cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Official Enjibara university

#enjibara_እንጅባራ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
638
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል (CPD Center) አቋቋመ። ********** ሐምሌ 26/2015 ዓ፣ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል ለማቋቋም አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት  ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም  የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እውቅና ሰጪ አማካኝነት ተገምግሞ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማቅረብ የሚያስችለዉን የእዉቅና ፈቃድ አግኝቷል። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አብርሐም አማረ የማዕከሉ መቋቋም እንደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሳይሆን የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና አጎራባች ዞኖች ያለውን የሙያ ማጎልበቻ ችግር መቅረፍ የሚችል  እና  በአግባቡ የተደራጀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የእንጅባራ ዩንቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ የውበምርት ሻረው በበኩላቸው ከዚህ ቀደም መሰል የሙያ ማጎልበቻ ማዕከል ባለመኖሩ ባለሞያዎች ወደተለያዩ አካባቢዎች ሄደው ይሰለጥኑ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ላይ እዚህ በመከፈቱ አላስፈላጊ እንግልትን ከመቀነስ ባሻገር ለባለሙያዉ በሚፈልገው ጊዜ እና ቦታ ተደራሽ እንደሚሆን ተናግረዋል።
نمایش همه...
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በነበረው የትምህርት ልማት ሥራ  ለመንገሻ ጀምበሬ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላደረገው ድጋፍ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል። ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ለክረምት መርሐ ግብር ተማሪዎች በሙሉ፦ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ትምህርት ዝግጅት  በማድረግ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል። ነገር ግን ባለው የተጣበበ ጊዜ ምክንያት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው ደብዳቤ መሰረት የ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት አለመኖሩን እናሳውቃለን።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ  ፈተና መሰጠት ተጀምሯል። -------- በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር  የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አስፈላጊውን የፍተሻ ስርዓት አልፈው በአሁኑ ሰዓት  የእንግሊዘኛ የትምህርት አይነት ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።  የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ  ፈተና ከዛሬ ሐምሌ 25 እስከ አርብ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  ፈተናን  በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚወስዱ  የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ። የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀብታሙ ዘገየ (ዶ/ር)  በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው  በመጀመሪያ ዙር እንደተሰጠው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በተሳካ መንገድ ፈተናውን ለማስኬድ የተፈታኝ ተማሪዎች በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ህግና ደንብ አክብረው እንዲፈተኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ማዕከል ኃላፊ አቶ ሳህለ ወይንሸት እና የጉድኝት ማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ወሰኔ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ በተዋረድ እስከ ተፈታኝ ተማሪዎች ድረስ ለሚገኙ የፈተና አስፈፃሚ አካላት ሰፋ ያለ ገለፃና ውይይት ቀደም ብሎ መደረጉን ጠቅሰው በዛሬው ዕለት ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተናውን ሂደት በተመለከቱ  ርዕሰ-ጉዳዮች ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ማብራሪያና ትንታኔዎችን ሰጥተዋል፡፡ በተያያዘም ፈተናውን በተመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ሌሎች ተጨማሪ ማብራሪያና ትንታኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ካሉ ከፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው  አስፈፃሚ አካላት ግልፅ ማብራሪያዎችን ማግኘት እንደሚችሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
የሁለተኛ ዙር 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል። በዚህ ዙር ከ6,500 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በነገው እለት አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎ ከማክሰኞ ጀምሮ ፈተናው የሚሰጥ ይሆናል። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ውጤት ይመኛል። ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና ለመፈተን ከተለዩዩ  ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ ፈታኝ መምህራን እና አስተባባሪዎች   የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር እና ጉብኝት ተካሄደ፡፡ -------------- በመርሐ ግብሩ ዩኒቨርሲቲውን እና ዘንገና ሀይቅ ላይ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን የምሳ ግብዣም ተደርጓል። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመፈተን እና ለማስተባበር እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የመጡትን በሙሉ ሀገራዊ ተልዕኮን ለመፈፀም እና  የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ እንዲሁም የዚህ ዓመት የመጀመሪያ ዙር   የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በስኬት መጠናቀቅ ሁሉም በየድርሻው ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  "ምሁር ድንበር የለውም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለመጡ ፈታኝ መምህራን  አስተባባሪዎች የጉብኝት እና ምሳ ግብዣ  ዋና ዓላማ አካባቢውን ለማስተዋወቅ እርስበርስ ለመተዋወቅ እንዲሁም  የአገው ህዝብ እንግዳ ተቀባይነትን ለማሳየት እና ኢትዮጵያዊነት የተላበሰ  አንድነትና መስተጋብር ለመፍጠር የራሱን ጉልህ ሚና ይጫወታል በሚል መርህ የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
نمایش همه...
آرشیو پست ها