ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
መስከረም ፰ ቀን ብቻ ዘካርያስ ይባላል።🌼
መስከረም ፰ ቀን በእሁድ ቢሆን መዝሙር።
በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ።በታች ቤት🌼 አጥመቆ ዮሐንስ ። የመስከረም ፰ ምስባክ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ዘቅዳሴ ምስባክ
ዕብ ፲፩፥፴፪-ፍ
ራይ ዮሐ ፮፥፱-፲፪
ግብ ሐዋ ፲፱፥፩-፮
ወንጌል ፦ማቴ ፳፫፥፳፫-ፍ
ቅዳሴ፦ ዘወልደ ነጎድጓድ
ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፣
እስመ ተዘከረ ዘይትሀሠሥ ደሞሙ ፣
ወኢረሥአ አውያቶሙ ለነዳያን ።
መዝ ፱፤፲፩
1 161
ል ነው።
❤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርዖንና በሠራዊት ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው።
❤ ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር። እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስለርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል። እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን "አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላልክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርዘኝ" አለው።
❤ ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ ሸፈነ ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሀን ፊቱ በራ።
❤ መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንደጠበቃቸው እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን "ለኢያሱ አስረክብ" ብሎ አዘዘው።
❤ ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝቡንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስትም እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠለት። ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በተራራ ውስጥ አረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ። የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ።
❤ በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጥላችው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ይሁዳ በጻፈው መጽሐፉ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው የእስራኤል ልጆችም አርባ ቀን አለቀሱለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሙሴ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ዲማድዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባል አውራጃ ደርሰባ ከሚሏት ከተማ ነው። እርሱ ሁል ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይገሠግሣል ድኆችንና በሽተኞችን መጐብኘትንም ይወዳል።
ብርሃናዊ ሰውም ተገልጦለት ሒዶ የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀበል አዘዘው ሰማያዊ የሆነ ቃል ኪዳንንም ገባለት በዚህም እጅግ ደስ አለው።
❤ አባቱንና እናቱንም ትቶ ከሀረጉ ወጣ ስለ ከበረ ስሙ በሚቀበለው መከራ ውስጥ ርዳታ እንዲሰጠው እንዲአጸናው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወደ ሀገር አትሪብም ሔዶ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ክርስቶስ ታመነ።
❤ መኰንኑም ታላቅ ስቃይን አሰቃይቶ የእስክንድርያ አገረ ገዥ ወደ ሆነ ወደ ሉክያኖስ ሰደደው። በመርከብም ውስጥ ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት በብዙ ደስታም አረጋግቶትና አጽናንቶ ቃል ኪዳንን ሰጠው ልቡናውም ፈጽሞ እጅግ ደስ አላት።
❤ መኰንኑ ሉክያኖስም በጽኑዕ ስቃይ አሰቃይቶ ራሱን በሰይፍ ቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበለ። የሀገሩ ሰዎችም መጥተው ስጋውን ወሰዱ ታላቅ ክብርንም አከበሩት ከስጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱስ ዲማንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ መስከረም 8 ስንክሳር።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ ለቅዱስ ዘካርያስ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለእግዚአብሔ ሰው ለሆነ፣ ለየዋሁ፣ ለቅኑ፣ ለጻድቁ፣ ለነቢያት አለቃ ለቅዱስ ሙሴ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ ዲማድዮስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባ አውራጃ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ ምግቡ የአጋዝን ወተት ከሆነ በዕረፍቱም ጊዜ ብዙ ተአምራትን ከአደረገ ከከበረ ከገዳማዊ ከቅዱስ ቂርቆስ ዕረፍት፣ ከሰማዕቱ ሉክዮስ ከመታሰቢያው፣ ከቅዱስ ኤርምያስና ከቅዱስ ዮሐንስ፣ ከቅዱስ አንዲዎና፣ ከቅዱስ ኤልያኖስና ከመነኰስ አሞንም ከመታሰቢያቸወ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚች ቀን የዓመቱ ወሮች መቊጠራያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣ ይኸውም መናዝል የሚለው ነው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውኅራ አሉ ምግብናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው።
+ + +
❤ "ሰላም ለዘካርያስ ካህን ወነቢይ ዘርእዮ ለካህን ዐቢይ ዘስሙ ዮሴዕ ዘይነብር ውስተ ምሥዋዒሁ ለእግዚብሔር"። ትርጉም፦ በእግዚአብሔር መሠዊያ ውስጥ ስሙ ዮሴዕ የሚባል ታላቁን ካህን ተቀምጦ ላየው ለካህኑና ለነቢዩ ዘካርያስ ሰላምታ ይገባል።ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ካህን ወነቢይ የበራክዩ ልጅ ቅዱስ ዘካርያስ፦ ይህም ካህን ስለ ልጁ ዮሐንስ መወለድ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በነገረው ጊዜ ነገሩን አምኖ አልተቀበለም። ስለዚህም ሕፃኑ እስቲወለድ ዲዳ ትሆናለህ አለው። በተወለደም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው የልጁንም ስም ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። እርሱና ሚስቱ በእግዚአብሔር ሕግ ያለ ነቀፋ የጸኑ ደጎች እንደሆኑ የከበረ ወንጌል ስለዚህ ምስክር ሆኗል።
❤ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም በተወለደ ጊዜ ሊሰግዱለት የጥበብ ሰዎች መጡ። ሄሮድስም ስለ መንግሥቱ ፈራ ደነገጠም። ስለዚህም ጭፍሮቹን ልኮ በይሁዳ አገር የቤተ ልሔምንና የገሊላን ሁሉንም ሕፃናት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመት የሚሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ገደላቸው ሰነፍ የሆነ ሄሮድስ ክርስቶስን ከሕፃናት ጋር እንደ ሚገድለው አስቦ ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጾለት ስለአዘዘው ጌታችን ሕፃኑንና እናቱን እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብጽ አገር መጡ። ኤልሳቤጥ ግን ሕፃኗን ዮሐንስን ይዛ ወደ ዱር ወጣች ወደ ሲና በረሃም ሸሸች በዚያም ሕፃኗን እያሳደገች ሰባት ዓመት ኖረች ከዚህም እርሷ አረፈች ሕፃኑም በመምህርነት ለእሥራኤል እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ።
❤ ሕፃናትንም ከገደላቸው በኋላ ዮሐንስ ክርስቶስ እንደሆነ ሄሮድስ አሰበ ተጠራጠረ ከአባቱ ከዘካርያስ ዘንድ ሕፃኑን ይሹ ዘንድ ወታደሮቹን ላከ ዘካርያስም "ሕፃኑ ያለበትን ወይም እናቱ ያለችበትን እኔ አላውቅም" አለ። ሄሮድስም ልጅህን "ካላመጣህልኝ እኔ እገድልሃለሁ" አለው። ዘካርያስም ከእርሱ ዛቻ የተነሣ አልፈራም ወታደሮቹንም አዝዞ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል ገደሉት ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም ሥጋውን ሠወረ ደሙ ግን እንደ ደንጊያ ሆነች።
❤ ካህናቱና ሕዝቡ እንደ ልማዳቸው ለጸሎት በመጡ ጊዜ ከካህናት አንዱ ወደ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገባ። የረጋ ደምን አገኘ ከመጠዊያውም እንዲህ የሚል ቃልን ሰማ "እነሆ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ተገደለ የሚበቀልም እስሚመጣ ደሙ ስትጮኽ ትኖራለች"።
❤ እንዲህ የሚልም አለ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት የሆነ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ይህ አይደለም ያ አልተገደለም በዕድሜው ኡረት በሚባል አገር ሞተ እንጂ ሥጋውም በዚያ ያለ ጥፋት ተገኝቶ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለታል። የዚህ ዘካርያስ ግን ሥጋው አልተገኘም ስለ መገደሉ የደሙ ድምፅ ምስክር ሆነ እንጁ።
❤ ደግሞ እንዲህ ተባለ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ከአይሁድ አንድ ሰው መጥቶ "የእግዚአብሔር መልአክ ትወልዳለህ" ብሎ ነግሮት ለዘካርያስ ልጅ ተወልዶለታል "ምናልባት እርሱ ክርስቶስን ይሆን" አለው። ስለዚህ ሄሮድስ ሕፃኑን ዮሐንስን ይገድሉት ዘንድ ወታደሮችን ላከ።
❤ ዘካርያስም ወታደሮችን እንዲህ አላቸው "ሕፃኑን እኔ ወደሌላ ቦታ ወስጄዋለሁ ከእኔ ጋራ መጥታችሁ ራሳችሁ ከዚያ ቦታ ውሰዱት" ወደ ቤተ መቅደስም እስከ አስገባቸው ድረስ ወታደሮቹ አብረውት መጡ። እርሱም ሕፃኑን ልጁን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኑሮ ጸለየበት ይህም የልጁን መወለድ የእግዚአብሔር መልአክ ለእርሱ የነገረበት ነው።
❤ ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ሕፃኑን ዚፈታ ወደሚባል በረሀ ነጥቆ ወሰደው ሕፃኑንም ባላገኙት ጊዜ አባቱን ዘካርያስን ገደሉት። ስለዚህም ጌታችን አይሁድን "በቤተ መቅደሰ መካከል የገደላችሁት የዘካርያስ ደም በላያችሁ ይደርሳል" አላቸው ለመገደሉ ምክንያት አይሁድ ናቸውና እንዲህ አለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በካህኑ ቅዱስ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለሙሴ ሊቀ ነቢያት ዘርእየ ሱራኄሁ ለጸባኦት፤ ዘተመጠወ እምእደዊሁ ኦሪተ በጾም ወበጸሎት"። ትርጉም፦ የሠራዊት ጌታን የብርሃን ወገግታ ያየ፤ በጾምና በጸሎት ከእጆቹም ኦሪትን (ሕግን) ለተቀበለ ለሊቀ ነቢያት ለቅዱስ ሙሴ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ፦ ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው።
ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም። እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና። በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው።
❤ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊውም ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው። በማግሥቱ ደግሞ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ። አንዱ ዐመፀኛም "ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን" አለው።
❤ ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቍጥቋጦ ውስጥም እሳት እየነደደ ራእይን አየ። አይቶ ሊረዳ በቀረብ ጊዜ ጳጦስ በተባለ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገረው። ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲአወጣቸው አዘዘው።
❤ ከዚህን በኋላ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ በግብጻውያን ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን አመጣ። መጀመሪያው የወንዙን ውኃ ደም ማድረግ የመጨረሻው የግብጻውያንን የበኵር ልጅ መግደ
1 161
ትዕቢት
ትዕቢት ከታላቅ ፈተና /ጥልቅ ጉድጓድ/ ለመውደቅ የሚዘጋጁበት የኑሮ መርዝ ፣ የኃጢአት ሥር ነው። ትዕቢት ራስን ከፍ እድርጐ ሌላውን ማዋረድ ነው፡፡ ትዕቢተኛ ሰው ከራሱ ጋር ብቻ የሚነጋገር እንጂ የሌላውን ምከርና ተግሳጽ የማይሰማ ነው። ሳጥናኤል ከስልጣኑ የተዋረደው በትዕቢቱ ነው። ትዕቢት የሚጠፋው በጾምና በጸሎት በስግደት ነው።
ማስረጃ
ኢሳ. 5፥15 ኢሳ.13፥11
ሚል.4፥13 መዝ.61፥10
ዘጸ. 9፥17 1ኛሳሙ.2፥3
ምሳሌ.11፥2 ፣ 8፥13 ምሳሌ.16፥5
ምሳሌ.21፥4ማቴ.23፥12
ሉቃ.14፥11 ሮሜ.11፥12
ሮሜ.12፥3 2ኛጢሞ.3፥2
ያዕ.4፥6 1ኛጴጥ. 5፥5
✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
https://t.me/Eotcw
1 161
የእለቱ የቅዳሴ#ምስባክ፦
መዝ ፹፫፥፮
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን።
#ትርጕም፦
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤
ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
https://t.me/Eotcw
1 161
ች ሰዎች ያስገባቸው ዘንድ ዕንባን በማፍሰስ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እግዚአብሔርም በእርሱ ላይ ብቻ ጽኑዕ ደዌ አመጣ ወደ ክርስቲያን ወገኖች ግን ምንም ምን አልደረሰም። በግብጽ አገር በፈርዖንና በሠራዊቱ በግብጻውያንም ላይ መቅሠፍት ሲታዘዝ ወደ እስራኤል ወገን እንዳልደረሰ እንዲሁ ሆነ።
❤ በዚያም ወራት እንዚያ ሥራየኞች የቅዱስ ሳዊርያኖስን ቃል ሰምተው ትእዛዙን ስለ አልተቀበሉ ስለዚህም ይህ ጽኑ ደዌ በላያቸው እንደመጣ አወቁ። ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስም መጥተው በደላቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ክርስቲያኖችም ያደርጋቸው አስተምሮ አጥምቆ ክብር ይግባውና ከክርስቶስ መንጋዎች ጋር አንድ አደረጋቸው። ያቺ አገር ሁለመናዋ አንድ ማኅበር አንድ መንጋ ሆነች።
❤ ሰይጣንም ልብሱ በተቀደደ ሽማግሌ አማሳል ሆኖ ፈጽሞ የሚጮህ ሆነ እንዲህም አለ። "ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአለው ቦታ ሁሉ ጨነቀኝ በግብጽ አገርም ጠንካሮች መነኰሳት ተመሉባት በሮሜ አገርም ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ በውስጧ ይኖራል ደግሞ በቁስጥንጥንያ ዮሐንስ አፈወርቅ አለ ይህ ቦታ ለእኔ ቀረልኝ ብዬ ነበር እነሆ ሳዊርያኖስ ከእጄ ውስጥ ነጠቀኝ" አለ።
❤ እንዲህም ሆነ የፋርስ ሰዎች ሊወጉአቸው ሽተው ወደ አኖሬዎስና ወደ አርቃዴዎስ መልእክትን ላኩ እሊህ ደጋጎች ነገሥታትም የፋርስ ሰዎች የላኩትን ደብዳቤ ወደ ቅዱስ ሳዊሮያኖስ ላኩት። እርሱም ያቺን ደብዳቤ በአነበባት ጊዜ የደብዳቤውን መልስ ወደ ነገሥታት አኖሬዎስና አርቃዴዎስ እያስረዳ እንዲህ ብሎ ጻፈ "እኛ የክርስቶስ ከሆን መንግሥታችንም የክርስቶስ ነው እንዲህም ከሆነ የጦር መሣሪያን የጦር ሠራዊትንም አንሻም"። እግዚአብሔርም ከቀደሙ ነገሥታት ጋር ሁኖ ያደረገውን እንዴት እንዳዳናቸው ጠላቶቻቸውንም እንዴት ድል እንዳደረጓቸው አስታወሳቸው።
❤ ታላቁም ጾም ሳይደርስ የፋርስ ሰዎች አፍረው ከእነርሱ ዘንድ ተመልሰው ሔዱ። ስለ ዮሐንስ አፈወርቅም ከኤጲስቆጶሳት ጋር በአመጡት ጊዜ ንግሥት አውዶክስያን በምክሩ ሁሉ መክሮዋትና ገሥጿት ነበር። ስለ ዮሐንስ መሰደድም እርሱ ምንም ምን ያደረገው ስምምነት የለም ንግሥቲቱም ምክሩን ባልሰማች ጊዜ ወደ አገሩ ተመለሰ።
❤ ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ እሊህም ሃይማኖታቸው የቀናች ሰዎች በአሉባቸው አብያተ ክርስቲያናት እስከ ዛሬ ይኖራሉ። ቅዱስ ሳዊርያኖስም ሸመገለ ዕድሜውም መቶ ዓመት ሆነው ከሥጋውም ከመለየቱ በፊት በዐሥር ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ከዚህ ዓለም ከድካምም ወደ እረፍት እንደ ሚወጣ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ጠራቸው ክብር ይግባውና የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸውና በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ነፍሱንም በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ። ዕረፍቱም የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ኤጲፋንዮስ በዐረፈ በሁለት ዓመት ዮሐንስ አፈወርቅ በዐረፈ በአንድ ዓመት ነው። ሥጋውንም እንደ ሚገባ በንጹሕ ልብስ ገነዙ ብዙ መዝሙራትንና ምስጋናዎችን አድርገውለት በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሳዊርያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱሳን ሰማዕታት አጋቶን፣ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ አሞን እናታቸው ቅድስት ራፊቃ፦ እሊህ ቅዱሳንም በላይኛው ግብፅ ቊስ ከሚባል አውራጃ ከቆንያ ከተማ ናቸው። ለእርሳቸውም ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ተገልፆላቸው። ከእነርሱ የሚሆነውን ስብራ በምትባል ከተማ እርሷም ወደ እስክንድርያ ክፍል ናት በዚያ የምስክርነት አክሊል እንደሚቀበሉ ሥጋቸውንም ወደ ግብፅ ደቡብ ነቅራሀ ወደሚባል አገር እንደሚወስዱ አስረዳቸው ቅዱሳኑም በዚች ራእይ ደስ አላቸው።
❤ በማለዳም ተነስተው ገንዘባቸውን ሁሉ ለድሆችና ለችግረኞች ሰጡ ከእነርሱም የሚበልጥ ወንድማቸው አጋቶን በሀረጉ ሹም ነበር በሁሉም ዘንድ የተወደደ ነው ራፊቃ እናታቸውም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ በመከራ ስቃይ ላይ የሚፀኑና የሚታገሱ እንዲሆኑ ታበረታታቸው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ቊስ ወደ ሚባል አገር ሲደርሱ በመኰንኑ በዲዮናሲዮስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። ከእነርሱም አስቀድሞ እናታቸው ራፊቃን አሰቃያት እርሷም በስቃይ ውስጥ በመታገስ ደስተኛ ነበረች ከዚህም በኋላ አራቱን ልጆቿን አሰቃያቸው።
❤ እነርሱንም በማሰቃየት በሰለቸ ጊዜ ወደ እስክንድርያ እንዲልካቸው ወገኖቹ መከሩት በእነርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ህዝቡ እንዳያምን ፈርተዋልና። እነርሱ በሁሉ ዘንድ የተወደዱ ስለሆነ በእርሳቸውም ምክንያት ከዚህ በፊት ብዙዎች ሰዎች በክብር ባለቤት በክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሙተዋልና የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀብለዋልና።
❤ ወደ እስክንድርያም ገዥ ወደ አርማንዮስ ቅዱሳኑን በአመጡአቸው ጊዜ በዚያን ወቅት ስሟ ስብራ በምትባል አገር በዚያ ነበር። የተጋድሎአቸውንም ፅናት አውቆ ፅኑ ስቃይን አሰቃያቸው ሥጋቸውንም ቆራርጦ ከመንኰራኩር ውስጥ ጨመራቸው። ዳግመኛም ዘቅዝቀው ሰቀሉአቸው በዚህም ሁሉ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መኰንኑና የርሱ ሰዎች ሁሉ እስቲአፍሩ ያለ ምንም ጥፋትና ጉዳት የሚያነሳቸው ሆነ።
❤ ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን ይቆርጡ ዘንድ ሥጋቸውንም በባሕር ሊጥሉ በታናሽ ታንኳ ጫኑአቸው። በዚያንም ጊዜ ከግብፅ በስተደቡብ መፂል ከሚባል አውራጃ ነቅራሀ ከምትባል መንደር ወደ አንድ ባለ ፀጋ እግዚአብሔር መልአኩን ላከ።
❤ የቅዱሳኑንም ሥጋ እንዲወስድ አዘዘው። እርሱም ወሰዳቸው "የፃድቃን ማደሪያቸው ይህ ነው" የሚል ቃልን ሰማ የመከራውም ወራት እስከሚአልፍ በዚያ አኖሩአቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ገለጡአቸው ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንንም ሰርተውላቸው ስጋቸውን በውስጧ አኖሩ። እግዚአብሔርም ከሥጋቸው ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራትን ገለጠ በዚያም ወራት ሥጋቸውን ስሙንጥያ ወደሚባል አገር አፈለሱ።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም፦ 7 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለዲዮስቆሮስ ሃይማኖተ ንጉሥ ዘተሣለቀ። ተዋሕዶተ አምላክ ወሰብእ አመ ለክልኤ ነፈቀ። ያስተጻንዕ ህየ እለ ሀለዉ ደቂቀ። ዘተነጽየ እምነ ጽሕሙ ወእምአስናኒሁ ዘወድቀ። ፍሬ ሃይማኖቱ ፈነወ ብሔረ ርኁቀ"። ትርጉም፦ ሰው የኾነ የአምላክን ተዋሕዶ ለኹለት በከፈለ ጊዜ በንጉሥ ሃይማኖት ላይ የተሣለቀ ለኾነ ለዲዮስቆሮስ ሰላምታ ይገባል፤ በዚያ ያሉትን ልጆች ያጽናና ዘንድ ከወደቁ ጥርሶቹ ከተነጨ ጽሕሙ የሃይማኖት ፍሬ አድርጎ ወደ ሩቅ ሀገሩ ላከ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም7።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝጰ83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥13-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥ 14-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥23-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች ማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል የቅድስት ሐና የልደት በዓልና የአባ ዲዮስቆሮስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።
https://t.me/Eotcw
1 161
ያገለገለቻት ናት።
❤ የዚች ቅድስት ሐና ኢያቄምን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋታን አናስታውሰውም አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥ እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክ በሥጋ ለወለደች ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባ ሆናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።
❤ ይች ቅድስት ሐና መካን በመሆኗ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔር በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባት ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷ አምላክ የወለደች አመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።
❤ ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጠን የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 11 ስንክሳር።
+ + +
❤ የገብላ ኤጲስቆጶስ የከበረ አባት አባ ሳዊርያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ የአበባቱ ስም አብስርያኖስ ይባላል የሀገረ አቴናንም ፍልስፍና ተማረ ከዚያም ወደ ቂሣርያ ሔዶ እውቀታቸውን ሁሉ ተማረ። ዳግመኛም ወደ ሮሜ ከተማ ተመልሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ ከጥቂት ዘመናት የብሉይንና የሐዲስን መጸሕፍት አጠና።
❤ ከዚህም በኋላ ቁጥር የሌለው ብዙ ገንዘብን ትተውለት ወላጆቹ አረፉ ስለርሱ ፈንታ መቶ ዕጥፍ ይቀበል ዘንድ ወዶ ያንን ገንዘብ ለክብር ባለቤት ለክርስቶስ ሊሰጥ ወደደና ድሆችን መጸተኘኞችን ምስኪኖችን ችግረኞችንም በውስጥ ይቀበል ዘንድ የእንግዳ መቀበያ ቤትን ሠራ። አትክልትም ተከለ ፍሬዎችን ተሸክመው የሚያመጡላቸውን ሠራተኞችን አደረገ እነዚያም ስለ ድሆችና ስለ ችግረኞች የተሠሩ ቦታወች እስከ ዛሬ በስሙ የሚጠሩ ሆኑ።
❤ አገረ ገዥ የሆነ አጎቱን በሮሜው ንጉሥ በአኖሬዎስ ዘንድ እንዲህ ሲል ወነጀለው "በከበረ ወንጌል ቃል ኪዳን እነደገባ ከእርሱ ዘንድ ስለ ርሱ መቶ እጥፍ እቀበላለሁና እኔ ገንዘቤን ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እሰጠዋለሁ" በማለት ሳዊርያሮስ ገንዘቡን ሁሉ እንደበተነ። ይህም ነገር ለንጉሡ ደስ አሰኘው ፈጸሞም በእርሱ ደስ አለው እጅግም ወደደው ከእርሱም ከቤተ መንግስቱ እንዳይለይ ንጉሡ አኖሬዎስ አዘዘው ከእርሱም ጋር ሁል ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን በመሔድ ሌሊቱን ሁሉ ቁመው ያድራሉ ንጉሥ አኖሬዎስም የመነኰሳትን ሥራዎች ስለሚሠራ ከልብሰ መንግሥቱ በታች በሥጋው ላይ ማቅ ይለብስ ነበር።
❤ በዚህም ወራት ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ የነበረ አባ ዮናክንዲኖስ ነው ለእርሱም ሳዊርያኖስ በብዙ ሕዝብ ላይ ኤጲስቆጶስ መሆን እንዲገባው እግዚአብሔር ገለጸለት። ሊቀ ጳጳሳቱም እጅግ የሚወደውና የሚያከብረው ሆነ ከቶ እንድለየውም አይሻም ነበር በሁሉም ዘንድ ተወዳድ ሆነ ዜናውም በቁስጥንያው ንጉሥ በቴዎዶስዮስ ዘንድ ተሰማ።
❤ ሰዎች ሁሉ እንደሚያከብሩት በአየ ጊዜ ድካሙ በውዳሴ ከንቱ እንዳይጠፍ ከዚያች ቦታ በሥውር ሊወጣ ወደደ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ተገለጸለት ወደ ሀገረ ገብሪ ሔዶ ለብዙ ነፍሳት የገዳም አባት እንዲሆን አዘዘው በሌሊትም ወጥቶ ሔደ የምንኰስና ልብስን ከለበሰ በኋላ ደቀመዝሙር ቴዎድሮስ ከእርሱ ጋር ነበር ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ ገብላ ገዳም እስከሚደርስ በፊቱ የምትሔድና የምትመራው በመኰራኩር አምሰል የብርሃን ሠረገላ ላከለት።
❤ በዚያም ገዳም አበ ምኔት የሆነ ጻድቅ ሰው ነበር የቅዱስ ሳዊርያኖስንም መምጣት ጌታችን በራእይ አስረዳው ወደርሱ መጥቶ ተቀበለው ሰላምታም ሰጠውና ስለእርሱ ጌታችን በራእይ ተገልጾለት እንዳስረዳው ነገረው የጌታንም ቸርነት እጅግ አደነቁ።
❤ ዜናውም በሀገሮች ሁሉ ተሰማ የማይቁጠሩ ብዙ ሰዎች ወደርሱ ተሰበሰቡ። ንጉሥ ቴዎዶስዮስም ለከበረ ሳዊርያኖስ ገዳማትን የሚሠሩለት ብዙዎች ሰዎችን ሹሞችንም ከእርሱ ዘነድ ላከ የእግዚአብሔርም መልአክ በውስጣቸው ገዳም የሚሠሩባቸውን ቦታዎች ወሰነላቸው ብዙ ነፍሳትን የሚያጽናና የሚያረጋጋ ሆነ።
❤ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ከእርሳቸውም በሀገር ገብላ መኰንን ልጅ ሰይጣን እንደደረባትና መኰንኑም "ሳዊርያኖስን ከዚህ አገር ካላበረርክ ከልጅህ አልወጣም ያለው ነው"። መኰንኑም ይህን ገነር በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ወደ ከበረ ሳዊርያኖስ ሒዶ ሰይጣን ያለውን ነገረው ደሞም ልጅን ያድናት ዘንድ ለመነው።
❤ ቅዱስ ሳዊርያኖስም እንድህ ብሎ ደብዳቤን ጻፈለት "ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሰሱስ ክርስቶስ ስም ከእሷ ወጥተህ ሒድ አባቷም ያንን ደብዳቤ ተቀብሎ ወደልጁ ሰደደ ጊዜም ከመኰንኑ ልጅ ሰይጣን ወጥቶ ሔደ ልጅቷም ዳነች።
❤ ዳግመኛም ታላቅ ሠራዊት እስቲሆኑ ድረስ ብዙዎች ወንጀለኞች ሰዎች ተሰበሰቡ ወደ ከበረ ሳዊርያኖስም ገዳም ገብተው ሊያፈረርሱት ፈለጉ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም በላያቸው ጨለማን አመጣ ምንም ምን ሳያዩ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ኖሩ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ይቅር ይለቸው ዘንድ ብዙ ዕንባ በመፍሰሰ ለመኑት እርሱም ወደ ቦታዎቻቸው መልሶ ሰደዳቸው።
❤ ዳግመኛም በገዳማቱ ውስጥ ያለ በእርሱ የሚተዳደሩ መነኰሳት ሁሉ ከእነርሱ የታመመ ቢኖር በላያቸው በመጸለይ ያድናቸዋው የሚያጸናናቸውና ሁሉም እንደ እግዚአብሔር መላእክት እስቲሆኑ ፈረሀ እግዚአብሔር የሚያስተምራቸው ሆነ። እንዲህም ሆነ ስሙ ፈላታዎስ የሚባል የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ እራይ ተገልጦለት ቅዱስ ሳዊርያኖስ በእርሱ ፈንታ ኤጲስቆጶስነት ይሾም ዘንድ እንዳለው አወቀ ያን ጊዜም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ላከ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ኤጲስቆጶስነት እንዲሾሙት አዘዛቸው ለዚች ሹመት እግዚአብሔር መርጦታና።
❤ ወዲያውኑ ደጋጎች ነገሥታት አኖሬዎስና አርቃዴዎስ ወስደው ገብላ በሚባል አገር ላይ ኢጶስቆጶስነት ሹሙት ስለ መንጋዎቹና ስለ ወገኖቹም አጠባበቅ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ።
❤ በዚያችም አገር እጅግ አዋቂ የሆነ የሙሴን ሕግ በማወቁ የሚመካ አንድ ስሙ ስቅጣር የሚባል ይሁዳዊ ነበር። እርሱም ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእርሱ ጋር ተከራከረ ግን ከቅዱስ ሳዊርያኖስ አንደበት የሚመጣውን ቃል ይሰማ ዘንድ አልተቻለውም።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ሳዊርያኖስ በራእይ ተገልጦለት ይህ አይሁዳዊ እርሱ ራሱ ክርስቶስ ከአከበራቸውና ከባረካቸው ወገን ውስጥ ሊሆን እንዳለው አስረዳው።
ያ አይሁዳዊውም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ አስጨናቂዎች የሆኑ የስቃይ ቦታዎች በሕልሙ በማየት እንዲህ የሚለውን ቃል "ታላቅ በሆነ የዘላለም ሥቃይ ውስጥ የሚኖሩ እሊህን ከሀዲዎች ዘመዶችህ አይሁድን እነሆ እይ እነርሱም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ያላመኑ ናቸው"። በማግሥቱም ያ አይሁዳዊ ወደ ቅዱስ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእግሩ በታች ወድቆ ሰገደለት ክርስቲያንም ያደርገው ዘንድ ለመነው ያን ጊዜም እርሱንና ቤተሰቦቹን የሀገር ሰዎችንም ሁሉ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
❤ የቀሩትም አይሁድ ሁሉ አለቃቸው ክርስቲያን እንደሆነ በሰሙ ጊዜ አምነው ተጠምቀው ክርስቲያኖች ሆኑ። እንዲሁም ኒሞንጦስ የሚባሉ ሌሎች ሥራየኞች ሰዎችን ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት እንዲገቡ ቅዱስ ሳዊርያኖስ ለመናቸው እነርሱ ግን በሥራያቸው ስለሚታበዩ ከእርሱ ቃሉን አልሰሙም እነርሱም ባዕድ ወደ እነርሱ የመጣ እንደሆነ በፊቱ አረርን ይበትናሉ ምንም ምን ማየት አይችልም።
❤ ቅዱስ ሳዊርያኖስንም ወደ ቀናት ሃይማኖቱ እሊህን ሥራየኞ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖት በጉባኤ ኬልቄዶን (ከለባት) በ 451 ዓ.ም በንጉሥ መርቅያኖስና በሚስቱ በንግሥት ብርክልያ (በሊዮናውያን) ጢሙን ለተነጨና ጥርሱንም ለተነቀለ ለታላቁ ሊቅ ለእስክድርያ ሃያ አምስተኛ ኤጴስቆጶስ ለአቡነ ዲዮስቆሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ለእመቤታችን እናት ለቅድስት ሐና ለልደቷ በዓል መታሰቢያ፣ ለመጥምቀ መለኮት እናት ለቅድስት ኤልሳቤጥ ለመታሰቢያዋ በዓል፣ ለገብላ ኤጴስቆጶስ ለከበረ አባት ለአባ ሳዊርያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት ለአጋቶንና ጴጥሮስ ለዮሐንስና ለአሞን ለእናታቸው ራፈቃ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ከቅዱስ ፋሲለደስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ ከሁለት ሺህ ሰዎች፣ ከጋንግራ ሰው ዳሳ፣ ከአንጾኪያ ኤጲስቆጶስ ከናውላ፣ ከመነኵሴውም ከጴጥሮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለዲዮስቆሮስ ዘተመልኀ ጥረሲሁ፤ ወተነጽየ ጽሕሙ ለክርስቶስ በእንተ ስሙ"። ትርጉም፦ በክርስቶ ስም (ስለክርስቶስ ስም) ጢሙን የተነጨ፤ ጥርሱንም የተነቀለ ለኾነ ለዲዮስቆሮስ ሰላምታ ይገባል።
+ + +
❤ የእስክንድርያ አገር ሃያ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ሊቁ አባ ዲዮስቆሮስ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ በጠሩት ጊዜ ሲደርስ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሠላሳ ስድስት የሆነ ታላቅ ጉባኤን አየ። እንዲህም አለ "ይህ ታላቅ ጉባኤ እስቲሰበሰብ ድረስ በሃይማኖት ላይ የተገኘው ጉድለት ምንድን ነው"።
"ይህ ጉባኤ የተሰበሰበው በንጉሥ ትእዛዝ ነው" አሉት። እንዲህም አላቸው "ይህ ጉባኤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጬ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ግን የዚህ ጉባኤ መሰብሰብ በንጉሥ ትእዛዝ ከሆነ የሰበሰበውን ጉባኤ ንጉሡ እንዳሻው ይምራ"።
❤ ከዚህም በኋላ አንዱን ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ሁለት ምክር የሚያደርግ የክህደት ቃል በውስጡ የተጻፈበትን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ የከበረና የተመሰገነ ዲዮስቆሮስ ቀደደ። በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የከበረ ዲዮስቆሮስም በጉባኤው ፊት እንዲህ ብሎ አስረዳ "ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት የጠሩት ጌታችን ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን ያደረገው ከሀሊ ስለሆነ ሰውነቱና መለኮቱ በሥራው ሁሉ የማይለይ አንድ ነው"።
❤ ደግሞ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ ከተናገረው የአካላዊ ቃል ተዋሕዶ እንደ ነፍስና ሥጋ እንደ እሳትና ብረት ተዋሕዶ ነው ያለውን ቃል ምስክር አድርጎ በማምጣትም አስረዳ። "እሊህም የተለያዩ ሁለቱ ጠባዮች ስለ ተዋሕዷቸው አንድ ከሆኑ እንዲሁም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አንድ መሲሕ አንድ ጌታ አንድ ባሕርይ አንድ ምክር ነው እንጂ ወደ ሁለት አይከፈልም" አላቸው።
❤ ከዚያም ከተሰበሰበው ጉባኤ ውስጥ ማንም ሊከራከረው የደፈረ የለም ከውስጣቸውም የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነው ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን ጉባኤ አስቀድሞ ተሰብስበው የነበሩ አሉ። ወደ ንጉሥ መርቅያኖስና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክልያ "ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ዲዮስቆሮስ በቀር ስለ ሃይማኖት ትእዛዛችሁን የሚቃወም የለም" ብለው ነገር ሠሩበት።
❤ ቅዱስ ዲዮስቆሮስንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት ከእርሱም ጋር ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ከጉባኤው የሆኑ ነበሩ ከጥዋትም እስከማታ እርስበርሳቸው ሲከራከሩ ዋሉ። የከበረ ዲዮስቆሮስም የቀናች ሃይማኖቱን አልለወጠም ንጉሡና ንግሥቲቱ በእርሱ ተቆጥተው እንዲደበድቡት አዘዙ ስለዚህም ደበደቡት ጽሕሙን ነጩ ጥርሶቹንም ሰበሩ እንዲህም አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ የተነጨውን ጽሕሙን ያወለቁትንም ጥሩሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ አገር ላካቸው "እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው" አላቸው። ለጉባኤውም የተሰበሰቡ ኤጲስቆጶሳት በዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን መከራ በአዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ በእርሱ የደረሰ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ ስለዚህም ከመናፍቁ ንጉሥ ከመርቅያኖስ ጋር ተስማሙ።
❤ በሲኦል ውስጥ ይቆርጡት ዘንድ ባለው ምላሳቸውም "ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት" አሉት ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ። ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ተመልሶ ያን በውስጡ የጻፉበትን ደብዳቤ ያመጡለት ዘንድ ወደእሳቸው ላከ እነርሱም ላኩለት እነርሱ እንደጻፉ በውስጡ እርሱ የሚጽፍ መስሏቸዋልና። እርሱ ግን አባቶቻችን ሐዋርያት ከአስተማርዋት ከቀናች ሃይማኖት በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጲሳት አባቶቻችን ከሠሩት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ።
❤ መናፍቁ ንጉሥም ተቆጥቶ ጋግራ ወደም ትባል ደሴት እንዲአግዙት አዘዘ ወደዚያም ወሰዱት። ከእርሱም ጋር የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አብሮ ተሰደደ። ሌሎችም አራት መነኰሳት የሸሹ አሉ። እሊህም ስድስት መቶ ሠላሳ ስድስት ኤጲስቆጶሳት ተቀምጠው በኬልቄዶን ለራሳቸው መመሪያ የሚሆናቸውን ሥርዓት ሠሩ።
❤ የከበረ ዲዮስቆሮስንም በአጋዙት ጊዜ ከዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት ኤጲስቆጶስ ንስጥሮሳዊ ስለሆነ ታላቅ ጉስቁልናንም አጎሳቁለው በእጆቹ ላይ ድንቆች ታላላቅ ተአምራቶችን እግዚአብሔር እስከገለጠ ድረስ። የደሴቱም ሰዎች ሁሉ ሰገዱለት አከበሩት ከፍ ከፍም አደረጉት እግዚአብሔርም የመረጣቸውን በቦታው ሁሉ ያከብራቸዋልና። አባ ዲዮስቆሮስም አባ መቃርስን "አንተ በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ አለህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከምእመናን ነጋዴዎች ጋር ወደ እስክንድርያ ላከው በእርሱ ላይ ትንቢት እንደተናገረ ገድሉን በዚያ ፈጸመ።
❤ የከበረ አባት ዲዮስቅሮስ ግን መልካም ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም አገልግሎ ከዚች ኃላፊት ከሆነች ኑሮው ወጥቶ ሔደ የሃይማኖቱንም ዋጋ አክሊልን ተቀብሎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ገባ ያረፈውም በዚያች በደሴተ ጋግራ ነው ሥጋውንም በዚያው አኖሩ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዲዮስቆሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለሐና እንተ ወለደታ ለማርያም ዘኮነት ተንከተመ ጽድቅ በኵሉ ዓለም፤ ድንግል ወእም፤ ወላዲቱ ለፀሓይ ዳግሚት ሰማይ"። ትርጉም፦ ፀሓይን የወለደችው ኹለተኛዪቱ ሰማይ፤ ድንግልም እናትም፤ ለዓለሙ ኹሉ የእውነት ድልድይ (መሸጋገሪያ) የኾነችዪቱን ማርያምን ለወለደቻት ለሐና ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ የእመቤታችን ቅድስት ሐና፦ ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን
