cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Holistic posperity

ሁለንተናዊ ብልፅግና ለላቀ ህይወት!! በዚህ ቻናል ⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች! ⚡በተለያዩ ዘርፎች ራስ አገዝ የሆኑ መፅሀፍትን ጥቆማ! ⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች! ⚡የታላላቅ ሰዎች ስሜትን ኮርኳሪ ንግግሮች! በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio መልክ ይቀርባሉ። 👉 @Rophiabi ለአስተያዬቶ እናመሰግናለን! https://t.me/+In-LNSEqGbc0ZWE0

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
360
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
አህምሮ የጦርነት አውደ ውጊያ ቦታ ነው! ጭንቀት፣ ጥርጣሬ፣ ግራመጋባት፣ ድብርት፣ ንዴትና የኩነኔ ስሜት ሁሉም አዕምሮ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ናቸው፡፡ በአሉታዊ ሃሳቦች እየተናጥክና እየተሰቃየህ ከሆነ እንደ ዋዛ ሳታየው የምር የሆነ እርምጃ ውሰድበት፡፡ ይህንን አዕምሮ ላይ ያነጣጠረ ወሳኝ ጦርነት በአሸናፊነት ይወጡት። ዕለት ዕለት አዕምሮህ ውስጥ የሚተራመሱትን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሀሳቦችን እንዴት በወጉ ማድረግ እንደምትችልና ሀሳብህን ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ማስማማት “ከምድራዊ” አስተሳሰብህ ተላቀህ፣ ማለትም ከአልባሌ አመለካከትና ሰዎችን ከእግዚአብሔር ከሚያርቅ ሰበብ ከሚሉት ነገር ወጥተህ ብርሃንን በመከተል አስበኸውም፤አልመኸውም የማታውቀውን ደስታንና ስኬትን ትጎናፀፍ ዘንድ ተራው የአንተ ነው፡፡ ለሌላ አሳልፈህ ለአንድ አትሰጥም ተጨማሪ ቀንም እንኳ እራስህን ለመከራ በአዕምሮህ ውስጥ የሚደረገው ጦርነት በአስተማማኝ መልኩ በድል ትወጣው ዘንድ የሚያስችልህን መንገዱ ዛሬ ፈልግ፡፡ ጆይስ ሜየር
نمایش همه...
#የናፖሊዮን_ሂል_ምርጥ_አባባሎች 🔴”የሚያቋርጥ ሰው አያሸንፍም፤ አሸናፊም አያቋርጥም።” 🔴 “እያንዳንዱ ችግር፣ እያንዳንዱ ውድቀት፣ እያንዳንዱ የልብ ስብራት የእኩል ወይም የላቀ የጥቅም ዘርን በውስጡ ተሸክሟል።” 🔴 “ታላላቅ ነገሮችን መስራት ካልቻልክ ትንንሽ ነገሮችን በትልቅ መንገድ አድርግ።” 🔴” አትጠብቅ... መቼም 'ትክክለኛው ጊዜ' አይሆንም... ከቆምክበት ስፍራ ጀምር እና በእጅህ ላይ ባለው ማንኛውም መሳሪያ ስራ፤ የተሻሉ መሳሪያዎች በመንገድህ ላይ ይገኛሉ።” 🔴 “አእምሮህን አንድ የተወሰነ ግብ ላይ አኑር እና ዓለም ልታሳልፍህ ምን ያህል በፍጥነት ዳር ይዛ እንደምትቆም ተመልከት።” 🔴 “የስኬት መንገድ በቀጣይነት እውቀትን የመፈለግ መንገድ ነው።” 🔴 “ከመናገርህ በፊት ሁለት ጊዜ አስብ፤ ምክንያቱም ቃልህ እና ተጽኖህ የስኬት ወይም የውድቀት ዘር በሌላ ሰው አእምሮ ውስጥ ይተክላል።" 🔴 “ከተከፈለው በላይ የሚሰራ ሰው በቅርቡ ከሚሰራው በላይ ይከፈለዋል።” 🔴”ብቸኛ ገደቦቻችን በራሳችን አእምሮ ውስጥ ያዘጋጀናቸው ብቻ ናቸው።” 🔴 “ጥንካሬ እና እድገት የሚመጣው ቀጣይነት ባለው ጥረት እና ትግል ብቻ ነው።" 🔴 “አብዛኛዎቹ ውድቀት የሚባሉት ጊዜያዊ ሽንፈቶች ብቻ ናቸው።” #አስበህ_ሀብታም_ሁን_መጽሐፍ 📗📒📕
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
‘Mindset: Changing The Way You Think To Fulfil Your Potential’ by Carol Dweck- በሳይንስ እና ተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ የተመሰረቱ እና መነበብ አለባቸው ካልናችሁ 12 ምርጥ የራስ አገዝ መፃሕፍት ውስጥ 12ኛው! በዓለም ታዋቂው በሆነው የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ካሮል ዲዌክ (ፒኤችዲ) ከብዙ አሥርት ዓመታት ጥናት በኋላ፣ ቀላል ግን መሠረታዊ የሆነ አዲስ ሐሳብ አግኝተዋል። ይህም የአስተሳሰብ ኃይል (the power of mindset) ነው። በዚህ ድንቅ መጽሃፏ ውስጥ ፀሐፊዋ በትምህርት፣ በስራ፣ በስፖርት፣ በኪነጥበብ እና በሁሉም የሰው ልጅ ጥረቶች ውስጥ የሚኖረን ስኬት ላይ ስለ ተሰጥዖአችን እና ችሎታችን ያለን አተያይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አሳይተውናል። የማያድግ አስተሳሰብ (fixed mindset) ያላቸው ሰዎች - ችሎታዎች የማያድጉ ወይም የማይለወጡ ናቸው ብለው የሚያምኑ - የሚያድግ አስተሳሰብ (growth mindset) ካላቸው ሰዎች- ችሎታዎች ሊዳብሩ ይችላሉ ብለው ከሚያምኑት ጋር ሲነፃፀር የማደግ ወይም የመለወጥ ዕድላቸው ያነሰ ነው ትለናለች። ይህ መጽሐፍ ወላጆች፣ መምህራን፣ መሪዎች እና አትሌቶች የላቀ ስኬትን ለማምጣት ይህንን ሃሳብ እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይተነትናል። መጽሐፉን ቢያነቡት ይጠቅማቸዋል ብላችሁ ለምታስቧቸው ወዳጅ፣ ጓደኞቻችሁ ማጋራትን አትርሱ። @Holistic_Prosperity☘ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለላቀ ህይወት!!
نمایش همه...
Mindset Changing The Way You Think To Fulfil Your Potential .pdf2.41 MB
The_ONE_Thing_The_Surprisingly_Simple_Truth_Behind_Extraordinary.pdf3.60 MB
Photo unavailableShow in Telegram
‘The ONE Thing’ by Gary Keller and Jay Papasan የዚህ መጽሐፍ ዋና ሀሳብ የሚያጠነጥነው በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ያልተለመደ ውጤት ለማምጣት የሚያስችለንን አንድ ነገር ስለማግኘትና በዚህ ላይ ሙሉ ትኩረት ስለማድረግ ነው። ለምሳሌ:- ማንኛውንም የሕይወታችሁን ክፍል (የግል፣ የቤተሰብ ወይም የስራ ህይወታችሁን) ውሰዱና በዚህ ላይ ልትወስዱ የምትችሉትን አንድ የለውጥ እርምጃ ፈልጉ፣ ይህም ከዚህ ውጭ የሆነ ማንኛውንም ነገር አላስፈላጊ ያደርገዋል። ፀሐፊው በመፅሃፉ ላይ እንዳብራሩት:- በማንኛውም ነገር ስኬታማ ለመሆን የተሻለውን እድል ስትፈልጉ፣ አካሄዳችሁ ሁልጊዜ አንድ የተወሰነ ነገር ላይ ማተኮር መሆን አለበት፡- ይህም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉንም ነገሮች ችላ ማለት (ignoring all the things you could) እና ማድረግ ያለባችሁን ማድረግ (doing what you should do) ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፤ ሁሉም ነገሮች እኩል አስፈላጊ እንደማይሆኑ በመገንዘብ፣በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማግኘት ማለት ነው። ያልተለመዱ ውጤቶችን ማምጣት የምንችለው ትኩረታችንን ጠባብ ማድረግ ስንችል እንደሆነ መፅሐፉ ያስረዳናል። መልካም ንባብ! @Holistic_Prosperity☘ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለላቀ ህይወት!!
نمایش همه...
በአሮጌ ማንነትህ አዲስ ዉጤት አጠብቅ!
نمایش همه...
በአሮጌ_ማንነትህ_አዲስ_ዉጤት_አጠብቅ!.m4a3.54 MB
#ዋናዉ_ዉስጥ_ነዉ! የበረከት ሁሉ ምንጭ ያለዉ ከዉጪያችሁ አይደለም። የማንነታችሁ አካል ነዉ። ግን ይህን በልባችሁ ያዙና በረከትን ከዉጪያችሁ ማስተዋል ጀምሩ።በዙሪያችን ያለዉን የህይወት ምልዓት ተመልከቱ። ጀንበር ብርሃኗን ሳትሰስት ታሞቃችኋለች፣ አበቦች ብሩህ ዉበታቸዉን ይመግቧችኋል፣ዝናብ ሲዘንብ ተመልከቱ ተፈጥሮ የህይወትን ሁሉ ምንጭ የሆነዉን ዉሀን ያበረክታል።የህይወት ምልዓት በየደረጃዉ ይገኛል። በዙሪያችሁ ያለዉን በረከት ማስተዋል በዉስጣችሁ ያለዉን ይቀሰቅሰዋል።ከዚያ ወደ ዉጪ እንዲፈነጥቅ ፍቀዱለት። ለማታዉቁት አንድ ሰዉ ፈገግ ስትሉ ለቅፅበት ያህል ሃይላችሁን ለግሳችሁታል። አበርካች/ሰጪ ሆናችኋል። ይህን ጊዜ ራሳችሁን ጠይቁ :- ''አሁንስ ምን ልሰጥ እችላለሁ ፣ይህንን ሰዉ እንዴት ላገለግለዉ እችላለሁ?'' በረከት እንዲሰማዎት የምንም ነገር በለቤት መሆን አያስፈልጋችሁም። ግን ይህን ስሜት ያለማቋረጥ የሚሰማችሁ ከሆነ ነገሮች ያለጥርጥር ወደ እናንተ ይመጣለ። በረከት የሚመጣዉ በረከት ላላቸዉ ብቻ ነዉ።ይህ ለሁላችን የሚሰራ ህግ ነዉ። በረከት እና ማጣት ሁለቱም በዉስጣችሁ ተፈትነዉ በእዉኑ ዓለም የሚንፀባረቁ ጥለቶች ናቸዉ። #ራስን_መለወጥ ከተሰኘዉ #ከ_ኤካርት_ቶሌ መፅሀፍ ከገፅ 142-143 የተወሰደ። @Holistic_Prosperity☘ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለላቀ ህይወት!!
نمایش همه...
ሰዎች ከመድሀኒት በፊት መድሀኒተኛ ነው የሚፈልጉት:: የጤና ባለሞያው ጤና እና ስብዕና... ከቀውስ ወደ ፈውስ......ክፍል 3 ዶ/ር ምህረት ደበበ የአዕምሮ ህክምንና ስፔሻሊስት ከቆዩ ቪዲዮዎች የተቀነጨበ... መልካም ቀን...🔅🌼 Join us here 👇 @Holistic_Prosperity☘ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለላቀ ህይወት!!
نمایش همه...
Dr meheret_3.mp36.10 MB
ከላይ ያሉት ምርጥ መፃፎች ናቸው!! ብታነቧቸው ብዙ ትር ታገኛላችሁ!
نمایش همه...