cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢትኤል777(Ethal777)

ኢትኤል777 :የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው 💚ለሰው ልጅ ምድራዊ ጥበብ የሰጠን አምላክ ታላቅ ነው 💛 የቀደም አባቶቻችንን ጥበብ እናይበታለን ❤ የታሪክና መንፈሳዊ መፃህፍት እናያለን Youtube👉 https://youtube.com/channel/UCy31jIuDx1aTo8IloPnzPYQ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
189مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

​​🌼 አበባዮሽ 🌼 እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2) አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ጌቶች አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) እሜቴ አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ዘመን መጣ ብለን አበባዮሽ ለምለም(2) ባልንጀሮቼ ለምለም ግቡ በተራ ለምለም በእግዚአብሔር መቅደስ ለምለም በዚያች ተራራ ለምለም እንድታደንቁ ለምለም የአምላክን ሥራ ለምለም ህይወት ያገኛል ለምለም እርሱን የጠራ ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ ለምለም (2) ክረምት አለፈ ለምለም ጨለማው ጠፋ ለምለም የመስቀሉ ቃል ለምለም ሆነልን ደስታ ለምለም እናገልግለው ለምለም ቤቱ ገብተን ለምለም ትንሽ ትልቁ ለምለም ተሰልፈን ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ ለምለም(2) ያንን ኩነኔ ለምለም ዘመነ ፍዳ ለምለም የሞቱ በራፍ ለምለም ያ ምድረበዳ ለምለም ልክ አንደ ክረምት ለምለም ሄደ ተገፎ ለምለም ፀሐይ ወጣልን ለምለም ጨለማው አልፎ ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ ለምለም(2) ይኸው መስከረም ለምለም ይኸው ፀሐይ ለምለም ንጉሡ ወርዶ ለምለም ከላይ ሰማይ ለምለም አውደ ዓመት ሆነ ለምለም ደስታ ሰላም ለምለም ፍቅር ሲገለጥ ለምለም በአርያም ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ ለምለም(2) ይኸው አበባ ለምለም ለምለም ቄጤማ ለምለም አዲሱ ዘመን ለምለም አምጥቷልና ለምለም በሩን ክፈቱ ለምለም መኳንንቶቹ ለምለም የክብር ንጉሥ ለምለም ይግባ ቤታችሁ ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ ለምለም(2) ቤታችሁ ይሙላ ለምለም ሰላም ደስታ ለምለም ሰጥቷችሁ እርሱ ለምለም የሁሉ ጌታ ለምለም ከዘመን ዘመን ለምለም ያሸጋግራችሁ ለምለም የሽበትን ዘር ለምለም ይሸልማችሁ ለምለም አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ ከብረው ይቆዩን ከብረው የክብርን ወንጌል ሰምተው የበጉን ሥጋ በልተው የአምላክን ፊቱን አይተው ከብረው ይቆዩን ከብረው
نمایش همه...
✞ ኢትዮጵያ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደትናት ትጋት እንደሸሸች ዛሬም እቺ ፅዋ ከእኛ ትለፍ ትመልከት ኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ የሃጢዓት ፅዋ ሞልቶ ፈሰሰ ወንድም ወንድሙን ተራምዶ አለፈ ፃድቅ ሲራብ ሲለምንእንጀራ ከቶ እንዳናይ ስጠን ባለ አደራ/2/ አዝ____ ላልበዛ እድሜአችን እልፍ ላንቆጥር ቀለንተገኘን በሃጢአት ወንበር ቃልን እረስተን ከቶ አንጣ ዋጋ የእውነት እረፍት አለ እና አንተ ጋ/2/ አዝ___ በቁጣ ቃልህ በስይፍ አንጥፋ ዘር ጎጠኝነት በስምህ ይጥፋ ከማይሞተው ካንተ ነው ዘራችን እግዚአብሔር ሰላም እርስታችን/2/ አዝ___ እጇን ዘርግታ አይኗን አቅንታ ትጠራሃለች ቀን ከሌት ተግታ በቅዱሳን ንኡዳን ክቡራን ተማፅነናል ባርክልን ኢትዮጵያን/2/     
نمایش همه...
“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29 ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡ በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29 የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!!👉🙏🙏
نمایش همه...
#ሾልኮ_የወጣው_ሰነድ ! ----------------------------- በሥልጣን ላይ ያለው ገዢው ሥርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማዳከምና ለማጥፋት ሥርዓታዊና መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ሥልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለሁሉ ግልጽ ነው። ሰሞኑን ከገዢው ፓርቲ ሾልኮ የወጣው ሰነድም የጥቃት ዒላማ ያደረጋቸውን የቤተክርስቲያኗን ማህበራት ፥ ተቋማት ፣ አባቶችና አገልጋይ መምህራንን ይዘረዝራል። ሾልኮ በወጣው ሰነድ ላይ የተገለጹት አካላትም ፦ ▪ በማኅበራት ደረጃ √ ማኅበረ ቅዱሳን √ የሰሜን አሜሪካ የካህናት ማኅበር ▪ በእንቅስቃሴ ደረጃ √ የሞዐ ተዋህዶ ግብረ ኃይል ንቅናቄ ▪ በግለሰብ ደረጃ እስትራጄቲክ [ልብ] መሪዎች ፦ √ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ √ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል √ ዶ/ር ዘርዓየሁ ስሜ √ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ √ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ √ ዲ/ን ታደሰ ወርቁ √ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ ▪ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና መረጃዎችን ለሕዝብ የሚያደርሱ √ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ √ አቶ ፋንታሁን ዋቄ √ መ/ር ገብረመድኅን እንየው √ መ/ር ኃይለማርያም ዘውዱ ▪ በሚድያ ደረጃ ፦ √ ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ √ መረጃ ቲቪ √ ኢትዮቤተሰብ ቲዩብ √ ጽዋ ቲዩብ √ አሐዱ ሬድዮ √ ኢትዮ 360 √ ኢኦተቤ ቲቪ √ ሃገሬ ቲቪ √ የማንቂያ ደዉል [ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ ና መ/ር ምህረተአብ አሰፋ] ይዘረዝራል። ሥርዓታዊና መዋቅራዊ የሆነውን ጥቃትና መጪውን ብርቱ የፈተና ጊዜ ለመቋቋም ይቻል ዘንድ ኦርቶዶክሳውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለቤተክርስቲያን ህልውና በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ይህ የአሁኑ ጊዜ ነው። #በፀሎት እንበርታ ምህመናን መስቀሉን ይዘን እንከተለው
نمایش همه...
👤ቴዲ አፍሮ✔️ አዲስ ሙዚቃ 🎧 ናታን 2022 ♦️➖--➖➖JOIN➖--➖➖♦️ ☆ @New_Ethiopian_music ☆ ☆ @New_Ethiopian_music  ☆ ★------------------------------------★ ☆ You Tube⚀ DondorTube  ☆ ☆  https://bit.ly/2WMka5Z ☆ ♦️➖➖➖➖--➖➖➖➖➖♦️
نمایش همه...
#ውሻ ነኝ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ባለ ብዙ ታሪክ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን ታዲያ ብዙ ሰዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ ይጠመቁ ነበር፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታዲያ አንዳንዶች የማትደገመዋን አንዲት ጥምቀት እንደ ጠበል ደጋግመው መጠመቅ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ለዚህ መላ አበጀ፡፡ አንድ ሰው ከተጠመቀ በኋላ በአንገቱ ላይ የማይወልቅ ክር እንዲያስር አደረገ፡፡ በሒደትም ይህን ክር ያሰረ ሰው የተጠመቀ ክርስቲያን መሆኑ ምልክት ሆነ የኋላ ሊቃውንትም ይህንን የማዕተብ ሥርዓት ከኦሪት እስከ ሐዲስ አጣቅሰው አስፋፍተው አስተማሩበት፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በክርስቲያኖች ላይ ይህንን ክር በማሰሩ ታዲያ የክርስትና ተቃራኒዎች ዘበቱበት ‘ብለህ ብለህ ደግሞ እንደ ውሻ በየሰዉ አንገት ላይ ክር ማሰር ጀመርህ?’ ብለው ተሳለቁበት ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ ፦ ‘ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው ፤ እኔ ለክርስቶስ ታማኝ ውሻው ነኝ’ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ #ሼር Telgarm👉https://t.me/Ethal777 Youtube👉https://youtube.com/channel/UCy31jIuDx1aTo8IloPnzPYQ
نمایش همه...