cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
4 439
مشترکین
+2124 ساعت
+1207 روز
+63630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አቶ ፈርሀን አብዱላሂ እና ቤተሰቦቻቸው ያደረጉትን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተረከበ፡፡ በዛሬው እለት የህክምና ቁሳቁሶችን የጫነው ኮንቴነር ሆስፒታል ደርሶ የህክምና ቁሳቁሶችን ርክክብ ተካሂዷል፡፡ ድጋፉ መደረጉ ሆስፒታሉ እየሰጠ ላለው ‹የሪፈራል› ህክምና አገልግሎት ላይ ያሉ የህክምና ቁሳቁሶችን እጥረት የሚያቃልል ነው ተብሏል፡፡ Cardiac Ultrasound (Echocardiography) እና vascular surgery set የመሳሰሉ በገበያ ላይ በቀላሉ የማይገኙ ከዋጋም አንፃር ውድ የሆኑ የሕክምና ቁሳቁሶች ያካተተ ድጋፍ በመሆኑ ድጋፉን ላደረጉት አቶ ፈርሀን አብዱላሂ እና ቤተሰቦቻቸውን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ እና ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኃላፊ ዶ/ር አህመድ መሀመድ አመስግነዋል፡፡ ዶ/ር አህመድ አክለውም ሆስፒታሉ በምስራቁ የአገራችን ክፍል ብሎም ከጎረቤት አገራት ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ይህን መሰል ድጋፎች መደረጋቸው በአግልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በድጋፍ የተገኙትን የህክምና መሳሪያዎች ወደ ስራ ለማስገባት በቂ ዝግጅት ሆስፒታሉ ማድረጉን እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሽኖቹ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲ አሚን አስታውቀዋል፡፡ ግንቦት 23/2016 ዓ/ም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
نمایش همه...
👍 4
👍 1
በሐረማያ ዩኒቨርስቲ የመፀዳጃ ቤቶች አየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም እና የሙቀት አማቂ ጋዞች (GHG) ልቀትን የሚገመግም ብሔራዊ አውደ ጥናት ተካሄደ ። ላለፉት አራት አመታት በድሬዳዋ እና ሐረር ከተማ የመፀዳጃ ቤቶች አየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ላይ እየተደረገ ያለው (sanitation and climate assessing resilience and GHG emission(SCARE)) ፕሮጀክት ግኝቶች በከፊል ይፋ ተደርገዋል ። የአውደ ጥናቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲ በተለያዩ አገራት በሚተገበረው ፕሮጀክት ዩኒቨርሲቲያችን አገርን ወክሎ በጥናቱ ተሳታፊ መሆኑን ገልፀዋል ። የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፋበት በመሆኑ ለቀጣይ ምርምረ ስራዎች ከአውደ ጥናቱ በረካታ ግብአቶች ይገኝበታል ብለዋል ። በጠቃላይ አራት አገራት ፤ ኔፓል ጨምሮ በአፍሪካ ሶስት አገራት ኢትዮጵያን ፣ ኡጋንዳ እና ሴኔጋል (onsite sanitation and climate change : resilience and GHGs emission) በቦታው ላይ የመፀዳጃ ቤቶች አየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም እና የሙቀት አማቂ ጋዞች (GHGs) ልቀት መጠን ልኬት ጥናትና ምርምር ከእንግሊዙ ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቢሊ እና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል ። በአገራችን የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በድሬደዋ እና ሐረር ከተማ  30 (ሰላሳ) ቦታዎች በመፀዳጃ ቤቶች እና የፍሳሽ ጉድጓዶች   ሊመነጭ ይችላል ተብለው ሚታሰቡ የ"ሚቴን"(CH4)  እና "ካርበንዳይ ኦክሳይድ"(CO2) በካይ ጋዞች ላይ ልኬት የመውሰድ ስራ መከናወኑን እና በዚህም ተጨማሪ ጥናት ቢጠይቅም አመላካች ውጤቶች መኖራቸውን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የSCARE ፕሮጀክት ኃላፊ ዶ/ር አብርሀም ገረመው ገልፀዋል ። ፕ/ር ጋይ ሐዋርድ ከብሪስቶል ዩኒቨርስቲ ፣ ፕ/ር ባርባራ ኤቫንስ ከሊድስ ዩኒቨርስቲ ፣ፕሮፌሰር ጁሊየት ዊልስ ፣ ዶ/ር ጀርሚ ኮሊትዝ እና በሐረማያ  ዩኒቨርስቲ የSCARE ጥናት ቡድን በአውደ ጥናቱ ስለ SCARE ፕሮጀክት በርካታ መረጃዎችን የያዙ ፅሁፎች አቅርበዋል ፤ በቀረበው ፅሁፍፎችም ከተሳታፊዎች ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቶ ውይይት ተካሂዷል ። የጤና ስርዓቱ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሚመጡ ጫናዎችን መቋቋም የሚችል አሰራሮችን መተግበር ይገባል ለዚህም እንደ SCARE ያሉ ፕሮጀክቶች እያከናወኑ ያለውን ጥናትና ምርምር ቀጣይነትና ውጤታማነት ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ፕሮፌሰር ባርበራ ኤዩንስ ተናግረዋል። የመፀዳጃ ቤቶች የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ ናቸው ለማለት እንደማይቻል እና በጋራ ፍሳሽ ማጠራቀሚያዎች ላይ በሐረር ከተማ የተደረገው ክትትል በመንግስት ሊተገበሩ የሚገባቸው እንደ ፍሳሽ ማስወገድ አገልገሎት ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን የ(SCARE) ፕሮጀክት ዋና ተመራማሪ ዶ/ሮ አብርሀም ገረመው አስታውቀዋል ። በጤና ሚኒሰቴር ከፍተኛ የጤና ባለሞያ የሆኑት አቶ አሽራፈዲን ዩያ በበኩላቸዉ የአየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከተለዉ ተጽንኦ ከፈተኛ እንደሆነና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጤና አገልግሎት የአየር ንብረት ለዉጥን መቋቋም የሚችል እንዲሆን እየሰራ እንደሆነና ለዚህም የተለያዩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ እንደ አየር ብክለትና ጤና ያሉ መመሪያዎችን በማዘጋጀት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በአውደ ጥናቱ ከሐረሪ ክልል ፤ ሶሜሌ ክልል ፤ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና ድሬደዋ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፤ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፤ የጤና ቢሮ እና ከአለም ጤና ድርጅት ተወካዮች ተሳታፋ የሆኑበትና በርካታ ግብአቶች የተገኘበት መድረክ ነው ተብሏል ። በአውደ ጥናቱ ማጠቃልያ የሙቀት አማቂ ጋዞች ከፍሳሽ ማጠራቀሚያ ውስጥ እንዴት ልኬት እንደሚወሰድ ተሳታፊዎች የመስክ ላይ ጉብኝት አካሂደዋል ። ግንቦት 22/2016 ዓ/ም የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
نمایش همه...
👍 2
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በታችኛው የሽንት ትቦ እና የሽንት ፊኛ ካንሰር (Locally advanced urethral ca)ተጠቂ ለሆኑት የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው እናት ሰባት ሰዓት ተኩል የፈጀ Anterior pelvic exentration +PLND +Mainz II pouch UD የተሰኘ ውስብስብ ቀዶ ህክምና ተደረገላቸው፡፡ ህክምናው የተደረገላቸው እናት አሁን በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ቀዶ ህክምናውን ያከናወኑላቸው ዩሮሎጅስት ሀኪሞች ዶ/ር ወንደሰን ለማ :ዶ/ር ሳቢት :ዶ/ር ፈሪድ እና የህክምና ቡድናቸው ስኬታማ ቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹የዩሮሎጂ› ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ወንደሰን ለማ እንዳሉት ይህን መሰል ህክምና በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ለሶስት ታካሚዎች እንደ ተሰጠና ሁሉም ታካሚዎች በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ ‹የዩሮሎጂ› ህክምና በሰው ልጅ የኩላሊት: የሽንት ፊኛ፤የሽንት ቧንቧ ፤የፕሮስቴት እና የወንድ መራቢያ አካላት ላይ ለሚከሰቱ ህመሞች የሚሰጥ ህክምና ሲሆን በቀዶ ጥገና ህክምና ውስጥ አንዱ የእፔሻሊቲ ዘርፍ መሆኑን ዶ/ር ወንደሰን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም የሽንት ፊኛ ካንሰር በዋናነት ሲጋራ ማጨስ እና ለተለያዩ ኢንዱስትሪያል ኬሚካሎች ተጋላጭ መሆን በሽታውን ሊያስከትሉ እንደሚችሉና ፡ ህመሙም ሲጀምር ደም የቀላቀለ ሽንት ማሸናት ምልክት የሚያሳይ ሲሆን ምልክቱ ከታየ ባፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ መመርመርና መታከም እንደሚገባ ዶ/ር ወንደሰን ለማ አስገንዝበዋል፡፡ የ ''ዩሮሎጅ'' ቀዶ ህክምና አገልግሎት ካለፉት ሶስተ አመታት ጀምሮ በሶስት እስፔሻሊስት ሀኪሞች እየተሰጠ ያለ በመሆኑ ፡ለተመሳሳይ ህክምና የሚደረግ ሪፈራልን በማስቀረትና ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጭና ጊዜ ማዳን አስችሏል።ማህበረሰቡም ይህንን  አውቆ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በእለቱ ቀዶ ህክምናው ሲደረግ ለተሳተፋ ሀኪሞች ፤ነርሶች፤ የአኔስቴዚያ ባለሙያወችና  ደም ልገሳ በማድረግ ትብብር ላደረጉት የላብራቶሪ አገልግሎት ክፍል ባለሞያዎችን ዶ/ር ወንደሰን እና የህክምና ቡድናቸው አመስግነዋል፡፡ ግንቦት 20/2016 ዓ/ም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
نمایش همه...
2👏 2
آرشیو پست ها