ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቋ ሰማዕት ሰይጣንን በራሱ ጠጉር ይዛ ለደበደበችው በእግሮቿም ለረገጠችው ለቅድስት መሪና ለዕረፍት በዓል፣ ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነ በመስቀል ላይ ጌታችንን ከሞተ በኋላ የቀኝ ጎኑን ለወጋው ለቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከአብጥልማዎስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሰማዕቷ ቅድስት መሪና፦ የዚችም ቅድስት የአባቷ ስም ዳኬዎስ ነበር እርሱም በአንጾኪያ ሀገር ለጣዖታት ካህናት አለቃ ነበር ያን ጊዜ ንጉሡም ከሀዲው ዳኬዎስ ነበር። አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ እናቷ ሞተች አባቷም ከከተማ ውጭ ለምትኖር ሞግዚት ሰጣት እርሷም ክርስቲያናዊት ነበረች የክርስቶስ የሆነ የሃይማኖት ትምህርትን ሁሉ አስተማረቻት። ዐሥራ አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ አባቷ ሞተ።
❤ ከዚህም በኋላ ሰዎች የሰማዕታትን ተጋድሏቸውንና መከራቸውን ሲናገሩ ሰምታ የጌታ ክርስቶስ ፍቅር በልቧ አደረ በሰማዕትነት መሞትንም ፈልጋ ሔደች።
በዚያን ጊዜም ከሀዲ መኰንን ወደዚያች አገር ደረሰ እርሷንም አይቶ ወደርሱ አስመጣትና "ከወዴት ነሽ" አላት "ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ሰዎች ወገን ነኝ ስሜም መሪና ነው" አለችው። ደም ግባቷንና ላሕይዋንም አይቶ መታገሥ ተሳነው እሺ ትለው ዘንድ በብዙ ነገር አባበላት። እርሷ ግን ረገመችው የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች።
❤ ያን ጊዜም በብረት ዘንጎች ይደበድቧት ዘንድ ደሟ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሕዋሳቷን ይቆራርጡ ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ጸለየች የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳናት። ሁለተኛም ወደ ወህኒ ቤት ያስገቧት ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ወደ ሰማይ አውጥቶ የቅዱሳን ሰማዕታትንና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳይቶ ወደ ቦታዋ መለሳት። በማግሥቱም ሥጋዋን በመጋዝ እንዲሠነጥቁ ጐኖቿንም እንዲሰነጣጥቁና በእሥር ቤት እንዲጥሏት አዘዘ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አዳናት።
❤ በወህኒ ቤቱ ውስጥም ቁማ ስትጸልይ እጅግ የሚያስፈራ ታላቅ ዘንዶ ወደ ርሷ መጣ በአየችውም ጊዜ ደነገጠች ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠ መናገርም ተሳናት። ያን ጊዜም እጆቿ በመስቀል ምልክት አምሳል እንደተዘረጉ በልቧም ስትጸልይ ወደርሷ ቀርቦ ዋጣት። ያን ጊዜም ሆዱ ተሠንጥቆ ያለ ጉዳት ወጣች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው።
❤ ሁለተኛም በጥቁር ሰው አምሳል ሰይጣንን አየችው እጆቹም በጉልበቶቹ ላይ ተጨብጠው ነበር። ፊቷንም በመስቀል ምልክት አማትባ በራሱ ጠጉር ይዛ ደበደበችው። በእግሮቿም ረገጠችው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና የጌታ ክርስቶስ ዕፀ መስቀል ተገለጠላት በላዩም ነጭ ርግብ ተቀምጣ እንዲህ ብላ አነጋገረቻት "መሪና ሆይ የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ አረቦን ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ"።
❤ በማግሥቱም መኰንኑ ልብሷን አራቁተው ዘቅዝቀው ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ደግሞም ውኃ ከአፈሉበት ጋን ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ። በውስጡም ሁና ስትጸልይ ከሰማይ ርግብ መጣ በአፉም ውስጥ የወርቅ አክሊል ነበር ማሠሪያዋንም ፈትቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሦስት ጊዜ አጠመቃት እግዚአብሔርንም እያመሰገነች ከውኃው ውስጥ ወጣች።
❤ መኰንኑም እንደ ዳነች በአየ ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ወደ ሰማዕትነቱ ቦታም በደረሰች ጊዜ ነፍሷን በፍቅር ይቀበል ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየች። ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገለጠላት ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያዋንም ለሚያደርግ ገድሏንም ለሚጽፍ ወይም ለሚያነበውና ለሚሰማው ኃጢአቱን እንዲአስተሠርይለት ለርሷም ርሱን እንዲሰጣት ቃል ኪዳን ሰጣት።
❤ ከዚህም በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጡ ከእርሷም ብዙ ተአምር ተገለጠ ዕውራን አይተዋልና፣ ሐንካሶች በትክክል ሔደዋልና፣ ደንቆሮዎችም ሰምተዋልና፣ ዲዳዎችም ተናግረዋልና ቁጥር የሌላቸው ብዙ ሰዎችም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቷ በቅድስት መሪና ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ወታደሩ ሰማዕት ቅዱስ ለንጊኖስ፦ ይህም ቅዱስ ከጲላጦስ ጭፍሮች ውስጥ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ደኅንነት መከራ እንዲቀበል የፈቀደበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ የፈለጉትን ያደርጉ ዘንድ ለዐመፀኞች ፈቅዶላቸው ነበር። ይህም ለንጊኖስ ጌታን ይሰቅሉት ዘንድ ጲላጦስ ከአዘዛቸው ወታደሮች ውስጥ ነበር።
❤ በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ ጌታችንን የቀኝ ጐኑን ወጋው ከጐኑም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ይህንንም አይቶ እጅግ አደነቀ ከዚህም በፊት ፀሐይ እንጨለመ፣ ጨረቃ ደም እንደሆነ፣ ዐለቱም እንደተሠነጠቀ፣ ሙታንም እንደተነሡ አይቶ ነበር።
❤ ጌታችንም በተነሣ ጊዜ ስለ ትንሣኤው የሆነውን ሰምቶ ይህን ምሥጢር ይገልጽለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ሐዋርያው ጴጥሮስንም ላከለት እርሱም ነቢያት ስለ ጌታችን፣ ስለ መከራው፣ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ መሞቱ፣ ስለ መነሣቱ፣ ስለ ዕርገቱም ትንቢት እንደተናገሩ ነገረው። እርሱም ከቅድስት ድንግል በሥጋ ተወልዶ ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆነ አስረዳው።
❤ ያን ጊዜም በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል አመነ የምድራዊ ንጉሥ አገልግሎትንም ትቶ ወደ ቀጰዶቅያ ሔደ በውስጧም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሐዋርያት ሰበከ። አይሁድም በጠላትነት ተነሡበት በመሳፍንትም ዘንድ ከሰሱት በላዩም የሐሰት ምስክር አስነሡበት ስለዚህም ሐምሌ 23 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ለንጊኖስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 23 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለለንጊኖስ ዘኂሩተ አምላክ ቀጸበቶ። ለጴጥሮስ ረድእ ከመ ይትወከፍ ትምህርቶ። ከመ ኢያሐስብ ቦቱ ዘኲናለ እዱ ርግዘቶ። በኃጢውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ። ምሕረቶ እሴብሕ ወዓዲ ትዕግሥቶ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 23።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኢይቀሥፍ ወትረ ወኢይትመዓዕ ዘልፈ። አኮ በከመ ኃጢአትነ ዘገብረ ለነ። ወኢፈደየነ በከመ አበሳነ"። መዝ 102፥9-10 ። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥5-ፍ.ም፣ ያዕ 2፥14-20 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-16። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 19፥31-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የዮሐንስ አፈወርቅ ወይም እግዚእነ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን ለመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) ለአንድ መቶ ሃያኛው (120) ለቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የዕለቱ መዝሙር፦ "አመ ሕንፂሃ ለገነተ ጽጌ አንሶሰወ ውስተ መርህባ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፡፡ምስለ ሠራዊቲ ዖዳ ማቴዎስ ቀደሳ ወአተባ በዕፀ መስቀሉ"። ትርጉም፦ ቅዳሴ ቤቷን ባከበረ ጊዜ ተመላለሰ በአደባባዯ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፡፡ከሠራዊቶቹ ጋር ዞራ ማቴዎስ አከበራት በመስቀሉ ደግሞ ባረካት። ድርስ መዝሙር።
+ + +
❤ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒልክ በአደዋ ጦርነት ጊዜ ለረዳቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ከድሉ ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ መሐል ከተማ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠሩ ስሟንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰየሟት የባረኳትም ሊቀ ጳጳሱ ግብፃዊው አቡነ ማቴዎስ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ጊዮርጊስ ልመናው አማላጅነቱ ከእኛ ጋር ይሁን አሜን!!!ተአምረ ጊዮርጊስ ተአምር17 ላይ።
+ + +
❤ የበዓሉ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ተቀደሲ ወንሥኢ ኃይለ ኦ ቤተ እግዚአብሔር እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ዘያበርግህ ለኪ በኃይሉ ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሐነፃ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ ቤተ እግዚአብሔር ሆይ ተቀደሺ ኃይልንም ልበሺ ንጉሥሽ እያበራ ወደ አንቺ ደርሷልና፡፡ ይእቺን ቤት አስቀድሞ አብ ሠራት ወልድ አነፃት መንፈስቅዱስ ፈፀማት፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የበዓሉ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወንሰግድ ውስተ መካነ ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ። ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ። አንተ ወታቦተ መቅደስከ"። መዝ131፥7-8 ወይም መዝ90፥13። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥23-30።
+ + +
❤ የበዓሉ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትተሐወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ45፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፊ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥4-11 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ
ሰላማዊት ኪዳነ ምህረት
✝✝✝
⏩ የጉዞ ቀን እሁድ ነሐሴ 22/12/14 ዓ.ም
⏩ የጉዞ ሁኔታ ደርሶ መልስ
⏩ የጉዞ ዋጋ 350 ብር መስተንግዶን ጨምሮ
⏩ የጉዞ መነሻ ሰዓት 11:00 ሰዓት
-----ስለ ሰላማዊት ኪዳነምረት ቃልኪዳን እና ተዓምር ከብዙ በጥቂቱ
➡️ በ1928 ዓ.ም በወቅቱ ለአንድ አመት ከፍተኛ ረሃብ በሀገሪቱ ላይ በመከሰቱ የማርያም ዕለት በ21 ሀሙስ ቀን ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ሰባት አባቶች እያዘኑ እያለቀሱ በቤተ መቅደሱ ይወድሰዋ መላዕክት ሲደግሙ እመቤታችን ተገልፃ ህዝቡን ሰብስቡና ንፍሮ ቀቅለው እንዲመጡ አድርጉ ንፍሮው ተባርኮ ከመበላቱ በፊት ሕዝቡን በሙሉ በመስቀል ባርኩ ጠበል እርጩ ልጅ የዘገየባቸውን ገድል አሳዝሉ ግቢዬ ውስጥ የበቀለውን እሬት እምነት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ ብላ ተሰወረች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስርዓቱ ሲካሄድ ቆይቶ እዚህ ደርሶ ብዙዎች እየዳኑ ልጅ እያገኙ ይገኛሉ።
➡️ መነሻ ቦታ
1 ቅዱስ ፋኑኤል ቤ/ክ
2 አለም ባንክ
3 አየር ጤና
⏩ ለበለጠ መረጃ
09 29 18 75 40
09 93 63 93 41
09 74 74 09 35
09 35 00 57 18
አዘጋጅ : ማህበረ እግዛብሔር አብ መንፈሳዊ ጉዞ✝✝✝✝✝✝✝
ከክርስቲያናዊ አለባበስ ጋር
1 161
❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣
አመ ፳ወ፪ ለሐምሌ ቅዱስ ዑራኤል ስርዓተ ማኅሌት
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
/ሥርዓተ ነግሥ/
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል
@EOTCW
@EOTCW
ነግስ፦
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም
ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም
ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
መላእክት ወሰብዕ ውሳጤሁ በእንተ ስሙ አሀዱ ማኅበሮሙ፤በእንተ መስቀሉ ለክርስቶስ፤አሐደ መርዔተ ኮኑ
@EOTCW
@EOTCW
ማህሌተ ፅጌ
ዑራኤል ለሔኖክ ዘአርአዮ ትእምርተ አምሳልኪ ቤተ ነድ፤ዘመብረቅ ጠፈራ ወኅብራ በረድ፤ በከመ ተነበይኪ ድንግል ጽጌ ነጎድጓድ፤ያስበጽዑኪ ኩሉ ትውልድ፤ ወእምኔሆሙ አንሰ ገብርኪ ዋሕድ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ዑራኤል ለሔኖክ ዘአርአዮ ትእምርተ አምሳልኪ ቤተ ነድ ትእምርተ አምሳልኪ/2/
ኩሉ ትውልድ ያስበጽዑኪ ድንግል በከመ ተነበይኪ/2/
ዚቅ፦
በቃለ ኃይሉ ዘይፌትት በረደ ድንግል በከርሣ አግመረት ነድ፤እምግርማ ዕበይ ሙሴ ዘርእደ፣እሞ ወላዲቱ ኮነቶ ገሃደ
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ዑራኤል፦
ሰላም ለኅንብርትከ ወለሐቔከ ዘቀነተ፣ሰይፈ በቀል ውዑይ እንተ ይሰድድ አጋንንተ፣ ዑራኤል አስተበቋህ እምሀበ ፈጣሪ ምህረተ፤ከመ ያዝንም ውስተ ምድርነ ዝናመ ተሣህሎ ህይወተ፤ ወዘርዐ ገርኅትነ ያሥምር ለይኩን ሲሲተ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ከመ ያዝንም ውስተ ምድርነ ዝናመ ተሣህሎ ህይወተ/2/
"እምኀበ ፈጣሪ ምህረተ"/2/ አስተበቋህ ዑራኤል/2/
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
ሰአል ለነ ዑራኤል ከመ ያዝንም ለነ ዝናመ ምሕረት እምነቅዓ ሕይወት ፤ዘእፀርዎ ሰቃልያን፤በጎልጎታ መካን ፤ሰትዩ ሕዝበ ክርስቲያን፤ስቴ ዘበአማን
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ሰአል ለነ ሊቀ መላእክት ኀበ እግዚአብሔር/2/
ከመ ያዝንም ለነ ዝናመ ምሕረት ዝናመ ምሕረት/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፣እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፣ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ፣ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፣ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ፦
ብፅዕት ይዕቲ ማርያም ቅድስት፤በብሩህ ደመና ዘከለላ መልዐክ በቃሉ ተናገራ፤ሐዳስዩ ጣዕዋ በሀኪ ማርያም እንተ እግዚእ ኃረያ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
"ብፅዕት ይዕቲ"/2/ ማርያም ቅድስት ይዕቲ/2/
በብሩህ ደመና ዘከለላ በቃሉ ተናገራ መልአክ/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ማርያም ፦
ሰላም ለቃልኪ እምአስካለ ወይን ጥዑመ፤ወእምድምፀ ናቢለስ አዳም ዘያረስዖ ለሕማም፤ማርያም ድንግል ዘብርሀነ ህይወት ተቋም፤እመ ተሀውከ በላዕሌየ በማዕበለ ዝንቱ አለም፤ከመ ያረምም ገሥጽዮ መሐሪት እም
@EOTCW
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ፣ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን፤አርእዮ ለሙሴ ግብራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ይእቲ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት/2/
ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን/2/
@EOTCW
ዚቅ(ዓዲ)፦
ዘካርያስ ካህን ተቋም ዘወርቅ፤እንተ ውስቴታ ማኅቶት ፀዳል፤ናስተፅዕ እንዘ ንብል ግርምተ ድንግል፤ሐዳሰ ሐመር ዘኢቀርባ ማዕበል፤አማን ዘዳዊት ፀምር፤ጽዋዓ ሕይወት ጽዋዓ መድኃኒት፤ ተውኅበ ላቲ በዕደ መላዕክት
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ናስተበፅዕ እንዘ ንብል ግርምት ድንግል አማን ሐዳሰ ሐመር ዘዳዊት ፀምር/2/
ተውኅበ ላቲ ጽዋዓ መድኃኒት በዕደ መላዕክት/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ማርያም፦
ሰላም ለአጻብዕኪ እምዕራኃ እዴኪ እለ ሰረጻ፤እም ኆልቁ ሠላስ ወስብዕ እንዘ ኢየሐፃ፤ ማርያም ድንግል ደብረ ኤልያስ ነቢየ ፋፃ፤ዕቀበኒ በረድኤትኪ እምነ አርዌ ዘኆፃ፤ህይንተ ሰናይ ለሰብዕ ዘይሁብ ዐመፃ
@EOTCW
ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል፤ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነብየ እስራኤል፤ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቦና ዘአስተርእዮ ዑራኤል
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ፦
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል፤ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነብየ/2/
ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቦና ዘአስተርእዮ ዑራኤል/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክአ ማርያም፦
ሰላም ለሐቔኪ በትረ ሌዋዊ ሣውዕ፤ዘኢሐፀነኪ ጠል ወዘኢሰቀየኪ ነቅዕ፤ማርያም ድንግል እግዝእተ መላዕክት ወሰብዕ፤ሰድኒ ብሔረ ፍግዕ በትንባሌኪ ባቑዕ፤ምስለ ኅሩያንኪ ደርገ አሀሉ በስንዕ
@EOTCW
ዚቅ፦
ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር ጻድቃን ይበውዑ ውስቴታ፤መላእክት ይኬልልዋ፤ላዕሌሃ ኃደረ ቃለአብ፤መላእክት ወሊቃነ መላእክት ይትለአክዋ፤እለ ይገብሩ መሥዋዕተ ዘበሕጉ
@EOTCW
ዚቅ(ዓዲ)፦
ለኪ ይደሉ ክብር ወስብሐተ ስግደት፤ እምኀበ ሰብዕ ወመላዕክት
@EOTCW
ወረብ፦
ለኪ ይደሉ ክብር ወስብሐተ ወስግደት ለኪ ይደሉ/2/
እምኀበ መላዕክት ወሰብዕ እምኀበ መላዕክት/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክአ ማርያም፦
ሰላም ዕብል ለዘዚያኪ ሰኮና፤ዘኢድኅፀ በውስተ ፍና፤ማርያም ድንግል ትእምርተ ኪዳን ቀስተ ደመና፤አዕምዝኒ በዕፍረትኪ ወጸግወኒ ጥኢና፤በከመ ትገብር እም ለንዑስ ሕፃና
@Eotcw
ዚቅ፦
እሰይም ቀስትየ በውስተ ደመና፤ እዜክር ኪዳንየ ይቤ እግዚአብሔር ፤ዘመሐልኩ ላቲ ለማርያም እምየ፤እሁብ ዘርዓ ወማዕረረ፣በረከት ፍሬሀ ለምድር
@Eotcw
@Eotcw
ወረብ፦
እዜክር ኪዳንየ ዘመሐልኩ ላቲ ለማርያም ይቤ እግዚአብሔር
እሰይም "ቀስትየ በውስተ ደመና" /2/እሰይም/2/
@EOTCW
@EOTCW
መልክአ ማርያም፦
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ።
@Eotcw
ዚቅ፦
እግዝእትየ ለአብርሃም ገራኅቱ፤ለሙሴ እህቱ ለዳዊት ወለቱ፤ዕንቁ ክቡር ውስቴታ የሐቱ፤ጼና አልባሲሃ አፈዋት ቦቱ
@Eotcw
ምልጣን፦
በብሩህ ደመና ዘከለላ፤በሐኪ ማርያም እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፤እንተ እምአፉሃ ይወጽእ ቃለ ጽድቅ
@Eotcw
@Eotcw
ወረብ፦
በብሩህ ደመና "ዘከለላ"/2/በብሩህ ደመና/2/
በሐኪ ማርያም እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት
@Eotcw
እስመ ለዓለም፦
ጾላፅኒ ሐሠረ ይመስሎ ወኩናትኒ ኢይክል አሕመምቶ፤ጻድቅ ብእሲ ዘይሐዊክል በፈጣሪሁ መራጸ አሕዛብ ኢይክሉ ዐቢየቶ፤ማ፦ ወረዋድያን ኢይኄስዎ ጻድቅ ብእሲ እዕገት ያመስጥ
@Eotcw
@Eotcw
አመላለስ፦
ወረዋድያን ኢይኄስዎ/2/
ጻድቅ ብእሲ እምዕገት ያመስጥ/4/
@Eotcw
@Eotcw
ወረብ፦
ጾላፅኒ ሐሠረ ይመስሎ ወኩናትኒ "ኢይክል"/2/ አሕመምቶ/2/
"ጻድቅ ብእሲ"/2/ እምዕገት ያመስጥ/2/
https://t.me/Eotcw
1 161
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️
ስርአተ ዋዜማ ዘሐምሌ ቅዱስ ዑራኤል
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ሃሌታ በ፩፦ ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክት ይትለአኩኪ፣ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት
@EOTCW
@EOTCW
አመላለስ፦
ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት/2/
ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት/4/
@EOTCW
@EOTCW
ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
በ፭፦ ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ ትጉሃን እለ ኢይነውሙ
@EOTCW
@EOTCW
እግዚአብሔር ነግሰ፦
ዑራኤል መልአክ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ወበእንተ ነፍሰ ኵልነ መልአኪየ ይቤሎ እመላእክት ሠምሮ መልአከ ኪዳኑ ለክርስቶስ
@EOTCW
@EOTCW
ይትባረክ፦
ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ ኪያከ አበ ይሴብሑ
@EOTCW
@EOTCW
ሰለስት፦
ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ፤ ሱራፌል በግርማሆሙ፤ ወኪሩቤል በውዳሴሆሙ፤ ኪያከ አበ ይሴብሑ
@EOTCW
@EOTCW
ሰላም፦
በ፮ ሃሌታ፦ሰአሊ ለነ ማርያም፤ሰአሊ ለነ ማርያም፤እሞሙ ለሰማዕት መስተጋድላን፤ ሰአሊ ለነ ማርያም ሰአሊ ለነ ማርያም ወእኅቶሙ ለመላእክት መንፈሳውያን ሰአሊ ለነ ማርያም፤ነሃሉ ወትረ በሰላም
@EOTCW
@EOTCW
አመላለስ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም/2/
ነሃሉ ወትረ በሰላም/4
https://t.me/Eotcw
1 161
ሙ ያነሥኡከ"። መዝ90፥11-12 ወይም መዝ62፥6። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 5፥4-12።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት። እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት። እምግብር ዘየሐውር በጽልመት"። መዝ90፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማር 13፥14-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ። መልካም የቅዱስ ዑራኤል በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ዑራኤል ለዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀት ፅዋ ላጠጣበት ዓመታዊ በዓል፣ ለፋሲለደስ ልጅ ለቅዱስ መቃርስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ፣ ለቅዱስ ለውንትዮስ ሰዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከቅዱስ መርካሎስ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሰላም እብል ለአዕዳዊከ አፃብእ። ወለአጽፋሪሆን ካዕበ ዘበላዕሌሆን ልኩእ። ዑራኤል መርዓዊ አኃዜ ቅዳሴ ካርካዕ። ተጋብኡ ውስተ ጽርሕከ ጽሙዓነ ሕይወት ሰብእ። እምጽዋዓ ዕዝራ ይርዕዩ እምዘለከ ነቅዕ። ትርጉም፦ ቅዱስ ዑራኤል ሆይ ለእጆችህ ጣት ሰላም እላለሁ። በጣቶችህም ሰላም እላለሁ። ቅዱስ ዑራኤል ሆይ የምስጋናን ለውዝ የያዝሆ ነበልባላዊ ሙሽራ እንደመሆንህ ከአንተ ዘንድ ከመነጭ ዕዝራ ከጠጣው ጽዋ ጠጥተው ይረኩ ዘንድ። ማየ ሕይወትን የተጠሙ ሰዎች ሁሉ ወደአዳራሽ ይሰብሰባሉ። መልክአ ቅዱስ ዑራኤል።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ፦ ይህም ሰማዕት የጭፍሮች አለቃ የሆነ የፋሲለደስ ልጅ ነው። ይህንንም ቅዱስ አማልክትን እርሱ እንደማያመልክ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ዘንድ ወነጀሉት ንጉሥም ወደ እስክንድርያ ወስደው በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።
እርሱም ወላጆቹን በተሰናበታቸው ጊዜ ለድኆችና ለችግረኞች እንዲአስቡ አደራ አላቸው። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሔደ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም ተገልጾለት አጽናናው የሚደርስበትንም ነገረው። ወደ እስክንድርያ ከተማም በደረሰ ጊዜ በመኰንን ኅርማኖስ ፊት ቆመ መኰንኑም የጭፍሮች አለቃ የፋሲለደስ ልጅ እንደሆነ አውቆ ብዙ አባበለው ለመነውም እርሱ ግን አልሰማውም ከመልካም ምክሩም አልተመለሰም።
❤ ከዚህም በኋላ ሰውነቱ እስከምትቀልጥ ድረስ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በሥቃይም ውስጥ እያለ ጌታችን የቅዱሳንን ማደሪያዎችንና የአባቱንና የወንድሙን ማደሪያ አሳየው። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ኒቅዮስ ሀገር ሰደደው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ምላሱንና ክንዱን ቆረጡት በጎኖቹም ውስጥ በእሳት ያጋሉአቸውን የብረት ችንካሮች ጨመሩ ጌታችንም አዳነው ያለ ጉዳትም በጤና አስነሣው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በእጆቹ ላይ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከእነርሱም ብዙ ሰዎች የሞተ ሰው ተሸክመው ሊቀብሩ ሲሔዱ አየ። ሁሉም እያዩት ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ማለደ። ስለዚያም ምውት ተነሥቶ ያየውን ይነግራቸው ዘንድ ለመነ። ወዲያውኑም ያ ምውት ተነሥቶ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የሁሉ ጌታ እንደሆነ ተናገረ። ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ብዙ አሕዛብ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ መኰንኑም ተቆጥቶ ያመኑትን ራሳቸውን አስቆረጠ ሰማዕታትም ሆነው የሰማዕታትን አክሊል ተቀበሉ።
❤ በዚያም የእንዴናው ገዥ አርያኖስ ነበረ በተመለሰ ጊዜም ቅዱስ መቃርስን ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ ሀገረ ሰጥኑፍም በደረሰ ጊዜ መርከቢቱ ቆመች የማትንቀሳቀስም ሆነች እነሆ ጌታችንም ለእርሱ ተገልጦ ተጋድሎውን በዚያ እንደሚፈጽም ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ። ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖታትን ቤቶች እንዲዘጉ አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲከፍቱ አዘዘ። ያን ጊዜም ስሙ አውሎጊዮስ የሚባል ምእመን መኰንን አብያተ ክርስቲያናትን ሊሠራ ጀመረ። ቅዱስ መቃርስም ተገለጠለትና ሥጋው ያለበትን ነገረው። መኰንኑም ወደ አመለከተው ቦታ ሔዶ የቅዱስ መቃርዮስን ሥጋ አገኘ ከዚያም ወሰደው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረ። ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ለውንትዮስ፦ ይህም ቅዱስ ክርስቲያን ከሀድያን ከሆኑ ሠራዊት ጋር ይኖር ነበር ሀገሩም ጠራብሎስ ነው መልኩም ያማረ በገድሉም ፍጹም የሆነ ነበር። አምላክ ያስጻፋቸው መጻሕፍትንም ያነብ ነበር። ይልቁንም የዳዊትን መዝሙር ሁልጊዜ ያነብ ነበር። ባልንጀሮቹ ለሆኑ ወታደሮችም ያስተምራቸው ይመክራቸውም ነበር። እግዚአብሔርንም እንዲፈሩ ያስገነዝባቸው ነበር። የማይጠቅሙ የረከሱ የአማልክትንም ሸክም ከትከሻችሁ ጣሉ ይላቸው ነበር። ከስሕተትም ተመልሰው ክብር ይግባውና በጌታችን ያመኑ አሉ። ከእነርሱም ወደ መኰንኑ ሒደው "ለውንትዮስ አማልክትን አቃለላቸው ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው ይላል" ብለው የከሰሱት አሉ።
❤ መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀርቦ ጠየቀው እርሱ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስን እንደሚያመልከው በመኰንኑ ፊት ታመነ ቅዱስ ጳውሎስ "ከፈጣሪዬ ከክርስቶስ ማን ይለየኛል እንዳለ ከታናሽነቴ ጀምሮ በፍጹም ልቡናዬ አመልከዋሁ ለእርሱም እሰግዳለሁ" አለው። መኰንኑም እጆቹንና እግሮቹን አሥረው በወህኒ ቤት ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። በማግሥቱም መኰንኑ አቅርቦ እንዲህ አለው "በምን ኃይል የንጉሥን ትእዛዝ ደፍረህ ትተላለፋለህ ሰዎችንም አማልክትን ከማምለክ በምን ኃይል ትመልሳቸዋለህ" ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት። "በእውነት ሰዎች ሁሉ ክብር ይግባውና ወደጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት እንዲገቡ እኔ እሻለሁ አንተም ስሕተትህን ትተህ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስን ብታመልከው የረከሱ አማልክትንም ማምለክ ብትተው የዘለዓለም መንግሥትን በወረስህ ነበር"። ይህንንም በሰማ ጊዜ መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስም ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እርሱም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ያመሰግነው ጀመረ።
❤ ከወታደሮችም አንዱ አዘነለትና በጆሮው አሾከሾከ "እኔ ስለአንተ አዝናለሁ ጉልምስናህንም ላድን እወዳለሁ አንተ ለአማልክትም እንደምትሠዋ ለመኰንኑ አንዲት ቃልን ብቻ ተናገር እኔም እዋስሃለሁ" አለው። ቅዱሱም ሰይጣን ከኋላዬ ሒድ ብሎ ገሠጸው። መኰንኑም ጭካኔውን አይቶ ሥጋው እስከ ሚቆራረጥ ደሙም እንደ ውኃ በምድር ላይ እስኪፈስ ድረስ ሥቃዩን እጥፍ ድርብ አደረገበት።
❤ ከዚህም በኋላ በውኃ እንዲዘፍቁት በእግሩም እንዲጐትቱትና በወህኒ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በዚያም ነፍሱን አሳለፈ ገድሉንም ፈጸመ። የምታምን ሀብታም ሴት መጥታ ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥታ የቅዱሱን ሥጋ ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው የወርቅ ሣጥንም አሠርታ በውስጡ አኖረችው። ሥዕሉንም አሣለች በፊቱም ሁልጊዜ የሚያበራ ፋና አኖረች። ለዚችም ሴት ቅዱሱ ያደረገላት የድካም ዋጋዋ ሰኔ አንድ ቀን ተጽፎ አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንትዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ፦ 22 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ለጠራብሎስ ማኅቶት። ለውንትዮስ ፈጻሚ ሥቃይ ስምዕ በበፆታ። እንዘ ትገብር ለበድንከ ዐራዘ ወርቅ ትርሲታ። ነጺረከ ዘንተ ብዙኅ አፍቅሮታ። ውስተ ቤተ ሞቅሕ ሮጽከ ታድኅኖ ለምታ። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 22።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ። ከመ ይዕቀቡከ በኲሉ ፍናዊከ። ወበእደዊሆ
1 161
ማይፈርስበት አቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ገዳም መላእክት ወስደው እንዳስቀመጡትና በዚያም እንደታየ ይናገራሉ፡፡ ሰሜን ሸዋ ሚዳ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው በአቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ውስጥ የቅዳሱኑ አጽም ሳይፈርስና ሳይበሰብስ የአንገት ክራቸው ራሱ ሳይበጠስ እንደዛው እንደነበሩ ስለሚገኝ ቦታውም እጅግ ትልቅ የቃልኪዳን ቦታ ስለሆነ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም በዚህ በጨረሻው ሀሳብ ይስማማል፡፡
❤ ሰማያዊ ክብርን የሚያስገኝ አኩሪ ገድል በመፈጸም የቤተክርስቲያን ታላቅ አለኝታ አባትና መሪ የሆኑት የዘመናችንን ታላቅ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን ትውልዱ የግድ ሊያስባቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (united nations) አቡነ ዼጥሮስን "የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት" ወይም በፈረንጅኛው አፍ (MARTYR OF THE MILLENIUM) በሚል መጠሪያ ሰይሟቸዋል።
❤ ላልተነገረላቸውና ላልተዘመረላቸው ለእኚህ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያናችን ድንቅ አባት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም እኚህን ሰማዕት "አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ" ተብለው እንዲጠሩ ወስኗል፡፡ በስማቸውም መቅደስ እንዲታነጽ ፈቅዶ በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረት (ኢሳ 56፡4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራ መታሰቢያ አቁማላቸዋለች፡፡ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም በስማቸው የተሰየመው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና መታሰቢያ ሐውልታቸው ሲሠራ የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ጭምር ለግንባታ የሚሆን አሸዋ ከመርዳት አንስቶ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ድንኳን እስከመትከል ተሳትፈዋል፡፡ በገንዘብም በጉልበትም ተባብረዋል፡፡ ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የአባታችንን እጅግ አኩሪ ታሪክ ሲያዘክራቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም በአ.አ መሐል ከተማ ላይ ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ምዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ጸዋል፡- "ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድ የተሰየሙት ዳኞቸ ሦሰት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንቶች ናቸው፤ መካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡
❤ የቀረበባቸውም ወንጀል "ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል" የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም "ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?" ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፡- "አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ" አሉ፡፡ "ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ፡- "አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን" ብለው አወገዙ፡፡
❤ ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍጥነት ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ እርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ፡፡ ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣሊያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ በዚህን ጊዜ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊው ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡ የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው፡፡ የሀገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒያ እውነተኛ ጳጳስ እንዲገደሉ ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይመታ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሄድ ከመካነ ፍትሑ ዐሥር ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ "ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?" ሲል ጠየቃቸው፡፡ "ይህ ያንተ ሥራ ነው" ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡
❤ ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ፡፡ ከዚያም በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተ ጀመርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ፣ ወዲያው አዛዡ "ተኩስ!" በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡
❤ ብፁዕነታቸው የተገደሉበት ቦታ መሐል አዲስ አበባ ላይ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው" በማለት የጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛው ፖጃሌ ስለ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ "አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?" ሲል በወቅቱ አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ በቦታው ላይ በአካል በመገኘት ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩትን ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውውም የሚከተለውን ተናረዋል፡- "አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት፡፡ ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
❤ ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ፡፡ ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት "በዚህ ቄስ መገደልኮ ሕዝቡ ተደስቷል" አለኝ፡፡ "እንዴት?" ብለው "አላየህም ሲያጨበጭብ?" አለኝ፡፡ "ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል" አልኩት፡፡ "እንዴት?" ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡ "ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ" ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ሰዓታቸውንም ጭምር አሳየኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተበስቷል፡፡ መስቀሉም ልክ በመሐሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል፡፡ የኪስ ሰዓታቸውንም እንዳየሁት እንዲሁ ጥይት በስቶታል" ብለው በወቅቱ የተመለከቱትን መስክረዋል፡፡
❤ ብፁዕ አባታችን በአደባባይ በሕዝብ ፊት የሰማዕትነት ጽዋቸውን ሲቀበሉ ከሕዝቡ ጋር ሆና ትመለከት የነበረች አንዲት ከድጃ የምትባል እስላም ሴት ማንም ሰው ያላየውን ታላቅ ነገር እርሷ ተመልክታለች፤ ይኸውም አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ሲቀዳጁ ተመልክታ በዚያው እርሷም "የእኚህን አባት ሃይማኖት እከተላለሁ" ብላ በመጠመቅ ክርስቲያን ሆናለች፡፡
❤ የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ሰማዕቱን አቡነ ጴጥሮስን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ ቀብራቸው በምሥጢር መፈጸሙን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምሥጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም "ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምሥጢር ቀበሯቸው" ከሚል ከመላምት ያለፈ ነገር ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ "ፉሪ ለቡ" ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው "ሙኒሳ ጉብታ" ላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ እየተነገረ ይገኛል፡፡
❤ እንዲሁም የአቡነ ጴጥሮስን ሥጋ በተመለከተ ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአ.አ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር እንዲቀበር መደረጉ በትንሣኤ መጽሔት ቁ.58 1978 ዓ.ም ላይ የተገለጠ ቢሆንም ነገር ግን አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ቅዱሳን መላእክት የጻድቃንን በድን እያመጡ ወደሚያስቀምጡበትና በውስጡ የሚቀመጥ አስክሬን ወደ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን የ20ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕት ለታላቁ ለሆኑት ለእውነተኛ ለኢትዮጲያዊው ጻድቅ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ቀን መታሰቢያ በዓልና ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል የካህናት ማሰልጠኛን ለመሰረቱን ለብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዕረፍት ቀን መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።
❤ ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፦ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር፡፡ "አለቃ ተጠምቀ" የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው "ኀይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ" ብለዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል፡፡
❤ ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መመህር ኀይለ ማርያም ይባሉ ነበር፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔው አውድማ ጎጃም በመሄድ በሸዋራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል፡፡ የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሄደው ተምረዋል፡፡ በመቀጠልም ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር ይመግቡ ወደነበሩት ወደ ሊቁ አካለ ወልድ ዘንድ በመሄድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በሚገባ አሒዱ፡፡
❤ ከዚህ በኋላ በ1900 ዓ.ም ወሎ አምሐራ ሳይንት ሄደው በምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ፡፡ በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ፡፡ ከዚያም መምህርነት ተሹመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ሄደው ለ6 ዓመታት ካስተማሩ በኋላ በ1916 ዓ.ም እንደገና በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት ተሹመው ለ3 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በ1919 ዓ.ም ወደ አ.አ በመምጣት የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የንስሓ አባት ሆኑ፡፡
❤ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በራሷ ተወላጅ ጳጳሳት ልጆቿ እንድትመራ ከ1600 ዓመታት በኋላ ስለተፈቀደላት ከዚህ በኋላ በሃይማኖታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ደጋግ አባቶች ሲመረጡ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን ጳጳስ ስትሾም አቡነ ጴጥሮስ ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ፡፡ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባታችን "አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቀ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ" ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ፡፡
❤ ብፁዕ አባታችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ቅድስት ሀገራችን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር፡፡ በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስም ይህንን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ማይጨው ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው በመርዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ አ.አ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል፡፡
❤ በደብረ ሊባኖስ ጫካዎች ውስጥ መሽጎ የነበረው የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር እና በሸንኮራ በኩል መሽጎ የነበረው የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር እንደሁም በምዕራብ ይመራ ከነበረው የእነ ደጃዝማች አባ ነፍሶ ጦር ሦስቱም በአንድ ጊዜ ወደ መሐል አ.አ በመግት አ.አ ላይ መሽጎ የነበረውን ፋሽስትን ለመውጋት ታቅዶ የነበረው ዕቅድ በመረጃ ክፍተት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ፡፡ በተለያየ ጊዜ መሐል አ.አ እየደረሱ ማለትም በመጀመሪያ የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር ለብቻው በኮተቤ አድጎ የካ ሚካኤል ላይ ሲድርስ ተመቶ ተመለሰ፤ ይሄኛው እንዳለቀ ቀጥሎ የእነ አባ ነፍሶ ጦር በባቡር ጣቢያ መጣሁ ቢልም በጠላት ጦር ድካሚ ተመቶ ተመለሰ፤ መጨረሻ ላይ የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር በእንጦጦ በኩል ቢመጣም እርሱም በጠላት ጦር ተመቶ ተመለሰ፡፡
❤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሦስቱም የአርበኞች ጦር በመረጃ ክፍተት ምክንያት እየተመታ ወደመጣበት ሲመለስ አቡነ ጴጥሮስ አብረው ከአርበኛው ጦር ጋር መመለሱን አልፈለጉትም ይልቁንም "ብችል ጠላት በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት ሆኖ የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሣ አደርገዋለሁ ካልሆነም ደግሞ እዚሁ እሞታለሁ" በማለት አባታችን ከአርበኞቹ ተነጥለው አ.አ ቀሩ፡፡ ይሁን እንጂ ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎች አባታችንን እንዳሰቡት ሊያነቀሳቅሷቸው አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም አባታችን "የሀገሬን ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሰማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል" ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑና የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለሆነው ለራስ ኀይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡት፡፡ እርሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጧቸው፡፡ ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ በሰማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሒደት ኮርየሬ ዴላሴራ የተባለው ጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ፖጃሌ የተባለው ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ በነበረ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰጠውን ፍርድና የተፈጸመውን የግፍ ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር።
❤ "ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ቄርሎስ የተባሉት ግብፃዊ ጳጳስ ቀርበው "ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ እንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም" ሲሉ ለግራዚያኒ ነገሩት፡፡ አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስን ሕይወት ለማትረፍ አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ግራዚያኒ የአቡነ ጴጥሮስ የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብጽ ከአ.አ ውጭ እንኳ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን እንዲፈጸም መመሪያ አስተላላፈ፡፡
❤ ወደ ምሥራቅ አፍሪካው ዜና መዋዕል አዘጋጁ ወደ ፖጃሌ ዘገባ እንመለስና የአቡነ ጴጥሮስን መልካቸውንና ተክለ ቁመናቸውን እንዲህ በማለት ይገል
