cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፍቅር በፍቅር❤️❤️😍

እዚህ chanal ላይ ቀልዶችን ምክሮችን አስገራሚ እውነታዎች። ዝም ብለው መኮምኮም ብቻ ነው ከዛ በተጨማሪ የtik tok እና fb. Comment ቶችን ያገኛሉ ለማስታወቂያ ስራ። @Mamila7 +251945481753 mamila አስታየት ካሎት @fkrbefkrebot

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
169
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#Kaldeslerim 💜🥰 I am in love with this movie
نمایش همه...
1.12 MB
በስደት ላሉ እህት ወንድሞቼ ተጋበዙልኝ🥺💔
نمایش همه...
7.20 MB
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 🔥ክፍል 7 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . ከአስር አመት በፊት ..................................... ከኮረብታማው ጥንታዊ አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ግርጌ ድሮ በጣሊያን ወረራ ጊዜ በጣሊያን ይዞታ ውሰጥ የነበረው እና ጣሊያን በአባት አርበኞች ድባቅ ተመታ ሴራዋ ተንኮላሽቶ አፍራ ስትመለሰ ስራ ያቆመው የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በ1999 ዓ.ም እደሳ ተደርጎለት ስራ ጀመረ ።ባላ ሀብቱ ከአዲስ አበባ መጥቶ የገዛው ሲሆን ስሙ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ይባላል ።የደብሩ አስተዳዳሪ እና ጠባቂ የአባ ቶማስ ዘመድ ነው አሉ እየተባለ ጭምጭምታ ይሰማል ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ጥንታዊው አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ሁለቱ ወንድማማቾች ማለትም አብርሀወአጵብሀ ወይም ኢዛና እና ሳኢዛና ኢትዮጵያን ይገዙበት በነበረበት ዘመን ክርስቶስ ከተወለደ 300 አመት ገደማ እንደተመሰረተ አባቶች ይናገራሉ።ቤተ ክርስቲያኗ በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ የጥፋቱ ገፈት ቀማሽ እንደሆነች እና እንደተቃጠለች አንዳንድ የታሪክ መፅሐፍት አና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ።ከዚህ በተጨማሪ ግን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቆቅልሽ ሆኖበት እየኖረ ያለው ነገር ከደብሯ በሰተ ደቡብ በኩል ያለው ሰፊው ኮረብታማ ቦታ ነው።ቦታው አጅግ የሚያስገርም ከመሆኑ በተጨማሪ ሲቆሙበት የሚያሰማው ድምፅ ለእንግዳ ሰው በድንጋጤ ይገድላል።ቦታው ሲረግጡት የሚያወጣው ድምፅ ከከበሮ አይተናነስም ።ህብረተሰቡ ውስጡ ዋሻ ሰለሆነ ነው አንደዚህ የሚጮኸው ይላሉ ።እውነት አላቸው።አዎ ዋሻ ነው ማረጋገጫው ደግሞ ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ ወረድ ብሎ ለዋሻው መግቢያ ተብሎ የተሰራ በሚመስል መልኩ ቅርፅ አልባ መስኮት መሳይ ቀዳዳ አለ።በተለምዶ የዘንዶው ዋሻ በር ተብሎ ይጠራል። ጥንት አባቶች እና እናቶች ንብረታቸውን ከጠላት ለማሸሽ የቆፈሩት ዋሻ ነው ይባላል ።ወስጡ መንፈሳዊ የሆኑ እና መነሰፈሳዊ ያልሆኑ ሀብቶች እንደተደበቁ እና በዘንዶ እንደሚጠበቅ ሰፊው ማህበረሰብ ብትጠይቀው የሚሰጥህ መልስ ነው።ወደ ውስጥ ግን ማንም አልገባም ማንም ሊገባ አልሞከረም።ምክንያቱም የዘንዶ እራት መሆን የሚፈልግ የለም።እየተባለ ይወራል። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከአምስት አመት በፊት ........................ የሔዋን ትልቅ ወንድም የአቶ አንድነት የግል ልጅ ምናሴ አንድነት ይህን የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ አስገራሚውን ኮረብታማ ቦታ ጎብኝቶ የተመለሰ ማግስት የውሀ ሽታ ሆነ።የአካባቢው ኗሪ የዮርዳኖስን ቤተሰቦች ጨምሮ ምናሴ የት ደረሰ ብለው ጠየቁ።የሔዋን ቤተሰቦችም ምናሴ ዲቪ ደርሶት አሜሪካ ሔደ ብለው ተናገሩ ።ኗሪው የአቶ አንድነት ልጅ አሜሪካ ሔደለት ብለው የአቶ አንድነትን ቤት በድግስ አስጨንቀውት ሰነበቱ ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከአንድ አመት በፊት ..................................... "እሰኪ ስለ ስደት ምን ትያለሽ ?"ሲል ሔዋንን ዮርዳኖስ ጠየቃት "ህዝባችን እኮ ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብ ለመርዳት ራስን ለመለወጥ ብሎ ከእናት ሀገሩ እየወጣ በበረሃ የጊንጥ ሲሳይ በባህር ደግሞ የአሳ ነባሪ እራት እየሆነ ፣ገሚሱ ደግሞ አልሳካለት ብሎ ተጠርዞ ሲመለስ ተስፋ ቆርጣ ፤የዚች ምስኪን ሀገር እጣፈንታ እርሱ ትክሻ ላይ መሆኗን ዘንግቶ በሱስ እየዳከረ የሱን ህይወት አባላሽቶ እሱን እያዩ ለሚያድጉ ታናናሽ እህት እና ወንድሞቹ ነገን እንዳያዩ የአይን ቆብ ሆኖባቸው የተሸከመውን የሀላፊነት ቀንበር ከ ጫንቃው ላይ ጥሎ ለቤተሰብም ለሀገርም ሸክም ይሆናል።ተሳክቶለት የወጣውም በአፍ ብቻ እናት ሀገሬን እወዳታለሁ።ከማለት ውጭ ለዚች ሀገር ምን የፈየደላት ነገር አለ?እንዲያውም የዚች ምስኪን ሀገር ጥሪት ሊያጫርስ ከነጫጭባ ፈረንጅ ባላንጣ ጋር ሆኖ ለወጥመዱ ሽቦ ሲያቀብል ይውላል። እስኪ የእኔን ወንድም ምናሴን ተመልከት ።ለእናት ሀገሬ እሞታለሁ እኔ የምኖረው እሷ ስትኖር ነው ።ጥርኝ አፈሯን ልሼ እንዳደኩ ሁሉ የላስኩባትን ጥርኝ አፈር ወርቅ አድርጌ እመልስላታለሁ እያለ ኖሮ እድል ሲቀናው ይኸው ትቷት ሔደ።ምን አደረገላት?ምንም።ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች በእስኮላር መልኩ ይወሰዳሉ ።ተምረው መጥተው ለዚች ሀገር የፈየዱት ነገር አለ?የለም።የእግሯን እሾህ በመርፌ ለመንቀስ የሞከረ ምሁር እስከ አሁን አላየሁም አልሰማሁም ።በሔዱበት ሀገር እስረኛ ሆነው ይቀራሉ ።እስኪ እሩቅ ሳንሔድ ከዚው ከመንደራችን እንነሳ ።እንዳወቀ ካሴ ምሁር ይባላል ።ሳይንቲስት ይባላል ።ግን ሳይንቲስት ሆኖ ለዚች ሀገር ምን ጠቀማት?ይልቅ በችግር ማቃ የሞተችውን እናቱን ለመቅበር በእልፍ አእላፍ የፈረንጅ ወታደር ታጅቦ።መጣ።አስቀበረ።እንባው እንኳን ሳይደርቅ ነበር አንጠልጥለው የወሰዱት ።ይሔ ዘመናዊ ባርነት አይደለም ?አየህ የአገርህን ሰርዶ በአገርህ በሬ ድሮ ቀረ። የአገርህን ጥሪት የአገርህ ልጆች አሳልፈው ሰጡ ለፈረንጆች ።ብሎ አገሬው መተረት ከጀመረ ቆይቷል ።ይቺን ሀገረ እግዚአብሔር ይቺን የተስፋ ምድር የቺን የቃል ኪዳን ሀገር ኢትዮጵያን ፤ቀቢፀ ተስፋ በልባችን ያደረብን ወጣቶቿ ከተስፋ መንገድ እየራቅን በትንሳኤዋ ፋንታ ተስፋዋን እያጨለምን እኛ ሌላ ሀገር እንሽታለን ።የእኛን ቤት እያፈረስን ለባዕድ አገር ምሰሶ እንተክላለን ።"ብላ በምሬት ስትናገር ቆይታ "የግል አሰተያየቴ ነው"አለችው። ይቀጥላል
نمایش همه...
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 🔥ክፍል አስር 10 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . ሔዋን ከኮረብታው አፋፍ ላይ ቆማ ዙሪያ ገባውን ተመለከተች።ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ የዚባ ወንዝ ከአፍ እሰከ አፉ ጢም ብሎ ሞልቶ ይጥለመለማል።ክረምት መሆኑን ተከተሎ ዙሪያ ገባው ጋራው ሸንተረሩ በአዝርእትና አረንጓዴ በሆኑ እፀዋቶች ተሸፍኗል።የሚነፍሰው ነፋስ ለአዕምሮ እርካታን ይሰጣል።ከተማ ለምኔ እንዲሉ ያደርጋል ። "እዚህ ቦታ ከዮርዲ ጋር ትዝታ መቅረፅ ነበረብን"ብላ ተፀፀተች። "ነይ ልጄ ተከተይኝ"አሉ አባ ቶማስ ኮረብታውን ቁልቁል እየወረዱ ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ቁልቁለቱን ወርደው እንደጨረሱ የዘንዶው ዋሻ በር ላይ ሲደርሱ ቆሙ።"ልጄ ከዚህ በፊት መጥተሽ አይተሽው ካልሆነ በአፈታሪክ የምትሰሚው የዘንዶው ዋሻ በር ማለት ይሔ ነው "አሉ አባ ቶማስ "መጥቼ እንኳን አላውቅም ቦታው ደስ ይላል"አለች ሔዋን ። "በጣም"አሉ አባ ወደ ውስጥ ለመግባት ጎንበስ ብለው። "አባ ምን እያደረጉ ነው ውስጥ እኮ ዘንዶ አለ እየተባለ ነው የሚወራው ።?እንዴት አልሰሙም "አለች ፍርሀት እየተናነቃት "ልጄ አትከተይኝም"ማለት ነው አሉ አባ ከአንገታቸው ሰበር ብለው እየተመለከቷት። "አረ እከተለወታለሁ"አለች በድንጋጤ ውስጥ ሆና ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አስራ አምስት ሜትር ገደማ በሆዳቸው እየተሳቡ ከተጓዙ በኋላ ዋሻው መስፋት ጀመረ።የእጅ ባትሪያቸውን ከኪሳቸው አወጡ እና አበሩት።"ተነሺ ልጄ ከዚህ በኋላ ቆመን ነው የምንራመደው።"አሉ ወደፊት ባትሪያቸውን በጨለማው ዋሻ እያበሩ።ዋሻው ተጠርቦ እንደተሰራ ባትሪው ከዋሻው ግድግዳ ላይ ብርሀኑ ሲያርፍ የሚታየው የመጥረቢያ ቅርፅ ያሳብቃል።ውስጥ ለውስጥ ብዙ ከተጓዙ በኋላ አንድ ቦታ ሲደርሱ ቆሙ።ባትሪያቸውን ፊት ለፊት ሲያበሩት አንድ አነስተኛ ከእንጨት የተሰራች በር ላይ የባትሪው ብርሀን አረፈ። አባ ቶማስ በሩን ለመክፈት ሔዱ።ሔዋን ግን በፍርሀት ሁለመናዋን እያላባት ነበር። ያየቻቸው ፊልሞች ላይ በዘንዶ ሲዋጡ በህሊናዋ እየመጣ፤ከአሁን አሁን ዘንዶ መጣብኝ እያለች በፍርሀት ተኮማተረች። "ልጄ ወዲህ ነይ አሉ" አባ ሔዋን በፍርሀት ሽምቅቅ እንዳለች ወደ አባ ቶማስ ተጠጋች ።ወደ ተከፍተው በር እንድትገባ ጋበዟት። ፨፨፨፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨፨፨፨፨ ሔዋን ወደ ውስጥ እንደገባች፤አባ ቶማስ ከዋሻው ግድግዳ ላይ ማብሪያ ማጥፊያ ተጭነው መብራት አበሩ።ሔዋን ህልም አለም ውስጥ ያለች እያቀዠች መሰላት።ክፍሉ ከሸክላ በተሰሩ ጋኖች ተሞልቷል።ከዚህም በላይ ያስገረማት ግን እዚህ ዋሻ ውስጥ እንዴት መብራት ሊኖር ቻለ።ለዛውም ደግሞ እዚህ ክፍል ብቻ ነው። "ልጄ ነይ ከዚህ ተቀመጪ" ብለው ዋሻው ሲፈለፈል አብሮ ከተሰራ መደብ ቢጤ ነገር ላይ አስቀመጧት እና ከፊት ለፊቷ ተቀመጡ ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "ልጄ አባቶቻችን ጠንካሮች ነበሩ።አባት አርበኞች ጠላትን ፊት ለፊት ሲዋጉ ሴቶች እና በአቅማቸው የደከሙት ደግሞ እንደዚህ አይነት ተዓምራዊ ዋሻ እየፈለፈሉ ንብረቶቻቸውን ይሰውሩ ነበር።ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወሩ አባቶች ይሔንን ዋሻ ፈልፍለው ንብረቶቻቸውን ደበቁ።ነገር ግን ለአቅም አስቸግራ ውስጥ ውስጡን ስራዋን መስራት ስትጀምር እና ንጉሰ ነገስት ከአገር ወጥተው ሲሔዱ።ጠላት በማን አለብኝነት ጥንታዊ ቅርሶችን ከእየቦታው እየቃረሙ እየዘረፉ ከዚህ ጥንታዊ ቂርቆስ ደረሱ።እነዚህ ሰላቢዎች ከይሲዎች እንዴት እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ይሔን ዋሻ ደረሱበት ።እሰየው የዘረፍነውን የምናከማችበት አገኘን ብለው።ከእየ አካባቢው የቃረሙትን ሀብት እያመጡ እዚህ ማከማቸት ጀመሩ ።ለታሪክ እንዳይበጅ አድርገው ወደ ዋሻው የሚገቡ አባቶችን በግፍ ገደሏቸው።የዋሻውን ምስጢር የሚያውቅ በሙሉ አለቀ። ዘንዶ ውስጥ እንዳለ እና ውስጥ የሚገቡትን እየሰለቀጠ እንደሆነ የተዛባ ታሪክ ተወራ።የነገሩትን የሚያምን ይሔ ምስኪን ህዝብ የውሀ ሽታ ሆነው የቀሩትን አባቶች ዘንዶ ዋጣቸው ብሎ መሪር ልቅሶን አለቀሰ።የደም እንባ አነባ።ቦታውም የዘንዶ ዋሻ ተብሎ ተሰየመ።ከዛ በኋላ ይሔ ቦታ ተፈርቶ እየኖረ ነው"ብለው እያዳመጠቻቸው እንደሆነ ተመለከቱ እና ቀጠሉ ። "ከዚያ በኋላ የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ ማምረቻውን አዳራሽ ጣሊያን አነፁ።ግን አላማቸው ድንጋይ መፍጨት አልነበረም።"ብለው ቀና አሉና ተመለከቷት። "ታዲያ ድንጋይ ወፍጮ ድንጋይ ከመፍጨት ውጭ ሌላ ምን አለማ አለው?"አለች ሔዋን በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ። በጥልቅ አስተያየት አይኗን ሲመረምሯት ከቆዩ በኋላ "አየሽ ልጄ የአነፁት አዳራሽ የጀርባ ግድግዳው ከዋሻው ምዕራባዊ በር ጋር የተያያዘ ነው።የአዳራሹ የጀርባ ግድግዳ ላይ በር አለ።በሩ የትም ሳይሆን የሚወስደው ወደ ዋሻው ነው።ምክንያቱም ግድግዳው ከተራራው ጋር ተጣብቆ የተገነባ ነው።ይሔ ክፍል ተለይቶ መብራት የተገጠመለት ለጥበቃ እንዲመቻቸው ነው።አየሻቸው እነዚህ ጋኖች ጣልያን የዘረፋት እና አባቶች ደብቀውት የነበረ ወርቅ ብር አልማዝ እንቁ የተሞላ ነው።ወፍጮው የተመሰረተበት አላማ እነዚህ የአካበቱአቸውን ቅርሶች ለመጠበቅ እና እንዲሁም የተፈጨ ድንጋይ አስመስለው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ እንዲመቻቸው ነው።ነገር ግን የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ቸር ነው።ኢትዮጵያን ሊጨክንባት አልወደደም እና ለአርበኞች ፅናትን ሰጥቷቸው አገራችሁ አገራችን ብለው የተቀመጡትን ጣሊያኖችን አባረሩ።ከእየቦታው ቃርመው ያስቀመጡትን ሳያሸሹ ወደ አገራቸው ተመለሱ።የድንጋይ ወፍጮው እስከ 1998ዓ.ም ተዘግቶ ነበር። ነገር ግን 1999 ዓ.ም አቶ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ገዝቶ እንደ አዲስ ስራ ጀመረ።አሁንም አላማው ድንጋይ መፍጨት አይደለም።"አሉ እና ከሚያስገመግመው ድምፃቸው አረፉ። ሔዋን በታሪኩ ብትመሰጥም ለእሷ ለምን እንደሚነግሯት አልገባትም ።ይሔ ታሪክ እና የእሷ አሜሪካ መሔድ ምንም የማይገናኝ ነገር ሆኖ ታያት። "እሺ አላማው ምንድን ነው"አለች ሔዋን። "እሱን ወንድምሽ ይነግርሻል?"አሉና ለመሔድ ተነሱ "ይሔን ታሪክ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?አለች "አሱን አሁን የምነግርበት ጊዜ አይደለም"አሉ አባ "እሺ መቼ ነው የምበረው?"አለች "ነገ ከኢያሱ ጋር አዲስአበባ ከነገ በስቲያ ደግሞ ወደ አሜሪካ ትበሪያለሽ ትኬትሽ ተቆርጧል"አሉ መብራቱን እያጠፉ ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ትንሿን ክፍል ለቀው ሀያ አምስት ሜትር ገደማ ከተጓዙ በኋላ ከብረት የተሰራ በር አገኙ።ባትሪውን ሔዋን እንድታበራላቸው ሰጧት እና ከቀሚሳቸው ኪስ ብዙ ቁልፎችን የያዘ ማሰሮ አውጥተው ሰረገላ ቁልፋን አሽከርክረው ከፈቱት።ሔዋን የነገሯት እውነት መሆኑን አረጋገጠች።በሩ ሲከፈት ቀጥታ የአዳራሹ ኮሪደር ላይ ነበር የገቡት።ከጨለማው ወጥታ ብርሀን ስታገኝ ሰላም ተሰማት።ነገር ግን አባ ጀምረው ያልቋጩት ታሪክ እየከነከናት ነው። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ሔዋን ከተሰጣት ክፍል ውስጥ ጋደም ብላ በአየችው ነገር ብቻዋን አየተገረመች ድንገት አንድ ሀሳብ መጣላት እና ቦርሳውን መጎርጎር ጀመረች ።ከትንሽ ፍለጋ በኋላ ከዮርዲ የተቀበለችወን የግጥም ደብተር አወጣችውና መመርመር ጀመረች ።አንድ ርዕሰ ላይ አፈጠጠች።"ፈራሁ"ይላል ገፅ አገላበጠች እና ግጥሙን አወጣችው ፈራሁ ውስጤ ቃተተ ስጋት ልቤ ሸመተ ፈራሁት ፍርሀቴን እንዳላጣት ሔዋንን
نمایش همه...
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 🔥ክፍል 12 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . ሰከንዶች እየበረሩ ደቂቃን ደቂቃዎች ዞረው ሰዓትን ሰዐታት ተሽከርክረው ቀናትን ቀናት ተደምረው ሳምንታትን ሳምንታት ተጣምረው ወራትን እየፈጠሩ ይሔው በደብረብርሀን ዮኒቨርስቲ ዮርዳኖስ አንድ ሴሚስተር ሊያስቆጥር ጥቂት ሳምንታት ቀርተውታል ።የሔዋን ናፍቆት ቢያንገበግበውም ነገር ግን ደሴ እና ቃል በእየቀኑ እየደወሉ ብርታትን ሰጥተውታል ።ሔዋን ደውላ አታውቅም።ለምን ብሎ ቤተሰቧን ሲጠይቅ የሔደችበት ቦታ ይሔንን አይፈቅድም ብቻ ነው መልሳቸወ።እሱም ከትራሱ በላይ ፎቶዋን አንጠልጥሎ ጠዋትም ማታም እንደ ስዕል አድኖ ይሳለማታል ።ታዲያ ዘላለም የሚባል የዶርሙ ልጅ አንድ ቀን "እኔ እምልህ ዮርዲ ፥ማን እሚሏት ሰማዕት ነች ባክህ እንደዚህ ጠዋት ማታ እሚሰገድላት?ነገረኝ እና እኔም ለነፍሴ ይሆነኝ ዘንድ ልስገድላት"ብሎ ቀልዶበታል።ዮርዲ የተመደበበት ዶርም ሁሉም ሰው ይቀናባታል።ፍቅራቸው መተሳሰባቸው ከብዙ አመት ቅርርብ የመነጨ እንጂ የአንድ ሴሚስተር ብቻ አይመስልም ።የመጀመሪያ ቀን በዘላለም እና በዮናስ መካከል የተፈጠረው ሰጣገባ ሁሉንም የዶርም አባላት አስበርግጎ ነበር። ..............እንዲህ ሆነ.................... ዮርዳኖስ ከተመደበበት ብሎክ 23 ማስታወቂያ መለጠፊያው ላይ የተመደበበትን ዶርም እና የዶርም አባላት ተመለከተ። ዶርም 106 ይልና 👉ዮናስ ግሩም 👉ዮናስ ካሳ 👉ዮናታን ስለሺ 👉ዮርዳኖስ ተሾመ 👉ዘላለም ደሴ 👉ዝናቡ አከለ እነኚህ ጋር ነበር ዮርዲ የተመደበው ።ዮርዳኖስ ዶርም ሲገባ ሁሉም አልጋቸውን አነጥፈዋል እሱ ብቻ ነበር የቀረው ።ሰላምታ ስጥቷቸው አልጋውን አነጠፈና ለመመዝገብ ወደ ዲፓርትመንት ወረደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ምሽት ላይ ሁሉም አልጋቸው ላይ አድፍጠዋል።ዘላለም እና ዮናታን ከአንድ አካባቢ ሳይሆን አይቀርም የመጡት ወሬያቸው ደርቷል ። ታዲያ ዮናታን ጋር ዘላለም ሲያወራ ቆየና በድንገት ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተረተ "የወሎ ልጅ ማር ነው አዘንብለሽ ጠጪው ሌላው ቅራሪ ነው ምንግዜም አታጪው"አለ ዘላለም ድምፁን ከፍ አድርጎ ። ከፊት ለፊት የተኛው ልጅ በደመ ነፍስ ተነሳና ዘላለም ላይ ተከመረበት አንገቱን አንቆ ይዞ "ማነው ቅራሪ አንተ ማንን ነው ቅራሪ የምትለው።"ብሎ ለመማታት እጁን ሲሰነዝር ሌሎች ልጆች ከአልጋው ላይ ወርድው አገላገሏቸው።የተናደደው ልጅ ንዴቱ ሲበርድለት ዘላለም ለስለስ ብሎ ለማግባባት ሞከረ። "ምን መሰለህ ወንድሜ እንዲሁ ሳይህ ጎጃሜ መሰልከኝ እና ጎጃሜ ደግሞ ቅኔ በመዝረፍ አንደኛ ናቸው ሲባል ሰምቼ የመጣህበትን እንደኔ በቅኔ እንድትነግረኝ አስቤ እንጂ ሌላ ተንኮል አስቤ አይደለም።"አለ ዘላለም ይቅርታ እየጠየቀ። "ወንድም ይቅርታ አድርግልኝ እኔ በአንድ ቀን ብሔር ተኮር ነገር ለመናገር አስበህ መስሎኝ እንጂ እኔም መጥፎ ሰው አይደለሁም።ለማንኛውም ዮናስ ካሳ ከጎጃም ሞጣ ነኝ።"ብሎ ሔዶ ጨበጠው። "ዘላለም ደሴ ከውሎ የደሴ ልጅ"ብሎ አፀፋውን መለሰለት። ሁሉም እራሳቸውን አስተዋወቁ ዮርዳኖስ ተሾመ ከጎጃም ደብረማርቆስ አካባቢ ዮናስ ግሩም ከአዲስአበባ ዮናታን ስለሺ ከወሎ የዘላለም የሰፈር ልጅ ነኝ ዝናቡ አከለ ከወሎ የራያ ልጅ ነኝ ከጥሙጋ ተዋወቁ ሌሊቱን በሙሉ ሲያወሩ አደሩ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዮናታን ዮናስ ካሳ እና ዮናስ ግሩም ስማቸው ተመሳሳይ ሰለሆነ ለማቆላመጥ አስቸገረ።ዮኒ ብሎ ሰው ሲጣራ ሶስቱም አቤት እያሉ ተቸገሩ።ስለዚህ ለሁሉም ቅፅል ስም ተሰየመ ዮናስ ካሳ👉ዮኒ ጎጃሜ (ጎጄ) ዮናስ ግሩም 👉ዮኒ ዮናታን ስለሺ 👉ናታን👉ናቲ ዮርዳኖስ 👉ዮርዲ ዘላለም 👉ዞላ ዝናቡ 👉ዜኖ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 👉ዞላ ማለት እየቀለደ ለመኖር የተፈጠረ በሚመስል መልኩ ሲቀልድ እንጂ ቁምነገር ሲያወራ ተሰምቶ አይታወቅም።በስህተት እንኳ ቢያወራ ዞላ ቁምነገር በአንተ አያምርም ብለው አፉን ያዘጉታል።ቤተሰቦቹ ተጭነው ስላሳደጉት ግቢ ከገባ ቀን ጀምሮ እንደልቤ ሆኗል ።ተከልክሎ ያደገ ልጅ ስለሆነ አሁን ያየው ሁሉ ያምረዋል።ሁሉን ቀማሽ ሆኗል።በእነዚህ ትንሽ ወራት ውስጥ ሀይለኛ ሱሴ ሆኗል።በዚህ ፀባዩ ዮርዲ ሁሌም ይናደዳል ። 👉ዮኒ ማለት ቁምነገር ነው ምክንያታዊ ሰው።ወሬወቹም ድርጊቶቹም በምክንያት የተደገፉ ናቸው።ተከራክሮ የማሳመን አቅሙ በጣም ከፍተኛ ነው።ድንጋይን ዳቦ ነው ብሎ ሊያበላ የሚችል ሰው ነው።ከዮርዳኖስ ጋር ልብ ለልብ ተገናኝተዋል ። 👉ዜኖ ማለት ካላወሩት የማያወራ ከዶርሙ ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሰው ነው።ዶርም ከጓደኞቹ ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ኢምንት ነች ።የትኛውም እንቅስቃሲያቸው ላይ ተሳታፊ አይደለም።ስለ ህይወቱ ስላሳለፈው እና ስለሚኖረው ላይፍ ለማንንም ትንፍሽ አይልም ቁጥብ ነው።ጓደኛው ሀንድ አውት ብቻ ነው። 👉ዮኒ ጎጄ ማለት ነገሮችን አጋኖ የሚያወራ የጠበበውን አስፍቶ ያላየውን ምስል ፈጥሮ ያልሰማውን ጥሩ ተረት መስርቶ ያልሆነውን ሆነ የማይሆነውን ይሆናል ብሎ የሚናገር ልጅ ነው።ታዲያ ለጨዋታ ድምቀት እንጂ ነገር ማስፋት ሱስ ሆኖበት አይደለም።ቁምነገር ላይ ቁምነገረኛ ነው። 👉ናቲ ማለት አወዛጋቢ ሰው ነው።እንዲያውም አንዳንዴ ሳሙና እያሉ ይጠሩታል።ያሙለጨልጫል።ዶርም ነኝ ብሎህ ካፌ ታገኘዋለህ።ካፌ ነኝ ብሎ ኳስ ሲጫወት ይገኛል ።ክላስ ልገባ ነው ብሎ ቴኒስ ሲጫወት ትይዘዋለህ።ታዲያ ነገሮችን በእቅድ ያለመምራት ችግር እንጂ ሌላ አመል አይደለም። 👉ዮርዲ ያው ሔዋን ከመለየቱ በፊት እንደነበረው ተጫዋች ባይሆንም።በመጠኑም ቢሆን ይቀልዳል ይጫወታል። ሔዋን እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ወደ ሔኖክ ቢሮ አመራች።ኮሪደሩን አቋርጣ ከቢሮ ስትደርስ ለማንኳኳት እንኳን ጊዜ አላገኘችም።በሩን ከፍታ ገባችና ፈቃድ እንኳን ሳታገኝ ከእንግዳ መቀበያው ወንበር ላይ ተቀመጠች ። ሔኖክ በአግራሞት ሲመለከታት ከቆየ በኋላ"ሔዋን ምነው የሆንሺው ነገር አለ እንዴ?"አለ "አቶ ሔኖክ እየሆነ ያለው ነገር ምንም ሊገባኝ አልቻለም"አለች ለምቦጯን እንደጣለች ። "ሔዋን በመጀመሪያ ደረጃ አቶ እንዳትይኝ ብዬ ደጋግሜ ነግሬሽ ነበር።ሲቀጥል ነገሮችን ተነጋግረን መፍታት እየቻልን እንደዚህ መቆጣቱ አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም"አለ ሔኖክ "እንዴት ነው የምረጋጋው?እዚህ አዳራሽ ውስጥ ታግቼ ይሔው ስድስት ወር ሞላኝ።ለወንድሜ ጉዳይ ብላችሁ አምጥታችሁ ምግብ ቀቃይ አድርጋችሁ አስቀመጣችሁኝ።ሔኖክ እውነት በቃኝ ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም ወደ ቤቴ ነው መሔድ የምፈልገው"አለች ሔዋን ። ሔኖክ የተናገረችውን በአፅንኦት ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ"ሔዋን ትዕግስትሽ ይቺ ብቻ ከሆነች መሔድ ትችያለሽ እውነቱን ልንገርሽ ለዚህ ፕሮጀከት ምናሴ እና አባ ቶማስ ሲመርጡሽ አኔ ተቃውሜ ነበር።ደግሞም ልክ ነኝ ህፃን ነች ብስለት ይጎድላታል ብየ ስናገር አይ እንደ እድሜዋ ሳትሆን እድሜዋን ቀድማ የሔደች በሳል ነች አሉ።ግን የታለ ብስለትሽ"ብሎ የመውጫ ወረቀት ፅፎ ሰጣት ። ወረቀቱን ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦክሱ ውስጥ ጣለችና"አይደለም እኮ ሔኖክ የፕሮጀክቱ አላማ እኮ ምንም አልገባኝም ደግሞስ ወንድምሽ ጋር ትሔጃለሽ ብላችሁ አምጥታችሁ በእኔ ተርታ ሌላ ሰው ላካችሁ እኔም እኮ ግራ ቢገባኝ ነው"አለች ሔዋን በሔኖክ ንዴት ደንግጣ ። "እሺ የፕሮጀክቱን አላማ ማወቅ ነው የፈለግሽው?እንግዲውያስ እዚሁ ጠብቂኝ"ብሎ ሔኖክ ክፍሉን ትቶ ወጣ ። ሔዋን ስህተት የሰራች መስሎ ተሰማት "ከመናገር በፊት ማዳመጥ ከስህተት ያድና
نمایش همه...
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 💞ክፍል 9 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . ከእነ ሔዋን ደጅ የተነሳው ላንድ ክሩዘር መኪና 15 ደቂቃ ያህል ከተጓዘ በኋላ ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በር ላይ ሲደርስ ቆመ። "እንዴ አባዬ እዚህ ምን እሰራለሁ?እዚህ ድንጋይ ተሸካሚ ልታደርገኝ ነው እንዴ"አለች ሔዋን አቶ አንድነት በሔዋን አነጋገር ፈገግ ብሎ "አይደለም ልጄ ከመሔድሽ በፊት እዚህ የሚጨርስ ጉዳይ አለ"አለ ሔዋን የወንድሟ ጉዳይ ስለሆነ ምንም ማለት አልፈለገችም።ሲኦል እንኳን ቢሆን እሔዳለሁ በሚል አቋም ፀንታለች። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አቶ አንድነት ሔዋንን ተሰናብቶ አስተዋይ እንድትሆን አስጠንቅቋት።በመጡበት መኪና ተመልሶ ሔደ።አብሯት የቆመው ወጣት የግቢውን መጥሪያ ደወል እየተጫነ።"ኢያሱ እባላለሁ"ብሎ እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት። "ሔዋን"ብላ አፀፋውን መለሰችለት "ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል"አለ "አመሰግናለሁ እኔም ስለተዋወኩህ ደስ ብሎኛል"አለች ከደቂቃዎች በኋላ በሩ ተከፈተና ተፈትሸው ገቡ።ድንጋይ ወፍጮው ምንም አይነት ሰው አይታይበትም።ከፊት ለፊቱ በተጣለው ድንኳን ውስጥ ግን ሴራሚክስ አምራቾች ቡድን ወደ ሀያ የሚደርሱ ወጣቶች እየተሯሯጡ ነው። ኢያሱ ጋር ለመተዋወቅ ያህል እያወሩ፤ ቡድኑ አጠገብ ሲደርሱ "በስራ የተጠመዱት ወጣቶች "እህታችን እንኳን ደህና መጣሽ"ብለው እያንዳንዳቸው ተዋውቀዋት ወደስራቸው ተመለሱ ።ኢያሱ እና ሔዋን በኢያሱ መሪነት ወደ ሰፊው አዳራሽ አመሩ።ብዙ ክፍሎች አቋርጠው ከሔዱ በኋላ አንድ ክፍል ላይ ሲደርሱ ቆሙ።በሩን አንኳኳ እና ከፈተው።ሲገቡ ኮምፒውተር ላይ ያፈጠጠ ወጣት ተቀምጧል።እጁን ለሔዋን ዘረጋላት እና "ሔኖክ እባላለሁ"አላት ወጣቱ "ሔዋን"አለች የዘረጋላት መዳፉን እየጨበጠች "በቃ ተዋወቁ እኔ ወደስራ ልመለስ"ብሎ ኢያሱ ሔደ። ሔኖክ የቢሮ ስልኩን ነካካ እና "ሔሎ አባ መጥታለች"ብሎ መልስ ሳይጠብቅ ስልኩን ዘጋው ። "እሺ ሔዋን አሜሪካ ለመሔድ መቼም ጓጉተሻል አይደል ?" ሔኖክ ፈገግ ብሎ ጨዋታ ለመጀመር ያህል ጠየቃት "አረ በፍፁም የማያውቁት ሀገር እኮ አይናፍቅም"አለች ኮስተር ብላ "እሱስ ልክ ነሽ። ግን እኛ ሰዎች ስንባል አዲስ ነገር ፈላጊዎች ነን"አለ ሔኖክ "አዎ አዲስ ነገር ፈላጊዎች ነን ነገር ግን አዲስ ነገር፣ለውጥ ስንሻ ጥቅሙን እና ጉዳቱን ማመዛዘን አለብን።ለውጥ እንፈልጋለን እና ከመሬት ተነስተን ለውጥን መናፈቅ የለብንም።እናታችን ሔዋን በገነት በአማረ ቦታ ላይ እየኖረች ነገር ግን የጠላት ምክር ተቀብላ የማታውቀውን ናፈቀች ያላየችው መንግሰት አማራት ስታ አዳምን አሳታቸው።ከምድረ እርስት ተባረሩ ።አየህ በግብዝነት ለውጥን አዲስ ነገርን መናፈቅ የለብንም ።ምክንያታዊ የሆነ አዲስ ነገር ነው መሻት ያለብን።ይቅርታ ብዙ አወራሁ መሰለኝ"አለች ሔዋን ። "አረ ልክ እኮ ነሽ እኔም የአንቺን ሀሳብ እጋራለሁ"አለ ሔኖክ "ግን እዚህ ለምን እንደመጣሁ አልገባኝም " ተናግራ ሳትጨርስ ግርማ ሞገሳቸው የሚያስፈራ አባት በሩን ከፍተው ገቡ።ሔዋን ደነገጠች።ታውቃቸዋለች አባ ቶማስ ናቸው ።የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ ደብር ጠባቂ እና አስተዳዳሪ ናቸው።ለሔዋን ቤተሰቦች ደግሞ የንስሐ አባት ናቸው።ሔዋን ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉልበታቸውን ስማ በመስቀል ተባርካ።ተቀመጠች ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ሔዋን በአባ ቶማስ መሪነት ረጅም ኮሪደር አቋርጠው ከሔዱ በኋላ አንድ ክፍል አባ ቶማስ ከፈቱ እና ሻንጣዋን እንድታስቀምጥ ነገሯት ።ወደ ውስጥ ስትገባ ክፍሉ መሬት ላይ በስርዓት የተነጠፈ ፍራሽ አንድ ጠረጴዛ እና ወንበር አለው።ቁልፍ ሰጧት እና "ልጄ ካልደከመሽ ቆልፊው እና ተከተይኝ"ብለዋት መልሷን ሳይሹ ፊታቸውን አዙረው መንገዳቸውን ቀጠሉ። "እንዴ ቃለአብ"አለ ዮርዲ ከፊታቸው ብስክሌት እያሽከረከረ የሚመጣውን ልጅ ለደሳለኝ እየጠቆመው "ማነው ቃለአብ?"አለ ደሴ ግራ በመጋባት አይነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ። ዮርዲ ግን እያዳመጠው አልነበረም።ልቡም አይኑም ብስክሌቱን እያሽከረከረ ከሔደው ልጅ ጋር አብሮ ሔዷል።ከአይኑ እስኪሰወር ድረስ ተመለከተለው ።ደሳለኝ በአግራሞት ሲመለከተው ከቆዬ በኋላ "አንተን እኮ ነው ቃለአብ ማነው?"አለና ደግሞ ጠየቀው ። "ባክህ ተወው"አለና በግርምት ጭንቅላቱን ወደግራ ወደቀኝ ናጠው። "እህ ይሔ ልጅ ጋር በሔዋን ተገናኝታችኋል ማለት ነው"አለ ደሴ ለማወጣጣት በሚመስል መልኩ "አንተ ተው ስሟን አታንሳ ልቧ ይሸበራል "አለ ወሬ ለመቀየር የደሳለኝ ጭቅጭቅ አላስቀምጥ ሲለው ዮርዲ በተሸናፊነት ስሜት"የሚጠቅም ታሪክ የለውም ብዬ ነው"አለ "እሺ ልስማው ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነው እኔ ያልሰማሁት ታሪክ የተደበቀኝ"አለ ደሴ ። "ምን መሰለህ"አለ እና ጉሮሮውን ጠራረገ።"ምን መሰለህ ይመስለኛል የዛሬ ስድስት ወር አካባቢ ነው።የሚገርም ህልም አየሁ።ቤዛ ነች እኔ ክፍል ድረስ የሆነ ልጅ ይዛ መጥታ "ዮርዲዬ ቃለአብ ይባላል መንታ ወንድምህ ነው"አለችኝ።ምን ያህል ደስ እንዳለኝ አትጠይቀኝ።ቃለአብ ብዬ አቀፍኩት አሱም ወንድሜ ብሎ እቀፈኝ ።የሚገርምህ እሱ ሲያቅፈኝ የተሰማኝን ስሜት ሔዋን እንደምታፈቅረኝ ነግራኝ ያቀፈችኝ ቀን እንኳ አልተሰማኝም ።"አለና በረጅሙ ተነፈሰ። "የሚገርም ነው ግን እንዴት እስከዛሬ አልነገርከኝም?"አለ ደሴ "እኔ ለራሱ እረስቼው ነበር።አሁን ብስክሌት እያሽከረከረ ያለፈው ልጅ ይሔን ነው መንታ ወንድምህ ብላ ያስተዋወቀችኝ።"አለ ዮርዲ "እስኪመለስ ጠብቀን ለምን አንተዋወቀውም" አለ ደሴ ። "ግን ሌላ ነገር እንዳትዘባርቅ ተዋውቀነው እንለያያለን "አለ ዮርዲ "ችግር የለውም"አለና ደሴ የጊዮርጊስ መግቢያ በር ጥግ ይዘው ቆሙ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከ አምስት ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ልጁ ከሔደበት እየተመለሰ በ200 ሜትር እርቀት ላይ ተመለከቱት።እየጠበቁት እንደሆነ እንዳይባንንባቸው እየተንቀሳቀሱ ጠበቁት።በአጠገባቸው እልፍ ሲል "ወንድሜ ወንድሜ"ብሎ ደሴ ተጣራ ባለ ብስክሌቱ ዞሮ ተመለከተና እሱን እንደጠሩት ሲያረጋግጥ ብስክሌቱን አዙሮ መጣ። "ሰላም እንዴት ነህ "አለና ደሴ እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ዮርዲም ተከተለ። ልጁ አፀፋውን መለሰ እና "ምን ልርዳችሁ?"አለ ፍፁም ትህትና በተሞላበት አነጋገር "ወንድም በፍጥነት ማድረስ የነበረብኝ መልዕክት ነበር ካላስቸገርኩህ ብስክሌቱን ለአስር ደቂቃ አከራየኝ"አለ ደሴ "አረ የምን ኪራይ ነው የምትለው!ሒድ መልዕክትህን አድርስ" አለና ከብስክሌቱ ላይ ወርዶ ብስክሌቱን ለደሴ ሰጠው ። ደሴ በፍጥነት ብስክሌቱን እያሽከረከረ ከአይናቸው ተሰወረባቸው ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "i think ዮርዳኖስ?አለ ልጁ ዮርዳኖስን ሲመለከት ከቆየ በኋላ ። ዮርዲ ደንገጥ ብሎ "አዎ ነኝ ግን እንዴት ልታውቀኝ ቻልክ?"አለ "ከሁለት ሳምንት በፊት የተዘጋጀው የግጥም ምሽት ላይ ግጥምህ አንደኛ ነበር የወጣው ።ስታቀርብ ተመልክቼሀለሁ።ጥሩ ገጣሚ ነህ ስላገኘውህ ደስ ብሎኛል ቃለአብ እባላለሁ"ብሎ በድጋሜ እጁን ዘረጋላት ። "ምን አይነት ግጥምጥሞሽ ነው በህልሜ ቤዛ ስታስተዋውቀኝም ቃለአብ ብላ ነበር ።የሆነ ነገርማ አለ"አለ በልቡ ዮርዲ የዘረጋለትን እጁን እየጨበጠ ። "እኔም ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል"አለ ዮርዲ "ሰፈርህ እዚህ አካበቢ ነው?"አለ ቃለአብ "አዎ ከዚህ ትንሽ ወረድ ብለህ ከምታገኘው ናዝሬት ከሚባለው ሰፈር ነኝ።አንተ ግን ከዚህ በፊት አላውቅህም እዚህ ሰፈር አይደለህም መሰ
نمایش همه...
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 💞ክፍል 8 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . "አንተ ዮርዲ ዮርዲ ተነሱ እንጂ ቁርስ ደርሷል እኮ"አለችና ቤዛ ብርድ ልብሱን ገፈፈቻቸው። "ምን አለበት ትንሽ ብንተኛ"አለ ዮርዲ እያዛጋ ያለውን አፋን በመዳፉ እየሸፈነ ። "ሁለት ሰዓት ሆኗል እማዬ ከጊዮርጊስ እስክትመለስ ተነስታችሁ ጠብቋት"አለች እና ትዕዛዝ ሰጥታ ተመለሰች ። "አንተ ግን ደና ነህ ?"አለ ዮርዲ ደሳለኝን እንዴት ሲጠጣ እንዳመሸ እያስታወሰ። "አንተ እራስህ ደህና ነህ?አንተ ስትጠጣ ያመሸኸው ፀበል መሆኑ ነው እንዴ እንዳልጠጣ ሰው ደና ነህ የምትለኝ "አለ ደሴ ቀና ብሎ ዮርዲን እያየው ። "ማን ብዙ እንደጠጣ ቤዛ ትጠየቅ !አሁን ተነስ ሻወር እንውሰድ እና ቁርስ እንብላ" ብሎ ዮርዲ ከአልጋው ላይ ወረደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዮርዲ እና ደሴ ማታ የጠጡት ቢራ ርሀብ ዘርቶባቸው ነበር ያደሩት ።ቁርስ አመጋገባቸውን እያዩ መላ ቤተሰቡ አስቂኝ ትዕሪት የሚያዩ በሚመስል መልኩ በአግራሞት ነበር የሚመለከቷቸው ።ቁርስ ከተበላ በኋላ እልፍነሽ የጠዋቱን ቡና ለማድረስ ጉድ ጉድ ማለቷን ተያያዘችው ።በዚህ መሀል አቶ አንድነት ጨዋታ ጀመረ ። "እኔ እምልህ ደሴ እንዲያው ይሔ ልጅ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ሲመርጥ ዝም አልክ?ወይ እዚሁ ደብረማርቆስ አለበለዚያ እዛው ወደ አንተ አታስሞላውም ነበር "አለ አቶ አንድነት "ፋዘርየ እኔም እንደዛ አስቤ ነበር ነገር ግን አልሰማም አለ የነገስታት የፃድቃን የቅዱሳን መፍለቂያ ብዙ ተዐምር የሚፈፀምበት ብዙ ታሪካዊ ቦታዎች ባሉበት ሰሜን ሸዋ ሔጄ ነገስታቱ ካረፉበት ቅዱሳኑ ከተወለዱበት ቦታ ተቀምጬ ነው የጀመርኩትን መፅሐፍ ማጠናቀቅ የምፈለገው፣ለመፅሐፌ ቦታው ይጠቅመኛል አለ ደራሲው ወንድሜ።"አለና ዮርዲን ቸብ አደረገው ። "እንግዲህ ካለ ምን ይደረጋል እሱ ከወሰነ ወሰነ ነው የማንንም ሀሳብ አይሻም"አለ አቶ አንድነት የቀረበለትን ቡና ፉት እያለ። "በራስ መተማመኑን እወድለታለሁ ግን አንዳንዴ ሰው የሚነግረውንም መስማት አለበት ።"አለች ወይዘሮ አለም ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዮርዲ ደሴን የሆነ ነገር በጆሮው ሹክ አለውና ተያይዘው ወደ ዮርዲ ክፍል ገቡ።ዮርዳኖስ ከመሳቢያው ሔዋን የሰጠችውን ፖስታ አወጣና ከፈተው ።ውስጡ ሀብል እና የታጠፈ ወረቀት አለ።ሀብሉን አወጣ እና እጁ ገር አሰረው ። "እህ አንገትህ ላይ አድርገው እንጂ "አለ ደሴ በአግራሞት እየተመለከተው "አይ ግዴለም ሳልሳዊት ታደርግልኛለች ።"አለና ወረቀቱን ፈታታው ።ማንበብ ጀመረ። "የእኔ ወድ ከመወሰኔ በፊት ላማክርህ ይገባ ነበር።ነገር ግን አባየም የአንተ አባትም መናገሩ ችግር እንደሚፈጥር ነገሩኝ።እኔም የሰማሁት አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው።አዎ ለወንድሜ ለምናሴ በዚህ ሰዐት እንደማስፈልገው እና እንደምሔድ እንዲሁም ፕሮሰሱን አባዬ እንዳስጨረሰልኝ ሰማሁ።ታውቀለህ ሀገር ጥሎ መሔድ አማራጭ እንደሆነ ባላምንም ግን የእኔ መሔድ ወንድሜን የሚጠቅመው ከሆነ ምንም አማራጭ የለኝም ።የጀመርከውን መፅሐፍ እንደምትጨርሰው ቃል ግባልኝ።በቅርብ ጊዜ እንገናኛለን እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ።ግን ጠብቀኝ አፈቅርሀለሁ። የአንተው ሔዋን" አንብቦ እንደጨረሰ ሰማይ እና ምድሩ ተደበላለቀበት።መሬቱ ዞረበት የመሬት መሽከርከርን ዛሬ ሳያምን አልቀረም።በቁሙ አልጋው ላይ ዘፍ ብሎ ተቀመጠ።ደሴ ደነገጠና ወረቀቱን አነበበው ።ቅስሙ እንክት አለ።ምንም ለማለት አልደፈረም ምንም ሊል የሚችለው ነገር የለምና ከጎኑ ቁጭ አለ።ዮርዲ ከተቀመጠበት ተነሳና በፍጥነት እርመድ እርመድ እያለ ግቢውን ለቆ ወጣ ደሴ ተከተለው ።ትንሽ እንደተራመዱ ከእነ ሔዋን ደጅ ላንድ ክሩዘር መኪና ሲሔድ ተመለከተ።ባለበት ቁጭ አለ።ደሴ ዮርዲን ከአንገቱ ቀና አድርጎ ተመለከተው እንባወ እንደ ጅረት ሲወርድ አየ።ደሴ የዮርዳኖስን እንባ ሲመለከት ውስጡ ታወከ ባር ባር አለው።ዮርዳኖስን ሲያለቅስ አይቶት የማያውቀው ደሴ ዛሬ እንባውን ሲመለከት ውስጡ አለቀሰ።እንባው ገንፍሎ ፊቱን ሸፈነው።ከተቀመጠበት አነሳ እና እንደ ታመመ ሰው ድግፍ አድርጎ ወሰደው።ማንም ሳያያቸው በጓሮ በር ይዞት ገባ እና አስቀመጠው ። "ዮርዲ አንተ የእኔ ወንድም ነህ ይሔንንም ታልፈዋልህ "አለ ደሴ ። "ደሴ እንዴት ብዬ ሔዋን ትቼ እንዴት ወደፊት ልራመድ"አለ እንባው እየተናነቀው ። "ሳይለፉ የሚበሉት እንደማይጣፍጥ ሁሉ ሳይፈተኑ የሚኖሩት ኑሮ ትርጉም አልባ ነው።ደግሞ ሔዋን ትመልሳለች ሀገሯን፣ቤተሰቧን፣ፍቅሯን በትና የምትኖር ልጅ አይደለችም።ስለዚህ አንተ በምን በማንም ሳትሰናከል ትልቅ ሰው ሆነህ።በመፅሐፍህ ዝነኛ ሆነህ ጠብቃት።አቅሙ አለህ ደግሞም ታደርገዋለህ አልጠራጠርም የእኔ ወንድም ነህ በእያንዳንዷ እርምጃህ ከፊትህ እግዚአብሔር ፣ድንግል ማርያም ፣ከጐንህ መላዕክት ፣ፃድቃን፣ሰማዕታት ፣ቅዱሳን በዙሪያህ ደግም የምትወዳቸው የሚወዱህ ሰዎች እንዳሉ እና እኔ ወንድምህ ደግሞ የጉዞህ አንድ አካል እንደሆንኩ አስብ"ብሎ አቀፈው ። ዮርዲ ቀና ብሎ ግድግዳው ላይ ከተንጠለጠለ ጥቀስ ላይ አይኑን ተከለ። "በፈተና የሚፀና የተባረከ ሰው ነው ።" ያዕ 1፥12 ይላል ። ደጋግሞ ሲመለከተው ከቆየ በኅላ "ትወደኝ የለ አበርታኝ እንደፈቃድህ ይሁንልኝ ።"አለ ዮርዲ ። "ጎሽ እተማመንብሀለሁ አሳፍረኸኝም አታውቅም "አለ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ደሳለኝ ቤት የምሰራው ስራ አለኝ ከሰዓት በኋላ እንወጣለን ብሎ ወደ ቤቱ ሔደ።እሱም ሳሎን ገብቶ በዝምታ ተቀመጠ።ዝምታ የማያውቀው ዮርዲ ጭምት ሆነ።ነሁልሏል ።በራሱ አለም ውስጥ ገብቶ ሌላ አዲስ ሰው ሆኗል። "ልጁ ምን ሆኗል ዛሬ?አንተ ዮርዲ ምን ሆነህ ነው እንዴ ቤቱን እኮ ጭር አደረግከው።"አለች ወይዘሮ አለም።እውነት ነው ዮርዲ ከሌለ ቤቱ ህይወት የለውም ማለት ይቻላል።ዮርዲ ዝም አለ ማለት ቤቱ ዝም አለ ማለት ነው። ዮርዲ ቀና ብሎ እናቱን ተመለከተና ዝም አለ። "አንተ መልስላት እንጂ እየጠየቀችህ አይደል?"አለ አቶ ተሾመ። አባቱ ሲናገር የበለጠ ተናደደ ሊቋቋመው አልቻለም ስሜቱ ገንፍሎ ሲወጣ ታወቀው "አባዬ ዝም በል ምንም የምትልበት አፍ የለህም ምንም አትበለኝ"ብሎ ዮርዲ ደነፋ ።ሁሉም በድንጋጤ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ።ዮርዲ እንኳን እንደዚህ አባቱን ሊናገር ይቅርና ከእድሜ እኩዮቹ ጋር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል እሰጣ ገባ ውስጥ ገብቶ አያውቅም ። ወይዘሮ አለም ተነስታ ዮርዳኖስን በአይበሉብሽ ጥፊ ፊቱን ከመታችው በኋላ "አንተ ከመቼ ያመጣኸው ባህሪ ነው?ጭራሽ አባትህን እንደዚህ ትናገራለህ"አለች "ምክንያታችሁን ንገሩኝ ቀለበት አስራችሁ ከፍቅሬ የለያያችሁበትንን አሜሪካ የላከችሁበትን።" አቶ ተሾመ ዮርዳኖስ የተናደደበት ስለገባው።ተረጋግቶ መናገር ጀመረ።"ልጄ ምናሴ ችግር ላይ እንደሆነ እና ሔዋን እንደምታስፈልገው ብቻ ነው አቶ አንድነት የነገረኝ።ሌላ ማብራሪያ ሊነግረኝ አልፈለገም ግን ከአንድ አመት በኋላ እንደምትመጣ በእርግጠኝነት ነግሮኛል።እኔ ትሒድ ብዬ ተስማምቼ አልላኳትም ልትሔድ እንደሆነ ነው የነገረኝ።ላስቀራት አልችልም እኔ በአንተ እንጂ በእሷ የመወሰን መብት የለኝም።ስለዚህ እኔን እንደጥፋተኛ አትመልከተኝ ።እንዲያውም ለአንተ የሚበጀውን የቃል ኪዳን ቀለበት አቶ አንድነትን ጨቅጭቄ እንድታደርጉ አደረኩ ።"አለ አቶ ተሾመ በዚህ ጊዜ ዮርዳኖስ ተፀፅቶ እናቱንም አባቱንም ተንበርክኮ ይቅርታ ጠየቀ። ይቀጥላል
نمایش همه...
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘 🔥ክፍል 13 ✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ . . . "ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ"አለ ዞላ "ነይ ማማዬ"ሁለቱ ዮኒዎች ተቀበሉ ።ዮርዳኖስ ፅፎ ለመጨር ጥቂት ምዕራፍ የቀረውን ልቦለዱን እያገላበጠ ነው።ዜኖ ላይብረሪ መሽጓል። "ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ "ዞላ ቀጠለ "ነይ ማማዬ "ዮናስ ጎጄ እና ዮኒ ተቀበሉት "ማማዬ ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፉ ማግባት" " ነይ ማማዬ ' "ማማዬ ገንዘቡንም ያልቅ እና ሁለተኛ ጥፋት"ዞላ ዘፍኖ ጨረሰ እና ልቡ እስኪፈርስ ሳቀ ሁለቱ ዮናሶች ተክትለው ዶርሙን በሳቅ አናጉት።ናቲ እየተናናደደ ነበር ።ምክንያቱም እሱን ለመንካት ብሎ ነው ዞላ የዘፈነው። "አይገርምህም እንዳንተ በእየሳምንቱ አዲስ ትዳር ከመመስረት እኔ አልሻልም?"አለ ናቲ "እንደዛማ እንዳትል ይቺን ድብልብል ሰው አትላት ጉማሬ የሆነች ፍቅረኛህ ጋር ፍቅር ፍቅር እያለ እሱ እንዳንተ አይጃጃልም"አለ ዮኒ ጎጄ ዞላን ወግኖ "ፍቅር የት ታውቅና ነው ደግሞ አንተ።ፍቅር በአንተ አፍ ሲጠራ ደስ አይልም"አለ ናቲ ዮኒ ጎጄን ናቲ ሰሞኑን ቺክ ጠብሶ ዞላ አላስበላ አላስተኛ ብሎታል።ለነገሩ እውነቱን ነዉ በዞላም አይፈረድም።ይሔን የመሰለ ሸበላ ልጅ ከዚያች ጉርድ በርሜል ከምታክል ሰው ጋር ሆኖ ሲታይ አይደለም ጓደኞቹ ሌላም መንገደኛ ቢያይ መናደዱ አይቀርም።ምኗም እኮ አያምርም።ምኗን አይቶ ነው የወደዳት ብለው ጓደኞቹ ገርሟቸዋል።ዞላ የባለሀብት ልጅ ነች ገንዘቧን አይቶ ነው እያለ ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፋ ማግባት እያለ ይዘፍንበታል።ናቲ ግን የምን ገንዘብ ነው የምታወሩት በቃ ተመችታኛለች ከማለት ውጭ ሌላ መልስ አይመልስም ። ዞላም ፀባዩ ብሶበታል ካልቃመ የማያወራ ሱሰኛ ሆነ።ዶርም የሚያድርባቸው ቀናቶች በጣት ይቆጠራሉ።ዛሬ ከሊሊ ነገ ከቲቲ ከነገ ወዲያ ከጀሪ አዳሩ እንደዚህ ሆኖ አርፏል።ታዲያ ዮኒ እና ዮርዲ ቁጭ አድርገው ቢመክሩት አልሰማ ብሏቸዋል።ሱሱም ይቅርብህ ሴት ጋር መዝለሉም ተዉ ዘመኑን ለአንተ መንገር አያስፈልግም ትልቅ ሰው ነህ ብለው ሲነግሩት እሱ ግን አሻፈረኝ ብሏል ።ጋጥ ውስጥ ታጉራ የዋለች እምቦሳ ስትለቀቅ እንዴት እንደምትሆን ታውቃላችሁ አይደል?በቃ እኔንም እንደዛ ተመልከቱኝ ተውኝ እንደልቤ ልሁን።ለሌላው ነገር አታስቡ እኔ ጅል አይደለሁም በመላጣው አልጠቀምም ብሎ ከኪሱ ሴንሴሽን አውጥቶ አሳይቷቸዋል።ዮኒ እና ዮርዲም የሚያደርጉት ጠፍቶባቸው ዝም ብለዋል። ዮኒ ቆንጆ የልጅነት ፍቅረኛ አለችው።አንድ ላይ አገር ሞልተው ከአንድ ሰፈር የመጡ ጥንዶች ናቸወ።ሔለን ትባላለች አውርቶ አይጠግባትም።በእየ ሰከንዱ ነው የምትርበው።ዮርዲ እነሱን ሲመለከት ሔዋን አሜሪካ ባትሔድ እኔም እኮ እንደ ዮኒ ነበርኩ።ይላል።ዮርዳኖስን የሚረዳው ዮኒ ነው።ሁሌም ከዛሬ ነገ ይሻላል ሔዋን ፍቅርህ እምነትህ ሁሉ ነገርህ ነች እምነቷን ጠብቀህ ጠብቃት ፍቅር ዋጋውን ይከፍልሃል።ብሎ ዮኒ ሲናገር፤ዮኒ ጎጄ ጣልቃ ይገባና፦አረ ወዲያ ምን ፍቅር ፍቅር እያላችሁ ትጃጃላላችሁ።እዚህ ምድር ላይ ፍቅር የሚባል ነገር ያለው በፊልም እና ልቦለድ ላይ ነው።ዝም ብላችሁ በምናባችሁ የምትፈጥሩትን ህይወት አትኑሩ።አንዳንዴ ዮርዳኖስን እና ዮኒን ስመለከት ቆንጆ የህንድ ፊልም እያየሁ ወይም በጥሩ ደራሲ የተደረሰ የፍቅር ልቦለድ እያነበብኩ ነው የሚመስለኝ።ሔይ ፍቅር ምንድን ነው?ፍሬንዶች አይናችሁን ግለጡ ፍቅርን ይሁዳ ገድሎ ቀብሮታል ለፍቅር ብሎ የወረደውን ጌታ በሰላሳ ዲናር ሲሸጠው ያኔ ፍቅር ሞተ።ለፍቅር የወረደውን ጌታን ሲሰቅሉ ያኔ በአይሁዳውያን እጅ ተጨፍልቃ ፍቅር ጠፍታለች ።ታዲያ የት የምታውቁትን ነው ፍቅር የምትሉ።አስመሳዮች አንሁን።ዮርዳኖስ የራስህን ኑሮ ኑር ሔዋንን እርሳት እሷም አሜሪካ ኑሮዋን እየኖረች አይደል።በቃ እርሳው ምንም እንዳልፈጠረ።ኑር ይላል ዮኒ ጎጄ ። "ዮኒ ጎጄ አትሳሳት ፍቅር ለዘለዓለም ትኖራለች።አላዋቂዎች አጎደፏት እንጂ ፍቅር ትላንትም ዛሬም ነገም ሁሌም ትኖራለች።እስኪ ልጠይቅህ ዮኒ ጎጄ፦እናትህ ላይ ሽጉጥ ተነጣጥሮባት ብታይ ይግደላት ብለህ ዝም ትላለህ? "አረ በናትህ ዝም በል"ዮኒ ጎጄ መለሰ "አየህ ይግደላት ብለህ ዝም አትልም።አሷን ትቶ አንተን እንዲገድልህ ትማፀናለህ እንጂ።ከዚህ በላይ ፍቅር አለ እንዴ?ይላል ዮኒ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዜኖ በጣም ተረብሾ ዶርም ገባ።ከወዲያ ወዲህ ይንጎራደድ ተያይዞታል ። "ምነው ቴንሽን ነገ ፋይናል ይጀምራል አሉህ እንዴ"አለ ናቲ "ዝም በል ባክህ ለፋይናል ሁለት ሳምንት ነው እኮ የቀረን ነገ ማለት አይደለም? ይልቁንስ እሱን ተወው እና የዚህ ዶርም ነዋሪ በሙሉ ጉድሽ ፈልቷል"አለ ዜኖ በጣም ከመፍራቱ የተነሳ እያላበው ነው። "የምንጉድ አመጣህ"አለ ዮኒ ደንግጦ ከአልጋው ላይ እየወረደ። "ዞላ ገና ከዚህም በላይ ነው የሚያደርገን ይሔ ጦሰኛ ልጅ"አለ ዜኖ "ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ "አለ ዞላ "ምነው የትኛዋ ልጅ አረገዘች፤በናትህ ዞላ የልጅ አባት ሊሆን ነው በለኝና ልሳቅ"አለ ዮኒ ጎጄ "እሱማ በምን እድላችን።አንዷ ብታረግዝማ እሷን የሙጥኝ ብሎ እግሩን ሰብስቦ ይቀመጥ ነበር"አለ ዜኖ እየተንቆራጠጠ "አረ ዜኖ ዝም በል አድጌ ሳልጨርስ ልጅ አሳዳጊ ልታደርግኝ ነው።የሰይጣን ጆሮ ይደፈን።"አለ ዞላ ዮርዳኖስ ከአልጋው ላይ ተነሳ እና ዜኖን አስቀመጠው።"ዜኖ እስኪ ተረጋጋ እና የሆነውን ንገረን"አለ ዮርዲ "እንዴት ነው የምረጋጋው።አሁን ሻንጣችንን እንሸክፍ እና ጊቢውን ለቀን እንውጣ"አለ ዜኖ "ቆይ ይሔ ልጅ ምንድነው የሚያቃዠው"አለና ዮኒ ጎጄ የሀይላንድ ውሀ እረጨው "የምን ቅዠት ነዉ የምታወራው።ልጁን ብታዩት እኮ ጎሊያድን ያስንቃል።"አለ ዜኖ የበለጠ እየተንቀጠቀጠ... ሴትዮዋ ልጇ ከመሔዱ በፊት አስቀምጦላት የሔደውን ደብዳቤ ከአነበበች በኋላ ምንም መረጋጋት አልቻለችም።ትንሿ ግሮሰሪ ውስጥ ጨዋታዋን ለምደው እስከ እኩለ ሌሊት ያመሹ የነበሩ ደንበኞች ዛሬ ሴትዮዋ ፍዝዝ ስትል ገና በሁለቱ ሰዐት ቤቱ ጭር ብሏል።መንጋው ቀበሮ እንዳየ የበግ መንጋ ተበትኗል።ከአቅሟ በላይ ይጨፈርባት ይጠጣባት ይሰከርባት የነበረች ግሮሰሪ ዛሬ ግን አስከሬን የወጣባት ለቅሶ ቤት መስላለች።ግሮሰሪዋ ለሰፈሩ ብቸኛ ግሮሰሪ ስለሆነች የሰፈሩ ጠጪ በሙሉ ይችን ቤት የሙጥኝ ብሎ ነው የሚያመሸው።መቀመጫ ጠፍቶ ባንኮኒ እና ግድግዳ ተደግፎ የሚጠጣውን ሰው ቤት ይቁጠረው። ሰው ሁሉ ማርዘነብ አንች ዝም ስትይ አታምሪም ባይሆን ድብርትሽ ሲለቅሽ ነገ መጥተን እንጠጣለን አያለ ውጥቶ አልቋል።በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት በግምት ወደ ሰማኒያ አመት ገደማ የሚጠጉ አቶ አድማሱ እሳቸው ብቻ ቀርተዋል።ፀጉራቸው ለምልክት እንኳ ጥቁር ፀጉር የሚባል ነገር የላቸውም።አናታቸው ላይ ሀጫ በረዶ የመሰለ ያደገ ፀጉር ተደፍቶባቸዋል።እድሚያቸው የገፋ ቢሆንም ጉልበታቸው እና ሃይላቸው ግን ወጣትን ያስንቃል።ታዲያ ጨዋታ አዋቂ ስለሆኑ የሚጣጣው ሰው ሁሉ ነው የሚጋብዛቸው።እሳቸውም የማርዘነብን ግሮሰሪ ሳይሳለሙ ማደር አይሆንላቸውም። ጠርሙሳቸውን ይዘው ወደ ማርዘነብ ሔደው ተቀመጡ። "ማርየ እንደው አፈር ስሆን ምን አገኘሽ ልጄ"አሉ አባ ባይወልዷትም እንደ ልጃቸው ነው የሚመለከቷት።እድሜዋ ሰላሳዎችን ጨርሳ አርባወችን መጣሁላሁላችሁ እያለች ነው። "ጋሽ አድማሱ ግሮሰሪው እንደሚያዩት ዛሬ ጭር ብሏል እንዝጋው እና ቡና አፍልተን ያጫውቱን?"አለች ማርዘነብ "አረ ምን ገዶኝ"ይለፍ ሀሳብ ነው አሉ ከቢራቸው እየተጎነጩ "ማነሽ ፀሐይ አንቺ ቡናውን ግቢና አደራርሽ ፣እርግቤ አ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.