cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Biruh

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 042
مشترکین
-424 ساعت
-177 روز
-15630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
“ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።” — ራእይ 2፥10
ብሩህና መልካም ሰንበት ብሩህ ሁኑልኝ @BiruhEthiopia
نمایش همه...
❤‍🔥 1 1
አዘጋጅ : ቶማስ አር ሼፔርድ ትርጉም : ታምሬ ሻዕማሎ ይህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ የሚዘጋጀው በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መስሪያ ቤት በሆነው በጄኔራል ኮንፍራንስ ውስጥ ሆኖ የጎልማሶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያን በሚያዘጋጀው ቢሮ ነው። መምሪያዎቹ የሚዘጋጁት የጄኔራል ኮንፍራንስ አስተዳደር ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሆነውና የመጽሐፍ ቅዱስ መምሪያዎችን በሚያሳትመው የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድ ነው። የታተመው መምሪያ በውስጡ ዓለም አቀፋዊ የሆነ የምዘና ኮሚቴ ሀሳቦችንና የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድን ማረጋገጫ ስለሚያንጸባርቅ የአዘጋጁን (የአዘጋጆችን) ሀሳብ ብቻ የሚወክል አይደለም። በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ማተሚያ ቤት ታተመ 3ኛ ሩብ ዓመት ከሰኔ 22/2016 -- መስከረም 17/2017 ዓ.ም የማርቆስ ወንጌል ከማርቆስ መጽሐፍ ጅማሮ አንስቶ አንባቢው ኢየሱስ መሲህ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያውቃል (ማርቆስ 1፡1)። ነገር ግን በአጋንንት ከተያዙት ሰዎች በስተቀር በታሪኩ ውስጥ ያሉ ሰዎች እርሱ ማን እንደሆነ እና ለምን እንደመጣ ለመረዳት ተቸግረው ነበር። አጋንንት ግን እርሱ ማን እንደሆነ በትክክል አውቀው ነበር! አጋንንቶቹ አውቀውት ብርቱ በሆኑ ቃላቱ ፊት ጠወለጉ። ነገር ግን ይህንን መረጃ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው (አዘዛቸው)። ይህ ጉዳይ በምስጢር እንዲያዝ ለምን አዘዘ? የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በየዘመናቱ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ሲያወጡና ሲያወርዱ ነበር። በትምህርታቸው ውስጥ መሲሃዊው ምስጢር የሚል ስም ተሰጥቶታል። ስለ ኢየሱስ ማንነት ዝም እንድንል ወንጌል የሚፈልገው ለምንድር ነው? በማርቆስ ወንጌል የጥናት ጉዞ ላይ ግልጽ የሚሆን ነገር ካለ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ምስጢር ብቻ ሳይሆን አስደናቂ መገለጥም መኖሩ ነው። በትክክል መገለጥ/ የምስጢር ጭብጥ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሲሆን በመጨረሻ ምሥጢራዊነቱ በሚያስደንቅ ሁኔታ አብቅቶ ኃይለኛ በሆነ የኢየሱስ መገለጥ የሚተካ ቢሆንም በማርቆስ ወንጌል ውስጥ በሙሉ ይታያል። የማርቆስ መጽሐፍ በሁለት ተለይተው በሚታወቁ ክፍሎች ሊከፈል ይችላል። ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ የስምንተኛው ምዕራፍ ማብቂያ አከባቢ እስኪደርስ ድረስ ያለው ኢየሱስ ማን ነው? የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ይመልሳል። መልሱ በትምህርቶቹና በተዓምራቶቹ ውስጥ እንዲታይ ተደርጓል። በተደጋጋሚ ክፉን አሸንፏል፣ ለተጨቆኑት ተስፋን አምጥቷል፣ ወደ ሰብአዊ ዘር የኑሮ እምብርት ዘልቀው የሚገቡ አሳማኝ እውነቶችን አስተምሯል፡ ይህ ሁሉ ለአንባቢው ኢየሱስ የዕብራውያን ሕዝብ ለረዥም ጊዜ ሲጠብቁት የነበረ መሲህ፣ ክርስቶስ መሆኑን ጮክ ብሎ ይናገራል። ነገር ግን አንድ በአጋንንት ያልተያዘ ሰው የመጽሐፉን አጋማሽ እስኪደርስና ከዚህም የተነሣ የመጽሐፉ የመጀመሪያው አጋማሽ ስለ ክርስቶስ ማንነት የሚያነሳውን ጥያቄ እስኪመልስ ድረስ እርሱ ማን እንደሆነ በትክክል መናገር አይችልም። “አንተ ክርስቶስ ነህ” ብሎ ያወጀው ያ ሰው ጴጥሮስ ነው(ማርቆስ 8:29)። የማርቆስ መጽሐፍ ሁለተኛው አጋማሽ ከማርቆስ 8፡31 እስከ መጽሐፉ መጨረሻ ያለው ክፍል ሲሆን ኢየሱስ ወዴት እየሄደ ነው? የሚለውን ሌላኛውን ጥያቄ ይመልሳል። መልሱ አስደንጋጭ ነው። በሮም ዓለም እጅግ አዋራጅና አሳፋሪ ወደ ሆነው ወደ መስቀል ሞት እየሄደ ነበር። ሮምን አሸንፎ እሥራኤልን ኃይለኛ ሕዝብ አድርጎ ይመሰርታል ብለው ለሚያስቡ ተከታዮቹ የመሲሁ መዳረሻ በፍጹም ያልተጠበቀ ነበር። ግራ የተጋቡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እርሱ ይናገር የነበረውን ነገር መረዳት አልቻሉም ነበር። መጽሐፉ ወደ ፊት እየቀጠለ ሲሄድ ስለዚህ የሚያም ርዕስ ማንሳታቸው እየቀነሰ የሄደ ሲሆን በመጨረሻም በዚህ የማይወደድ እውነት ፊት ዝም ወደማለት ደርሰው ነበር። ኢየሱስ ስርዓተ ቀብሩን ለመፈጸም የሚዶልቱ የኃይማኖት መሪዎችን ሲጋፈጣቸው ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተስፋ አስቆራጭ ይመስሉ ነበር። ባለግርማ የሆነ መንግሥትን ተስፋ ያደርጉ የነበሩ ደቀ መዛሙርት ከጠበቁት በተቃራኒ እርሱ ሲያዝ፣ ወደ ፍርድ ሲቀርብና ሲሰቀል እጅግ ደንግጠው ነበር። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ኢየሱስ ወዴት እየሄደ እንደሆነና እርሱ ሙቶ ከሙታን መነሳት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልጽና ዘለቄታ ያለው መልእክት እያስተላለፈ ነበር። የመጨረሻው እራት እንጀራና ጽዋ አካሉንና ደሙን የሚወክል ሲሆን (ማር. 14፡22-25) እርሱ ለብዙዎች ቤዛ ይሆናል (ማር. 10፡45)። ይህ ማለት እርሱ ወደ መስቀል የሄደው ስቃዩን በማይገልጽ ጸጥታ ነው ማለት አይደለም። በጌተሰማኔ ከውሳኔው ጋር ትግል ያደረገ ሲሆን (ማርቆስ 14፡ 32-42) በመስቀል ላይ ተስፋ በመቁረጥ “ አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውከኝ?” ብሎ ጩኾአል (ማር. 15:34)። የማርቆስ ወንጌል ክርስቶስ የተለማመደውን ጨለማና ድነታችን ያስከፈለውን ዋጋ ያሳየናል። ነገር ግን መስቀል የጉዞው መጨረሻ አይደለም። ከትንሣኤው በኋላ በገሊላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት አቀደ። እንደምናውቀው ከዚህ የተነሣ የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ተጀመረ። ከወንጌል ጸሐፊው ከራሱ ምንም ተጨማሪ ሀሳብ ሳያካትት በአጭሩ እና ፈጣን እንቅስቃሴ በሚታይበት ዘይቤ የተነገረ እጅግ አስደናቂ ታሪክ ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስን ሕይወትና ሞት በተመለከተ ዝም ብሎ ታሪኩን በመንገር ቃላቶቹ፣ ሥራዎቹና ተግባሮቹ ለራሳቸው እንዲናገሩ ትቷል። ቶማስ አር ሼፔርድ (ፒ ኤች ዲ) በአንድሪውስ ዩኒቨርሲቲ ባለው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሰሚናሪ ውስጥ የአዲስ ኪዳን አንጋፋ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው። እሳቸውና ባለቤታቸው ሼሪ ሁለት ጎልማሳ ልጆችና ስድስት የልጅ ልጆች አሏቸው። @BiruhSoft
نمایش همه...
3
ካነበብኩት አንድ አባት የ11 አመት ልጁ ሲያለቅስ ተመለከተ። እንዲህ ሲልም ጠየቀዉ። "ምን ሆንክ ልጄ?" ልጁም "ሀብታም የክፍል ጓደኞቼ እየተሳለቁብኝ ፣እያሾፉብኝ ነዉ፣ የቆፋሪ ልጅ ብለው ይጠሩኛል፣ ደሃ መሬት ቆፋሪ እያሉ በክፍል ዉስጥ ይናገሩኛል።" አለዉ አባትየው ለአፍታ ቆም አለና። "ልጄ ከእኔ ጋር ና፣ አበባ እንተከል። ደስ የሚል ጊዜ ታሳልፋለህ አለዉ።" እጁን ይዞ ወደ አትክልቱ ቦታ አመሩ፣ ከዚያም ጥቂት የአበባ ዘሮችን አውጥቶ እንዲህ አለዉ። "እስኪ ለሁለት አንድ ሙከራ እናድርግ። ሁለት አበቦችን ለየብቻ እንትከል። አንዱን እንከባከባለሁ፣ ሌላውን ደግሞ ትንከባከበዋለህ፣ የእኔን ከሐይቁ ንጹህ ውሃ አጠጣለሁ፣ አንተ ግን የአንተን ከኩሬው በቆሸሸ ውሃ ታጠጣለህ። ውጤቱን በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ እናያለን" አበቦቹን ከአባቱ ጋር ሆኖ በመትከሉ ልጁ ተደስቶ ነበር። በመጨረሻ የአበባው ዘር ለመብቀል ጥቂት ቀናት ወሰደባቸዉና በቅደም ተከተል የሚያስፈልገዉን እየሰጡ ይንከባከቧቸው እና ሲያድጉ ይመለከቷቸዋል። በኋላም አባት ልጁን ወደ አትክልቱ ስፍራ አምጥቶ እንዲህ አለው። "ሁለቱን አበቦች ተመልከት እና አስተውለህ ንገረኝ" ልጁም መለሰ። "የእኔ አበባ ካንተ የተሻለ እና ደህና ትመስላለች ። የምታጠጣዉ ውሃ ንፁህ ሆኖ ሳለ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ?" አባትየው ፈገግ አለና እንዲህ አለ። "ምክንያቱም ቆሻሻ ውሃ አንድን ተክል እንዳያድግ አያግደውም ይልቁንም እንዲያብብ እንደ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ ሆኖ ያገለግላል። አየህ ልጄ፣ በህይወትህ ውስጥ የማያስቀምጡህ፣ በህልምህ የሚሳለቁብህ፣ ቆሻሻ የሚጥሉብህ ሰዎች አሉ። ምንጊዜም በአንተ ላይ ምንም ችግር እንደሌለው አስታውስ። ስለዚህ፣ ከሰዎች የሚሰነዘሩ መጥፎ ቃላት እንዲነኩህ አትፍቀድ፣ ይልቁንም፣ የተሻለ ሰው እንድትሆን ያበረታታህ። ይህንንም ስታደርግ እንደ ተክሉ ትሆናለህ እናም በቆሻሻ መካከል ዉብ እና የተወደድክ ሆነህ ትበቅላለህ።" አለዉ።
نمایش همه...
👍 6
⭕️ አማላጅነት የሚለው ሀሳብ በመፅሐፍ ቅዱስ ምን ትርጉም አለው ? ❗️እኛን ለማማለድ ብቁ የሆነው አካል ማን ነው? ⭕️ማነው የሚማለደው? ❓ ማንስ ነው የሚማልደው? 🛑ለማንስ ነው የሚጠይቀው? ❓ምንድነው የሚጠየቀውስ? 🔎 እነዚህና መሠል ተያያዥ ሀሳቦች ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር በጥልቀት የተዳሰሱበትን የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት እንድትመለከቱ ለሌሎችም እንድታጋሩ እንጋብዛችኋለን ! https://youtu.be/ID-up7juBI4?si=7vnEenKs8vDYB1HM #Yekaluamdoch
نمایش همه...
የቃሉ ዐምዶች ፱ኛ ትምህርት፡ አማላጅነት

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርሃ ግብር በፍኖተ ብራና አገልግሎት (Living Parchment Ministry (LPM)) በየሳምንቱ እሁድ በ7 ሰዓት በድጋሚ ረቡዕ ቀን በ8 ሰዓት እንዲሁም ማክሰኞ ምሽት በ2 ሰዓት እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው። ፍኖተ ብራና አገልግሎት ከዚህ ሳምንታዊ ጥናት በተጨማሪ “ጊዜው” የተሰኘውን መጽሔት የሚያዘጋጅ ሲሆን እስካሁን የታተሙትን መጽሔቶች እዚህ (

https://www.giziew.org/)

ላይ ማግኘት ይቻላል። በቀጣይ ባሉት ሳምንታት ዘለግ ላለ ጊዜ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን። በዚህ ውይይትም ሆነ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዮች እንዲብራራ ወይም እንዲመለስ የሚፈልጉት ጥያቄ ካለ በሚከተሉት አድራሻዎች በአንዱ ሊያደርሱ ይችላሉ፤ ስልክ፡ 0949-61 11 11 | 0717-96 43 73 ቴሌግራም፡ @giziew7 ፌስቡክ፡ fb.me/giziew7 ኢሜል፡ [email protected] YouTube: @Giziew ድረገጽ: giziew.org (

https://www.giziew.org/)

“ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም” ማርቆስ 13፡33። #pillarsoffaith #28fundamentalbeliefs #Intercession

    የማይጠገብ ብፌ      " እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። መዝሙረ ዳዊት 34 : 8       ካልቀመስናቸው ጣዕማቸውን ልናውቃቸው የማንችላቸው ነገሮች ብዙ አሉ። አንድን ነገር ጣዕሙን ለማወቅ መቅመስ የተፈጥሮ ህግ ነው። የማርን መጣፈጥ ለማወቅ የሬትን መምረር መቅመስ ያስፈልጋል። ኃጢአትን፣ በደልን፣ ክፋትን፣ አመንዝራነትን፣ ዘፋኝነትን ያወቅነው ሰይጣንን ቀምሰነው ነው። አዎ ሰይጣን የሚቀመስ ነው ጣዕሙ ግን እንደ ሬት መራራ ነው።       እግዚአብሔር የሚቀመስ አምላክ ነው። አንድን ነገር በመመኘት ብቻ ጣዕሙን ልናውቀው አንችልም። ሰዎች ቀምሰው ሲያጣጥሙት አይተን እኛ ልንረካ አንችልም። እግዚአብሔርን ልንቀምሰው ይገባል። ጣዕሙ ከማር በላይ ጣፋጭ ነው።        የእግዚአብሔር ጣዕም የማያልቅ ብፌ ሆኖ ዘወትር በፊታችን የቀረበ ነው። ፍቅሩ፣ ምህረቱ፣ ቸርነቱ፣ መልካምነቱ፣ ይቅርታው፣ በጎነቱ፣ ፈውሱ፣ በረከቱ ሁሉ በፊታችን የተንጣለለ ገበታ ነው።         ወዳጆቼ የትኛውም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል የማይሰጠን የተሰናዳ ብፌ እግዚአብሔር ነው። ሰው የሚወደውን ምግብ ነው መርጦ ከብፌ የሚያነሳው ነገር ግን ወዶ ባነሳው ምግብ ሊታመም ይችላል። እንዴት? ካልከኝ ዝሙትን ፈፅሞ ሰው በኃጢአት በሽታ ይታመማል፤ ሰው ገድሎ በፀፀት ቁስል ይመታል ምክንያቱም ከሰይጣን ብፌ መርጦ ያነሳው በመሆኑ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ተጓዳኝ ችግር በሽታ የሌለበት የዘላለም ምግባችን ነው። ምህረቱን ዕለት ዕለት ባንቀምሰው መች የዛሬ ሰው እንባል ነበር? ምህረቱ የመቆማችን ምስጢር ነው። ፍቅሩ ከአራዊትነት የለየን ሰዎችንም ራሳችንንም ወደን እንድንኖር ያደረገን የህይወት ቁልፍ ነው። ቸርነቱ እንደኛ ብኩንነት በአንድ ቀን የምንጠፋውን ደግፎ ያቆመ ምርኩዛችን ነው። ይቅርታው የእንደገና እድል የሚሰጠን መሀሪያችን ነው።     ወዳጆቼ ህይወት የመረረባችሁ ጣዕሙ የጠፋባችሁ፤ መድከማችሁ ፍሬ አልባ የሆነባችሁ፤ ተግባራችሁ ውሉ የጠፋባችሁ፤ እርካታ ከህይወታችሁ የተሟጠጠባችሁ፤ ደስታ የራቃችሁ ሁላችሁ እግዚአብሔርን ቅመሱት ህይወታችሁ ትጣፍጥላችሁ፤ ወደ ማዕዱ ቅረቡ ተቋደሱት ነፍሳችሁ ትማረክላችሁ። ከእግዚአብሔር መፆም አንችልም ፆም የለውም። በማለዳም በቀትርም፤ በምሽትም በሌሊትም የምንመገበው የሰላማችን ብፌ ነው።     አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፦        ስለበዛልን ምህረትህ፣ ስለበዛልን ማዳንህ፣ ስለበዛልን ትድግናህ፣ ስለበዛልን ባርኮትህ፣ ስለበዛልን ቸርነትህ፣ ስለበዛልን ፍቅርህ፣ ስለበዛልን ጥበቃህ ተመስገን። የማትጎድል መሶባችን ሆነህ አጥግበኸናል፤ የማታልቅ ወይናችን ሆነህ ተጎንጭተንኻል ስለዚህም ተመስገን። ስለማይጠልቅብን መልካምነትህ በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናመሰግንሀለን።                @Biruhsoft
نمایش همه...

4👍 2
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤... " ኤር 6: 16። 🎉🎉መልካም ሰንበት ይሁንልን ።🎉🎉🎉
نمایش همه...
👍 8 4
ሁላችሁም ከጎነ ናችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
نمایش همه...
👍 3
ለተፈጠረውና በአንድ ቦታ ባለመገኘታችን ይቅርታ እየጠየቅን ባለፈው በአድስ ሁኔታ ነገሮች አደራጅተን እንጀምራለን እንዳልነው እንቀጥላለን ። አዳዲስ ነገሮችንም ለማስገባት የተለያዩ በመንፈሳዊ ዙርያ የሚሰሩ አስተዳዳሪዎችን የሚንጨምር ይሆናል ።  ስለተፈጠረው አሁን ከልብ ይቅርታ ። አዲሱ ሰንበት ትምህርት በቅርቡ ተዘጋጅቶ ወደ እናንተ ይደርሳል ። 🎉🎉ተባረኩልኝ ብሩህ ምሽት 🎉🎉
نمایش همه...
5👍 2
ለተፈጠረውና በአንድ ቦታ ባለመገኘታችን ይቅርታ እየጠየቅን ባለፈው በአድስ ሁኔታ ነገሮች አደራጅተን እንጀምራለን እንዳልነው እንቀጥላለን ። አዳዲስ ነገሮችንም ለማስገባት የተለያዩ በመንፈሳዊ ዙርያ የሚሰሩ አስተዳዳሪዎችን የሚንጨምር ይሆናል ። ስለተፈጠረው አሁን ከልብ ይቅርታ ።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.