ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
😭 አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልና። ከሰው ልጆች መተማመን ጐድሏልና። መዝ 11፥1።
😭 ታላቁ መንፈሳዊው አርበኛ አባ ዕጓለ
ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
.
😭 በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የኖሩት አባ ዕጓለ ብርሐን ሐምሌ 8 ቀን 2014ዓ.ም በ97 አመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
.
😭 አባ ዕጓለ አንጎለላ ኪዳነ ምህረት ስሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳም/ በ1917 የተወለዱ ሲሆን በዕድሜ ባለፀጋ በፀሎት የሚራዱ እንዲሁም በደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤልን በማዕጠንት ለብዙ ዓመት በባዶ እግር እንደ ጥንቱ ገዳማውያኖች በማገልገል ይታወቃል።
😭 ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎ በተጋደሉበት በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟ። የአባታችንን የአባ ዕጓለ ነፍስ እግዚአብሔር አምላክ ከደጋጎቹ ካህናት መልከ ጼዴቅ፣ ከቅዱስ አሮን፣ ከመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና አቡነ ተክለሃይማኖት አጠገቡ ያሳርፍልን።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሐምሌ ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ ናትናኤል ለተባለው ለሐዋርያው ስምዖን ቀለዮጳ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ከላድያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት መላእክት ይጎበኙት ለነበረ ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ለነበረ ለአባ ብስንዳ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) አብራ ሰማዕትነት ከተቀበለች ከቅድስት ቴዎና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ መሐሪ ውእቱ ይሁብ ለዘራኢ፤ አዝ፣ ያሠርቅ እክለ ለሲሳይ ያነሥኦ እድ ለነዳይ፤ አዝ፣ ዘየኀይድዎ ሥልጣነኖ ዘይኤዝዝ ትፍሥሕት ለጻድቃኒሁ፤ አዝ፣ ወሠርዐ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍተ ገባሬ ሕይወት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ"። ትርጉም፦ ከዓለም በፊት ክርስቶስ ንጉሥ ነው፣ ክርስቶስ ይቅር ባይ መሐሪ ነው፣ ለዘሪ ዘርን ይሰጣል፣ የተዘራውን ዘር ለምግብ እንዲኾን ፍሬያማ ያደርገዋል፣ ደሀውን ከድህነቱ ያነሣዋል፣ ባለጠጋ ያደርገዋል። ክርስቶስ ንጉሥ ነው ሥልጣኑን የማይቀሙት፣ ለጻድቃን ደስታን የሚያዝ የሚሰጥ፣ እርሱ የሕይወት መገኛ በመሆኑ የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ፤ ክረምትን በየዓመቱ የሚያመጣ ክርስቶስ ንጉሥ ነው፤ ክርስቶስ ንጉሥ ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ)፦ ይህንንም ሐዋርያ አይሁድ ጌታችንን ወንድም ያዕቆብን ከገደሉት በኋላ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሐዋርያት ሾሙት። እርሱም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ከአይሁድ ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው ተአምራትንም አድርጎአልና በሽተኞችንም አድኗልና።
❤ ንጉሡ እንድርያኖስም ሴቶችን ከባሎታቸው እንደሚለይ ንጽሕናቸውንም እንዲጠብቁ እንደሚአዝዛቸው ስለ እርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ሐምሌ 10 ቀን እንዲቆርጡ አዘዘ ከእርሱም ጋር ቴዎና የምትባል አንዲት ድንግል ተገደለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁላችንም የክርስቲያን ወገኖች ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ከላድያኖስ፦ ይህም ቅዱስ አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዘጠነኛ የሆነ ነው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበር ዐሥራ አራት ዓመት መንጋውን እየጠበቀ ከኖረ በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ከላድያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ አባት አባ ብስንዳ፦ ይህም ቅዱስ ጥልቅ በሆነ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቆሞ ሲጋደል ኖረ መላእክትም ይጎበኙትና ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ነበር። ከዚህም በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 10 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ናትናኤል ዘቃና። እስራኤላዊ ንጹሐ ሕሊና። ሐዋርያ ሐዲስ ሠናየ ርሥእና። በረከተከ ከዐው ለሕዝብከ መንገለ ይትፈቀድ ፍና። ከመ ዝናማተ ይክዑ ደመና"። ሊቁ አርከ ሥሉስጨ(አርኬ) የሐምሌ 10።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ1፥44-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ። ወሐምልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው። ከመ ያውፅእ እክለ እምድር"። መዝ 103፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም፣ ግብ፡ ሐዋ 27፥21-33። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥36-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ወይም የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀለዮጶ) የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❄️❄️❄️❄️❄️
መዝሙር ዘሰንበት
✨✨✨✨✨
ሃሌ ሉያ
ይሠጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ፤ ለኩሉ ዘሰአሎ፤ እግዚአ ለሰንበት አምላከ ምሕረት ፤ማ፦ ያርኁ ክረምት በበዓመት፤ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት
አመላለስ፦
ያርኁ ክረምት በበዓመት/2/
ይሰምዑ ቃሎ ደመናት/4/
https://t.me/Eotcw
@EOTCmahlet
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
1 161
❤ ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።
❤ ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 9 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ዕብል ለብእሲ ምእመን። እንተ ይሰመይ ኅልያን። ከመ ግዕዘ ምስለ ፫ቱ ዕደው ኅብረ ፀዓዳ ልቡሳን። ያብርህ ሎቱ በውስተ መጽልም መካን። እምበረ እዴሁ ወጺኦ መስቀል ዘብርሃን"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 9።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 3፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 13፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሐምሌ ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን ለአምስቱ አገር ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ቴዎድሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመስተጋድል ከአባ ኅልያን ዕረፍት በዓልና ለቆጵሮስ አገር ለሆነ ለቅዱስ ታኦድሮስ ከእርሱም ጋር ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት ለነበሩ ለሁለት መኳንንት ለሉክያኖስና ለድግናንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመብራጣንና ከቀፈጠላ ኤጲስቆጶስ ከንድራኦስ ከመታሰቢያቸው፣ ከግብጻዊው ከቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሴ ቤት ከከበረችበት፣ ከአባ ኤሲ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ ከአምስት ሽህ አምስት መቶና ከአራት ጭፍሮች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ደምረነ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳኒከ ምስለ እለ ገብሩ ፈቃደከ እለ እምዓለም አሥመሩከ፡፡ እለ ዐቀቡ በንጽሕ ሥርዓተ ቤትከ (ወእለ ሰበኩ በሠናይ)/፪/ በሠናይ ዜናከ"። ትርጉም፡- ፈቃድህን ከሠሩ በሕይወታቸውም ካስደሰቱህ የቤትህንም ሥርዓት ከፈፀሙ ዜናህንም በመልካም ካስተማሩ ቅዱሳንህ ሁሉ ጋር ደምረን፡፡
+ + +
❤ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባ ቴዎድሮስ፦ ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር። ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።
❤ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም"። መኰንኑም "በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ የምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን?" አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ "አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው" አለው።
❤ መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን ሐምሌ 9 ቀን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ቴዎድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ መስተጋድል አባ ኅልያን፦ የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።
❤ በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ "ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም" አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም "አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ" አላት።
❤ ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።
❤ ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።
❤ ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር። የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።
❤ ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው "አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም" አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።
❤ ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኅልያን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ከቆጵሮስ አገር የሆኑ ሰማዕቱ ቅዱስ ታውድሮስ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ፦ ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሐምሌ ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለኢትዮጵያዊው ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ እስትፋሰ ክርስቶስ በአባይ ባሕር ውስጥ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመት ከጸለዩ በኋላ ከጌታችን ቃል ኪዳን ለተቀበሉበት ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
+ + +
❤ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በአባይ ባሕር ዘጠኝ ዓመት እንደ ጸለዩና ከጌታችን ቃል ኪዳን እንደተቀበሉ፦ ከዚህም በኋላ ወደ ዋልድባ ደርሶ በዚያ በዋሻው ውስጥ እየጾመ ለገዳሙ እያገለገለ አራት ዓመት ቆየ፣ ከአራት ዓመት በኋላ ከአቡ ሳሙኤል ጋራ ተገናኘ አቡነ ሳሙኤልም "የአንተ ክፍል ይህ ነው" ብሎ ቦታውን ነገረው።
❤ ከአራት ዓመትም በኋላ አረጋውያን መነኰሳትን ተሰናበታቸው እነርሱም መርቀውት የኢትዮጵያን ገዳማት ተዘዋውሮ እየጎበኘ ገዚም ወደ ሚባል አገር ደረሰ ይኸውም ጎጃም (ጎዣም) ነው በዚያ እያስተማ፣ እያጠመቀ፣ የታመሙትን እየፈወሰ፣ የዕውራንን ዐይን እያበራ፣ ሙታንንን እያስነሣ፣ በዚያ ተቀመጠ ተአምራትንም እያደረገ በጾምና በጸሎት የምታታቸውን ዕፀዋት የጥንቁልናቸውን ሥራ ሻረባቸው። እነርሱም ምታታቸውን ጥለው ንስሓ ገቡ።
❤ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ባሕር ውስጥ ገብቶ ፱ (ዘጠኝ) ዓመት ለኢትዮጵያ ጸለየ። ከጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ "የመነኰሳት መጨረሻው ከመነኰሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ይህችን ሀገር እና የኢትዮጵያን ሰዎች ምሬልሃለሁና ከዚህ ባሕር ውጣ" አለው።
❤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ከባሕር ውስጥ ወጥቶ ተንበርክኮ ለጌታችን ሰገደ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም "የማረፊያህ ቦታ የምትሆን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ ዳውንት ሂድ ዳግመኛም ዝክርህን የዘከረ፣ ስምህን የጠራ፣ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፣ የጻፈውን፣ ገድልህን ያነበበ፣ የተረጎመ የሰማውን እስከ ሰባት ትውልዶ እምርልሃለሁ ስለድካምህ ብዛት ኃጢአታቸውንም ይቅር እላቸዋለሁ" ይህን ብሎ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ከአባታችን ከአቡነ እስትፋንሰ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ እስትፋንሰ ክርስቶስ 9፥9-13።
+ + +
❤ "ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፋከ ዘጥዕመ። ዕክለ በረከቱ ለክርስቶስ በሥጋ ማርያም ዘሐመ። እስትንፋሰ ክርስቶስ መናኒ እንበለ ትበል ጌሠመ። በጌባል ምድረ መርገም አመ። በረከትከ ቆመ ፍሬ ዕፀ በለስ መሪር ተረክበ ጥዑመ"። መልክዐ አቡነ እስትፋንሰ ክርስቶስ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ዛሬ ለምንድነው ሚነግሰው?
➣ ሥሉስ ቅዱስ
➼ በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸው
➼ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
➼ ከፍጥረታትወገንከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
➼ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንምአቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትምየይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች::
➼ እንደ ዘንድሮወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ ብለው ነበርናበዚህምምክንያት ነው ይስሐቅ የተባለው::
➼ ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል አድረዋልና
ሐምሌ 7 ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጠለት በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው
1 161
❤ መኰንኑም በአየው ጊዜ ሹም እንደሆነ አውቆ ከእርሱ ንዋየ ቅድሳትን ፈለገ ዳግመኛም ለአማልክት እንዲሠዋ ፈለገ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ስለ ንዋየ ቅድሳት ከእኔ ልትሻ አይገባህም የረከሱ አማልክትንም ስለማምለክ ትእዛዝህን አልሰማም እኔ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁና"። መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጥቶ ምላሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም እንደ ቀድሞው ምላሱን መለሰለት። ከዚህ በኋላ በማበራያ ውስጥ አበራዩት በብረት ዐልጋ ላይም ቸንክረው በበታቹ እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጉዳትም አስነሣው።
❤ ከዚህ በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገልጾለት አጽናናው ከዚህም በኋላ በወህኒ ቤት ጨመሩት በዚያም ተአምራትን አደረገ። ጋኔን ያደረባት የአቅፋሃስ ሀገር ሰው የዮልያኖስ እኅት ነበረች ቅዱስ ቢማም ያንን ጋኔን ከእርሷ ላይ አወጣውና አሳደደው ዜናውም በሀገሩ ውስጥ በተሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ።
❤ መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃየው በመንኰራኵርም የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች አወለቁ በእሳትበአጋሉት በብረት ሰንሰለትም አሥረው ጐተቱት። በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥም ጣሉት ከዚህም ጌታችን አዳነው። ከዚህም በኋላ በአንገቱ ታላቅ ደንጊያ አንጠልጥለው በባሕር ውስጥ ጣሉት አሁንም ጌታችን አዳነው። ሁለተኛም ከእሳት ጨመሩት። ከዚህም ጌታችን አዳነው በእሳቱም መካከል እየጸለየ ቆመ።
❤ መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያም ያሠቃዩት ጀመሩ ዘቅዝቀውም ሰቀሉት ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ ጨምረዉ በላዩ እሳትን አነደዱበት ጌታችንም ተገለጠለትና ከእሳቱ አዳነው። ከዚህም በኋላ ጌታችን ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉን ለሚጽፍ በስሙም ምጽዋት ለሚያደርግ ሁሉ የዘለላም ሕይወትን ያድለው ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው።
❤ መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንደ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ። የአቅፋሃስ ከተማ ሹም የሆነ የዮልዮስ ባሮችም ሥጋውን አንሥተው ወደ ሀገሩ ወሰዱት እስከ ስደቱ ዘመን ፍጻሜ ድረስም በመልካም ቦታ አኖሩት። ከዚህም በኋላ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያንንና ገዳምን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ በሽተኞችም ሁሉ ይፈወሱ ነበርና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በአባ ቢማ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 8 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለብሶይ ዘአፈድፈደ ተጋድሎ። እስከ በመንፈስ መጺኦ ቆስጠንጢኖስ ይቤሎ። መንግሥተ ምድር ወትፍግዕተ ዓለም ዘይመስሎ ሶበሰ አእመርኩ እምገደፍኩ ኵሎ። ክብረ መነኰሳት ከመዝ በሰማይ ዘሀሎ"። ትርጉም፦ በሰማይ ያለው የመነኰሳት ክብር እንዲኽ መኾኑን ባወቅ ኖሮ የምድር መንግሥትን የዓለም ደስታን የመሰለውን ኹሉ በጣልኊ ነበር ብሎ ቆስጠንጢኖስ በመንፈስ መጥቶ እስኪነግረው ድረስ ተጋድሎን ያበዛ ለኾነ ለብሶይ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ8።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዮም አመ ሰማዕክሙ ቃሎ። ኢታጽንዑ ልበክሙ። ከመ አመ አምረርው በገዳም"። መዝ 94፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 9፥8-16።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር። እግዚኦ አነ ገብርከ። ገብርከ ወልደ አመትከ"። መዝ 115፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 6፥10-19፣ 1ኛ ጴጥ 3፥10-15 እና የሐዋ ሥራ 26፥12-19። የሚነበበው ወንጌል ማር4፥1-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባቶቻች የአባ ኪሮስና አባ ብሶይ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
