ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል ወአእላፍ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCW
@EOTCW
✨መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCW
🌱ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈራ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ፦
ምስጢረ መንግስት ሰናይ ለኃቢዕ ወግብረ ጽጌኪ በክብር ለከሢት፤ሩፋኤል መልአክ በከመ ይቤሎ ለጦቢት፤ተአምርኪ ማርያም ለዘየኀብዕ ስሑት፤ትኅብዖ ምድር ሕያዎ እስመ አኀዞ ቅንአት፤በከመ ኃብአቶ ለዳታን ትካት
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ምስጢረ መንግስት ሰናይ ለኃቢዕ ወግብረ ጽጌኪ በክብር ለከሢት/፪/
በከመ ይቤሎ ሩፋኤል መልአክ ለጦቢት ይቤሎ መልአክ/፪/
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል፤ ምስለ ዑራኤል ወሩፋኤል ሠናያነ ራእይ እለ ዜነዉ ምስጢራተ ሰማይ
@EOTCW
@EOTCW
🌱🔹ዓዲ ዚቅ(ሌላ)፦
በምድረ ጽዮን ኢይኩን ሀከክ፤ወበገራሕታ ኢይብቍል ሦክ፤ጸሊ ኀበ አምላከ ሩፋኤል መልአክ፤ፍሬ ምድርነ ከመ ይትባረክ
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ዘወለደት ጽጌ ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ፅጌ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናየትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
@EOTCW
🌱ዚቅ
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት ንባብኪ አዳም ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ።
@EOTCW
@EOTCW
✨ማኅሌተ ፅጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱም ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCW
🌱ዚቅ
ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት
@EOTCW
@EOTCW
✨ሰቆቋወ ድንግል
ጐየ ዮሴፍ ብሔረ ግብፅ ተንሢኦ እምንዋሙ፤ መልአከ እግዚአብሔር ሌሊተ በከመ ነገሮ በሕልሙ፤ነሢኦ ሕፃነ ዘምስለ ማርያም እሙ፤ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ፤እምእርአይ ለወልድየ ዘይትከዓው ደሙ
@EOTCW
❣❣ወረብ፦
ዮሴፍ ጐየ ዘምስለ እሙ ማርያም ነሢኦ ሕፃነ/፪/
መልአከ እግዚአብሔር በከመ ነገሮ በሕልሙ ሌሊተ/፪/
@EOTCW
@EOTCW
🌱ዚቅ፦
ወነቂሖ ዮሴፍ እምንዋሙ ገብረ በከመ አዘዞ መልአከ እግዚአብሔር ፤ነሥአ ሕፃነ ወእሞ ወሖረ ብሔረ ግብጽ
@EOTCWW
@EOTCWW
🌿መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወሠነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ ወሰማይ ወምድረ ዘእንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።
@EOTCW
@EOTCW
አመላለስ
@EOTCW
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/2/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/4/
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
1 161
11/2/2015 ዓ.ም (፲፩/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ የቅዳሴ የሚባል ምስባክ
መዝ ፹፫፥፮
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን።
#ትርጕም፦
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤
ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለጲላግያ ለርእሳ ኬንያ ዘኮነት ስምዐ ለወልደ ማርያም"። ትርጉም፦ ለራሷ በመጠበብ ለማርያም ልጅ ምስክርን የነበረች ለኾመች ለጲላግያ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለጲላግያ እንተ አፍቀረት ትዴግኖ። ለጳውሎስ አብ ሶበ አጽምዓት ምዕዳኖ። ወበእንተዝ ሐለየት ወአጥብዓት ለተኰንኖ። ላህበ ብርት ውዑይ እስከ ለላህያ አርሰኖ። እንዘ ልቡናሃ ይሬኢ ለክርስቶስ ስኖ"። ትርጉም፦ የአባት ጳውሎስን ምክሩን ባዳመጠች ጊዜ ትከተለው ዘንድ የወደደች ለኾነች ለጲላግያ ሰላምታ ይገባል፤ ስለዚኽ ነገርም መከራን ለመቀበል ቈርጣ ዐሰበች፤ ልቡናዋ የክርስቶስ ደም ግባትን እያየ፤ የሚቃጥል የጋለ ብረት እንፋሎት ደም ግባቷና እስኪያቃጥል ድረስ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 11።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን ለገድለኛዋ ለቅድስት ጲላግያ ለዕረፍት በዓልናከአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ አባት ከያዕቆብ ዕረፍትና ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት ለአባ ያዕቆብ ዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት አርማሚ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ገድለኛዋ ቅድስት ጲላግያ፦ ይቺም ከአንጾኪያ አገር የሆነች ናት ወላጆቿም ከሀድያን ናቸው እርሷም አስቀድማ ከረከሰ ሃይማኖቷ ጋር በረከሰ ሥራ ጸንታ መኖርን ገንዘብ አደረገች። እርሷም በመሸታ በጨዋታ ቤት በመዋል ስትሣለቅና ስታመነዝር ስትዘፍንም ትኖራለች።
❤ በአንዲት ቀንም የገሀነም እሳትና የዘላለም ሥቃይ እንደሚጠብቃቸው እያሳሰበ ዝንጉዎችንና አመንዝራዎችን ሲገሥጻቸው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስን ሰማችው ምክሩም በልቧ አደረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደርሱ ሒዳ የሠራችውን ሁሉ ተናዘዘች እርሱም አጽናንቶ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራትና አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት። በቀደመው ሥራዋም እየተጸጸተች በጾም በጸሎት በስግደት ሰውነቷን ማድከም ጀመረች።
❤ ከዚህም በኋላ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዳ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ ሰግዳ ሁሉንም ቦታዎች ተሳለመች ወደ ኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳትም ተመለሰች። እርሱም ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ከደናግል ገዳማት ወደ አንዱ ላካት የምንኵስናንም ልብስ ለብሳ በጽኑዕ ገድልም ተጠምዳ ሠላሳ ዓመት ያህል ኖረች እግዚአብሔርንም አገልግላ በሰላም ጥቅምት 11 ቀን ዐረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ጲላግያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት ስንክሳር።
+ + +
❤ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ያዕቆብ፦ ይህም ቅዱስ ብዙ መከራ ደርሶበታል ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አርዮሳውያን አሳደውት በደሴት ብዙ ወራት ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ የአንጾኪያ ምእመናን ሰዎች ተሰብስበው መከሩ። መልእክትም ልከው ወደ እነርሱ መልሰውት ጥቂት ቀኖች ኖረ። ከዚህም በኋላ ሁለተኛ አርዮሳውያን ተነሡበት አሳደዱትም በስደትም ውስጥ ሰባት ዓመት ኑሮ በዚያው ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1 ጢሞ 4፥9-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥11-17። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ የዓባይ ውሃ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ በጸሎታቸው አቁመውት ለነበሩ ለታላቁ አባት ለአቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ ለመታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ፦ የትውልድ ሀገራቸው አክሱም ነው፡፡ የአቡነ አረጋዊ 3ኛ የቆብ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ውቅሮ የሚገኘው የጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ቤተ መቅደስ አጣኝ ነበሩ፡፡ እኚህ ጻድቅ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ገድል አላቸው፡፡ በቀን 548 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን እየጸለዩ 666 ጊዜ ይሰግዱ ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዓባይ የሀገራችንን አፈርና ዛፉን ሁሉ ጠራርጎ ሲወስድ ቢመለከት ድምጹን ከፍ አድርጎ "ኦ አባይ አይቴ ተሐውር ወለመኑ ተሐዲጋ ለኢትዮጵያ" ብሎ ሲዘምር ዓባይ ቀጥ ብሎ ቆሟል፡፡ መልአኩም ወዲያው መጥቶ "ለምን ትደክማለህ? ለምንስ ተፈጥሮን ትከለክላለህ? ሕጉን አታፍርስ" ሲለው ቅዱስ ያሬድ ደንጎጦ "አጥፍቻለሁ ዓባይ ሆይ ሂድ የተፈጥሮ ግዴታህን ፈጽም" ብሎ አሰናብቶታል፡፡ የኢትዮጵያ ብርሃኗ ቅዱስ ያሬድ በዜማው ዓባይን ቀጥ አድርጎ እንዳቆመው ሁሉ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮም በጸሎታቸው ዓባይን ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ አድርገውት ነበር፡፡
❤ ታቦተ አብርሃ ወአጽብሓን ይዘው ከኢትዮጵያ ጠረፍ ዳር ኑብያ ሄደው ድንጋይ ከዓባይ ዳር ደርድረው ታቦቱን አስቀምጠው ሥዕለ ማርያምን አድርገው መሥዋዕት ሰውተው "ዓባይ ከኢትዮጵያ እንዳትወጣ ገዝቼሃለሁ" ሲሉት ዓባይም ተመልሶ ቆሟል፡፡ ዓባይ ምድረ ኑብያን ሲያጥለቀልቃት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ "ለምን የእግዚአብሔርን ስነ ፍጥረት ታስጨንቃለህ?" ብሎ ተቆጣቸው፡፡ ጻድቁም "ውኃው ይሂድ ግን ዛፉን አፈሩን ይዞ ከኢትዮጵያ አይውጣ" ብለው መልአኩን ጠየቁት፡፡
❤ ቅዱስ ገብርኤልም "ውኃ ሲሞላ ዛፉን ቅጠሉን ይዞ መጓዙን እንዴት ትረሳዋለህ? የጸሎት ጊዜህ ደርሷልና ወደ በዓትህ ተመለስ" ብሎ በቁጣ የእሳት ሰይፉን ሲያዛቸው ግዝታቸውን አንሥተው ታቦታቸውን ይዘው ወደ በዓታቸው ውቅሮ ተመልሰዋል፡፡ አባቶቻችን እንዲህ ናቸው እንኳን ሃይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ስብዕና ማንነታችንን ይቅርና የሀገራችንን አፈር እንኳን ለባዕድ አሳልፈው የማይሰጡ ቅዱሳን ጻድቃን ነበሩ፡፡ ከአባታች ከአቡነ ኤልያስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን ከከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ሠራዊት ውስጥ ለቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ ለሆነ ለቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓል፣ ለእስክድርያ አገር ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለሆነ ለአቡነ አውማንዮስ ለዕረፍትና ለመስተጋድል ከተጋድሎው ብዛት የተነሣ ራሱን በሚላጭ ጊዜ በውኃ ሳያርስ ይላጭ ለነበረ ከቀሲስ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ፦ ይህም ቅዱስ ከከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ሠራዊት ውስጥ የቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ የሆነ ነው። ንጉሥ መክስምያኖስም ወደ ሶርያ አገር ወደ አንጥያኮስ በላካቸው ጊዜ ቅዱስ ባኮስን ከውኃ በማስጠም በዚህ ወር በአራተኛ ቀን ገደሉት። ቅዱስ ሰርጊስን ግን አሥሮ በወህኒ ቤት አኖረው።
❤ ከዚህም በኋላ በእግሮቹ ውስጥ ረጃጅም የብረት ችንካሮችን ቸንከረው ከፈረሰኞች ጋር ሩጻፋ ወደሚባል አገር እንዲወስዱት መኰንኑ አዘዘ። ሲወስዱትም ያስሮጡት ነበር ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር በጐዳናም አንዲት ድንግል ብላቴና አገኘ ከእርሷም ዘንድ ውኃን ጠጣ "ሥጋዬን ትወስጂ ዘንድ እስከ ሩጻፋ ተከተይኝ" አላት እርሷም ራራችለት ለጒልምስናውም አዘነችለትና ተከተለችው።
❤ አንጥያኮስም እንዲህ ብሎ ጽፎአልና "ሰርጊስ ትእዛዜን ተቀብሎ ለአማልክት ካልሠዋ ራሱን በሰይፍ ይቁረጡ"። እርሱም ለቅዱስ ሰርጊስ ወዳጅ ነበርና ስለርሱም ይችን ሹመት አግኝቷት ነበርና በዚያንም ጊዜ ወታደሩ የቅዱስ ሰርጊስን ራስ ቆረጠው ያቺም ብላቴና ቀርባ ከእርሷ ጋር በነበረ የፀጕር ባዘቶ ከአንገቱ የፈሰሰውን ደሙን ተቀበለች። የስደቱም ወራት እስከ አለፈ ድረስ ሥጋውን ጠበቀች።
❤ ከዚህም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትም አከበሩዋት የቅዱስ ሰርጊስንም ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ እጅግ ሽታው ጣፋጭ የሆነ በሽተኞችን የሚፈውስ የሽቱ ቅባት ከሥጋው ይፈስ ነበርና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ ሰርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የእስክንድርያ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ አውማንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ።
❤ ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ።
❤ መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን ዐረፈ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት ዐረፉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አውማንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቀሲስ ቅዱስ ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ከተጋድሎው ብዛት የተነሣ ራሱን በሚላጭ ጊዜ በውኃ አያርሰውም ነበር። እግዚአብሔርም ምስጋና በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 10 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለሰርጊስ እንተ ላዕሌሁ ኀለፋ። መዋግደ ሥቃይ ኵሎን በምድረ ፎራት ወሩጻፋ። ሐራዊ በመጥባሕት አመ ለክሣዱ ሰየፋ። ከመ ተመነየ ወከመ ተሰፈወ ተስፋ። ለአክሊለ ሕይወት ወስምዕ ይእዜ ተወክፋ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 10።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ። ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ። በእንተ ዳዊት ገብርከ"። መዝ 131፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥7-12፣ 1ኛ ጴጥ 5፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማር 13፥9-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ከዚህም በኋላ የግብጽ አገር ወደ ሆነ የፍየል ጠባቂ በጦርነት ምክንያት ወደ መለመሉት ስሙ አግሪጳዳ ወደ ሚባል ሰው ሰይጣን መጥቶ አደረበት ወደ አንጾኪያም በደረሰ ጊዜ የመንግሥት ፈረሶች ባልደራስ አደረጉት። የአንጾኪያም ንጉሥ በሞተ ጊዜ መንበሩ ከንጉሥ ተራቆተ በአንዲት ዕለትም የንጉሡ ሴት ልጅ በቤቷ ደርብ ስትመላለስ ሲዘፍን አየችው እርሱም ለፈረሶች ክራርና መሰንቆ ሲመታላቸው እንደሚዘፍን ሰው ሁነው ያሽካኩ ነበር። ስለዚህ ወደደችውና ባል አድርጋ አነገሠችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰየመችው። ያን ጊዜ በዘመኑ ለተደረገ ዓመፅና ግፍ ወዮ ምን ዓይነት ዓመፅና ግፍ ነው።
❤ ክብር ይግባውና ክርስቶስን ከካደው በኋላ ጣዖታትን አመለከ በክርስቶስም ያመነውን ሁሉ ገደለ እንደ ነጣቂዎች አራዊትም የሰውን ሥጋ የሚበላ ደማቸውንም የሚጠጣ ሆነ። የተመረጡ የመንግሥት ልጆችን ሁሉ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች በተናቸው ከእነርሱ ውስጥ በችንካሮች ቸንክሮ የገደላቸው አሉ በማረጃ አርዶ የገደላቸው በጦር ወግቶ በእሳትም አቃጥሎ የገደላቸው አሉ አሥሮ አፋቸውንም በልጓም ለጉሞ ወደ ግብጽ አገሮች እስከ ሰደዳቸው ድረስ ልቅሶና ዋይታም በአንጾኪያ አገር እስከመላ ድረስም ባል ስለ ሚስቱ ሚስትም ስለ ባልዋ እናትና አባት ስለ ልጆቻቸው ልጆችም ስለ ወላጆቻቸው ሰዎችም ሁሉ ስለ ወገኖቻቸው የቅዱሳን ሰማዕታትም ሥጋቸው በሀገሩ ጥጋጥግ የወደቀ ሆነ። ለጠባቂዎች ገንዘብ ሰጥተው በሥውር ወስደው ከሚቀብሩአቸው በቀር ቀባሪ የላቸውም።
❤ ይህም ቅዱስ እስጢፋኖስ የምስክርነት አክሊልን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ኖረ። የመጀመሪያዪቱ ቀን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በግዛቱ ውስጥ ላሉ አገሮች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ የጣዖት ቤቶች እንዲከፈቱና እንዲአመልኳቸው እነርሱ በጦርነት ውስጥ ድል አድራጊነትን ይሰጡናልና ይህንንም ትእዛዝ የሚቃወምና እምቢ የሚል ቢኖር ንብረቱ ይወረስ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ይሠቃይ ርኅራኄ በሌለው አሟሟት እስኪሞት ብሎ የሚያዝ የአዋጅ ደብዳቤ ጻፈ።
❤ የመንግሥቱን ታላላቆች ሁሉ ሕዝቡንም ታላቁንም ታናሹንም ሰበሰባቸው። ይቺ የረከሰች ደብዳቤም በተሰበሰቡት ፊት ትነበብ ዘንድ አዘዘ ቅዱስ እስጢፋኖስም በሰማ ጊዜ ስለ ቀናች ሃይማኖት በክርስቶስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ። ዲዮቅልጥያኖስንም ተመለከተው እንደ ኢምንትም አደረገው። እንዲህም አለው "ንጉሥ ሆይ አጵሎንን ያመልኩ ዘንድ የምታዝ ይቺን የረከሰች ደብዳቤ በመጻፍህ የምታሳየው ይህ ዓመፅ ምንድን ነው ይህንንም ሁሉ ያጠፋው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ" ይህንንም ብሎ ይችን የረከሰች ጽሑፍ በያዘ ወታደር ላይ ተወርውሮ ነጠቀውና ቀደዳት በጣጥሶም ጣላት።
❤ ንጉሡም ቅዱስ እስጢፋኖስን "ይህ የምትሠራው ምንድር ነው ለራስህ ጥፋትን አምጥተሃልና" አለው ከዚህም በኋላ ሰይፉን መዝዞ መታውና ከሁለት ከፈለው የቅዱስ እስጢፍኖስም ራስ ለረጅም ጊዜ በንጉሥ ፊት ሁና በክርስቲያን ወገኞች ላይ የሚደረገውን ሁሉ ግፍ ዳግመኛም በስተኋላ በንጉሡ ላይ የሚመጠበትን ዐይኖቹ እንደሚታወሩ ምጽዋትንም እንደሚመጸወት ከዚያም በኋላ እንደሚጠፋ ተናገረች።
❤ ከዳተኛ ንጉሥ ሄሮድስን የምጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ እንደ ዘለፈችው የቅድስ እስጢፋኖስም ራስ ዲዮቅልጥያኖስን ስትዘልፈው ያዩዋት ዘንድ ብዙ ሕዝቦች የሚመጡ ሆኑ ሄሮድስና ዲዮቅልጥያኖስ አንድ ጠባይ ናቸውና በከፋች ሥራቸውም አይለያዩም።
❤ ሴቶች ከወለዱአቸው የሚመስለው የሌለ የልዑል ነቢይ የሆነ ጻድቅ ሰውን ሄሮድስ በገደለው ጊዜ ዝሙቱ እንዳይገለጽ ሽቶ ነበር ስለዚህም ተልቶ ተበላሽቶ እስኪሞት ሚስቱንም ምድር እስከ ዋጠቻት ልጅዋም እስከ አበደች ድረስ ጉስቍልና አገኘው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስም ዝሙቱን ግልጽ አድርጋ ዘለፈችው። ይህም ጐስቋላ ዲዮቅልጥያኖስ የረከሱ የጣዖታትን አምልኮ ሊገልጥ የማይደበቅ የሕያው እግዚአብሔርን አምልኮ ሊደብቅ ወዶ የቅዱስ እስጢፍኖስን ራስ ቆረጠ የቅዱስ እስጢፍኖስ ራስ ግን ዘለፈችው አማልክቶቹም የርኩሳን አጋንንት ማደሪያዎች እንደ ሆኑ ገለጠች አሳፈረችውም።
❤ በምድርም ውስጥ እንዲደፍኑዋት አዘዘ። እርሷም በምድር ውስጥ ተደፍና ሳለች ዝም አላለችም ሦስት ቀን ያህል አብዝታ እየተናገረች ትዘልፈው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ይሰሟታል እጅግም አፈረ ከእርሳስም ሣጥን ውስጥ እንዲጨምሯትና ሣጥኑን አሽገው ከጥልቅ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወረደ ሣጥኑንም ከባሕር አውጥቶ በባሕሩ ዳር አኖረው ።
❤ እናቱም ሥጋውን እየፈለገች በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዚያ ደረሰች አግኝታውም ዘመን እስቲያልፍ በሥውር ቦታ አኖረችው በፊቱም መብራት አኖረች የመከራውም ወራት ከአለፈ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን በደግ ሰው በኢዮብ ዘመነ መንግሥት በሊቀ ጳጳሳቱ በአባ ቄርሎስ የሹመት ዘመን በዓለም ውስጥ ፈጽሞ የሚያስደንቅ ሥራ ሆነ። በቀኑ እኩሌታ ፀሐይ ጨልሟልና ከዋክብት ታዩ ሌሊትም ሁኖባቸው ሰዎች ፋናዎችን አበሩ ታላቅ ፍርሀትም ፈርተው ወደ እግዚአብሔር በመጮህ በፋጹም ልቡናቸው ለመኑት። ጌታችንም ወደርሱ የጮኹትን ሰምቶ ያንን ጨለማ አስወገደላቸው ፀሐይም እንደ ልማዱ ወጣ ለሁሉ ዓለምም አበራ ደስ ብሏቸውም ክብር ይግባውና ጌታችንን በፍጹም ልባቸው አመሰገኑ።
❤ ሕዝቡም ሁሉ ተሰብስበው ለእግዚአብሔር በዓልን አደረጉ ስለ ኀጢአታቸው አላጠፋቸውምና ፈጥኖ ይቅር አላቸው እንጂ ምስጋናውንም አብዝተው አመሰገኑት ለእርሱ ምስጋና ክብር ገንዘቡ ነውና ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 9 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ለብሔረ ሕንደኬ ዘአሠርጎካ። በልብሰ ሃይማኖት ጽዱል አምሳ ፔካ። መሠንየ ላሕይ ቶማስ እምነ ጽጌ መዋካ። ከመ ታብእ ህየ ኪያሁ ምህርካ። ለንጉሠ ጎና ሐነፅከ በሰማይ ታዕካ"።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ናሁ ይእዜ አልዐለ እግዚአብሔር ርእስየ ዲበ ጸላእትየ። ዖድኩ ወሦዕኩ ውስተ ደብተራሁ መሥዋዕተ። ወየበብኩ ሎቱ"። መዝ 26፥6። የሚነበቡ መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 3፥1-8፣ 1ኛ ጴጥ 5፥2-9 እና የሐዋ ሥራ 6፥8-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥19-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ መዝገበ ሥላሴ የዕረፍት በዓል፤ የአቡነ ፊሊጶስ የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
