cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Tofa al-inaya

አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ይህ የማዲህ Tewfik Selahudin የቴሌግራም ቻናል ነው :: https://t.me/tewfikalinaya ለአስተያየት ወይም ለጥያቄ 👉https://t.me/Tofaalinaya መሃባው ጮሌ ነው ሀድራ መገስገሻ ፤ መሃባው ታጅም ነው የስንቱ መንገሻ ፤ መሃባው መደድ ነው የአላህ መለገሻ ፤ 🍀🍀🍀🍀🍀

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
198
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Surah alkahf□Juma mubarek File size 7.00 mb Medina Tube https://t.me/medina_tube
نمایش همه...
ከርበላእ 2 የነቢያቸውን የልጅ ልጆች በተበጣጠሰ ልብስ ከፊታቸው አስቁመው ቃለ መጠየቅ የሚያደርጉት እኚህ አንባገነኖች በመጨረሻም አቅመ አዳም ያልደረሰን እና በህመም የሚማቅቅን የነቢን ሰዐወ ልጅ ከመኃከል ለይተው እንዲታረድ አዘዙ። የነቢ ልጅ ልጅ የሆነው ዘይነል ዓቢዲን እንደሚገድሉት ሲያምን፦‹‹እኚህ እህቶቼ በመንገድ እንዳይባክኑ እባክህ አብሯቸው ወደ መዲና የሚመልሳቸውን ሰው መድብላቸው›› ብሎ ተማፀነ። አስተዳዳሪውም፦‹‹እራስህ አብረኃቸው ሂድ››አለው'ና ከግድያ ተረፈ። በመቀጠልም ይህ አስተዳዳሪ እኚህን አሳዛኝ የነቢን ቤተሰቦች ለጉዞ አዘገጅቷቸው እና ዘይነል ዐቢዲን የተሰኘውን ልጅ ደግሞ እጅ እግሩን ጠፍሮ በማሰር ወደ ጠቅላይ ገዢ ወደ የዚድ ላካቸው። ንጉስ የዚድ የነቢ ልጆች ከቤተመንግስት መድረሳቸውን ሲሰማ ሹማምንት እና ከበርቴዎቹን ቤተመንግስት እንዲገኙ አዘዛቸው። ከዙፋኑ ተቀምጦ በዙርያው ከበርቴዎቹን ካሰለፈ በኋላ የነቢ ሰዐወ ልጆችን ወደ ፊት አስጠርቶ ህዝብ እየተመለከተ ፊቱ አስቆማቸው። ንጉስ የዚድም፦‹‹አባትህ ዝምድናዬን ቆረጠ፣ ክብሬን ረሳ፣ ንግስናዬን ሊመነትፈኝ ሞከረ፣ ይኸው ምታየውን ዱብዳ አላህ አደረሰበት›› ብሎ የነቢ ሰዐወ ልጅ ልጅ ዘይነል ዐቢዲን ላይ አፌዘበት። የነቢ ልጅ ምላሹን ከቁርአን አንቀፆች እንዲህ ሲል መለሰለት፦‹‹በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡›› ነቢያዊው ቤተሰብ እንዲህ ያለ ያማረ ምላሽ ሲሰጥ ንጉስ የዚድም በተሰበሰበው ሰው ፊት ወደራሱ ልጅ በመዞር አቻ ምላሽ እንዲሰጥለት አዘዘው፤ ግና ለነቢ ልጅ አቻ ምላሽ ኬት ይምጣ! ልጁ ዝም አለ። ንጉሱም ለዘይነል ዐቢዲን(የነቢ ሰዐወ ልጅ ልጅ) እንዲህ ሲል ማይገናኝ ቁርአናዊ ምላሽ ሰጠው፦‹‹ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡›› 14 አመት ያልሞላው ዘይነል ዓቢዲን ከዚህ በላይ ሙግት ውስጥ መግባት አልፈለገምና ዝምታን መረጠ። ከዚያም የነቢ ልጅ ልጆች ወደ ህዝቡ ፊት ወጣ ብለው እንዲቆሙ ተጠሩ። ልብሳቸው ተቀዳዷል፣ ፍፁም በአዋራ ቆሽሸዋል፣ የስነልቦና ጉዳቱ አኮራምቷቸዋል፤ አንገታቸውን ደፍተው እፊት ወጥተው ቆሙ። ንጉሱ የዚድ ይህን ሲመለከት፦‹‹ኢብኑ መርጃና(አስተዳዳሪው) የስራውን ይስጠው ከናንተ ጋር ዝምድና ቢኖረው እኮ እንዲህ ባላደረጋችሁ›› ብሎ ዘመድ መስሎ ለመታየት እና ለማዘን ሞከረ። በዚህ መኃል ከቤተመንግስት ውስጥ ካሉት ሰዎች አንዱ ብድግ ብሎ፦‹‹ያችን ልጅ በምርኮ መልክ ስጠኝ›› ብሎ ንጉሱን ጠየቀው። ልጅቱ ፋጢማ ትባላለች የነቢ ልጅ ልጅ ስትሆን መልኳ እጅግ ቀላ ያለ እና እምታጋጓም ነበረች። እድሜዋም ለጋ ስለነበር በግድ ሊወስዱኝ ይችላሉ በማለት በፍርሃት ታለቅ እህቷ ቀሚስ ስር ሂዳ ተወሸቀች። የፋጢማ ታላቅ እህት ዘይነብም እህቷን አቅፋ፦‹‹ዋሸህ፤ ተረገምክም። እኛ ላንተም ለንጉሱም ምርኮ ሁነን እንድትወስዱን ኢስላም አይፈቅድላችሁም›› ስትል ምላሽ ሰጠች። ይሄኔ ንጉሱ የሙዓዊያ ልጅ በንዴት በገነ፦‹‹ወላሂ እኔ ከፈለግኩ በምርኮ ልወስዳችሁ እችላለሁ›› ብሎ ዛተም። ‹‹ወላሂ ይህን ማድረግ አትችልም፤ ከእስልምና ሌላ እምነት እከተላለሁ እስካላልክ ድረስ›› አለችው ዘይነብ። ንጉስ የዚድ ንዴቱ ተፋፋመ፦‹‹ለኔ ነው እንዴ እንዲህ ያለ ምላሽ ምትሰጪኝ! ከእስልምና ሌላ እምነት የተከተሉትማ አባትሽ እና ወንድምሽ ናቸው›› ብሎ ታላቁን ሰሓቢይ ዐሊይን ለማክፈር ሞከረ። ‹‹አንተም፣ አባትህም፣ አያትህም ወደ ኢስላም የተመራችሁት እኮ በአላህ ፈቃድ በአባቴ እና በአያቴ እኮ ነው›› ብላ መለሰችለት። ‹‹ዋሸሽ። አንች የአላህ ጠላት›› ብሎ በነቢ ሰዐወ መመራቱን ሊያስተባብል ሞከረ። እስልምና ካለ ነቢ ሰዐወ ከየት ሊገኝ ይሆን! ‹‹እንዲህ እየተዛለፍክ እና በንግስናህ እየተመፃደቅክ፤ አንተ አሁን የምእመናን መሪ ነህን!›› ስትል ሞገተቸው። ይህን ግዜ ቀድሞ ፋጢማን ስጠኝ ያለው ሰውዬ ወደ ንጉስ የዚድ ዞር አለ'ና፦‹‹ኧረ እንድየውም ይህችን ታላቋን ስጠኝ›› አለው። ንጉሱም፦‹‹ዞርበል ከዚህ ድራሽህ ይጥፋ!›› ብሎ አንጓራበት። ከዝያም ይህ ንጉስ እኚህን የምድር ከዋክብት ወደመጡበት መዲና ሊመልሳቸው ወስኖ ስንቅ እስኪያዘገጃጅ ድረስ እዚህ ቤተመንግስት ሊያስጠልላቸው ከግቢው አስገባቸው። የነቢ ልጆች ወደ ቤተመንግስቱ መኖርያ ሲገቡ በውስጡ ያሉት ሴቶች ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ለቅሶን ተያያዙት። ያ ለቅሶም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ዘለቀ። በዚህ መሀል የነቢ ልጅ ልጅ የሆነው ዑመር ቢን ሁሰይን ከንጉሱ ልጅ ጋር ቤተመንግስት ግቢ ውስጥ እየተጫወቱ ሳለ ንጉሱ ብቅ አለ፦‹‹ይህን ልጅ ታሸንፈዋለህ እንዴ?›› ሲል ዑመርን ጠየቀው። ጨቅላው ዑመርም፦‹‹ለሁለታችንም ቢለዋ ስጠንና ተመልከተን›› አለው። ይህን ግዜ ንጉሱም፦‹‹ይህችንማ ድሮም እናውቃታለን፤ እባብ እባብን እንጂ ሌላን አትወልድም›› ብሎ ተሳደበ። ከሶስት ቀናት በኋላም ንጉሱ ስንቅ አስይዟቸው እና ጠባቂ መድቦላቸው ወደ መዲና ሸኛቸው። በርካታ ሁነው ከነቢ ሰዐወ ከተማ የወጡት የነቢ ልጆች አሁን ቁጥራቸው አንሶ ወደ መዲና ይመለሱ ጀመር። ጉዞዋቸው ላይ የተመደበላቸው ጠባቂያቸውም እጅግ ሲንከባከባቸው እና በስስት ሲያያቸው መዲና አደረሳቸው። ልክ መዲና እንደገቡም ፋጢማ፦‹‹ይህ ሰው እንዲ ሲንከባከብ አምጥቶ እዚህ አድርሶናል። የሆነ ስጦታ ልንሰጠው ይገባል›› አለች ለእህቷ ዘይነብ። ‹‹እንደምታዪው ደኅይተናል፤ ካጠለቅነው ጌጥ ውጭ ምንም የለንም ምን እንስጠው?›› አለቻት። ፋጢማም፦‹‹ጌጦቻችንንም ቢሆን እንስጠው›› አለች። ከዝያም ጌጦቻቸውን አወላልቀው፦‹‹ምንም የሌለን በመሆኑ ይህን ልንሰጥህ ተገደናል፤ ስለመልካምነትህ እናመሰግናለን›› ብለው በሰው ላኩለት። ሰውዬውም፦‹‹ወላሂ የከፈልኩላችሁ መስዋዕትነት በምንም አይተካም፤ ይህንንም ያደረግኩት ለአላህ እና ለነቢ ስል ነው›› ብሎ መለሰላቸው። ከዝያ ግዜ ጀምሮ ያ ቤተሰብ መዲና ላይ መኖር ጀመረ። ይሁን እንጂ በተለያዩ ግዜ የሚነሱ ኢስላማዊ መንግስታት ይህንን ቤተሰብ መቆንጠጥን እንደ ጀግንነት ይመለከቱት ነበር። ይህን የታሪክ ዕውነታ ለመደበቅ እና ለጥፋታኛው ከለላ ለመሆን በርካታ ብዕርተኞችም ታሪኩ እንዳይሰራጭ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም ታሪኩ በህዝበ ሙስሊሙ ልብ የማይሽር ቁስል ሁኖ ሊቆይ ችሏል። ተፈፀመ/ሳይፈፀም Sefwan ማሳሰብያ! ይህን ክስተት በመቶዎች የሚቆጠሩ የታሪክ መዛግብት ዘግበውታል። ከሁሉም መዛግብት ጉዳዩን አለዝቦ የተረከውን የታሪክ ድርሳን የሆነውን ቢዳያ ኒያሃን ብቻ ተጠቅምያለሁ። ከዚህ ድርሳንም ህሊናን ሊያስቱ የሚችሉ የጭካኔ ሁነቶችን ዘልያቸዋለሁ።
نمایش همه...