fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን ጌታችን ይወደው ለነበረ ከሞቱ በኋላ በአራተኛው ቀን ላስነሳው ለማርያምና ለማርታ ወንድም ለጻድቁ ቅዱስ አልዓዛር ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና ለእስክንድርያ ሠላሳኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ቅዱስ አልዓዛር፦ ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኀኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ። አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ❤ ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ ግንቦት27 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቅ አባት በቅዱስ አልዓዛር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ዮሐንስ፦ ይህም አባት በእስክድርያ ለተሾሙ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ ነው። ደግ የተማረም ነበር። ከልጅነቱም ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ነበር። ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። የትሩፋቱና የዕውቀቱም ዜና በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሹሙት። ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ እግዚአብሔርም በዘመኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን አጸና። ❤ ይህ አባት በተሾመበት ወራት ደግ ምዕመን አንስጣዮስ የሚባል ንጉሥ ነበር። በአንጾኪያም የከበረ አባት አባ ሳዊሮስ ነበር እርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲህ ብሎ በመልእክቱ ውስጥ ጻፈ "ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋህዶው በኋላ እንደ አባቶቻችን እንደ አባ ድሜጥሮስና እንደ አባ ዲዮስቆሮስ እምነት ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለዋወጥ፣ ያለ መለያየትና ያለ መጨመር አንዲት ባሕርይ አለችው"። አባ ዮሐንስም መልእክቱን ተቀበለው ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ተለያይተው የነበሩ። ሕዋሳትም ተመልሰው አንድ ስለ ሆኑ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰገኑት። ❤ ከዚህም በኋላ ለመልእክቱ መልስ አባ ዮሐንስ ለአባ ሳዊሮስ እንዲህ ብሎ ጻፈለት "ይኸውም ስለ መለኮትና ትስብእት የአንድ ባሕርይ ህልውና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ያለ መለያየት፣ ያለ መቀላቀልና ያለ መለወጥ ሁለት ያይደለ የሰውን ባሕርይ ከመለኮቱ ባሕርይ ጋራ አንድ አድርጎ በመዋሐድ ሰው ስለመሆኑ። ጌታችንንም የሚከፋፍሉትን ወይም ተጨመረበት የሚሉትን ወይም ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቀሎ የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚሉትን በመለኮት ባሕርይ መከራ ተቀብለ የሚሉትን አወገዘ። "የቀናች ሃይማኖትስ ይቺ ናት እግዚአብሔር ከእኛ በነሣው ሥጋ ስለ እኛ መከራ እንደ ተቀበለ እናውቃለን እኮን። ይቺም የሚጓዝባት የማይሳሳትባትና የማይደናቀፍባት የሕይወት መንገድ ናት" አለ። ❤ አባ ሳዊሮስም ይቺን የአባ ዮሐንስን መልእክት በአነበባት ጊዜ በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በአንጾኪያ አገርም ሰበከባት ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመካከላቸው ሰላም ፍቅርና ስምምነት ሆነ። ይህም አባት ሕዝቡን እያስተማረ ዐሥራ አንድ ዓመት ኑሮ ከዚህ በኋላ ግንቦት 27 ቀን በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት27 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአልዓዛር ኤጲስቆጶስ ዘተሠይመ። ረቡዐ መዋዕለ ድኅረ በመቃብር ተሐትመ። ኢየሱስ ክርስቶሰ ድኅረ አንሥኦቶ ቀደመ። ምስለ ምውታን እስከ ያነሥኦ ዳግመ። በዛቲ ዕለት አዕረፈ ወኖመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 27። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት። ወመኑ ዘያድኅና ለነፍሱ እምእደ ሲኦል። አይቴ ውእቱ ዘትካት ሣህልከ እግዚኦ"። መዝ 88፥48-49። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 23፥1-27። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 6፥1-12፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አልዓዛር የዕረፍት በዓልና የበዓለ ዕርገቱ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለጽንሰትከ እማኅፀነ ቅድስት ዮስቴና። በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና። ሀብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና። መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቡና። አፍቅሮ ቢጽ እኅሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና"። ትርጉም፦ ምግባሩ የተወደደ የሆነ የጻድቅ ባህታዊ ብሥራት ለተጸነስክበት የእናትህ የቅድስት ዮስቴና ማህፀን በእውነት ሰላምታ ይገባል። ጻድቅ አባቴ ሀብተ ማርያም ሆይ እንደዮና ልጅ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ የእውነት ስራን አስተምረኝ አይነልቡናየንም አብራልኝ። ፍጽምት ከሆነች ትሕትና ጋር ባልጀራየን እንደራሴ እወድ ዘንድ። መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም ባሕሩን በዚያ ዐውሎ ነፋስ እንደ ቀድሞው መለሰው በየዓመቱም እንዲህ ይሆናል ሁልጊዜ እስከ ዛሬ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለቶማስ እንተ ደለዎ ይግሥሦ። ለርጉዝ በግዕ ድኅረ ተንሥአ ደቂሶ። ለአንቅሖ ሙታን ሰብእ ወነፍሰ ድውያን ለፈውሶ። አንሶሰወ ውስተ ኵለሄ ወነገደ መርሶ። አምሳለ ፅፍነት እንዘ ይጸውር ማዕሶ"። አርከ ሥሉስ(አርኬ) የግንቦት 26። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ18፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 20፥24-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘእምኀቤከ ረድኤቱ እግዚኦ። ወዘይሔሊ በልቡ ዘበላዕሉ። ውስተ ቈላተ ብካይ ብሔር ኀበ ሠራዕኮሙ"። መዝ 83፥5-6። የሚነበቡቱ መልዕክታት ሮሜ 8፥22-31፣ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 14፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሀብተ ማርያምና የአቡነ ኢየሱስ ሞዐ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ለሆነው ዲዲሞስ ለሚባለው ለከበረ ለሐዋርያው ለቅዱስ ቶማስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን አልፋውስና ከዘካርያስ፣ ከሉክዮስና ከቅድስት አርሶንያም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ፦ እርሱም በሕንደኬ አገር ሉክዮስ ለሚባል ለአንድ መኰንን ራሱን ባሪያ አደረገ መኰንኑም የንጉሥ ወዳጅ ነው ቅዱስ ቶማስንም "የምታውቀው ሙያህ ምንድነው?" አለው። ቅዱስ ቶማስም "እኔ ግንበኛ ነኝ ምኵራቦችን፣ አዳራሾችን እሠራለሁ ደግሞ ጠራቢ ነኝ ሞፈሮችን፣ ወንበሮችንም ሌሎች ዕቃዎችንም እሠራለሁ። ደግሞ ጥበበኛ፣ ባለ መድኃኃነኝ በሽተኛውን ሁሉ አድናለሁ" አለ። መኰንኑም ነገሩን በሰማ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኘው "ለንጉሥ ጠቃሚ የሆነ ባሪያ አገኘሁ" አለ። ❤ በዚያን ጊዜ ለቅዱስ ቶማስ ገንዘብ ሰጥቶ ቤተ መንግሥትም እንዲሠራ አዝዞ መኰንኑ ወደ ንጉሥ ሔደ። እርሱ ቅዱስ ቶማስም የመኰንኑን ሚስት የእግዚአብሔርን ሕግ ያስተምራት ጀመር በፊቷም ተአምራት አደረገ። እርሷም በክብር ባለቤት ጌታችን አመነች ከርሷ ጋራም ብዙዎች አመኑ ንጹሕናዋን በመጠበቅ እንትጸና አዘዛት የሃይማኖትም ምሥጢር እንድታስተውል አደረጋት። መኰንኑም ከንጉሥ ዘንድ ሲመለስ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ያደረገውን አየ። ጠራውና "አንተ ክፉ ባሪያ እሠራቸዋለሁ ያልካቸው በጎ ሥራዎች ወዴት ናቸው" አለው። ቅዱስ ቶማስም "አልዋሽሁም ምኵራቦችና አዳራሾች የሠራኋቸው ለሰማያዊ ንጉሥ ማደሪያ የሆኑ እሊህ የሰዎች ነፍሳት ናቸው። የጠረብኳቸው ሞፈሮችም የኃጢአትን እሾህና አሜከላ ከሰዎች ልብ የሚነቅሉና አርሰው የሚያለሰልሱ እነርሱ የወንጌል ትምህርቶች ናቸው፤ ጥበብ ያልሁትም አንድ ነው የሚገድል የኃጢአትን መርዝ አጥፍቶ የሚፈውስ የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ቅዱስ ቶማስንም በምድር ላይ እንዲአስተኙት በአራት ማዕዘንም ችካል ተክለው እጆቹንና እግሮቹን በገመድ ወጥረው አሥረው ቆዳውን እንዲገፉ ጨውና ኮምጣጤ በተገፈፈው ሥጋው ላይ እንዲደፉበት አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ ይሁን ሁሉ አደረጉበት እርሱም ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትዕግሥት ይህን ሥቃይ ተቀበለ። ❤ የመኰንኑም ሚስት ቆዳውን ሲገፉት በቤቷ ሰገነት መስኮት በአየችው ጊዜ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች መኰንኑም እጅግ አዘነ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ቅዱስ ቶማስን አጸናው ወዲያውኑ ተነሣ ከላዩ የገፈፉትንም ቆዳ ወስዶ ከመኰንኑ ሚስት በድን ላይ ጥሎ "አርሶንያ ሆይ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሺ" አለ። ወዲያውኑ ዐይኗን ተለጠች ፈጥና ተነሥታም ለሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ሰገደችለት ሉክዮስም አይቶ ደነገጠ። ለሐዋርያውም ሰገደለት ይቅርታም ያደርግለት ዘንድ በመለማመጥ ለመነው። ቅዱስ ቶማስም "በጌታችንን ካመንክ ትድናለህ" አለው እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። እንዲሁም የአገር ሰዎች ሁሉም አመኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው። ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው። እያስተማራቸውና በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ከእርሳቸው ዘንድ ኖረ። ደዌ ያለበትንም በላዩ ቆዳውን ሲያኖርበት ወዲያው ይድናል። ❤ ከዚህ በኋላም ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ቀንጦርያ ከሚባል አገር ገባ ሲገባም አንድ ሽማግሌ ሰው መራራ ልቅሶ እያለቀሰ አገኘ። ቅዱስ ቶማስም "እንዲህ ለምን ታለቅሳለህ" አለው። ሽማግሌውም "ሰባት ልጆች ነበሩኝ በሐሰት ነገር ንጉሥ ገደለብኝ። ደግሞም ዕዳ አለብኝ ከነእርሱ አንዱ እንኳ ቀርቶ ቢሆን ለኑሮዬ በተራዳኝ ነበር" ብሎ መለሰለት። ቅዱስ ቶማስም ሰምቶ ቆዳውን ሰጠውና "ይህን ወስደህ በልጆችህ መቃብር ላይ አኑር" አለው። እንዳዘዘውም በአደረገ ጊዜ ሰባቱ ሁሉ ልጆቹ ሌሎቹም ስምንት ወንዶች በዚያ አስቀድሞ ተቀብረው የነበሩ በአንድነት ተነሡ። ይቺም ተአምር በአገሮች ሁሉ ተሰማች የጣዖታት ካህናትም ተቆጥተው በደንጊያ ሊወግሩት ጀመሩ። ያን ጊዜ እጆቻቸው ደረቁ "የቸር አምላክ ሐዋርያ ሆይ ከፈጣሪህ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አመን። ማረን ይቅርም በለን" እያሉ ጮኹ ያን ጊዜም አዳናቸው የቀናች ሃይማኖትንም አስተምሮአቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው። ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመላቸው። ❤ ከዚህ በኋላም ወደ አቴና ወደ መቄዶንያ ሔዶ በውስጥዋ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ሰበከ ስለእርሱም ነገሥታቱና መኳንንቱ ሰሙ። ይዘውም አሠሩት የንጉሡም ሚስት ከልጅዋ ጋራ ወደ ወህኒ ቤት እየመጣች የቅዱስ ቶማስን ትምህርቱን ትሰማ ነበር። ብዙዎችም በሥውር እየመጡ ያስተምራቸው ነበር በክብር ባለቤት ጌታችንም አመኑ። ንሡም ስለ ሚስቱ ተቆጣ ነገር ግን በሕዝብ መካከል መግደልን ፈራ። ከከተማውም ውጭ ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስን አውጥቶ እስከሚሞትም በጦር እንዲወጉት አራት ወታደሮችን አዘዘ። የንጉሥ ልጅም ቁሞ ይመለከት ነበር። የአገር ሰዎችም በአወቁ ጊዜ ከወታደሮች እጅ ሊያስጥሉት ወጡ ግን ሙቶ አገኙት አንሥተው ገንዘው ከነገሥታት መቃብር በአንዱ አኖሩት። ❤ በንጉሡ ልጅም ሰይጣን ተጭኖበት የሚያንከባልለው ሆነ ከልብሱም ጥቂት ወስደው በንጉሡ ልጅ አንገት ላይ ሊአንጠለጥሉለት ወደ ቅዱስ ቶማስ ሥጋ መጡ መቃብሩንም በከፈቱ ጊዜ አላገኙትም። ጌታችን ከዚያ አፍልሶታልና ከመቃብሩ አፈርም በእምነት ወስደው በንጉሡ ልጅ አንገት ላይ አንጠለጠሉ ያን ጊዜ ዳነ። ንጉሡም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም ለብዙዎች ተገለጸላቸው እርሱ ሕያው እንደ ሆነ ጌታችንም በመንግሥቱ ውስጥ እንደተቀበለው ነገራቸው። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አዘዛቸው። የሐዋርያ ቅዱስ ቶማስም በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ ዳግመኛም ከተአምራቶቹ አንዱን እንጽፋለን። አንድ ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርን የሚፈራ በግብጽ አገር ይነግድም ዘንድ ወደ ሕንደኬ ሔደ። ግንቦት ሃያ ስድስትም ሲሆን በሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ በዓል ብዙ ሕዝቦችን የቅዱስ ቶማስ እጅ በውስጡ በምትኖርበት ባሕር ዳር ተሰብስበው አያቸው። በዚያንም ጊዜም የባሕሩን ውኃ ጨርሶ እስከ ሚአስወግደው ድረስ ጥልቅ ነፋስ ተነሣ ሰዎችም ሁሉ በደሴት ወደአለች ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሲጸልዩ አደሩ። በማግሥቱም በቅዱስ ቶማስ በዓል ቅዱስ ቊርባንን ለማቀበል ቀደሱ። የሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ እጅ ያለ ጥፋት ሕይወት ያላት ስለሆነች የጌታችንን ሥጋ በላይዋ አደረጉ። ❤ በቅዱስ ሐዋርያ ቶማስ እጅም ቅዱስ ቊርባንን ሊቀበሉ አንዱም አንዱ ከሕዝቡ መጡ። አንድ ሕዝባዊ ሰውም ሊቀበል መጥቶ የቅዱስ ቶማስ መሐል እጁን ጨበጠ። ያን ጊዜ ተሠወረች ሁሉም "ኪርያላይሶን" እያሉ በጠጮህ ብዙ ጊዜ ረጅም ጸሎት ጸለዩ። ከዚህ በኋላም የቅዱስ ቶማስ መሐል እጁ ተገለጠችና ያሰው ቅዱስ ቊርባንን ተቀበለ። ሕዝቡም ሁሉ ተቀበሉ ከዚህም በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ወደ ቤታቸው በሰላም ገቡ።

photo content

photo content

photo content

photo content

+ + + ❤ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ፦ አገራቸው ጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ሲና ዳኅና በሚባል ቦታ ነሐሴ 26 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 26 ቀን 1210 ዓ.ም ከአባታቸው ከቅዱስ ዘክርስቶስና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ክብራ ተወለዱ፡፡ የተወለዱትም በቅዱስ ነአኲቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ❤ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የቆብ አባት ሲሆኑ ታላቁን ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገዳም የቆረቆሩ ደገኛ አባት ናቸው፡፡ ዕድሜያቸው 30 ዓመት እስከሚደርስ ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ1240 ዓ.ም ይህንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያጠኑ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ እጅ ምንኲስናን በ1247 ዓ.ም ተቀበሉ፡፡ ❤ አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ "የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ" አላቸው፡፡ አባታችንም "ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ?" በማለት መልአኩን ቢጠይቁት "ተነሥ! ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ" አላቸው፡፡ አባ ኢየሱስ ሞዐ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበዓታቸው ተነሥተው ተከተሉት፡፡ የብዙ ወራት መንገድ የሆነውን ጐዳናም በስድስት ሰዓት አደረሳቸው፡፡ በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው የቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ፡፡ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ከመግባታቸው በፊት ለ 6 ወራት ያህል በቅዱሳን በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡ ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፡፡ በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበው ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ፡፡ ❤ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሠረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብፃዊ ጻድቅ ናቸው፡፡ ሐይቅን አባ ሰላማ ካልዕና ዐፄ ድል ነአድ በ862 ዓ.ም ነው የቆረቆሩት። ገዳሙን ካቀኑት በኋላ "የማንን ታቦት እናስገባ?" ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ የቅዱስ እስጢፋኖስንና የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ታቦት አገኙ፡፡ በላዩም ላይ "ይህንን ታቦት በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍ አገኙ፡፡ ይህ ከሆነ ከ 400 ዘመን በኋላ ነው አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ወደዚህ ቦታ የመጡት፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ለ52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ሥራቸውን እየሠሩ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ❤ አባ ኢየሱስ ሞዐ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመገልበጥና በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ በዚሁ ገዳም ውስጥ የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ትምህርት ቤት በማቋቋም 800 መነኰሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ ሾመው በመላ ሀገራችን እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል፡፡ ከእነዚህም ተማሪዎቻቸው መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ደብረ ሊባኖስ)፣ አቡነ ኂሩተ አምላክ (ጣና ሐይቅ ዳጋ እስጢፋኖስ)፣ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቦረና)፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል (ቦረና)፣ አቡነ ገብረ እንድርያስ (ቦረና)፣ አቡነ ሕዝቅያስ (ቦረና)፣ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዳውንት)፣ አቡነ አሮን (መቄት)፣ አቡነ ተክለ ኢየሱስ ሞዐ (ሐይቅ)፣ አቡነ አላኒቆስ (ትግራይ)፣ አቡነ በግዑ (ሐይቅ)፣ አቡነ ሠረቀ ብርሃን (ሐይቅ)፣ አቡነ ብስጣውሮስ (ሐይቅ)፣ አቡነ ዮሴፍ (ላስታ) ዋና ዋናዎቹና በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ጻደቁን ንጉሥ ዐፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸውና ኮትኩተው ያሳደጉት ጻድቁ አባታችን ናቸው፡፡ ❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ ነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ሐይቁን በእግራቸው ጠቅጥቀው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኵሰዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ እጅግ በጣም ብዙ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ የመጀመሪያው መነኩሴ አባ እንጦንስ ነው፡፡ እንጦንስ መቃርስን፣ መቃርስ ጳኵሚስን፣ ጳኵሚስ ቴዎድሮስን፣ አቡነ አረጋዊንና 8ቱን ቅዱሳን አመነኰሱ፡፡ አቡነ አረጋዊም ወደ ኢትዮጵያ በ460 ዓ.ም መጥተው ክርስቶስ ቤዛን፣ አባ ክርስቶስ ቤዛም መስቀለ ሞዐን፣ መስቀለ ሞዐም አባ ዮሐኒን፣ አባ ዮሐኒም አባ ኢየሱስ ሞዐን፣ አባ ኢየሱም ሞዐም አቡነ ተክለ ሃይማኖትን አመነኰሱ፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ምን ያህል ቀደምትና ባለ ታሪክ አባት እንደሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ❤ በዮዲት ጉዲት እጅጉን ተጐድታ የነበረችው አገራችን ዳግም የወንጌሉ ብርሃን እንዲበራባት ሊቃውንት፣ እንዳይታጡባት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይቆነጻጸሉ፣ መነኰሳት አባቶች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወርደው ገዳማትን እንዲያስፋፉ ያደረጉት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለአገራችን ትልቅ ባለውለታ ናቸው፡፡ በተለይም በሐይቅ እስጢፋኖስ ያፈሯቸውን 800 ሊቃውንት መነኰሳት በመላዋ ኢትዮጵያ በመሰማራታቸው ዛሬ የምናያቸውን አብዛኛዎቹን ገዳማትና ቅዱሳት መጻሕፍት አቆይተውልናል፡፡ አባታችን ለ45 ዓመታት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምን በአበ ምኔትነት እያስተዳደሩ ከቆዩ በኋላ ኅዳር 26 ቀን 1292 ዓ.ም በዕለተ እሑድ ዐርፈዋል፡፡ ከአባታች ከኢየሱስ ሞዐ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ገዳሙን የተሳለመ ሰው ኢየሩሳሌም ጎልጎታን እንደተሳለመ የሚቆጠርለት ሲሆን በገዳሙ ውስጥ የተቀበረ ሰው ወቀሳ የለበትም፡፡ ከአካሉም ላይ ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን ቆርጦ በገዳሙ ክልል ውስጥ የቀበረ ሰው ቢኖር መልአከ ሞትን ፈጽሞ እንደማያይና ገዳሙ የሚገኝበት አካባቢ በእግር ለመጓዝ አስቸጋሪ ቢሆንም ቦታውን የረገጠ እስከ 15 ትውልድ ምሕረትን እንደሚያገኝ ጌታችን በቃልኪዳን አጽንቶታል፡፡ ሌላው ቀብጽያ ገዳምን ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፈዋሹ ጠበል ከጻድቁ አቡነ አሞፅ መቃነ መቃብር ሥር የሚፈልቅ መሆኑ ነው፡፡ ከዋሻው ሥር የተንጠባጠበው ጠበል ወደ ጠንካራ ዓለትነት የሚቀየር ሲሆን እርሱን ለእምነት የተጠቀሙበት ሰዎች ከተለያዩ በሽታዎች ተፈውሰዋል፡፡ በቅርቡም ከ6 ዓመት በፊት በዚህ እምነት የተሻሸች አንዲት ሴት ከዘመኑና መድኃኒት ካልተገኘለት ከHIV በሽታና ከመካንነቷ ተፈውሳ ልጅ ወልዳለች፡፡ ይህ አስደናቂ ቀብጽያ ገዳም ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ቢሆንም ከጊዜና ብዛት ጉዳት ስለደረሰበትና የሚያድሰው አካል ስላላገኘ በአሁኑ ወቅት ሌላ አዲስ ቤተ መቅደስ እየታነጸ ይገኛል፡፡ በቀብጽያ ገዳም ውስጥ 336 ዓመት የሆነው የወይራ ዛፍ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ስውራን የሆኑ ቅዱሳን ሦስት ጊዜ ደወል ሲደውሉበት ተሰምቷል፡፡ ❤ አቡነ አሞፅ በ1592 ግንቦት 26 አርብ ቀን ሲያርፉ ጌታችን ከድንግል እናቱ ጋር ተገልጾላቸው ከላይ ያየናቸውን አስደናቂ ቃልኪዳኖች ከሰጣቸው በኋላ ነፍሳቸውን እመቤታችን አቅፋ አሳረገቻቸው፡፡ ዐፅማቸው ያረፈበትን መካነ መቃብር ታላላቅ ዘንዶዎች ይጠብቁታል፡፡ ጠበላቸውም የፈለቀው ከመቃብራቸው ሥር ነው፡፡ ቦታው በስውራን ስለሚገለገል የከበሮ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን የእጣንም ሽታ ይሸታል፡፡ ከአባታች ከአቡነ አሞፅ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገዳሙ ካሳተመው ስዕል ጀርባ የተገኘ ታሪክ እና ከገድላት አንደበት። + + + ❤ አቡነ ሀብተ ማርያም ልደት፦ " የኢትዮጵያ ንጉሥ እስክንድር በነገሠ በሺህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት ዓመተ ምሕረት ቅዱስ ፍሬ ብሩክ የሚባል አንድ ሰው በዚያች ሀገር ውስጥ ነበር፤ ይኸውም ከከበሩም ሰዎች ተለይቶ ብዙ ገንዘብ ያለው ባለ ጸጋ ነበር። በሕጋዊው ጋብቻ ስሟ ቅድስት ዮስቴና የምትባል ሴት አገባ፤ ይኽችውም ሴት በደግ ሥራ ሁሉ የተሸለመች ያጌጠች ነበረች። ❤ ብዙ ደግቷንና ትሩፋቷን ኋላ እንነግራችኋለን፤ ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕጋዊ ባሏ ጋር በንጽሕ ጋብቻ እግዚአብሔር በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የውሃትንና ትሕትናን ገንዘብ አድርጋ በትግሥት በበጎ ሥነ ምግባር ሁሉ ጸንታ እንደኖረች እነግራችኋለን። ❤ እንዲህ ባለ ሥራ ሳለች መንፈሳዊ ሐሳብ እንዲህ ሲል ተነሳባት፤ "ለአንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሻል የሚል መጣባት፤ ዛሬ የሚያልፍ የሚጠፋ ነውና፤ ጌትነቱ የሚመሰገንበት ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ሌላ ዓለም ይገለጣልና"፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል "ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ በነፍሱ ከተጎዳ ምን ይጠቅመዋል ምን ይረባዋል" እንዳለ። ❤ "ለአንቺ ግን በሰማይ ጸንቶ መኖርና ሁለተኛዋን ሀገር መያዝ ይሻላል" የሚል ሐሳብ መጣባት፤ ይህን ካሰበች በኋላ ፈጥና ተነሥታ በሌሊት ከቤቷ ወጥታ፤ በሀገሯ አንጻር ትይዩ ወደ ሆነው በረሃ ሄደች፣ በውስጡ ከሰው ወገን የማይኖርበት ቦታ መካከሉ ምድረ በዳ ወደ ሆነው በረሃ ደረሰች። ከጅቦች፣ ከነብሮች፣ ከዓሣሞች፣ ከጦጦችና ከዝንጆሮች በስተቀር ምንም ምን የማይኖርበት በረሃ ነበር። ❤ በዚያችም ቦታ ደጃፏ ያልተዘጋች ትንሽ ዋሻ አገኘች ምንም ምንም ሳትናገር ከዋሻው ውስጥ ገባች። በዋሻው ውስጥ ቁሞ በትጋት መዝሙረ ዳዊትን በአንክሮ በተደሞ የሚደግም ክቡር ባሕታዊን አየች፤ ባየችውም ጊዜ ደነገጠች። እርሱም ሴቲቱን ባያት ጊዜ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላዩ ላይ ወረደበት፣ በመስቀል ምልክትን አማተበ። ይህም ቅዱስ ባሕታዊ ፊቱን በአማተበና ስመ እግዚአብሔርንም በጠራ ጊዜ እንዳልሸሸች ስለአየ ይህች ሴት ክርስቲያን መሆኗን አወቀ። ❤ መጀመሪያ ስትገባ የጋኔን ምትሐት መስላው ነበርና፤ ሰው መሆኗን ባወቀና በተረዳ ጊዜ ተቆጣት። "አንቺ ዘማዊት ሴት ምንኵስናየን ታፈርሽ ዘንድ ከየት መጣሽ" አላት። "ወይም ደግሞ ሰይጣን በልብሽ ገብቷልን"። "ጌታዬ እኔስ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ እንጅ አንተ እንደምትለኝ ዘማዊት አይደለሁም" አለችው። "ነገር ግን ቤቴን ንብረቴን ያለኝን ትቼ መጥቻለሁ፣ በዓለም ውስጥ ያለውን ሁሉ ንቄ እመንን ዘንድ እወዳለሁና ስለዚህም ወደዚህ ምድር በዳ መጣሁ። በዚህም ገዳም ወይም በረሃ ሰው እንዳለ አላውቅሁም ነበር፤ ሰውን የሚባሉ አራዊት ብቻ የሚኖሩበት ይመስለኝ ነበር" አለችው። ❤ ይህም ባሕታዊ በትሕትና በፈሪሃ እግዚአብሔር ይህን የሚያስደንቅ መልካም መልስ በመለሰችለት ጊዜ። አንድ ሰዓት ያኽል ካሰበ በኋላ "በፍቅር አንድነት ወደ ቤትሽ ተመለሽ" ብሎ በሰላም ተናገራት። እርሷም "ወደዚህ ቦታ ዳግመኛ አልመጣም እንጅ ካንተ ዘንድ ተለይቼ እሄዳለሁ። ነገር ግን ወደ ቤቴ ተመልሼ አልሄድም። ከገዳማት በአንድ ቦታ መንኵሼ መኖር እወዳለሁ እንጅ" አለችው። ጌታ "በወንጌል እርፍን በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም" እንዳለ ወደ ዓለም አልመለስም" አለችው። ❤ ያም ባሕታዊ "ምንኵስናስ የለሽም አልታዘዘልሽም፤ ነገር ግን በሰላም ወደ ቤትሽ ወደ ሕጋዊ ባልሽ ተመለሽ። የተፈቀደልሽንስ እነግርሻለሁ ከሕጋዊ ባለቤትሽ ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ይሆናል። የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕይወተ ሥጋ ሳለ በፈጣሪው በእግዚአብሔር ፈቃድ የብዙዎቹን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል። እንደ መላእክትም ክንፈ ጸጋ ተሰጥቶታል። በሰው አካል በሥጋ ሁኖ ሳለ በተመሥጦ ወደ ሰማይ ወጥቶ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነት ምሥጢር ያያል"። ❤ ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባሕታዊ ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች፤ "የፈጣሪየ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ" አለች፤ ይህን ብላ ተመልሳ ወደ አገሯ ወደ ቤቷ ገባች፤ ቤተሰቦቿም መውጣቷንም መግባቷንም ምንም አላወቁባትም፤ ጥቂት ወራትም ከቆየች በኋላ፤ መልኩ እንደ በረዶ ነጭ እንደ ጽጌ ረዳም ብሩህ ቀይ የሆነ መልከ መልካም ልጅ ወለደች ሁለተናውም ጨረቃ የጉለቱ ምልዓት 15 ሌሊት ሁኖ በብሩህ ብርሃን በምልዓት በሚያድርበት ጊዜ እንደሚያበራው መልካም ብርሃን ገጹ ብሩህ የሆነ ልጅ ወለደች፤ ይህ ሕፃን በግንቦት ወር በ 26 በተወለደ ጊዜ በአባቱ (ፍሬ ብሩክ)ና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታን ሆነ፤ ሜሉን ገቹን አርደው ዘመዶቻቸውን ጎረቤቶቻቸውን አማቾቻቸውን ምርዓቶቻቸውን ጠርተው ለበዓሉ እንደሚገባ መብሉንና መጠጡን ሰጥተው በሚገባ አጠገቡዋቸው፤ ...ካህኑም ተቀብሎ አጠመቀው ከአጠመቀውም በኋላ ለነፍሱ ዋስ (ለክርስትና አባቱ) አሳልፎ ሰጠው ስሙንም ሀብተ ማርያም ብሎ ሰየመው፤..." ከአባታችን ከአቡነ ሀብተ ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን መልአከ ሞትን የማያሳይ ታላቅ ቃልኪዳን ላላቸውና ታላቁን ቀብጽያ ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ ለአባት አቡነ አሞጽ ለዕረፍታቸው፣ ለአባታችን ለአቡነ ሀብተ ማርያምና ታላቁ ገዳም ሐይቅ እስጢፋኖስ ላቀኑ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ለልደታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ አሞፅ፦ ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የመነኰሱት ደብረ ሊባኖስ በአቡነ ዮሐንስ ከማ እጅ ነው፡፡ አቡነ ዮሐንስ ከማ በመልአክ ታዘው 10 መነኰሳት 500 ሕዝብ ተከትሏቸው ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሳምረ ወረዳ ላይ ሲደርሱ ሕዝቡ ቢራብ ዋርካ ዕለቱን አብቅለው ባርከው መግበውታል፣ ውኃም አፍልቀው አጠጥተውታል፡፡ ከዚኽም በኋላ የበቁትንና ቅዱሳን የሆኑትን ዓሥሩን መነኰሳት ገዳም እንዲገድሙ ወደተለያዩ ቦታዎች ላኳቸው፡፡ ከእነዚኽም ዓሥር ቅዱሳን መነኰሳት መካከል አቡነ አሞፅ አንዱ ናቸው፡፡ ❤ አባታችን አባ አሞጽም ቀብፅያ የተባለችውን ቦታ ለመገደም እና በቦታው ለመቀመጥ ዘወትር የማትለያቸውን ጽላት ማርያምን ይዘው ወደ ደላ ከተማ መጡ ነገር ግን ይህ ስፍራ አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር ጀምሮ የተባረከች እና የስውራን ባሕታውያን ቦታ ስለነበር ስለ ክብሯ ተሰወረቻቸው እርሳቸውም ቦታይቱ እስክትገለጥላቸው ድረስ በደላ ከተማ የምትገኘው በቅድስት ማርያም ደብር ለሦስት ዓመት ሱባኤ ያዙ ነገር ግን ስላልተገለጠላቸው በትግርኛ ቋንቋ "ቀቢጼያ" በማለት ተናግረው ወደ መንፈስ አባታቸው ወደ አቡነ ዮሐንስ ከማ ተመልሰው ሄዱ ቀቢጼያ ማለት አጣኋት ማለት ነው። ❤ ከዚህ በኋላ አቡነ አሞጽ ከመንፈስ አባታቸው ከአቡነ ዮሐንስ ከማ ጋር ተመልሰው ወደ ደላ ከተማ በመምጣት በአንድነት ሱባኤ ገቡ ሱባኤያቸውን በፈጸሙ ሰዓት ከእግዚአብሔር የታዘዘ አንበሳ እየመራቸው ወደ ገዳሙ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ የገዳሙን ስም መጀመሪያ ቦታዋን አጥተው ስላገኝዋት "ቀቢጼያ" ከምትል ቃል ተነስተው "ቀብፅያ" በማለት ሰየሟት የመንፈስ አባታቸውም ቦታውን ባርከው ከሰጧቸው በኋላ ወደ በዓታቸው ተመለሱ ከዚህም በኋላ ፃድቁ አባታችን አባ አሞጽም በቦታው ላይ አንዲት የተፈጥሮ ዋሻ አግኝተው ለአንድ መቶ ዓመታት ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ❤ አቡነ አሞፅ ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን የእመቤታችን መከራ የሚተርከውን ድንቅ ድርሰት ሙሉውን ክፍል በብራና ላይ በሥዕል ገልጸው በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከሰማይ የወረደላቸው የወርቅ መስቀላቸውም በገዳሙ ይገኛል፡፡ ❤ በዘንዶዎች የሚጠበቀው ይህ አስደናቂ ገዳም በብዙ መልኩ ከሌሎች ገዳማት የተለየ ነው፡፡ የገዳሙን አፈር ቅዱሳን መላእክት ናቸው ከገነት ያመጡት፡፡ ጌታችን 12 እልፍ መላእክቱ ልኮ ከገነት አፈር አምጥተው በዝናብ አምሳል በቀብጽያ ገዳም ላይ እንዲነሰንሱት አዟቸዋል፡፡ ❤ ገዳሙን የተሳለመ ሰው ኢየሩሳሌም ጎልጎታን እንደተሳለመ የሚቆጠርለት ሲሆን በገዳሙ ውስጥ የተቀበረ ሰው ወቀሳ የለበትም፡፡ ከአካሉም ላይ ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን ቆርጦ በገዳሙ ክልል ውስጥ የቀበረ ሰው ቢኖር መልአከ ሞትን ፈጽሞ እንደማያይና ገዳሙ የሚገኝበት አካባቢ በእግር ለመጓዝ አስቸጋሪ ቢሆንም ቦታውን የረገጠ እስከ 15 ትውልድ ምሕረትን እንደሚያገኝ ጌታችን በቃልኪዳን አጽንቶታል፡፡ ሌላው ቀብጽያ ገዳምን ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፈዋሹ ጠበል ከጻድቁ አቡነ አሞፅ መቃነ መቃብር ሥር የሚፈልቅ መሆኑ ነው፡፡ ከዋሻው ሥር የተንጠባጠበው ጠበል ወደ ጠንካራ ዓለትነት የሚቀየር ሲሆን እርሱን ለእምነት የተጠቀሙበት ሰዎች ከተለያዩ በሽታዎች ተፈውሰዋል፡፡ በቅርቡም ከ6 ዓመት በፊት በዚህ እምነት የተሻሸች አንዲት ሴት ከዘመኑና መድኃኒት ካልተገኘለት ከHIV በሽታና ከመካንነቷ ተፈውሳ ልጅ ወልዳለች፡፡ ይህ አስደናቂ ቀብጽያ ገዳም ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ቢሆንም ከጊዜና ብዛት ጉዳት ስለደረሰበትና የሚያድሰው አካል ስላላገኘ በአሁኑ ወቅት ሌላ አዲስ ቤተ መቅደስ እየታነጸ ይገኛል፡፡ በቀብጽያ ገዳም ውስጥ 336 ዓመት የሆነው የወይራ ዛፍ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ስውራን የሆኑ ቅዱሳን ሦስት ጊዜ ደወል ሲደውሉበት ተሰምቷል፡፡ ❤ አቡነ አሞፅ በ1592 ግንቦት 26 አርብ ቀን ሲያርፉ ጌታችን ከድንግል እናቱ ጋር ተገልጾላቸው ከላይ ያየናቸውን አስደናቂ ቃልኪዳኖች ከሰጣቸው በኋላ ነፍሳቸውን እመቤታችን አቅፋ አሳረገቻቸው፡፡ ዐፅማቸው ያረፈበትን መካነ መቃብር ታላላቅ ዘንዶዎች ይጠብቁታል፡፡ ጠበላቸውም የፈለቀው ከመቃብራቸው ሥር ነው፡፡ ቦታው በስውራን ስለሚገለገል የከበሮ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን የእጣንም ሽታ ይሸታል፡፡ ከአባታች ከአቡነ አሞፅ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገዳሙ ካሳተመው ስዕል ጀርባ የተገኘ ታሪክ እና ከገድላት አንደበት። + + + ❤ አቡነ አሞፅ፦ ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የመነኰሱት ደብረ ሊባኖስ በአቡነ ዮሐንስ ከማ እጅ ነው፡፡ አቡነ ዮሐንስ ከማ በመልአክ ታዘው 10 መነኰሳት 500 ሕዝብ ተከትሏቸው ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሳምረ ወረዳ ላይ ሲደርሱ ሕዝቡ ቢራብ ዋርካ ዕለቱን አብቅለው ባርከው መግበውታል፣ ውኃም አፍልቀው አጠጥተውታል፡፡ ከዚኽም በኋላ የበቁትንና ቅዱሳን የሆኑትን ዓሥሩን መነኰሳት ገዳም እንዲገድሙ ወደተለያዩ ቦታዎች ላኳቸው፡፡ ከእነዚኽም ዓሥር ቅዱሳን መነኰሳት መካከል አቡነ አሞፅ አንዱ ናቸው፡፡ ❤ አባታችን አባ አሞጽም ቀብፅያ የተባለችውን ቦታ ለመገደም እና በቦታው ለመቀመጥ ዘወትር የማትለያቸውን ጽላት ማርያምን ይዘው ወደ ደላ ከተማ መጡ ነገር ግን ይህ ስፍራ አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር ጀምሮ የተባረከች እና የስውራን ባሕታውያን ቦታ ስለነበር ስለ ክብሯ ተሰወረቻቸው እርሳቸውም ቦታይቱ እስክትገለጥላቸው ድረስ በደላ ከተማ የምትገኘው በቅድስት ማርያም ደብር ለሦስት ዓመት ሱባኤ ያዙ ነገር ግን ስላልተገለጠላቸው በትግርኛ ቋንቋ "ቀቢጼያ" በማለት ተናግረው ወደ መንፈስ አባታቸው ወደ አቡነ ዮሐንስ ከማ ተመልሰው ሄዱ ቀቢጼያ ማለት አጣኋት ማለት ነው። ❤ ከዚህ በኋላ አቡነ አሞጽ ከመንፈስ አባታቸው ከአቡነ ዮሐንስ ከማ ጋር ተመልሰው ወደ ደላ ከተማ በመምጣት በአንድነት ሱባኤ ገቡ ሱባኤያቸውን በፈጸሙ ሰዓት ከእግዚአብሔር የታዘዘ አንበሳ እየመራቸው ወደ ገዳሙ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ የገዳሙን ስም መጀመሪያ ቦታዋን አጥተው ስላገኝዋት "ቀቢጼያ" ከምትል ቃል ተነስተው "ቀብፅያ" በማለት ሰየሟት የመንፈስ አባታቸውም ቦታውን ባርከው ከሰጧቸው በኋላ ወደ በዓታቸው ተመለሱ ከዚህም በኋላ ፃድቁ አባታችን አባ አሞጽም በቦታው ላይ አንዲት የተፈጥሮ ዋሻ አግኝተው ለአንድ መቶ ዓመታት ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ❤ አቡነ አሞፅ ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን የእመቤታችን መከራ የሚተርከውን ድንቅ ድርሰት ሙሉውን ክፍል በብራና ላይ በሥዕል ገልጸው በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከሰማይ የወረደላቸው የወርቅ መስቀላቸውም በገዳሙ ይገኛል፡፡ ❤ በዘንዶዎች የሚጠበቀው ይህ አስደናቂ ገዳም በብዙ መልኩ ከሌሎች ገዳማት የተለየ ነው፡፡ የገዳሙን አፈር ቅዱሳን መላእክት ናቸው ከገነት ያመጡት፡፡ ጌታችን 12 እልፍ መላእክቱ ልኮ ከገነት አፈር አምጥተው በዝናብ አምሳል በቀብጽያ ገዳም ላይ እንዲነሰንሱት አዟቸዋል፡፡

#ዕርገት #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ Be ዲ/ን ቃለ አብ @ https://t.me/Eotcw የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡ ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡ እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡ ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡ ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ) 🔴ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ https://t.me/Eotcw

ዕርገት በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ tineshe enemelekate