cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎የትምህርት ክፍል ✞︎⛪️

✞︎✞︎✞︎በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞︎የተለያዩ_ተከታታይ ትምህርት ✞︎ስንክሳር _የቅዱሳን _ገድል _ በየዕየለቱ አለ ✞︎ስበከት ✞︎መንፈሳዊ ጥያቄዎች በዕየለቱ አለ ✞︎የተለያዩ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎ ✞︎በዚህ ቻናል ✞︎ ይቀርብበታል።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 445
مشترکین
+4424 ساعت
+2257 روز
+1 02530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ትምህርተ ሃይማኖት ቀጣይ ክፍል ሀልዎተ እግዚአብሔር የማይታይና የማይመረመር ኹሉን ማድረግ የሚችል ኹሉን የፈጠረ የመጀመሪያ ያልነበረው መጨረሻም የማይኖረው ለዘላለም የሚኖር አንድ አምላክ መኖሩን ማመን ለሰው ልጆች መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ያለው ዕውቀት ኹለት ዓይነት ነው:- 1ኛ ሰው በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ ስለተፈጠረ በተፈጥሮ የተሰጠው ዕውቀት እያደገ ሲኼድ ፈጣሪውን ተመራምሮ የማወቅ ችሎታ አለው፡፡ 2ኛ ሰው ፈጣሪውን በተፈጥሮ ያገኘው ዕውቀት ቢኖረውም በተጨማሪ በእግዚአብሔር ልዩ መገለጥ ፈጣሪውን ያውቃል፤ ይኹን እንጂ ሰው ስለእግዚአብሔር ያለው ዕውቀት የተወሰነ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይመዘንና የማይለካ በመሣሪያም የማይመረመር ስለኾነ የሰው እውቀት እጅግየተወሰነ በመኾኑ ነው፤ ሰው በዓይኑ ዐይቶና በእጅ ዳብሶ በመሣሪያም መርምሮ ማረጋገጥ የሚችለው የተፈጠረውን ግዙፍ ነገር ብቻ ነው፡፡ ስለኾነም ሀልዎተ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ሀለወ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጉሙም መኖር ማለት ነው፡፡ ስለዚኽ ሀልዎተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር ለዘመኑ የጊዜ ቀመር አይቀመርለትም፡፡ በዚኽን ጊዜ ነበር በዚኽኛው ጊዜ ደግሞ አልነበረም አይባልም፡፡ እግዚአብሔር ከዓለም /ከፍጥረት ኹሉ/ አስቀድሞ መኖሩ ይታወቃል እንጂ የኖረበት ዘመን አይቆጠርም፡፡ “እነሆ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ አናውቀውምም፡፡ የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም፡፡ ” [ኢዮ 36፥26] እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እንደዛሬው ኹሉ በሙሉ ክብሩ ነበር የዓለም አለመኖር ከእግዚአብሔር ክብር ላይ የሚያጎድለው / ያጎደለው / ነገር የለም፡፡ “ እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከ ዘለዓለም ድርስ በሦስትነቱ አለ እግዚአብሔር በመለኮቱ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና ከጽባሕ በፊት በመላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ የየብስም ፊት ሳይታይ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከፀሓይና ከጨረቃ ከከዋክብትም በፊት ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ .” [ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ከቍ. 3 -8፣ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ከቍ. 4–13] “እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው ” [መዝ. 73፥12] “እግዚአብሔር ከጊዜ ውጪ ነው ” በክርስትና ሕግ የአግዚአብሔርን መኖር ለማወቅ እናለመረዳት ቍልፍ እምነት ነው፡፡ ከእምነት ያልተነሣ ሰው በፍጹም ወደ እግዚአብሔር ሊደርስ አይቻለውም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ግንኙነት ዋናው መሠረት እምነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን የማወቅ መሠረቱ እምነት ስለኾነ “በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና ” [2ቆሮ. 5፥6] ተብሎአል፡፡ ክርስትና ማየት ማመን ነወ በሚለው ብሒል አትመራም፡፡ ጌታችንም “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” ያለው እምነት መሠረት በመኾኑ ነው፡፡ [ማቴ. 5፥1] ይኹን እንጂ የእግዚአብሔርን መኖር ለማወቅ መሠረቱ እምነት ቢኾንም ብቸኛው ግን አይድለም፡፡ ፈጣሪን እናውቅ ዘንድ የሚያግዙንን ነገሮች ሰጥቶናል፡፡ እንድናውቀው አጋዥ አድርጎ ከሰጠን ውስጥ ሥነ ፍጥረት ሕሊና፣ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ዝንባሌ እና ቃለ እግዚአብሔር ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ¶ ስለ እግዚአብሔር ህልውና የሚያስረዳ ትምህርቶች † እግዚአብሔር አለ ከተባለ ለምን አይታይም? እግዚአብሔር ባሕርይው የማይዳሰስ ረቂቅ ስለኾነ ባሕርዩ ለፉጡሩ አይታይም ምክንያቱም ፉጡር ሊያየው የማይችል መንፈስ መለኮት ነውና እንኳን ንጹሐሥጋ በሌለን በእኛ ሊታይ ባለሟሉ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሊያየው ሽቶ የተሰጠው መልስ « ሰው ዐይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም» የሚል ነው [ዘጸ‹33÷17-20, ዮሐ 4÷24] መለኮት መንፈስ ነው የሚታይ አይደለም እግዚአብሔር በባሕርዩ ረቂቅ ነው፡፡ ስንል በርቀት ከእርሱ ጋር የሚወዳደረው የለም ከማየት እንኳን ማየት ይርቃል በምሳሌ ከአፈር ውሃ ይረቃል ከውሃ አየረ ይርቃል እንዲኹም ከመላዕክትም ከአየርም ርቀት የእግዚአብሔር ርቀት ይበልጣል፡፡ ስለዚኽ እግዚአብሔር በሰው አእምሮ አይመረመርም፡፡ ይቆየን... ✝ ቻናሉን ሼር በማድረግና እየጋበዛችሁ ተሳተፍ🙏 https://t.me/egzihabern_amesgnu_cher_newna
نمایش همه...
✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎የትምህርት ክፍል ✞︎⛪️

✞︎✞︎✞︎በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞︎የተለያዩ_ተከታታይ ትምህርት ✞︎ስንክሳር _የቅዱሳን _ገድል _ በየዕየለቱ አለ ✞︎ስበከት ✞︎መንፈሳዊ ጥያቄዎች በዕየለቱ አለ ✞︎የተለያዩ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎ ✞︎በዚህ ቻናል ✞︎ ይቀርብበታል።

[ + ጴጥሮስ ወጳውሎስ + ].mp36.35 MB
[ + ጴጥሮስና ጳውሎስ + ] .mp36.48 MB
Photo unavailableShow in Telegram
                        †                            🕊   💖  ዼጥሮስ ወዻውሎስ  💖   🕊                          🕊                          [  እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ   ] ❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞ [   ተአምኆ ቅዱሳን   ] ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን ፣ ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ። †     🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    † 🕊                        💖                       🕊                                    
نمایش همه...
                         †                           [      🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊      ] [ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ተርእዮን [ መታየትን ] አለመውደድና ለታይታ ብሎ ምንም ነገር አለማድረግ !  ] 🕊 " በጆሮህ ትመገብ ስለ ነበር ነው .... ! " ........ በአንድ መንደር ውስጥ አብዝቶ ከመጾሙ የተነሣ "ጾመኛው" እየተባለ እስከ መጠራት የደረሰ አንድ ሰው ነበር፡፡ አባ ዜኖ ስለ እርሱ ሰማና ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፡፡ "ጾመኛውም" በደስታ መጣና ከጸለዩ በኋላ ተቀመጡ፡፡ አረጋዊው አባትም በፀጥታ ሆኖ ሥራውን መሥራት ጀመረ፡፡ አረጋዊው የማያዋራውና ምንም የማይለው በመሆኑ "ጾመኛውን" ይሰለቸው ጀመር፡፡ ስለዚህም ለአረጋዊው ፦ "አባ ፣ ልሄድ ነውና ጸልይልኝ" አለው:: አረጋዊውም "ለምን?" ሲለው "ምክንያቱም ልቤ ልክ በእሳት ላይ እንደ ተጣለ ያህል ሆኖ ይሰማኛል ፣ ነገሩ ምን እንደ ሆነ አልገባኝም። በምኖርበት መንደር ሳለሁ በእውነቱ እስከ ምሽት ድረስ ስጾም ምንም ዓይነት እንዲህ ያለ ነገር ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር" አለው:: አባ ዜኖም ፦ "በመንደር ሳለህ በጆሮህ ትመገብ ስለ ነበር ነው:: ነገር ግን አሁን ሂድና ከዚህ በኋላ በዘጠኝ ሰዓት ተመገብ ፣ የምታደርገውን ማንኛውንም ነገር በስውር አድርግ" አለው:: በዚህ ምክር መሠረት ማድረግ ሲጀምር "ጾመኛው" እስከ ዘጠኝ ሰዓት መቆየት ከባድ ሆነበት። በፊት እስከ ምሽት ድረስ ሲጾም ያውቁት የነበሩ ሰዎችም በዘጠኝ ሰዓት ሲመገብ ሲያዩት ፦ "አይ ፣ ዛሬስ ጾመኛውን ሰይጣን ይዞታል!" ይሉ ጀመር፡፡ እርሱም ወደ አረጋዊው አባት ሄደና ይህን ነገረው ፣ አባ ዜኖም ፦ "ይህ መንገድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ነውና በዚሁ ቀጥል" አለው:: " የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
                          †                           [    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ] [        ክፍል  አሥራ ሦስት         ] 💛 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ [ ወደ ቅዱስ እንጦንስ ዘንድ መሄዱ ! ]                          🕊                          ❝ ቅዱስ መቃርዮስም ተነሥቶ ከጸለየ በኋላ ወደ ቅዱስ እንጦንዮስ ጉዞ ጀመረ፡፡ ከቅዱሱ አረጋዊ ከእንጦንስ ጋር በተገናኘ ጊዜ በታላቅ ፍስሐ ተቀበለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ልጅ በአባቱ ፊት እንደሚሆን ሀሳቡን ሁሉ ገለጠለት ፤ ምንም ነገር አልደበቀውም፡፡ ቅዱስ እንጦንዮስም የቅዱስ መቃርዮስን ራሱን ሳመው ፤ እንዲህ አለው ፦ "ልጄ መቃርዮስ ሆይ እንደ ስምህ ትርጓሜ ብፁዕ ትባል ዘንድ አለህ ፣ እግዚአብሔር አምላኬ የአንተን ግብር ከብዙ ዘመን አስቀድሞ ገልጦልኛልና ፤ ወደ እኔ እንደምትመጣም ነግሮኝ ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ እኔ መምጣትህን ስጠብቅ ኖርሁ ፤ ስለ ደህንነትህም የማስብ ሆንሁ" አለው፡፡ ቅዱሱ አረጋዊ እንጦንስ በብዙ ነገር እየተናገረ  ለምንኩስና ግብር እንደሚገባ መከረው አጽናናው ፤ የሰይጣናትን ጾርም እንዴት እንደ ሆነ ገልጦ አስረዳው ፤ እነርሱ በክፉ ህሊና በስውርና በገሃድ እስከ ሞት ድረስ አጽንተው እንደሚዋጉት ነገረው፡፡ "ቢታገሉህም እስከ ሞት ድረስ ፈጽሞ የምትታገሥ ሁን" አለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመነው፡፡ እርሱ ግን አልፈቀደለትም ፤ እንዲህ አለው ፦ "ከእኛ እያንዳንዱ እግዚአብሔር በወሰነለት ቦታ በትዕግሥትና በአርምሞ ይኑር" አለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስ በቅዱስ እንጦንስ በነበረበት ጊዜ የምንኩስናን የአኗኗር ሥርዓት ተማረ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ለአባ ሰራጵዮን እንዲህ አለው ፦ "በቅዱስ እንጦንስ ዘንድ በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ ሌሊት ፈጽሞ ተኝቶ አይቼው አላውቅም፡፡ ትዕግሥቱና ገድሉ ሁሉ የሚደነቅ ነበር፡፡" እግዚአብሔር የአንዱን ገድል ለሌላው ገልጦ ያሳየው ነበርና፡፡ ❞ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡ ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
✝ደቂቀ ነቢያት ቅዱሳን አሠርቱ ወክልኤቱ፤ እለ አውኃዙ ትንቢተ ለክርስቶስ በአፍቅሮቱ፤ ሶፎንያስ ዘገብረ ለእግዚአብሔር ዘከመ ሥምረቱ፤ አቡቂር ወዮሐንስ ጽዑራነ ዘሞቱ! ✝እንኳን አደረሰን ! https://t.me/zikirekdusn
نمایش همه...
1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.