ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የተባረከ የጥምት ወር የቀኑ ሰዓት ዐሥራ አንድ ነው ከዚህም በኋላ ይቀንሳል።
❤ ጥቅምት ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን ከሮሜ አገር ለሆነች በገድል ተጠምዳ ለኖረች በጨካኙ ንጉሥ በዳኬዎስ ወታደሮች እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች ለቅድስት አንስጣስያ ለዕረፍት በዓልና ለዓላአዛር እኅት ለቅድስት ማርያም ለመታሰቢያ በዓሏ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኅርጣንና ከድንግል ቅድስት ሶስና ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሰማዕቷ ቅድስት አንስጣስያ፦ ይችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርዓት አሳደጓት።
❤ በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቧት ፈለጉ እርሷ ግን ይህን ሥራ አልፈለገችም የምንኲስናን ልብስ መልበስ ፈለገች እንጂ፤ ከታናሽነቷም መንፈሳዊ ገድልን መረጠች። ስለዚህም በሥውር ሒዳ በሮሜ ካሉ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባች ታናሽ ስትሆንም የምንኲስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ የዚህን ዓለም ሐሳብ ሁሉ ከልቡናዋ ቆርጣ በመተው በመጋደል ሥጋዋን አደከመች።
❤ በቀኑ ርዝመትም ሁሉ የምትጾም ሆነች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን የምትመገበው የለም። በሰንበታትም የምትመገበው ከቀትር ጸሎት በኋላ ነው። በነዚያም በምንኲስናዋ ወራት በእሳት ያበሰሉትን ወጥ አልቀመሰችም።
❤ በገዳሟ አቅራቢያም ሌላ የደናግል ገደም አለ የዚያ ደብር በዓልም በደረሰ ጊዜ እመ ምኔቷ በዓሉን ለማክበር ይቺን ቅድስት አንስጣስያን ከእኅቶቿ ደናግል ጋር አስክትላት በአንድነት ተጓዙ። ሲጓዙም የንጉሥ ዳኬዎስን ወታደሮች አየቻቸው። ከእርሳቸውም ጋር የታሠሩ ክርስቲያኖች አሉ ወታደሮቹም አሥረው በቁጣ ይጎትቷቸው ነበር። ልቧም በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና ያን ጊዜ እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው "የእውነት ፈጣሪን የካዳችሁ ልባችሁ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለእነርሱም ነፍሱን ለሞት አሳልፎ በሰጠላቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላችሁ"።
❤ ይህንንም በአለቻቸው ጊዜ ወታደሮች ተቆጡ ይዘውም ወደ መኰንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት "በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን?" እርሷም "ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለሁ" ብላ መለሰችለት።
❤ በዚያን ጊዜም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዚህም በኋላ ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በዚህ በታላቅ ሥቃይም ውስጥ ሳለች ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በበሰማቷ ቅድስት አንስጣስያ ጸሎቱ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 1 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለማርያም ለዓላአዛር እኅቱ። እንተ አንሥኦ ክርስቶስ እምነ መቅበርቱ። በሀሊተ ብካይ ጊዜ ተቀበሎቶ ሎቱ። ሶበሰ እግዚእየ ሀሎከ በዝንቱ። እመኢትውህበ እኅየ ለሞቱ"። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 1።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ። ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ። ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ"። መዝ 102፥14-15። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 7፥32-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 17፥10-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
#ድንግሊቱ ስለሚያገባት ሙሽራ ማጥናት አያሻትም፤ልታለል እችላለሁ ብላም አትሰጋም። #ሙሽራዋ #እግዚአብሔር #እንጂ #ሰው አይደለምና፤ጌታ እንጂ እርሷን የሚመስል ገብር #አይደለምና።በሙሽሮቹ መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነውና።ከጋብቻቸው ማሰሪያ አንፃርም ስንመለከታቸው የሙሽራው ስጦታዎች ቀለበት፣ ቁራጭ መሬትእና ብዙ መክሊት ወርቅ አይደሉም
#መንግስተ ሰማያትና በዚያ ያሉ በጎ በጎ ነገሮች እንጂ በተጨማሪም ያገቡ ሴቶች በሌሎች ብዙ ምክንያቶች መካከል ከትዳር አጋራቸው ሲለያቸው እንደሚችል አስበው ሞትን ይፈራሉ ድንግሊቱ ግን ሙሽራዋን ፊት ለፊት ማየት ፈልጋና ያንን ክብር ሽታ #ሞትን #ትናፍቀዋለች፤በሕይዎት መቆየትንም ትጨነቃለች።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#በእንተ #ድንግልና #ከሚለው #መፅሀፍ #የተወሰደ።
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማር. 1:16-23 ፡ " ወእንዘ የኀልፍ " - " በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና። ኢየሱስም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት። ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ። እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ። "
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
30/1/2015 ዓ.ም (፴/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም።
ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ።
ከመ ዕፍረት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ።
መዝ 132÷1
🕯 ትርጉም
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው።
እነሆም ያማረ ነው።
ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስ ሽቱ ነው።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 4:18-23 " ወእንዘ ያንሶሱ መንገለ ባሕረ ገሊላ"÷ "በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና እርሱም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት። ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸው እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው6 ተከተሉት። "
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
30/1/2015 ዓ.ም (፴/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ።
ወምስለ ብእሲ ንጹሕ ንጹሐ ትከውን።
ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን።
መዝ 17፥25
🕯 ትርጉም
ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ።
ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ።
ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ።
1 161
መልካም የአቡነ አቡሳዲ የዕረፍት በዓል፣ የጾም ጊዜ እና ዕለተ ሰነበት ለሁላችንም ይሁንል።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን የዘብዴዎስ ልጆችን ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ለሐዋርያነት ለጠራበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ ሲል እራሱን እንደ እብድ መስሎ ታላቅ ተጋድሎ ለአባ ሣሉሲ ለዕረፍት በዓል፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በከበረና በተመሰገነ በአባ አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ቀን በዓልና ለአቡነ አሮን ዘገሊላ ለመታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ከአቡነ ጎርጎርዮስ ከመታሰቢያቸው፣ ከአባ ቡላ፣ ከማርዩ፣ ከብትሩስ፤ ከሰማዕቱም ከቅዱስ አስታሬስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ ፬ "ትዌድሶ መርዓት እንዘ ትብል ነዐ ወልድ እኁየ ንጻዕ ሀቅለ፤ አዝ፣ ንርዓይ ለእመ ጸገየ ወይን ወለእመ ፈረየ ሮማን፤ አዝ፣ አሠርገወ ሰማየ በከዋክብት ወምድረኒ በስነ ጽጌያት፤ አዝ፣ እስመ ውእቱ ወልድ ዋህድ እግዚአ ለሰንበት ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ ወልድ እኁየ ቃልከ አዳም። ትርጉም፦ ሙሽሪት ወልድ ወንድሜ ና ወደ ቆላ እንውጣ እያለች ታመሰግነዋለች ወይን አፍርቶ ሮማንም አፍርቶ እንደኾነ እናይ ዘንድ ወደ ቆላ እንውጣ ሰማይን በከዋክብት ሸለመ ምድርንም በአበቦች አስጌጠ የሰንበት ጌታ እርሱ ነውና ልጅ ወንድሜ ሆይ ቃልክ ያማረ ነው እያለች ታመሰግነዋለች። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ አባ ሣሉሲ፦ ይህም ቅዱስ መስጋድል ሲሆን ራሱን እንደ እብድ አደረገ እርሱም በሥውር ይጸልያል ይጾማልም በሰው ፊት ግን ምንም ምን አይጸልይም አይጾምም በየጥዋቱ ሁሉ የሚመገበውን የሣር ፍሬ አድርጎ በሰው ፊት ያላምጣል በምሽት ጊዜ ግን ከውንድሞች መነኰሳት ጋር ምንም ምን አይቀምስም። አበ ምኔቱ አባ ይስሕቅና መነኰሳቱ ሁሉ ከሥራው የተነሣ ያደንቃሉ ይህንንም ልማዱን ሊአስጥሉት ይሻሉ ነገር ግን ልቡን እንዳያሳዝኑት ያስባሉ።
❤ በአንዲትም ዕለት የገዳማቸው በዓል ሆነ አበ ምኔቱ አባ ይስሐቅም መነኰሳቱን እንዲህ አላቸው "ቅዱስ ቁርባንን ከመቀበሉ በፊት እህልን እንዳይቀምስ አባ ሣሉሲን ጠብቁት"። እነርሱም ጠበቁት የሚበላበትም ጊዜ ሲደርስ ከእነርሱ ሊለይ ወደደ መነኰሳቱም ከለከሉት እርሱም "በረኃብ እንዳልሞትና በእናንተ ላይ በደል እንዳይሆንባችሁ ልቀቁኝ ብሎ ጮኸባቸው"። ባልተውትም ጊዜ በዚያን ወቅት ቆቡን ከራሱ ላይ አውልቆ "እመቤቴ ማርያም ሆይ ከእሊህ መነኰሳት እጅ አድኝኝ" ብሎ የቤተ ክርስቲያኑን ግድግዳ በቆቡ መታበት ሕንፃውም ተሠንጥቆለት በዚያ ወጥቶ ሔደ የግድግዳውም ግምብ ተመልሶ እንደቀድሞው ሆነ።
❤ የተሰበሰቡትም ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ሦስት መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን እያሉ ጮኹ በዚያንም ጊዜ ያቺን ቆብ ወድቃ አገኙአት በታላቅም ክብር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩዋት ድውያንንም በመፈወስ ከእርሷ ብዙ ተአምራት ተደረገ። ሊቀ ጳጳሳቱም በሰማ ጊዜ ከእርሷ ሊባረክ ወዶ ያቺን ቆብ ሊወስዳት ፈለገ በየጊዜውም ሲወስዳት ወደቦታዋ ወደዚያ ገዳም ትመለሳለች እንዲህም ሦስት ጊዜ ሆነ ከዚህም በኋላ መውሰዱን ተወ።
❤ ከብዙ ወራትም በኋላ እንደ ዛሬው ሁሉ በዚች ቀን አባ ሣሉሲ በዚሁ ገዳም በዐረፈበት ቦታ ተገልጾ ተገኘ በክብርም ገንዘው ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሣሉሲ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በከበረና በተመሰገነ በአባ አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ተአምር፦ ይህም ሁለተኛም ቈስጠንጢኖስ ወደ ረከሰች የአርዮስ ሃይማኖት በገባ ጊዜ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስን አሳድዶ ከሀዲውን ጊዮርጊስን በእስክንድርያ መንበር ላይ ሾመው። የአርዮስንም ሃይማኖት እንዲአጠናክር የረከሰ የአርዮስን ሃይማኖት የማይቀበሉትን ግን ሁሉንም ይገድላቸው ዘንድ አዘዘው ብዙዎች ፈረሰኞች ጦረኞችን ለእርሱ ሰጥቶታልና። ስለዚህም ከእስክንድርያ ሰዎች ቁጥር የሌላቸውን ብዙዎች ምእመናንን ገደላቸው።
❤ ቅዱስ አትናቴዎስም በተሰደደበት ስድስት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ልጅ የካደው ታናሹ ቈስጠንጢኖስ ወደአለበት ወደ ቊስጥንጥንያ ተነሥቶ ሔደ ንጉሡንም እንዲህ አለው "ወደ ተሾምሁበት መንበሬ ትመልሰኝ እንደሆነ መልሰኝ ይህ ካልሆነ የምስክርነት አክሊልን እንድቀበል ግደለኝ"።
❤ ንጉሡም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ በታናሸ መርከብ አድርገው ያለ ቀዛፊና ያለ መብልና መጠጥ በባሕር ውስጥ እንዲተዉት አዘዘ ንጉሡም በስጥመት ወይም በረኃብና በጥም እንደሚሞትለት አስቦ ነበርና የቀናች ሃይማኖትንም ስለመለወጡ እንዳይዘልፈው ከእርሱ ያርፍ ዘንድ እንዲሁም ንጉሡ እንዳዘዘ በቅዱስ አትናቴዎስ ላይ አደረጉበት። ንጉሡም እንጀራና ውኃ ባይሰጠው ከሰማይ ለእርሱ የወረደ እንጀራ ስለርሱ የፈለቀ ውኃም አለው። የመርከብም ቀዛፊ ቢከለክለው እነሆ ዓለሙን ሁሉ በቃሉ የሚጠብቅ የሚመራ ከእርሱ ጋር ነበር። ስለዚህም ቅዱስ አትናቴዎስ በውስጧ የተቀመጠባት ያቺ መርከብ መላእክት እየቀዘፏት በጸጥታና በሰላም ተጓዘች በሦስተኛውም ቀን ከእስክንድርያ ወደብ ደረሰ።
❤ የምእመናን ወገኖችም ደግ ጠባቂያቸው እንደ ደረሰ በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው መብራቶችንም በመያዝ በምስጋና እየዘመሩ ሊቀበሉት ወጡ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡት። ከሀዲው ጊዮርጊስም ከወገኖቹ ጋር ወጥቶ ሔደ።
❤ በዚያችም ቀን ቅዱስ አትናቴዎስ ለእግዚአብሔር ታላቅ በዓልን አከበረ የእስክንድርያም ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ያከብሩ አታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም የቅዱስ አትናቴዎስም በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 30 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለክሙ ጽጉባነ ምዑዝ ጽጌረዳ። ዘረከበክሙ ክርስቶስ ለባህረ ገሊላ በዐውዳ። አመ ሰዓተ ደይን ያዕቆብ ወዮሐንስ በዕለተ ፍዳ። በሉኒ ሊተ ዘዚአነ ወለትምህርትነ ወልዳ። እንዘ ትእኅዙ ለነፍስየ እዳ። ትርጉም፦ መልካም መዓዛ ያለውን ጽጌረዳ ለጠገባችሁት ለእናንተ ሰላም እላለሁ። ክርስቶስን በገሊላ ባህር አጠገብ ያገኛችሁት ቅዱስ ያዕቆብና ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በቁርጥ የቅጣት ሠዓትና በፍርድ ቀን ነፍሴን በእዳ ይዛችሁ እርሱ እኮ የእኛ ነው የትምህርታችን ልጅ ነው በሉልኝ።
+ + +
❤ "ሰላም ለክሙ መምህራነ ዕበይ ወተድላ። ዘደብረ ማርያም አብሳዲ ወአሮን ዘገሊላ። ትትኖለዉኒ ሥሙረ መንገለ ወፈርኩ ኵላ። ኢይንዐወኒ ዐርየ ከመ ይንዕዉ ገድላ። አንበሳ ርኁብ ወካይኡ ተኵላ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 30።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ፍሬ ፃማከ ተሴሰየ። ብፁዕ አንተ ወሠናይ ለከ። ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙረ ውስተ ጽርሐ ቤትከ"። መዝ 127፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥21-ፍ.ም፣ ራዕ.ዮሐ 21፥1-9 እና የሐዋ ሥራ 21፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 3፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ።
1 161
ጠራ መታሰቢያህን ያደረገ እስከ ዐሥራ ሁለት ትውልድ እምርልሃለሁ። አንተ ግን ሞትን አትቀምስም"። ብሏቸው ሰኔ 17 ቀን ተሰወረ። ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል። ከአባታችን ከአቡነ ገሪማ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ለተሻገሩት ለታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ለሆኑ በኤራትራና በኢትዮጵያ ገዳም ለመሰረቱ ለታላቁ አባት ለአቡነ አቡሳዲ ለዕረፍታቸው በዓልና ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለአቡነ ይስሐቅ ተአምር ሰረተው አቡነ ገሪማ ተብለው እንዳጠሩ ላተረጉበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም (ክሳሄ)፦ እኚህ ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር የተሻገሩት የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ የደብረ ክሳሄው አቡነ አብሳዲ ገድላቸውን የፈጸሙት ኤርትራ ውስጥ ነው፡፡
❤ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጌታችን በቃሉ ጠርቶ "በላይህ ላይ ያለውን ቅዱስ መንፈስ በወዳጅህ በልጅህ አብሳዲ ላይ አሳድር፣ ሙሴ የራሱን መንፈስ በነዌ ልጅ በኢያሱ ላይ እንዳሳደረ፣ ኤልያስም በረድኡ በኤልሳዕ ላይ እንዳሳደረ" አላቸው፡፡ ምክንያቱም ልጆቻቸውን ትተው ወደ ኢየሩሳሌም ከዚያም ወደ አርማንያ እንዲሔዱ ነግሯቸዋልና ነው፡፡ አባታችንም ልጃቸውን አቡነ አብሳዲን ሦስት ጊዜ "አብሳዲ አብሳዲ አብሳዲ" ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም አባቱን "አቤት ጌታዬ እነሆ ጠርተኸኛልና" አለው፡፡ አባታችን ኤዎስጣቴዎስም "እነሆ በረከት ከሰማይ ለአንተ ተሰጠች፣ ይህችንም በረከት ብርንና ወርቅን የማይወዱ ራሳቸውንም ወደ ጠባብ በር ያስገቡ እንደ አንተ ካለ ጻድቃንና ከተመረጡት በቀር መቀበል የሚችል የለም፤ እነርሱም ሥጋቸውን አሳልፈው ለጻዕር ለጭንቅ የሰጡ ናቸው፤ ከተወለዱም ጀምሮ ጣፋጭ የሆኑ የምድር ምግቦችን ያልወደዱ ናቸው፣ ራሳቸውንም እንደምታልፍ ነፋስ ያደረጉ ናቸው"፡፡
❤ አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ይህንን ተናግረው በአብሳዲ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡ ሙሴ በኢያሱ እንደጫነ፣ ያዕቆብም በይሁዳና በሌዊ ላይ እጁን ጭኖ ለመንግሥትና ለክህነት እንደባረካቸው ዮሴፍም ልጆቹን ኤፍሬምና ምናሴን ይባርካቸው ዘንድ ወደ አባቱ እስራኤል አምጥቷቸው እርሱም የተባረከና ቅዱስ ሕዝብ ያድርጋችሁ ብሎ እንደባረካቸው እንደዚሁም ሁሉ አባታችን ኤዎስጣቴዎስ ልጃቸውን አብሳዲን እንዲህ እያሉ ባረኩት፡- "የቀደሙ አባቶች በረከት፣ የነቢያትና የሐዋርያት በረከት፣ ድል የሚነሡ የሰማዕታት በረከትና በተጋድሎ የጸኑ የጻድቃን በረከት፣ የቅዱሳን መላእክት በረከት፣ ማኅበረ በኩር የተባሉ የሁሉም ቅዱሳን በረከት፣ አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት፣ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ በረከት በአንተ ላይና በልጆችህ ላይ ይደር፤ መታሰቢያዬንና መታሰቢያህንም በሚያደርጉ ላይ ይደር ለዘለዓለሙ አሜን" ብለው መባረክን ከባረኩት በኋላ አብሳዲን ግንባሩን ቀብተው አተሙት፡፡
❤ አቡነ አብሳዲ ገዳማትንና ምንኵስናን ለማስፋፋት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ቀንና ሌሊት ሳያርፉ ምእመናን በማስተማር አባታቸው ኤዎስጣቴዎስ እንዳስተማሯቸው ገዳማትንና ምንኵስናን በኤርትራና በኢትዮጵያ በማስፋፋት ለገዳማዊ ምናኔ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሐዋርያ ናቸው፡፡ በመንፈስ የወለዷቸው በርካታ መነኵሳት ልጆቻቸው አማካኝነት በኢትዮጵያና በኤርትራ የተገደሙት ገዳማት ከ120 በላይ ናቸው፡፡
❤ በልጆቻቸው አማካኝነት በኤርትራ ከተገደሙት ገዳማት ውስጥ፦ ደብረ ኮል አቡነ ብሩክ (መራጉዝ)፣ የአቡነ ዮናስ ገዳማት (ደብረ ድኹኻን ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ ሣህል ዛይዶኮሎም)፣ ደብረ አቡነ ሙሴ (ማይ ጎርዞ)፣ ደብረ ሲና አቡነ ድምያኖስ፣ ምድሪ ወዲ ሰበራ፣ ደብረ ሐዋርያት አቡነ ሴት (ዓዲ ቂታ)፣ ደብረ ማርያም (ዓይላ) እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ እነኚህን እንደ ምሳሌ ጠቀስን እንጂ በኢትዮጵያም የአቡነ አብሳዲ ልጆች የመሠረቷቸው በርካታ ገዳማት አሉ፡፡
❤ አባታችን የረጅም ዘመን ተጋድሏቸውን በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኹለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸው "በሰሜን ያለች ይኽችን ገዳም ባርኬልሃለውና ከልጆችህ ጋር በእርሷ
ኑር" ካላቸው በኋላ ቃልኪዳን ገብቶላቸው ተሰወረ፡፡ ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይኽችም ለአባታችን የተሰጠቻቸው ገዳም ደበረማርያም (ደብረ ክሳሄ) ናት፡፡
❤ ከዚኸም በኋለ ቅዱስ አባታችን አብሳዲ ደከመኝ ልረፍ ሳይሉ መላ ዘመናቸውን ሐዋርያዊ ተልዕኳቸውን ፈጽመው ከእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ተቀብለው በ101 ዓመታቸው መስከረም 30 ቀን 1383 ዓ.ም ዐርፈው ቆሓይን በምትገኘው ገዳማቸው ደብረ ክሳሄ ደብረ ማርያም ገዳም ተቀበሩ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አቡሳዲ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!።
+ + +
❤ አቡነ ይስሐቅ (አቡነ ገሪማ ዘመደራ)፦ እኚህ ጻድቅ
የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሮም ውስጥ ነው። ወላጆቻቸው መስፍንያኖስ እና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ። እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት። ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለሰባት ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።
❤ አንድ ቀን ግን ከግብጽ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው። ላኪው አባ ጰንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘላለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና!" የሚል ነበር። ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብጽ አባ ጰንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው።
እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኰሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ። ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው። ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር።
❤ አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ጰንጠሌዎን አዘኑ። ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ"። አሉ። አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል"። ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (ሁለት መቶ ሜትር) ተጠራርጎ ሸሸ። ይህንን የተመለከቱት አባ ጰንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ)።" አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ ገሪማ" ተብለው ቀሩ።
❤ አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ"። እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል። ይህም የተደረገው በዚህች ዕለት መስከረም ፴ ቀን ነው።
❤ ጻድቁ ወንጌልንና ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል ከሰራቸው ተአምር መካከል፦
፩. ስንዴ ጧት ዘርተውት በዘጠኝ ሰዓት ያፈራ ነበር። "በጽባሕ ይዘርዕ ወበሠርክ የአርር" እንዲል።
፪. ጧት የተከሉት ወይን በዘጠኝ ሰዓት ያፈራ ነበር።
፫. አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጠበል ሆኖ ዛሬም አለ።
፬. ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች።
፭. አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል።
❤ ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። "ስምህን የ
