fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ለቅድስት ሥላሴ ወደ አብርሃም ቤት ለገቡበት የይስሐቅን መወለድ ለአበሰሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳስ ለሐዋርያው ለቅዱስ አግናጥዮ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍት በዓልና ለባሕታውያን አለቃ ለሆነ ለመስተጋድል አባ ሲኖዳ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ከአባ መቃቢስ፣ ከአግራጥም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገሪጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "እምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም መዘምርኒሃ ለደብ ብርሃን አያርም እንዘ ብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለኅሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ። እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ። ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ። ሠለስተ እደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ሐይምት ርእየ። ወለአሐዱ ነገሮ ረሰየ"። ትርጉም፦ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በበጎ ሃሳቡጰበቸርነቱ ለሚታወቀው ኅሊናችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከከላውዴዎን ይልቅ የካራንን ምድር የመረጠ አብርሃም የሦስትነታችሁን ትክክለኛ ሦስትነት ከተረዳ በኋላ ከድንኳኑ በስተምሥራቅ ወይም ባሻግር ሦስት ሰዎች አየ ተመለከተ፡፡ ከሦስቱ አንዱም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀበለ። መልክአ ቅድስት ሥላሴ። + + + ❤ በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት (አጋዝእተ ዓለም ሥላሴ) በኦሪት መጽሐፍ እንደተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገብ ያቀረበላቸውን ተመገቡ የይስሐቅንም ልደት አሠሰሩት ባረኩት አከበሩትም። ለእግዚአብሔር ይስጋና ይሁን በአባታችን በቅዱስ አብርሃም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ታሪኩን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 18 ላይ ያንብቡ። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ሲኖዳ ዘፍጹም በምንከኵስናሁ ዲበ ሥጋሁ ዘለብሰ ጻማሁ"። ትርጉም፦ በሥጋው ላይ መከራን የተጎናጠፈ በምንኵስናው ፍጹም ለኾነ ለአባ ሲኖዳ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል አባ ሲኖዳ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት። ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት "ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ"። ❤ እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው "አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ" አሉት። "ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ" አላቸው። ❤ አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው "እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት። ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት" አለ። ❤ በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር። አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ "ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና" አለው። አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው። ❤ ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ "እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ"። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ። ❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው "እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እግዚአብሔር አዝዞሃል"። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው። ❤ ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ። ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት። ❤ ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። "አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን" ብሎ ሰላምታ አቀረበ። በመርከብ ያሉት ሁሉም "ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን" አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ያህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ። ❤ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው "ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን?"። ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት "ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን?። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ" ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ። ❤ በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ + + + ❤ "ሰላም ለዕዝራ ነቢይ ዘከብዶ እንግድዓሁ ልቡና ወዘአእመረ ምስጢሮ ለእግዚአብሔር ወርእየ ሀገሮ ቅድስተ፤ ወኀብኦ ብሔረ ሕይወት ምስለ እለ ከማሁ"። ትርጉም፦ እንደርሱ ካሉ ሰዎች ጋራ በብሔረ ሕያዋን የሰወረውና ቅድስት ሀገሩንም ያየ የእግዚአብሔንም ምስጢር ያወቀ፤ ትንቢታዊ ዕውቀት ልቦናውን የመላው ለኾነ ለነቢዩ ዕዝራ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ጳውሎስ ለተባለው ለቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ለቅዱስ መርቄሎስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና አሰቀድማ ኃጢያተኛ ለነበረች በንስሐ ከተመለሰች በኋላ ብዙ ለተጋደለች ለኢየሩሳሌም ሰዎች ለሆነች ለቅድስት ንስተሮኒን ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚተረሰቡ፦ ከሐዋርያው ከበርተሎሜዎስ፣ ከአንድ ሽህ ሰማዕታትና ከማርቆስ ዘጠነኝ ከሚሆን ከሊቀ ጳጳሳት ከላድያኑ ከመታሰቢያቸው፣ በሰማዕትነት ከዐረፈች ከቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት ከገድለኛዋ ከቅድስት ቴዎዳስያ፣ ከርሷ ጋርም ሰማዕት ከሆኑ ከሁለት መኳንንቶችና ከዐሥራ ሁለት ሴቶች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ጳውሎስ የተባለ ቅዱስ መርቄሎስ፦ ይህም ከባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ ነው። እርሱም ሐዋርያትን አገልግሎአቸዋል ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር ሔደ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን መልእክቶች አደረሰ በመከራውም ጊዜ አገለገለው ከእርሱም ጋር መከራ ተቀበለ ከእርሱም አልተለየም። ወደ ሮሜ አገርም ከርሱ ጋር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን አስተማረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ከአረማውያን ብዙዎቹን መለሳቸው። ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው። ❤ የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ አቅርቦ ጠየቀው እርሱም ለሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ አመኑ ደግሞም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ። ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ "እንዴት ሁነህ መሞት ትሻለህ በምን አይነት ሞት ልግደልህ ንገረኝ" አለው። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰ "እኔ ሕይወት በሆነ በክርስቶስ ስም መሞት እሻለሁ አንተ ግን በፈለግኸው ዓይነት ግደለኝ ፈጥነህም ወደ ፈለግኸው አድርሰኝ"። ❤ ያን ጊዜም ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሐምሌ 6 ቀን እንዲሁም አደረጉበት። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅድስት ንስትሮኒን፦ እርሷም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ውስጥ ነበረች። አስቀድማ ኃጢአተኛ ነበረች ከዚያም በኋላ ንስሓ ገብታ ወደ እግዚአብሔር በተቃጠለ ልብ ተመለሰች የሥጋን ፍላጎቶች ሁሉ ናቀች እመምኔት እስከሆነች ድረስ በበጎ ሥራ ሁሉ ትሩፋትንና ተጋድሎን አበዛች። ❤ እኅቶችም ከገድል ብዛትና ምግብን ከመተው የተነሣ ሥጋዋ እንዳለቀ አይተው "ሥጋሽን እንድተረጂ ጥቂት እህል በወጥ ብዪ" አሏት። አብዝተውም ግድ ባሏት ጊዜ "ልጆቼ ሆይ ወደ ቀድሞ ልማዴ እንዳልመለስ ጥቂት ወጥ ስለ መብላት አትድከሙ ስለዚህ ወጥ አልበላም አለቻቸው"። ከዚህ በኋላ ሐምሌ 6 ቀን በሰላም ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ንስትሮኒን በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የቅድስ አብሮኮሮንዮስ እናት ገድለኛዋ ቴዎዳስያ ከእርሷ ጋርም በሰማዕትነት ያዐረፉ ሁለቱ መኳንቶችና አሥራ ሁለት ሴቶች፦ ይህም እንዲህ ነው ይቺ ቅድስት ልጇ አብሮኮሮንዮስን "ክርስቲያን ነው" ብለው እንደወነጀሉትና ለሞት እስቲደርስ ጽኑዕ ሥቃይን እንዳሠቃዩት ሰማች። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያች ሌሊት ተገለጠለት ከሥቃዩም አዳነው ያለ ምንም ጉዳት ጤናማ ሆነ። ❤ እሊህ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች ከእናቱ ጋር በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ እንዲህ ብለውም ጮኹ "እኛ በአብሮኮሮንዮስ አምላክ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማትም የክብር አክሊልን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእኒህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 6 ሰንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለመርቄሎስ ጳውሎስሃ ዘተሰመየ። እንተ ገነዞ ለጴጥሮስ ግንዘተ ሠናየ። ሶበ መኰንን ይቤሎ እመ ትፈርህ ሥቃየ። ንግረኒ ዘትፈቅድ መዊተ አየ። ይቤሎ በዘተፈቅድ ትቀትለኒ ኪያየ"። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 6። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

📌 ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ❗ ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ ውዳሴ ማርያም የሐሙስ 👉 ታላቅ የንግስ
📌 ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ❗ ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ ውዳሴ ማርያም የሐሙስ 👉 ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስናየዓለም ብርሃንቅዱስ ጳውሎስ ሐምሌ 5 የእረፍት መታሰቢያ በዓልን ታስቦ ይውላል። ይህንን ታላቅ በዓል በሀዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ ስም በተሰየመው በጥንታዊው በነገስታቱ መናገሻ በሆነው በ ሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ( ኮልፌ አቡዬ )ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል። እርሶም ከወዳጆ ከዘመዶ ጋር በመምጣት ከቃልኪዳናቸው ይሳተፉ ዘንድ በአምላከ ጴጥሮስወ ጳውሎስ ስም ተጋብቻችኃል። አድራሻ ኮልፌ(ልኳንዳ) ፈጥኖ ደራሽ ካምፕ አጠገብ

❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ጴጥሮስ ወጳውሎስ 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ❣ ሥርዓተ ነግሥ:- ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCWW @EOTCWW ❣መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለቃልክሙ መታሬ እሳት ነዳዲ: ሥሉስ ቅዱስ ንዋያተ ዕፁብ ነጋዲ: አመ በንስሐ ተወልዱ እምጸጋክሙ ወላዲ: ተወፈየ መርኆ ሰማይ የማነ ጴጥሮስ ከሐዲ: ወመምህረ ወንጌል ኮነ ጳውሎስ ሰዳዲ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ጸጋ ዘአብ ኂሩት ዘወልድ: ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ: ተውህቦሙ ለሐዋርያት። @eotcw @eotcw ❣ነግሥ ሰላም ለመልክዕክሙ እመልክዐ አዳም ዘተቶስሐ: እግዚአብሔር መሐሪ ዘኮነክሙ መርሐ: ፲ወ፪ እለ ሰበክሙ ቃለ ንስሐ: ሥረዩ ኃጢአትየ ወጌጋይየ ብዙኀ: በእንተ ማርያም ድንግል በህሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ሐዋርያተ ሰላም ክቡራነ ስም: ሥረዩ ኃጢአተ ዓለም: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ድንግል እም። @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ለመቃብሪከ በመካነ ሐዋዝ ሃሌሉያ፡ወለትንሣኤከ ድኅረ ዘይከውን በዕለተ ምርያ፡ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሞተከ ታብዕል ኢትዮጵያ፡ለጴጥሮስ በዓለ መርኆ ወለጳውሎስ ሐዋርያ፡ከመ ተዝካሮሙ ታብዕል ሮምያ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ንግበር ተዝካሮሙ ለእለ ኃረዮሙ ዓጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘአልባስጥሮስ አፈው: ወለሥዕርትክሙ ጸሊም ዘድላሌሁ ፍትው: ምቱረ ክሣድ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ቅንው: ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስል መዓዛሁ ቅድው: ደመ ስምክሙ ሐዋርያ ዘኅብሩ ከዋው። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ሃሌ ሉያ: ከዋው እገሪሆሙ: ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ: ዘእግዚአብሔር ፈነዎ: ቃለ እግዚአብሔር ይነግር። @eotcw @eotcw ❣አመላለስ ሃሌ ሉያ/፪/ ከዋው እገሪሆሙ/፪/ @eotcw @eotcw ❣❣ወረብ ከዋው እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ ለእለ ይዜንዉ/፪/ ዘእግዚአብሔር ፈነዎ ይነግር ቃለ እግዚአብሔር/፪/ @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለአዕዛኒክሙ ለሰሚዓ ወንጌል ዘተሰብሐ: ወለመላትሒክሙ ቀይሐት እምነ ሮማን ዘቄሃ: መሥዋዕተ አምልኮት ኩኑ ወዘመሃይምናን ምክሐ: ደምከ ጴጥሮስ ወልደ ዮና በጽዋዓ መስቀል ተቀድሐ: ወደመ ጳውሎስ ሐዋርያ ሰማያተ ጸርሐ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም እንተ ትቀትሎሙ ለነቢያቲሃ: ወትዌግሮሙ ለሐዋርያቲሃ: ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ: እምደመ ጳውሎስ ሐዋርያ: እስከ ደመ ጴጥሮስ ወልደ ዮና። @eotcw ❣❣ወረብ ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ ለኢየሩሳሌም/፪/ እምደመ ጳውሎስ ሐዋርያ እስከ ደመ ጴጥሮስ ወልደ/፪/ @eotcw @eotcw ❣ዓዲ እግዚአብሔር : እንተ ተሰመይኪ ገነተ: ደሞሙ ለሰማዕታትኪ ውኅዘ ከመ ማይ: ድምፀ ነጎድጓዶሙ በጽሐ እስከ ሰማይ። @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለዘባናቲክሙ በምኲራባት እለ ተቀሥፋ: ወለእንግድዓክሙ ዘሰፍሐ መልዕልተ ጠበብት ወፈላስፋ: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተጸፍአ ቅድመ ቀያፋ: ሀበኒ ጴጥሮስ መስቀለከ ይኲነኒ ተስፋ: ወጳውሎስ ዉቅየተከ እንተ ደም ለከፋ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ: ዘተሠውጠ ላዕለ ኲሎሙ ሐዋርያት: በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት: ይኲነኒ አክሊለ መዊዕ ወተስፋ: በረከቶሙ ለሳውል ወኬፋ። @eotcw @eotcw ❣❣ወረብ እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘተሰውጠ ላዕለ ሐዋርያት/፪/ በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት/፪/ @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ዕብል ብርሃናተ ፪ኤተ: በዓውደ ንጉሥ ኔሮን እለ ፈጸሙ ሩጸተ: ጳውሎስ ወጴጥሮስ ዘያጸንዑ ፀበርተ: አሐዱ በመስቀል ተሰቅለ ቊልቊሊተ: ወካልዑ ተመትረ ክሣዱ ክብርተ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ብርሃናተ ዓለም ሐዋርያተ ሰላም ሱቱፋነ ሕማም: አሥራበ ምሕረት ከዓዉ እምአርያም። @eotcw @eotcw ❣❣ወረብ ሐዋርያተ ሰላም "ብርሃናተ ዓለም"/፪/ አሥራበ ምሕረት ከዓዉ ከዓዉ እምአርያም/፪/ @eotcw ❣ መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተዘኪረከ ክርስቶስ ዘሐዋርያት ኲሎሙ: ህየንተ ክቡር ደምከ እለ ከዓዉ ደሞሙ: አክሊለ ስምዕ ሀበኒ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ: ወደምስስ ለአጽራርየ እመጽሐፈ ህይወት ዝክሮሙ: ከመ ለይሁዳ ረሲዕ ተደምሰሰ ስሙ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ ስምዖን ጴጥሮስ ወአኃዊሁ ሱቱፋነ ሕማምከ: እለ ከዓዉ ደሞሙ ህየንተ ደምከ: ከመ ይኩን ተውሳከ ለሴጠ አሕዛብ በስብከተ ወንጌልከ: በከመ ተቶስሐ መዓዛ ክህነትከ በክህነቶሙ: ቶስሕ ስእለተነ በስእለቶሙ: ጸግወነ ሎሙ ከመ ንድኃን ቦሙ። @eotcw @eotcw ❣❣ወረብ ስምዖን ጴጥሮስ ወአኃዊሁ "ሱቱፋነ ሕማምከ"/፪//፪/ እለ ከዓዉ ደሞሙ ደሞሙ ህየንተ ደምከ/፪/ @eotcw @eotcw ❣መልክዐ ኢየሱስ ሰላም ለእራኅከ መክፈልተ ሕማማት ሱቱፍ: ወቅንዋቲሁ እኤምሕ በአፍ: ኢየሱስ ክርስቶስ በላዕለ ቅዱሳን ዕሩፍ: ይፀነስ ውስተ ከርሥየ ዘርአ ቃልከ መጽሐፍ: ጸዳለ እምጸዳል ከመ ትፀንስ ዖፍ። @eotcw @eotcw ❣ዚቅ እግዚአ ውእቱ ለሰንበት ውእቱ: አቡሃ ለምሕረት ውእቱ: ኃያል ወብዙኅ ሣህል ውእቱ: ዘባሕቲቱ በቅዱሳኒሁ ዕሩፍ። @eotcw @eotcw ❣❣ምልጣን ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ ወኢትናፍቅ እምዝ ዳግመ ኢንመውት ዳግመ ወእምዝ ዳግመ ኢንመውት። @eotcw @eotcw ❣አመላለስ፦ ወእምዝ ዳግመ /2 ዳግመ ኢንመውት/4/ ❣❣ወረብ ይቤሎ ጴጥስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ እኁየ/፪/ ወኢትናፍቅ ዳግመ እምዝ ዳግመ ኢንመውት/፪/ ❣እስመ ለዓለም ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን: አርድዕት ልዑላን አዕማደ ቤተክርስቲያን: ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ: ወኲሎሙ ሐዋርያት: ፈድፋደ ቦሙ ሞገሰ በኀበ ኲሎሙ ሕዝብ። @eotcw ❣❣ወረብ ሕዝበ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን/፪/ ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ/፪/ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ✨https://t.me/EOTCWW✨ ✨https://t.me/EOTCWW✨ ✨https://t.me/EOTCWW✨ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ https://t.me/EOTCWW #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

ነገ ማኅሌቱን🙌🙌

ጴጥሮስ ወጳውሎስ መኃትው ዋዜማ https://t.me/Eotcw

☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘ አመ 5 ለሐምሌ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ስርአተ ዋይዜማ ☘ዋዜማ በ6 ሃሌታ- @ EOTCWW ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወረዱ ወቦዑ፤ ሀገረ ፊልጶስ፤ ቦኡ ልድያ ወበህየ ረከቡ ብእሴ ፤ ዘስሙ ኤንያ ፤ በሰላሳ ወስምንተ ክረምተ ሐመ ፤ፈወስዎ ወአሕየውዎ፤ ማ፦ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ @EOTCWW @EOTCWW ✨ምልጣን፦ በሰላሳ ወስምንተ ክረምተ ሐመ ፤ፈወስዎ ወአሕየውዎ፤ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ፤ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ @EOTCWW @EOTCWW ☘አመላለስ፦ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ/2/ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ/4/ @EOTCWW @EOTCWW ☘ለእግዚአብሄር ምድር በምላህ፦ አዕማድ እሙንቱ የማኖሙ ወድሙር ኩሉ ንዋዮሙ አዕማድ እሙንቱ የማኖሙ @EOTCWW @EOTCWW ☘እግዚያብሔር ነግሰ፦ ኃረየ ዐስርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ ሤሞሙ ኖሎት ይቤሎሙ ኢየሱስ ዘኪያክሙ ስምዓ ኪያየ ስምዖ ለዘፈነወኒ @EOTCWW @EOTCWW ☘እግዚኦ ጸራእኩ ኃቤከ፦ ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ለእንተ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን @EOTCWW @EOTCWW ☘ይትባረክ እግዚያብሔር ፦ አንትሙሰ ኅሩያን ፍጥረትክሙ ስብኩ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት ሕዝብ ዘኃርየ ወጸውዐ ሎቱ ለርስቱ @EOTCWW @EOTCWW ☘ስቡዕኒ፦ ዘኪያክሙ ስምዓ ኪያየ ስምዐ ስምዖ ለዘፈነወኒ @EOTCWW @EOTCWW ☘ጸሎተ ዘሰለስቱ ደቂቅ፦ ስምዖን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፤ ቦኡ ሀገሮ ለኤንያ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ @EOTCWW @EOTCWW ☘ሰላም፦ ስምዖን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፤ ቦኡ ልድያ ሀገሮ ለኤንያ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ ዘስሙ ለኢየሱስ ገብሩ ሰላመ @EOTCWW @EOTCWW ☘አመላለስ፦ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ /2/ ዘስሙ ለኢየሱስ ገብሩ ሰላመ /4/ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ @EOTCWW☘☘☘☘☘☘ # Join & share #

መዝሙር ይሰጠዎ ከሐምሌ ፫ እስከ ሐምሌ ፱ ይሰጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ ለኲሉ ለዘሰአሎ እግዚኣ ለሰንበት አምላከ ምሕረት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ይሰምዑ ቃሎ ደመናት ትርጉም፦ ይመልስለታል የለመነውን ሁሉ ጸሎቱን ይሰማዋል የይቅርታ አምላክ የሰንበት ጌታ በየዓመቱ ክረምትን ይከፍታል (በጋና ክረምትን ያፈራርቃል) ደመናት ቃሉን ይሰማሉ የዕለቱ ምስባክ፦ አርውዮ ለትለሚሃ ወአሥምሮ ለማእረራ ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ መዝ ፷፬፥፲ ትርጉም፦ ትልሟን አርካው መከሯንም አብጀው በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች ምሥጢር፦ የኢየሩሳሌም ትልሟን አርካው መከሯን የበጀ/የሚጠቅም አድርገው እንዲህ የሆነ ጠብ ጠብ ብሎ በሚዘንመው ዝናም ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለች። ብርቱ ዝናም የዘነመ እንደሆነ ከነመሬቱ ድሶት (ጠራርጎት) ይሄዳል፤ ለሰስ ብሎ የወረደ እንደሆነ ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለችና አንድም ልቡናዋን ደስ አሰኘው ሚጠተ ሥጋውን የበጀ አድርግላት በዘሩባቤል ደስ ብሏት ተካክላ ትወጣለች አንድም ነፍሷን ደስ አሰኘው ሚጠተ ነፍሷን የበጀ አድርገው ከቀኝ ጎንህ በፈሰሰ ጽሩይ ማይ ተጠምቃ ደስ እያላት ከሲኦል ወደገነት ትወጣለች የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፲፫፥፩ - ፴፩ ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ

☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘ አመ 5 ለሐምሌ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ስርአተ ዋይዜማ ☘ዋዜማ በ6 ሃሌታ- @ EOTCWW ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወረዱ ወቦዑ፤ ሀገረ ፊልጶስ፤ ቦኡ ልድያ ወበህየ ረከቡ ብእሴ ፤ ዘስሙ ኤንያ ፤ በሰላሳ ወስምንተ ክረምተ ሐመ ፤ፈወስዎ ወአሕየውዎ፤ ማ፦ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ @EOTCWW @EOTCWW ✨ምልጣን፦ በሰላሳ ወስምንተ ክረምተ ሐመ ፤ፈወስዎ ወአሕየውዎ፤ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ፤ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ @EOTCWW @EOTCWW ☘አመላለስ፦ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ/2/ ሖረ ወገብአ ምስሌሆሙ/4/ @EOTCWW @EOTCWW ☘ለእግዚአብሄር ምድር በምላህ፦ አዕማድ እሙንቱ የማኖሙ ወድሙር ኩሉ ንዋዮሙ አዕማድ እሙንቱ የማኖሙ @EOTCWW @EOTCWW ☘እግዚያብሔር ነግሰ፦ ኃረየ ዐስርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ ሤሞሙ ኖሎት ይቤሎሙ ኢየሱስ ዘኪያክሙ ስምዓ ኪያየ ስምዖ ለዘፈነወኒ @EOTCWW @EOTCWW ☘እግዚኦ ጸራእኩ ኃቤከ፦ ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ለእንተ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን @EOTCWW @EOTCWW ☘ይትባረክ እግዚያብሔር ፦ አንትሙሰ ኅሩያን ፍጥረትክሙ ስብኩ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት ሕዝብ ዘኃርየ ወጸውዐ ሎቱ ለርስቱ @EOTCWW @EOTCWW ☘ስቡዕኒ፦ ዘኪያክሙ ስምዓ ኪያየ ስምዐ ስምዖ ለዘፈነወኒ @EOTCWW @EOTCWW ☘ጸሎተ ዘሰለስቱ ደቂቅ፦ ስምዖን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፤ ቦኡ ሀገሮ ለኤንያ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ @EOTCWW @EOTCWW ☘ሰላም፦ ስምዖን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፤ ቦኡ ልድያ ሀገሮ ለኤንያ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ ዘስሙ ለኢየሱስ ገብሩ ሰላመ @EOTCWW @EOTCWW ☘አመላለስ፦ ወበህየ ፈወሱ ዱያነ /2/ ዘስሙ ለኢየሱስ ገብሩ ሰላመ /4/ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ ☘☘☘@EOTCWW✨✨✨ @EOTCWW☘☘☘☘☘☘ # Join & share #

ያው እንደ ተለመደው ዋዜማ እና ሥርዐተ ማኅሌት ሲኖር ቀደምን ስንክሳርና የየእቱ ምስባክ ስለምንለቅ ከሐምሌ 1-5 የለቀቅን ሲሆን ☝️☝️ወደኋላ እየተመለሳችሁ የየእለቱ ስንክሳር እንዳታነቡ ስንል እንጠይቃለን ።

photo content

ሰዋስው ☘☘☘☘ - آمار و تحلیل کانال تلگرام @eotcw