cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🏷 قناة السلف الصالح 🔍

🔍የተለያዩ ዳእዋዎች ትምህርቶች እንዲሁም ለዑማው ጠቃሚ ነገሮች በሱና ኡስታዞች የሚተላለፍበት ቻናል ነው:: 🔘ቁርአንና ሐዲስን በቀደምቶች በሰሃቦች አረዳት ለዑማው ማድረስ.. ከሽርክ እና ቢዳአ ማስጠንቀቅ❗️ 👉ሀቅ ለሚፈልግ ሰው አንድ ደሊል ይበቃዋል ለስሜት ባልተቤቶች ምንም ቦታ የለንም :

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
274
مشترکین
-124 ساؚت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-330 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ » " ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ ፡፡ " የአላህ መልእክተኛ የዘረኝነት አስከፊነትና የከረፋ ጥንብ መሆኑን እንዲሁም አንዱ ሙስሊም በሌላው ላይ ያለው ሐቅ ምን እንደሆነና መግደሉ ኩፍር መስደቡ ፊስቅ መሆኑን የተናገራባቸው ሐዲሶች አንድ መፅሀፍ ይወጣቸዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ልቦና በወንጀል ከታወረ ማየትም መስማትም አይችልምና ከልቦና መታወር ጠብቀኝ ብሎ አላህን መለመን ያስፈልጋል ። አላህ አላዋቂዎች በሚሰሩት ግፍ ምክንያት ከሚመጣ መቅሰፍትና ፈተና ይጠብቀን ። የሰውም የአጋንንትም ሸይጣኖችን የስራቸውን ሰጥቶ የወንድሞቻችንን ደም ይጠብቅልን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የማንም ብሄር ሆኖ መፈጠር ወንጀል አይደለም ። ይድረስ በሳውዲና በየትኛውም የዐለማችን ክፍል ለምትኖሩ ኢትዮዽያዊያን ሙስሊሞች ። የትም ኑሩ የትም ተፈጠሩ የየትኛውም ብሄር ወይም ጎሳ አባል ሁኑ ይህ በማናችሁም ላይ ወንጀል ሊሆን አይገባም ። ምክንያቱም ማንም ከዚህ ብሄር ( ጎሳ ) መፈጠር እፈልጋለሁ ብሎ አላህ ዘንድ ማመልከቻ አስገብቶ የተፈጠረ የለም ። ለምን ኦሮሞ ሆንክ ለምን አማራ ሆንክ ብሎ ሰውን መግደል ፣ አካል ማጉደል ፣ ደም ማፍሰስ የተከበረውን የሰው ልጅ ከፈጠረው አምላክ ጋር መዋጋት ነው ። በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ነብዩ ከመላካቸው በፊት የነበሩት የመሀይማን ህዝቦች ተግባር ነው ። እንደዚህ አይነቱ ተግባር በተለይ በሙስሊሞች ሲፈፀም በጣም ያሳዝናል ። በአላህና በመጨረሻ ቀን ያመነ ሙስሊም ፣ ነገ ራቁቱን አላህ ፊት የሚቆም መሆኑን ያመነ ሙስሊም ። እንዴት ወንድሙን ከዚህ ብሄር ነው የተፈጠርከው ስለዚህ ሞት ይገባሀል ብሎ ይገድላል ? ‼ አሳፋሪ ነው ። ኢስላም አላህ የሰውን ልጅ በብሄርና በጎሳ ከፋፍሎ የፈጠረው ሊተዋወቁበት እንጂ ሊፎካከሩበት ፣ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ሊባባሉበት እንዳልሆነ በሑጅራት ምእራፍ 13ኛው አንቀፅ እንዲህ በማለት ይነግረናል : – « يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ » " እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው ፡፡" በዚህ መለኮታዊ የአላህ ቃል አላህ የሰውን ልጅ ከወንድና ከሴት በጎሳና በነገድ ከፋፍሎ የፈጠረው ለመተዋወቅ እንደሆነና ከዚህ ውጪ ትርጉም የሌለው መሆኑን ነው ። በዚህ መለኮታዊ የአላህ ቃል የሚያምን ሙስሊም በምን መመዘኛ አንዱን ከዚህ ጎሳ መፈጠር አልነበረብህም ወይም ሆነህ በመፈጠርህ ወንጀለኛ ያደርግሀል ብሎ አባሮ አድኖ ይገድለዋል ? ‼ እስኪ መልሱን ይንገሩን ። ይህ ማለት ጦርነቱ ከአላህ ጋር ነው ማለት ነው ። እንዴት እገሌን አማራ ወይም ኦሮሞ አድርገህ ፈጠርክ ብሎ ጠርነት መክፈት ነው ። በጣም አሳፋሪ ተግባር መሆኑ ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ጥፋት እንዲሰፍን መቅሰፍት እንዲመጣ የሚያደርግ ነው ። የዚህ አይነቱን ተግባር የማያወግዝ ትውልድ መቆሚያ የሌለው በላእ ለመቀበል ራሱን ያዘጋጅ ። እንዲህ አይነቱን ድርጊት ማስቆም የማይችል መንግስት በመከራና ሰቆቃ የሚኖር ሀገርን ለመምራት ራሱን ያዘጋጅ ። አላህ የሰው ልጆች የሚሰሩት ሀጢያት በምድር ላይ ጥፋት እንዲንሰራፋ ምክንያት የሚሆን መሆኑን ሲነግረን በሩም ምእራፍ በ41 ኛው አንቀፅ እንዲህ ይለናል : – « ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ » " የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና ፡፡ " በዚህ አንቀፅ አላህ እንደሚነግረን የሰው ልጆች በሚሰሩት ግፍ ምክንያት በምድርና በባህር ላይ መከራ እንደሚንሰራፋ ( አላህ መቅሰፍት የሚያመጣ ) መሆኑን የመቅሰፍቱ መምጣት ሰዎቹ ከግፋቸውና ከበደላቸው ይመለሱ ዘንድ ተፈልጎ መሆኑን ነው ። ይህ ማለት ሰዎች በሰው ሲመከሩ አሻፈረኝ ካሉ የሚመክራቸው መከራ መምጣቱን ነው ። ነገር ግን መከራም መጥቶ ላይመከሩ ይችላሉ ። እንከን የሌለው የኢስላም አስተምሮ አንድ ሰው ሌላውን ያለ ወንጀሉ በግፍ ከገደለ የሰውን ዘር በሙሉ እንደገደለ መሆኑን በተቃራኒው አንዲትን ነፍስ ከሞት ለመትትረፍ ምክንያት የሆነም የሰውን ዘር ባጠቃላይ ከሞት ለመትረፍ ሰበብ እነደሆነ ነው የሚነግረን ። ይህ የመጠቀ መርህ በማኢዳ ምእራፍ በ32 ኛው አንቀፅ አላህ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – « مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِالْبَيِّنَاتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِي الْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ » " በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው ፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን ፡፡ መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው ፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው ፡፡ " የእነዚህ ረቂቅ መርሆችና አስተምሮዎች ባለቤት የሆነ ሙስሊም ወንድሙን በግፍ እንዴት እንደ ከብት አስተኝቶ ያርዳል ?‼ ነው ወይስ ለሸይጣናዊ አመለካከት ዲኑን ሽጦ ከአላህ ጋር መገናኘት የሚባል ነገር የለም ብሎ በመጪው ዐለም ክዶ ነው ? ይከብዳል ።!!!!! እባካችሁ ሙስሊሞች ከእንቅልፋችሁ ንቁ አኼራን አስታውሱ ካልነበራችሁበት ያስገኛችሁን እሱ ፊት ራቁታችሁ የምትቆሙት አላህን ፍሩ ። ወደራሳችሁ ተመለሱ ሀገራችሁንና ህዝባችሁን ከመከራ አድኑ ። በሰው ልጆች ደምና መከራ ለሚከብሩ በሰው አምሳል ለተፈጠሩ ሰው በላ አውሬዮች ሸቀጥ አትሁኑ ። በጣም የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው በአሁኑ ጊዜ ቁርኣን በወረደበት ፣ ጅብሪል በተመላለሰበት ፣ ነብዩ አውስና ኸዝረጅን ከ50 አመት የእርስ በርስ የመሀይምነት እልቂት በኋላ በላ ኢላሃ ኢልለላህ ( በኢስላም) አንድ ባደረጉበት ሀገር ሳውዲ ላይ የዚህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በሀገራችን ሙስሊሞች መካከል መፈፀሙ ነው ። ውድ በሳውዲ የምትኖሩ የሀገራች ሙስሊሞች ዛሬ ነገ ሳትሉ ካላችሁበት የዘረኝት ስካር ወጥታችሁ ወደ አላህ ተመልሳችሁ ተውበት አድርጉ ። ውድ የኦሮሞና አማራ መሻኢኽና ዑለሞች እንዲሁም ዱዓቶች አላህ የጣለባችሁን አደራ ከምን ጊዜውም በላይ የምትወጡበት ጊዜ አሁን ነውና በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ድርሻችሁን ተወጡ ካልሆነ የሚመጣውን ፊትና ለመቀበለደ ተዘጋጁ ። ‼ አላህ በምድር ላይ ጥፋት ተንሰራፍቶ ግፍ ሲበዛ ግፈኞቹን ብቻ ለይቶ የማይነካ ፈተና የሚመጣ መሆኑንና እንድንጠነቀቅ በአንፋል ምእራፍ በ25ኛው አንቀፅ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –
نمایش همه...
👉 የሙሐረም ወርና ሙስሊሞች የሙሐረም ወር ከሂጅሪያ ወሮች የመጀመሪያውና አላህ ለይቶ ካላቃቸው አራቱ ወራቶች አንዱ ነው ። ይህ ወር የሂጅሪያ ወር መጀመሪያ ቢሆንም ሙስሊሞች የዘመን መለወጫ ብለው በዚህ ወር መግቢያ ላይ የተለየ የሚሰሩት ነገር የለም ። ይልቁንም ሙስሊሞቸው ህይወታቸው የሰከንዶች ሽርፍራፊ ጥርቅም መሆኑንና እየአንዳንዱ ሽርፍራፊ በተቀነሰ ቁጥር ከእድሜያቸው እየተቀነሰና ወደ ቀብር እየተጠጉ መሆናቸውን ነው የሚያውቁት ። በመሆኑም በየትኛውም ዘመን ፣ አመት ፣ ወር ፣ ሳምንት ፣ ሳአት ፣ ደቂቃና ሰከንድ ለሚቀጥለው ዐለም መዘጋጀት እንዳለባቸው ያውቃሉ ። ከዚህ ዝግጅታቸው አንዱ ምንዳና ቱሩፋት አለባቸው በተባሉ ቦታና ጊዜያቶች የታዘዙትን መልካም ስራዎች መስራት ነው ። በመሆኑም በሙሐረም ወር ውስጥ የታዘዙ የአምልኮ አይነቶችን ይፈፅማሉ ምንዳውንም ከጌታቸው ይጠብቃሉ ። የሙሐረም ወር ከአራቱ የተከበሩ ወራቶች ለመሆኑ በመልእክተኛው ሐዲስ የተረጋገጠ ሲሆን ከ12ቱ አራቱ የተከበሩ መሆናቸው ደግሞ አላህ በተከበረው ቃሉ በተውባ ምእራፍ 36ው አንቀፅ እንዲ ብሎ ይነግረናል : – ÂŤ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ وَقَاتِلُوا الْمُشْرِكِينَ كَافَّةً كَمَا يُقَاتِلُونَكُمْ كَافَّةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ Âť " የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው ፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው ፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው ፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው ፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ ፡፡" የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – የተከበሩት ወራት የተኞቹ እንደሆኑ በሚከተለው በሐዲሳቸው ነገረውናል : – عن أَبي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أنه قَالَ :  " إنَّ الزَّمَانَ قَدْ اسْتَدَارَ كَهَيْئَتِهِ يَوْمَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ " متفق عليه አቡ በክረተ የተባለ ሶሐብይ እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : – " ዘመን አላህ ሰማይና ምድር ሲፈጥር ወደ ነበረበት ተመልሷል ። ( የሐጅ ወር አላህ በዙል ሒጃ አድርጎታል ። መሀይማኖች የቀየሩት ውድቅ ሆኖ ወደዛው ተመልሷልና ይህን ያዙ ) ። አመት አስራ ሁለት ወር ነው ። ከእነሱ ውስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው ። ሶስቱ ተከታታዮች ናቸው ። ዙል ቀዕዳ ፣ ዙል ሒጃ ፣ ሙሐረም , ረጀብ ደግሞ በጁማደ ሳኒና በሻዕባን መካከል ነው ። " ከእነዚህ ከአራቱ ደግሞ ሙሐረም ይበልጥ የተከበረ ወር መሆኑን ሲነግሩን የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ : – عن أبي Ř°Řą رضي الله عنه قال :  سألت Ř§Ů„نبي – صلى الله عليه وسلم – : أي الليل خير وأي الأشهر أفضل؟ فقال : " خير الليل جوفه وأفضل الأشهر شهر الله الذي تدعونه المحرم " አቡ ዘር የተባለ ሶሐብይ – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛን የትኛው ለይል ይበልጣል ? የትኛውስ ወር በላጭ ነው ብዬ ጠየቋቸው ። እሳቸውም እንዲ አሉ : – " ከለሊቱ ውስጥ በላጩ ድቅድቁ ( ከመካከለኛው በኋላ) ያለው ነው ። ከወሮች ደግሞ እናንተ ሙሐረም ብላችሁ የምትጠሩት ነው ። " በዚህ ወር ውስጥ ተወዳጅ የሆው መልካም ሾል ደግሞ ፆም ነው ። ይህንንም መልእክተኛው እንዲህ በማለት ይነግሩናል : –  ŘšŮ† أبي هريرة أن النبي صلى الله عليه وسلم قال :  " أفضل Ř§Ů„ؾيام Ř¨ŘšŘŻ شهر رمضان شهر الله الذي تدعونه المحرم وأفضل الصلاة بؚد الفريضة Ů‚يام الليل " . رواه مسلم አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል : – " ከፆሞች ሁሉ በላጩ ከረመዳን ወር በኋላ ሙሐረም ብላችሁ የምትጠሩት ወር ( መፆም ነው) ከሶላት ሁሉ በላጩ ከፈርድ ሶላት በኋላ የለይል ሶላት ነው ። " የአላህ መልእክተኛ በሙሐረም ወር መፆም ( የቻሉትን ማለት ነው) ከረመዳን ወር ፆም ቀጥሎ የተወደደ መሆኑን እየነገሩን ነው ። በመሆኑም አንድ ሰው በሙሐረም ወር ውስጥ የቻለውን ያክል ቢፆም በጣም ተወዳጅ ነው ። እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ከረመዳን ውጪ ወሩን ሙሉ መፆም እንደማይቻል ነው ። በዚህ በሙሐረም ወር የዐስረኛውን ቀን መፆም ያለፈውን አመት ወንጀል የሚያስምር መሆኑን መልእክተኛው በሚቀጥለው ሐዲሳቸው ነግረውናል ። عن أبي قَتادة رضي الله تعالى عنه ، عن الرّسول - صلّى الله عليه وسلّم - قال : " صوم ؚاشوعاإ يكفِّر السّنة الماضية " رواه النسائي አቡ ቀታዳ የተባለ ሶሐብይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : – " የዓሹራእ ቀንን መፆም ያለፈው አመት ወንጀል ያስምራል ። " ከእነዚህ መረጃዎች በመነሳት ሙስሊሞች በሙሐረም ወር ከፆም የበለጠ የተወደደ ሾል አለመኖሩን ያውቃሉ ። በቻሉት አቅም በፆም ወደ አላህ ይቃረባሉ ከዚህ ውጪ አላስፈላጊ አመለካከትና እምነት ከኢስላም አንፃር ቦታ የለውም ። አላህ ከተጠቃሚዮች ያድረገን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 1
ሙስሊም፣ ሙስሊም ወንድሙን ይቅርና ሌላውንም መበደል አይፈቀድለትም!! ————— አላህ መበዳደልን በእጅጉ እርም አድርጓል!!። ሙስሊሙንም ሆነ ሙስሊም ያልሆነን አካል መበደል አምላካችን አላህ በእጅጉ የከለከለው ተግባር ሲሆን ሙስሊም ከሙስሊም ሲሆን ደግሞ ይበልጥ የከበደ ነው!!። አላህ እንዲህ አለ:- وَوَقَعَ الْقَوْلُ عَلَيْهِم بِمَا ظَلَمُوا فَهُمْ لَا يَنطِقُونَ «በመበደላቸውም በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እነርሱም አይናገሩም፡፡» አን-ነምል 85 በምንወደውም ሆነ በምንጠላው ሰው ላይ ፍትሃዊ እንድንሆንና ከበደል እንድንርቅ እንዲህ በማለት ነግሮናል:- يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡» አል-ማኢዳ 8 የቅርብን ሰውም ሆነ የሩቅ ሰው፣ ሙስሊምም ሆነ ሌላን አካል መበደል በእስልምናችን በእጅጉ የተወገዘ ሀራም ተግባር ነው!። መበዳደልን የሚከለክሉ ሌሎች በርካታ የቁርኣን አንቀፆችም አሉ። አላህ በሀዲሰ'ል ቁድስ መበዳደልን እርም እንዳደረገ እንዲ በማለት ነግሮናል:- “ባሮቼ ሆይ! እኔ መበደልን በራሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ፣ በመካከላችሁም እርም አድርጌያለሁና አትበዳደሉ።” [ሙስሊም 2577 ዘግበውታል።] ከኢበኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለውም፣ አያዋርደውም። ለወንድሙ ጉዳይ የቆመ (የሆነ) ሰው፣ አላህ ለርሱ ጉዳይ ይሆንለታል። ለአንድ ሙስሊም ከጭንቀቱ መውጫ ያበጀ (ያስተነፈሰ ሰው)፣ አላህ ለርሱ ከቂያማ ቀን ጭንቀቶች መውጫ ያበጅለታል። የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሸፈነ ሰው አላህ በእለተ ትንሳዔ (ቂያማ) ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል።” [ቡኻሪ 2442 ዘግበውታል] ከጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “ወዮላችሁ በደልን ተጠንቀቁ! እሱ እኮ በእለተ ትንሳዔ ጭለማ ነው…” በሌላ ዘገባም እንዲህ ብለዋል:- “በደልን ፍሩ እርሱ እኮ የቂያማ ቀን ጭለማ ነው…” [አህመድ በሙስነዳቸው፣ ቡኻሪ በአደቡል ሙፍረድ፣ ሙስሊም በሶሂሃቸው ዘግበውታል] በደልን እንጠንቀቅ!! ውጤቱ የከፋ ነው!! የተበዳይ ዱዓም ግርዶሽ የለበትም!! በዳይ ከመሆን ተበዳይ መሆን ይሻላል!! ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
نمایش همه...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

ጫት እና አደጋው ✅✅✅✅ 🏝 ከኡስታዝ አቡ ኢልሃም ቻነል ተወስዶ ወደ pdf በወንድም አቡ ዒምራን የተዘጋጀ ➽ ጫት ዱንያዊ የሆኑ ጉዳቶች ያሉት ሲሆን 1, በገንዘብ ላይ፣ 2, በጤና ላይ፣ 3, በጊዜ ላይ፣ 3, በቤተሰብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ተዳሷል። ➼ በሌላ በኩል አኸራዊ ጉዳቶች ያለት ሲሆን ➻ ለምሳላ ከፆም፣ ➻ ከሶላት፣ ➻ ወንጀል ከመዳፈር አንፃር፣ ➻ ከሽርክ ጋር በተያያዘ እና የመሳሰለት ተዳሰዋል። 🚥 የቃመ ተጠቀመ ሳይሆን የቃመ ተለቀመ ነው የሚባሆው አዎ የቃመ ጥርሱን ይለቅማል ቤተሰቡን ይበትናል፤ ወንጀል ያጠራቅማል፤ ራሱንም ቤተሰቡንም ዲኑንም ሀገሩንም ይጎዳል። ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  đŸ–   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
نمایش همه...
ጫት እና አደጋው.pdf2.09 MB
👍 1
👉 የኒቃብ ጥላቻ በሽታ ሲሆን የታሪክ መዛግብቶች እንደ ሚያስነብቡት የአላህ መልእክተኛ ከመላካቸው በፊት አዩሁዶችና ነሳራዎች ( ክርስቲያኖች ) ዘንድ ኒቃብ የንፁህነትና የክብር ራስን የመጠበቂያ ምልክት እንደነበር ነው ። በዛን ዘመን አንድ ክብሯን የምትጠብቅና ከፀያፍ ተግባር ለመራቅ የፈለገች ሴት ሙሉ ልብስ ከነኒቃቡ ጋር ትለብስ እንደነብርና የዚህ አይነት ልብስ የምትለብስ ወጣት በማህበረሰቡ የተከበረች እንደነበረች መዛግብቶቹ ያስረዳሉ ። አላህ ነብዩ ሙሐመድን ሲልክ ሴትን ልጅ የክብር ማማ ላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው ሕያው ቃሉ ስለ ሒጃብ በሚቀጥለው ቃሉ አስቀምጧል ። « وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ » النور (31) " ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ፡፡ በእነዚህ አንቀፆች ሴት ልጅ የውበቷ መገለጫዎች ለማን ግልፅ ማድረግ እንዳለባትና ከማን መሰተር እንዳለባት አስቀምጧል ። በመሆኑም ኒቃብ ኢስላም ሴት ልጅ ክብሯን መጠበቅ ስትፈልግ እንድትለብሰው ሳይሆን ለብሳው ክብሯን መጠበቅ እንዳለባት አዟል ። ኒቃብ በኢስላም ክብንና ንፅህናን የሚጠብቁበት ብቻ ሳይሆን ወደ አላህ የሚቃረቡበት የአምልኮ ክፍል ነው ። ምክንያቱም አምልኮ ( ዒባዳ) ማለት የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ መፈፀም ስለሆ ነው ። በመሆኑም ኒቃብ በሁለቱም ሀገር እጅግ በርካታ ቱሩፋቶች ያሉት መሰተሪያ ሲሆን ከእነዚህ ቱሩፋቶቹ ውስጥ ጥቂት በቅርቢቱ ዓለም ካሉት ውስጥ እንመልከት : – አንደኛና ሁለተኛው – ተለይተው እንዲታወቁና ጎንታይ ባለጌዎች እንዳይጎነትሏቸው እንዳያስቸግሩዋቸውም ይረዳል ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ያላል : – « يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا » الأحزاب ( 59 ) " አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም ፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው ፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡" ሶስተኛው – ክብራቸውን ይጠብቁበታል ። አራተኛው – አላህን የመፍራታቸው ምልክት ነው ። አምስተኛው – ልባቸው በተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የታመሙ ሰዎች በእነርሱ ምክንያት እንዳይሳሳቱ ያደርጋል ። ስድስተኛ – ዝሙት እንዳይስፋፋ ያደርጋል ። እነዚህ ከብዙ ጥቂት ቱሩፋቶቹ ናቸው ። በመሆኑም ኢስላም ሴትን ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጣት ስለሆነ አንድ ሴት ጌጥ የሆነው ወርቋን ደብቃ ከምትጠብቀው በላይ ራስዋን ደብቃ ለሚገባው አካል ብቻ እንድታስረክብ ያዛታል ። ይህን ስትፈፅም የክብሩ ማማ ላይ ትወጣለች ። በጣም የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ኒቃብ የኋላ ቀርነት ምልክት አድርጎ ያየዋል ። ከዚህም በላይ አንዳንዶች ልጃቸው ዝሙት ሰርታ በዝሙት አርግዛ ሲያዩ የማይደነግጡትና የማይበሳጩት አይነት ብስጭት ኒቃብ ለብሳ ሲያዩ ይበሳጫሉ ።‼ ይህ በርግጥ ትልቅ በሽታ ነው ። ከዚህም በላይ ደግሞ ልጃችሁ ከፍራለች ቢባሉ በብስጭት የማይታመሙትን ያክል ታመው ሆስፒታል ይገባሉ ። ይህ ምናባዊ ሀሳብ ሳይሆን በገሀዱ ዐለም ያለ እውነታ ነው ። በቅርቡ ሶስት ኒቃብ የለበሱ እህቶቻችን ቤተሰቦች ላይ ከታየው አሳፋሪ ተግባር ውስጥ የአንደኛዋ እህት እናትና አባት በብስጭት ታመው አባትየው ሆስፒታል ይገኛሉ ። ‼ በእነዚህ እህቶች ላይ ከተማም ገጠርም ያለ ዘመድ አዝማድ በሙሉ ኒቃቡን ለማስወለቅ የሚችለውን ያደረገ ሲሆን የሁለቱ እስካሁን አልተሳካም ። በተለይ ቤተሰቦቿ በዚህ ምክንያት የታመሙት ፀንታ ነው ያለችው ። ከሁለቱ እህቶቿ አንደኛዋ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ መብትሽ ነው እኔ ጋር ነይ ብሎ ከዘመዶቿ አንዱ ወደ ማታውቀው ከተማ እንድሄድ ካደረገ በኋላ መንገድ ላይ ጠብቆ ከመኪና ስትወርድ የምታወልቂ ከሆነ ልውሰድሽ ካልሆነ አዚሁ ጥዬሽ ነው ምሄደው ብሎ የቀን ጨለማ ውስጥ እንድትገባ አድርጎ አስሆልቋቷል ። ‼ አላህ ይድረስልን እንጂ ኒቃብ ለበሽታ ሰበብ የሚሆንባቸው ሙስሊሞች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ። ለእህቶቻችን ፅናቱን ለቤተሰቦቻቸው አላህ ሂዳያ እንዲሰጣቸው ዱዓእ እናድርግ እላለሁ ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 6
👉 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል ሶስት የመጨረሻው ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ካወደመና ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድንና መማክርቶቹን እንዲሁም ጠባቂዮቹን ካስረሸነ በኋላ ዲርዒያን ሙሉበሙሉ ለማፅዳት ባደረገው ዑለሞችን የማደን ሂደት ሸይኽ ሱለይማን ኢብኑ ዐብዲላህ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብን በቁጥጥር ስር አደረጋቸው ። ሸይኽ ሱለይማን ማለት ተይሲሩል ዐዚዚል ሐሚድ ሸርሕ ኪታቡ ተውሒድን እየፃፉ የነበሩ ታላቅ ዓሊም ሲሆኑ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጅ ናቸው ። የጀመሩት ኪታብ የአጎታቸው ልጅ ዐ/ራሕማን ኢብኑ ሐሰን ፈትሑል መጂድ በሚል ጨርሰውታል ። ኢብራሂም ባሻ ስልጣናችን ተነካ ባሉ የቱርክ ኤምፓየር መሪዮች የፈለገውን ሰርቶ ስልጣናቸውን ከስጋት እንዲከላከልላቸው በአባትየው አማካይነት ስልጣን የተሰጠው አረመኔ ነውና የቁርኣንና ሐዲስ ዓሊም ክብር ምኑም አይደለም ። ሸይኽ ሱለይማንን የፊጥኝ አስሮ ወደ መቃብር ቦታ ወሰዳቸው ። እዛ ከመረሸንና ከረሀብ የተረፈውን ህዝብ ሰብስቦ የግብፅ የሙዚቃ ባንድ እያስጨፈረ በከባድ መሳሪያ እንዲመቱ አደረገ ። የሸይኽ ሱለይማን ስጋ ተቆራርጦ ተበታተነ ።‼ ጀናዛቸው ታጥቦ ተከፍኖ ሊቀበር ይቅርና አካላቸው እንኳን መሰብሰብ አዳጋች ሆነ ። በዚህ አላበቃም ኢብራሂም ባሻ ወደ ሱለይማን አባት ሄዶ በግብፅ አነጋገር ያ አጉዝ ( አጁዝ ) ( አንተ ሽማግሌ ሆይ) ቀተልና ኢብነክ ( ልጅህን ገደልኩት ) አለው ። የሸይኽ ሱለይማን አባት ግን ታሪክ የማይረሳው መልስ ሰጡት ። መልሱ የኢብራሂም ባሻን አእምሮ እንደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ሰርስሮ ገባ ። አባትየው እንዲህ ነበር ያሉት : – ኢን ለም ተቅቱልሁ ማተ ( ባትገድለውም ኖሮ ሟች ነበር ። !!!!! ከዚህ በኋላ ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያ ላይ አሻንጉሊቶቹን አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ ። ግብፅ ላይ ሹማምንቶች ፣ የጦር አበጋዞችና ዑለሞች ተሰብስበው እየጠበቁት መሆኑን ተነገረው ። እሱም በትካዜ የኋልዮሽ ተመልሶ እያየ ዑለሞችማ የዲርዒያ በረሀ ላይ ቀሩ አለ ። የሸይኽ ሱለይማን አባትም ዓሊም መሆናቸውን ያውቅ ነበርና ንግግሩ ከአእምሮ አልወጣ ብሎት ። በቱርክ ኤምፓየርና በመምለካ ተዋጊዮች መካከል የነበረው ጦርነት ለስልጣንና ለተውሒድ የተደረገ ጦርነት ነበር ። የአላህ ስራ አስገራሚ ነውና አላህ ያን ግዙፍ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር ስርወ መንግስ ከአምስት አመት በኋላ ዲርዒያ ላይ ዳግም ላይመለስ ገርስሶ ከእነዚያ የተውሒድ መሪዮች ጋር ተቀብሮ የነበረው የተውሒድ ችግኝ እንቡጥ በደማቸው በዐብዱላሂ ልጅ ቱርኪ አማካይነት ዳግም እንዲያብብ በማድረግ የተውሒዷን ሀገር እስከ ዛሬ እንድትቀጥል አድርጓል ። የቱርክ ኤምፓየር ግን በዛው ማብቂያው ሆኗል ። ለአላህ የሆነ ይቀራል የሚባለው ለዚህ ነው ። ተፈፀመ ክፍል አንድን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5079 ክፍል ሁለትን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5081 https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ…

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የሸይኽ ሙሐመድና የዳዕዋቸው ሁኔታና የተከታያቸው ብዛት ሲያይ ሶስት ነገር ቃል እንዲገቡለት ጠየቃቸው ። 1ኛ — የያዝከው ነገር አላህ ከፍ ሲያደርገው ጥለኸኝ ላትሄድ 2ኛ – በየአመቱ የምቀበለው ግብር አለ ላትከለክለኝ 3ኛ – የዲን ጉዳይ እሳቸው ሊመሩና የዱንያዊው ስልጣን ለሱ እንዲሆን ሸይኽ ሙሐመድ ጥሎ መሄድን በተመለከተ ደሜ ከደማችሁ ጋር ነው ጥዬህ አልሄድም ። የግብሩን በተመለከተ አላህ በምርኮ ይተካልሀል ። የዱንያው ስልጣን ያንተ ነው አሉት ። ከዚህ ስምምነት በኋላ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በስልጣን ዲኑን እየረዳ ሸይኽ ሙሐመድ ዲኑን እየመሩ ዳዕዋው ቀጠለ ። በጋራ ሆነው የሚመለኩ ቀብሮች ላይ የተሰሩ ዶሪሖችን መናድ ጀመሩ ። ሸሪዓ በስራ ላይ ዋለ ። ዝሙት የሰራ እየመጣ ሸሪዓዊ ቅጣት ልቀጣ ማለት ጀመረ ። ሽርክና ቢዳዓ አንገታቸውን ደፉ ። ወንጀል መክሰም ጀመረ ። የተውሒዱ ብርሀን አድማሱን እያሰፋ በአራቱም አቅጣጫ ይኖግድ ጀመር ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ስዑዲያ) የሚባለው ሀገር በሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ አባት ስም ተመሰረተ ። ሳውዲ ከመመስረቷ በፊት ነጅድና አል ጀዚራ አል ዐረቢያ የሚባሉ ግዛቶች በወቅቱ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር አያውቀውም ነበር ። እነዚህ አካባቢዮች በአብዛኛው በጎሳ መሪዮች የሚመሩ የነበሩ ስለሆኑና እንዳጠቃላይ በረሀማ ግመል አርቢ ዘላኖች የሚበዙበት ለስርኣቱ የሚያስገኘው ብዙ ጥቅም ስላልነበረ ከዑስማንዮች ትኩት ተነፍጓቸው የቆዩ ነበሩ ። በተወሰነ መልኩም ቢሆን ትኩረት የሚሰጠው ለመካና ለመዲና ነበር ። ይህም የዐለም ሙስሊሞች ልባቸው የሚንጠለጠልባቸውና ለሐጅና ዑምራ እንዲሁም ለነብዩ መስጂድ ዚያራ የሚፈለጉ ስለነሩ ነው ። በፍቅ የሻፍዕይ መዝሀብ በዐቂዳ ሱፍይ የነበረው የቱርክ ኢምፓየር ስርኣት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ ሳውዲን መመስረትና የተውሒድ ዳዕዋ ማወጅ የቀብር አምልኮ ማስወገድና ሸሪዓ በስራ ላይ ማዋል የራስ ምታቱ ሆነ ። መስራቾቹ ለትውልድ አስረክበው ሄደዋል ። ማግኘት አይቻልም ። የተመሰረተውን ሀገር ማፍረስና መሪዮቹን ማጥፋት የቱርክ ኤምፓየር ትልቅ የቤት ስራ ሆነ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 1
🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ የቱርክ ኤምፓየር ሱዑዲያ የምትባለውን ሀገር ማጥፋትና መካና መዲናን ማስመለስ ጊዜ የማይሰጠው ዋናው ስራ አደረገው ። ግዙፍ ጦር አዘጋጅቶ ወደ ዐረቢያ ግዛት ላከ ። ጦሩ ወደ መዲና ለመድረስ በሚያደርገው ግስጋሴ ያገኘውን ሁሉ ከምድር በታች እያደረገ ጉዞ ቀጠለ ። መዲና ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዶ ህፃን አዋቂ ፣ ሽማግሌ አሮጊት ሳይል እየረሸነ መዲናን ተቆጣጠረ ። መዲና የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶችን ወደ ኢስታንቡል ጫነ ። እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች አሁንም በቱርክ ዋና ከተማ ሙዘየም ላይ ይገኛሉ ። አላማው የመምለካን መሪዮች የሱዑዲ ዋና ከተማ የነበረችው ዲርዒያን ወሮ መሪዮቹን ማርኮ መቀጣጫ ማድረግና የተውሒድዋን ሀገር ማፈራረስ ነበርና መገስገስ ጀመረ ። ጉዞውን ወደ መካ ያደረገው ይህ ጦር ማውደሙንና መረሸኑን በመቀጠል መካ ደረሰ ። መካ ላይም የተለመደውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማድረግ በቁጥጥሩ ስር አደረጋት ። ሒጃዝን ( መካና ነዲናን) በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ጉዞውን ወደ ነጅድ አደረገ ። የዚህን ትልቅ ሀላፊነት መወጣት ለሚስር ( ግብፅ ) መሪዮች አስረከበ ። በወቅቱ የነበረው ሙሐመድ ዐሊ ባሻ ጦሩን እየመራ ወደ ዲርዒያ አቀና ። ከመጀመሪያ የባሰ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተለያዩ ከተሞች እያደረሰ ቢሄድም ዲርዒያን መቆጣጠር አልቻለም ። መሪነቱን ለልጁ ኢብራሂም ባሻ አስረክበ ። ኢብራሂም ባሻ በአዲስ መልኩ ጦሩን አደራጅቶ ሳር ቅጠሉን እያነደደ የህፃንና አዋቂን የአረጋዊያንን ጀናዛ ለአሞራ እየተወ ወደ ዲርዒያ ገሰገሰ ። ዲርዒያን ለሰባት ወር አካባቢ ከበባት ። ምንም ነገር እናዳይገባና እንዳይወጣ ከለከለ ። ረሀቡና ጥሙ ህፃናትና አረጋዊያንን ማርገፍ ሲጀምር የሳውዲ ( የሱዑዲ ) መሪ የነበረውን ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ከበባው እንዲያበቃና ዋስትና ከሰጠው እጁን እንደሚሰጥ መልእክት ላከ ። ኢብራሂም ባሻ ጥያቄውን የተቀበለው መሆኑና ምንም ጉዳት እንደማያደርስ መልስ ሰጠ ። ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ከነመማክርቱና ጠባቂዮቹ እጅ ሰጠ ። አሳፋሪው ኢብራሂም ባሻ ግን ቃሉን አፍርሶ ዲርዒያን አነደዳት ። ‼ በህዝቡ ላይ የተለመደውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ አካሄ ። ሙርከኛቹን ወደ ግብፅ ላካቸው ። ከግብፅ ወደ ቱርክ ተላኩ ። ቱርክ ላይ ዐብዱላሂ ኢብኑ መሐመድ ተገሎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ የቱርክ ኤምፓየር መሪ ተላከ ። የተቀሩትም ተረሸኑ ። ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ለማፅዳት ዑለሞቹን ማደን ጀመረ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 1
♻️ #እኔ_ሰለፍይ_ነኝ_ማለቱ ምን አስፈለገ #ሙስሊም_በሚለው ለምን #አንብቃቃም ? ➥ይሄ የመከፋፈል ጥሪ አይደለምን? የሸይኹ መልስ፡ ሙሐመድ ናስር አል-ዲን አል አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና ጥሩ ውይይት፣ ሰለፊይ የሚለውን ቃል ለማረጋገጥ ጥሩ ውይይት። በውስጡ መከፋፈልን በመፍራት እኔ ሰለፊይ ነኝ ማለትን ለሚቃወሙት ምላሽ ይዟል። ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁላህ ስለ ጉዳዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ወንድሞቻችንን የእውቀት ፈላጊወች ይህንን ውይይት እንዲያስታውሱት እጠይቃለሁ። ምክንያቱም ፍሬው በጣም አስፈላጊ ነውና። ➛ጥያቄው ፦ አንዳንድ ዱዓቶች እንዲህ ይላሉ፡- #እኔ_ሰለፍይ_ነኝ ማለትን #እቃወማለሁ (ምክንያቱም) #ሰዎች እንደ #ወገንተኛ #እንዳይመለከቱኝ_በመስጋት፣ #ይህ አባባል #ትክክል ነው #ወይንስ #ሰለፊያን_ለሰዎች_ማስረዳት_አለብኝ? መልስ፡- በእኔ እና በቁርኣንና በሱና አብረውን ካሉት የእስልምና ጸሃፊዎች በአንዱ መካከል ውይይት ተደረገ። የእውቀት ፈላጊወች ይህንን ውይይት እንዲያስታውሱ እጠይቃለሁ; ምክንያቱም ፍሬው በጣም አስፈላጊ ነው። ➜ እኔም እንድህ አልኩት፦ #አንድ_ጠያቂ #መዝሃብህ_ምንድነው? #ብሎ_ቢጠይቅህ፡ መልስህ ምንድን ነው? ➛እርሱም እንድህ አለኝ፡- #ሙስሊም (ብየ እመልሳለሁ) ➜እኔም እንድህ አልኩት፦ #ይህ_መልስ_ስህተት ነው። ➛እርሱም፡- #ለምን? አለኝ ➜ እኔም ፦ #አንድ_ጠያቂ #ሃይማኖትህ_ምንድነው? ብሎ ቢጠይቅህስ አልኩት ➛እርሱም፡- #ሙስሊም (ብየ እመልሳለሁ) አለ ➜ እኔም እንድህ አልኩት፡- #በመጀመሪያ #ሃይማኖትህ_ምንድን ነው? ብየ አልጠየቅኩህም። #የጠየቅኩህ_መዝሃብህ ምንድነው? ብየ ነበር። ➤ እና ዛሬ #በእስልምና_ምድር ላይ #ብዙ እና #በጣም_ብዙ_መዝሃቦች እንዳሉ ታውቃለህ። ➥ #ጥቂቶቹ_በፍፁም_የእስልምና አካል #እንዳልሆኑ_በመወሰንም_ከእኛው_ጋር_ነህ። ➥ለምሳሌ እንደ ድሩዝ፣ ኢስማዒሊያ፣ ዓላውያ እና የመሳሰሉት። ⛔️እንድህ ከመሆኑም ጋር እነርሱ ግን፡- #እኛ_ሙስሊሞች_ነን ይላሉ። ➥እዚህ ላይ #በእርግጥ_ከእስልምና_ወጥተዋል_የማንላቸው_ሌሎች_አንጃዎችም አሉ። ● #በብዙ_ጉዳዮች_ከቁርኣንና_ከሱና #ያፈነገጡና_የተሳሳቱ_አንጃዎች_መካከል #መሆናቸው_ምንም_ጥርጥር_የለውም። እንደ ሙዕተዚላ፣ ኸዋሪጅ፣ ሙርጂዓ፣ ጀብሪያ እና የመሳሰሉት። እና ምን ይመስልሃል #ዛሬ #እነዚህ (አንጃወች) #አንተ_ጋር_አሉ_ወይ?(አሉ ብለህ ታምናለህ ወይ) ➛እርሱም፡- አዎ አለኝ ➜ እኔም እንድህ አልኩት፦ ከዚሁ ጋር #ከእነዚህ #ሰዎች_አንዱን #መዝሃብህ #ምንድነው? #ብለን_ብንጠይቀው ልክ እንዳንተ ንግግርህን በመጠበቅ #ሙስሊም_በማለት_ይናገራል ! ➤ #አንተም_ሙስሊም ነህ #እርሱም_ሙስሊም ነው። ➦አሁን #ከእስልምናህና_ከሃይማኖትህ_በኋላ #ስለ_መዝሃብህ_በመልስህ_ግልጽ_እንድታደርግ_እንፈልጋለን? ➛እርሱም፡- #ስለዚህ_መዝሃቤ_ቁርኣንና #ሱና_ነው አለ። ➜እኔም ፡- #በድጋሚ ይህ #መልስ_በቂ_አይደለም አልኩት። ➛እርሱም፡- #ለምን? አለኝ ➜እኔም ፡- 👉ምክንያቱም #የጠቀስናቸው_ሰዎች_ሙስሊም_መሆናቸውን_ስለራሳቸው_ይናገራሉ። ➤አንዳቸውም ቢሆኑ፡- #እኔ_ቁርኣንና_ሱናን_አልከተልም_አይሉም ። ⛔️ ለምሳሌ፡- #ሺዓዎች፡- #እኛ_ቁርኣንና_ሱናን_እንቃወማለን_ይላሉ? ይልቁንም፡- #እነሱ_በቁርኣንና_በሱና #ላይ ነን #ይላሉ። #እናንተም_ከቁርኣንና_ከሱና_አፈንግጣችኋልይላሉ። ኡስታዝ ሆይ፡- እኔ #በቁርአን_እና_በሱና ላይ #ሙስሊም_ነኝ_ማለቱ_በቂ_አይደለም። #ሌላ #ማቀፊያ_መኖር_አለበት። ➦ ምን ይመስልሃል፡ #ቁርኣን እና #ሱናን #በአዲስ_መንገድ_መረዳት_ይፈቀዳል? ወይንስ #ቁርኣን እና #ሱናን #በመረዳት_ረገድ #የሰለፉነ_ሷሊህ(የመልካም ቀደምቶቻችን) አረዳድን #መጠበቅ_ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው? ➛እሱም: #ይሄማ_ቅሮት_የሌለው_ጉዳይ ነው አለ። ➜እኔም፡- የሌላ መዝሃብ ተከታዮች - ከእስልምና ውጪ ያሉት ፤ #እስልምናን #የሚሞግቱት አሁንም #በእስልምና_ክበብ ውስጥ ያሉ ነገር ግን #አንዳንድ_ፍርዶቹን_የተው #ከአንተና_ከእኔ ጋር ፡ #እኛ_በኪታብና_በሱና ላይ #እንድሁም #በሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ ላይ ነን #ማለት #አለባቸው_ብለህ_ታምናለህን? አልኩት። ➛እሱም: #አይ_ከእኛ_ጋርማ_መጋራት #የለባቸውም። አለ ➜እኔም ፡- #ስለዚህ #እኔ_ኪታብና_ሱናን_እከተላለሁ ማለት #በቂ_አይደለም፡ #ሌላ—ማቀፊያ_ሊኖር ይገባል። አልኩት ➛እርሱም፡- አዎ። አለ ➜ እኔም፡- እንደዛ ከሆነ ፡ #እኔ_በቁርኣንና_በሱና እንዲሁም #በሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ ላይ ነኝ እንዲህ ማለት አለብህ። ➤ አሁን ወደ ዋናው ነጥብ እንደርሰናል #የፊደል_ሰውና እና #ጸሃፊ_ለሆነው እንዲህ አልኩት፡- #እነዚህን ሁሉ #ቃላቶች_የሚያጠቃልልን በአረብኛ ቋንቋ አንዲት ቃል አለች ወይ፦ #ሙስሊም_በቁርኣንና #በሱና ላይ እና #የሰለፉነ_ሷሊህ_መንሃጅ የሚሉትን የሚያጠቃልል #ለምሳሌ #እኔ_ሰለፍይ ነኝ? ማለትን ይመስል እርሱም፡- #አወ_እንደዚሁ ነው። (ትክክል ነው) አለ (እሱም) #ተፀፀተ_መልሱም_ይህ ነው። አለ ➤አንድ ሰው እንደዚህ (ስለሰለፊያ) ቢቃወምህ የጠቀስናቸውን ቃላት ንገረው፡ አንተስ? እሱም ፡ ሙስሊም ነኝ ይልሃል እና የቀረውን ከእሱ ጋር ውይይቱን ቀጥል። አላህ ሆይ ጥራት ይገባህ ምስጋና ይድረስህ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። መሃርታህንም እጠይቅሃለሁ ወደአንተም እመለሳለሁ። 📚 ምንጭ፡ ሲልሲለቱ አል'ሁዳ ወአል'ኑር -725። ሰለፍይ የሚለውን ቃል ለማረጋገጥ ጥሩ ውይይት https://t.me/selefochin_enketel
نمایش همه...
«ሰለፎችን እንከተል» channel

قال الحافظ ابن حجر رحمه الله :  فالسعيد من تمسك بما كان عليه السلف واجتنب ما أحدثه الخلف" 📗{فتح الباري(13\143) 

👍 5
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.