fa
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

رفتن به کانال در Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

نمایش بیشتر
3 584
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
+5330 روز
آرشیو پست ها
የሪል እስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ቢካተቱ የምላቸው ነጥቦች:-
1) የተፈጻሚነት ወሰኑ ትኩረት  ከ50 ቤቶች በላይ ለሚገነቡ የሪል እስቴት አልሚ ተብለው የተጠቀሱት ላይ መሆኑ። 2) ከ50 ቤቶች በታች የሚገነቡና የተገነባ አንድ ቤት ብቻ ያለው ባለቤት ግብይት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊመራበት የሚችል አቅጣጫ አለማስቀመጡ። 3) ከውጭ ለሚመጡ አልሚዎች አነስተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል መጠንና ሊገነቡት የሚገባ አነስተኛ የቤት ቁጥር አለመቀመጡ። በኢንቨስትመንት ጋይዱ መሰረት ከተወሰደ ከ200ሺ ዶላር ጀምሮ ስለሚያስተናግድ ፍትሃዊ አይሆንም። 4) የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በጋራ ወደ ሪል እስቴት ቢዝነስ ሲገቡ በጋራ ሊሰሩት ስለሚገባው የፕሮጀክት መጥንና አነስተኛ ድርሻ የተጠቀሰ ንገር የለውም። 5) ተጀምረው በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ህጉ ማዕቀፍ ስለሚገቡበት አግባብ የተጠቀሰ አካሄድ የለም። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከሚጠናቀቁት ውጪ ወደ ህግ ማዕቀፉ የሚገቡበት መንገድ መቀየስ ይኖርበታል። 6)ግንባታ ላልጃመሩ አልሚዎች ሊከፈል ስለሚገባው ትልቁ የቅድመ ክፍያ መጠን ገደብ አላስቀመጠም። ብዙ ሃገራት ከ10% እንዳይበልጥ ያደርጋሉ። 7) የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የሚዳኝ የተለየ አካል እንደሚኖር አይገልጽም። ዘርፉ የተወሳሰበና ልዩ እውቀትንና ዝግጅትን ስለሚፈልግ ሪል እስቴት ጉዳዮችን ብቻ የሚዳኝ የተለየ የህግ አካል ይፈልጋል። 8) ከውል መዋዋል እስከ ርክክብ ያለውን የግብይት ሂደት የሚያሳይ ግልጽ የስራ ሂደትን የሚያሳይ አካሄድን ማሳየት ይጠበቃል። 9) ግብይቱን ለመምራት ወጥ የሆነ መሪ ውል ተዘጋጅቶ አስገዳጅ መሆን አለበት። 10) የሽያጭ ባለሙያዎችንና እንደራሴዎችን በተመለከተ ፈቃድ ማውጣት እና ማሳደስ እንዳለባቸው እንጂ በዘርፉ ሰልጥነው ተፈትነው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የሚገልጽ ሃሳብ የለውም። 11) የቤት ብድር ለመስጠት የሚቋቋሙ ባንኮች ከተቋቋሙበት ዓላማ ማለትም ለቤት ገዢዎች ከማበደር ይልቅ ወደማልማት እንዳይገቡ አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት። 12) አልሚዎች በራሳቸው አመቻችነት  ለቤት ገዢዎች ብድር በሚያመቻቹበት ጊዜ መከተል ስለሚገባቸው አሰራርና ስለሚተገበር ክትትል የሚያሳይ ነገር የለውም። 13) አልሚዎች ለደንበኛቻቸው በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ቤት በሚሸጡበት ወቅት ሊያስከፍሉ የሚችሉት ትልቁ የወለድ ምጣኔ መካተት አለበት። 14) አልሚዎች በተቀመጠው የፕሮጀክት ማስረከቢያ ጊዜ ተቀባይነት የሌለው መዘግየት ከተከሰተ ሊከፍሉ ስለሚገባው ቅጣት በዝርዝር አልተቀመጠም። አንዳንድ ሃገራት ደንበኛው የገዛውን ቤት የሚመጥን ቤት የሚከራይበትን ወርሃዊ የቤት ኪራይ ሲያስከፍሉ በመዘግየቱ የተነሳ ውሉን ደንበኛው  ለማቋረጥ ከፈለገ ክፍያው አልሚው ገንዘቡን በተጠቀመበት ጊዜ የሚለካ ከፍተኛው የሃገሪቱ የብድር ወለድ ምጣኔ ተሰልቶ እንዲመለስ ያደርጋሉ።  15) ለቅድመ ክፍያ እንደ ዋስትና የተጠቀሰው የአልሚውን ካርታ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ማገድ ነው። ይህ ለቤት ገዢ አስተማማኝ ዋስትና አይደለም። ግብይቱ በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ በመሆኑ ለተከፈለው መጠን የሚመጥን ዋስትና ከዋስትና ሰጪ ተቋማት እንዲሰጥ ቢደረግ ለአልሚውም ለገዢውም ጥሩ ይሆናል። 16)ስለ ግንባታ ጥራት ቁጥጥር ምንም ያለው ነገር የለም። 17) ስለ ልኬት ምንም የተባለ ነገር የለውም። በሀገራችን የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ አንዱ አወዛጋቢ የ Net Area, common arae  እና Gross Area ቀመር ነው። ከ ዋና መጠቀሚያው አንጻር የጋራ መጠቀሚያ መጠን ገደብ ሊኖረው ይገባል። ይህ የጋራ መጠቀሚያ ከዋናው መጠቀሚያ ከ20-80% የሚደርስ ሆኖ ገበያ ውስጥ ይታያል። ገደብ እንዲኖረው ቢደረግ። አንዳንዶች ደረጃና የአሳንሰር መዘዋወሪያውን የውሃ ማማዎችን ሳይቀር አስልተው ይጨምራሉ ይህም ገደብ እንዲኖረው ሊደረግ ይገባል። 18)በውጭ ምንዛሪ ስሌት ስለሚደረግ የግብይት ውልስ ምን ታስቧል ? ይህም በግልጽ መልክ ሊይዝ ይገባል። 19) ከርክክብ በኋላ ስለሚሰጥ ዋስትናና የዋስትናው የጊዜ ገደብ ዋስትና የሚሰጥባቸው እንከኖችን በተመለከተ ምንም አልተባለም። ብዙ ሃገራት ከ አንድ እስከ ሁለት ዓመታት ለጥቃቅን ለማይታዩ እንከኖች (latent defects) ሲሰጡ ለ መዋቅራዊ እንከኖች  (Structural defects) ከ 5 እስከ10 ዓመታት እንዲሰጥ ያስገድዳሉ። የእኛም ገደብ ይኑረው። 20) አልሚዎች ቀድመው ከፍለው ለሚገዙ ደንበኞቻቸው የፕሮጀክቱን ሂደት በየተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚያሳውቁበት አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት። ብዙሃገራት አልሚዎች ለደንበኞቻቸው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ሂደት የሚያሳውቁበት ድረ ገጽ እንዲኖርና አንዳንዶች በየወሩ ብዙዎች በተ ሶስት ወሩ የደረሰበትን እንዲያሳውቁ (Update) ያስገድዳሉ። 21)በሽያጭ ሰራተኞችና አልሚዎች/ገዢዎች መካከል ስለሚደረግ የእንደራሴነት ስራ እንዲሁን በወኪሎችና በስራቸው የሚሰሩ የሽያጭ ሰራተኞች ስምምነትና የክፍያ ሁኔታ ፣ የክፍያ መጠንና የጊዜ ገደብ መተማመንን የሚፈጥር የውል ስምምነት እንዲኖር ቢደረግ መልካም ነው። ጥቂት የማይባሉ የሽያጭ ወኪሎችና የሽያጭ ሰራተኞች የስሩበትን ሲያጡ ይስተዋላል። 22) ታላላቅ ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ኢንቨስተሮች የተጠቀሰውን የ40% ለአነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የሚሆን ቤት እንዲያቀርቡ መሬት ከማመቻቸት ባሻገር የተለያዩ ማበረታቻዎች ሊቀርብ እንደሚችል ቢገለጽና ቢተገበር። በተለይ ከቀረጥ ነጻ መብቶች። 23) የሪል እስቴት ግመታ ስራ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው አንዳንድ አንቀጾች አለመተማመንን የሚፈጥሩና ለንብረት ገማቾች ነጻነትን የማይሰጡ ናቸው። ግምት ሁሉ ግምት ነውና ልዩነት የሚጠበቅ ነው። ታሳቢ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮችን በሚገባ ዘርዝሮ በየጊዜው መረጃ በማሰባሰብና በማጋራት ለሁሉም የሚያግባባ ነገር መፍጠር ላይ ትኩረት እንዲደረግ ቢደረግ መልካም ነው። 24) በዝግ ሂሳብ የሚገባው ገንዘብ ፕሮጀክቱ እስኪጀመርና ውል እስኪፈረም መሆን ይኖርበታል። ፕሮጀክት ትግበራው ላይ የሚቋቋማው አካል የስራ ድርሻ በየጊዜው በሚደርሰው ሪፖርት መሰረት ገንዘቡ ቀጥታ ለታሰበው ፕሮጀክት መዋሉን ማረጋገጥ ነው የሚጠበቅበት። የሌሎች ሃገራት ልምድ ከገባው ገቢ ውስጥ ከ70% በላይ ቀጥታ ፕሮቃጀክቱ ላይ ማዋሉን ያረጋግጣሉ። የአንዱ ፕሮጀክት ገቢ ለሌላ ፕሮጀክት አለመዋሉን ይከታተላሉ። እያንዳዱ ፕሮጀክት የተለየ የባንክ አካውንት ይኖረዋል። 25) በተለያዩ ተጠያቂ በሚያደርጉ ጉዳዮች የሚጠየቀው አካል ተለይቶ መቀመጥ አለበት። አንዳንድ ሃገራት አልሚ ተቋማትን ብቻ ሲቀጡ አንዳንዶች የስራ መሪዋችን እስከ መቅጣት ይደርሳሉ።
እስኪ የእናንተስ ሀሳብ?? ከደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ገንቢ እና ሪል ስቴት አማካሪ

🔺በስራ ላይ~  ሸጋ ቀን!🤚

የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች🏗 የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣
የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች🏗
የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው። ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው [1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል [2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ [3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት [4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ [5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ [6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት። [7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡-  ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል [8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት [9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል [10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ -   𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦  የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ [11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ  - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦  በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር እነዚህ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በዝርዝር እና በጥልቀት ይዘው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል።

የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content) በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering) ሥራዎች በብዛት የምንጠ
የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content) በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering)  ሥራዎች በብዛት የምንጠቀምባቸው ሦስት የግንባታ ግብአቶች ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር (Cement, Sand/Fine aggregate & Coarse Aggregate) ናቸው። ሲሚንቶ ዋናው ዓላማው የግንባታ ግብአቶች እስር በእርሳቸው ያላቸውን የመጣበቅ/የመጣመር ሂደት ማጠናከር (As binding agent) ሲሆን የአሸዋ ድርሻ የውስጥ ለውስጥ (air voids) መሙላትና ማእከላዊ የሆነ ማጣበቅና ጥንካሬ መስጠትን ማገዝ ነው። የጠጠር ዋናው ድርሻ ደግሞ የኮንክሬት ክፍሎችን ጥንካሬ መስጠት ነው።  አሸዋ (Fine aggregate) ማእከላዊ ወሳኝ ግብአት ተብሎም ይታወቃል። በትላልቅ አውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በተለይ በህንድ እና በቻይና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እና እንደሲሚንቶ የአሸዋ ማጣሪያ ፋብሪካ ጭምር የተገነባለት ግብአት (material) ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የአሽዋ መሰረታዊ የቤተሙከራ  ማረጋገጫ ምዘናዎች ውስጥ ቀላሉ ነገር ግን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የደለል ይዘቱ (silt content) ነው። /ደለል ማለት በጣም የላመ ወይም የደቀቀ ዱቂታማ የአፈር አይነት ነው/። አሸዋ በተቻለ መጠን ምንም የደለል ይዘት አንዳይኖረው ይመከራል። ደለላማ የአፈር መጠን በአሸዋ ውስጥ በብዛት ካለበት አሸዋው ጥቅም ላይ ሲውል የአርማታ ባህርይን ወደ ጭቃማ ጸባይ ይቀይራል ማለት ነው። ደለላማ የአፈር ክፍል አሸዋው ማንኛውንም የቤተሙከራ መስፈርት (laboratory tests) በብቃት እንዳያልፍ ያደርገዋል። አርማታ ጥንካሬ እንዳይኖረው እና ልስን በቀላሉ እንዲፈራርስ የሚያደግ ነው። ደቃቅ አፈር/ደለል (silt content) የሚባለው እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ልዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ቢሆንም በ'ASTM, AASHTO, IS እና በሌሎች መመሪያዎች ላይ እንደተጠቆመው በብዛት ከ75 micro-millimeter sieve በታች የሚወርደውን ክፍል ነው። በመሆኑም አሸዋ በውስጡ ከስድስት በመቶ (6%) በላይ ደለላማ አፈር (silt content) እንዲኖረው አይፈቀድም። በግንባታ ቤተሙከራዊ የግብአት መስፈርቶች (Experimental criterion) መሰረት አሸዋ ከ6% በላይ ደቃቅ አፈር አንዳለበት ከታወቀ ሁለት አይነት ርምጃ ይወሰዳል። አንደኛው:- አሸዋውን በአሸዋ ወንፊት መንፋት (sieving) ሲሆን (ሁለተኛው) አሸዋውን አስወግዶ (rejection) ሌላ መስፈርቱን የሚያሟላ አሸዋ መጠቀም ነው። በብዙ የሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ አሸዋ በቁም ወይም በአግዳሚ ወንፊት ሲነፋ የሚስተዋለው ይህንን የደለል ለመቀነስ እና ከአሸዋ ቅርጽ መጠን በላይ (Above determined sieve size of sand) የሆነ ጠጠራማ ክፍልን (aggregated particles) ለመለየት ነው።

❇️ የ2017 የአንደኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት ይህን ይመስላል።

👉ያልተገነባ ቤት /ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው። 🏷ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል። 🚧አዲሱ ረቂቅ አዋጅ እንዴት አገኙት ? @etconp

ድርጅታችን ኢትዮ ያማ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከኮንክሪት (አርማታ )አቅራቢ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት ስለሚፈልግ ኮንክሪት የምታቀርቡ ድርጅቶች በዚ ስልክ አናግሩን /0933599571/ ይደውሉ

የሪል ስቴት አልሚዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንዲያወጡ የሚያስገድድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ
በሪል ስቴት ልማት ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሃብቶች “የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ”እንዲያወጡ የሚያስገድድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ።  አግባብ ባለው አካል፤ የሪል ስቴት ወቅታዊ ዋጋ አመላካች የሆነ “መነሻ እና መድረሻ ጣሪያ” በየጊዜው እንደሚወጣም በአዲሱ የአዋጅ ረቂቁ ተደንግጓል። “የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ” በሚል ርእስ የተዘጋጀው የአዋጅ ረቂቅ፤ በሰባት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን በውስጡ 36 አንቀጾች ይዟል። አዋጁ ከተዘጋጀባቸው ምክንያቶች አንዱ “የቤት ፈላጊዎች በእጥረት እና በገበያ ግልጽነት መጓደል ምክንያት የሚደርስባቸውን ጫና ለመታደግ” መሆኑ በሰነዱ ላይ ተመልክቷል። “የቤት እጥረት የከተሞችን አቅም እና የዜጋውን ኑሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ መሆኑን” የሚጠቅሰው የአዋጅ ረቂቁ፤ በዚህም ምክንያት “በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን ለመደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ”ድንጋጌው መዘጋጀቱን ሰነዱ ያትታል። ዛሬ ሐሙስ መስከረም 30፣ 2017 ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ፤ መንግስት ለሪል ስቴት አልሚዎች “መሬት በስፋት እንዲቀርብላቸው” የሚያደርግበትን የድጋፍ አሰራር አብራርቷል። የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ የሪል ስቴት አልሚዎች የእዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት፤ በአዋጅ ረቂቁ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ነው። የሪል ስቴት አልሚዎች እንደከተሞች ደረጃ “በአንድ ጊዜ “ከ500 እስከ አምስት ሺህ የሚሆኑ ቤቶች የሚገነቡ” ከሆነ እና ከዚህ ውስጥም “40 በመቶ የሚሆነውን” ለዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍል “ተደራሽ” የሚያደርጉ ከሆነ መሬት በስፋት ሊቀርብላቸው እንደሚችል በአዋጅ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።  
ሙሉ ዝርዝር https://ethiopiainsider.com/2024/14332/#
ምንጭ~ Ethiopia Insider

🤚 ሸጋ ምሽት የዛሬ 🔺ቁ10. ጥያቄ:-🚧 ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በመደበኛ የግንባታ ሥራ ውል ሰነድ(Contract document) ውስጥ ለብቻው ተነጥሎ እንደሥራ ተቆጥሮ(As Separately described task) የምናገኘው የትኛውን ሥራ ነው?
Anonymous voting

Share ECWC Research Competition.docx

💥አስደሳች ዜና🏗 በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተግባራዊ ምርምር እና ፈጠራን ለማበረታታት ይፈልጋል።
ለዚህም የ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ECWC) ከሰራተኞች አዳዲስ የምርምር ሀሳቦችን በማስተዋወቅ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ እድገት እና እውቀትን የማጎልበት ፖሊሲውን በማስቀጠል ግልፅ ውድድር እንደሚካሄድ አስታውቋል። የዚህ ማስታወቂያ አላማ የ ECWC ሰራተኞችን የጋራ እውቀትን ማበረታታት ነው ወደተወሰኑ የምርምር ጭብጦች የሚያጠኑ የምርምር ሀሳቦችን እንድታቀርቡ ይጋብዛል።  💫ይህ ጥሪ የኮርፖሬሽኖቻችንን አሠራር ለማሻሻል አዲስ አስተሳሰብን የሚያነሳሳ እና ተግባራዊ መፍትሄዎችን ያበረታታል። ሽልማቶች፡- 1ኛ አሸናፊ፡ 200,000 ብር 2ኛ አሸናፊ፡ 150,000 ብር 3ኛ አሸናፊ፡ 100,000 ብር የምርምር ገጽታዎች፡- 💫የግንባታ ቁሳቁስ 💫የግንባታ ቴክኖሎጂ 💫የግንባታ ዘዴ 💫የግንባታ አስተዳደር 🚧ውሎች እና ሁኔታዎች፡- ብቁነት፡ ይህ ጥሪ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ክፍት ነው። የዳኝነት መስፈርት፡ ወረቀቶች የሚገመገሙት በዋናነት፣ ከጭብጡ አግባብነት፣ የጥናት ጥልቀት፣ የአቀራረብ ግልፅነት እና ተግባራዊ እንድምታዎች በባለሙያዎች ቡድን ነው። የማስረከቢያ መስፈርቶች፡ ወረቀቶች ኦሪጅናል ያልታተሙ መሆን አለባቸው፣ እና ከተጠቀሱት የምርምር ጭብጦች አንዱን የሚያብራራ ለማንኛውም ጆርናል ወይም አሳታሚ መሆን የለበትም፡ የግንባታ ቁሳቁስ፣ የግንባታ ቴክኖሎጂ፣ የግንባታ ዘዴ ወይም የግንባታ አስተዳደር። መብቶች እና ፈቃዶች፡- ወረቀት በማቅረብ ተሳታፊዎች ገንዘቡን ይሰጣሉ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ ይዘቱን አሳትሞ ለፓተንት ወይም ለስራ ማስኬጃነት የመጠቀም መብት አለው።  መስፈርቱን የሚያሟላው ፕሮፖዛል/ወረቀት/ጥናት ሙሉ ወረቀቱን ለማቅረብ ይነገራል። ብቁ አለመሆን፡ የማስረከቢያ መመሪያዎችን የማያሟሉ፣ ከቀነ-ገደቡ በኋላ የሚቀርቡ፣ ወይም የሀሰት ወሬዎችን የሚያሳዩ ወይም የትኛውንም አይነት ታማኝነት የጎደላቸው ወረቀቶች ውድቅ ይሆናሉ። የማስረከቢያ ቀን • የማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ኖቬምበር 5፣ 2024 • ፕሮፖዛሉን ሲያዘጋጁ፣ ከዚህ በታች የተያያዘውን ቅጽ ይጠቀሙ።
📩በኢሜል ያስገቡ፡- projm2021@gmail.com ወይም rkmt2017@gmail.com ይላኩ
• አስቻለው መርሻ፣ ስልክ ቁጥር  +251 912 687699 ወይም • አንሙት ሞላ፣ ስልክ ቁ.  +251 964 063944

🔺ኮንስትራክሽን የምትውዱ እኛን ተቀላቀሉ!
http://t.me/consitesolution 🚧🏗
❤ለሌሎችም ተያያዥ ስራ ላላቸው ባልደረቦቻችሁ አጋሩ! መልካም ቀን!🤚

በርካታ ምክንያቶች በሲቪል ምህንድስና ውስጥ ለጠፍጣፋ ንጣፍ/Flat Slab ውድቀት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋና ምክኒያቶችን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡-
ከመጠን በላይ መጫን/Overloading፡- ስላቡ ከዲዛይን አቅም በላይ የሆነ ጭነት ሲገጥመው ለምሳሌ ከባድ ዕቃዎችን ወይም ከባድ ቁሳቁሶችን ላዩ ላይ ማከማቸት። ደካማ የግንባታ ልምዶች፡- በቂ ያልሆነ የኮንክሪት ድብልቅ-mix ወይም ተገቢ ያልሆነ የማጠናከሪያ-Reinforcement አቀማመጥ ያሉ ጉዳዮች ስላቡን ያዳክማሉ። የጎደለው ዲዛይን፡- እንደ በቂ ያልሆነ ውፍረት ወይም ተገቢ ያልሆነ ጭነት ማከፋፈል ያሉ ጉድለቶች የስላቡን ታዐማኒነት ሊነሱት ይችላሉ። የቁሳቁስ መበላሸት፡- የማጠናከሪያ-Reinforcement ወይም የኬሚካል ጥቃት ኮንክሪት ላይ መበላሸት በጊዜ ሂደት ስላቡን ሊያዳክም ይችላል። የፋውንዴሽን አሰፋፈር፡- የመሠረቱን እኩል አለመስተካከል ስላቡን ከአቅሙ በላይ ሊያስጨንቀው ወንም Stress ሊፈጥርበት ይችላል። የሴይስሚክ እንቅስቃሴ፡- የመሬት መንቀጥቀጦች ወይም የመሬት መንቀጥቀጦች ተለዋዋጭ-dynamic ሸክሞችን ሊጭኑ ይችላሉ፣የሚከሰተዉን ሸክም ስላቡ በበቂ ሁኔታ ካልተቋቋመ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል። የሙቀት ውጤቶች፡ የሙቀት መስፋፋት እና መኮማተር በተለይም ከፍተኛ የሙቀት ልዩነት ባለባቸው ክልሎች በዲዛይኑ ላይ በትክክል ካልተሰራ ወደ መሰባበር-cracks እና ውድቀት ሊመራ ይችላል። Collapse/ውድቀትን ለመከላከል እነዚህን ሁኔታዎች በተገቢው ዲዛይን፣ የግንባታ ጥራት እና የጥገና አሰራር መፍታትን ይጠይቃል።