Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
رفتن به کانال در Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
نمایش بیشتر3 584
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
+5330 روز
آرشیو پست ها
Share Proceeding on Cconstruction Law (1).pdf
አሜን(3) ቤተሰብዎች- እንኳን ለአዲስ አመት (2017) ዘመነ ማቴዎስ በሠላም አደረሳችሁ | አደረሰን!
"በቸርነትህ ብዛት ዓመትን ታቀዳጃለህ፣
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።"
መዝ 64(65)-:-11
መልካም በአዲስ ዓመት!
ይሁንልን | ይሁንላችሁ!
እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም አደርሰን~አድረሳችሁ! ✨🌼
መልካም ዘመን እንዲሆንላችሁ
እንመኛለን! ✨🌼✨🌼✨🌼✨
✨መልካም አዲስ ዓመት!✨
ጥያቄ፦ በግንባታ ሥራ ሂደት የሚመጡ የሥራ መለዋወጦች ወይም በውል ከተያዘው ሥራ የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ልዩነቶች (Variation) ሲኖሩ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በራሱ ውሳኔ ማጽደቅ የሚችለው በውል ከተያዘው የግንባታ ዋጋ ላይ ከስንት ፐርሰንት በላይ ካልጨመረ ወይም ካልቀነሰ ነው? http://t.me/con_site_solution🚧ስለሥራ መለዋወጥ (ጭማሪ ወይም ቅናሽ - Variation) ትንሽ እናብራራላቹ.. .) በግንባታ ሂደት የሥራ መለዋወጥ (Variation) የሚከሰት አጋጣሚ ሲሆን ይህ መለዋወጥ የሥራ መቀነስ ወይም የሥራ መጨመር ሊሆን ይችላል። ይህ የሥራ መለዋወጥ በተቆጣጣሪ መሐንዲሱ (Engineer) ትዕዛዝ የሚከናወን ነው። ነገር ግን በ1988 እና በ1992 ሁለተኛ እና ሦስተኛ እትም በወጣበት FIDIC 1987 አንቀጽ (clause) 52.3 መሰረት የሥራ መለዋወጡን ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ለአሠሪው አካል ሳያሳውቅ የማጽደቅ መብታ ያለው የውሉን ጠቅላላ ዋጋ ከ15% በላይ የማይጨምር ወይም የማይቀንስ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው። የሥራ መለዋወጡ ከ15% በላይ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ከሆነ ግን ከአሠሪው ባለቤት (Employer) ጋር ተወያይቶ በጋራ ቃለጉባኤ ወስነው መሆን ይገባዋል። ስለዚህ ከላይ ለተነሳው ጥያቄ መልሱ፦ 15% ነው።
ጥያቄ፦ በግንባታ ሥራ ሂደት የሚመጡ የሥራ መለዋወጦች ወይም በውል ከተያዘው ሥራ የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ልዩነቶች (Variation) ሲኖሩ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በራሱ ውሳኔ ማጽደቅ የሚችለው በውል ከተያዘው የግንባታ ዋጋ ላይ ከስንት ፐርሰንት በላይ ካልጨመረ ወይም ካልቀነሰ ነው???http://t.me/con_site_solution
ለገጠር መንገዶች ግንባታ 407 ሚሊየን ዶላር ተዘጋጀየከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የገጠር መንገዶችን ከቀበሌ እስከ ዋና መንገዶች የሚያስተሳስር የ407 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል። የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና የተሰኘ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ እና በክልሎች መንገድ ፈንድ የሚተገበር መሆኑን የከተማና መሠተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ሄለን ደበበ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ በገጠር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ በማድረግ ኑሯቸውን እንደሚያሻሽል አንስተዋል። አርሶ አደሮች ምርታቸውን በተገቢው ሰዓት ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግም ጠቅሰው፤ በሁሉም ክልሎች እንደሚተገበርና ከ11 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። የመንገድ ግንባታው በቀጣይ 5 ዓመታት የሚከናወን ሲሆን፥ ለ200 ሺህ ዜጎች በቀጥታና ለ360 ሺህ ዜጎች ደግሞ በተዘዋዋሪ የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል
የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች ፣ የከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እና የፕላንቶች መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
Invitation for International Opening BidTender No. ECWCT-ICB-PW-18/2017 The Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) here by invites sealed bids from eligible bidders all over the world for the procurement of sub contract for construction of Grouting works at Upper Gudder Fatol Dam & Appurtenant structures construction project under International Competitive bidding. This project aims to enhance the quality and durability of our construction initiatives through advanced grouting techniques. 1. Bidders or Representatives should submit registration documents and copy of legal license renewed for 2024 and power of attorney from their principal along with their bid documents. 2. Bidding document should be prepared in English language. 3. A set of bidding documents can be obtained with none refundable payment of ETB 600.00 (Six hundred birr only) during working hours from the Procurement and property administration main department. 4. Bid must be accompanied with a Bid Security an amount of ETB 200,000.00 (Two hundred thousand birr only) in the form of certified check (CPO) or unconditional Bank guarantee. Bid Bond in the form of insurance bond or in any other form shall not be accepted. 5. The bid bond will be confiscated; if the bidders failed to sign contract to conduct Grouting works for which they are awarded. 6. Interested bidders should submit their bid documents in person to Procurement and property administration main department where the tender box is found. 7. Bids must be submitted to the above address until the Bid Submission Deadline October 09/2024 at 03:00 P.M 8. Bid will be opened in the presence of bidders or their legal representatives who wish to attend on October 09/2024 at 03:30 P.M at Procurement and property administration main department. 9. The buyer (ECWC) reserves the right to cancel or reject part or all bids 10. Bidders may get further information at the following address: Ethiopian Construction Works Corporation. Gurd Shola behind Athletics federation’s building and Infront of Andinet international College Telephone 011 8 96 29 91/01118 67 80 89 Addis Ababa, Ethiopia
"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?"የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው። በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል። ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል። የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ ውኃ መጠጣት አለበት። የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል። (ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል። ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው
በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ??http://t.me/con_site_solution
ኮንስትራክሽን ክሌምየኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው። የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ መለየት ይገባል። DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል። የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም። ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል። ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል። በጉባዔ አሰፋ
ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን። [2] - መኮማተር (Shrinkage) ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking) ያስከትላል ። መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ። [3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል። [4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል። [5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing) ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት። ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት። [6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution) አለመመጣጠን በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution) nonlinear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል። [7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።
+2
ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች ለመሰንጠቅ (cracking) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎች🏗👇👇
NEW VACANCY 🚧Position: Interior DesignerJob Time: Full-Time Job Type: Permanent Place of Work: Addis Ababa - Ethiopia Deadline: September, 15/2024 Key Responsibilities: Assist in creating interior design concepts and space planning based on client requirements. Develop design presentations, mood boards, and sketches to communicate ideas. Prepare detailed drawings, floor plans, and layouts using design software (e.g., AutoCAD, SketchUp, or Revit). Select materials, woodwork, furnishings, lighting, and accessories that complement the design concept. Coordinate with vendors and suppliers to source materials and furniture within budget. Support senior designers in project management, ensuring timelines and budgets are met. Conduct site visits to ensure design implementation aligns with project plans. Collaborate with architects, contractors, and other professionals to achieve project goals. Stay updated on the latest design trends, techniques, and materials. Qualification: Bachelor’s degree or above in Interior Design, Construction, or Architecture ONLY 0-2 years of experience in interior design or a related field. Those who can prepare realistic proposals Proficiency in design software such as AutoCAD, SketchUp, Revit, or similar tools. Basic knowledge of materials, finishes, and furniture sourcing. Female candidates are highly encouraged to apply How to apply Interested and Qualified applicants who fulfill the above requirements are invited to send your application CV and Portfolio to
📩Email: Tesfumemhr@gmail.com or Telegram @tes4288 📞For more information, you can call to 0967606162
ጥያቄ፦ በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው?
መልስበኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው።
👉የደመወዝ ጭማሪ ረቂቅን በተመለከተ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ ሰነድ📜
@etconp
Repost from Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉የደመወዝ ጭማሪ ረቂቅን በተመለከተ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ ሰነድ📜
@etconp
በኮንስትራክሽን ውል🚧 ስለንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract), ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) እና በአሰሪው የሚታወቅ ንኡስ ተቋራጭ(Nominated Subcontracting) እናያለን ይጠብቁን.. .🤚
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
