ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአርሳንዮስ እንተ መሀረ ትምህርተ። ደቂቀ ንጉሥ ፪ተ። ሶበ ጸለየ ለአምላክ ከመ ይመርሖ ፍሬተ። መጽአ ቃል ኀቤሁ እንዘ ይብል ዘንተ።እምዓለም ጉየይ ወትድኅን አንተ"። ትርጉም፦ ሁለቱ የንጉሥ ልጆችን ትምህርትን ለአስተማረ ለአርሳንዮስ ሰላምታ ይገባል፤ መንገዱን ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ አንተ ከዚህ ዓለም ውጣ ትድናለህ አለው። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 13።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ለደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያ ቅዳሴ ቤቱ ለስድስተኛ ዓመት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የበዓሉ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ተቀደሲ ወንሥኢ ኃይለ ኦ ቤተ እግዚአብሔር እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ዘያበርግህ ለኪ በኃይሉ ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሐነፃ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ ቤተ እግዚአብሔር ሆይ ተቀደሺ ኃይልንም ልበሺ ንጉሥሽ እያበራ ወደ አንቺ ደርሷልና፡፡ ይእቺን ቤት አስቀድሞ አብ ሠራት ወልድ አነፃት መንፈስቅዱስ ፈፀማት፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በ2009 ዓ.ም አዲሱ ቤተ መቅደስ አልቆ ግንቦት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ገብቶ ግንቦት 13 የተከበረበት በዓል ነው። በ2014 ዓ.ም ደግሞ ስድተኛ ዓመቱ ክብረ በዓል ይከበራል።
+ + +
❤ የበዓሉ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወንሰግድ ውስተ መካነ ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ። ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ"። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥44-ፍ.ም።
+ + +
❤ የበዓሉ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትተሐወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ 45፥4-5። የሚነበበው መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 14፥29-34፣ 2ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 13፥38-44። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ እግዚአብሔር አብ የቅዳሴ ቤት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ አባት በገድል ተጠምዶ ለኖረ ለብልህ ከልቅሶ ብዛትም የተነሣ የቅንድቡ ጠጉር ለተነቀለ ለአባ አርሳንዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አባ አርሳንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ሰዎች ከባለጸጎችና ከታላላቆቿ ነው። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረው ዲቁናን አሾሙት። ከዚህም በኋላ አቴና ወደሚባል አገር ሒዶ ፍልስፍናን የፀሐይንና የጨረቃን የከዋክብትም አካሔዳቸውን የዘመናትንም መለኪያና መቊጠሪያ ተምሮ በመልካም አጠና። ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ። በመንፈሳዊ ትምህርቱም ፍጹም ሁኖ አምላካዊ ትሩፍትን የሚሠራ ሆነ።
❤ በሮሜ አገርም ታላቁ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ ልጆቹን አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን የሚያስተምርለት ጥበበኛ ደግ ሰው ፈለገ። ይህንንም ቅዱስ ወደ ንጉሥ ወሰዱት። ንጉሡም ልጆቹን አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን እንዲያስተምርለት አዘዘው እርሱም ታዝዞ የንጉሡን ልጆች እንሚገባ ሊያስተምር ጀመረ። በብዙ ትግልና ድካም ስለሚአስተምራቸው ያለርኅራኄ ብዙ ድብደባን ይደበድባቸው ነበር።
❤ ንጉሥ ቴዎዶስዮስም በዐረፈ ጊዜ ልጆቹ አኖሬዎስ በሮሜ አገር አርቃዴዎስም በቊስጥንጥንያ ነገሡ። እግዚአብሔር በአርሳንኖስ ልብ ፍርሀትን አሳደረ በታናሽነታቸው ጊዜ ሲአስተምራቸው የሚመታቸው ስለሆነ በዚህ ምክንያት ከዓለም ይወጣ ዘንድ የነፍሳቸውንም ድኅነት ለሚሹ የሚበራ መብራት ሁኖ ሌሎች ይበሩበት ዘንድ አነሣሣው። ምን እንደሚአደርግ በልቡ እያሰበ ሳለ እንሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል መጣ "አርሳኒ አርሳኒ ከዚህ ዓለም ውጣ አንተም ትድናለህ"። ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ተነሣ እንጂ አልዘገየም ወዲያውኑ ልብሱን ለውጦ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። ከዚያም የከበረ የአባ መቃርስ ገዳም ወደ አለበት ወደ አስቄጥስ በረሀ ደርሶ በጾም በጸሎት በመስገድ በመትጋት በአርምሞና በትሩፋት ሁሉ ፍጹም ተጋድሎን ተጋደለ።
❤ ስለ ዝምታውም በጠየቁት ጊዜ "እኔ ስለ ራሴ ብዙ አዝናለሁ" አላቸው እርሱ ግን በውስጥና በአፍአ ትሑትና ቅን የዋህ ነው የእግዚአብሔርንም ሥራ ይሠራል ሁል ጊዜም እጀ ሥራውን አያቋርጥም ከዕለት ምግቡ የሚተርፈውንም ይመጸውታል። የነፍሳቸውንም ድኅነት ለሚሹ ጥቅም ያላቸውን ብዙ ድርሰቶችንና ተግሣጾችን ደረሰ።
❤ ወደ ቤተ ክርስቲያንም በሚገባ ጊዜ ሰው እንዳያየው ምሰሶ ኋላ ይሠወራል። ይህም አባት ድንቆች ተአምራትን ያደርጋል የብዙዎች ሰዎችን ገድል እግዚአብሔር ገልጦለታልና።
❤ መልኩም ያማረ ሕዋሳቱም የጸኑ ፊቱም ብሩህና እጅግ ደስ የሚል ጽሕሙም ከወገቡ መታጠቂያ የሚደርስ ረጅም ነው። ከልቅሶ ብዛትም የተነሣ የቅንድቡ ጠጉር ተነቀለ ቁመቱም ረጅም ነው ግን ያጐነብሳል ወደ መልካም ሽምግልናም ደረሰ ዕድሜውም ሁሉ መቶ ዓመት ሆነ። በሮሜም አርባ ዓመት ኖረ። በአስቄጥስ ገዳም ሠላሳ አምስት ዓመት በምስር ገዳም ሃያ ዓመት በእስክንድርያ ሦስት ዓመት ከዚህም በኋላ ወደ ምስር ገዳም ተመልሶ በዚያ ሁለት ዓመት ተቀምጦ ግንቦት13 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአርሳንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት13 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እቤ አዐቅብ አፋየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ። ወአንበርኩ ዐቃቤ ለአፉየ። ሶበ ይትቃወሙኒ ኀጥአን ቅድሜየ"። መዝ 38፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 6፥1-10፣ 1ኛ ጴጥ 3፥10-15 እና የሐዋ ሥራ 21፥27-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 20፥1-17። የሚቀደሰው የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም ቅዳሴ የቅዳሴ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ አርሳንዮስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ አፉሁ ዘወርቅ ለጳጳሳት ሊቅ እለ ይነባ ከናፍሪሁ ምድራሳተ ጽድቅ"። ትርጉም፦ ከናፍሮቹ የእውነትን (ትርጓሜያትን፣ ስብከቶችን) የሚናገሩ፤ የጳጳሳት አለቃቸው አፉ የወርቅ የተባለ ለኾነ ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው "አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ? ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን?" አለው። የከበረ ዮሐንስም "ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ። ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው" አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና "አፈ ወርቅ ዮሐንስ፣ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ፣ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ" የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።
❤ ንጉሡና ከእርሱ ጋራ ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ጸሎት ይማረን በረከትም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የመላልዔል ልጅግ ቅዱስ ያሬድ፦ ያሬድም መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ኑሮ ኄኖክን ወለደው ኄኖክንም ከወለደው በኋላ ስምንት መቶ ዓመት ኖረ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። መላው ዘመኑም ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ሆነው በዕለተ ዓርብም በሦስት ሰዓት ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቀደሙ አባቶቻችንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚች ቀን በኢየሩሳሌም አገር በጎልጎታ ላይ ፀሓይ በልጦ በሚበራ ብርሃን የከበረ መስቀል መገለጥ ሆነ። ይኸውም ለኢየሩሳሌም አባ ቄርሎስ ኤጲስቆጶስ ሆኖ በተሾመበት በታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ በሚያንሰው ቈስጠንጢኖስም ዘመነ መንግሥት ነው። መገለጡም የሆነው ከቀኑ ከስድስት ሰዓት ነው። የመስቀሉም ብርሃን የፀሐዩን ብርሃን ሸፍኖ በግልጥ እየታየ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ቆየ ሰዎችም ሁሉ ያዩት ዘንድ ከቦታው ሁሉ ይወጡ ነበር።
❤ አባ ቄርሎስም እንዲህ የሚል መልክትን ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሲልክ "ንጉሥ ሆይ ዕወቅ አስተውል በከበረ አባትህ በጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ዘመን እንደ ከዋክብት መስቀል በሰማይ ታየ። ሁለተኛም በዘመንህ በቀራንዮ ላይ የብርሃን መስቀል የፀሐይንም ብርሃኑ ሸፈነው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብርና እስከ ደብረ ዘይት ተዘረጋ" አለው። ሁለተኛም በዚች ደብዳቤ እንዲህ አለው "ንጉሥ ሆይ ከከፋችና ከረከሰች ከአርዮስ ሃይማኖት ተጠበቅ የሚያምኑባትንም አትቀበላቸው በምንም በምን አትሳተፋቸው" አለው።
❤ ከዚህም በኋላም አባ ቄርሎስ ይህ የከበረ መስቀል በተገለጸበት ቀን በዓልን አደረገ እርሱ በሥውርና በግልጥ ለሚመጣብን ጠላት ተዋግተን የምድንበት የጦር መሣሪያችን ነውና በጸና እምነት በምንማፀንበት ጊዜ። እግዚአብሔርም በመስቀሉ ላዳነን በከበረ ደሙም ፈሳሽነት ለአነጸን ምስጋና ይሁን ዛሬም ከሚጣላን ሁሉ ይጠብቀን ይቅርም ይበለን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የንግንቦት12 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ እንተ አብደረ ስደተ። እምይሳተፍ በግፍዕ መፍቀሪተ ንዋይ ንግሥተ። እምነ አፉሁ ዘይወጽአ ሰሚዖ ግዘተ። እንበለ ይዕርግ ላዕለ ወንእንበለ ይረድ ታሕተ። መልአከ ሰማይ ቆመ ፲ተ ዓመተ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 12።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ83፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ5፥1-17።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "በዓመፃ ሰደዱኒ ርድአኒ። ሕቀ ክመ ዘእምደምሰሱኒ ውስተ ምድር ወአንሰ ኢኀደጉ ትእዛዘከ"። መዝ 118፥86-87። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 6፥1-9፣ ዕብ 13፥13-22 እና የሐዋ ሥራ 13፥16-20። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ10፥29-38 ። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን የዓለም ሁሉ መምህር ለሆነ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለዕረፍቱ በዓልና ለመላልዔል ልጅ ለቅዱስ ያሬድ ለዕረፍት በዓልበሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ወደ ነቢዩ ዕንባቆም ከተላከበት፣ ከኢትዮጵያዊው ንጉሥ ከእስክድር ዕረፍት፣ በኢየሩሳሌም አገር በጎልጎታ ላይ ከፀሐይ በልጦ በሚበራ ብርሃን ከከበረ መስቀል መገለጥ ከሆነው፣ ሰማዕታት ከሆኑ ከዲያቆን ሚናስና ከእስጢፋኖስ ከመታሰቢያቸው፣ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዓለሙ ሁሉ መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፦ ይህም አባት ከእስክድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የተወለደውም በ349 ዓ.ም ነው። የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናስያ ነው። እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።
❤ ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተዉለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።
❤ በዚህም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ቅዱስ ጴጥሮስንና ቅዱስ ዮሐንስን አያቸው ቅዱስ ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት "በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታላቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደአንተ ተልከናልና ዕወቅ "እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ"። ሁለተኛም እኔም "በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ"። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል"። ጻድቅ ሲስኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንዲሾም ዐወቀ።
❤ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ። በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ እግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው "ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ " አለው የእግዚአብሔር መልአክም "ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በማዕረጋቸው የሚያዝህም አድርግ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም" አለው።
❤ ከዚህ በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘ በመግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በዐረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቊስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና በ397 ዓ.ም ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኢጲስቆሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፋትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።
❤ ንጉሥ አርቃድዮስ ሚስቱ አውዶክስያንም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የድኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት። ቊጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንዲገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፋ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አሰተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።
❤ የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስ ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ "ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም"። መልእክታቸውንም በአነበበው ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቊስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ።
❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው በ407 ዓ.ም ግንቦት12 ቀን ዐረፈ። ንጉሥ አኖሬዎስ ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት።
❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ከቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደዐረፈና ሥጋውንም ወደ ከቊስጥንጥንያ ከተማ እንደአመጣጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት።
❤ ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውዶክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም። ወደ ቅዱስ ዮሐንስም መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታምራትን ገለጠ።
1 161
ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔርንም ፈጽማ አመሰገነች። ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ።
+ + +
❤ "ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ፡፡ እምውሳጤ ገዳም ዔላመ። ወእምነ ዔላምኒ ደብረ ሊባኖስ ዳግመ። ተክለ ሃይማኖት ባህለ ከመ ወንጌላዊ ቀደመ። እመ ረከቡ ደቂቅከ በዓለም ሕማመ። በኀቤከ፡አባ ይርከቡ ሰላመ"። ትርጉም፦ ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ከገዳመ ዔላም (ደብረ አስቦ) ወደገዳመ ደብረ ሊባኖስ ለፈለሰው ሥጋህ ሰላም እላለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፤ ስብከተ ወንጌላዊ ስብከት ነው እኮን። አባት ሆይ ልጆችህ በዚህ ዓለም ብዙ መከራ ቢያገኛቸውም በአንተ ዘንድ ፍጹም ሰላምና ዕረፍትን እንደሚያገኙ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ። መልክአ ተክለሃይማኖት።
+ + +
❤ የመነኰሳት ሁሉ አለቃ ሐዋርያ ሰማዕት የታላቁ መምህር የክቡር አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሥጋው ፍልሰት፦ የፍልሰቱም ምክንያት በሃምሳ ስድስት(57) ዓመት ከዋሻ (ደብረ አስቦ) ውስጥ ወደ አነፁልህ መቃብር ያፈልሱታል ብሎ እግዚአብሔር የነገው ዘመን በደረሰ ጊዜ ያንጊዜም ተአምር ተደርጎ ዕውራን አዩ አንካሶች ተስተካከሉ።
❤ ይህም በወራሴ መንበሩ በአባ ሕዝቅያስ ዘመን ሆነ ዕለቱም ግንቦት ዐሥራ ሁለት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ተጋዳይ በሆነ ሰው በጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጌታን ደስ በአሰኙት በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 12 ስንክሳር።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው አስገቧት ...
❤ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሳጥናኤል ምሕረት እንደለመነች፦ ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ዓርብ ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ስለሰው ልጆች ስትጸልይ ሣለ። ዓለሙ ሁሉ ከንቱ እንደሆነና የሰውም ልጅ ሕይወት እንደጥላ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ፈጽማ ተመለከተች። ነቢዩ ዳዊት "ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል ዘመኑ ወይም ሕይወቱ እንደጥላ ያልፋል" ሲል ተናግሯልና። ዳግመኛም "ሰው ክብር እንኳ ቢሆን ሊኖር አይችልም እንደሚጠፋ ወይም ማስተዋል እንደሌለው እንስሶች መሰለ... አለ ክቡር ዳዊት። ስለዚህም ሁሉ ነገር አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው መፃተኛዋ ባሪያህንም ኃጢአቷን አታስብባት እያለች ወደፈጣሪዋ መሪር ዕንባን አለቀሰች። ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ወደስዋ መጣ። በታላቅ ግርማ ሆኖ ባየችውም ጊዜ ደነገፀች ከእግሩ ሥርም ወደቀች። ከዚህ በኋላ ነውር በሌለባቸው ንዑዳት ክቡራንና ንጹሐን በሆነ እጆቹ አነሣት። ቀጥሎም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ አትደንግጭ ነገር ግን የልብሽን ሃሳብ ንገሪኝ" አላት። እስዋም "አቤቱ ባሪያህንስ በባለሟልነት ካሠለጠንካት አባታችን አዳምን በአርአያህና በአምሣልህ ስለምን ፈጠርከርው። በእንጨት መስቀልስ ላይ ለምን ተሰቀልክ ስለአዳምና ስለልጆቹ አይደለምን?" አለችው። "አዋን ስለነሱ ስል ተሰቅያለሁ" አላት። "እግዲያውስ መሰቀልህ ወይም የተሰቀልከው ስለነሱ ከሆነ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱን ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው" አለችው። "አንተ ቸር ይቅር ባይ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ ነህና ከአንተ ሌላ አምላክ የሌለ እውነተኛ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃልና የሚሣንህ ነገር ከቶ የለምና ዓለም በጠቅላላዋ በእፍኝህ አትሞላም" በማለት እያለቀሰች ለመነችው። በዚያ ጊዜ ጌታ መልሶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ አንቺ ራስሽ ፍረጅ አዳም ከነልጆቹ ከሠራው ኃጢአት እና እኔ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን በቀያፋና በሐና አደባባይ በዕለተ ዓርብ ከተቀበልኩት ሕማማተ መስቀል ቢመዘን የትኛው ይመዝን ይመስልሻል?" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ደነገጠችና ከመሬት ላይ ወደቀች። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት በሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣትና "እንግዲህ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩ ለማን ወይም በማን ምክንያት ይመስልሻል" አላት።...
❤ ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ የልብሽን ሃሳብ ወይም ፍላጐትሽን ንገሪኝ" አላት። በዚህን ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆች ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ። የኃጥእን መመለሱን እንጂ ጥፋቱን አትወድምና" አለችው። "የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እርሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት እንጂ። የነሱ ሥጋ ሥጋየ እንደሆመኑ መጠን የኔም ሥጋ ሥጋህ ነውና" አለችው። ይህንም ባለችው ጊዜ ጌታ ፍግግ ብሎ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ሌሎች ካንቺ በፊት የነበሩ ካንቺም በኋላ የሚነሱ የማያስቡትን እጅግ የሚያስደንቅ ልመና አቀረብሽ" አላት። ይህንም ካለ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ስትል ልመና አቅርባለችና እሺ ካላት ታወጣው በንድ ወደሲዖል ይዘሃት ሂድ" ብሎ አዘዘው። በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እሺ ብሎ ሰግዶ እጅ ነሥቶ ወደሲዖል ይዞአት ሄደ። አብረው በሚጓዙበትም ጊዜ "እንግዲህ ዲያብሎስ ከታረቀ ወይም ከተማረ የሰው ልጆች ሁሉ ያርፋሉ" እያለች ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ታሳስበው ነበር። ይህን አምላክነትን ሲሻ ከክብሩ የተዋረደ ዲያብሎስ ምሕረት ለማግኘት ይሻ መስሏት ነበርና።
❤ ከሲዖል አፋፍ በደረሱም ጊዜ የተመለከተችው ሥቃይ ተነግሮ የማያልቅ ነው ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደውሻ ይናከሱ ነበር። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ምሕረት የሚፈልግ ከሆነ እስኪ በይ ዲያብሎስ ብለሽ ጥሪው" አላት። በዚህ ጊዜ በመላእክት ቋንቋ ሦስት ጊዜ "ሣጥናኤል ሣጥናኤል ሣጥናኤል" በማለት ጠራችው። ዲያብሎስም "ከዚህ በብዙ ሠራዊት ላይ ነግሼ ከምኖርበት አገር ማን ነው እሱ የሚጠራኝ" እያለ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ። ከዚህም በኋላ "ለብዙ ዘመን ስፈልግሽ ወይም ሳድንሽ ቆይቼ ነበር ዛሬ ግን ከምኖርበት ቤቴ ድረስ መጣሽን" አላት። እርሷም "ጌታ ይቅርታ አድርጓልሃልና ከዚህ ከሥቃይና ከመከራ ቦታ ከወገኖችህ ጋራ ና ፈጥነህ ውጣ" አለችው። ይህንም በለችው ጊዜ ልቡ እንደ እሳት ነደደ አፈፍ ብሎ ተረማምዶ በግራ እጁዋን ይዞ ከሲዖል ረግረግ ውስጥ ወረወራት። በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ ከኋላ ከኋላዋ ይከተላት ነበርና ይህን ምሕረት የሌለው ዕቡይ ዲያብሎስ በያዘው ሰይፍ ቢቀጣው የሲዖል ደጃፍ ተከፈተች። በዚህ ሰዓት ታላቅ ጨኸትና ውካታ ወይም መደበላለቅ ሆነ በሲዖል ያሉ የሰዎች ነፍሳት እንደንብ ከበቧት ወይም ሠፈሩባት። በዚያን ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና በስዋም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲዖል የወጡት ነፍሳት ቁጥር ዓሥር ሺህ ያህል ነበር። እነዚህ ከመከራ ያመለጡ ከሥቃይ የወጡ ነፍሳትን ባየች ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የእናቱን ጡት እየጠባ እንደሚዘል እምቦሳ ጥጃ በመካከላቸው ትዘል ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ "አቤቱ ፍርድህ ከቶ እንደዚህ ነውን?" እያለች አደነቀች። ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዲያብሎስን ድል አድርገሽ ጥቂት ምርኮን አገኘሽን" አላት። እስዋም "አዋ ጌታዬ በኃይልህና በቸርነትህ አገኘሁ" አለችው። ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "እሊህን ነፍሳት ዓለም ሳይፈጠር ወደ አዘጋጀሁላት ወደ ክርስቶስ ሠምራ መኖሪያ ቦታ ውሰዳቸው" አለው። በዚህ ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ የእኔ መኖሪያየ ወዴት ነው?" አለችው። ጌታም "መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋራ ነው እነሆ በትረ ማርያም ብየ ሰየምኩሽ መቀመጫሽን ወይም ደረጃሽን ከእርስዋ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ የባለሟልነት ግርማ አጐናጸፍኩሽ አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ፈጽማ ደስ ተሰኘች ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ብትመለከት ለዓይን የሚያንፀባርቁ ዓሥር አክሊላት አየች። በየአንዳንዳቸው አክሉል ላይ ዐራት ከዋክብት አሉ ባቸው የእሊህ ከዋክብት ቊጥራቸው ሲደመር አርባ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ከስዋ ጋራ የነበረውን መልአክ "እሊህ በላያቸው ብርሃናውያን ከዋክብት ያሉባቸው አክሊላት ለማን የተዘጋጁ ናቸው ሰውነቴ እጅግ አድርጋ ወዳቸዋለችና" አለችው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ላንቺ ቢሆን ደስ አይልሽምን?" አላት። እርስዋም "አዎን ጌታየ ለኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያስ ላንቺ የተዘጋጁ ናቸው" አላት። "በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ለታላቋ ለሰላም እናት ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ብላ ለጠየከችበት፤ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ከሲዖል ዐሥር ሺህ ነፍሳት ለአወጡበት በዓልና ለልደቷ በዓል፣ ለታላቁ አባት ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለሥጋቸው ፍልሰት ካዐረፉ ከ57 (56) ዓመት በኋላ ከደብረ አስቦ ወደ ገዳማቸው ደብረ ሊባኖስ ለፈለሰበትና በአባታችን ተክለ ሃይማኖት መንበር ለተሾሙ መምህራን ዐሥራ ሰባተኛ ቁጥር ለሆነው ለደብረ ሊባኖስ መምህር ለአባ አብርሃም ለዕረፍት፡ በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ክርስቶስ ሠምራ የአምላክ አገልጋይ
ይበራል ስምሽ ዛሬም በምድር ላይ
መመረጥ በእግዚአብሔር እንደ በትረ ማርያም
ለሰው ልጅ ጸልዪ እስከ ዘለዓለም
አዝ............................................
በትረ ማርያም ብሎ ክርስቶስ ሠምራ
ስሟን ለወጠላት ክርስቶስ ሠምራ
ሚካኤል ቀኝ እጅ ረዳት ቢያደርግላት
ዐሥር ሺህ ነፍሳት ክርስቶስ ሠምራ
ማረከች ከሲኦል ክርስቶስ ሠምራ
ባዶ ሆነ ቤቱ አፈረ ሳጥናኤል
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ መዝሙር።
ስንኙ ይቀጥላል
+ + +
❤ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፦ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ግንቦት 12 ቀን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።
❤ በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማዊ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።
❤ ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት። ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።
❤ ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።
❤ ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም "ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት
1 161
