cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

The Jubair || The ጁበይር

ሀሳብ አስተያየታቹን በ @thejubair ያድርሱኝ ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው በቻናላችን አጫጫር ዳዕዋዎችን | ፈጣን መረጃዎችን | አጫጭር የቁረዐን አያቶችን| እንዲሁም ሌሎች እጅግ አስተማሪ ነገሮችን በአላህ ፍቃድ ያገኛሉ . ይህን ሁሉ ቻናላችንን Join በማድረግ ብቻ ሀያ ቢስሚላህ 😊 ሹክረን ;)

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 633
مشترکین
+124 ساعت
-117 روز
-3230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✍“እይታህን እይታ አታስከትላት የአንተ የመጀመሪያዋ ብቻ ናት” በዚህም የተፈለገው መጀመሪያ በድንገት የተመለከትከው ወንጀል የለውም፤ያንን ተከትለህ (በዚያው ቀጥለህ) አትመልከት ማለት ነው። ሙስነድ ውስጥ በተጠቀሰው ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ { النظر سهم مسموم من سهام إبليس } “እይታ(መመልከት) ከሸይጧን ጦሮች መካከል በመርዝ የተሞላችዋ ናት።” ✍ምልከታ የአብዛኛዎቹ ሰውን የሚጎዱ ነገሮች መነሻ ነው። ምልከታ ትውስታን ትፈጥራለች፤ ትውስታ ማሰብን ትፈጥራለች፤ ማሰብ ስሜትን ትፈጥራለች፤ ስሜት ፍላጎትን ትፈጥራለች፤ከዚያም ይህ ተጠናክሮ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ይደረሳል። በመጨረሻም ስራው ይፈፀማል።  አላህ ይጠብቀን! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا እነዚያም «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለቅ ነውና» የሚሉት ናቸው፡፡ [ሱረቱል ፉርቃን : 63-65] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_299 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
ዚክርና ጥቅሞቹ 🕯አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት 🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው 🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው 🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል 🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል 🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል 🔹ዚክር የከበደውና ከዚክር የሠነፈ ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል 🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል 🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል 🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል 🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል 🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል 🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም ያድናል 🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡ 🔹የህሊናን እረፍት ይሠጣል 🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል 🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣ ቀብር ውስጥም አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡ 🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡✨ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣ ረሡልም ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣ 🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا (ሡረቱል አህዛብ፡41-42) [ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል 🚩በሌላውም የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልፅ እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋል የሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል ፣ 🚩በሌላኛው የቁርኣን አያም "አሥታውሡኝ አሥታውሣችኋ ለሁ "ብሏል፡፡ ሐጅ ሥርአት ላይ ዒባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህ ሡብሀነ ወተአላ አሥታውሡ ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላል " "አላህን ሡብሀነ ወተዓላ በብዛት አሥታውሡት ፣እነሆ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ" ይላል 🔸በተለያዩ የቁርኣን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጿል። 📎ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋል("አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ዒባዳ አልደነገገም ዒባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ!" ) ▶ይህን ዒባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሰዎችን ኡዝር ባላቸው ሠአት ይህን ዒባዳ ቢተውት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ ዚክር ሢቀር 👌 📌ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያህል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም ፣እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ለማንም አልፈቀደም ለመተዉም ኡዝር አልሰጠም። አእምሮውን የሣተ፣ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሰው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡ እንዲሁም ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በጊዜ የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል ፣በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆነ በስተቀር! እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡ ቆማችሁም፣ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡ቀንም ሌሊትም ባህርም ውስጥ የብሥም ላይ አላህን አሥታውሡ፣ ሀገርም ላይ ይሁን መንገድ ላይ ፣በድንጋጤና በሀዘንም ሆነ በደሥታ ጊዜ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜ አላህን አሥታውሡ! በገሀድም በሚሥጥርም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታውሡት! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
👍 1
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَفَأَنتَ تَهْدِي الْعُمْيَ وَلَوْ كَانُوا لَا يُبْصِرُونَ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡ [ሱረቱል ዩኑስ : 43-44] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_298 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
🔘(የልቦና ባለቤቶች ሆይ አስተውሉ) "የሞቱ" ሰዎች ቀብራቸው ውስጥ ታግደው ባሳለፉት ነገር ይፀፀታሉ "በህይወት" ያሉት ደግሞ ቀብር ውስጥ ያሉት በሚፀፀቱበት ነገር ላይ ይገዳደላሉ ወይ እነዚያ -የሞቱት- በህይወት ወዳሉት ሰዎች አይመለሱም በህይወት ያሉትም ቀብር ውስጥ ሆነው በሚፀፀቱ ሰዎች አይመከሩም 📂(ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ) አላህ ይሁነን እንግዲ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
🏷በወንጀል ምክንያት የሚመጣን ቅጣት ሊያስቀሩ የሚችሉ 10 ነገሮች ✨የአላህን ምህረት ማግኘት ትልቅ ዕድል ነው፣ወንጀላችንን ያለሱ ማንም ሊምረንና ይቅር ሊለን አይችልምና! ▪ሙእሚን ወንጀሉ ያሳስበዋል ▪ሙናፊቅ ግን ከምንም አይቆጥረውም 🔸ቁርኣንና ሐዲሥ የወንጀል መዘዙ ሰዎች/ሰሪዎቹ ላይ እንዳይደርስ የሚያደርጉ 10- ነገሮች እንዳሉ አመላክተዋል እነሱም፥ ① ተውበት (ተጸጽቶ ወደ አላህ መመለስ) ②ኢስቲጝፋር ማድረግ ③ መልካም ስራዎችን ማብዛት ④ ስንሞት ሙእሚኖች የሚያደርጉልን ዱዓና ኢስቲጝፋር ለምሳሌ ሰላተል-ጀናዛ ላይ ⑤ ለሞተ ሰው የሚደረጉ መልካም ነገሮች ለምሳሌ ሰደቃ... ⑥ የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ምልጃ ⑦ ሙእሚንን ዱኒያ ላይ የሚገጥሙ የተለያዩ ችግርና መከራዎች ⑧ የቀብር ጭንቀትና ፈተና/ድንጋጤ ⑨ የቂያማ ቀን መከራና ስቃይ ①∅ ከወንጀለኛው ወይም ከሰው ልጆች በኩል ምንም ሳይደረግ በአላህ እዝነትና ይቅር ባይነት በወንጀላችን ምክንያት ኣኺራ ላይ ይጠብቀን የነበረ ቅጣት ሊቀር ይችላል:: (ከሸይኹል-ኢስላም ንግግር የተወሰደ) ▪ወንጀልን መጀመሪያውኑ ከበሽታ በላይ እንጠንቀቅ ከተፈተንን ግን ተስፋ አንቁረጥ የአላህ ረሕመቱ ሰፊ ነው! ከላይ ከተጠቀሱ ነገሮች በአንዱ ምክንያት ምህረትን እንደምናገኝ ተስፋ እናድርግ ዛሬ ነገ ሳንልና ሞት ሳይቀድመን ተጸጽተን እንመለስ! 🔸መስፈርቱን ያሟላ ተውበት የማይሰርዘው ወንጀል የለም! አብሺሩ ያ ዒባደላህ (لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ الله) ✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
1
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَرَبُّكَ الْغَفُورُ ذُو الرَّحْمَةِ ۖ لَوْ يُؤَاخِذُهُم بِمَا كَسَبُوا لَعَجَّلَ لَهُمُ الْعَذَابَ ۚ بَل لَّهُم مَّوْعِدٌ لَّن يَجِدُوا مِن دُونِهِ مَوْئِلًا ጌታህም በጣም መሃሪው የእዝነት ባለቤቱ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነሱ ባስቸኮለባቸው ነበር፡፡ ግን ለእነሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው፡፡ وَتِلْكَ الْقُرَىٰ أَهْلَكْنَاهُمْ لَمَّا ظَلَمُوا وَجَعَلْنَا لِمَهْلِكِهِم مَّوْعِدًا እነዚህ ከተሞችም በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፡፡ ለመጥፊያቸውም የተወሰነ ጊዜን አደረግን፡፡ [ሱረቱል ከህፍ : 58-59] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_297 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
⭕️👉ሁሌም እስቲغፋር የሚያደርግና ይንን ባህሪው የሚያደርግ ሰው ..! ~አላህ ሪዝቁን ያመቻችለታል፦ ~ነገሩን ሁሉ የገራና የተሳካ ያደርግለታል፦ ~ሀይሉና ጉዳዩ የተጠበቀ ያደርግለታል። 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ (በመሳሳትም ብታጠፉ) እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው፡፡ وَآتِ ذَا الْقُرْبَىٰ حَقَّهُ وَالْمِسْكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَلَا تُبَذِّرْ تَبْذِيرًا ለዝምድና ባለቤትም መብቱን ስጥ፡፡ ለምስኪንና ለመንገደኛም (ስጥ)፡፡ ማባከንንም አታባክን፡፡ إِنَّ الْمُبَذِّرِينَ كَانُوا إِخْوَانَ الشَّيَاطِينِ ۖ وَكَانَ الشَّيْطَانُ لِرَبِّهِ كَفُورًا አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፡፡ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡ [ሱረቱል ኢስራዕ : 25-27] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_296 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
3
00:55
Video unavailableShow in Telegram
ሶላት ውስጥ እጅ ከፍ የሚደረገው አራት ቦታ ላይ ነው። ✨ተክቢረተል-ኢህራም ላይ፡ ✨ለሩኩዕ ሲወረድ፡ ✨ከሩኩዕ ስንነሳ/ቀጥ ስንል፡ ✨ከመጀመሪያው ተሸሁድ ስንቆም፡ مواضع رفع الأيدي في الصلاة. الشيخ: خالد المشيقح. 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
نمایش همه...
👍 3