cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሰብሕዎ በክሂሎቱ sebihowo bekihilotu

ይህ ቻናል የተከፈተው የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ዜማዎችን መዝሙሮችን ትምህርቶችን ስብከቶችን በሚያስተላልፈው በ"ሰብሕዎ በክሂሎቱ " መንፈሳዊ ቲዩብ የሚተላለፉትን መልዕክቶች በቴሌግራም ለመልቀቅ ነው።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
179
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! + እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡ ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ ‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6 ‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10 ‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7 እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡ ‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12 ‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5 ‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31 የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24 አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ] ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18 ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡ የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡ ’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጋቢት 18 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
نمایش همه...
#ጀሃድ_አወጁ!!☝️☝️☝️ ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ይሄነን ቮይስ ስሙ!☝️ እኛ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እና እንድትጠነቀቁ እንጅ ግደሉ ሚል አምላክ ስለሌለን እንደ እነሱ ገጀራ አናነሳም! የክርስቲያን ዝርያት በሙሉ የተዋሕዶ ልጅ ሆነ ፕሮቴስታንት የሆነ ሁሉ ይዳረስ ይስማ በክርስቲያን ላይ በሙሉ ነው እያወጁ ያሉት! ማንኛውም ሰው በቴሌግራም አካውንት ላለው ኦርቶዶክስ በሙሉ ሸር ያድርግ!!! ለበለጠ መሰል መረጃዎች በቴሌግራም ሊንኩን በመጫን ተከታተሉ👉 t.me/DebteraMedia
نمایش همه...
3.80 KB
ስንክሳር ዘወርኀ ጥር - 18 ስንክሳር ዘወርኀ ጥር ፲፰ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ዐሥራ ስምንት በዚች ቀን የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ አፅሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት ነው በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን ። አርኬ ጠ ሰላም እብል ውዕየተ ዐፅምከ በነድ ። እንዘ ታዜምር ጊዮርጊስ ሃይማኖተከ በዐውድ ። እንበለ ወልጦ ሀበኒ በረከተከ ዘልማድ ። ዕብነኑ ይሁቦ በእድ ። ኅበ አቡሁ ኅብስተ ሶበ ይስእል ወልድ ።
نمایش همه...
نمایش همه...
የጥምቀት ግእዝ መዝሙራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መዝሙር Ethiopian Orthodox temket

نمایش همه...
ጥር ፯ ሥላሴ ወረብ በመምህር መሪጌታ ሰሎሞን ሙሴ Ethiopian Orthodox selase wereb

Watch "ገና ወይስ ጌና ምርጥ አስተማሪ የጥያቄዎች መልስ በዲያቆን ሲሳይ ኩማ" on YouTube https://youtu.be/8Svy2xAcaWM
نمایش همه...
نمایش همه...
ታኅሣሥ ተክለሃይማኖት ወረብ በመምህር መሪጌታ ሰሎሞን ሙሴ Ethiopian Orthodox betekerestiyan

نمایش همه...
የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ወረብ እና ምልጣን በመምህር መሪጌታ ሰሎሞን ሙሴ Ethiopian Orthodox aba samuel zewaldeba wereb

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.