የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
رفتن به کانال در Telegram
1 411
مشترکین
+224 ساعت
+257 روز
+8530 روز
آرشیو پست ها
1 411
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን “ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በአዳማ ከተማ አከበሩ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ሰራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን “ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በአዳማ ከተማ ኢፍታህ ሆቴል በድምቀት አከበሩ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ሲሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ በአሉን ስናከብር ከበዓል አከባበበር ባሻገር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አንድነትን በማጠናከርና ሴቶች የሚገባቸውን መብት በመስጠት በማንኛውም ነገር ላይ እኩል ተጠቃሚና ውሳኔ ሰጪ በማድረግ ሴቶችን በማብቃት ልማትንና ሰላምን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል
ዶ/ር ሀሚድ አያይዘውም ሴቶች በየዘርፉ ያሉ ጅምር የልማት እቅዶችን በማሳለጥ እንዲሁም የሀገሪቱን የለዉጥ ጉዞ በማረጋገጥ ረገድ የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑና ተቋማችን ደግሞ የቁጥጥር ተቋም እንደመሆኑ መጠን በቁጥጥሩ ስራ እንቅስቃሴ ውስጥ ደግሞ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዙት ሴቶች በመሆናቸው ሴቶች ያሉባቸውን ተጽዕኖዎች በመቀነስና በኢኮኖሚ ስራ እንዲሳተፉ በማድረግ ሀገርን ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ብለዋል
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ወ/አገኝ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገባቸውን እውቅናና ስፍራ እንዲያገኙ ትልቅ መሰረት የጣለ አለም አቀፍ ሁነት ሲሆን የፆታ እኩልነትን በማስፈን ሴቶች ከነበረባቸው ድርብርብ ተጽዕኖ እንዲላቀቁና በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮችም እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡
ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የመጡት ወ/ሮ ኤቨሪና ወ/መስቀል በበኩላቸው ሴቶች በሰላም ዙሪያ ያላቸው ሚና በሚል ለውይይት መነሻ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት ሴቶች ግጭትን ለመቀስቀስ ሆነ ለማብረድ የሚያስችል ቁልፍ አቅም እንዳላቸው በመገንዘብ አቅማቸውን ለሰላም ግንባታ ማዋል እንዳለባቸው እና ለዚህ ደግሞ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል
በመጨረሻም የቀረቡ ገለፃዎች መሰረት በማድረግ ለቀረቡ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ሴቶችን ለቁም ነገር በማብቃት እስከ ታች ያሉትን በማጠናከር ሰላምና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ እና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሴቶችን መደገፍና ማገዝ እራስን ማገዝ መሆኑ ግንዛቤ ተይዞ ቀኑን በማስመልከት ወ/ሮ መሰረት አበባው ያላቸውን የህይዎት ተሞክሮ ለሴቶች ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በተጨማሪም ግጥም ቀርቦ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡
1 411
የኢትዮጵያ የፈሳሽ ማዳበሪያ ደረጃ የጥራት መስፈርቶችን ማሞላት ካልተቻለ የብቃት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት ፈቃድ ሊታገድ ወይም ሊሰረዝ እንደሚችል ተገለፀበኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የፀረ ተባይና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ባዘጋጀው መድረክ በወጣው የፈሳሽ ማዳበሪያ ደረጃ ላይ ከፈሳሽ ማዳበሪያ አምራች ባለሀብቶች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይረተክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ሲሆኑ የውይይት መድረኩ ዋና ዓለማ በወጣውን የፈሳሽ ማዳበሪያ ደረጃ ወይም ስታንዳርድ ላይ የተሟላ ግንዛቤ ለመፍጠርና በቀጣይ ፀድቆ የወጣውን የኢትዮጵያ የፈሳሽ ማዳበሪያ ደረጃ የጥራት መስፈርቶችን አሟልታችሁ መስራት እንድትችሉ ያለመ ነው ብለዋል፡፡አቶ ወንዳለ አያይዘውም ይህንን ስራ እየሰራን ያለነዉ በአዋጅ ቁጥር 137/1991 አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀፅ 1 (መ) እንዲሁም በደንብ ቁጥር 509/14 በተሰጠን ሰልጠና መሰረት በተለይ ማዳበሪያን በተመለከተ የኢትዮጵያ የፈሳሽ ማዳበሪያ ደረጃ የጥራት መስፈርቶችን ማሞላት የግድ እንደሆነና ይህን መስፈርት ማሞላት ካልቻለ የብቃት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት ፈቃድ ሊታገድ ወይም ሊሰረዝ እንደሚችል በግልጽ እንደተቀመጠ አብራርተው በዚህ ደረጃ ላይ በቂ የሆነ እዉቀት ካገኛችሁ በኋላ ሁላችንንም የሚገዛን ይህ ደረጃ መሆኑን ተገንዝበን ሁላችሁም ወደ መስመር እንድትገቡ ያገዝናችሁን ያህል ከመስመር የወጣችሁትን ደግሞ ባለስልጣን መ/ቤታችን እያስተካከለ የሚሄድ መሆኑን ጭምር አፅንዖት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይም ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ሰታንዳርድ ማለት በመግባባት የሚዘጋጅ፡ እዉቅና ባለዉ አካል የሚጸድቅ በዚህ አጋጣሚ ጥቅም ላይ ዉሎ ዉጤታማነቱ በየጊዜው እየተረጋገጠ የሚሄድ ህይወት ያለዉ ሆኖ የሚቀጥል ዶክመንት እንደሆነ እንዲሁም ይህ ደረጃ ሲዘጋጅ የሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት እንደተሳተፉበትና እነሱም የተለያዩ አገራትን ተሞክሮ በማጣቀሻነት እንደተጠቀሙ አብራርተዋል፡፡በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ከመድረኩ ለኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትም ሆነ ለኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ሳይንሳዊና ተጨባጭ የሆነ መረጃ ካቀረባችሁ በማንኛዉም ጊዜ ደረጃዎችን ማሻሻል የሚቻል መሆኑ በመግለፅና በመግባባት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገር ለሚላኩ የሮዝ አበባ ምርቶች ላይ ከአውሮፓ ህብርት በተላለፉ ውሳኔዎች ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከኢትዮጵያና ከሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ወደ አውሮፓ ህብረት ለሚላኩ የሮዝ የአበባ ምርቶች ላይ Folse Codiling Moth (FCM) የተባለ ተባይ የሮዝ አበባ አንዱ የመግቢያ መንገድ እነደሆነ የአዉሮፓ ኮሚሽን ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ኢትዮጵያም የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እና ከFCM ነፃ የሆነ ምርት ለመላክ ሀገሪቱ ጠበቅ ያለ የአሰራር ስርዓት መዘረጋት እንዳለባት የሚገልፅ ውሳኔ መተላለፉን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሆልቲ ካልቸር አምራችና ላኪዎች ማህበር ጋር በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ ለሚላኩ የሮዝ አበባ ምርቶች ላይ Folse Codling Moth (FCM) የተባለ ተባይ በሮዝ አበባ አምራች ላኪዎች ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ጉዳትና የመፍትሄ ሀሳቦች እንዲሁም ለቀጣይ ስለሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በተመለከተ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ሆልቲ ካልቸር አምራችና ላኪዎች ማህበር ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
የባለስልጣኑ አማካሪ የሆኑት አቶ ፍቅሬ ማርቆስ ባቀረቡት ሪፖርት ብራስልስ ላይ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን እና ኮሚሽኑ/ DG SANTE/ ጋር የተደረገውን ውይይትና የተላለፈ የውሳኔ ሀሳብ ' አጠቃላይ ኢትዮጵያ ከ2019 እስከ 2023 እ.ኤ.አ በFCM የተገኘባቸው እርሻዎች በኮድ 'ቀደም ሲል ባለስልጣኑና ማህበሩ በጋራ የተሰሩ ስራዎች ' አሁን ያለንበትን ሁኔታ እና በቀጣይ የአውሮፓ ህብረት ባስቀመጣቸው መስፈርቶች መሰረት የሮዝ አበባ አምራች ላኪዎች አሟልቶ ለመላክ የሚጠበቁ ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ አካሂደዋል፡፡
በመድረኩ በቀረቡ ገለፃዎችና በተላለፉት ውሳኔዎች ላይ በተሳታፊዎቹ የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶች የተንሸራሸሩ ሲሆን በነዚህ ሀሳቦች ላይም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ምላሽ ሰጥተውባቸው በተለይም የአበባ ምርቶችን ጤንነት፣ ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሚላኩ ምርቶች አውሮፓ ሲደርሱ FCM ተገኝቶባቸው የሮዝ ምርታቸው እንዳይጣል እና ችግር እንዳይገጥማቸዉ በተለያዩ ጊዚያት ምክክር በማደረግ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የተባይ መቆጣጠሪያ ፕሮቶኮል (Pest Monitoring Protocol) በማዘጋጀት ተከታታይነት ያለው የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከወትሮው በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባና በተጨማሪም በየሩብ ዓመቱ ኦዲት እንደሚያደርግ አሳስበዋል::
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ተባዩን ማጥፋት ባይቻልን ወደ ተለያዩ የአበባ እርሻ ምርት እንዳይተላለፍ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባና ኤርፖርት ሲደርስም ተባዩ መኖርና አለመኖሩን የመቆጣጠር ስራ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በተለይ አገራችን ከቡና ምርት በመቀጠል ከፍተኛ ዶላር በማስገኘት ላይ የሚገኘው የአበባ ምርት በመሆኑ ይንንም ለማስቀጠል የተቀናጀ አሰራርና ጥብቅ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡
1 411
የቁም እንስሳትና ተዋፅዖን የገበያ መዳረሻ ለማስፋት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የቁም እንስሳትና ተዋፅዖችን የገበያ መዳረሻ ለማስፋት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብት ልማት የውጪ ምንዛሪ በማግኘት በዘርፉ ተጠቃሚነቷ ለማስፋት ሰፊ ተግባራት እያከናወነች እንደሆነ ይገለጻል።
በ2003 ዓ ም የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የሀገሪቱን የእንስሳት ጤና አገልግሎት ገምግማ መሻሻል ያለባቸውን አቅጣጫዎች ማስቀመጡ ይታወቃል።
በተቀመጡት አቅጣጫዎች መሰረትም በኢትዮጵያ የእንስሳት ጤና እና ምርታማነትን ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎችን በሚመለከት ኢዜአ በግብርና ሚኒስቴር ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የስራ ሃላፊዎች አነጋግሯል።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤና እና ቬተርነሪ ፐብሊክ ኸልዝ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ውብሸት ዘውዴ፤ በእንስሳት ጤና የገበያ መዳረሻና ምርታማነትን በተመለከተ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
የቁም እንስሳትና ተዋፅዖችን የገበያ መዳረሻ ለማስፋት ከሀገራት ጋር ስምምነት መደረጉን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እንስሳትና ተዋፅኦን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ላይ መዳረሻዎችን ለማስፋት ስራዎች መጀመራቸውን አብራርተዋል።
ቻይናና ማሌዢያ ከኢትዮጵያ ጋር የቁም እንስሳትና ተዋፅኦን ለመውሰድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት።
በኢትዮጵያ የግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ምርት ሬጉላቶሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አያሌው ሹመት በበኩላቸው መንግስት የእንስሳት ጥራትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ባለፉት ሶስት ዓመታት 40 ሚሊዬን ብር በመመደብ የአቅም ግንባታ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ዓለምአቀፍ እውቅና ያለው የሚሌ የእንስሳት ኳራንቲን በመከፈቱ ከዚህ ቀደም ከነበረው ቁጥር ከፍ ያለ የቁም እንስሳት ወደ ውጪ ለመላክ መቻሉንም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ወደ ተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ፣ ሳዑዲና ኳታር የቁም እንስሳትና ተዋፅኦን እየላከች መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ስምንት ወራት 8ሺህ 100 ቶን ስጋና ተረፈ ስጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ ውጪ መላኩንና ወደ 200ሺህ እንስሳት ኤክስፖርት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ስምምነት ከተደረሰባቸው ሀገራት በተጨማሪ በሌሎችም የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋትና ጥራት ያለው ምርት ለማቅረብ ከተለያያ አገራት ጋር ግንኙነት መጀመሩን ነው ዶክተር አያሌው የተናገሩት።
ኢትዮጵያም የእንስሳትን ጤና በመጠበቅ የተሻለ ገቢ ለማግኘት ሰፊ ስራ እየሰራች መሆኑን የገለጹት ዶክተር አያሌው፤ በዚህ ረገድም ድንበር ዘለል በሽታዎችን ለመከላከል የህክምናና የክትባት አገልግሎት በስፋት እየተሰጠ ነው ብለዋል።
የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና እንደ ሀገር ከእንስሳት ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግም በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳት በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር በመውጣታቸው በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ እንደምታጣ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
1 411
ሴቶችን በአመራርና ውሳኔ ሰጭነት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ለሴት አመራሮችና ዴስክ ሀላፊዎች በአመራርና ውሳኔ ሰጭነት ላይ በአዳማ ከተማ ሮቢ ሆቴል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ሴቶች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ከፋተኛ እንደሆነ ሁሉ በአመራርና ውሳኔ ሰጭነት ላይ ያላቸውን አቅም ለማጎልበት እንዲሁም በክህሎትና በእውቀት ለመገንባት ስልጠናው መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትግስት በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል።
የሴቶች ማህበራዊ ሚኒስቴር የሴት ማብቃት ዴስክ ተወካይ ሀላፊ ወ/ሮ ኢቨሪና ወ/መስቀል በበኩላቸው መሪነት ማለት በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት፣ እምነት፣ ክብር እና መተማመን ላይ የተመሰረተ ትብብርን ለማግኘት የሚረዳ እንዲሁም ተፅዕኖ ለመፍጠርና ለመምራት የሚያስችል ጥበብ ነው ብለዋል። ጨምረውም ሴቶች ኋላቀርና ጎጂ ከሆኑ ልማዶችና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች በመላቀቅ ራሳቸውን ወደ አመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት ማምጣት አለባቸው ያሉ ሲሆን በተለይም ስለ መሪነት ፅንስ ሀሳብ መሪና አስተዳደር እንዲሁም ስርዓተ-ፆታና አመራርነት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው ሴቶች በእውቀት፣ በክህሎትና በተለያዩ ስልጠናዎች ራሳቸውን በማዳበርና በመገንባት የአመራር ብቃታቸውን እንዲሁም በውሳኔ ሰጭነት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማዳበር ችግር ፈችዎች መሆን አለባቸው ብለዋል።
1 411
በዱባይ እየተካሄደ ባለው የገልፍ ፉድ በተጏዳኝ በሀገራችን ዘመናዊ የእንስሳት ቄራ በሞጆ እና አዳሚ ቱሉ በማቋቋም ትልቁን የስጋ ምርት ወደ ውጭ የሚልከው የአለና ግሩፕ ባለቤትና ስራ እስፈፃሚ ከሆኑት ኢርፋን አለና ጋር ኩባንያቸውን ከጎበኙ በኋላ ውይይት ሲያካሂዱ
1 411
የሚሌ እንስሳት ኳራንቲንን የግል ባለሀብቶች እንዲያስተዳድሩት ከተደረገ ወዲህ በቁም እንስሳት ኤክስፖርት ላይ የተገኘው ውጤት የሚበረታታና ተነሳሽነትን የፈጠረ ነው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ስራ ከጀመረበት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ያከናወናቸውን ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ከእንስሳት ላኪና አስመጪዎች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት ሲሆን የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ላይ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም በጥንካሬ ያሉትን የምናስቀጥልበትና ድክመቶችን ደግሞ ለማረም እንዲቻል የምንማማርበትና በቀጣይ የምናስተካክልበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በቁም እንስሳት ኤክስፖርት ላይ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበትና ለወደፊትም ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴርና ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተሻለ ስራ ለመስራት የምንቀሳቀስበት ነው ብለዋል።
የባለስልጣኑ የእንስሳት ኳራንቲን ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰይፉ ሀይሉ በበኩላቸው የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ስራ ከጀመረበት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከአሁን ባከናወናቸው ተግባራት ላይ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ድክመቶችና ያጋጠመው ችግሮች እንዲሁም የተወሰዱ መፋትሔዎችን በተመለከተ ገለፃ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ሀላፊ ዶ/ር መሀመድ በቁም እንስሳት ኤክስፖርት በተሰሩ ስራዎች ላይ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ጥሩ ውጤት የተገኘበትና በቀጣይም አጠናክሮ ለመሄድ ተነሳሽነት የፈጠረ ስራ መሆኑን አስረድተዋል።
በመቀጠልም የቀረቡ ገለፃዎችን መሰረት በማድረግ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ከመድረኩ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን የግል ባለሀብቶች እንዲያስተዳድሩት ከተደረገ ወዲህ በቁም እንስሳት ኤክስፖርት ላይ የተገኘው ውጤት የሚበረታታና ተነሳሽነትን የፈጠረ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይም በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠልና የውጪ ምንዛሪያችን ለማሳደግ ባለን ሀብት ጠንክረንና በርትተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ በርካታ የእንስሳት ሀብት ያላት አገር ብትሆንም ማግኝት ያለባትን ጥቅም እያገኘች አይድለም ያሉት ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ ነው ብልዋል። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተሰሩት ስራዎች አበረታች ውጤቶች ማምጣት ችለናል ለዚህም ማሳያ የሚሌ እንስሳት ካራንቲን አንዱ ሲሆን ይህንንም ውጤት ለማስቀጠል የሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ማምጣት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።
