመላቸው ሦስት ካህናትንም ሾመላቸው ስማቸውም ወልዮስ፣ መሪደስና በሪሞስ ይባላል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮም ሰባት ዲያቆናትን አንድ ላይ አሥራ አንድ ሰዎችን ሾመላቸው፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ብርቃ ወጣ ለዓመታትም በእርሷ ተቀመጠ፡፡ በሁሉም አገራት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትን ሾሞላቸው ወደ እስክንድርያም ተመለሰ፡፡ በእግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ጸጋና ማመን በዛባት የላም ቦታ በሚባለው በባሕሩ ዳር ካለው ቦታም ቤተ ክርስቲያን ሠሩ ከዚያ ቦታ ከዓለቱ ሥርም ታላቅ ድንጋይ ቁራጭ ነበር፡፡ ጻድቁም ስለ ምዕመናን መልካም ሃይማኖት እግዚአብሔርን አመሰገነ ብዙ ዘመን በቆየ ጊዜም ክርስቲያኖች በዙ አማልክትንም ተዘባበቱባቸው፤ አረማውያንንም ናቋቸው፡፡ አረማውያንም ቅዱስ ማርቆስ እንደሆነ ወደ አገራቸው እንደደረሰ ተረዱ፡፡ ከሰሙት ተአምራት ብዛት የተነሳ ልቡናቸው በቁጣ ተሞላ እርሱ ሕመምተኞችን ይፈውስ፣ ለምጻሞችንም ያነጻ፣ ደንቆሮዎችንም እንዲሰሙ፣ እውራንንም እንዲያዩ ያደርጋል መልካም ተስፋንም ያስተምራቸው ነበር ይይዙት ዘንድም ፈለጉት፤ በየቤታቸውም ጥርሳቸውን ያፋጩ ነበር፤ በአማልክቱ ምኵራብም "እኛ ለዚህ ጠንቋይ ተሸነፍን" እያሉ ጮኹ፡፡ ምዕመናን የሚያከብሩት ዕለት ሰንበት የተባረከው የፋሲካ በዓልም በሰንበት ቀን ሆነ፤ ይህም ዕለት ሚያዝያ 17 ቀን ነው፡፡ ❤ በዚያች ዕለትም በእነርሱ ዘንድ የሰራቢስ የልደቱ ቀን ነበር፡፡ ያማረች ዕለትን አገኙ ሰላዮችን ላኩና ያዙት፡፡ እርሱን የቅዳሴ ጸሎት ሳይፈጽምም በሰንሰለት አሠሩት በላሞች ቦታ እንጐትተው እያሉም እንደ አውራ ፍየል በየመንገዱ ጐተቱት፡፡ ቅዱስ ማርቆስም በጐተቱት ጊዜ አግዚአብሔርን አመሰገነው፡፡ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በተቀደሰው ስምህ መከራን እንድቀበለ አዘጋጅተኸኛልና አመሰግንሃለሁ” አለ፡፡ ሥጋውም በየመሬቱ ተቆራረጠ ደሙም በየዐለቱ ፈሰሰ፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነ በእስክንድርያ (በግብፅ) ያለቱ አምልኮ ጣኦታት (ላሕም) ላጠፍ ወንጌልን ለሰበከ ለወንጌላዊው ለሐዋርያው ለቅዱስ ማርቆስ ለልደቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ሐዋርያው ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ፦ የቅዱስ ማርቆስ ወላጆች ስም የአባቱ ስም ቅዱስ አርሰጡጳውሎስ ሲሆን የእናቱ ስም ቅድስት ማርያም ይባላል፡፡ አባቱ ባለፀጋና ያላገባ ነበር የአባቱ ስም ስምዖን ይባል ነበር፡፡ ስምዖንም አርስጡጳውሎስን እንዲያገባ ይገፋፋው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ በቤቷ እንግዶችን የምትቀበልና የምታስተናግድ ማርያም የተባለችውን የወንጌላዊ የቅዱስ ማርቆስ እናት አገኘ፡፡ እሱም እሷመ ሳያስቡት ባዩት ሕልምና በመፈክራነ ሕልም (በሕልም ፈቺዎች) በተነገራቸው መሠረት ተገናኝተው የትዳር ሕይወትን መሠረቱ፡፡ ❤ አርስጡጳውሎስ ከከበረውና በባለጸግነቱ ከታወቀው ከአባቱ ካገኘው ሀብት ለነዳያን የሚመጸውት፣ ዐሥራት በኩራት የሚያወጣና ወደ እግዚአብሔርም ዘወትር የሚጸልይ ደግ አባት ነበር፡፡ እሱም የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ዘመድ የአክስት ልጅ እንደሆነና ቅዱስ ጳውሎስም በመልአክቱ የጠቀሰው እሱን እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ "አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ የበርናባስም የወንድሙ ልጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" ቈላስይስ 4፥10 ነገር ግን አንዳንድ የግሪክ፣ የላቲን፣ የግእዝና የኮኘት ትርጉሞች "የበርናባስ የወንድሙ ልጅ" የሚለውን ሐረግ አይጠቅሱም ይህም ምንአልባት አንዳንድ የግሪክ ቃላት ከአንድ በላይ ትርጉም ስላላቸው ይሆናል፡፡ ❤ የቅዱስ ማርቆስ እናት ማርያም ተብለው ከተጠሩት ብዙ ቅዱሳት አንስት መካከል አንዷ ናት፡፡ ቤቷ በኢየሩሳሌም እንደነበረና ምዕመናንም በቤቷ በጸሎት ይሰበሰቡ እንደነበር በሐዋ 12-12-17 በሰፊው ተገልጾአል፡፡ ይህም በጥንት ወይም በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ካሉት መንፈሳውያኑ ሴቶች (ቅዱሳት አንስት) ከፈተኛ ቦታ ያላት እንደነበር ያመለክታል። በዚያን ጊዜ የነበሩ ምዕመናን በአንድነት በክርስቶስ ስም ይሰባሰቡ ስለነበር ክርስቲያን የሚለውን ስም ያገኙትም በዚሁ ወቅት ነበር፡፡ "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፤ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ"፡፡ ሐዋ ሥራ 11፥26 ❤ የቅዱስ ማርቆስ እናት የማርያም ቤት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ለጸሎት የሚሰበሰቡበት ነበር፡፡ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት በጽርሐ ጽዮን ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ እንደተገለጸላቸውና መንፈስ ቅዱስን እንደላከላቸው በቅዳሴ ዲዮስቆሮስ እንዲህ ተጽፏል "አመ ሣልስት ዕለት ተንሥአ እሙታን ወቦአ ኀበ ሀለው አርዳኢሁ ጉቡአን ወአስተርእዮሙ በጽርሐ ጽዮን … ወበ ፶ ዕለት ፈነወሎሙ መንፈሰ ቅዱስ ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኩሉ በሐውርት … በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ የተሰበሰቡ ደቀ መዛሙርት ባሉበት ገባ በጽርሐ ጽዮንም ታያቸው …በ50ኛው ቀንም በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስን ሰደደላቸው በአገሩ ቋንቋ ሁሉ ተናገሩ" ❤ በኢየሩሳሌም ውስጥ የማርያም ቤት የሐዋርያት መገናኛና መሰባሰቢያ ነበር፡፡ ስለዚህም የማርቆስ እናት የማርያም ቤት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ኀብረት መለያ ሆኖ ይታወቃል፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ የተወለደው በአባቱ ወገን ከነገደ ይሁዳ ሲሆን የተወለደበት ቦታ ከአምስቱ የምዕራብ ከተሞች አንዷ በሆነችው በሊቢያ በሲርኔ ይኸውም አብራይሮሎስ በተባለች ትንሽ መንደር ተወለደ፡፡ ትውልዱ ዕብራዊ ቤተሰቦቹም ይኖሩበት የነበረው በሰሜን አፍሪካ በጥንታዊቱ ፔንዲፓሊስ ሲሪኒካ (ቀሪና) በተባለችው በዛሬው ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ከተማ ስለነበር ቅዱስ ማርቆስ አፍሪካዊ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሉሌ መላኩ ቤተክርስቲያንህን እወቅ። ❤ ቅዱስ ማርቆስ ሰኔ 3 ቀን በዕለተ ረቡዕ ተጸንሶ መጋቢት 3 ቀን በዕለተ ዐርብ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ተወለደ፡፡ ነገር ግን በዓለ ልደቱ የሚከበረው መጋቢት ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል የሚከበረው ጥቅምት 30 ቀን ነው። ❤ የቅዱስ ማርቆስ የስሙ ትርጓሜ ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው ንብ ከሁሉ እንዲቀስም አስቀድሞ ከክርስቶስ በኋላም ከሐዋርያት ተምሮአልና፡፡ ❤ አንድም አንበሳ ማለት ነው አንበሳ ለላሕም ጌታው እንደሆነ እንዲሰብረው እርሱም አምልኮተ ላሕምን ከግብጽ አጥፍቷልና፡፡ ❤ አንድም ካህን ልዑክ ማለት ነው፡፡ ብሥራተ ማሪ ማርቆስ ይላል የተደራረበ ቀለም ነው፡፡ ሁሉም ካህን ማለት ነው፡፡ እመልአክተ ሲኖዲቆስ ባለ ጊዜ መልእክትም ሲኖዲቆስም ክታብ ማለት እንደሆነ ….። ❤ የቅዱስ ማርቆስ ሁለተኛ ስሙ ዮሐንስ ይባላል። "ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለ ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ" ሐዋ12፥12 ❤ የቅዱስ ማርቆስ ተክለ ቁመናና መልክ እንዲሁም አለባበሱን እንዲህ በማለት ተጠቅሷል፡፡ "የግብጽና የኢትዮጵያ ኮከብ ብፁዕና ቅዱስ ማርቆስ መልኩ ቀይ ቅንድቦቹም ከበድ ያሉ ዓይኖቹም እንደሰማያዊ ኀብር የጠሩ ቁመቱ ረጅም ከአንገቱም ስር ስርጉድ የሆነ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ ራሰ በራህ የሆነ ቀሚስ (ልባልባውም) በወገቡ የሆነ የግብጽና የኢትዮጵያ አባት የቅዱስ ማርቆስ ምልክቱ ይኸ ነበር፡፡ ❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዊ በሚሰብክበት ጊዜ ቅዱስ ማርቆስ ወጣት ነበር፡፡ ልቦናው የቀና እንደሆነም አውቆ ከሰባ ሁለቱ አርድእት በፊት የመጀመሪያ አድርጐ መረጠው ከዚህ በኋላ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆኖ ጌታ ወንጌልን ሲያስተምር፤ ተአምራት ሲያደርግ ያስተውል ነበር ፡፡ በምሴተ ሐሙስ በአይሁድ ሲያዝና መከራን ሲቀበል ቅዱስ ማርቆስ በኢየሩሳሌም መንገድ ላየ ሆኖ በርቀት ድርጊቱን ይከታተለ ነበር፡፡ በወንጌሉም እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ አርሱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ "ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጐበዝ ይከተለው ነበር ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ"፡፡ ማር 14፥51-52 ❤ ቅዱስ ማርቆስ በቤቱ መጻፊያ ይዞ የጌታን ተአምራት ይጽፍ ነበር፡፡ የግሞ ሊናሮስ የሚባል አገልጋዩን ጌታን እንዲከተልና የሚያደርገውንም ተአምራት እንዲጽፍ ያደርግ ነበር ፡፡ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን ሲያከብር ተከተሉት" የተባለውም ቅዱስ ማርቆስን እንደሆነ እንዲህ ተጽፍል፤ "ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እነዲህም አላቸው ወደ ከተማ ሂዱ ማድሃ ውሃ የተሸከመ ሰውም ያገኛችኋል ተከተሉት የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ መምህሩ፣ ከደቀመዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው ይላል በሉት፡፡ እርሱም በደርብ ላይ ያለውነ የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፣ በዚህም አሰናዱልን፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ ፋሲካም አሰናዱ" ማር 14፥13-15፤ ሉቃ 22፥10-12።

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 2:1-8 "ወኮነ በውእቱ መዋዕል" - "በዚያም፡ወራት፡ዓለሙ፡ሁሉ፡እንዲጻፍ፡ከአውግስጦስ፡ቄሳር፡ትእዛዝ፡ወጣች። ቄሬኔዎስ፡በሶርያ፡አገር፡ገዢ፡በነበረ፡ጊዜ፡ይህ፡የመጀመሪያ፡ጽሕፈት፡ሆነ። ሁሉም፡እያንዳንዱ፡ይጻፍ፡ዘንድ፡ወደ፡ከተማው፡ሄደ። ዮሴፍም፡ደግሞ፡ከዳዊት፡ቤትና፡ወገን፡ስለ፡ነበረ፡ከገሊላ፡ከናዝሬት፡ከተማ፡ተነሥቶ፡ቤተ፡ልሔም፡ወደምትባል፡ወደዳዊት፡ከተማ፡ወደ፡ይሁዳ፥ፀንሳ፡ከነበረች፡ከዕጮኛው፡ከማርያም፡ጋራ፡ይጻፍ፡ዘንድ፡ወጣ። በዚያም፡ሳሉ፡የመውለጃዋ፡ወራት፡ደረሰ፥የበኵር፡ልጇንም፡ወለደች፥በመጠቅለያም፡ጠቀለለችው፤በእንግዳዎችም፡ማደሪያ፡ስፍራ፡ስላልነበራቸው፡በግርግም፡አስተኛችው። በዚያም፡ምድር፡መንጋቸውን፡በሌሊት፡ሲጠብቁ፡በሜዳ፡ያደሩ፡እረኛዎች፡ነበሩ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.28 KB

29/2/2015 ዓ.ም (፳፱/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል። በብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ፡፡ መዝ. 109፥3 🕯 ትርጉም ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን። በቅዱሳን ብርሃን። ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content
+1

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን በከሀዲው በመክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ ለቅድስ ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደበት ከልደቱ (ከበዓለ ወልድ) ወራዊ በዓል መታሰቢያ፣ ከድሜጥሮስ ወዳጅ ከሰማዕቱ ስቅጣር ዐረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከተሰሎቄ አገር ነው የከበረች የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ በቀናች ሃይማኖት ጸና ሕዝብንም የሚያስተምር ሆነ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በመስበክ ብዙዎቹን ከስህተት መለሳቸው። ስዚህም በከሀዲው ንጉሥ ዘንድ መነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ እንዲያወጡት አዘዘ በንጉሡም ዘንድ አንድ ሥጋው የደነደነ የጸና አጥንቱ የሠፋ ሰው ነበር ለሰዎችም ሁሉ እርሱ ሁሉንም የሚያሸንፍ እርሱን የሚያሸንፈው የሌለ ይመስላቸው ነበር ንጉሡም ይወደዋል ይመካበታል እንዲህም ይል ነበር "ይህን አካሉ ግዙፋ የሆነ ሰው የሚያሸንፍ ብዙ ገንዘብ እሰጠዋለሁ"። ❤ በዚያን ጊዜ ስሙ በስጥዮስ የሚባል አንድ ክርስቲያናዊ ሰው ተነሥቶ ወደ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሆደ እንዲጸልይለትና በስጋውም ሁሉ አሸናፊ በሆነ በመስቀል ምልክት እንዲያማትብበት ለመነው እርሱም በላዩ ጸለየለት በሥጋው ሁሉ ላይ በመስቀል አማተበበት ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ገብቶ ከዚያ ሥጋው ግዙፋ ከሆነው ጋር ያታግለው ዘንድ ለመነው ንጉሡም ፈቀደለት በታገሉም ጊዜ ሥጋው የደነደነውን ያ ክርስቲያናዊ ሰው አሸንፊ ጣለው ንጉሡም አዘነ አደነቀም ሥጋው የደነደነውም በመሸነፉ አፈረ ተመክቶበት ነበርና። ንጉሡም ስለዚህ ነገር ወታደሮቹን ጠየቀ እነርሱም ቅዱስ ድሜጥሮስ በላዩ እንደጸለየለትና በሥጋው ላይ በመስቀል ምልክት እንዳማተበበት ነገሩት። ❤ ንጉሡም ይህ በሰማ ጊዜ በቅዱስ ድሜጥሮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ለአማልክትም እጣን እስከማያሳርግ ድረስ እንዲገርፉት አዘዘ ንጉሡም እዳዘዘ እንዲሁ አደረጉበት የንጉሡንም ትዕዛዝ ባልሰማ ጊዜ እስከሚሞት በጦሮቹ እንዲወጉት ሁለተኛ አዘዘ። ❤ ለቅዱስ ድሜጥሮስም ይህ ፍርድ ነገሩት ሃይማኖቱን ትቶ ለአማልክት የሚሰግድ መስሏቸው ነበርና ቅዱስ ድሜጥሮስም "እኔ ከእውነተኛ አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት እሰግድ ዘንድ እጣን ማሳረግም አድቅድም የወደዳችሁትን አድርጉ" አላቸው። በዚያን ጊዜ ንጽሕት ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ እስከሚሰጥ በጦር ወጉት ሥጋውንም በጣሉት ጊዜ ምዕመናን ወደእርሳቸው ወሰዱት የስደቱም ወራት እስከሚያልፍ በሳጥን አድርገው በቤታቸው ውስጥ ሰውረው አኖሩት። ❤ የስደቱም ወራት ከአለፈ በኋላ እግዚአብሔር ገለጠውና ከዛ አወጡት ያማረች ቤተ ክርስቲያንንም በተሰሎንቄ አገር ሰሩለት ሥጋውም በውጧ አኖሩ ድንቅ የሆነ ታላቅ ተአምርን እያደረገ እስከ ዛሬ አለ ሽታው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከእርሱ ይፈሳልና በእምነት የሚቀቡትን በሽተኞች ሁሉንም ያድናችዋል። ይልቁንም በዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ጥቅምት 29 ከሌሎቹ ዕለታት ተለይቶ በብዙ ይፈሳል ከአውራጃ ሁሉ ብዙዎች ሰዎችም ይመጣሉ ከዚህም ቅባት ወስደው በማሰሮቻቸው ያደርጋሉ ይች ምልክትም እስከ ዓለም ፍጻሜ በመኖ እንደምትገኝ ደጋጎች ካህናት ምስክሮች ሆኑ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በሰማዕቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 29 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ድሜጥሮስ ሰማዕት። ርጉዘ ገቦ በኵናት። እስእለከ ኅፅረኒ በጽጌ ቅድሳት። ኢያማዕርር ጒርዔየ ጸቃውዐ ዘማ ኅስርት። ፈዳዬ መጥባሕት ስሑል ወመሪር ሞት"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 29። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ 109፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወታቀንተኒ ኃይለ በጸብእ። ወአዕቀጽኮሙ ለኵሎሙ እለ ቆሙ ላዕሌየ በመትሕቴየ"። መዝ 17፥39-40። የሚነበቡት መልክዕታት 2ኛ ቆሮ 7፥1-10፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-12 እና የሐዋ ሥራ 9፥20-23። የሚበበው ወንጌል 8፥1-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ታዴዎስ የተአምራት በዓልና መልካም የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content
+2