cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የግብጽ ፓትሪያሪክ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ያስተማራቸውን ግሩም መንፈሳዊ ትምህርቶችን በዚህ ቻናል በሰፊው ያገኛሉ ። እንዲሁ የተለያዩ ዝማሪዎችን ስበከቶችን በተጨማሪ የምናቀርብ ይሆናል ። ቤተሰብ ይሁኑ !

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
236
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+1230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
✝️ እንኳን አደረሳችሁ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81 ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ) 4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ 2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል 3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ 5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ 6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ 7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ 8፡ ጉባኤ ሰማዕታት
✝️ ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::
نمایش همه...
1
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ ❶ በሚስጢረ ንስሀ ውስጥ የተነሳሂ ድርሻ ምንድን ነው? ሀ, መዘጋጀት ለ, የተፀፀተ ልብ ሐ, ቀኖና መስጠት መ, ሀ ና ለ መልስ ናቸው ❷ በንስሀ ከሚገኙ ፀጋዎች መካከል አንዱ ነው? ሀ, ከእግዚአብሔር መራቅ ለ, ሰላም ማግኘት ሐ, የሀጢያት ስርይት ማግኘት መ, ለ ና ሐ መልስ ናቸው ➌ ቁርባን የእብራይስትና የሱርት ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ስጦታ ማለት ሲሆን በግዕዝ ትርጉሙ ምን ይባላል? ሀ, አማሀ ለ, እጅ መንሻ ሐ, መቅረብ መ, ሁሉም ❹ የቤተክርስቲያን አሰራር አይነቶች ምን ምን ናቸው? ሀ, ሰቀላማ ለ, ክብ ሐ, ዋሻ መ, ሁሉም ❺ ቤተ-ንጉስ በመባል የሚታወቀው የቤ/ክ አሰራር የቱ ነው? ሀ, ሰቀላማ ለ, ክብ ሐ, ዋሻ መ, መልስ የለም ❻ ከሚከተሉት ውስጥ ጉልላት የሌለው የቤ/ክ አሰራር የቱ ነው? ሀ, ዋሻ ለ, ክብ ሐ, ሰቀላማ መ, ለ ና ሐ መልስ ናቸው ➐ ንጉስ ሰሎሞን ከሰራው ቤተ-መቅደስ የተወሰደ የቤ/ከ አሰራር የቱ ነው ሀ, ሰቀላማ ለ, ክብ ሐ, ዋሻ መ, መልስ የለም ➑ የመስቀል አይነቶች ከአገልግሎት አንጻር በስንት ይከፈላል? ሀ, በ 3 ለ, በ 4 ሐ, በ 5 መ, በ 2 ❾ መስቀል ከሚሰራበት ቁስ አንጻር በስንት ይከፈላል? ሀ, በ 3 ለ, በ 4 ሐ, በ 5 መ, በ 2 ❿ ሰራዊው ዲያቆን ክቡር ደሙ ለቆራቢያን የሚያቀብልበት ንዋይ ቅድሳት ምን ይባላል? ሀ, ምስዋዕ ለ, ጻህል ሐ, እርፈ መስቀል መ, አውድ ➊➊ ከሚከተሉት ንዋየ ቅድሳት መካከል የቅዱሳን መላዕክት ምሳሌ ነው ሀ, ማገር ለ, ጉልላት ሐ, ምሶሶ/አእማድ መ, ጉበን ❶❷ ከሚከተሉት ንዋየ ቅድሳት መካከል የቤተልሔም ህጻናት ድምጽ ምሳሌ ነው ሀ, የጣሪያው ዙሪያ ሻኩራዎች ለ, ቤተ-መርፋቅ ሐ, የተጠረቡ ድንጋዮች መ, ቤተልሔም ❶❸ የሚከተሉት የቤተ-መቅደስ ንዋየ ቅድሳት ናቸው ሀ, ታቦት ለ, መንበር ሐ, ፅዋ መ, ሁሉም ❶❹ ከሚከተሉት ንዋየ ቅድሳት ውስጥ የእመቤታችን ምሳሌ ናቸው ሀ, ፃህል ለ, ፅዋ ሐ, አውድ መ, ሀ ና ለ መልስ ናቸው ❶❺ ከሚከተሉት መካከል አትሮንስ የምን ምሳሌ ነው? ሀ, የእመቤታችን ለ, የጌታችን ሐ, የሐዋርያት መ,የሰማዕታት
نمایش همه...
👍 2
🛑👉 #የሰኔ ፆም 2016 #ጾመ_ሐዋርያት →#መቼ_ይገባል ? ```````````````````````````````````````````````````` 🔵👉ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን የሥጋ ፍላጎት ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ብሎ መተው ማለት ነው። 🔴👉ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚየሰጥ ነው፡፡ 🔵👉ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ 🔴👉ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ በየትኛውም አመት ላይ ቢውሉ ሰኞ ቀን ከሚጀምሩት አፅዋማትም አንዱ ነው፡፡ 🔵👉ይህም ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል ያሁኑም ጾም ሰኔ 17 ይገባል፡፡ ! #ሐዋርያት መቼ_ጾሙ? ! 🔴👉ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡ 🔵👉ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ በጌታችን አስቀድሞ ትንቢት የተነገረለት ቀን የተቆጠረለት ምላሴ የተመሰለለት ታላቅ ፆም ነው። 🔴👉ይህስ እንደምን ሆነ ቢሉ :- የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር። << እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› 9 9:15-16 ! #የሰኔ_ጾም_የቄስ_ብቻ_ነውን? ! 🔵👉ይህ ጥያቄ ከብዙ ሰዎች ዘንድ የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምዕመናን የሰኔን ጾም አይፆሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ ታላቅ የበረከት ጾም ነው፡፡ 🔴👉ዛሬ ዛሬ ግን ብዙ ሰዎች ትተውት ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም 🔵👉እኛ ይህንን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን <<መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡ ! #እንዴትና_ከምን_እንጹም? ! 🔴👉የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኋይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅ ታዟል። 🔵👉ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙር 109፥24 ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ ብላል ። ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም። 🔴👉ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከፀሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ ያሠጣልና በጸሎት በመትጋት በስግድት ወደ እግዚአብሔር በፍፁም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ይህን ጾም ባርኮልን የቅድስና ሥራን የምናበዛበት ያድርግልን አሜን🙏፡፡ ✍️ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም ግንቦት 26/2016 ዓ.ም
نمایش همه...
👍 2
#ግንቦት_28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ስምንት በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ዓለምን ንቃ የተወች #ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ አረፈች፣ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም #አባ_መርቆሬዎስ አረፈ፣ #የቅዱስ_ኤጲፋንዮስ ሥጋ ወደ ቆጵሮስ ደረሰ፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን አባ #ጌርሎስና_አርባ_አምስቱ_ልጆቹ በሰማዕትነት አረፉ፣ ደግሞም የከበሩ አባቶች የ #አብርሃም የ #ይስሐቅና የ #የያዕቆብ መታሰቢያቸው ነው፣ ደግሞም በዚህች ዕለት የአባ #ስንጣ የሰማዕት #አጋቦስ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸው ይደርብን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ ግንቦት ሃያ ስምንት በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ዓለምን ንቃ የተወች አባ ዳንኤል ስለርሷ እንደተናገረ የዓለምን ፍላጎት ሁሉ ድል የነሣች ቅድስት አመተ ክርስቶስ አረፈች። ሀገሯ ልዩ ስሙ ተጉለት ሲሆን በተጋድሎዋ በእጅጉ ትታወቃለች፡፡ መጽሐፍ ተሐራሚት ገዳማዊት ይላታል፡፡ በበረሃ ውስጥ በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ 38 ዓመት ብቻዋን ማንም ሳያያት የኖረች ታላቅ እናት ናት፡፡ አባ ዳንኤል ስለርሷ እንዲህ አለ በበረሀም ሳለሁ በሌሊት ተነሥቼ በጨረቃ ብርሃን ተጓዝኹ በተራራ ላይ የተቀመጠ ሰውንም አየሁ ጠጉሩም ሁለመናውን ሸፍኖታል በልቤም ወደርሱ ሔጄ ይህ ምን እንደሆነ ልወቅ ብዬ ወደርሱ ሔድሁ። በአየችኝም ጊዜ ወደ ተሠነጠቀ አለት ውስጥ ገባች ሰው እንደሆነ አውቄ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ አልሁ እጅግም አብዝቼ ለመንሁ። ከዚህም በኋላ አባት ሆይ አልወጣምና ይቅርታ አድርግልኝ አለችኝ። ስለምን አልኋት እኔ ሴት ነኝ ራቁቴን ስለሆንኩ አለችኝ። ይህንን ሰምቼ የለበስኩትን ዐጽፍ ጣልሁላት ለብሳም ወጣች በአንድነትም ጸለይን። ከዚህ በኋላ እናቴ ሆይ ከዓለም ወደዚህ ስለመውጣትሽ ይኸንን የተሠነጠቀ ዐለት እንዴት እንዳገኘሽ ንገሪኝ አልኋት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችልኝ በወላጆቼ ቤት ድንግል ሁኜ በኢየሩሳሌም የምኖር ነኝ ሁል ጊዜ የሚጎበኘኝና ከእኔ ጋራ የሚነጋገር አንድ መነኰስ ነበረ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ወደርሱ ሔድኹ በእግዚአብሔር ፊትም ኃጢአቱን እየታመነ ሲአለቅስ አገኘሁት። ደጁንም በአንኳኳሁ ጊዜ አልከፈተልኝም እየተጸጸተ ልቅሶን አበዛ እንጂ። በዚያን ጊዜ በልቤ እንዲህ እልኩ እኔስ ስለ ጕስቊልናዬና ስለ ኃፍረቴ የማላለቀስና የማልጸጸት ለምንድነው ወደ ማደሪያዬም ፈጥኜ ሔድኹ ማቅ ለበስኩ በዘንቢልም ሽምብራ በጽዋ ውኃን ያዝሁ። በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዘንድ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ አቤቱ ጽኑዕ ኃያል ለዘላለሙ ድንቅ የሆንክ የጠፉትን የምታድን የወደቁትንም የምታነሣቸው ወደ አንተ የሚጮኹትንም የምትሰማቸው የታመነችብህ ባሪያህን ታድናት ዘንድ ይቅርታህንና ምሕረትህን ላክ። ከምግባር ድኃ የሆንኩ ባሪያህን ጐብኘኝ ንስሓዬንም ተቀበል። ለረጅም ዘመን ስንቅ ይሆነኝ ዘንድ ይህን ሽምብራና ይህን የጽዋ ውኃ ባርከው ስለ ነፍሴ ድኅነት የአሰብኩትን እንዳላቃልል ለሆዴ ምግብ ስለሚአሻኝ። ከዚህ በኋላም ነፍሴን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ወጥቼ ወደ በረሀ ሔድኹ እስከ ኤርትራ ባሕርም ደረስኩ። ከዚያም ወደዚህ በረሀ መጥቼ ይህን የተሠነጠቀ ዐለት አገኘሁ ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ ነው አልሁ። እነሆ በዚህ በረሀ ውስጥ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነኝ ያለ አንተ ሰው አላየሁም። ይህም የዘንቢል ሽምብራና የጽዋ ውኃ ሠላሳ ስምንት ዓመት ከእሳቸው ስመገብ አልጐደሉም ልብሴ ግን አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ስለ ልብስ መከለያ ሆነኝ። የበጋ ፀሐይ ትኩሳትም አላስቸገረኝም ቁር ቢሆንም በዕድሜዬ ዘመን ሁሉ አላስጨነቀኝም። ከዚህ በኋላም ከዘንቢል ካለው ሽምብራ እንድመገብ ማለደችኝ ከሽምብራውም በላሁ ከውኃውም ጠጣሁ። ግን አልጎደለም እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ልብሴንም ልተውላት ወደድሁ እርሷም ከዚህ የተሻለ አምጣልኝ ብላ ይህን እምቢ አለችኝ። ከዚህ በኋላም ከእርሷ ዘንድ ሔድኩ ወደ ገዳም ደርሼ ስለርሷ ለአበ ምኔቱ ነገርኩት። እርሱም ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው አንዱን ይስጥ ብሎ ጮኸ ፈቃደኞች የሆኑም አመጡለት ያን ጊዜም ይዤ ሔድኩ ለአመተ ክርስቶስ ልስጣት ብዙ ደከምኩ እርሷን በመፈለግ ዞርኩ አላገኘኋትም። ከጥቂት ቀኖች በኋላም አረጋውያን ወደ እኔ መጡ እንዲህም አሉኝ ወደ ኤርትራ ባሕር የሚያደርሰውን መንገድ ይዘን በጣኔዎስ በረሀ ስንጓዝ ከዋሻ ዘንድ ሴት ተቀምጣ አይተን ከእርሷ በረከት ለመቀበል ሮጥን ሸሽታ ከዋሻው ገባች ወደ ዋሻውም አፍ ቀረብን ግን አላየናትም። ሽምብራ በዘንቢል ውኃም በጽዋ አግኝተን በላን ጠጣን ያን ጊዜም አለቀ እስከ ንጋትም አደርን። በነጋም ጊዜ በረከቷን ለመቀበል ቅድስቲቱን ፈለግናት ሙታም አገኘናት ጠጉሯም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል። በዚያም ሰገድን በበዓቷም ውስጥ ቀበርናት የዋሻውንም አፍ በደንጊያ ዘጋን የቅድስቲቱን በረከት እንድንቀበል አድሎናልና እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደ በዓታችን ገባን። በሰማሁም ጊዜ አስቀድሜ ያገኘኋት እንደሆነች አወቅሁ የነገረችኝንም ሁሉ ነገርኳቸው። ጠላት ዲያብሎስን ድል ያደርገው ዘንድ ክፉዎች አጋንንትንም ደካማውን ድኃ የሚረዳ የተመሰገነ እግዚአብሔርን ፈጽመን አመሰገን ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_መርቆሬዎስ_ገዳማዊ በዚችም ዕለት ከአባ ጳኵሚስ ገዳም አባ መርቆሬዎስ አረፈ። እንጦንዮስም እንዲህ አለ ለእኔ ገዳም አለኝ ይኸውም የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ እያሉ ወደእኔ መነኰሳት የመጡበት ነው እኔም በረከቱን ለመቀበል ወደርሱ በሔድኩ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመሥጦ ላይ አገኘሁት። ከመነኰሳቱ ጋራ በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶች ኖርን በሦስተኛዪቱም ዕለት ነፍሱ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ በአየንም ጊዜ ከእኔ ዘንድ ምን ሰበሰባችሁ አለን። እኛም የሆነውን ሁሉ ነገርነውና ከዚህም በኋላ ያየውን እንዲነግረን ለመንነው እርሱም የሚአስፈራ ሰው ወደርሱ መጥቶ ነፍሱን እንደወሰደ የኃጥአንን ሥቃይ እንዳሳየው የጻድቃንንም ዋጋቸውንና ተድላቸውን እንዳሳየው ነገረን። ከዚህ በኋላ ወዮ ብሎ በማልቀስ በግምባሩ ከምድር ላይ ተደፋ እንዲህም አለን ወንድሞቼ ሆይ ወደ ሐራጺት ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ማደሪያ ሒዱ። ከእኔ ጋራ የነበረውን መልአክ መርቆሬዎስን መልሳችሁ በትንሽ በዓት ውስጥ ሲጋደል የኖረ ጊዮርጊስን አምጡት ሲል ሰምቼዋለሁና ይቺም ሥጋው እስቲቋጠር የተጋደለባት የጨው በረሀ ናት። ወንድሞች መነኰሳትም በሔዱ ጊዜ ሙቶ አገኙት ወደዚህ ገዳምም አምጥተው ቀበሩት። ይህም ወንድም መርቆሬዎስ እንደ ደረቀ እንጨት እስቲሆን ሥጋውን እጅግ አሠቃየ። ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም ይሔድ ዘንድ ተሰናበተኝ። ደግሞ ግንቦት ሃያ ስምንት ቀን ወደኔ ና ታገኘኛለህና አለኝ። በቀጠረኝም ቀን ወደርሱ ሔጄ አገኘሁትና እኔ ወደ አባቶቼ እሔዳለሁ። ወደ አንተም ሦስት አጋዘኖች ይመጣሉ ሥጋዬንም በጀርባቸው ላይ ጫን እነርሱም ወደ ቦታዬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይመሩሃል። በዚያም በማደሪያዬ ውስጥ ድፈኑኝ አለኝ። እንደ ቃሉም ሆነለት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ኤጲፋንዮስ በዚህችም ዕለት የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥጋ ወደ ቆጵሮስ ደረሰ። ይህም እንዲህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ መንበረ ሢመቱ እንደማይደርስ ትንቢት እንደተናገረበት ወደ ቆጵሮስ ሳይደርስ በመርከብ ውስጥ ሳለ ግንቦት ዐሥራ ስድስት ቀን አረፈ።
نمایش همه...
Repost from N/a
፲፫` ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?Anonymous voting
  • የክርስቶስ ተከታይ
  • ክርስቶሳዊ
  • መዐዛ ክርስቶስን የሚሸት
  • ሁሉም
0 votes
Repost from N/a
፲፭` ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው ❓Anonymous voting
  • የፀጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
  • የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
  • የአስተብርኮ ስግደት
  • ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም
0 votes
Repost from N/a
፲፬` እመቤታችን በቤተ መቅደስ የኖረችው ለስንት ዓመታት ነው ❓Anonymous voting
  • ፲ ፪ ዓመታት
  • ፫ ዓመት ከ፫ ወር
  • ለ፫ ዓመታት
  • ለ፲ ፭ ዓመታት
0 votes
Repost from N/a
፲፮` የቅዱሳ መላዕክት አገልግሎት ያልሆነው የቱ ነው❓Anonymous voting
  • ማማለድ (መለመን)
  • ማበርታት ፣ማጽናናት
  • መቅጣት
  • ሁሉም
0 votes
Repost from N/a
፲` ከእመቤታችን የዘር ሐረግ ውስጥ የማይካተተው ነገድ የቱ ነው❓Anonymous voting
  • ነገደ ሌዊ
  • ነገደ ይሁዳ
  • ነገደ ዳን
  • ሀ እና ለ መልስ ይሆናሉ።
0 votes
Repost from N/a
፱` ከሚከተሉት መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?Anonymous voting
  • ለመዳን ምግባር ብቻውን በቂ ነው።
  • ሃይማኖት መሠረት ምግባር ደግሞ ጣራ ግድግዳ ነው።
  • ሃይማኖት ብቻውን ለመዳን በቂ ነው።
  • ሁሉም መልስ ናቸው።
0 votes
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.