የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
رفتن به کانال در Telegram
1 411
مشترکین
+224 ساعت
+257 روز
+8530 روز
آرشیو پست ها
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፤ እያለ መልካም ምኞቱን ሲገልፅ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር አላህ ለመልዕክተኛው መርጦ ያላበሳቸውን መልካም ስነምግባራት በመላበስና ለሌሎችም አርዓያ በመሆን ሱናቸውን (ፈለጋቸውን) ሕያው በማድረግ መርህ ሊሆን ይገባል
መልካም በዓል
1 411
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል።
ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር። በውስጥ ፈተና በውጭ ጫና ነበረብን። ከፈጣሪ ጋር የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚህ ደርሰናል። ነገር ግን የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም። በቀጣዩ ጊዜ ያቀድነውን አጠናቅቀን ፈጣሪን እንደምናመሰግን እምነቴ ነው። ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።
1 411
ባለሥልጣኑ ለቡድን መሪና በላይ ላሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፤
***
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ሰልጣንና ተግባር በብቃት በመፈጸም በግብርናው ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር እየሰራ ሲሆን በሰራዎቹ በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የስራ ሀላፊዎችንና የባለሙያዎችን አቅም በተለያዩ መንገዶች መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑ በማመን በስሩ ላሉ ስራ አስፈፃሚዎች ፣ ደስክ ኃላፊዎችና ለቡድን መሪዎች ከነሐሴ 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ በድሬ ሆቴል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የስልጠናው ዋና አላማ ባለስልጣኑ በሲቪል ሰርቪስ መመሪያ መሰረት በአዲስ የሰራተኛ ድልድል በስራ ልምዳቸውና በትምህርት ዝግጅታቸው መሰረት የሰራተኛ ምደባ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ባለስልጣኑ የተቆጣጣሪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከተለመደው አሰራር በመውጣት ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ መደብ ላይ ውጤታማ በመሆን በአዲስ መንፈስ እና ተነሳሽነት የባለስልጣኑን ተልዕኮ በብቃት ይወጡ ዘንድ አቅምን የሚገነባ ስልጠና ከቡድን መሪና በላይ ላሉ አመራሮች መሰጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ስልጠና የመጀመሪያ ዙር ስልጠና መሆኑንና በቀጣይ ለሁሉም ሰራተኞች በተለያዬ ዙር እንደሚሰጥ አምባሳደር ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለመፈጸም ያቀዳቸውን ስራዎች ከተለመደው አሰራር በመውጣት በተጠያቂነት መንፈስ ስራዎችን በብቃት መፈፀምና ማስፈፀም ተገቢ ስለሆነ ስልጠናውን በንቃት መከታተልና የስራ መመሪያ በማድረግ በቀጣይ ለስራ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አምባሳደር ድሪባ ሰልጣኞችን አሳስበው ስልጠናው ተጀምሯል::
የስልጠና መድረኩ ላይ ስለ ሊደር ሽፕ ምንነት በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በአምባሳደር ድሪባ ኩማ ፣ በቲም ቢውልድንግና ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ በባለስልጣኑ የእንሰሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በዶክተር ሀሚድ ጀማል ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በቀረበው የሰልጠና ርዕስ ላይ መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች ተዘጋጀተው ሰልጣኞች በሁለት ቡድን ተከፍለው እንድወያዩባቸው ተደረጎ የደረሱበትን የውይይት ሃሳብ በየቡድን ተጠሪያቸው ለመደረኩ አቅረበዋል፡፡
በሌላ በኩል የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አሰፈጻሚ በወ/ሮ መሰረት አበባው የባለስልጣኑን የአስር አመት ፣ የሶስት አመት እና የበጀት አመቱን እቅዶች ያቀረቡ ሲሆን እቅዱን እንዴት መፈጸምና ከግብ ማድረስ እንዳለባቸው እንድሁም እቅዱን ለመፈጸም እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ በቡድን በመውያየት የደረሱበትን የውይይት ሀሳብ በተመሳሳይ ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች የተሰጠው ስልጠና ወቅታዊና ለስራቸው በጣም አሰፈላጊ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል ፣ ከቅንጅታዊ አሰራር ፣ የተመደበላቸውን ሀብት በአግባቡ ከመጠቀም አኳያ ፣ ለሌሎች ባለሙያዎች ልምድ በማካፈል ብቁ ባለሙያን ከመፍጠር ፣ ምቹ የስራ ቦታና ሆኔታዎችን በመፍጠርና በተቋሙ ያሉ ባለሙያዎች ለአንድ ዓላማና ግብ እንድሰለፉ ከማድረግ አኳያ ያሉባቸውን ውስንነቶች አንሰተዉ ለችግሮች መፍትሄ በማሰቀመጥ ለተቋማዊ ግንባታ ስራ ያላቸው ሚና ከፈተኛ በመሆኑን በነገንዘብ ከዚህ ሰልጠና በኋላ የሚሰጡ አቅጣጫዎችን በመቀበል በጊዜ የለኝም መንፈስ ፈጥነው ወደ ስራ እንደሚገቡ በመደረኩ ላይ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
የእፅዋት ሪጎላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የተዘጋጀው ስልጠና የእርስ በእርስ መማማሪያና የተግባቦት መድረክ እንደመሆኑ መጠን አቅምን በመገንባት ለሌሎች ባለሙያዎች ያለንን ልምድ በማካፈል ስራዎቻችንን በብቃት መፈጸምና ተቋማችንን የማዘመን ስራ መስራት አለብን በማለት ገልጸዋል፡፡
አቶ ወንዳለ በመድረኩ ለተነሱ ሃሳቦች የመፍትሄ ሀሳብ ያስቀመጡ ሲሆን ከበጀት አንጻር ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ ሁላችንም በመረዳት ያለንን ሀብት በአግባቡ መጠቀምና ያለብንን የበጀት ችግር ለመፍታት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሪሶርስ ለማፈላለግ ዝግጁ መሆን ፣ ውጤታማና ችግር ፈች የሆነ ኤክስቴንሽን እንድኖር በትኩረት መስራት እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተሰጣችሁን ተግባርና ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለባችሁ በማለት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ አቶ ወንዳለ አያይዘውም በቀጣይ የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ የአጭርና የረጅም ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን የማማቻቸት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና አሁን እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የባለስልጣኑን ሁሉም ሰራተኛ ባካተተ መልኩ በአጭር ጊዜ የሚሰጥበት አግባብ እየተመቻቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ለውይይት የቀረቡት ሀሳቦች ሁሉን አካታችና ሁሉም አካል ራሱን ፈትሾ ለተሻለ ስራና ውጤት የሚነሳሳበት ፣ ሁሉም ከጠባቂነት መንፈስ በመውጣት በሚፈጠሩ ችግሮች ከመረታት ይልቅ ለችግሮቻቸው ራሳቸው መፍትሔ የሚያስቀምጡበት አካሄድ መኖር እንዳለበትና ለአንድ ተቋማዊ ዓላማና ግብ እስከተሰለፍን ድረስ ያለንን ሀብት በአግባቡና በፍትሃዊ መንገድ በጋራ በመጠቀም ከግዴለሽነት አሰራር በመውጣት በቅንጅት በመተባበርና በመደጋገፍ በሀላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ ስራን አክብሮ መስራት እንደሚገባ አሳስበው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች አቅም በማሳደግ ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱን የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፉ ገብያ በማቅረብ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፤
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ ብቁ የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎችን በማፍራት የአገሪቱን የሥጋ ምርት ጥራቱ ተጠብቆ ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፉ ገብያ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡ ይሄን ታሳቢ በማድረግ የባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ሄርድ ከተባለ መንግስታዊ ኘሮጀክት ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተውጣጡ ከ 50 በላይ የማዘጋጃ ቤት የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች ቢሾፍቱ በሚገኜው የሚድሮክ ኤልፎራ አግሮ ኢንደስትሪ የሥራ ላይ ሥልጠና ሰጥቷል።
የሥልጠናው ዓላማም የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በማዘጋጃ ቤቶች በኩል የሚካሄዱ እርዶች ጥራታቸው የተጠበቀና የምግብ ደኅንነት ሥርዓቱን መስፈርቶች አሟልተው እንዲሰሩ በማድረግ የምግብ ደኅንነት የአሰራር ሥርዓቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ ነው ያሉት በባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አያሌው ሹመት ባለሥልጣኑ የማዘጋጃ ቤት የሥጋ መርማሪዎችን በመሰል የሥራ ላይ ሥልጠናዎች አቅማቸውን ለማጎልበትና ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር አያሌው አክለውም የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች አቅም በማሳደግ ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱን የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፉ ገብያ በማቅረብ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ዘርፉ ልዩ ትኩረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሥራ ላይ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ውጤታማ ሥራ እንደሚያከናውኑ ያለቸውን እምነት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች ሥልጠናው የስጋን ጥራት ለማስጠበቅና ከዘርፉ የሚገኜውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና ከዘመኑ ጋር እያደገ የሚሄድ የምግብ ደህንነት አመራር ስርዓት በቄራዎች ተፈጻሚነቱንና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ በቅድመ እርድና ድኅረ እርድ ምርመራ በማከናወን እና የቄራዎችን ሐይጅንና ሳኒቴሽን እንዲጠበቅ በመቆጣጠር ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱን የተጠበቀ ለገበያ የሚቀርብ እና ለሰው ምግብነት የሚውል የስጋ ምርት እንዲመረት በማስቻል በኩል ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 70.2 ሚሊየን የቀንድ ከብት፣ 42.9 ሚሊየን የበግ፣ 8 ሚሊየን የግመል እንዲሁም 52 ሚሊየን አካባቢ የፍየል ኃብት እንዳላት መረጃዎች ያመላክታሉ።
1 411
ለሰላም መስፈን እንቅፋት የሆኑ ችግሮች በውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ ተገለፀ፤
*
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞ ጋር ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ/ም በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ወይይት አካሄደ።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን አሁን ባለው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በአማራ ክልል እየታዬ ያለው ቀዉስና አለመረጋጋት መነሻው የህዝቡን ፍትሃዊ የሆነ ጥያቄ በመጥለፍ በኃይል የራስን ፍላጎት ለማስፈፀም የሚደረግ የፀረ -ሰላም ሀይሎች ሙከራ ነው ያሉ ሲሆን በነዚህም ችግሮች ምክነያት በሕዝቡ ላይ የሞት ፣ የመፈናቀል ፣ የሰላም ዕጦት እና በሚጠቀምበት የመሰረተ ልማት ላይ ውድመት ተፈጥሯል:: በመሆኑ ሁላችንም ሰላም አንዲሰፍን ችግሮች በመነጋገር አንዲ ፈቱና ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅና ለሰላም አንቅፋት የሚሆኑ አካሄዶችን በመታገል ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል ፡፡
አምባሳደር አክለውም ለሰላም መስፈን እንቅፋት የሆኑ ችግሮች በውይይት ሊፈቱ ይገባል እንጂ ጦርነት ሰላምን አያመጣም በመሆኑም እኛም ይህንን ባህል አድረገን አገራችን ላይ የሚታዩ ችግሮች በሰለማዊ መንገድ እንዲፈቱ ሁላችንም ጥረት ማደረግ አለብን ብለዋል፡፡
የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሚድ ጀማል በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ በአማራ ክልል ላይ የሚታየውን ግጭትና አለመረጋጋት በተመለከተ ለመንግስት ሰራተኞች የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ ተመስርተው ችግሮች በሰማዊ መንገድ መፈታት አንዳለባቸው ፣ ሁሉም ለሰላም ዋጋ አንድሰጥና ለዚህም ሁሉም በኃላፊነትስሜት ሊሰራ ይገባል ፣ ችግሮች ተባብሰው ወደ ሀይል ከመሄዳቸው በፊት ውይይትና መግባባት ላይ እንድደረስ እና አሁን እየታዬ ያ ለው የሰላም መ ደፍረስ በፍጥነት አንድስተካከል የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናደረግ ይገባል የሚሉ ኃሳቦች አንስተዋል ፡፡
የአማራ ሕዝብ ለረጅም ዘመን ሲያነሳቸው የቆዩ መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉት ያሉት የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ መንግስትም ጥያቄዎቹ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ የሚፈቱበትን አግባብ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ጽንፈኛ ኃይሎች የሕዝቡን ትክክለኛ ጥያቄ በመጥለፍ በክልሉ ግጭትና አለመረጋገት እንድፈጠር ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ወንዳለ አክለውም አሁንም መንግስት ችግሮችን በዉይይትና በመነጋጋር መፈ ታት እንዳለባቸው እንደሚያምን ገልፀው ፣ ነገር ግን ይህ ባለመሳካቱ ችግሩ ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ በመሆኑ መንግስት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ወንዳለ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን በመሰለፍ፣ መልካም አስተዳደር እንድሰፍን፣ የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎችን እና ለግጭት የሚያነሳሱ ንግግሮችንና ጽሁፎችን ከሚያሰራጩ አካላት ራሳችንን በማራቅና እነዚህን አካላት በመታገል እንደ መንግስት ሰራተኛ ለሀገራችን ሰላም መስፈን የድርሻችንን መወጣት አለብን በማለት አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ
ዌብሳይት http://www.eaa.gov.et
ፌስቡክ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣናት /Ethiopian Agricultural Authority /
ቴሌግራም eaa_123
@ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
1 411
በኢትዮጵያ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት በኩል የባለድርሻ ተቋማት ትብብር ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል ተባለ፤
*
በኢትዮጵያ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ባለድርሻ ተቋማት ያላቸውን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር 36ኛው ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የልማት አጋሮችና የሙያ ማኅበራት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ባላት የእንስሳት ኃብት ልክ እንዳትጠቀም ከሚያደርጓት ጉዳዮች መካከል አንደኛው የእንስሳት ጤና ችግር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት ጤና ችግር የወጪ ንግድ ገቢ ላይ አሉታዊ ጫና የማሳደር አቅም እንዳለውም ነው የጠቆሙት፡፡
የእንስሳት ጤና በአግባቡ ካልተጠበቀ፣ የእብድ ውሻ በሽታ እና ኮሶ የመሳሰሉ በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው እንደሚተላለፉም እንዲሁ፡፡
የእንስሳትን ጤና በማስጠበቅ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ጥቅም እንድታገኝ ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም በተለያዩ ክልሎች የእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከማስፋፋት ጎን ለጎን አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶች እንዲሟሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በሽታዎችን ለመከላከል በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የክትባት አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን መደረጉን ጠቅሰው፤ ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የእብድ ውሻ በሽታን ለመከላከል 200 ሺህ ውሾች በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲከተቡ ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም የ"ደስታ" በሽታን በአሥር ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ሥራ መገባቱን ገልፀዋል፡፡
የእንስሳት ጤና እና ደኅንነት አዋጅ ሥራ ላይ ለማዋል እንቅስቃሴዎች መጀመሩ እየተሰሩ ካሉ ሥራዎች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ከእንስሳት ኃብት ተጠቃሚ በማድረግ ሂደት የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችም ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ በኩል ባለሙያዎች ምክረ-ሀሳብ በማቅረብ፣ ከመንግሥት ጋር ተናቦ በመሥራት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ጤና ሐኪሞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ቦጃ እንደቦ በበኩላቸው፤ ማኅበሩ በዓመት ሁለት ጊዜ በጀት በመመደብ ጥናቶችን በማድረግ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት የእንስሳት ጤና አገልግሎት እየተሰጠ ያለው በአብዛኛው በመንግሥት መሆኑን ጠቅሰው፤ በመንግሥትና የግል አጋርነት አሠራር አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ጥናቶችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ከሚሰጠው የእንስሳት ጤና አገልግሎት ውስጥ ምን ያህሉ በመንግሥት እና በግል ጤና ተቋማት ሊሸፈኑ እንዲሁም የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የክህሎት ደረጃ ምን ሊሆን እንደሚገባው በጥናቱ እንደሚዳሰሱም አስረድተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሚሌ ኳራንቲን ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ 7000 በጎች ወደ ሳኡዲ አረቢያ መላኩን አስታወቀ፤
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ወደ ውጭ የሚላኩ የቁም እንስሳቶቻችን ከበሽታ ነጻ መሆናቸው እዚሁ አገራችን ላይ ተረጋግጦ እንዲላክ በማድረግ እንስሳትን በስፋት ወደ ውጭ ለመላክና አገልግሎቱን ለማሻሻል በማሰብ የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ጣቢያን በቅርቡ ሥራ ማስጀመሩ የገለጹት በባለሥልጣኑ የእንስሳት ኳራንቲንና ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰይፉ ኃይሉ ኳራንቲን ጣቢያው ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰርተፊኬት ጤንነታቸው የተጠበቁት 7000 በጎች ወደ ሳኡዲ አረብያ መላኩን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ሰይፉ አክለውም ቀደም ሲል የቁም እንስሳት ወደ ውጭ የሚላከው በጅቡቲ ኳራንቲን በኩል የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን የሚሌ ኳራንቲን በሳውዲ አረብያ በኩል እውቅና ማግኝቱን ተከትሎ ከሚሌ ኳራንቲን ጣቢያ በጁቡቲ ዶራሌ ዘርፈ ብዙ ወደብ በኩል በቀጥታ ወደ ሳኡዲ መላክ መጀመሩን አብራርተዋል፡፡
ባለሥልጣኑ በእንስሳት ዘርፍ የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር ብሎም የንግድ ሥርዓቱን ማዘመንና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ከዘርፉ የሚገኜውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከዚህ በፊት ተቋቁመዉ ስራ ያልጀመሩ እንደጅጅጋ ያሉ ኳራንታይን ጣቢያዎች በቅርብ ስራ የሚጀምሩበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ያሉት ዶ/ር ሰይፉ የሚሌ ኳራንቲን ጣቢያ በቁም እንስሳት ላይ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የእንስሳት ንግድ በመታደግ አገሪቱ በእንስሳት ኃብቷ ልክ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ እና ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢዎን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ከዚህ በፊት ከነበሩት የቁም እንስሳት ኤክስፖርት መዳረሻ ገበያዎቻችን ማለትም ከመካከለኛ ምስራቅ እና ከሰሜን አፍርካ አገራት በተጨማሪ ለአውሮፓ እና ለሌሎች አገራት በመላክ የአገራችንን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በእንስሳት ኃብቷ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ከዓለም የመጀመሪያዎቹ 10 አገራት ተርታ እንደምትመደብ የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ፤
