ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የነሐሴ ፳፬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማኅሌት
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
#ስቡዕ_ከተባለ_በኃላ
@EOTCW
❣መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤
ዘኢይነውም ትጉህ በውስተ ቅዱሳን ስቡሕ፤ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ፡፡
@EOTCWW
❣መልክአ ሚካኤል:-
ሰላም ለሕጽንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ጸሎተ ቅዱሳን ዉኩፍ፤ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አዕላፍ፤ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤እንዘ ትሰርር ነዓ በከልኤ አክናፍ፡፡
@EOTCW
❣ዚቅ
ርድአኒ ወአድኅነኒ፤ ወሥመር ብየ፤በከመ ሠመርኮሙ ለቅዱሳን አበውየ፡፡
@EOTCW
❣ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙለወልድኪ፤ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ለሙ፤እግዚአብአሄር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ፤
@EOTCW
❣ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኀኒት፤
እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት፡፡
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ማርያም ቅድስት አንቀጸ ሕይወት አመ ኖኅ አንቀጸ ሕይወት/2/
ይእቲ " እንተ ኮነት"/2/አንቀጸ ሕይወት/2/
@EOTCW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘጥንተ ፊደሉ መስቀል፤ስም ክቡር ወስም ልዑል፤ተክለ ሃይማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል፤ከመ እወድስከ መጠነ አውሥኦተ እክል፤ማእሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል፡፡
❣ ዚቅ
ወንጌለ መለኮት ሰበከ ስምዐ ጽድቅ ኮነ ወበእንተዝ ተክለ ሃይማኖት ተሰመይከ
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ወበእንተዝ "ተሰመይከ"/2/ ተክለ ሃይማኖት/2/
"ስምዐ ጽድቅ ኮንከ"/2/ተክለ ሃይማኖት/2/
@EOTCW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለአዕይንቲከ ዘአርአያሆን ሐዋዝ፤እለ ጽዱላት እማንቱ ከመ ሠርቀ ቤዝ፤ተክለ ሃይማኖት ኅብዓኒ እሞተ ኃጢአት አዚዝ፤ለከሰ አኮ ከመዝ፤ኢይረክበከ ሞት ዳግመ እምዝ፡፡
@EOTCW
❣ዚቅ
ዳግመ እምዝ ኢይረክቦ ሞት ከመዝ ዳግመ እምዝ፡፡
@EOTCW
❣አመላለስ፦
ዳግመ እምዝ/4/
ኢይረክቦ ሞት ለተክለ ሃይማኖት/2/
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
"ዳግመ እምዝ"/2/ኢይረክቦ ከመዝ ሞት ለተክለ ሃይማኖት/2/
ኢይረክቦ እምዝ ሞት ለተክለ ሃይማኖት/2/
@EOTCW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለኵልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግሥት፤ኢየሱስ ክርስቶስ አበ ብርሃናት፤ተክለ ሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት፤ጸሎትከ ዘገበርካሃ እስከነ ኍልቈ ምዕት ዓመት፤መድኀኒተ ትኩነኒ እምግሩም ቅሥት፡፡
❣ዚቅ
ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኀኒት ጸሎትከ ትኩነነ ፀወነ እመንሱት ተክለ ሃይማኖት ሰባኬ መድኀኒት
@EOTCW
❣❣ወረብ
ሰባኬ መድኀኒት ተክለ ሃይማኖት/2/
ጸሎትከ ትኩነነ"ፀወነ እመንሱት"/2/ /2/
@EOTCWW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ በስብሐተ አእላፍ እንግልጋ፤ለዓለም ዛቲ እምግብርናቲሃ ወጹጋ፤ተክለ ሃይማኖት ቶማስ ለመርዓስ ዐቃቤ ሕጋ፤ለእለ ገብሩ ተዝካረከ እንዘ ሀለው በሥጋ፤ሀቦሙ እግዚእየ ሞገሰ ወጸጋ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ወአብእዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡
@EOTCWW
❣❣ወረብ፦
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/2/
ወአብእዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ ወአብእዎ ለተክለሃይማኖት/2/
@EOTCWW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ኤልሳዕ መምህር ዘገነዛ፤በሠናይ ጼና መዓዛ፤ተክለ ሃይማኖት ሰባኬ ፊሊጶስ ዘብሔረ ጋዛ፤ለሥጋየ መሬታዊት አመ የኃልቅ ዕዘዛ፤ስብረተ ዐጽምከ ይኩነኒ ቤዛ።
@EOTCWW
❣ዚቅ
ሖረ ኀቤሁ ለተክለ ሃይማኖት ቀዲሙ ሌሊተ፤ኤልሳዕ ስሙ መልአኮሙ ለአርድዕት፤ውእቱኒ አምጽአ ከርቤ አፈዋተ፤ገነዝዎ በሰንዱናት ለተክለ ሃይማኖት፡፡
@EOTCW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዘቦቱ ይትመሐፀኑ፤ነገሥተ እስራኤል ኄራን ዘአስተሣነይዎ በበዘመኑ፤ተክለ ሃይማኖት ሠዋዒ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤አድኅነኒ እምፀብአ ከይሲ ዘዐሥር ቀርኑ፤ወእምብእሲ ዘክልኤ ልሳኑ።
@EOTCW
❣ዚቅ
መላእክት አእመሩ ሃይማኖተከ፤ነገሥት ሐነፁ መካነከ፤አባ ተክለ ሃይማኖት ክርስቶስ ዘአፍቀረከ፡፡
@EOTCWW
❣መልክአ ተክለኃይማኖት
ሰላም ለመቃብሪከ እምቅድመ ትኑም ውስቴታ፤ታቦተ ማርያም ድንግል ዘአንበርከ በውሳጢታ፤ተክለ ሃይማኖት አቡየ ለወልድከ ዕጓለ ማውታ፤ለበረከትከ ይከልለኒ ረድኤታ፤ወይዑደኒ ዘጽድቅከ ወልታ።
@EOTCWW
❣ዚቅ
ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተቀብረ ሥጋየ፤ወተክዕወ ደምየ ህየ ይኩን በረከት፡፡
@EOTCWW
❣መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሶበ አዕረፈ ተክለ ሃይማኖት ከዊኖ ህልወ በጾማዕቱ፤እንዘ ርኁብ ወእንዘ ጽሙዕ ውእቱ፤ላዕካነ ማርያም አሜሃ እለ መጽኡ ለአፍልሶቱ፤ተበሃሉ በአርጋኖን ወዘመሩ ሎቱ፤አማን ለጻድቅ ክቡር ሞቱ።
@EOTCWW
❣ዚቅ
ይቤሎ ኢየሱስ ለተክለ ሃይማኖት፤ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስዕለተከ፤እምብዙኅ ፃማ አአርፈከ፤ኀበ ሀሎ ፍሥሐ አነብረከ፡፡
@EOTCWW
❣❣ወረብ፦
ኀበ ሀሎ"ፍሥሐ አነብረከ"/2/ /2/
ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስዕለተከ እምብዙኅ ፃማ አአርፈከ/2/
@EOTCWW
መልክዐ ተክለሐይማኖት
በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ...
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ቶማስ እዴከ መጥወኒ፤ወተክለኃይማኖት አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ቶማስ እዴከ መጥወኒ ቶማስ እዴከ/2/
ወተክለኃይማኖት አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ/2/
@EOTCW
@EOTCWW
❣ምልጣን:-
አባ አቡነ አቡነ መምህርነ እምአዕላፍ ኅሩይ፤ሐውጽ እምሰማይ ብርሃነከ ከመ ንርአይ፡አማን ተክለኃይማኖት ፀሀይ
@EOTCWW
❣ዓዲ
ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ፤
እስመ ለጻድቅ ይትሌዓል ቀርኑ በክብር
ጻድቃን እለ አሥመርዎ ለእግዚኦሙ ምድረ ብርህተ ወጽዕዱተ ይወርሱ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ፦
ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ/2/
እስመ ለጻድቅ ይትሌዓል ቀርኑ በክብር/2/
@EOTCWW
❣እስመ ለዓለም
ደሪዖሙ ተዓጊሦሙ መጠዉ ነፍሶሙ ለሞት፤እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ እም ፀሐይ ይበርህ ገጾሙ፤እለ አጥረይዋ በትዕግሥት፤ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት ለመጽብብ ከመ ይባዕዎ ለመርህብ፤ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት ዓደዉ እሞት ውስተ ሕይወት፤ኦ እፎ አምሰጥዎ እለ ጸውዖሙ ወይቤሎሙ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ፤እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ አመ ያቀውም አባግዓ የማኑ ወአጣሌ በጸጋሙ ፤ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት አሜሃ ይቤሎ እለ በየማኑ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ ፤ወያወርሶሙ ምድረ ሐዳሰ እንተ ታውኅዝ ሐሊበ ወመዓረ ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት፤ማ፦ገነተ ትፍሥሕት ኪያሃ አውረሶሙ ወአቀቦሙ ከመ ብንተ ዐይን ለጻድቃን እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ፡፡
@EOTCW
❣አመላለስ፦
ገነተ ትፍሥሕት ኪያሃ አውረሶሙ ወአቀቦሙ ከመ ብንተ ዐይን ለጻድቃን/2/
እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ/4/
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
አሜሃ ይቤሎ"እለ በየማኑ"/2/ /2/
ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ ለአቡየ ንዑ/2/
1 161
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ስርአተ ዋዜማ ዘነሐሴ ተክለኃይማኖት
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
❣በ 1 ሀሌታ-
እንተ አጽናዕኮሙ ለአድባር በኃይልከ፤ወቅኦታን እሙንቱ በኃይል፤ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ፤ጸሊ በእንቲአነ
@EOTCWW
❣❣ምልጣን፦
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ
@EOTCWW
@EOTCWW
❣አመላለስ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ/2/
አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ/4/
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣እግዚአብሔር ነግሰ፦
ተክለኃይማኖት ፃመወ እምገድለ ቅዱስ ምክዕቢተ ከመ ይፍረይ ፍሬ ህየንተ አሀደ፴ወስምንተወ፻ተ ኢያድነነ ትልሞ ወኢገብዓ ድኅርተ እመንፈስ ቅዱስ ነሢዖ አሦተ
@EOTCWW
❣እግዚኦ ጸራዕኩ ሀቤከ ስምዐኒ፦
ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ለእንተ ይበልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ዓዲ(ሌላ)፦
ጸለየ ተክለኃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ በረከት
@EOTCWW
❣ሰለስት፦
በመንፈስ የሐውር እምኃይል ውስተ ኃይለ ተክለኃይማኖት ካህን ወድንግል
@EOTCWW
❣ሰላም፦
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት፤ አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣አመላለስ፦
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት፤(2)
አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም፤(4)
@EOTCW
@EOTCW
❣ዓዲ ሰላም፦
እስመ በኩሉ ይሴብሕ እግዚአብሔር በሰማይኒ ወበምድርኒ በፍስሐ ወበሰላም ንርአይ ስና ለቤተ ክርስትያን ወንግበር ተዝካሮሙ ለብፁዕ አበ ኩልነ አባ ተክለኃይማኖት አስተጋብዓነ ለስብሐት እግዚአብሔር
@EOTCW
አመላለስ፦
አበ ኩልነ አባ ተክለኃይማኖት/2/
አስተጋብዓነ ለስብሐት እግዚአብሔር/4/
https://t.me/Eotcw
#Join & share
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊ ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚነኘው ደብረ ጥሉል ገዳምን ለመሰረቱ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ላለማየት ሳይወለዱ በእናታቸው ማኅፀን 7 ዓመት ከ6 ወር ለቆዩት ለታላቁ አባት አቡነ አብራኒዮስ ዓመታዊ ለዕረፍት በዓላቸው በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ አብራኒዮስ፦ አባታቸው ወልደ ክርስቶስ እናታቸው ወለተ ትንሣኤ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተወለዱት በ1624 ዓ.ም ምሥራቅ ጎጃም አካባቢ ልዩ ስሙ እነብሴ ይሁን እንጂ ተጋድሏቸውን ያደረጉትና ገዳማቸውን የገደሙት በዛሬዋ ኤርትራ ውስጥ ነው፡፡ ገዳሙ ኤርትራ ውስጥ ዞባ ድባርዋ ደቂ ድግና በተባለ አካባቢ ይገኛል፡፡ የገደሙት ጻድቁ በ1705 ዓ.ም ነው፡፡
❤ አቡነ አብራኒዮስ የተፀነሱት በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ጻድቁ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ላለማየት ሳይወለዱ በእግዚአብሔር ፈቃድ በእናታቸው ማኅፀን 7 ዓመት ከ6 ወር ተቀምጠዋል፡፡ በዚህም ወቅት እሳት ልትጭር ከጎረቤቷ የመጣች አንዲት ሴት የአቡነ አብራኒዮስ እናት "የማትወልጂው ምን ሆነሽ ነው?" ብላ ስትናገር ጻድቁ በእናታቸው ማኅፀን ሆነው "…ለምን ክፉ ትናገሪያለሽ?" ብለው መልስ ሰጥተዋታል፡፡ ይህም ቅዱሳን ልክ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ገና በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ እንደሚመረጡ አንድ ማሳያ ነው፡፡
❤ በርካታ ምእመናንን በሰማዕትነት ከገደሉ በኋላ በመጨረሻም ዐፄ ሱስንዮስ በመቅሰፍት ተመተው ሊሞቱ ሲሉ "ሃይማኖት ይመለስ፣ ፋሲል ይንገሥ" ብለው የቤተ ክርስቲያን ሰላም መልሰው ንስሓ ገብተው ሞቱ፡፡ አቡነ አብራኒዮስም ይህ የቤተ ክክርስቲያን የመከራ ዘመን ሲያልፍና ሃይማኖት ሲመለስ ተወለዱ፡፡ ገና በ5 ዓመታቸው ከጥንቆላ መጻሕፍት በቀር ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንና ምሥጢራትን ሁሉ ተምረው ዐወቁ፡፡ በ12 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡ ዲቁና ሲሾሙም ጳጳሱ "ገና ሕፃን ነው፣ አሁን አልሾመውም" ሲሉ የሰማይ መላእክት "ይባዋል" ብለው መስክረውላቸዋል፡፡
❤ በልጅነታቸውም መነኰሳቱ ወደ ጫካ ሔደው ዕንጨት እንዲሰብሩ ሲያዟቸው ጌታችን ግን ለአቡነ አብራኒዮስ ኃይል ሰጥቷቸው በነፋስ ሠረገላ እየሔዱ የ6 ሰዓቱን የእግር መንገድ እሳቸው ግን ዕንጨቱን ሰብረው በቶሎ ይመለሱ ነበር፡፡ ይህም ሲታወቅባቸው ውዳሴ ከንቱን ንቀው ከዚያ ገዳም ወጥተው ወደ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ዘንድ ሔዱ፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ አቡነ ተጠምቀ መድኅን "በአንተ ምክንያት ብዙ ነፍሳት ይድናሉ፣ ክፍልህ በዚያ ነው" ብለው አሁን ገዳማቸውን ወደገደሙበት ቦታ (ኤርትራ) ላኳቸው፤ ሲመጡም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየመሯቸው እንደመጡ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ ወደዚህ ገዳም ሲመጡ በፊት ይቀመጡባት የነበረችው ትልቅ ድንጋይ በተኣምር ከመሬት 7 ክንድ ከፍ ብላ አብራቸው መጥታለች፡፡ ድንጋይዋ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው በክብር ስለተቀመጠች ምእመናን እየዳሰሷት ይባረኩባታል፣ መካኖች ይወልዱባታል፣ ሕሙማን ይፈወሱባታል፡፡
❤ አቡነ አብራኒዮስ በቅዳሴ ጊዜ ጌታችንን በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ሆኖ ይመለከቱት ስለነበር በኀዘን በተመስጦ ሆነው ይቆዩም ስለነበር ሕዝቡም "በቅዳሴ ሰዓት ይተኛል" እያሉ ያሟቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጻድቁ ወደ አካለ ጉዛይ በመሔድ በዘንዶ ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን ሰይጣን በጸሎታቸው አጥፍተው ዘንዶውን ገድለው ሕዝቡንም አስተምረው በንስሓ መልሰው አጥምቀዋቸዋል፡፡ ወደ ታላቁ ገዳም ደብረ ቢዘንም ሲሔዱ 6400 አጋንንትን አግኝተው በጸሎታቸው አጥፍተዋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ አብራኒዮስ "ሰዳዴ አጋንንት-አጋንንት አባራሪ" ተብለዋል፡፡
❤ አቡነ አብራኒዮስ ወደ ሌላ ቦታ ሔደው ሰለዳዋ የምትባል ቦታ ላይ ሆነው ሳለ አንድ ሰው ወደ ገዳማቸው ገብቶ አንዲትን ዛፍ ሲቆርጥ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት አዩት፡፡ ቆራጩም ሰው "ተው አትቁረጥ" የሚል የአባታችንን ድምፅ ሰማ፣ በአካል የሉም ብሎ እምቢ አለ፣ ነገር ግን በመቅሠፍት ተመቶ ወዲያው ሞተ፡፡ በአንድ ዕለትም ልጃገረዶች እየዘፈኑ ሲሔዱ ብዙ አጋንንት በዘፈናቸው ተደስተው አብረዋቸው ሲጨፍሩ አባታችን በመንፈስ ተመልክተው ለልጃገረዶቹ ዘፈን የአጋንንት መሆኑን እንዳስተማሯቸው ገድላቸው ይናገራል፡፡
❤ ለአቡነ አብራኒዮስ ለዕፍታቸው ሲደርስ ክብርት እመቤታችን ተገልጻ "ቤተ ክርስቲያን በስሜ አንጽልኝ" አለቻቸው፡፡ እርሳቸውም ውብ አድርገው በእመቤታችን ስም አነጹ ነገር ግን ፍጻሜውን ሳያዩ በዕለተ ቀኗ ነሐሴ 21 ቀን ዐረፉ፡፡ በዕረፍታቸውም ወቅት ጌታችን ተገልጦ ታላቅ ቃልኪዳን ሲሰጣቸው "...ዋስ እፈልጋለሁ፣ ዋስ ስጠኝ" አሉት፡፡ ጌታችንም "ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ከአንተ በፊት የነበሩ ጻድቃን ያልጠየቁኝን አንተ እንዴት ጠየከኝ?" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "አምላኬ ሆይ! አንተ መሐሪና በጽድቅ ፈራጅ ቃልህም የማይለወጥ እንደሆንክ አውቃለሁ" አሉት፡፡ ጌታችም ፍግግ ብሎ "ይሁን የምትሻውን አላሳጣህም" በማለት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች ክብርት እመቤታችንንና ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ዋስ አድርጎ ቃል ኪዳን ከገባላቸው በኋላ ነሐሴ 21 ቀን 1713 ዓ.ም በሰላም ዐረፉ። ከታላቁ ጻድቅ ከአባታች አቡነ አብራኒዮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ታቦተ ጽዮንን ወደ አገራችን ላመጣ ለንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ እናት ለንግስት ማክዳ ወይም ለንግስተ ሳባ (አዜብ) ለልደት በዓል፣ ለንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ለንግሥት እሌኒ የልደት በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ "ሰላም ለእሌኒ ንግሥት ዘከሠተት መስቀለ በጎልጎታ ለክርስቲያን ዘይከውን ወልታ፤ እምኀበ ወጽአ ጢስ በሃይማኖታ፤ ወዓዲ ረከበት ቅንዋተ መስቀሉ ለክርስቶስ፣ ወአግበረት ልጓመ ፈረስ በከመ ይቤ ዘካርያስ"። ትርጉም፦ ጢስ በሃይማኖቷ ከወጣ ዘንድ ለክርስቲያን ጋሻ የሚኾን መስቀልን በጎልጎታ ያወጣች ለኾነች ለንግሥት እሌኒ ሰላምታ ይገባል፤ ዳግመኛም የክርስቶስን የመስቀሉን ችንካሮች አገኘች፤ ዘካርያስ እንደተናገረው ለፈረስ ልጓም አሠራች። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ንግሥት ቅድስት ዕሌኒ፦ ይቺም ቅድስት በፊት የአንድ ነጋዴ ሰው ሚስት ነበረች እርሱም በነገረ ሠሪ ንጽሕት ሁና ሳለች ወደ ባሕር ጣላት። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ፈቃድም ሮሐ ከሚባል አገር ደርሳ የበራጥያ ንጉሥ ቊንስጣ አገኛት። ውበቷንና ደምግባቷንም አይቶ አገባት። ለክርስቲያን ነገሥታት መጀመርያቸው የሆነውን ቈስጠንጢኖስን ወለደችው ምግባርንና ሃይማኖትን በማስተማር በመልካም አሳደገችው።
❤ ልጇም በነገሠ ጊዜ "ወደ ኢየሩሳሌም ሔደሽ የክብር ባለቤት የሆነ የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ግለጪ የከበሩ ቦታዎችንም ሥሪ" የሚላትን በሕልሟ አይታ እንዴት እንዳየች ይህን ለልጇ ነገረችው እርሱም ከብዙ ሠራዊቱ ጋራ ሰደዳት። በደረሰችም ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን መስቀል መረመች አዳኝ የሆነ መስቀሉንም ሁለት ወንበዴዎች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች ጋራ አገኘችው። የክብር ባለቤት የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታውቅ ዘንድ በወደደች ጊዜ ከራሱ በላይ "ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው" የሚል በእንጨት የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ምልክት ታይ ዘንድ ፈለገች የሞተ ሰውም አግኝታ መስቀሎችን በበድኑ ላይ አኖረች አልተነሣም። ከዚህ በኋላ ሦስተኛውን መስቀል በላዩ አኖረች። ያን ጊዜ ያ ምውት ተነሣ ሃይማኖቷም ጸና ደስታዋም በዛ።
❤ ከዚህ በኋላ ዜናቸው በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት የተጻፈ በከበሩ ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ትሠራ ዘንድ ጀመረች። ለአባ መቃርስም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሠራ ብዙ ገንዘብ ሰጠችው።
❤ ከዚህ በኋላ ወደ ልጇ ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ነገረችው የከበረ መስቀል በመገኘቱ እጅግ ደስ አለው። ይቺም ቅድስት በጎ ገድላሏን ከፈጸመችና እግዚአብሔርንም ከአገለገለች በኋላ ስለ ካህናትም ልብስና ቀለብ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ብዙ ጉልቶችና ርስቶችን ለድኆችና ለምስኪኖችም እንዲሁ ከሠራችና ከተከለች በኋላ ግንቦት9 ቀን በሰላም ዐረፈች መላ ዕድሜዋም ሰማንያ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ዕለኔ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የግንቦት9 ስንክሳር።
+ + +
❤ ንግሥተ ሳባ፦ ይህቺ ኢትዮዽያዊት ንግሥት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት። በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች።
❤ ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች። ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ቀዳማዊ ምኒልክን ወልዳለች።
❤ ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች። (ማቴ. 12፥42) በስምም ሳባ፣ አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች። ዛሬ ዕለተ ልደቷ ነው። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥25-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1-1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-18። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
