cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

ቲቶ 2 (Titus) 11፤ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 544
مشترکین
+2324 ساعت
+1447 روز
+59430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ዛሬ ምክንያት እየፈለግን እናመሰግንሃለን አንተን ምናመሰግንበት አናጣምና ተመስገን እግዚአብሔር የቀኔ ባለቤት፤ ተመስገን እግዚአብሔር የሕይወቴ መሪ፤ ተመስገን እግዚአብሔር የልቤ ማረፊያ ተመስገን። ስላሳየኸኝ በጎነትህ፣ ስላልነጠፈብኝ ፍቅርህ፣ ስላላጣሁት ምህረትህ ተመስገን። ስላደረክልኝ በረከት፣ ስለላክልኝ ቸርነት፣ ስላበዛህልኝ በጎነትህ አመሰግንሀለው። አስቸጋሪ በሆነው ጊዜ ውስጥ እንኳ ተስፋዬ እንዳይጨልም ስላለመለምክልኝ፣ ያረጀውን እያደስክ በቀና ጎዳና ስለመራኸኝ፣ እኔን ይቅር ማለት ስላልሰለቸህ፣ አስቸጋሪውን እኔን መሸከም ስላልከበደህ፣ በብዙ እድል ስላኖርከኝ የእንደገና አምላክ ሆነህ ስላቆምከኝ ተመስገን። ከእኔ ጋር መዋል ማደር ስላልታከተህ በማይቋረጥ እንክብካቤህ ከጎኔ ስለሆንክ መቼም ስለማትተወኝ ልቤን ከልብህ ጋር ስላቆራኘኻት አመሰግንሃለሁ። ኃጢአቴን እየደመሰስክ በደሌን ከእኔ እያራቅህ ነፃነትና ሕይወት እንዲኖረኝ ስለከፈልክልኝ አስደናቂ መስዋዕትነት አመሰግንሃለሁ። ዛሬም አዕምሮዬን በማስተዋልህ ልቤን በፅኑ ምክርህ መንፈሴን በቅዱሱ መንፈስህ ተቆጣጠርልኝ። መንፈሴን አድስ ሰላምና ደስታን ሙላኝ ቀኑን ሙሉ እወድሀለሁ። አንተ ብቻ ይገባሃልና ክብር፣ ምስጋና፣ አምልኮ አቀርብልሃለሁ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን። የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል @lovedbychrist @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
🙏 4
ዕለታዊ ጁስ 🍹 🍹 ዛሬ ተአምር ነው ፤ በምስጋና ጀምረው! የሰዎች ማረጋገጫ ፣ ጭብጨባ እና ትኩረት እንዲያጠፋህ አትፍቀድ ። ትሁት ሆነክ ቆይ ፤ ስላሳካሃቸው ነገሮች ሁሉ አመስግን ፤ ታላቁ ሁልጊዜ በአንተ ላይ በስራ ላይ እንደሆነ እወቅ ። ስኬት ፍጥረትህ እንደሆነ እወቅ ስለዚህም በምታደርገው ነገር ሁሉ ስኬትን ታመጣለህ ። 🍹 አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ፤ በሀሴት ፣ በፍቅር እና በበረከቶች የተሞላ ህይወትን እንድትኖር ተሹመሃል ። ደስታህን በክርስቶስ ማን እንደሆንክ እና ምን እንዳለህ ላይ እንጂ በሰዎች እና በነገሮች ላይ አትሰረው ። የትናንትናውን መከናወንህ ባሳካኸው ጊዜ በምታየው የደስታ አይን አትመልከተው ። ወደፊት ተመልከት እና ትናንት ካሳካኸው የተሻለ አድርግ ! @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
2
ትዝ ይለኛል አምላኬ ለኔ ያረገው ትውስ ይለኛል ጌትዬ ለኔ ያረገው ×2 እኔ አውቀዋለው ከየት እንዳነሳኝ ብዙ ውለታ ለኔ ዋለልኝ እስሬን ፈቶ በሕይወት ላኖረኝ ልሰዋ ቅኔ ያማረውን ×2 ትዝ ይለኛል አምላኬ ለኔ ያረገው ትውስ ይለኛል ጌትዬ ለኔ ያረገው ×2 ብዙዎች ነበሩ ከኔ የተሻሉ በመልካም ስራ የተመሰገኑ ደም አፍሳሹን ሰው እኔን አዳንከኝ በሰማዩ ጠል አረሰረስከኝ × 2 ትዝ ይለኛል አምላኬ ለኔ ያረገው ትውስ ይለኛል ጌትዬ ለኔ ያረገው ×2 መስፍን ጉቱ ድንቅ መዝሙር @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
3
በኃይለ ደሙ ፀንቷል መዳናችን! መልካም አዳር
نمایش همه...
🙏 4
ስምህ ብቻ አይደለም ስራህ ይናገራል የበላይ አሃ ሃ ተስፋዬ ጫላ @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
የሰኞ ቀን ባርኮት አሜን ብላችሁ ተቀበሉ 🖐️ ትንሳኤህ በዓለም ላይ ብዙ መቃብሮች አሉ ብቸኛው ባዶ መቃብር ግን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ባዶ መቃብር የድል ምሳሌ ነው። ድንጋዩ ምንም ይሁን ምን፣ ጠላቶቹ ማንም ይሁኑ ማን ኢየሱስ ተነስቷል። በባዶው መቃብር ውስጥ ልብሱ እንጂ ኢየሱስ አልነበረም። የትንሳኤው ኃይል ከተዘጋጀላችሁ የሞት ወጥመድ ያስመልጣችሁ። ሰይጣን የመከረው፣ የቆፈረው ሴራ ሁሉ በትንሳኤው ኃይል ይፍረስላችሁ። ጌታ የመቃብር ልብሳችሁን ከእናንተ ያንሳላችሁ። ህመምን፣ ሀዘንን ከሚያመጣ ነገር ሁሉ ይነጥላችሁ። ወደ ኢየሱስ መቃብር የሄዱት ሴቶች ልባቸው ከብዶና አዝኖ ነበር። ነገር ግን ባዶውን መቃብርና የተነሳውን ጌታ ሲያዩ ደስታቸው ወሰን አልነበረውም። ትንሳኤው ሁልጊዜ ከሙታን ጋር ሳይሆን በሕያዋን መካከል እንድትገኙ ያድርጋችሁ። መንፈሳዊ ሕይወታችሁ፣ ትዳራችሁ፣ ንግዳችሁ፣ አገልግሎታችሁ ሁልጊዜ በሕይወት ካሉት ፍሬያማ ከሆኑት ጋር ያድርግላችሁ። ከሞቱት ጋር አትቆጠሩ። ከማንኛውም ዓይነት ሞት ነፃ መውጣትን አግኙ። ሀዘናችሁን ወደ ደስታ ይለውጥላችሁ። በመባረኩ ይባርካችሁ፤ የበረከት ቀን ይሁንላችሁ! የእግዚአብሔር ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን @lovedbychrist @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
🙏 12🔥 2
“ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።” — 1ኛ ዮሐንስ 5፥18
نمایش همه...
🙏 3
ዛሬ አንድ ነገር ገባኝ.... ትዝ ይላቿል ከዛሬ 5 አመት በፊት COVID-19 በሽታ ሲመጣ እነ BBC እና CNN Break News ብለው በሽታውን ለአለም አብስረው ነበር የእኛም ሚዲያዎች በየ ጊዜው በጦርነትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰበር ዜና ብለው ልብ አንጠልጣይ ዜናዎችን አፈራርቀው ዘግበው ነበር ነገር ግን እነዛ በሰዓቱ ልባችንን ላይ ትኩስ የነበሩት ሰበር ዜናዎች ሁሉ ዛሬ ላይ ትዝታ ሆነው እንደ አዲስ የሚሰማቸው ሰው ጠፍቷል ነገር ግን ሰማይ ከዛሬ 2000 አመታት በፊት ሰበር ዜና ብሎ ያበሰረውን ድል ዛሬም ስንሰማው እንደ አዲስ ዜና ልባችን ይደነግጥለታህ... የአለም ሰበር ዜናዎች ሁሉ በጊዜ ሂደት ደብዝዘዋል የትንሳኤው ዜና ግን ዛሬም ሰበር ነው ኢየሱስ ተነስቷል። መልካም ፋሲካ በዓል 🤗 @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
🙏 11 5🔥 3🥰 2
የከሃዲዎቹ ፀፀት መልካም ውጤት በሌለው ፀፀት የጋየው ይሁዳ ኢየሱስን በገንዘብ አሳልፎ ሲሸጥ፤ ልክ ጴጥሮስ ኢየሱስን በገረድ ፊት ሁሉ ክዶት ሲያበቃ የተሰማው ፀፀት ከይሁዳ ጋር አንድ አይነት ነበር። በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ [ኢየሱስ] እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፡— ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።" (ማቴ 27:3፣ 5) ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።" (ሉቃስ 22:62) ልዩነቱ ግን ጴጥሮስ ከተፀፀተ በኋላ ንሰሃ ሲገባ ወይም ሲመለስ ይሁዳ ግን በራሱ ላይ እርምጃ ወስዶ ነበር። //የጴጥርስንና የይሁዳን ክህደት እያበላለጡ ሃሳብ ማንሳቱ ጥቅም ያለው አይመስለኝም ክህደት ያው ክህደት ነው::// ከክህደቱ በኋላ የወሰዱት እርምጃ ግን ከክርስቶስ ጋር መቀጠላቸውንና ቀጣይ ጉዟቸውን ያሳየ እንዲሁም የእግዚአብሔርን መሃሪነት ያስተማረ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ፀፀት በራስ ላይ የሚወሰድ እርምጃ/ራስን ማጥፋት፣ ተስፋ መቁረጥ...../ እነዚህን የሚመሳስሉ ነገሮች ውስጥ የሚያስገባን መሆን የለበትም። ይልቁንም መመለስን ከክርስቶስ ጋር መቀጠልን ምርጫችን መሆን አለበት።“እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።”( 2ኛ ቆሮ 7፥10) ስለዚህ መፀፀትና በጥፋት መንገድ ላይ መሆናችንን ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። በክርስቶስ ዋጋ ተከፍሎ የተሰጠንን ህይወት ቸል ሳንል ከክርስቶስ ጋር የጀመርነውን መንገድ መቀጠል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል @lovedbychrist @lovedbychrist
نمایش همه...
1
.          አንበሳ ነው ዘማሪ ተከስተ ጌትነት|✟ነስቷል   ⌚5:13 ደቂቃ | 💾 4.1 MB sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯   ✅ @lovedbychrist ✅   ✅ @lovedbychrist ✅            🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን
نمایش همه...
1