fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ አካለ ክርስቶስ ዘቤጌምድር ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል፣ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት ለአቡነ አረጋዊ ለልደታቸውና ደብረ ደሞ ለወጡበት ቀን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለቊስጥንጥንያ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ልጅ ለሙሽራወ ለቅዱስ ለገብረ ክርስቶስ ለበዓሉ መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለአባ አረጋዊ ምንኵስናሁ ዘፈጸመ፤ በፍኖተ ጽድቅ ዘቆመ። ሰላም ለገብረ ክርስቶስ ብእሴ እግዚአብሔር ለነፍሱ ዘኮነ ኬንያ ዘአብዕዎ መላእክት ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ"። ትርጉም፦ በእውነት ጐዳና የቆሞ ኾኖ ምንኩስናውን ፍጹም ላደረገ ለአባ አረጋዊ ሰላምታ ይገባል። ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መላእክት ያስገቡት ለነፍሱም ጠቢብ የእግዚአብሔር ሰው ለኾነ ለገብረ ክርስቶስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ አቡነ አካለ ክርስቶስ ዘቤጌምድር፦ ከአባታቸው ከገላውዴዎስ ከእናታቸው ወለተ አዳም ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን ተወለዱ። በተወለዱም ጊዜ ሙት አስነሥተዋል። የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሲሆኑ በ21 ዓመታቸው ነው በሐይቅ እስጢፍኖስ ገዳም የመነኰሱት። ዘገብርኤል የተባለ በስሙ አሳሳች የሆነ ጣዖት አምላኪ ለጣዖት አልሰግድም ቢሉ ወስዶ በእጅጉ አሠቃቷቸዋል። በ6 ችንካሮች ቸንክሮ ሲያሠቃያቸው ጌታችን ተገልጦላቸው እንደ ጊዮርጊስ ጽና ብሎ ተስፋውን ሰጥቷቸዋል። ❤ ጻድቁ አገራቸው ጋይንት ሲሆን በዚሁ አካባቢ ምዕራፈ ቅዱሳን በተባለው ቦታ አንድ የወይራ ዛፍ ተደግፈው ሳይንቀሳቀሱ 40 ዓመት ቆመው የጸለዩበት ወይራ ዛፍ ዛሬም በገዳሙ ተከብራ ትኖራለች። ቤተ መቅደሱ ሳይታጠን የቀረ እንደሆነ ወይም ዲያቆኑ መብራት ሳያጠፋ የሄደ እንደሆነ የጻድቁ መቋሚያቸው እንደ ሰው አፍ አውጥታ ታቃጭላለች። ያበደ ሰው በመቋሚያዋ 7 ጊዜ ቢተሻሽባት ይድናል። በአካባቢው ብዙ መርዛማ እባቦች ቢኖሩም የአቡነ አካለ ክርስቶስን ስም ከተጠራባቸው ምንም ጉዳት አያደርሱም። በሌላም ቦታ ሆኖ እባብ የነደፈው ሰው እምነታቸውን ከተቀባ ጸበላቸውን ከጠጣ ፈጥኖ ይድናል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

እፎ ሀሎክሙ ተለውተ ክርስቶስ ኩልክሙ። ዮም አነ እጽሕፍ ለክሙ በይነ ጥምቀት። * ተለውተ ክርስቶስ --> የክርስቶስ ተከታዮች * በይነ ጥምቀት --> ስለ ጥምቀት •••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፲ወ፪ ወይብል ከመዝ ``... እምቃለ ቅዱስ ቄርሎስ (ከቅዱስ ቄርሎስ ድርሰት) ° ወተጠምቀ እም ዮሐንስ። (ከዮሐንስ ተጠመቀ።) ° በወርኀ ፅርዕ ጦቢ አመ ፲ወ፩ ለጥር። ወበወርኀ ሮሜ ቅድመ ሰመንቱ። (በፅርዕ ቋንቋ ጦቢ በሚባል በጥር በዐሥራ አንድ ቀን። በሮም አቆጣጠር በስምንተኛው ቀን ዋዜማ ከሌሊቱ በዐሥር ሰዓት።) ° ወበግእዝ አመ ፲ወ፩ ለጥር በዐሠርቱ ሰዓት ዘሌሊት። (በኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥር በዐሥራ አንድ ቀን በዐሥረኛው ሰዓት ሌሊት ተጠመቀ።) ° አሜሃ ሖሩ ክልኤሆሙ ውስተ ዮርዳኖስ። (ያንጊዜ ሁለቱ ጌታና ዮ።ሐንስ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ።) ° ወፈልሑ ማያት ከመ ዘሞቀ። (ውኃው በእሳት እንዳፈሉት ፍልቅልቅ አለ።) ° ወሶቤሃ ተርኅወ ሰማይ። ወወረደ መንፈስ ቅዱስ በአርአያ ርግብ ወነበረ ዲቤሁ። (ሰማይ ተከፈተ። መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ።) ° ወተጠሚቆ ወፅአ ወቃልሂ እምሰማይ ተሰምዐ ከመ ፀዓይ ዓቢይ። እንዘ ይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ፍቁር ዘቦቱ ሠመርኩ። (ተጠምቆ ከወጣ በኋላ የምወደው የምወልደው ለተዋሕዶ ለመሥዋዕትነት የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው የሚል ቃል ከሰማይ እንደ መብረቅ ተሰማ።) ° ወውእቱ ኢየሱስ አመ ፴ ዓመቱ ተጠምቀ እምዮሐንስ። (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠላሳ ዘመኑ ከዮሐንስ ተጠመቀ።) ... #_ናሁ_ፈጸምነ_ዘይእዜ_ትምህርተ_እግዚአብሔር_ያስተራክበነ_ለይመጽእ_ጊዜ_በሰላም_ወበጥዒና። @Eotcw ሠናይ ሶቤ✋

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ሥርዓተ ማኅሌት ዘቃና ዘገሊላ 🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። @EOTCW መልክአ ሥላሴ ሥላሴክሙ ሥላሴ ይረስየኒ መካነ፤ ድኅረ ተዋሃድኩሰ ዘሥላሴሁ ብርሃነ፤ ዮርዳኖስክሙ ዝየ እስመ ኲለንታየ ኮነ፤ ኢየኃሥሥ እምዮርዳኖስ ሰማዕተክሙ ምዕመነ፣ ወኢይትሜነዮ ለታቦር እስመ ታቦር አነ። @EOTCW ዚቅ ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ፤ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ፤ እማርያም ዘተወልደ አፍቂሮ ኪያነ፤ መጽአ ኀቤነ ዘነቢያት ሰበኩ ለነ፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይፌጽም ኲሎ ሕገ፤ ወአስተርአየ ገሃደ። @EOTCW መልክአ ሚካኤል ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤ ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤ አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ። @EOTCW ዚቅ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ ዘበተዋሕዶ ይሤለስ፤ እምኀበ ትጉሃን ይትቄደስ፤ እሳተ ሕይወት ዘኢይትገሠሥ፤ ወዘኢይጤየቅ ለዓይን ረቂቅ መንፈስ፤ ንሰግድ ለትሥልስቱ አሐተ ስግደተ፤ ወሎቱ ናቄርብ ስብሐታተ። @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ፤ አሕጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ። @EOTCW ዚቅ ወዘምሩ ለስሙ፤ ሀቡ አኮቴተ ለስብሐቲሁ፤ በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ። @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለክሣድክ ግብረ መንፈስ ቅዱስ ኬንያ፤ አዳም ስና ወመንክር ላህያ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ ወሐዋርያ፤ አመ ወጽአ ስሙዓቲከ በአድያመ ኲሉ ሶርያ፤ ብጹአት አእይንት ኪያከ ዘርእያ። @EOTCW ዚቅ ምድረ ዛብሎን ወንፍታሌም፤ ፍኖተ ባሕር ማዕዶተ ሦርያ ዘገሊላ፤ ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእዩ ብርሃነ፤ እስመ ብርሃን ሠረቀ ሎሙ፤ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር፤ እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም፤ ንዑ ናንሶሱ በብርሃኑ። @EOTCW ወረብ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም/፪/ በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ/፬/ @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለመከየድከ አሐዱ አሐዱ፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ለምሕሮ እለ ገይሠ ለመዱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመዓዛ ፍቅርከ ዕቊረ ናርዱ፤ አኃዊከ ሰማዕታት ቆላተ ህማማት ወረዱ፤ ወጻድቃኒከ ገዳማተ ዖዱ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔዓለም፤ ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔዓለም፤ ወይኬልልዎ ለመድኃኔዓለም፤ ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔዓለም፤ ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔዓለም፤ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲአሁ። @EOTCW ወረብ ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔዓለም ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔዓለም/፪/ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ/፪/ @EOTCW @EOTCW አንገርጋሪ እንዘ ሥውር እምኔነ ይእዜሰ፤ ክሡተ ኮነ ማየ ረሰየ ወይነ፤ ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ፤ በቃና፤ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ። @EOTCW አመላለስ በቃና ዘገሊላ/፪/ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ/፬/ @EOTCW ወረብ ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ/፪/ በቃና 'ዘገሊላ'/፪/ ከብካብ ኮነ/፪/ @EOTCW እስመ ለዓለም ዘበዳዊት ተነበየ፤ ወበዮሐንስ ጥምቀት ኃርየ፤ በቃና ዘገሊላ ማየ ወይነ ረሰየ፤ መዓዛ ቃልከ ይትወከፍ ጸሎትየ። @EOTCW አመላለስ፦ በቃና ዘገሊላ ማየ ወይነ ረሰየ፤ መዓዛ ቃልከ ይትወከፍ ጸሎትየ። @EOTCW ዕዝል፦ አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፤ ኮነ እሙነ አስተርዮቱ ለመድኃኒነ ክርስቶስ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW ምልጣን፦ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW አመላለስ፦ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW አቡን፦ በ፭ ወእንዘ ሀለው ውስተ ከብካብ፤ ቅረቡ ኃቤሁ ኩሎሙ አርዳኢሁ ፤አንክርዎ ለማይ አእኰትዎ ለኢየሱስ፤ በእንተ ማይ ዘኮነ ወይን @EOTCW @EOTCW ምልጣን፦ አንክርዎ ለማይ አንክርዎ አእኰትዎ ለኢየሱስ፤ አንክርዎ ማይ አንክርዎ @EOTCW አመላለስ፦ አንክርዎ ለማይ አንክርዎ፤ አእኰትዎ ለኢየሱስ አእኰትዎ ለኢየሱስ። ዓራራይ፦ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ ለመድኃኒነ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራጽዮን፤ ፆፍ ፀዓዳ፤ ንጉስ አንበሳ እምዘርዓ ዘመጽአ @EOTCW @EOTCW ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW @EOTCW ምልጣን ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW @EOTCW ወረብ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/ 👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share # መልካም አገልግሎት

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን ለገሀድ (ጋድ) ጾመ፣ ለከተራ በዓልና ለአባ ታውብንጦ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ከጠምያኒ፣ ከኪናርያና ከንግሥት በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ ሰላም፦ "ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት፤ በፍሥሐ ወበሰላም"። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና። ❤ እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው። ❤ በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ። ❤ በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ። ❤ የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው። ❤ መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ታውብንጦስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት። ❤ ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት። ❤ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር10 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ። ዘስሙ ገሀድ። መምህራነ ሥርዓት አቀሙ ለዘይመጽእ ትውልድ። እመባልዕት ጥሉላት ወእምነ ቅሡም ማዕድ። አንስት ይትሀረማ ወይጹሙ ዕድ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥር 10። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ። ላዕሌየ ይዛውዑ እለ ይነብሩ ውስተ አናቅጽ። ወኪያየ የኀልዩ እለ ይሰትዩ ወይነ"። መዝ68፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥1-9። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። መዝ 84፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 3፥20-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥14-18 እና የሐዋ ሥራ 13፥24-30። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 3፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም ቀንና የከተራ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ቅኔ ዘዲያቆን የአብስራ ይትናዛህ ማየ ምስለ አብያጺሁ ኖሎት ዘኢፈርሃ ማየ ኖትያተከዚ ጥምቀት ትርጉም እና ሰም ፦ ውሃ የማይፈራ ዋናተኛ ጥምቀት ከጎደኞቹ እረኞች ጋር ውሃ ይረጫጫል። ወርቅ፦ ለወርቁ ደግሞ ካህናት በእረኛ ሲመሰሉ ውሃ ይረጫጫሉ የተባለው ደግሞ ካህናት ምዕመናንን ይረጫሉ ነው። ሙያ፦ ይትናዛህ..........ማሰሪያ ይስባል እንጂ አይሳብም ማየ........የይትናዛህ ተሳቢ ምስለ አገባብ ፍቺው ጋር ሙያው አፈቃቃሪ አብያጽ ኖሎት ምሳሌ አብያጽ ሰም ኖሎት ወርቅ ተመስሎ ያፈቃቃሪ ባለቤት ዘ......አገባብ ፍቺው የ ሙያው ቅፅል ቅፅልነቱ ለኖትያ ጥምቀት ኢ........አሉታ ሙያው አፍራሽ ፈርሀ......እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል ማየ.........የፈርሀ ተሳቢ ኖትያ ጥምቀት ምሳሌ ኖትያ ሰም ጥምቀት ወርቅ ተመስሎ የቅኔ ባለቤት ተከዚ........የኖትያ ተሳቢ ዘአምላኪየ ኢይሰቲ ወይነ እንዘ ፍና ባህር ያንሶሱ ጥምቀት እንግዳ ዘበራህ ርእሱ በጽሩይ ማይ አምጣነ ተመልዐ ከርሱ ትርጉም እና ሰም፦ ራሱ በራ የሆነ😂 ጥምቀት እንግዳ የባህር መንገድን እየተመላለሰ ጠላ አይጠጣም 🤷‍♀ ሆዱ በንፁህ ውሃ ሞልቷልና ወርቅ፦ ጥምቀት እንግዳ የተባለው በአመት አንዴ የሚመጣ በዓል ስለሆነ ሲሆን በውሃ ጠግቧልና የተባለው ደሞ ጥምቀት ለሀብታምም ሆነ ለደሀ የሚፈፀመው በውሃ ብቻ ስለሆነ ነው

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት 💧💧💧💧💧💧💧💦💦💦💦💦 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" @EOTCW ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። @EOTCW @EOTCW መልክአ ሥላሴ ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤ ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ፤ በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ፤ ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ፤ ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤ እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤ እለ አሐዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤ እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ይቀድስ ማያተ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ጸጋ ወጽድቅሰ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ። @EOTCW @EOTCW ነግሥ ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤ መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ። @EOTCW ዚቅ ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ። @EOTCW ወረብ ርእዩከ 'እግዚኦ'/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/ 'ደንገፁ'/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/ @EOTCW @EOTCW ትምህርተ ኅቡዓት እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤ በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ ወማየ መንጽሔ ዚአነ። @EOTCW @EOTCW ወረብ 'ወደሞ ክቡረ'/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/ ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/ @EOTCW አንገርጋሪ ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤ እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ። አመላለስ፦ አማን በአማን መንክር ፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ። @EOTCW ወረብ ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/ 'ወለደነ ዳግመ'/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/ @EOTCW እስመ ለዓለም ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ። @EOTCW አመላለስ፦ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።(4) ወረብ ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/ @EOTCW ዕዝል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ወተገሠ በሥጋ፤ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ ወረደ ዲበ ምድር፤ ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ። @EOTCW @EOTCW ምልጣን ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ። @EOTCW አመላለስ ወገብረ መንጦላዕተ/፪/ ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፪/ @EOTCW አቡን በ፭: እስመ ሰምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ ዘኪያሁ ሠምርኩ ይቤ፤ ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ። @EOTCW @EOTCW ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW @EOTCW ምልጣን ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW @EOTCW ወረብ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/ 👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @Eotcw #Join & share

ይሄውላችሁ

photo content

photo content
+1