cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🌸[Ⓡⓐⓗⓜⓘⓘ Ⓣⓤⓑⓔ]🌸

❤ሁሌም ቢሆን ለዲንህ ትልቁን ቦታ ስጥ!! ይህ ቻናል የተለያዩ ኢስላማዊ የሆኑ ሀዲሶች እንዲሁም ታሪኮች እና አዝናኝ አስተማሪ ነገሮች የተካተቱበት ነው። Join&share

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
206
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ታሪኩን የፃፍኩት for the first time selehone just አንድ አንድ ቦታ ግር ሊላቹ ይችላል ለሱም ይቅርታ መጠየቅ ፈልጋለው አስተያየት ካላቹ ደሞ ሀሳብ መስጠት ትችላላቹ
نمایش همه...
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ ሰባት       ╚════•| ✿ |•════╝   "የኔ ልጅ ሁሌም ዱአዬ ወስጥ ትኖራለህ,በሄድክበት ሁሉ አላህ ይከተልህ በሰላም ሂደህ በሰላም ተመለስልኝ "አሚን እማዬ መራርቃኝ፣አንዴ ስታቅፈኝ አንዴ ስትስመኝ አለቅህ አለችኝ የእናት ነገር አያስችል... ጉዞ ወደ ዩኒቨርስቲ እዛ ደርሰን ት/ቤቱን መመልከት ጀመርን ክላሳችንን እና ዶርም'አችንን በቃ ምን ልበላቹ ሙሉ ጊቢውን ዞርን በጣም ደክሞን ስለነበር ከመርየም ጋ ተሰነባብተን ወደየ ዶርም'አችን ገባን ለ fresh ተማሪ ከባድ ቢሆንም ማይለመድ ነገር የለም ደሞም ጥሩ ጥሩ ጉዋደኞችን አፍርቻለው  áŠĽáŠ” እና መርየም ብዙ መከራ አይተንበታል እኔን የሚወዱኝ ሴቶች ነበሩ እሷንም የሚያስቸግሯት ወንዶች አይጠፋም በሁለታችን መሀል ገብተው ለመለየት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ነገር ግን እኔ እና እሷን ሊያለያዩን አልቻሉም እንደውም ይበልጥ እንድንጠነክር አደረጉን ከአህመድ ጋ አልፎ አልፎ እንደዋወላለን እኔ እና መርየም በአንድ የትምህርት ዘርፍ ነው ምናጠናው(ምንማረው)ሁለታችንም ዶክተር ነን ከኡሚ ጋ ሁሌ ነው ምንደዋወለው ድምጿን ሳልሰማ አላድርም ከአባቢም ጋ እንደዋወላለን ከሰባት አመት በዃላ ዛሬ የመመረቂያ ቀናችን ነው አልሃምዱሊላህ በዚህ ዩኒቨርስቲ ስንት ችግር አይቼበታለው ያ መከራ አልፎ ዛሬ ደረሰ በጣም ነው ደስ ያለኝ ኡሚን ክረምት ላይ ሂጄ ባገኛትም በጣም ናፍቃኝ ነበር ቤታችን የመመረቄን ምክንያት አስመልክቶ ድግስ ተደገሰ አባቢ:-አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ በመጀመሪያ ጥሪዬን አክብራቹ ስለመጣቹ አመሰግናለው ያው እንደምታውቁት ዛሬ የልጄ ምርቃትን አስመልክቶ ለልጄ የማበረክትለት ስጦታ አለኝ የኔ ቆንጆ ልጅ ደስታዬ ወደር የለውም እንደምታኮራኝ አልጠራጠርም ነበር በጣም ወድሀለው አላህን ሁሌ አመሰግነዋለሁ አንተን የመሰለ ልጅ ስለሰጠኝ።አህመድ አይኑን ሸፍንልኝ በጣም ደስ ከማለቴ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ኡሚን ሳያት በደስታ ብዛት ታለቅሳለች አህመድ ትዛዙን ለመፈፀም አይኔን ሊያስረኝ መጣ "አትፍራ እሺ ገደል አይደለም ምንከትህ አሀሀሀ "ልቤ በሀይል የመታ ነው አህመድ "ጠጋ በል ልሰርህ አይኔን አሰረና እጄን ይዞኝ ሄደ ስጦታው ቦታ ደረስን መሰለኝ ቆመ "አሁን አይንህን መግለጥ ትችላለህ ያየሁትን ማመን አቃተኝ በጣም የምወደውን መኪና ነበር የሸለመኝ አልቻልኩም አለቀስኩ ሂጄ አባዬን አቀፍኩት አህመድ:-አረ አንተ ሜካፕህ እንዳይለቅ፣ደሞ በደስታ ቀን የምን እልቅሻ ነው ሁሉም ሳቁ የተዘጋጀ ኬክ ነበር አብረን ከአህመድ ጋ ቆረስን ውይ ረስቼው አህመድም ተመርቆ ኢንጂነር ሁኗል አልሃምዱሊላህ እዚህ ላደረሰን ጌታ.. ለእማዬ ሾለ መርየምም ነገርኳት ቤቱን በእልልቷ ቀወጠችው "አረ እማዬ ምን ሁነሻል ድምፅሽን ቀንሺ "ደስ ብሎኝ እኮ ነው የኔ ልጅ በቃ ከአባትህ ጋ እንመካከርበታለን መርየምም ለቤተሰቦቻ ተናግራ ልክ እንደኔው ተብላለች ሁለታችንም ተጨንቀናል ይፈቅዱልን ይሆን! ለሰላት ከእንቅልፍ ተነስቼ ሱብሂ ሰግጄ ትንሽ ቁርአን ቀርቼ ዱአ አደረኩና እዛው መስገጃ ላይ ጋደም አልኩ ኡሚ መታ ቀስቅሳኝ አባቢ እንደሚፈልገኝ ነገረቺኝ እንደነገረቺው ወዲያው ገባኝ ውስጤ በጣም ፈራ። ልብሴን ቀይሬ ወደ ታች ወረድኩ ሳሎን ኡሚና አባቢ አንድ ላይ ቁጭ ብለው ያዩኛል አባቢ ተኮሳትሯል ያአላህ ፈጠንኩ እንዴ ለትዳር! ሊከለክለኝ ይሆን ውስጤ ተጨነቀህ "የኔ ልጅ ና ቁጭ በል እንጂ ሂጄ ኡሚ አጠገብ ተቀመጥኩ "እናትህ ሁሉን ነገር ነገረቺኝ እስቲ ሾለ ልጅቷ ንገረኝ "ሁሉንም ነገር ነገርኩት ከዛ ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ "አልሃምዱሊላህ እኔ ባንተ አንድ ቀን አዝኜ አላውቅም ልጅ ለመውለድ ብዙ ጊዜ ተቸግረን ነበር ሁሌ ዱአ እናደርጋለን ልጅ እንዲሰጠኝ አላህም አላሳፈረንም አንተን የመሰለ ልጅ ሰጠን አንተ ለኔ አንድ ልጅ ብትሆንም አላህ ብዙ ልጆችን እንደሰጠኝ እስኪመስለኝ ድረስ አሳይቶኛል አሁን ደሞ አንተ አድገህልኝ የልጅ ልጅ ልታሳየኝ መንገድ እየገባህ ነው ማሻአላህ በኔ በኩል ፍቃደኛ ነኝ ልጄ አላህ ሁሌም ደስተኛ ያድርግህ "ማመን አቃተኝ ያአላህ መርየምን እንዳገባ ፈቀደልኝ! አባቢ የምርህን ነው ፈቀድክልኝ "አሀሀሀ አው ልጄ ፈቅጄልሀለው ቆምኩኝ ማደርገው ነገር ጠፋኝ መልሼ ተቀመጥኩ አባዬን ሂጄ አቀፍኩት። ስልኬ ጠራ መርየም ነበረች ይህ ደስታዬ እንዳይጨልምብኝ በጣም ተጨነኩህ ማንሳትም ፈራው እንዴትም ራሴን ተቆጣጥሬ አነሳሁት "ሀሎ "አሚር ዝም አለች በቃ አልተፈቀደላትም ነው ብዬ ደስታዬ ወደ ሀዘን ተቀየረ "ሀሎ አይሰማም አሚር "ይሰማል መርየም "ምነግርህን ነገር አታምንም ለነገሩ እኔም ማመን ከብዶኛል "ወይኔ ጉዴ መርየም አታስጨንቂኝ በአላህ ንገሪኝ "አባዬ እና ማሚ ፍቃደኛ ሁኗል በቃ ሽማግሌ ላክ ስልኩን ሳልዘጋው ቤቱን ባንድ እግር አቆምኩት እማዬን ጨመኳት ማለት ይቀላል እሺ እንደተባለች ነገርኳቸው ወዲያው ሽማግሌ ተላከ :-ከወር በዃላ❤ የሰርጋችን ድባብ ተጀምሯል እናቶቻችን በስራ ተጠምደዋል ወጣቶቹ ደሞ በመንዙማ አድምቀውታል መርየምን የግሌ ላረጋት ነው በቃ ህልም የመሰለኝ ነው የመጀመሪያ ሚዜ አህመድ ሁለተኛው ደሞ ሰሚር ሌሎቹ cousin'ኖች ናቸው ልብሴን አለባበሱኝ በጣም አሳምረውኛል፡መርየምን እስከማያት በጣም ጓጉቻለው ሁሉም ነገር ተዘገጃጅቷል ጉዞ ወደነ መርየም ቤት እዛ ደርሰን ወደ ቤታቸው በመንዙማ አጅበውን ገባን እንደ ወተት ነጭ የሆነ ትልቅ ቬሎ ለብሳ ፊቷ ተሸፍኗል እንባዬ መጣ ወደሷ መቅረብ ከበደኝ ልቤ ፈራ እንደምንም ወደሷ ተጠጋሁኝ የተሸፈነው ፊቷን ከፈትኩኝ አልቻልኩም አለቀስኩ ግንባሯን ስሜያት ይዣት ወጣሁ አህመድ ወደኔ ጠጋ አለና ከመርየም ሚዜዎች አንዷን አሳይቶኝ "ይቺን እንዴት አየሀት ለኔ ምትሆን ሚስት አገኘው ጠብቅ በቅርብ የኔንም ሰርግ ትበላለህ "አሀሀሀ ኢንሻአላህ... አልሃምዱሊላህ እኔ እና መርየም በፍቅር መኖር ከጀመርን ሁለት አመት ሞላን አንድ ቆንጅዬ ልጅም አላህ ሰቶናል መርየም የልጄ እናት ለኔ ነብሴ ናት ከማንም በላይ ታስፈልገኛለች አህመድም በቅርብ አግብቶ ሚስቱ እርጉዝ ነች በቃ ህይወት የህልም ኑሮ የምኖር እንዲመስለኝ አድርጎኛል... በርግጥም ከችግር በዃላ ምቾት አለ! ተ.ፈ.ፀ.መ @kehalalBetoch #share
نمایش همه...
💯 2👍 1
Repost from N/a
00:20
Video unavailableShow in Telegram
ከላሙላህ in beauty sound
نمایش همه...
8.97 KB
❤‍🔥 3
 "የህልም ኑሮ" የመጨረሻ ክፍል ኢንሻአላህ ነገ ይለቀቃል
نمایش همه...
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ ስድስት       ╚════•| ✿ |•════╝   ዞር ብዬ ስመለከት መርየም ነበረች ለምን እንደሆነ አላውቅም ደስ አለኝ "እእ እኔ አንቺን የማየቱ አቅም የለኝም በቃ ምን እንደምልሽ አላውቅም ለኔ ጥሩ አስበሽ ያደረግሺውን ነገር በመጥፎ ተረዳሁት እኔ ላንቺ ምገባ ሰው አይደለሁም በስራዬ በጣም አፍሬያለው ትንሽም ቢሆን ለኔ የቀረ ስሜት ካለሽ ይቅርታ አድርጊሊኝ! "ትናንት ያደረከው ነገር ልክ ባይሆንም እንዲህ ታደርጋላቹ ብለ ስለማታስብ ተናደህ ይሆናል በሚል ወስጄዋለው እና በቃ ይቅርታ ከማድረግ ውጪ ምን አማራጭ አለኝ "የምርሽን ነው መርየም! በጣም ደስ አለኝ ግን አህመድን ላገኘው ስላልቻልኩኝ ትንሽ ተጨነኩ "ምነው አሚር ምን ሆንክ! "ይሄ ሁሉ ጊዜ ከሱ ርቄ ብቻዬን ሁኜ ያሳለፍኩት ጊዜያቶች ከባድ ነበሩ በርግጥ እሱን የዘጋሁት ከአንቺ ጋ አብራቹ ስለሆናቹ አይደለም በቃ ለሹ አልገባውም ብዬ በማሰብ ነው። እንደዛ የሚመክረኝ ለኔ ጥሩ የሚያስብ ወንድሜን በራሴ ጥፋት አጣሁት እኔ ለሹ ምንም አድርጌለት አላውቅም ግን በቃ ናፍቆኛል "እኔም በጣም ናፍቀኸኛል ወንድሜ በጣም ደስ አለኝ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ለካ ከሁዋላ ሁኖ የማወራውን ነገር የሰማ ነበር ዞር ብዬ ተመለከትኩት የሱም አይኖች እንባ አቀርቅሮዋል ወደ ልሴ ስቤው አቀፍኩት ይቅርታ አድርግልኝ ወንድሜ "በሁለት ወንድማማቾች መሀል የምን ይቅርታ ነው መርየም ሁኔታችንን እየተመለከተች ነበር በጣም ደስ እንዳላት ታስታውቃለች "አረ በቃቹ እኔን እረሳችሁኝ እኮ ነው ወይስ አታስፈልጊም ነው "አረ በጣም ነው ምታስፈልጊን ደሞ የወደፊት ሚስቴን እንዴት ረሳታለው "ቀስ በል ከኔ ጋ እኮ ገና ፍቺ አላደረገችም የተሳሳቅን ወደየ ክፍላችን ገባን ከመርየም ጋ ቁጭ ብለን ተማርን ለኔ ልዩ ቀን ነበር ብቻ እረፍት ሰአት ደርሶ እኔ,መርየም እና አህመድ አንድ ላይ ቁጭ ብለን እያወራን ድንገት ዞር ስል ሀናንን አየኋት በጣም እንደተናደደች ያስታውቃል በመናደዷ ደስ ብሎኛልም ከፍቶኛልም ደስ ያለኝ ከመርየም ጋ ተጣርቀን በማየቷ ነው የከፋኝ ደሞ ጉዋደኛዋን እንዲ በማድረጌ ነው አንገቴን ደፋው ሁኔታዬን መርየም ስትከታተል ነበር "አሙ ደና ነህ? "እ ምንድነው ያልሺው 'አሙ' ስትዩ ሰማው እኔ አላምንም አህመድ ሰማሀት አሙ ብላ አቆላመጠችኝ እኮ "ወይ ወንድሜ አበደ መሰለኝ ምን ሁነሀል ከቀልብህ ሁን እንጂ ገና ለገና አቆላመጠችኝ ብለህ እንዲ ትዘላለህ ላንተ አሙ መባል ከመች ጀምሮ ነው ብርቅ የሆነብህ! እንዲ እብድ እስክትሆን ሚያስደስትህ በል በል በዚህ ሁኔታ ከቀጠልክ ሆስፒታል ለሆስፒታል ታሯርጠናለህ "አንተ ምንድነው ባሌ ላይ ምታሟርተው "አረ መርየም ተይ ዛሬ ወንድሜን ልትገይብኝ ነው ደሞ ሀይማኖታቹን እንዳረሱ እንጂ ያለ ኒካ አትነካካ ይህ ማለት ደሞ ምላስንም ያካትታል ስለዚህ ቆጠብ በሉ ደሞ ፈተና የደረሰ ስለሆነ ተቀጣጥረን ማጥናት አለብን እኔ እና መርየም በሀሳቡ ተስማማን እንዲህ እንዲህ እያለ የፈተናችን ቀን በጣም ተቃረበ እኛም ማጥናታችንን ተያይዘነዋል ሁላችንም እንደምናልፍ ራሳችንን አሳምነነዋል ቀሪውን ለአላህ ብለናል ማይደርስ ቀን የለምና ፈተናችን ደርሶ ተፈተንን ያን ያህል ሚከብድ አልነበረም። "መርየም አንድ ዩኒቨርስቲ ቢደርሰን እንዴት ደስ እንደሚለኝ የሁል ጊዜ ዱአዬ ነው "ኢንሻአላህ ይደርሰናል አንተ ደሞ ምን አስቸኮለህ መጀመሪያ ውጤታችን ይምጣ እስቲ አሀሀሀ "ያለኔ አስችሎዋቹ እንዴት ቁጭ አላቹ ወይ ደሞ ለኔም የምትሆን ሚስት ፈልጉልኝ እኔ እና መርየም ሳቅንበት ከወራት በሃላ ውጤታችን መጣ የሚገርመው ተከታታይ ነጥብ ነበር ያመጣነው ከፍተኛ ያመጣሁት እኔ ነበርኩኝ ደሞ ዱአዬ የሰራ ይመስላል እኔ እና መርየም አንድ ዩኒቨርስቲ ነው የደረሰን እዚው አ/አ, አህመድ ግን ድሬዳዋ ነው ከኛ በመለየቱ በጣም አዝነናል ቢሆንም መታገስ አለብን አባቢ ስላለፍኩኝ እጅግ በጣም ደስ ብሎታል ኡሚም እንደዛው። ልብሶቼን እያዘጋጀው ነው ከነ ኡሚ መለየቱ በጣም ከብዶኛል ኡሚም ቢሆን እንደማያስችላት አውቃለው ... ይቀጥላል @kehalalBetoch #share  
نمایش همه...
👍 1❤‍🔥 1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ አምስት       ╚════•| ✿ |•════╝   መርየም:-አሚር ላወራህ ፈልጌ ነበር "ምነው መርየም ከአህመድ ጋ ሰላም አይደላችሁም እንዴ? "ሰላም ነን "እና ምንድነው ደሞ ለምንድነው ምታለቅሺው "አሚር አልቻልኩም "ምንድነው ያልቻልሽው መርየም ግልፅ አድርጊሊኝ እንጂ አህመድ መጣ ግራ ገባኝ ምን ተፈጥሮ ነው "አሚር በቃ ያኔ አህመድን ነው ማፈቅረው ያልኩህ ውሸቴን ነው ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ተነሳው አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው እና ማንን ነው ምታፈቅሪው ወይስ ከኔ ለመለየት የፈጠርሽው ነገር ነው! "አሚር እኔ አንተን ነው ማፈቅርህ "ምን! አሀሀሀ መርየም ምታወሪውን እያወቅሽ ነው አህመድ አንድ ነገር በል እንጂ ምታወራውን እየሰማህ ነው አይደል? "እውነቱን ነው የነገረችህ አሚር,የምታፈቅረው እኔን ሳይሆን አንተን ነው አንተ እንድታስተካክል ወደ ቀልብህ እንድትመለስ ያቀድነው ነገር ነው። መርየም ይሄ ሁሉ ጊዜ ባንተ ፍቅር ተጎታለች እኔም እስካሁን ዘግተኸኝ ያሳለፍኳቸው ጊዜ ከባድ ነበሩ።በቃ ወደ ቀድሞ እንመለስ "አረ ባካቹ ይኸው ጭብጨባ ያስፈልጋቹሀል ፐ በጣም ጥሩ እቅድ ነው ባክህ ይሄ ሁሉ ጨዋታ ለምን አስፈለገ እ!እንደምታፈቅሪኝ ነግረሺኝ መስተካከል አልችልም ነበር? ይሄ ሁሉ ጊዜ የት ነበርሽ !እንደዛ በፍቅርሽ ስሰቃይ ቀን እና ማታ ሳለቅስ በእንባዬ ብዛት ትራሴ ረጥቦ ሳድር የት ነበርሽ አሁንስ ለምን መጣሽ ተስተካክሏል ብለሽ ስላመንሽ በጣም ታሳፍራላቹ አሁን ሂዱልኝ መርየም:-እባክህ ይቅርታ አድርግልን ሂዱልኝ ብዬ ጨውኩባቸው መርየም ደንግጣ እያለቀሰች ሄደች አህመድም ተከትሏት ሄደ አህመድ:-መርየም ተረጋጊ አሚሬን አውቀዋለሁ ንዴቱ ሲበርድለት ሁኔታዎችን ማሰብ ሲጀምር ይቅር ይለናል አታስቢ የተፈጠረው ነገር ህልም መሰለኝ እንደምንም ራሴን አረጋጋውና ወደ ክፍል ገባሁ ተምረን ስንጨርስ ወደ ቤት ሄድኩኝ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ መርየም ላይ እንደዛ የጨውኩባት,አህመድን እንደዛ ሳመናጭቀው ሳስታውስ በራሴ አፈርኩ ለኔ ብለው ያደረጉት መሆኑ ገባኝ እንደዚ የመስተካከሌ ውጤት እነሱም እንዳሉበት ተረዳው። ከአልጋዬ ተነስቼ ውዱእ አድርጌ ሁለት ረከአ ሰገድኩኝ እጆቼን ወደ ላይ ዘረጋው ያረቢ አንተ ታላቁ ጌታ እኔ ያንተ ባሪያ ነኝ ያላንተ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም ደካማ ነኝ ያረቢ መርየምን ለኔ ካልካት በሀላል መንገድ አድርግልኝ ለኔ ካላልካት ከኔ አርቅልኝ... ራሴን ስላመመኝ ቁርአን ከፍቼ ጋደም አልኩኝ የመግሪብ አዛን ሲል ወደ መስጂድ ሄድኩኝ ጀመአ ሰግደን ኢሻ እስኪያዝን እዛው መስጂድ ቁጭ ብዬ ቁርአን ቀራው ኢሻ አዝኖ ሰግጄ ወደ ቤት ተመለስኩኝ ዛሬ መርየምን አና አህመድን ይቅርታ ለማለት ወስኛለው ክፍል ስገባ መርየምን አጣሁዋት ደነገጥኩኝ ምን ሁና ነው!ወደነ አህመድ ክፍል ሄድኩኝ አህመድንም አጣሁት ያአላህ ምን ተፈጥሮ ነው ደረጃውን ወርጄ እነሱን መፈለግ ጀመርኩኝ "ማንን እየፈለክ ነው የሚል ድምፅ ሰማሁ... ይቀጥላል @kehalalBetoch  
نمایش همه...
👍 6
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ አራት       ╚════•| ✿ |•════╝   ጥላኝ ሄደች እንባዬ ወረደ ምርር ብዬ አለቀስኩ አይሆንም መርየም ይሄማ በጭራሽ አይሆንም ከአህመድ እንዴት ፍቅር ሊዩዝሽ ቻለ!ማስታወስ ጀመርኩ መርየም እና አህመድ አንድ ላይ ቁመው ሲያወሩ እንደዛ ሲተያዩ አህመድ ሴትን ማውራት ሚፈራው ልጅ ከሷ ጋር ቁሞ ሲያወራ ምንም ያለመፍራቱ ቆይ ግን ለምን አምላኬ ምን አልባት እስካሁን በሰራሁት ጥፋት በተጫወኩባቸው ሴቶች ቅጣቴን የቀጣኸኝ ይሆን! የመርየም ቦታ ላይ ቁጭ አልኩና አንገቴን ደፋው   መርየም:-አህመድ "አሚር"... "አሚር ምን ሆነ!? "እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ "ታዲያ ምን አልሺው? "አላፈቅርህም ብዬ በጣም አስከፋሁት "የእውነት ከልቡ ካፈቀረሽ አንቺን ለማግኘት ምንም ነገር ያደርጋል ያኔ አንቺም ከልቡ እንዳፈቀረሽ ትረጃለሽ።አሁን ወደ አሚር መሄድ አለብኝ "አሚር ምነው አሞሀል እንዴ? "አው አሞኛል በመርየም የተነሳ አብጃለው ትምህርቴን መማር እስኪያቅተኝ,ራሴን እስከረሳ ድረስ አፍቅሬያታለው ፍቅሬን ስገልፅላት ምን እንዳለችኝ ታውቃለህ! መናገር ስላቃተኝ ቦርሳዬን ይዤ ከክፍል ወጣሁ መርየም የክፍል መግቢያው ላይ ቁማ ነበር "አታስቢ መርየም እኔን ያለማየት አንቺን ሚያስደስትሽ ከሆነ አጠገብሽ አልደርስም።አህመድን ከፈለግሽ እኔ አናግርልሻለው። ይቅርታ አድርጊሊኝ ላጠፋሁት ጥፋት አንድ እውነታ ግን ልንገርሽ ከልቤ አፈቅርሻለሁ ብያት ጥያት ሄድኩኝ ቤት ከገባው ኡሚ ትጨነቃለች ብዬ ወደ መስጂድ አመራው እዛም ደርሼ ዉዱእ አድርጌ ሁለት ረከአ ሰግጄ እዛው ጋደም አልኩኝ ቁርአን ተከፍቶ ነበር አቤት ሰላሙ ለችግሮቼ መፍትሄ ያገኘው ይመስል ቀለል አለኝ ከዚህ በሃላ ሰላቴን ላላቋርጥ ለልሴ ቃል ገባው ትምህርቴ ላይ ጠንክሬ ተምሬ የኡሚን ደስታ ለማየት,በሴት ልጅ ላይ እንደማልጫወት ቃል ገባው ልክ ከት/ቤት የምንለቀቅበት ሰአት ሲደርስ ወደ ቤት ሄድኩኝ ቤት ገብቼ ኡሚ ታፋዋ ላይ ተኛሁኝ እሷም ደስ ብሏት ፀጉሬን አሸት አሸት እያደረገቺችኝ "ተሻለህ የኔ ልጅ? "አው እማዬ ተሽሎኛል... እንዲ እንዲ እያለ ቀን በቀን ተተክቶ ወራቶች አለፉ የፈተናችን ቀንም ተቃረበ በዲኔ ጠንካራ ሁኛለው በ አንደኛ ሴሚስተር የ15ቀን እረፍቴ ቂርአት ቀርቻለው መስጂድ ሂጄም መስገድ ጥናት ማጥናት ዘወትር ማደርገው ነገር ነው ። Fb ከስልኬ አጥፍቻለው ከዚህ በሃላ ሴት ልጅ ላይ እንደማልጫወት ቃል ገብቻለው ለዚህም ስራዬ አምላኬ ይቅር እንዲለኝ አጥብቄ የለመንኩት ነው መርየምን አሁንም ድረስ ባፈቅራትም የኔ እንዳልሆነች ራሴን አሳምኜዋለሁ።ብቻዬን ት/ቤት እየሄድኩኝ ብቻዬን ወደ ቤት እመለሳለው እማዬ የፀባዬ መቀያየር ቢያስገርማትም ዲኔ ላይ ጠንካራ በመሆኔ ደስተኛ ሁናለች እለተ ሰኞ ከእንቅልፍ ተነስቼ ዪኒፎርሜን ለብሼ ቁርስ ለመብላት ወደ ታች ወረድኩኝ ከእማዬ ጋ አብረን በልተን ተሰናብቻት ወደ ት/ቤት ሄድኩኝ እዛ ስደርስ አህመድ እና መርየም ሲያወሩ ተመለከትኳቸው የኔ ባለመሆና ቢከፋኝም አህመድን የመሰለ ልጅ ስላገኘች ደስተኛ ነኝ ወደ ክፍል ገባሁ ተማሪዎች ይንጫጫሉ ጩኸታቸው ስለረበሸኝ ቦርሳዬን አስቀምጬ የምወዳት ቦታ ሂጄ ተቀመጥኩ... ይቀጥላል @kehalalBetoch #share
نمایش همه...
👍 2🔥 1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ ሶስት       ╚════•| ✿ |•════╝   አህመድ:-መርየም አሚር የት ነው ያለው አይተሺዋል "ቅድም አስተማሪው አስፈቅዶ ወደ ቤት ሂዷል መሰለኝ ደሞ ፊቱ ትክክል አልነበረም ለምን እንደሆነ አላውቅም ጨንቆኛል "አብሽሪ እህቴ ምንም አይሆንም በቃ ቸው ስልክ ተደወለልኝ አህመድ ነበር "ሀሎ አህመድ "ምን ሁነ ነው በጊዜ ወደ ቤት የገባኸው ? "ትንሽ እንደ ራስምታት አሞኝ ነው "በቃ መጣው ቤት ነህ አይደል! "አረ እኔ ደና ነኝ አታካብደው አረፍ ስልበት ይተወኛል "እሺ በቃ አላስጨንቅህም አላህ አፊያ ያድርግህ "አሚን አሚን ስልኩን ዘግቼው ማሰብ ጀመርኩ ቆይ ምን ላደርግ ነው ገና ለገና ለመርየም ፍቅሬን ገልፅላታለው ብዬ ሳስብ ምን ሁኛለው ከዚህ በሃላ ልታየኝ ምትፈልግ ሁላ አይመስለኝም በሀሳብ ተዋጥኩ ድንገት የክፍሌ በር ተንኳኳ "የኔ ልጅ መግባት ችላለው "እንዴ እማዬ ከመች ጀምሮ ነው የኔን ፍቃድ መጠየቅ የጀመርሺው!? "ተኝተህ ይሆናል ብዬ ነዋ ያዝ ይቺን ሾርባ እንደምትወደው አድርጌ ነው የሰራሁት ሳይቀዘቅዝብህ ጠጣ ከዛ አረፍ በልበት ይተውሀል "ኡሚዬ ለምን ትጨነቂያለሽ እኔ እኮ ደና ነኝ "አይ የኔ ልጅ የሰሞኑ ሁኔታህ ትክክል አይደለም ራስህን አስተውለህ ታውቃለህ አሁን ፈገግ ትልና ወዲያው ትናደዳለህ ትቆዝማለህ ለምን የሆንከውን አትነግረኝም "ኡሚ ምንም አልሆንኩም አሁን መተኛት ፈልጋለው "እሺ በቃ ተኛ ኡሚ እንዳለቺው ፀባዬ ተቀይሯል እንዴ ወይ አሚር አበድኩ መሰለኝ ሾርባውን ጠጥቼ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩኝ እንቅልፍ ወሰደኝ። እንደተለመደው ጡዋት ተነስቼ ዩኒፎርም ለብሼ ከቤት ወጣሁ ት/ቤት መሄድ በጣም እያስጠለኝ ነው ከአህመድ ጋ ተገናኝተን ወደ ት/ቤት ሄድን ወደ ክፍል ስገባ መርየምን ሳያት ፊቷን አዞረቺብኝ በእረፍት ስአት አወራታለው ብዬ ቦታዬ ላይ ተቀመጥኩ አስተማሪው ገብቶ ማስተማር ጀመረ ትምህርቴን በትኩረት መማር ጀመርኩ። አስተማሪው ጥያቄ ጠየቀህ እኔ እና መርየም እጃችንን አወጣን አስተማሪው እድሉን ለኔ ሰጠኝ እኔም ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መለስኩ (ጎበዝ ልጅ)ብሎኝ ማስተማሩን ቀጠለ መርየም ዞር ብላ አይታኝ ወደ አስተማሪው ዞረች ጎበዝ ተማሪ አልመሰልኳትም ነበር መሰለኝ ብቻ ተምረን ጨርሰን ማይደርስ ነገር የለምና የእረፍት ስአት ደረሰ መርም ከክፍል መውጣት ማትፈልገው ልጅ ዛሬ ምን እንደነካት አላውቅም ልትወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሯ ተነሳች "መርየም አንዴ እናውራ? "ምንም ምናወራው ነገር የለም ያልከውን ሙሉ ሰምቻለው ምትጠላኝ ከሆነ እኮ ማስመሰል አያስፈልግም ነበር "እንደዛ ያልኩበት ምክንያት ካለኝስ "የምን ምክንያት ነው እ!ከዚህ በሃላ ላይህ አልፈልግም "አው ብዙ ሴቶችን ጊዜ ለማሳለፍ ቀሪቤያቸዋለው ከአንዳቸውም ግን እውነተኛ ፍቅር አላገኘውባቸውም አንቺ ግን ከነሱ ተለየሽብኝ መርየም እኔ አፍቅሬሻለሁ ካንቺ ተለይቼ መኖር አልችልም እባክሽ አንድ እድል ስጪኝና ሁሉንም ነገር ልንገርሽ "ምንም ምሰማህ ነገር የለም ምክንያቱም እኔ አላፈቅርህም ለምን እንደሆነ ታውቃለህ አስመሳይና ውሸታም ስለሆንክ እውነቱን ልንገር "ለመስማት እየጓጓው የምን እውነት "ከጉዋደኛህ ፍቅር ይዞኛል በቃ እኔ አህመድን ነው ማፈቅረው... ይቀጥላል @kehalalBetoch #share  
نمایش همه...
👍 1😱 1👌 1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......     የህልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒         @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ ሁለት       ╚════•| ✿ |•════╝   "እሱን አንተን ልጠይቅህ እንጂ ግን እኮ ልክ ናት አሚርን አፍቅሬዋለው "ምን!? "አው አፍቅሬዋለው ከነሱ መሀል ገብቼ ግን ላጣላቸው አልፈልግም አሚር የሚወደው ሀናንን ነው "መርየም እያለቀሽ እኮ ነው በቃ ተረጋጊና ቁጭ ብለን እናውራ "ብቻዬን መሆን ነው ምፈልገው ከሀናን ጋ አውርተን ከጨረስ በሃላ ወደ ክፍል መሄድ ጀመርኩ አህመድ የክላሳቸውን በር ተደግፎ ቁሟል የተናደደም ይመስላል "አህመድ ምን ሁነ ነው የተፈጠረ ነገር አለ? "አሀሀሀ የእውነት የጠየከኝ ነው "አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገህ ነው "ይሄንን ካንተ አልጠብቅም ነበር "የምትለው ነገር ለሰሚው ግራ ነው ለምን በግልፅ አትናገርም "እንጊዳውስ ግልፅ ላርግልህ ቅድም መርየምን እንደምታፈቅራት ነግረኸኝ አልነበር! "አው ነግሬህ ነበር እና ምንድነው "ድሮም አንተን ማመኔ ማፍቀር የሚችል ልብ የለህም "አህመድ ትግስቴን እያስጨረስከኝ ነው መናገር የፈለከውን በቀጥታ ንገረኝ "ለሀናን የነገርካትን ሁሉ ነገር ነዋ ምን እንዳልካትም ማወቅ ፈለክ እንዴ! ያቺ እባብ አንተ ስለመርየም ጠይቃህ የነገርካትን በሙሉ ሪከርድ አድርጋ ለመርየም አሰምታታለች "ምንድነው ምትለው ወይኔ መርየም ምን የተሰማት ይሁን ግን እኮ እኔ ይሄን አስቤ አልነበረም "እና ምን አስበህ ነበር እ "በቃ አትጩህብኝ ምን ማድረግ ነበረብኝ የማፈቅራት ልጅ ናት ብዬ ነው መናገር የነበረብኝ ጥሎኝ ሄደ,ወይኔ አሚሬ ምን አይነት ጣጣ ውስጥ ነው የገባኸው ከፎቁ ላይ ሁኜ ወደ ታች ስመለከት ሀናን ከወንድ ልጅ ጋ ስትተቃቀፍ አዬሁዋት በጣም ተናድጄ ወደ ታች ወረዱኩ ልክ እኔን ስታየኝ ለልጁ ምን እንዳለቺው አላውቅም ሄደ "አንቺ እባብ ምንድነው ያደረግሺው ምን አይነት ሰይጣን ብትሆኚ ነው አሁን ከኔጋ አውርተሽ እንደጨረሽ ከሌላ ወንድ ጋ ምትተቃቀፊው! ከሱም ብሶ ያወራነውን ሪከርድ አድርገሽ ለመርየም ያሰማሻት ምን ባደርግሽ ነው ተናገሪ "ከአንተም ብሶ ትጮሀለህ አሀሀሀ ፐ ያንተ ነገር ሲነካብህ እንዴት እንደሚያደርግህ ማየት ቻልኩኝ ብዙ አትናደድ እዚጋ ድፍት ካልክ ሚያነሳህም ያለ አይመስለኝም ምክንያቱም መርየምም ሆነች አህመድ ሊያዩህ አይፈልጉም "ቆይ አንቺ ማነሽ ምንድነው ከኔ ምፈልጊው! "ካንተ ምን ይፈለጋል አንተ በሌሎች ሴቶች እንደምታደርገው ነው ያደረኩት ነው ወይስ ባንተ ላይ ሲደርስ በጣም ተናደድክ መርየምን እንደምታፈቅራት አውቃለው ሆን ብዬ ነው ድምፅህን ሪከርድ አድርጌ ያሰማሁዋት ትዝ ትልሀለች ሱመያ ወንድን ቀና ብላ ማታይ በትምህርቷ ጎበዝ የነበረች ልጅ ድንገት አንተ የውሸት ፍቅርህን ይዘህ መጥተህ በፍቅር ቃላቶችህ አታለሀት ልክ እንዳፈቀረችህ ስታውቅ የተውካት ልክ እንደቆሻሻ የጣልካት አሁን አብዳ ትምህርቷን ትታ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባት ነው ምትኖረው።እኔም የጉዋደኛዬ እንዲ መሆን አላስቻለኝም ከስልኳ ቁጥርህን ወስጄ በFb ማውራት ጀመርኩኝ እንድታፈቅረኝ አድርጌህ ልርቅህ ነበር አሳቤ ግን የምታፈቅራትን ልጅ እንዳታገኛት አደረኩ መርየም ምንም ብትላት ምን አታምንህም ያሳዝናል ያኔ ጉዋደኛዬን አልፈልግሽም ስትላት እንደዚህ ነበር የሆነችው አንተ ግን ፈጣሪ ልሹ ይቅር ይልሀል? በዚህ አስተሳሰብህ ሴት ልጅ ጋ እንዳደርስ ጨርሻለው ቸው እሷም ጥላኝ ሄደች ራሴን ጠላሁት ምን ያህል ልሾ ወዳድ እንደሆንኩኝ ገባኝ እንደምንም ወደ ክፍል ሄድኩኝ አስተማሪ ገብቶ ነበር አንኳኳው "የት ነበርክ እስካሁን? "ትንሽ አሞኝ ነው ፍቃድህ ከሆነ ቦርሳዬን ልውሰድ "እሺ ቶሎ ወስደህ ውጣ ቦርሳዬን ለመውሰድ ወደ ክፍል ገባው መርየምን ሳያት ያ የሚያማምሩ አይኖቻ ቀልተዋሉ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ቦርሳዬን ይዤ ወደ ቤት ሄድኩኝ "የኔ ልጅ ምነው በጊዜ መጣህ ትምህርት የለም ነው ፊትህ ደሞ ምንድነው የጠቋቀረው አሞሀል አይደል በል ቶሎ ልብስህን ቀይር ወደ ሀኪም ቤት እንሄዳለን "የምን ሀኪም ቤት ነው ኡሚ!ደና ነኝ ስተኛበት ይተወኛል ወደ ክፍሌ ገባሁ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ መሰለኝ ምን እንደማስብ ሁላ ላውቅ አልቻልኩም እባዬ ሳላስበው መውረድ ጀመረ ይቺ የተረገመች ልጅ መርየምእንድትጠላኝ አደረገች ቆይ ምን ባደርግ ነው ሚሻለኝ መርየምን ማውራት አለብኝ አው ነገ ት/ቤት ላወራት ይገባል... ይቀጥላል @kehalalBetoch  
نمایش همه...
👍 1😱 1
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗           .......    á‹¨áˆ…ልም ኑሮ  ......              ✎ ፀሐፊ፦ ራህሚ ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒        @kehalalbetoch የተዘጋጀ ┖━─━─━─━─━─━─━─━┚       ╔════•| ✿ |•════╗              #ክፍል_ አስራ አንድ       ╚════•| ✿ |•════╝   "ፍቅሬ እኔ ትምህርት ቤቱን ሙሉ ስፈልግህ አንተ እዚ ብቻህን ምን ትሰራለህ ኦ ይቅርታ አላየሁሽም ነበር ሀናን እባላለው የአሚር ፍቅረኛ ነኝ መርየምን ቀና ብዬ ሳያት የተናደደች ትመስላለች "በቃ እኔ አልረብሻቹ ደሞ ደብተሬንም ስጠኝ ከሌላ ሰው ተውሼ ፅፋለው አህመድ:-መርየም አንቺ መርየም ቁሚ እንጂ ምንድነው እንዲህ መበርገግ መርየም:-አይ ምንም እንዲው ዝም ብዬ ነው ግን እንዴት ፍቅረኛ እንዳለው አልነገረኝም አንተስ ቢሆን ለምን ደበከኝ "ሀናን ማለት ልክ እንደሌሎች ሴቶች ለጊዜያዊ እንደሚፈልጋቸው እሷንም እንደዛ በማሰብ ነበር የቀረባት ግን "እ ግን ምን? "አሚር ዛሬ ወደ ትምህርት ቤት ስንመጣ እንደሚያፈቅርሽ ነገረኝ "ልክ እንደሌሎች ሴቶች ማለት ነው! " No No የአሁኑ ከምሩን ይመስላል እንደዚ ሲሆን አይቼው አላውቅም "ቆይ እቅዳችንስ! "እሱ እንዳለ ነው ሚሆነው አልተቀየረም የሚወዱትን ማጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንዲሰማው ማድረግ አለብን በቃ አሁን ልሂድ እኔ እና አንቺ ከታየን... ብሎ ሳይጨርስ እነ አሚር ከክፍል ወጡ "ወይኔ መርየም ያልኩት ነገር አልቀረም በቃ ቸው አህመድ ከመርየም ጋ ቁሞ ሳየው ግራ ገባኝ መርየም ገለማምጣኝ ወደ ክፍል ገባች። ከሀናን ጋር ወደ ታች መውረድ ጀመርን "ፍቅሬ ቅድም ክፍል ውስጥ አብራህ የነበረቺው ማናት? "መርየም ትባላለች,የክፍሌ ልጅ ናት እንደምትወደኝ እየነገረቺኝ ነበር "እና! አንተ ምን አልካት "አረ ቀስ በይ እንዴ,ታውቆሻል ጨውሽ እኮ ደሞ ፍቅረኛ አለኝ ከዚህ በሃላ ላይሽ አልፈልግም እንዳልኳት አንቺ መጣሽ "ፍቅሬ መጣሁ አንዴ እዚው ጠብቀኝ "ወዴት ልትሄጂ ነው? "መጣሁ እዚ ነኝ "እሺ ጠብቅሻለው ሀናን:-ምነው ብቻሽን ክፍል ውስጥ ቁጭ አልሽ,ወይስ ባሌን የጠበቅሺው ነው! እንደምትወጂው ያስታውቅብሻል ግን ምን ዋጋ አለው የምትወጂው ሰው ሌላ የሚወዳት ሴት አለች እሷም እኔ ነኝ ስለዚህ ከዚህ በሃላ ከፍቅሬ ጋ ላይሽ አልፈልግም አዝኜልሽ ነው እንጂ እውነቱን ንገሪኝ ካልሽ አሚር አይፈልግሽም እንደሚጠላሽ ነግሮኛል "አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? "ይሄን ስትሰሚ በደንብ ይገባሻል ቆይ ላሰማሽ ቅድም ታች አብረን ስንወርድ የነገረኝን ሪከርድ አድርጌዋለው "በቃ ዚጊሊኝ ደሞ ይሄን ማድረግ አይጠበቅብሽም ነበር እኔ እና አሚር ምንም ግንኙነት የለንም አታስቢ አጠገቡም አልደርስም "አረ ቀስ እያልሽ ሂጂ እንዳትወድቂ,ጨዋታው ተጀመረ ውይ አሚር ለካ የጠበከኝ ነው አሀሀሀ "ቆየው እንዴ ፍቅር "አይ ብዙም አልቆየሽም "ይቅርታ እሺ ውዴ እ ምን ላይ ነበር ያቆምነው መርየም:-አህመድ አንዴ ላናግርህ "ምን ሆንሽ ችግር አለ "አው ችግር አለ ቅድም አሚር አፍቅሮሻል እያልክ አልነበር ውሸታም ነህ "መርየም ምንድነው ምትዪው "ሀናን ከደቂቃዎች በፊት መጥታ አውርታኝ ነበር "እና ምን ተፈጠረ "አሚርን እኔ ወድጄው እንደቀረብኩት እሱ እንደማይፈልገኝ ሲያወራ ሪከርድ አድርጋ አሰማቺኝ "ምን!ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል "እሱን አንተን ልጠይቅህ እንጂ ግን እኮ ልክ ናት አሚርን አፍቅ... ይቀጥላል @kehalalBetoch  
نمایش همه...
😱 2
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.