fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
✝️የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያው የአዋጅ ጾም፤ ከሐሙስ ኅዳር 15፣ 2015 ዓ.ም እስከ ቅዳሜ ታህሳስ 29፣ 2015 ዓ.ም✝️ሰናይ ፆም ያድርግልን✝ ✝️ጾመ ነቢያት፣ጾመ ገና፣ጾመ ልደት✝ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ገና፣ ጾመ ልደት፣ ጾመ ስብከት ይባላል፡፡ ጾመ ነቢያት መባሉ ነቢያት ስለጾሙት ጾመ ድህነት መባሉም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፍቶ ድኅነት የተገኘበት ስለሆነ ነው፡፡ አዳም በእፀ በለስ ምክንያት ልጅነቱን ካጣ ከገነት ከወጣ በኋላ “ወአልቦቱ ካልዕ ኅሊና ዘእንበ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ” እንዲል “እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ታህል ቦታ በኃጢአቴ ምክንያት አጣሁ” እያለ ሲያዝን ጌታ ኀዘኑን አይቶ ጸሎቱን ሰምቶ በዕለተ ኀሙስ “ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ”፤ “በአምስት ቀን ተኩል ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ሰው ሰውኛውን ኖሬ በመስቀል ተሰቅዬ በሞቴ አድንሀለሁ” ብሎ ተስፋውን ሰጥቶታል፡፡ ከእርሱ በኋላ የተነሱ ነቢያት በግዝረታቸው በመስዋዕታቸው መዳን የማይቻላቸው ቢሆን ለአዳም በሰጠው ተስፋ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ በሕማሙ በሞቱ ያድነን ብለው በየዘመናቸው ግብር ገብተው ቀኖና ይዘው “አንስእ ኃይልከ ፈኑ እዴከ” ብለዋል፡፡ ጌታም የተናገረውን የማያስቀር ነውና አምስት ቀን ተኩል (አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን) ሲፈፀም ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ ሰው ሰውኛውን ኖሮ በ33 አመቱ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ስጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ሁሉ አድኗል፡፡ ጾመ ነቢያት ነቢያት ጌታችን ይወርዳል ይወለዳል እያሉ በትንቢት እየተናገሩ ትንቢቱም ይፈጸም ዘንድ አጥብቀው በመለመን አጥብቀው የጾሙት ጾም ነው። በመሆኑም ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለሰው መዳን የጾሙትን የጸለዩትን በማዘከር ከበዓለ ልደት አስቀድሞ ያሉትን ስድስት ሳምንታት (44 ቀናት) እንጾማለን፡፡ እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አዋልድ የታሪክ መጻሕፍት አስተምህሮ 44 ቀናት ማለት 40ው ቀን የነቢያቱ፣ 3ቱ የአብርሃም ሶርያዊ፣ 1ዱ ደግሞ ጾመ ገሃድ) መሆኑን ልብ ይሏል። ✝️መልእክት✝️ በመሆኑም በዚህ ዓመት (2015 ዓ.ም) ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ በመሆኑ የጾሙ መግቢያ የፊታችን ሐሙስ ኅዳር 15፣ 2015 ዓ.ም ሲሆን የጾሙ መውጫ ደግሞ ቅዳሜ ታህሳስ 29፣ 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለዚህም የመጨረሻው የቅበላ ቀን ማግሰኞ ኅዳር 13፣ 2015 ዓ.ም ይሆናል ማለት ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ረቡዕ ኅዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ራሱን የቻለ የጾም ቀን ስለሆነና የቅበላ ቀን መሆን ስለማይችል ነው። በዓለ ልደት፣ በዓለ ገና ደግሞ ቅዳሜ ታህሳስ 29፣ 2015 ዓ.ም ይሆናል። ----------------------------------------- ጾምን እንጹም ወንድሞቻችንን እንውደድ እርስ በእርሳችን እንዋደድ፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ ሰማእታትን፣ ጻድቃንን፣ መነኮሳትን፣ አበው ሊቃውንትን በጾም በጸሎትና በተጋድሎ ያጸናህ አምላክ እኛን ልጆችህን ከስርዓትህ ፈቀቅ አንዳንል እርዳን አሜን፡፡ ጾሙንም የኃጢአት መደምሰሻ የዲያቢሎስ ድል መንሻ የመንግስተ ሰማያተ መውረሻ አድርግልን፡፡ ለጾም የበረታ ሰውነት፣ ለጸሎት የሚተጋ ልብ፣ በጎ የሚያደርግ ህሊና፣ መልካም የሚያይ አይን፣ በደልን የሚረሳ አዕምሮ፣ ይቅርታ የሚጠይቅ አንደበት፣ ለተቸገሩ የሚመጸውት እጅ እንዲኖረን እርዳን፡፡ አሜን፡፡ ----------------------------------------- ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር።

photo content

photo content

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግዕዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሐና እምአንስት ተዐቢ ወትትሌአል እስመ ወለደታ ለድንግል ዘወለደት ዘሀሎ ቅድመ መዋእል ዮሐንስ ወንጌላዊ በከመ ዜነወ በወንጌል"። ትርጉም፦ ሃሌ ሉያ ሐና ከሴቶች ሁሉ ትበልጣለች ክፍከፍም ትላለች፣ ቃልን የወለደችውን ድንግልን ወልዳታለችና፣ በዮሐንስ ወንጌላዊው ዘመን ወንጌል እንደነገረን። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤"ሰላም ለሐና እንተ ወለደታ ለማርያም ዘኮነት ተንከተመ ጽድቅ ለኵሉ ዓለም፤ ድንግል ወእም፤ ወላዲቱ ለፀሓይ ዳግሚት ሰማይ"። ትርጉም፦ ፀሓይን የወለደችው ኹለተኛዪቱ ሰማይ፤ ድንግልም እናትም፤ ለዓለሙ ኹሉ የእውነት ድልድይ (መሸጋገርያ) የኾነችዪቱን ማርያምን ለወለደቻት ለቅድስት ሐና ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን አምላክ ለወለደች ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም እናት ለሆነች ለተመሰገነነች ለቅድስት ሐና ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሁለተኛው ከአርኬላዖስ ሰማዕት፣ ከአበምኔት ኤልሳዕ፣ ከመነኰስ ጳኵሚስና ከሰማዕቱ ሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ " ኢትዘኪሮ አበሳነ ዚአነ ፍጹመ ኢኀደገነ ፍጹመ ንማስን ኄር እግዚአብሔር አዘዞሙ ሙሴ ለሕዝብ ያክብሩ ሰንበተ ጽድቅ"። ትርጉም፦ ቸር እግዚአብሔር በደላችንን ሳያስብ ፈጽሞ እንጠፋ ዘንድ አልተወንም፤ በእውነት ሕዝብህ ሰንበትን ያክብሩ ብሎ ሙሴን አዘዘው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ቅድስት ሐና፦ ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት። ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥ ወለደቻት። ❤ ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቆም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው። ❤ የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር። ❤ ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በቅድስት ሐና በጸሎቷ የሚኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 11 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰለም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ። ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ። ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ። እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ። እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 11። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳት። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኲሉ ተዒይኒሁ ለያዕቆብ"። መዝ 86፥1-2 ወይም መዝ 44፥9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 3፥23-ፍ.ም ወይም ሉቃ 18፥1-9። ። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘካትካት።ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ። እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ"። መዝ 78፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥1-18 እና የሐዋ ሥራ 1፥22-1-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥5-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ወይም የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት ሐና የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

photo content

Share 'ህዳር 12(2).pdf'

❄️❄️መዝሙር ዘአስተምህሮ ኢተዘኪሮ-ሰላም @EOTCW

🔹🔹አመላለስ ዘአቡን ነዋ ሚካኤል @EOTCW

❣❣፯ኛ ወረብ ሚካኤል መልአክ @EOTCW

❣❣፮ኛ ወረብ ውእቱ ሚካኤል @EOTCW

❣❣፭ኛ ወረብ ተወከፍ ጸሎተነ @EOTCW

❣❣፬ኛ ወረብ በገዳም @EOTCW

❣❣፫ኛ ወረብ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ @EOTCW

❣❣፪ኛ ወረብ ረዳኤ ምንዱባን @EOTCW

አመ፲፪ ለኅ ቅዱስ ሚካኤል ❣❣፩ኛ ወረብ አንተኑ ሚካኤል @EOTCW