fa
Feedback
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

رفتن به کانال در Telegram

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

نمایش بیشتر
1 411
مشترکین
+224 ساعت
+257 روز
+8530 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ሁለተኛውን ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ለፈፃሚ ባለሙያዎች ሰጠ፤ **** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ሰልጣንና ተግባር በብቃት በመፈጸም በግብርናው ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር እየሰራ ሲሆን በሰራዎቹ በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የባለሙያዎችን አቅም በተለያዩ መንገዶች መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በማድረግ በስሩ ላሉ ፈፃሚ ባለሙያዎች ከታህሳስ 25/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ኤፍታህ ሆቴል ሁለተኛውን ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡ የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ የተደራጀ እና እየተገነባ ያለ ተቋም እንደመሆኑ መጠን በየደረጃው ያሉ አመራሮችንና ሰራተኞችን አቅም በመገንባት በተመደቡበት የስራ መደብ ላይ ውጤታማ በመሆን በአዲስ መንፈስ እና ተነሳሽነት የባለስልጣኑን ተልዕኮ በብቃት ይወጡ ዘንድ አቅምን የሚገነባ ስልጠና መሰጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ለአመራሮች መሰጠቱን አስታውሰው አሁን እየተሰጠ ያለው 2ኛ ዙር የፈፃሚዎች ስልጠና ይህንኑ ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ወንዳለ አክለውም በበጀት ዓመቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቀዳቸውን ተግባራት በውጤታማነት ለመፈፀም በተጠያቂነት መንፈስ በመደጋገፍና በመተባበር ተግባራትን በብቃት መፈፀም ተገቢ ስለሆነ ስልጠናውን በንቃት መከታተልና የስራ መመሪያ በማድረግ በቀጣይ ለስራ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ ቲም ቢውልድንግ እና ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ በሚሉ ርዕሶች ላይ ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣን መ/ቤታችን የእንሰሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሚድ ጀማል ሲሆኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አሰፈጻሚ ወሮ መሰረት አበባው ደግሞ ስለ ስትራቴጅክ ምንነት እና የባለስልጣኑን የአስር አመት እቅድን ለስልጠና ተሳታፊዎች አቅርበዋል:: በመጨረሻም በቀረቡ የስልጠና ርእሶች ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ የግልፅነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በአሰልጣኞች ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ከተደረገ በኋላ የእፅዋት ሪጎላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የተዘጋጀው ስልጠና የእርስ በእርስ መማማሪያና የተግባቦት መድረክ እንደመሆኑ መጠን ባለሙያዎች ያገኙትን እውቀት መሬት ማስነካት እንዳለባቸው ገልፀው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንም በመጠቀም የራሳቸውን አቅም በመገንባት ስራዎቻችንን በብቃት መፈጸምና ተቋማችንን የማዘመን ስራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡ ያነጋገርናቸው የስልጠናው ተሳታፊዎችም የተሰጠው ስልጠና ወቅታዊና ለስራቸው በጣም አሰፈላጊ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣ ከቅንጅታዊ አሰራር፣ የተመደበውን ሀብት በጋራና በአግባቡ ከመጠቀም አኳያ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በተከታታይ መሰጠት አንዳለባቸው፣ በተቋሙ ያሉ ባለሙያዎች ለአንድ ዓላማና ግብ እንዲሰለፉ ከማድረግ አኳያ፣ እቅዶች በወቅቱ ለሰራተኛው ቀርበው እየተገመገሙ መሄድ አንዳለባቸው እና ሌሎችንም ሃሳቦች አንሰተዉ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ለተቋማዊ ግንባታ ስራ ያላቸው ሚና ከፈተኛ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ሰልጠና በኋላ የሚሰጡ አቅጣጫዎችን በመቀበል በአዲስ መንፈስ ፈጥነው ወደ ስራ እንደሚገቡ በመደረኩ ላይ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

✅ደረሰ ደረሰ ደረሰሰ ታህሳስ 30 ደረሰ❗️ እንኳንንንን ደስስስስ አላችሁ👇👇👇 ብሄራዊ ሎተሪ ለባለ ዕድለኞች አስደሳች ዜና ይዞ መጥቷል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ የማህበረሰቡን የቤት እጦት እና
✅ደረሰ ደረሰ ደረሰሰ ታህሳስ 30 ደረሰ❗️ እንኳንንንን ደስስስስ አላችሁ👇👇👇 ብሄራዊ ሎተሪ ለባለ ዕድለኞች አስደሳች ዜና ይዞ መጥቷል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ የማህበረሰቡን የቤት እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ከEthio Telecom ጋር በመተባበር፣ #100_ሚሊዮን_ብር በመመደብ #ታህሳስ 30/2016 የሚጠናቀቅ ልዪ የሆነ "ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ " ፕሮግራም አዘጋጅቷል። የኢትዮ ቴሌኮምና ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በወሰነው መሰረት  ድርጅታችን በቴሌቪዢንና በሬድዮ ለማስታወቂያ ይመድበው የነበረውን በጣም ከፍተኛ ገንዘብ በመቀነስ የቴሌግራም ቻናል በመክፈት ራሱን እያስተዋወቀ ይገኛል!! ቴሌግራም ገፃችንን ብዙ ተከታይ እንዲያገኝ (ሼር) ላደረጉ ተከታዮቻችን 1ኛ እጣ ባለ 3 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 2ኛ እጣ ባለ 2 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 3ኛ እጣ ባለ 1 መኝታ ለ 50 ዕድለኞች እና ቀጥሎ ላሉ 200 እድለኞች የ1 አመት ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት ይኖረዋል፡፡ አሁንስ ምን ይጠብቃሉ ሊንኩን ተጭነው ከገቡ በኃላ፣ ይህን ፅሁፍ ለ40 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ወዳጅ ጓደኛችዎና ግሩፓች ላይ ሼር ፎርዋርድ ሲያደርጉ፣ የመሸለም እድሎ የሰፋ ነው። ይህን የማይገኝ አጋጣሚ በከንቱ እንዳያሳልፉ አሁኑኑ ሼር ፎርዋርድ ያድርጉ ፡፡ ከ40 በላይ ሼር ማረጋችሁ የመሸለም እድላችሁን ያሰፋዋል በኮምፒውተር እጣ አወጣጥ መሠረት #ታህሳስ 30/2016 በገና ማግስት ተሸላሚ ባለ ዕድለኛዎችን በ ቴሌግራም ቻናላችን የምንገልፅ ይሆናል መልካም እድል ከ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር @NATIONAL_LOTTERYET @NATIONAL_LOTTERYET ♻️ ሼር ሲያረጉ እኛ ደሞ እንሸልሞታለን!!

የኢትዮጵያ ስብራት ጥገና ቀን

ሰበር ዜና! ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች **** ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእፅዋት ዝርያ ለቀቃ እና ምዝገባ ረቂቅ መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፤ ***** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 509/2014 ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል የእፅዋት ዝርያ ብቃትና የዘር ጥራትን መቆጣጠር ነው፡፡ በዚህም መሰረት የእፅዋት ዘር አዋጅ ቁጥር 1288/2015 መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው የዕፅዋት ዝርያ ለቀቃ እና ምዝገባ ረቂቅ መመሪያ ላይ በደብረ ዘይት ከተማ በሊሳቅ ሪዞርት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል። የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ለተሳታፊዎች ካሰተላለፉ በኃላ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመ ጀመሮ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ማለትም በግብርናው ዘርፍ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋት እና በመተግበር በዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው ፣ በእንስሳት እና በዕጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጂ ተጽኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ ለማስቻል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ እና ስራዎቹን ለመተግበር ሁሉን አቀፍና በሌሎች የተቀባይ ሀገራት ዘንድ አመኔታ እንዲኖር የሚያስችል የህግ ማዕቀፎች መከተልና መተግበር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር አክለውም ለውይይት የሚቀርበው ረቂቅ መመሪያ የዝርያ ለቀቃና ምዝገባ ሂደቱን በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥ አስፈላጊ በመሆኑ የውይይቱ ተሳታፊ አካላትም በእያንዳንዱ የረቂቅ መመሪያው ክፍል ላይ ተገቢውን ውይይት በማደረግና ገንቢ የማጠናከሪያና የማሰተካከያ አስተያየቶችን በማንሳት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም አምባሳደር ድሪባ ይህ መመሪያ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አሰተዋጾ ላበረከቱ ባለሙያዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበው የውይይት መድረኩን አሰጀምረዋል፡፡ የእፅዋት ዝርያና የዘር ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሀ ተሾመ አጠቃላይ የዝርያ አለቃቅ ስርዓቱን፣ የእጽዋት ዘር አዋጅ ቁጥር1288/2015 ከነባሩ የዘር አዋጅ ቁጥር782/2005 ጋር በማነጻጸር ልዩነቱን ፣እንዲሁም አስተያየት እንዲሰጥበት የተዘጋጀውን ረቂቅ መመሪያ አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ረቂቅ መመሪያ በየአንዳንዱ አንቀጽ ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ እድሉ ተሰጥቶ በርካታ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ አስተያቶች ተነስተው የጋራ ዉይይት የተደረገባቸው ሲሆን የቀሩ አስተያቶች ካሉ ደግሞ በኢሜል ለአርቃቂ ኮሚቴዎች እንዲላኩ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያ ለቀቃ እና ምዝገባ ሥርዓት በመዘርጋት ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ጠቀሜታ ለማሳደግ እንዲሁም በቀጠናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ የዕፅዋት ዝርያ ለቀቃ እና ምዝገባ ሥርዓት ጋር በማጣጣም ሃገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ተጠቃሚነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የዚህ መመሪያ መዘጋጀት አሰፈላጊ በመሆኑ በውይይቱ የተነሱ ገንቢ አስተያቶችን በማካተትና በማዳበር እንድሁም የኢንግሊዘኛ ትርጉም ስራ ተሰርቶለት እንዲጸድቅ ለሚመለከተው አካል እንደሚቀርብ ገልጸው መድረኩ ተጠቋል፡፡

የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ የሚያመጡትን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር መጎልበት ወሳኝ ነው ተባለ፤ **** የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ፣ ከአለም የጤና ድርጅትና የእንስሳት ጤና ድርጅት፣ ከአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት እና ከዓለም አካባቢ ጥበቃ ድርጅት ጋር በመተባበር የፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶች ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ‹‹ የፀረተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድን በጋራ መከላከል›› በሚል መሪ ቃል ከህዳር 7- 14 /2016 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከበረ፡፡ የፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒት በጀርሞች መላመድ በአሁኑ ስዓት በሰውና በእንስሳት ላይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንና ለዚህ ችግር መባባስ ምክንያት የሆነው ህብረተሰቡ ስለመድሀኒት አወሳሰድ በቂ የሆነ ግንዛቤን ባለማግኘት ሲሆን፤ ያለ ጤና ባለሙያ የታዘዙ መድሀኒቶችን መውሰድ፣ የግልና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ጉድለት፣ መልካም የሆነ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ እና አያያዝ ልምድ ያለመኖር፣ የፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒት ቅሪት ያለበትን ምግብ በመመገብ መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መድሀኒት ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ ጥቅም ላይ የዋሉ ፀረተህዋሲያን መድሀኒቶች በቆሻሻ መልክ ወጥተው ጤናማ የተፈጥሮ አካባቢን ሲበክሉ፣ የጥራት ጉድለት ያለባቸው እና ህገ ወጥ ፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶች ጥቅም ላይ ሲውሉና፣ የታዘዘን የፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒት ማቋረጥ መጠኑን መጨመር ወይም መቀነስና የመውሰጃ ስዓትን ማዛባት እንዲሁም ከሌላ ሰው ተውሶ መውሰድ ችግሩን እንደሚያባብሱ አስረድተዋል፡፡ የፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ ተጓዳኝ ጠንቃቸው ከፍ ሲል የማዳን ኋይላቸው ዝቅ ያለ ሌሎች ውድ መድሀኒቶችን ለመጠቀም ወይም አንዳንዴም ምንም አይነት አማራጭ እንዳይኖር ሊያደርግ እንደሚችል የገለፁት ዶ/ር ሰለሞን ከሰው ወደ እንስሳት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች የስርጪት መጠን በመጨመር እንዲሁም ምርታማነትን በመቀነስ በአገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስ ተናግረዋል፡፡ የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒትን ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ የእያንዳንዱ መንግስታዊይም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ባለሙያዎች እንዲሁም መላው ህብረተሰብ በቅንጅት ሆነው መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ ር ሰለሞን በተለይም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አተኩሮ ሊሰራ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

የባለሥልጣኑን ሴት ሠራተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ፤ ***** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሴቶች ማኅበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሴቶችን ብቃት በማሳደግና ወደ ተሻለ ደረጃ በማምጣት ለቁጥጥር ተግባሩ ያላቸውን ሚና በማጎልበት እና የማህበራዊ አካቶ ትግበራን በማሻሻል የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖን በመቀነስ የባለሥልጣኑን ሴት ሠራተኞችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ ሁሉን አቀፍ የሴቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የባለሥልጣኑ ሁሉም የሥራ ክፍሎች በያገባኛል ጉዳይ ሊሰሩ እንደሚገባ የገለጹት በሴቶች ማኅበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሰይድ ዑመር ተቋሙ አዲስ ቢሆንም ሴት አመራሮችን ጨምሮ ሁሎም የባለሥልጣኑ ሴት ሰራተኞችን የአቅም ክፍተት በመለየት ተከታታይ ስልጠናዎችን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰይድ አክለውም ሴቶች እራሳቸውን የሚያበቁበት የሴቶች ፎረም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ በማድረግና ለሴት ሰራተኞች ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር እና አቅማቸውን ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት በሥራ ክፍሉ እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የሴት ሠራተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በሴቶች ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ለማረቅ፣ በሥርዓተ ጾታ ምንነት እና ጾታዊ ትንኮሳን በመከላከል ዙሪያ ለሁሉም የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ግንዛቤ ለመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሰይድ ሁሉምየስራ ክፍሎች የሥርዓተ ጾታን ጉዳይ በእቅዳቸው አካተው የመስራት ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ ይሄን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡ ለሴት ሰራተኞች ምች የስራ አካባቢ እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያ ከወሊድ ፈቃድ በኋላ ህፃናት ልጆቻቸውን የሚያቆዩበት የህፃናት ማቆያ ማዕከል በመሥሪያ ቤቱ በማቋቋም ህፃናቱ አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያገኙ እና ሴት ሰራተኞችም ህፃናት ልጆቻቸውን በቅርበት እንዲከታተሉ ለማስቻል በሥራ ክፍሉ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ቢያቀርቡም እስከአሁን የሕጻናት ማቆያ አለመኖሩን አቶ ሰይድ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ልጅ ያላቸው የመ/ቤቱ ሴት ሰራተኞች መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ የሥራ ክፍሉ ውጤታማ ሥራ እንዲሰራ ከግብዓት፣ ከበጀት እና ከሕጻናት ማቆያ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ሰይድ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የአንድ ክፍል ብቻ ሳይሆን በተቋም ደረጃ የሥርዓተ ፆታ ጉዳይ በባለሥልጣኑ ስትራቴጅክ እቅድና በሁሉም የሥራ ክፍሎች ዓመታዊ እቅድ ውስጥ በማካተት ሴቶችን አቅም ሊያጎለብቱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡