ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
ስርአተ ዋዜማ ዘደብረ ታቦር
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ዋዜማ
ሃሌ ሉያ ወአመ ሰዱስ ነሥኦም ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለያዕቆብ ወለዮሐንስ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ወተወለጠ አርአያሁ በቅድሜሆሙ ፤ወአልባሲሁኒ ኮነ ፀአዳ ከመ በረድ ፤ወመጹ ኀቤሁ ሙሴ ወኤልያስ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ ለኢየሱስ፤እንዘ ይትናገሩ መጽአ ደመና ብሩህ ወጸለሎሙ:ማ-መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።
@EOTCWW
@EOTCWW
ምልጣን፦
እንዘ ይትናገሩ መጽአ ደመና ብሩህ ወጸለሎሙ:መጽአ ቃል እም ደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።
@EOTCWW
@EOTCWW
አመላለስ፦
መጽአ ቃል እም ደመና ዘይብል/2/
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ/4/
@EOTCWW
@EOTCWW
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር ምልዓ፦
ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት በዓለ ደብረ ታቦር ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት
@EOTCWW
@EOTCWW
እግዚአብሔር ነግሠ፦
እስመ ውእቱ ቀደመ አዕምሮ
ወዜነዎሙ ለአርዳኢሁ በደብረ ታቦር በእንተ መንግስቱ ዳግመ ምጽአቱ በዓቢይ ስብሐት ።
@EOTCWW
@EOTCWW
ይትባረክ፦
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሁ ወይሴብሑ ለስምከ ታቦር ወአርሞንኤም ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሁ ዮም ታቦር ወአርሞንኤም ።
@EOTWW
@EOTCWw
ሰላም፦
ሃሌ ሉያ ሰላም ለኪ ኦ ማርያም ደብረ መቅደሱ ለእግዚአብሔር፤ ሰላም ለኪ እንተ መልዕልተ ኩሎሙ ቅዱሳን ፤ ሰላም ለኪ ኦ ዓባይ ሀገር ፤ ሀገረ ናዝሬት እመ አኅጉር ሀገሩ ለክርስቶስ ፤ ሰላም ለከ ኦ ደብረ ታቦር ዘከለሎ ብርሃን ይሴኒ ላህዩ አምኵሉ አድባር ።
https://t.me/Eotcw
ምልጣን
ደብረ መቅደሱ ለእግዚአብሔር ማርያም ሰላም ናዝሬት ሰላም ዘአኅጉር እም ደብረ ታቦር ሰላም ሰላም ለላህይከ አዳም
Eotcw
Eotcw
አመላለስ፦
ደብረ ታቦር ሰላም ሰላም ደብረ ታቦር/2/
ሰላም ለላህይከ አዳም/4/
https://t.me/Eotcw
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
1 161
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ለንጉሥ። ጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ። ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ"። መዝ 71፥1-2። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 9፥17-ፍ.ም፣ ይሁዳ 1፥8-14ና የሐ ሥራ 24፥1-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ወደ ንግሥት ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ለተላከበት ለእርሱም ጠላቶቹን አሸንፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ለሰጠበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰበው፦ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ከገባበትና በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ከነገሠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለቈስጠንጢኖስ ለነገሥት ርእስ፤ ዘከለሎ እምሰማይ ሞገስ፤ እምኵሎሙ ነገሥት ይትሌዓል ቀርኑ፤ ዘከደነ ስፍሐ ዓለም ሃይማኖተ ሥኑ፤ ዘአስተጋብአ ጳጳሳተ ጽድቅ ሃይማኖተ እለ ሠርዑ ወወሰኑ፤ ማዕከለ ሁከቶሙ ለዕልዋን ዘአንሐለ ጥቅመ፤ ኵሎ ዓለም በሃይማኖት ዘከሠተ ጸጋ ብርሃነ ዘኮነ ለኵሉ ዘሥጋ ወቦቱ ተሐደሰ ለመርዓት ሕጋ"። ትርጉም፦ የሙሽሪት (ቤተ ክርስቲያኒቱ) ሕጓ ዐዲስ የኾነበት፤ ለሥጋዊ ለደማዊ ብርሃንን የኾነ የወልድ መስቀሉን በጸጋ የገለጠ፤ ዓለሙን ኸሉ በሃይማኖት የሸለመ (የጠለፈ)፤ የክፉዎችን የሁከት ማዕበል እንደ ግንብ ያፈረሰ፤ ሃይማኖትን የወሰኑና የደነገጉ የእውነት ጳጳሳትን የሰበሰበ፤ የሃይማኖቱ ደም ግባት የዓለምን ስፋት የሸፈነ፤ ከኹሉም ነገሥታት ይልቅ ሥልጣኑ ከፍ ከፍ ያለ፤ ከሰማይ ሞገስ የጋረደው ለኾነ ለነገሥታት አለቃ ለቈስጠንጢኖስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ እሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስካሸነፍቸው መንግሥቱን እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።
❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እንድናደርግ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮች ሁሉ ላይ ነገሠ። ዜናውንም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ጽፈናል። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 12 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ መልአከ ኪዳኑ ወምክሩ። ለእግዚአብሔር ልዑል ዘግሩም ግብሩ። በረድኤትከ ረዋጺ ዘአሠረ ነፋስ አሠሩ። ሶበ ላዕሌየ እኩየ መከሩ። ጉባኤ ፀርየ ሚካኤል ዝሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 12።
+ + +
❤ የዕለቱ ማኅሌቱ ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሉቃ. 6:20-24 "ወውእቱሰ አንሥኣ አዕይንቲሁ" - "እርሱም፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ዐይኑን፡አነሣ፡እንዲህም፡አላቸው፦እናንተ፡ድሃዎች፡ብፁዓን፡
ናችሁ፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡የእናንተ፡ነውና። እናንተ፡አሁን፡የምትራቡ፡ብፁዓን፡ናችሁ፥ትጠግባላችሁና።እናንተ፡አሁን፡የምታለቅሱ፡ብፁዓን፡ናችሁ፥ትሥቃላችሁና። ሰዎች፡ስለሰው፡ልጅ፡ሲጠሏችሁ፡ሲለይዋችሁም፡ሲነቅፏችሁም፡ስማችሁንም፡እንደ፡ክፉ፡ሲያወጡ፥ብፁዓን፡ናችሁ። እንሆ፥ዋጋችሁ፡በሰማይ፡ታላቅ፡ነውና፥በዚያን፡ቀን፡ደስ፡ይበላችሁ፡ዝለሉም፤አባቶቻቸው፡ነቢያትን፡እንዲህ፡ያደርጉባቸው፡ነበርና። ነገር፡ግን፥እናንተ፡ባለጠጋዎች፡ወዮላችሁ፥መጽናናታችሁን፡ተቀብላችኋልና።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
ነሐሴ ፲፩
#ምንባባት
፩ ቆሮ ም ፭ ቊ ፲፩-ፍጻ
፩ዮሐ ም፪ ቊ፲፬-፳
ግብ ሐዋ ም ፲፪ቊ ፲፰-ፍጻ
#ምስባክ
መዝ ፵፬ቊ፲፮-፲፯
ህየንተ አበውኪ ትውልዱ ለኪ ደቂቅ።
ወትሰይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር።
ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ።
#ትርጉም
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ ፣
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፣
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ ፣
#ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ም ፮ቊ፳-፳፬
#ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን ለአውሲም አገር ኤጲስቆጶስ ለአባ ሞይስስ ለዕረፍትና ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ለሆነ ለቅዱስ አብጥልማዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላሞ አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከአረፉ በአንጾኪያ ከተማ የሠራዊት አለቃ ከነበረው ከቅዱስ ፋሲለደስ በሰማዕትነት ከዐረፉ ማኅበሮች ከሦስት መቶ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የአውሲም አገር ኤጲስቆጶስ አባ ሞይስስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም ነበረ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ ተምሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባ። በአንድ ጻድቅ ሰው ዘንድም መነኰሰ በዚያም እያገለገለ በጠባብዋ መንገድም ተጠምዶ ያለመብልና መጠጥ ያለእንቅልፍም እየተጋደለ ዐሥራ ስምንት ዓመት ኖረ።
❤ ከብዙ ፍቅርና ትሕትና ጋር ዘወትር በጾምና በጸሎት ይተጋ ነበር። ትሩፋቱም በበዛ ጊዜ ከአባ ገሞስ በኋላ በአውሲም ከተማ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። ይህም አባ ሞይስስ በተሾመ ጊዜ ትሩፋት መሥራትን አብዝቶ ጨመረ ስለ እነርሱም በጸሎት እየተጋ መንጋዎቹን ነጣቂዎች ከሆኑ ከዲያብሎስ ተኲላዎች ጠበቀ።
❤ በሕይወቱም ዘመን ሁሉ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ የሚሰበስብ አልነበረም። አባ ሚካኤልም በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜና ደሙ ሳይፈስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ ይህ አባ ሞይስስ በእሥር ቤት ከእርሱ ጋር ነበር ብዙ ስለገረፉት እግሮቹንም ለረጅም ጊዜ በእግር ብረት አሥረው ስለ አሠቃዩት ብዙ መከራ ደረሰበት።
❤ በዚህ አባት ሞይስስ እጅም እግዚአብሔር ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ የሚያውቁትም በተአምራቶቹ ደግነቱንና ትሩፋቱን ተረዱ። ዳግመኛም ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ከመሆኑም በፊት ብዙ ነገርን ተናገረ እንደተናገረውም ይሆን ነበር። የምስር ኤጲስቆጶስ ስለሆነው ስለ አባ ቴዎድሮስ ከሔደበት እንደማይመለስ ትንቢት ተናግሮበት እንዲሁ ተፈጸመበት።
❤ ዳግመኛም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ነበር። ብዙዎች ሕሙማንንም ፈወሳቸው። ገድሉንም በመልካም ሽምግልና ፈጸመ። እግዘአብሔርንም አገልግሎ ጥቂት ታመመ የሚያርፍበትንም ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና ባረካቸው በቀናች ሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነሐሴ 11 ቀን ዐረፈ። አለቀሱ ለትም ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ በዝማሬና በማኀሌት በታላቅ ክብር ገንዘው ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም የሚሆን ፈውስ ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋነ ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት በአባ ሞይስስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ አብጥልማዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ነው። ቅዱሱንም ክርስቲያን እንደሆነ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። መኰንኑም በአስቀረበው ጊዜ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃይቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብጥልማዎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ዕብል ለሞይስስ ፍጹም። ኤጲስቆጶስ ዘብሔረ አውሲም። ለጸሎት ዘተግሀ ወተጋደለ በጾም። አመ ርሥእናሁ በንስቲት ሕማም። እምፃማ ዓለም አዕረፈ ዮም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የነሐሴ 11።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20ና የሐ ሥራ 12፥18-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
የዕለቱ ምስባክ፦ "ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ። ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ"። መዝ 73፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
