cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ተግባራዊ ክርስትና

|| #በስመ #አብ #ወወልድ #ወመንፈስ #ቅዱስ #አሐዱ #አምላክ #አሜን || "እንዲሁ ዝም ብለን ራሳችንን ክርስቲያን ብለን እንድንጠራ አልተጠየቅንም ፤ የተጠየቅነው በምግባራችን ክርስቲያኖች እንድንሆን ነው።" [ ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾክያ ] Tik Tok http://tiktok.com/@applied_ortodox YouTube https://www.youtube.com/@maytube_ortodox

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 764
مشترکین
+724 ساعت
+227 روز
+16530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#ሞትን_ስታስብ_ምን_ይሰማሀል? ልክ ስትሞት በዚህ ምድር አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ የአንተ ወዳለመሆን ይሸጋገራል። የለፋህበት የተጣላህበት ነገር ሁሉ ከንቱ ይቀራል። በዚህ ምድር ያሉት ሀብት ሥልጣን ክብር ጉልበት ዕውቀት እና የመሳሰሉት በዚህ ምድር እስካለህ ድረስ ብቻ የሚያገለግሉህ ናቸው። ስትሞት እነዚህ ሁሉ ምንም ናቸው። በእርግጥ እኒዚህን ነገሮች ከሞት በኋላ ለሚመጣው ሕይወት ካዋልካቸው ለነፍስህ ጥቅምን ይሰጣሉ። ብዙ ቅዱሳን የዚችን ዓለም አጭርነት ተረድተው ንቀዋት በምናኔ በየጫካው በየኮረብታው በጾም በጸሎት ተወስነው ያሳልፏታል። ሞት አንዱ የሕይወታችን አካል ነው። ቀድሞ የነበሩ ሰዎች አሁን በሥጋ የሉም። ዓለምን አንቀጥቅጠው የገዙ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ሰዎች አሁን የሉም ሞተዋል። መጀመሪያውንም ካለመኖር ያመጣን እግዚአብሔር በሥጋ ወደ አለመኖር ይወስደናል። ሞት ሲታሰብ ይጨንቃል ምክንያቱም ሞተን ስላላየነው አናውቀውም። ሞት በዚህች ምድር ሳሉ ሥልጣናቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን ሀብታቸውን በአግባቡ ለመልካምነት ለተጠቀሙት ሰዎች ዕረፍት ነው በተቃራኒው ሌላውን ለመጉዳት ለተጠቀሙት ሰዎች ደግሞ ሁለት ሞት ነው። ስለዚህ ሞትን ላለመፍራት ከፈለግህ በዚህች ምድር እስካለህ ድረስ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቅ። አንድ ሊቅ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል ብሏል። 1ኛ #ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ 2ኛ ለፍርድ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም 3ኛ ሲፈረድባት ሁላችንም ካለመኖር እንድንኖር ያደረገን እግዚአብሔር ፊት እንቆማለን። ስለዚህ የእርሱን ረድኤት ጋሻ አድርገን በእርሱ ፊት ለመቆም የሚያበቃንን ስራ እንስራ። ሁላችንንም እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
3🙏 3👍 1
#ሞትን_ስታስብ_ምን_ይሰማሀል? ልክ ስትሞት በዚህ ምድር አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ የአንተ ወዳለመሆን ይሸጋገራል።የለፋህበት የተጣላህበት ነገር ሁሉ ከንቱ ይቀራል። በዚህ ምድር ያሉት ሀብት ሥልጣን ክብር ጉልበት ዕውቀት እና የመሳሰሉት በዚህ ምድር እስካለህ ድረስ ብቻ የሚያገለግሉህ ናቸው። ስትሞት እነዚህ ሁሉ ምንም ናቸው። በእርግጥ እኒህን ነገሮች ከሞት በኋላ ለሚመጣው ሕይወት ካዋልካቸው ለነፍስህ ጥቅምን ይሰጣሉ። ብዙ ቅዱሳን የዚችን ዓለም አጭርነት ተረድተው ንቀዋት በምናኔ በየጫካው በየፍርክታው በጾም በጸሎት ተወስነው ያሳልፏታል። ሞት አንዱ የሕይወታችን አካል ነው። ቀድሞ የነበሩ ሰዎች አሁን በሥጋ የሉም። ዓለምን አንቀጥቅጠው የገዙ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ሰዎች አሁን የሉም ሞተዋል። መጀመሪያውንም ካለመኖር ያመጣን እግዚአብሔር በሥጋ ወደ አለመኖር ይወስደናል። ሞት ሲታሰብ ይጨንቃል ምክንያቱም ሞተን ስላላየነው አናውቀውም። ሞት በዚህች ምድር ሳሉ ሥልጣናቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን ሀብታቸውን በአግባቡ ለመልካምነት ለተጠቀሙት ሰዎች ዕረፍት ነው። በተቃራኒው ሀብታቸውን ሥልጣናቸውን እውቀታቸውን ሌላውን ለመጉዳት ለተጠቀሙት ሰዎች ሁለት ሞት ነው። ስለዚህ ሞትን ላለመፍራት ከፈለግህ በዚህች ምድር እስካለህ ድረስ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቅ። አንድ ሊቅ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል ብሏል። 1ኛ #ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ 2ኛ ለፍርድ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም 3ኛ ሲፈረድባት ሁላችንም ካለመኖር እንድንኖር ያደረገን እግዚአብሔር ፊት እንቆማለን። ስለዚህ የእርሱን ረድኤት ጋሻ አድርገን በእርሱ ፊት ለመቆም የሚያበቃንን ስራ እንስራ። ሁላችንንም እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
01:29
Video unavailableShow in Telegram
"ትዕቢት ምንድነው ?" #በየግሩፑ_ያጋሩ ! ¶ Tik Tok [ http://tiktok.com/@applied_ortodox ] JOIN [ @menfesawi_tik_tok ] ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧     ❍ㅤ             ⎙ㅤ              ⌲         ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ          ˢᵃᵛᵉ              ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
oAS7bBCc1vUExZEZjTNmyBQGiiQgzUQAEILDC.mp42.30 MB
🙏 5👍 3
ሦስተኛ የሞት ደረጃ ደግሞ እስከመቃብ የሚደርሱት የሞት ዓይነት ነው። ይህ ደግም በአልአዛር ሕይወት የኾነው ነው ዮሐ 11፡1። አልአዛር ሞቶ ተቀብሮ አራት ቀናት ከኾኑት በኋላ ነው ጌታችን ከሞት እንዲነሣ ያደረገው። ይህ ደግሞ ኃጢአትን በአደባባይ ከመፈጸም አልፈው ልምድ እስክትኾንባቸው ድረስ ልባቸውን የከፈቱላት ሰዎችን የምታመለክት ናት! በኃጢአት ሥራ ተጸምደን ቀንና ሌሊት ኃጢአትን እንደመብል የሚበሉና የሚሠሩት ሥራ ትክክል አይደለም ሲባሉ አልቀበልም የሚሉ ሰንት ወዳጆች አሉን?! በእርግጥ እኛው ራሳችን በኃጢአታችን ሞተን ተቀቅረናል። ኃጢአታችን ጽድቅ ኾኖ እንዲቆጠርልን እንጂ ትክክል እንዳልኾነ እስኪሰወረን ድረስ የለመድን አረ ብዙ ሰዎች አለን!! በዘፈን ሱስ ነፍሳችንን አስክረን ዘፈንን የምናጠይምና በአንዳንድ ጥቅሶች ለማስፈቀድ የምንጥር የለምን?! በመጠጥ ብዛት ሰክረን የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦይ ውስጥ እስከመግባት ደርሰን፥ ነገር ግን ይህ ድርጊታችን ልክ አለመኾኑን ሲነገረን "ወይን ያስተፌስሕ ልበ ሰብእ" እያል ለኃጢአታች ጋሻ ያበጃጀን ሰዎች የለንም? እንግዲያው ንጉሥ ክርስቶስን አስነሣን እንበለው በኃጢአት ሞተን ተቀብረናልና። ይህ የኃጢአት ደረጃ የመጨረሻው የኃጢአት ደረጃ መኾኑን ለራሳችን እንንገርና አስነሺውን እንፈልገው። በአመንዝራነት ግብር እንደ ሱስ ተይዘው የተመለሱ ብዙ ሰዎች መኖራቸውን አንርሳ! ጌታችንም አልአዛርን ያስነሣው በምንም ዓይነት ኃጢአት ውስጥ ብንኾን የሚያድነን መኾኑን በምሥጢር ሊያስገነዝበን ነውና። አምላካችን እግዚአብሔር ከእነዚህ የኃጢአት ሞቶች ያስነሣን አሜን። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
5👍 1
ሁለተኛው ሞት የመበለቲቱ ልጅ ሞት ነው። ይኽኛው ሞት ለመቀበር እስኪሄዱ የሚያደርሰው ሞት ነው ሉቃ 7፥11። የመበለቲቱን ልጅ ከምተ በኋላ ገንዘው ይዘውት ሲሄዱ በመንገድ ላይ ከጌታችን ጋር ተገናኙ ጌታችንም በፍቅሩ ከሞት እንዲነሳ አደረገው። ይህ ደግሞ አደባባይ የወጣ ኃጢአት ነው። በልብ ብቻ ሳይኾን በግብርም ጭምር የምንፈጽመውን ኃጢአት የሚያሳይ ነው። በልብ የታሰበውን ኃጢአት ጸንሰን በተግባር ወልደን በሰው ሁሉ ፊት የታወቀልን ኃጢአተኞች ስንቶች ነን?! በግልጽ የምንሳደብ፣ በግልጽ የምንታበይ፣ በግልጽ የምንዘፍን፣ በግልጽ ሰዎችን የምናሰነካክል አልበዛንምን?! ሰው ሁሉ ጉዳችንን ያወቀልን፣ በክፉ ግብራችን በሚዲያ የምንታወቅ፣ ወዲያው በግልጽ ዘረኝነታችንን የምንገልጽ፣ መከፋፈልን የምንዘራ ስንቶች ነን?! ይህ ሁለተኛው ደረጃ በኃጢአት ወጣት የመኾን ደረጃ ነው። ጌታም የመበለቲቱን አንድያ ልጅ ከሞት አስነሳላት፤ ለአንዲቷ እናት ለቅድስት ቤተክርስቲያን አንድያ ልጇ ሰጣት። ይቀጥላል... #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
7
Photo unavailableShow in Telegram
#ሥሉስ_ቅዱስ በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት) በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው። በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና። ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት #ቅድስት_ሥላሴ እንላቸዋለን የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል በቤቱም መጥተው ያድራሉ። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
14👍 1🙏 1
#ሦስቱ_ሞቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን ሦስት ጊዜ ያደረጋቸውን ከሞት የማስነሣት ተአምራት ሊቃውንት ይመሰጡባቸዋል። በእርግጥ እነዚህን ከሞት መነሣቶች ቅዱስ ቄርሎስ የጌታችን ትንሣኤ ሕያው ማሳያቸው አድርጎ ያነሣቸዋል። በእርግጥም የጌታችን ትንሣኤ ታላቅ ነገር በመኾኑ ምክንያት በማንም ሰው ልቦና ውስጥ የጥርጣሬ መንፈስ እንዲኖር የማይፈቅደው አምላክ አስቀድሞ ሁሉንም ነገር እኛ በሚገባን መንገድ ለትንሣኤው ማመላከቻ አድርጎ አቅርቦልናል። ከሞት መነሣት የለም የሚለውን የተጠራጣሪዎች አሳብ በብዙ ኅብረ አምሳል ዐሳየ!! ሊቁ አውግስጢኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጹት ሦስት ሞቶች በኩል የእኛን ሕይወት ለእኛ ይነግረናል። አንደኛው ሞት የምኩራቡ ሽም ልጅ ሞት ነው ማር 5፡35። የሞተችው ልጅ ወደ መቃብር ከመሄዷ በፊት ሞታ እቤቷ ሳለች ነው ጌታችን ከሞት ሊያስነሣት የመጣው። ሊቁ አውግስጢኖስ ይህን ሞት በልብ ውስጥ በምንፈጽመው ኃጢአት የሚገጥመንን ሞት ይገልጽበታል። ይህቺ የሞተችው ሴት ልጅ በእኛ ውስጥ ያለው ሙት ሥራና ፈቃድ የሚያመለክት ነው። ይኽውም ድርጊታችን በግልጽ ያልወጣብን ነገር ግን በልባችን ውስጥ በስውር በብዙ የኃጢአት ሥራ የምትን ሰዎችን የሚያመለክት ነው። በአሳባች፣ በፈቃዳችን በብዙ የፍትወት ስሜት ፈቃዳት አልሞትንም? በእርግጥ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ብዙ ዓይነት የአሳብ ፈተና እንደሚያመጣብን የታወቀ ቢኽንም፥ ለሚመጣብን የውስጥ ፈተና ፈቃድ ሰጥተን ውስጣችንን በኃጢአት ስሜቶቻች ስለምን እናረካዋልን? ይህ ነው ውስጣዊ ሞት። በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ኾነው ቃሉን እየሰሙ ነገር ግን በምግባራቸው ያልሞቱ ከእኛ ውስጥ ይኖር ይኾን? እንግዲህ  ቸሩ አምላካችን ከሕሊና ሞት ያድነን፤ ይህ አንደኛው ሞት ነው። ይህ በኃጢአት የሕፃንነት ደረጃ ላይ መኾን ነው። ይቀጥላል... #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
👍 7🙏 1
01:38
Video unavailableShow in Telegram
"አንቺን ካላገኝው ታንቄ እሞታለው !" #በየግሩፑ_ያጋሩ ! ¶ Tik Tok [ http://tiktok.com/@applied_ortodox ] JOIN [ @menfesawi_tik_tok ] ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧     ❍ㅤ             ⎙ㅤ              ⌲         ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ          ˢᵃᵛᵉ              ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
oIiY0NAAAHreiKJefOBMevHAgYAsb0fAcA4tM5.mp47.78 MB
8👍 3
በክርስትና ሕይወት ውስጥ ይቅርታ የአፍ ብቻ ሳይሆን ከልብ የሚመነጭ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ካስተማረው አንዱ ስለ ይቅርታ ነው፡፡ ‹‹ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም፡፡›› እንዲል (ማቴ. ፮፥፲፫) አንድ ሰው ስለ ይቅርታ ስላወቀ ብቻ ይቅር ሊል አይችልም፤ የይቅርታ ልብም ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ይቅር የሚል ልብ ሰው ሲጣላ የሚጀምር አይደለም፤ ወይም ሁለት ሰዎች ተጣልተው ቢሆን ብዙ ሽማግሌዎች ለማስታረቅ ሂደው ያን ጊዜ እንዲታረቁ ያስሟሟቸዋል፡፡ እነዚህን ሰዎች ማስታረቅ ቀላል የሚሆነው ሰዎቹ የይቅርታ ልብ ካላቸው መጀመሪያውኑ ይቅርታ ለማድረግ የተዘጋጀ ልብ ሲኖራቸው ነው፡፡ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ጠላ ሁልጊዜ አይጠመቅም፡፡ ባለሙያ ሴት ሁሉን ነገር አዘጋጅታ ድፍድፉን ታስቀምጠዋለች፤ እንግዳ በመጣባት ጊዜ እርሱን ለወስ ለወስ አድርጋ ወዲያውኑ ታቀርበዋለች፤ ሊጥም እንደዚሁ ነው፡፡ የሊጥ ማብኪያው ባዶውን አይሆንም፡፡ እንግዳ እንጀራ ሳይኖር ቢመጣ ወዲያውኑ ምጣዱን አስምታ ወዲያውኑ ትጋግራለች፡፡ ይህች ሴትዮ ዝግጁ ናት ማለት ነው፡፡ እንግዳ ለመቀበል፣ ለማብላት፣ ለማጠጣት ዝግጁ ናት፡፡ ለይቅርታም እንዲህ ዓይነት ዝግጁነት ያስፈልጋል፡፡ ሰው መጀመሪያውኑ ይቅር ለማለት የሚችል ልብ ካለው ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡ ሰው ይቅር ማለት ያለበት ሲጠየቅ ብቻ አይደለም፤ ሳይጠየቅም ይቅርታ ማለት አለበት፡፡ ይህ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ሰው የይቅርታ ልብ ካለው ሰው ሲበድለው ይቅር ብየሃለሁ ሊል ይገባል፡፡ ተበድለውም የሚረሱ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እነዚህ ሰዎች የይቅርታ ልብ ስላላቸው ነው፡፡ የይቅርታ ልብ የሌለውን ሰው አስተምሮ ታረቅ ማለት በጣም ከባድ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዱ ሰዎች ‹‹እናንተ ቤቴ ድረስ ስለመጣችሁልኝ እሺ ልበላችሁ እንጂ እኔ ግን በልቤ ቂሜን አልተውም›› ይላሉ፡፡ በአንደበት ብቻ ይቅርታን ማድረጉን የሚገልጽ ሰው የይቅርታ ልብ የለውም፡፡ በጸሎት፣ በጾም እና በትጋት ይቅርታን ማድረግ ልንለምድ ይገባል፡፡ ይቅር ማለት እየፈለገ ያልቻለ ሰው ‹‹ቂሜን መተው እፈልጋለሁ፤ ግን አላስችል አለኝ፤ የደረሰብኝ በደል ትዝ ይለኛል፤ ሳስበው ያንገሸግሸኛል፤ ግደለው ግደለው የሚል ሐሳብ ይመጣብኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ለመርሳት ሞከርኩ ግን አልቻልኩም›› ይላል፡፡ ይህ ነገር ከባድ ቢሆንም ማስወገድ የሚቻለው በጾም እና በጸሎት በመሆኑ ከልብ ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
👍 8
#የይቅርታ_ልብ የሰው ልጅ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ይመለስ ዘንድ የይቅርታ ልብ ሊኖረው ይገባል፡፡ አዳም ይቅርታ ባይጠይቅ እና ከእግዚአብሔር ይቅርታን ባያገኝ ኖሮ የዘለዓለም ቅጣት ይፈረድበት ነበር፡፡ ሆኖም ከሚኖርባት ገነት ወደ መሬት በመምጣት ቅጣት ተቀብሏል፡፡ አዳም ዕንባ ሲያልቅበት ደም፣ ደም ሲያልቅበት እዥ እያነባ ‹‹በድያለሁ ይቅር በለኝ›› ብሎ ፈጣሪን ይቅርታ በመጠየቁ ድኅነትን አግኝቷል፡፡ ይቅርታ ሰውን እንደገና ወደጥንት ክብሩ የመለሰ ትልቅ ጸጋ ነው፡፡ ያለ ይቅርታ ዓለም ለኃጢአት ስርየትም ሆነ ቸርነት የበቃ አይሆንም፡፡ ሰዎች ለሌሎች የምናደርገው ይቅርታ እና እግዚአብሔር ለዓለም ያደረገው ይቅርታ ይለያያል፡፡ እግዚአብሔር ለዓለም ያደረገው ይቅርታ በቃል ኪዳን የታሠረ ነው፡፡ በማንኛውም ጊዜ ‹‹ይቅር በለን›› ብለው የሚለምኑትን ሁሉ እግዚአብሔር ይቅር ይላል፡፡ ይቅርታ የጠየቁትን ሰዎች ሁሉ ይቅር ይል ዘንድ እግዚአብሔር ሁልጊዜም መሓሪ ስለሆነ በቃሉ ይቅርታን ያደርጋል፡፡ የሰው ልጅ በየዕለቱ ሊያጠፋና ኃጢአት ሊሠራ ይችላል፡፡ ‹‹ሰማያት በፊቱ ንጹሓን አይደሉም›› ተብሏልም፡፡ በሰማያት ይኖሩ የነበሩት መላእክት (ሠራዊተ ዲያብሎስ) እንኳን ስተዋልና ነው፡፡ የሰው ልጅም ሌት ከቀን ኃጢአት ይሠራል፡፡ ነገር ግን ሰው በዚህ ሁሉ ጥፋት እያለ  በዚህች ምድር የኖረው እግዚአብሔር ይቅር የሚል አምላክ በመሆኑ ነው፡፡ (ኢዩ.፲፭፥፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የኃጢአት ደሞዙ ሞት ነው›› እንዳለ ሰው ኃጢአት በሠራ ቁጥር ሞት ይገባዋል እንደማለት ነው፡፡ ለምን እኛ ኃጢአት በሠራን ቁጥር አንሞትም ቢባል እግዚአብሔር የይቅርታ አምላክ ስለሆነ ነው፡፡ ስንለምነውና ስንጠይቀው ይቅር ስለሚልን ነው፡፡ አንድ ሰው ሲያስቀይመን፣ ሲበድለን ወይም በእኛ ላይ ክፉ ሲያደርግ ችላ ብሎ ማለፍ በራሱ ከይቅርታ የሚቆጠር ነው፡፡ ለምናጠፋው ለእያንዳንዱ ጥፋት ዋጋው ሞት ነው፤ ለበደላችን ቅጣት አለብንና በጸጸት እንዲሁም ንስሓ በመግባት ይቅርታ ማግኘት ይገባል፡፡ (ሮሜ.፮፥፲፫) በሰዎች ዘንድም የይቅርታ ልብ በመኖሩ በምንጋጭበት ጊዜ ከተጣለነው ሰው ጋር በይቅርታ መስማማት አለብን፡፡ ሰው አብሮ ከኖረ በመካከላችን ግጭት፣ ክርክርና ንግግር መኖሩ ምንም የማይቀር ነገር ነው፡፡ ታላቁ አባት ኢትዮጵያዊው አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ገብተው በነበረ ጊዜ ብቻቸውን በተባሕትዎ እያሉ ደቀ መዝሙሮቻቸው ‹‹ውሾች ወደዚህ ሰፈር መጡ›› ብለው በነገሯቸው ጊዜ ‹‹አይ ውሻማ ከመጣ ሰው መጣ፣ ሰው ከመጣ ነገር መጣ ማለት ነው›› ብለው ጥለው ሄዱ ይባላል፡፡ በሚዋደዱና በሚፋቀሩ ሰዎች መካከል እንኳን አለመስማማት ይኖራል፡፡ የአባትና የልጅ፣ የወንድምነትና እኅትነት እንዲሁም የትዳር፣ ግንኙነት እንዲዘልቅ ይቅርታ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ (ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል) ሀገራችን ሰፊ በመሆኗ ብዙ ሕዝብ ይኖርባታል፤ በዚህ መሐል ሕዝብን የሚበድሉ ባለሥልጣናትም ይኖራሉ፡፡ የእነዚያን ሰዎች መሻሻልና መስተካከል አይቶ ሕዝብ ይቅር ማለት አለበት፡፡ ቂምና በቀል የሚቋጥር ከሆነ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር ጥላቻ ይኖራል፤ ይህ እንዳይሆን ሕዝባዊ ይቅርታ ያስፈልጋል፡፡ ይቀጥላል.... #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ
JOIN @Applied_CHRISTIANITY
نمایش همه...
6🙏 2👍 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.