ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም)
***************************
ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር 15 ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው የአዋጅ ጾም ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ ፣ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ ፣ ስለ መሰቀሉ ፣ ስለ ሞቱ ፣ ትንሣኤው ፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል ፤ ትንቢቱ ደርሶ ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
ምንጭ፡-ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው አንቀጽ ፲፭
©ተዋሕዶ ሚዲያ
#Share #Share #Share
#ቃለ_እግዚአብሔር_ለሁሉ_እንዲዳረስ
ለሁሉም ሼር 👉👉@eotcw ያድርጉ
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሥርዓተ ማኅሌት ዘአእላፍ /ህዳር ፲፫/🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለመታክፍቲክሙ መሠረተ ዓለም እለ ፆሩ: ኖትያተ ኖኅ ሥላሴ ወዕፀወ ዐባይ ሐመሩ: ዲበ መንበርክሙ ሰብአ ሶበ አምላክ ነጸሩ: ኪሩቤል ወሱራፌል ታህተ እገሪሁ ገረሩ: እስመ ለሊሁ አዘዘ ወእሉ ተፈጥሩ፡፡
ዚቅ፦
ሱራፌል ይሰግዱ ሎቱ፤ ወኪሩቤል ይሴብሕዎ፤ ይጸርሑ እንዘ ይብሉ፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ በኀበ አዕላፍ ወክቡር በዉስተ ረበዋት።
ነግስ
ይትባረክ ስምኪ ማርያም ለዘአውፃእከነ እምፀድፍ፤ በርኅራኄኬ ትሩፍ፤ ይዌድሱኪ ኪሩቤል በከናፍር ወአፍ፤ ሐራ ሰማይ ትጉሃን አኁዛን ሰይፍ፤ አምሳለ ደመና ይኬልሉኪ በክንፍ
ዚቅ፦
ኩሎሙ ሠራዊተ መላእክት አዕላፍ፤ እለ ይሠርሩ በአክናፍ፤ እምጽንፍ እስከ ጽንፍ፤ ይሴብሑኪ ማርያም በዘኢያረምም አፍ።
መልክአ አእላፍ፦
ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘኢይትክሀል ለተነግሮ፤ እንበለ ዳዕሙ አንክሮ፤ ትጉዐን አዕላፍ እለ ትጽሕቁ ለዘምሮ፤ለቅሑኒ ንዋየ ጽድቅ ዘዚአክኪሙ አእምሮ ፤ዜና ውዳሴክሙ እንግር ወእከሥት ምስጢሮ
ዚቅ፦
አስማቲሆሙ ለመላእክት ይቀድም ተጽሕፎ፤ ወዓዲ መልክዓ ገዳሙ፤ ወይቤ ኪሮስ ርኢኩ ወልድ ይነብር በየማኑ።
መልክአ አእላፍ፦
ሰላም ለገበዋቲክሙ ሠርጎ ወርቅ ዘኢለብሳ፤ ወለከርሥክሙ ርኁብ እመ ብልዐ ዕልው ኀሠሳ፤ ካህናት ሰማይ አእላፍ አንጽሑኒ ዐበሳ፤ ወዘልፈ ተኖለወኒ ኢይምስጠኒ አንበሳ፤ ከመ ዘሥጋ ወደም ወየዋህ እንስሳ።
ዚቅ፦
ሠረገላሆሙኒ ምሉዓነ አዕይንት፤ ወዓዲ ዘባናቲሆሙ፤ መልአከ ሰላም ቆመ ማዕከሎሙ፤ ውእቱ ሚካኤል ሊቆሙ ወመልአኮሙ፤ ሠርዖሙ በበደወሎሙ።
ወረብ፦
ሠረገላሆሙኒ ሠረገላሆሙኒ ምሉዓነ አዕይንት፤
ወዓዲ ዘባናቲሆሙ ቆመ መልአከ ሰላም
መልክአ አእላፍ፦
ሰላም ለአእናፊክሙ ዘተደለዉ ለሐዊር ፤ ለዘባንክሙኒ እሳታዊ መንበር፤ አመ በእግረ ነፍስ አዓርግ ውስተ ሰማያዊት ሀገር ፤ አዝማደ ነፍስየ አዕላፍ ተወከፈኒ በፍቅር፤ ወኢትትሐየዩኒ እኩን ስላቀ ለፀር።
ዚቅ፦
ወመላእክት ተጋቢዖሙ፤ ሰፍሑ ክነፊሆሙ፤ ወጸለሉ ላዕለ ተክለ ሀይማኖት ፤ ወቢህየ ገብሩ በዓለ።
ወረብ፦
ወመላእክት ተጋቢዖሙ ሰፍሑ ክነፊሆሙ ወጸለሉ ላዕለ ደብረ ገነት[፪] ፤
ወቢህየ ገብሩ በዓለ[፬]
ምልጣን፦
እሎንቱ ሊቃናት መልአክተ ምህረት እለ ግልቡባን በነደ እሳት ሱራፌል ወኪሩቤል፡ ይትፌነዉ ለሣህል እምአበ ልዑል ፡ሩጸቶሙ ይቀልል እምሩጸተ ነፋሳት
ወረብ ፦
እሎንቱ ሊቃናት መልአክተ ምህረት ሱራፌል ወኪሩቤል፤
እለ ግልቡባን እለ ግልቡባን በነደ እሳት በነደ እሳት
ወረብ፦አዲ
ሱራፌል ወኪሩቤል(፪) ይትፌነዉ ለሣህል እምአበ ልዑል ፤
ሩጸቶሙ ይቀልል እምነፋሳት(፬)
እስመ ለአለም፦
ኪያከ ይሴብሑ ፻ት እምዓት፤ዕልፍ አዕላፋት ሠራዊተ መላእክት በ1 ቃል፤ሚካኤል ወገብርኤል ሱራፌል ወኪሩቤል ፤ማ፦ ይቀውሙ ዓውዶ፤አዕላፈ መላእክት ይትለእክዎ
ሰላም፦
ሠረገላሆሙኒ ምሉዓነ አዕይንት፤ ወዓዲ ዘባናቲሆሙ፤ መልአከ ሰላም ቆመ ፤ ውእቱ ሚካኤል ሊቆሙ ወመልአኮሙ፤ ሠርዖሙ በበደወሎሙ።
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
መልካም በአል
1 161
🌸🌸🌸🌸🌸
ኅዳር 12 ምስባክ
🍀🍀🍀🍀🍀
፨ምስባክ ዘነግህ
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሳሕ ንጉሥ ፤
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ ፤
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ
፨ወደ ሮሜ ሰዎች ም. ፱ ቊ. ፲፯ - ፳፬
፨የይሁዳ መልእክት ም. ፩ ቊ.፱ - ፲፬-፲፭
፨የሐዋርያት ሥራ ም. ፳ ቊ. ፳፰ - ፴፩
ምስባክ ዘቅዳሴ
ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ ፤
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ፤
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር
ወንጌል
-የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፱ ቊ. ፲፩ - ፵፰
-የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፲፭ - ፳፩
