cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

MERJA TUBE

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
211
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
+330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አሜሪካና ብሪታኒያ የሁቲ አማፂያን ይዞታዎችን መደብደባቸው ተነገረ‼️ ሀገራቱ በዛሬው ዕለት በጥምረት እርምጃ የወሰዱት አማፂያኑ ለሣምንታት በቀይ ባሕር ቀጣና ጥቃት ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘ ታይምስ ኦቭ እስራዔል ዘግቧል፡፡ በጥቃቱ ዓየር ማረፊያ፣ ዓየር መንገዶች እና የጦር ካምፕ መመታታቸውን የሁቲ አማፂዎቹ የቴሌቪዥን ጣቢያ አል-ማሲራህ ዘግቧል፡፡ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በበኩላቸው÷ እርምጃ የተወሰደው የሁቲ አማፂያን በሚጠቀሟቸው ሰው አልባ ድሮኖች፣ ባላስቲክ እና ክሩዝ ሚሳኤሎች እንዲሁም የድንበር እና የዓየር ክልል መቆጣጠሪያ ራዳሮች ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢራን፣ ሄዝቦላህ እና የሃማስ ቡድኖች ሀገራቱ በጥምረት ያደረሱትን ጥቃት ማውገዛቸው ተመላክቷል፡፡ ድብደባው "የየመንን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን የጣሰ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕጎችን፣ ደንቦችን እና መብቶችን የገረሰሰ ነው" ሲሉም ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን÷ አጸፋዊ እርምጃ የወሰድነው አማፂያኑ በቀይ ባሕር ቀጣና ተደጋጋሚ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል፡፡ እንደ አሥፈላጊነቱ ሀገራቱ በጥምረት ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ እንደማይሉም አመላክተዋል።
نمایش همه...
በደብረ ብርሃኑ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች ተናገሩ‼️ ከትናንት በስትያ ታኅሣሥ 24/ 2016 ዓ. ም. በአማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ እና የሆስፒታል ባልደረባን ጨምሮ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከትናንት በስትያ ከሰዓት እና ትናንት ቢያንስ የሰባት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት መከናወኑን ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን ከተማ ባሳለፍነው ረቡዕ እስከ ቀኑ አጋማሽ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፣ የፋኖ ታጣቂዎች እና የፀጥታ ኃይሎች ከትናንት በስትያ ጠዋት አንስቶ የተኩስ ልውውጥ ያካሄዱት “በተለያዩ የከተማዋ አቅጣጫዎች” ነው። የረቡዕ ዕለቱን ሁነት አስመልክቶ ትናንት ታኅሣሥ 23/ 2016 ዓ. ም. መግለጫ ያወጣው የደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢው ኮማንድ ፖስት “ጽንፈኛ” ሲል የጠራው ኃይል “ጉዳት ለማድረስ በማሰብ” ወደ ከተማዋ “በአቋራጭ” ገብቶ እንደነበር አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ክልል አድማ ብተና እና የከተማዋ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በወሰዱት “የተቀናጀ ኦፕሬሽን በአጭር ጊዜ ከተማው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው” መመለሱንም ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል። ኮማንድ ፖስቱ “የፀጥታ ችግር” ሲል በጠራው የትናንት በስትያው ክስተት “በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት” መድረሱን በመግለጫው አስታውቋል። ይሁንና መግለጫው በምን ያህል ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ በቁጥር አልጠቀሰም።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጭ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ እንደተወሰዱና አንድ ግለሰብ ደግሞ ተጎድቶ ሄዶ ሕይወቱ ማለፉን ተናግረዋል። ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የተወሰዱት አራት ግለሰቦች “በአጀብ” ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውን የሚገልጹት የቢቢሲ ምንጭ፤ በዚህም ምክንያት የፀጥታ ኃይል አባላት ናቸው የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል። ወደ ሆስፒታሉ ከገባ በኋላ ሕይወቱ ያለፈው ተጎጂ በአንጻሩ ሲቪል ግለሰብ መሆኑን አመልክተዋል። ይህንን ግለሰብ ጨምሮ ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ የተወሰዱ ንጹሃን ዜጎች ቁጥር አራት መሆኑን የሚናገሩት የቢቢሲ ምንጭ፤ ከእነዚህ ውስጥም “አስጊ” በሚባል ደረጃ የተጎዳው ታካሚ የሆስፒታሉ ባልደረባ መሆኑን አብራርተዋል። የቢቢሲ የሆስፒታል ምንጭ እንደሚያስረዱት፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የሆስፒታሉ ባልደረባ ለተሻለ ሕክምና አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የቃጠሎ፣ የአደጋና ድንገተኛ ሆስፒታል (አቤት) ተዛውሯል። ይህ ግለሰብ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ቀሪዎቹ ንጹሃን ዜጎች የቆሰሉት “በተባራሪ ጥይት” መሆኑንም አክለዋል። ቢቢሲ በከተማዋ ከሚገኙ ሌሎች የጤና ተቋማት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይሁንና ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ ግለሰቦች ባሻገር ሌሎችም ሰዎች በረቡዕ ዕለቱ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ የከተማዋ ነዋሪ፤ “በተባባሪ ጥይት” ተመትተው ሕይወታቸው ያለፈ ንጹሃን ዜጎች ትናንት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መከናወኑን ገልጸዋል። ሌላ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፤ “ከትናንት በስትያ ከሰዓትም የተቀበሩ አሉ። እኔ የማውቃቸው ልጆች መሞታቸውን ሰምቻለሁም፤ አውቄያለሁም። ... ፖሊስ፣ አድማ በታኝ፣ ጥበቃዎችን ጨምሮ ቀብራቸው የተፈጸመው ቢያንስ ከአስር በላይ ሰዎች ይሆናሉ” ሲሉ ከፍ ያለ ቁጥር ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች አጠቃላይ የአሐዝ መረጃ ለማግኘት ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ያደረገው የስልክ ጥሪ አልተሳካም። ረቡዕ ዕለት የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በከተማዋ ቆሞ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃ ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢው ኮማድ ፖስትም ትናንት ባወጣው መግለጫ “የመንግሥት ተቋማት፣ ሱቆች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት” ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውን አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
نمایش همه...
👍 1
በደብረብርሃን ከተማ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታን ምክኒያት በማድረግ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጣለ! በዛሬዉ እለት የደብረብርሃን ከተማ መስተዳድር ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታውን መሠረት በማድረግ በደብረብርሃን ከተማ ለሁለት ቀናት የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ኮማንድ ፖስቱ አስቀምጧል ሲል አስታዉቋል። በደብረብርሃን ከተማ የባጃጅ ተሽከርካሪ በቀን 24 እና  25 /04/2016 ዓ/ም ማሽከርከር  እንደማይቻል ኮማንድ ፓስቱ ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።  በዚህም መሠረት የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናቶች ከማሽከርከር ወይም ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡም አሳስቧል። @Addis_Mereja
نمایش همه...
ተሰናባቹ የፈረንጆቹ አመት ለኢትዮጵያ :- ዘ ኢስት አፍሪካን የተሰኘ ኬኒያዊ ጋዜጣ "እየተገባደደ ያለው የፈረንጆች አዲስ ዓመት ለኢትዮጵያ መጥፎ ዓመት ነበር" ሲል ይጀምርና መገለጫዎቹን ማብራራት ይቀጥላል። ሃገሪቱ (ኢትዮጵያ) እጅግ ዝቅተኛ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ እንዳላት፣ በባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት (የኑሮ ውድነት) ምክንያት የኑሮ ውድነት ህዝቡን እየፈተነው መሆኑን፣ እጅግ ከፍተኛ የውጭ እዳ እንዳለባት ያብራራና ዓለምአቀፍ የኢኮኖሚ አማካሪዎች "ኢትዮጵያ የብድር ወለድን እንኳን መክፈል አለመቻሏን መሰረት አድርገው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያጋጥማት ጫፍ ላይ ደርሳለች" ማለታቸውን ጋዜጣው ያትታል። Via - The east Africa
نمایش همه...
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስገዝ ስትራቴጂክ እቅድ ረቂቅ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ውይይት ቀረበ፡፡ በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ÷ የአምስት ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት ሒደትና ዘጠኝ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል። የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የሴክተር መስርያ ቤት አመራሮች እና የኢንዱስትሪ ተቋማት ሃላፊዎች በስትራቴጂክ ዕቅዱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ረቂቅ ሰነዱ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሙሉ ራስ ገዝነት የሚያደረገውን የሽግግር ሒደት ማሳካት የሚያስችለውና የሚያረጋግጥበት መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል። ተሳታፊዎች የአምስት ዓመት ዕቅዱ የባለድርሻ አካላትንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፍላጎት ያገናዘበ እንደሆነ መናገራቸውንም የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል።   ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
የመፍትሄ ያለህ . . . " መፍትሄ የሚባል ነገር ሳይሰጠን የትምህርት ዓመቱ 5ኛው ወር ሊገባ ነው " - ተማሪዎች በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ወደ ሚማሩበት ዩኒቨርሲቲዎች አልተጠሩም። ተማሪዎቹ መቼ እንደሚጠሩ አያውቁም ፤ መፍትሄም አልተሰጣቸውም። ስለተማሪዎቹ ጉዳይ መፍትሄው ይሄ ነው ሳይባል የትምህርት ዘመኑ 5ኛ ወር ሊገባ ተቃርቧል። ተማሪዎቹ ቤት ከዋሉ ወራት አልፈዋል። ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ላይ የሚገኙ ሲሆን የነሱ እኩዮች የትምህርት ዓመቱን አጋማሽ ለማጠናቀቅ ቀርበዋል። ተማሪዎቹ እስካሁን ወደ ሚዲያ ወጥቶ መፍትሄ የሚናገር አካል ባለማግኘታቸው " በዚህ ዓመት ላንማር እንችላለን " የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። እነዚህ ተማሪዎች  ፤ በቅድሚያ በኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ፣ በኃላም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ይፈጠሩ በነበሩ የፀጥታ ችግሮችና አሁን ደግሞ በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ የሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን ባግባቡ መማር አልቻሉም። ተማሪዎቹ በእነሱ ጉዳይ ተገቢ መረጃ የሚሰጥ አካል እንደሌለ ይናገራሉ። በራሳቸው መንገድ እየደወሉ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ሲጠይቁ " ምንም አናውቅም " ይሏቸዋል። አንዳንዶች ስልክ አያነሱም፣ አጭር የፅሁፍ መልዕክትም አይመልሱም ፤ ተስፋ የሚሰጥ ነገርም አይናገሩም ሲሉ ይወቅሳሉ። ተማሪዎቹ የዚህ ጊዜ " ባች " ከአንደኛ ዓመት ጀምሮ ብዙ ተግዳሮቶችን እየተጋፈጠ የመጣ " ባች " ነው ብለዋል። * በኮሮና ምክንያት ብዙ ጊዜ ግቢ ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል። * በተለያዩ አለመረጋጋቶች የትምህርት ክፍለጊዜዎች እየተጓተቱ፣ እየተቆራረጡ፣ አንድ ወሰነ ትምህርት በ45 ቀናት እየተማሩ ነው የመጡት። * ብዙ የትምህርት ክፍሎች አልተሸፈኑም፣ እነዚህ ደግሞ የመውጫ ፈተና አካል ናቸው ተማሯቸውም አልተማሯቸውም " ተምረዋቸዋል "ተብሎ ነው የሚታሰበው። * የተማሯቸው የትምህርት ክፍሎች እንኳ በበቂ አልተማሯቸውም። * የመውጫ ፈተና ላይ እንዴት ልንሆን ነው የሚልም ሃሳብ አለባቸው። አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ቢገቡ ያልተሸፈነው ትምህርት እንዴት መሸፈን እንዳለባቸው ሲያስቡ ተማሪዎቹ ካሁኑ ጭንቅ ውስጥ እንደገቡ አስረድተዋል። ተማሪዎቹ ያለትምህርት ረጅም ጊዜ ቤት መቀመጣቸው ለከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እንደዳረጋቸውም ገልጸዋል። ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ድረስ ተማሪዎች ተወክለው ቢጠይቁም ፤ ብዙ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ አመልክተዋል። በተለይም የጤና ተማሪዎች ፤ ትምህርታቸው ተጨማሪ ኮርሶች ያሉት የትምህርት መስክ በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ትምህርቱ ካልተሰጠ አስቸጋሪ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ምናልባት ጊዜ ካለፈ በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ በይድረስ ይድረስ ትምህርቱ የሚሰጥ ከሆነ ተማሪው በቂ እውቀት ይዞ አይወጣም ብለዋል። በመጨረሻም ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቷቸው መፍትሄ የሚለውን ነገር በይፋ እንዲያሳውቃቸው ጥሪ አቅርበዋል። ሁኔታው ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም አስገንዝበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ቃል የወሰደው ከዶቼ ቨለ ሬድዮ እንዲሁም በውስጥ ከመጡ መልዕክቶች ሲሆን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ መሰል መልዕክት ማጋራታችን ይታወሳል። የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ብዙ ጥረት ብናደርግም ይህ ነው ተብሎ ለተማሪና ወላጅ የሚነገር ምላሽ አላገኘንም። @tikvahethiopia
نمایش همه...
" ' አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው ' እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " -  የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ " አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው " እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ገልጿል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል ፤ ተሽከርካሪዎች የሚያወጡት በካይ ጋዞች (ጭሶች) አካባቢን እንዳይበክሉ ተቋሙ የልኬት ቁጥጥር ያደርጋል ሲል አሳውቋል። በዚያ መሰረትም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብሏል። ለዚህ የቁጥጥር ስራ እንዲያመች ደግሞ ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ጠቁሟል። መመሪያው አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከመስመር ለማስወጣት ሳይሆን በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በመቆጣጠር ማስተካከያ እንዲያደርጉ የሚያስችል እንደሆነም ነው ባለስልጣን መ/ቤቱ ያስረዳው። በዚህም ከዓመታዊ #የቦሎ_እድሳት ጋር የተሽከርካሪው የበካይ ጋዝ ምርመራ የማረጋገጫ ስራ አንዱ መሆኑ ተነግሯል። የበጋይ ጋዝ / ጭስ ምርመራ ተደርጎ ችግር ያለባቸው እንዲያስተካክሉ ይደረጋል እንጂ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚወራው " አሮጌ መኪናዎች " ሊታገዱ ነው የሚለው ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አስገንዝቧል። @fjvokv
نمایش همه...
የአዲስ አበባ መስተዳድር በስሩ ለሚገኙ ከጽህፈት ቤት እስከ ወረዳ ደረጃ መዋቅር ላሉ ሰራተኞቹ የምዘና ፈተና ሊስጥ ነው። ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ በአቅማቸው ይመደባሉ አልያም መቋቋሚያ ተከፍሏቻው ከስራ ይሰናበታሉ። ከሰሞኑ ፈተናውን የሚወስዱ ተቋማት ተለይተዋል። ሁሉም ሰራተኞች እስከ ጥር ወር ድረስ ለፈተና ይቀመጣሉ።
نمایش همه...
አዲስ አበባ መስተዳድር እስከ ወረዳ ላሉ ሰራተኞች ፈተና ሊሰጥ ነው፣ ፈተናውን ያላለፉስ? - Wazemaradio

ዋዜማ- የአዲስ አበባ መስተዳድር በስሩ ለሚገኙ ከጽህፈት ቤት እስከ ወረዳ ደረጃ መዋቅር ላሉ ሰራተኞቹ የምዘና ፈተና ሊስጥ ነው። ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ በአቅማቸው ይመደባሉ አልያም መቋቋሚያ ተከፍሏቻው ከስራ ይሰናበታሉ። ከሰሞኑ ፈተናውን የሚወስዱ ተቋማት ተለይተዋል። ሁሉም ሰራተኞች እስከ ጥር ወር ድረስ ለፈተና ይቀመጣሉ። ዝርዝሩን ዋዜማ እንደሚከተለው አስናድታዋለች። አንብቡት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አዲስ የመዋቅራዊ ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት

#TayeDendea የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተሰምቷል። ለሚኒስትር ዴኤታው የተፃፈው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ ፦ " ከመስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነዉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመስገንኩ ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት የተነሱ መሆኑን አስታዉቃለሁ። " ይላል። ደብዳቤው ከራሳቸው አቶ ታዬ ገፅ የተገኘ ነው። ይህ ተከትሎ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተችተው ፅፈዋል። አቶ ታዬ ፤ " ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ " ብለው ባሰራጩት ፅሁፍ " የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ። " ብለዋል። " እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር። " ያሉት አቶ ታዬ " ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ። " ብለዋል። " ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። " ያሉት አቶ ታዬ " ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ። እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል " ሲሉ ፅፈዋል። ምንም እንኳ አቶ ታዬ ደንደአ በተለያየ ጊዜ እሳቸው ያሉበትን መንግሥት በመተቸት ይታወቃሉ።
نمایش همه...