fa
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

رفتن به کانال در Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

نمایش بیشتر
1 868
مشترکین
-324 ساعت
-87 روز
-5730 روز
آرشیو پست ها
ዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት 500 ‘ሰብስክራይበር’ ይበቃል እያለ ነው፣ ይህ ምን ማለት ነው? ዩቲዩብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ በይነ መረብ ብቅ ያለው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 23/2005 ነበር። የድርጅቱ ሽርክ መሥራች የሆነው ጃዌድ ካሪም ከዝሆኖች ፊት ቆሞ የለጠፈው የ19 ሰከንድ ተንቀሳቃሽ ምስል የመጀመሪያው የዩቲዩብ ይዘት ነው። ዩቲዩብ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ይዘት፤ራሳቸው ቀርፀው እንዲለጥፉ ያበረታታል። ለዚህ ነው ይድዲያ የቅጂ [ኮፒራይት] ጉዳይ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል የሚለው። የመጀመሪያው እርምጃ ግን ‘አፕላይ’ ማድረግ ነው። “ወደ ዩቲዩብ አካውንትህ ስትገባ የሞኒታይዜሽ (ገንዘብ የማግኛ) ቦታ አለ።አንድ ሺህ ሰብስክራይበር እና 4 ሺህ ሰዓት መታየቱን ለማመልክት አረንጓዴ ጭረት አለ። ሁለቱ አረንጓዴ ሲሆኑ ነው ‘አፕላይ’ የምታደርገው (የምታመለክተው) ።” ተጠቃሚዎች የዩቲዩብ መስፈርት ካሟሉ በኋላ ገቢ ማግኛውን ተጭነው ይሁንታ እስኪሰጣቸው ከ24 አስከ 48 ሰዓታት ሊጠብቁ ይችላሉ። ከወደዱት ለወዳጅዎ  ሼር ያድርጉልን! 📢: t.me/TechnologyMasterPage

⑤Power Supply Unit 〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመ
⑤Power Supply Unit 〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

④Hard Drive 〰〰〰〰〰 ❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
④Hard Drive 〰〰〰〰〰 ❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡ ❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

③ Random Access Memory (RAM) 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታች
③ Random Access Memory (RAM) 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡ ❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል

②Central Processing Unit (CPU) 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂ
②Central Processing Unit (CPU)   〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡ ❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡ ❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡ ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡

① Motherboard 〰〰〰〰〰 ❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Moth
① Motherboard      〰〰〰〰〰 ❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡ ❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡

" ስለ ኢቶክ ሰምተዋል   ካልሰሙ  ኢቶክ የኢትዮጲያ ማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን በሃገር ልጅ የተሰራ ድንቅ ማህበራዊ ሚዲያ ነው ይህንን ማህበራዊ ሚዲያ  ሲጠቀሙ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ክፍያ ያገኛሉ። ማልትም በ Post ፣ በ Comment ፣ በ LIKE እና   ለወዳጅ ዘመድዎ ኢቶክን ሲጋበዙ ክፍያ ያገግኛሉ። አሁኑኑ ኢቶክን ይጠቀሙ። ከፕሌይ ስቶር ላይ app ጫኑ!  https://play.google.com/store/apps/details?id=ethiopia.socialmedia.etok

🔴 ስለ ኪቦርድ ፊደል አደራደር ምን ያውቃሉ? ♦️ ኪቦርድ ላይ የኢንግሊዘኛ ቃላት አደራደር Q | W | E | R | T | Y እያለ ነው የሚቀጥለው። ይህም የአልፋቤት ተርታውን የጠበቀ አይደለም።
🔴 ስለ ኪቦርድ ፊደል አደራደር ምን ያውቃሉ? ♦️ ኪቦርድ ላይ የኢንግሊዘኛ ቃላት አደራደር  Q | W | E | R | T | Y  እያለ ነው የሚቀጥለው። ይህም የአልፋቤት ተርታውን የጠበቀ አይደለም። ይህ ደሞ የሆነበት ምክንያት አለው። ♦️ ኪቦርድ መጀመሪያ ሲፈበረክ የትክክለኛ አልፋቤት ተርታ ነበረው። ይህም ሰዎች በጣም በፍጥነት መፃፍ እንዲችሉ አርጓቸው ነበር። ይህም በጊዜው የነበሩት ኮምፑተሮች ፍጥነታቸው ቀርፋፋ ስለነበር በጣም እንዲዘገዩ እና ስታክ አርገው እንዲቆዩ እያረጋቸው ነበር። ስለዚህ ለተጠቃሚዎች ፍጥነታቸውን እንዲቀንሱ በማሰብ አሁን የምንጠቀምበትን የተዘበራረቀ ተርታ ያለውን ኪቦርድ ተሰራ። ♦️ በአሁኑ ሰአት ግን በተዘበራረቀው ኪቦርድ በፍጥነት መፃፍ ለብዙዎች ከባድ ነገር አይደለም!! _____________________________ t.me/TechnologyMasterPage

#የኮምፒውተር_ሀርድ_ዲስክ_ብልሽት_ምልክቶችን_ይዘንላቹ_ቀርበናል! ▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄ ✏️ያው ሃርድ ዲስክ ሲበላሽ ብዙ ዳታዎች የጠፋሉ እናም ብዙ ችግሮች ሊያጋጥሙዋቹ ይችላል! ነገር ግን ሃርድ ዲስክኩ መበላሸቱ በፊት በሚያሳያቸው ምልክቶችን ይህንን መከላከልሊያስችላቹ ይችላል። ❶. ኮምፕዩተራችሁ የመዘገም (ስሎው) የማለት ባህሪ ሲያጋጥሞ ❷. ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለው ፊደላትን ሲያዩ ❸. በተደጋጋሚ እስታክ ማረግ ሲጀም ❹. የተለያዩ ኢረሮችን(ችግሮችን) ማሳየት ሲጀምር ❺. ኮምፕዩተሩ ጠፍቶ ሲበራ የተለያየ ችግሮች ካሉት ❻. የተለያዩ ሶፍትዌሮች ክራሽ ሲያረጉ ❼. አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲያወጣ ለምሳሌ፦ ፕሪንት ሊደረግ ሲል የተለየ ነገር የሚያወጣ ከሆነ ❽. ዳታዎቻቹ ሲጠፉ ወይም ኮራፕት ሲያረጉ ❾. አንድን ዳታ ለመክፈት ብዙ ሰዓታትን ሲፈጅ ❿. የተለያዩ አላስፈላጉ የሆኑ ድምጽ ከኮምፕዩተራቹ ሲወጣ ኮምፕዩቹህ ይህንን ሁሉ የሚያረግ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሃርድ ዲስክ ሊበላሽ ይችላል ማለት ነው::    ❖ሰለዚህ ይህንን ብልሽት እናንተ ላይ ችግር እንዳያስከተል የተወሰኑ ነገሮችን ብታረጉ የተመረጠ ነው። ⚙እኛ በበኩላችን የምን መርጣችው ሁለት አማራጮች አሉ እነሱም፡ ■የመጀመሪያው S.M.A.R.T (Self-Monitoring, Analysis and Reporting Technology) የተባለን ሶፍትዌር ዳውንⶀድ (በማውረድ) ብልሽቱ ከመፈጠሩ በፉት በማስታወስ ኮምፕዩተሮ ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ፍንጮችን እንድታገኙ ያስችላቹሃል! ■ሁለተኛው ደሞ ኮምፕዩተራቹህ ውስጥ ያሉትን ፋይሎች በየጊዜው ባካፕ(ሌላ ኮፒ በማስቀመጥ) መጠንቀቅ እና ሊጠፉ የሚችሉ ፋይሎችን መታደግ እንችላለን። ባክ አፕ ለመውሰድ ግድ ፍላሽ ወይም ሌላ መሳሪያ አያስፈልጋቹም በኢንተርነት ላይ የተለያዩ የመጫኛ ሳይቶችን መጠቀም ተችላላቹ ══════❁✿❁ ══════           🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ t.me/TtechnologyMasterPages          ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛

በዛሬው የ ኮምፒውተር ትሪክ የምናየው እንዴት በቀላሉ ዊንዶውስ  ጄኒውን (እውተኛ) እንደምናደርግ ነው :: ጄኒውን ማድረግ ማለት original የ window CD    በምንገዛበት ጊዜ አብሮት የሚሰጠንን product key በምናስገባበት ጊዜ ጄኒውን ያደርገዋል። ኦርጅናል ካልሆነ ግን በተለያየ መንገድ ማድረግ ዘዴዎች አሉት። የ Genuine አስፈላጊነት የ ፕሮግራሙ አምራች  የሆነው ማይክሮሶፍት እንዲያቀው እና የፈለግነውን ሶፍትዌር እንድንጭን እንዲሁም የ ኮምፒዩተራችንን ደህንነት በ ማይክሮሶፍት እንዲጠበቅ ይረዳናል። Genuine ወይም Activate ያልሆነ ኮምፒዩተር ከታች የ ሰአት ቦታው አከባቢ ምልክት ያሳየናል። አለበለዚያም setting ውስጥ ገብተን update and privacy የሚለው ውስጥ ስንገባ እናገኘዋለን። ለዛሬ የ window   እናያለን! 1. በመጀመሪያ (cmd) ብለን ሰርች ባር ላይ ትጸፋለችሁ በመቀጠል Right click the Command Prompt listing and select “Run as Administrator” ራይት ክሊክ አድርጋችሁ ራን ቱ አድሚንትሬተር የሚለውን ትቻናላችሁ 2. ዊንዶው ላይ “SLMGR -REARM” ብላችሁ ትጽፋላችኁ ከዛ ኢንተርን እንጫናለን command successfully executed. Restart now የሚቀጥለው ሜሴጅ ሲመጣ ኮምፒውተራችንን restart ok እናደረጋለን። t.me/TechnologyMasterPages

1.ሮስተር መስሪያ.xlsx2.30 KB

🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አልስነይን 1 #ዙልሂጃ 1444 ሂ በሳውዲ የዙልሂጃ ጨረቃ መበከሯን ታውጇል በዚህ መሰረት፦ ➭ ዙልሂጃ ነገ ሰኞ 1 ብሎ ይጀመራል። ➭ ማክሰኞ ሰኔ 20 የ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አልስነይን 1 #ዙልሂጃ 1444 ሂ በሳውዲ የዙልሂጃ ጨረቃ መበከሯን ታውጇል በዚህ መሰረት፦ ➭ ዙልሂጃ ነገ ሰኞ 1 ብሎ ይጀመራል። ➭ ማክሰኞ ሰኔ 20 የአረፋ ቀን ይሆናል። ➭ እሮብ ሰኔ 21 የኢደል አድሃ ቀን ይሆናል። ©️BuhariMuslimAmharic t.me/ReshadIbnuMuzemil

+1
#በድጋሚ ወደ Mp4 ቀይሬው ✴️ Income tax ✴️ Pension ✴️ Allowance ✴️ Net payment #Excel ላይ እንዴት እንደ ሚሰራ #MB size = 13.9MB #Time = 9 Minutes #Sound: Reshad Muzemil #Prepared by: Reshad Muzemil ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ t.me/TechnologyMasterPage #ለኮሌጅ ተማሪዎች ያዘጋጀሁት ቪድዮ ነው፤ ለናተም ይጠቅማችኋል!!

‌〽️ እንኖራለን በሀሴት ኢንዲ ስትል ፃፈች - ያረገዘችው ብዕሬ ለእጄ እንዳይከብደኝ - ክዳኗን ወርውሬ እናም መፃፍ ጀመርኩ - እንዲህ ስል ጀምሬ ግን ገንፍላለችና - ቀለሟ እንዳያልቅ እውነቱ ላውጣው - ልቤ እንዳይጨነቅ በሀቅ ትደሰት - ብዕሬ ትቦርቅ። እስቲ ልሞነጫጭር - ሀሳቤን ልግለጥ ግን አልችልም - ውብ ቃሎችን መምረጥ አጣዳፊ ነውና - ያረገዘቺው ብዕሬ ምጥ። የዕድሜችን ጉዞ ሽሽት የተስፋችን ቅዠት የመኖራችን ሚስጥር የህይወት ቁም ነገር የኑሮ ስንክሳር እንጨነቃለን ኢሀው - ምንም ላንፈጥር በሆነ ጊዜና - ስትጠልቅ ጀምበር ድቅድቁ አይሎ - ጨለማው ሲደራ እኛም ረስተን - ሰባዓዊ ፉጥርነታችንን ፍንትው ብሎ ወጣ - ኢሀው ጭካኔያችን ልብሳችን ሸፍኖት - ያን ትምኪት አንደበት ስንኖር አምሮብን - ኑሮን የውሸት ሰው መች ይህነ አወቀ - እኛነታችንን እውነት ፀሃይ ማብራት ስትጀምር - ለሰው ልጅ በተራ ፍርድም ሲጓደል - እውነት ሲሆን ተራ ከፋፍለን ስንጨርስ - ሰዎችን በጎራ እናም አስተዛዘበን - የአስተሳሰባችን ስፍራ። ጌዜም ሚስጥር ሆነ - እንደ ስልክ ኮድ ሚከፍተው ያለ አይመስልም - አወይ የኛስ ጉድ ወይስ በኮፒ እንክፈተው - በአርተፊሻል ፓስዎርድ ቀኑ ቶሎ መሸ - ለሊቱ ረዘመ ልባችን ታመመ - እኛን እያከመ ሀሴት መበፈለግ - ውስጣችን ከሰመ እንቅፋት በዝቶበት - ደስታን ሚቀማ ግራ ገብቶን አለን - የጭቀት አላማ። ሰኞን እየጠበቅን - ማክሰኞ ደረሰ እሮብ አለፈ - ሀሙስ ተጋመሰ ጨለማው ረዝሞ - ብርሃን  ታመሰ ደስታም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ ቀኑ 24 ሰዓት - እኛ ግን ዜሮ ማሳለፍ ለምደን - ጭንቀትን በጓሮ ለውጥ ላናመጣ - አሰማን ሮሮ ኢሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ ኢሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ። ደግነት ይፃፍበት - በጥላቻ ሰነድ እውነት ይስፈርበት - በጨለማው መንገድ እስቲ ደግ እንሁን - በቃ ሰው እንውደድ በቃ ሰው እናክብር- ውስጣችን እንዳይናድ ለውዴታችን ግን - ምላሽ አንጠብቅ በሚመስጥ ትህትና - ከእውነት እንታረቅ ተስማምተው ከሄዱ - እምነትና ተስፋ ሃቅ ገኃድ ከወጣ - የሰው ልጅ ካልከፋ እውነት ሚስጥር ካልሆነ - ካወጣነው ኢፋ ይሄኔማ ሰው እንሆናለን - ደግነት ያቀፈ ሁሉም ለበጎ ይሆናል - ይጠፋል ብስጭት መመኘት እንጀምራለን - እውነተኛ ምኞት በደስታ ያበበ - ውብ ማራኪ ጊዜያት እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት። በረሻድ ሙዘሚል ቀን፦ ነሃሴ 18/2011[Aug 24/2019] t.me/ReshadIbnuMuzemil t.me/InspiresWorld

ስልኮትን ፓተርን ረስተውት ስልኮ አልከፍት ብሎታል? 👉የተረሳውን ፓተርን አጥፍተን እንዴት ስልኩን እንደገና መክፈት እንደሚችሉ ያቃሉ ⚠️📌  በዚህ Method  ማወቅ ያለብን  ነገር ቢኖር Install ያደረጉት አፕሊኬሽን እንዲሁም የመዘገቡት ስልክም ካለ መጥፋቱ የማይቀር ነው። ያለቦት ስልኮት በቂ battrey እንዳለው check ያርጉ። 📱ከታች ያሉትን 6 ስቴፖች በመጠቀም በ Patternም ሆነ በ Pin የተዘጋ አንድሮይድ ስልክን መክፈት ይቻላን። 1️⃣:- ስልኮትን switch off ያድርጉትና ለጥቂት ሰከንዶች ይጠብቁ። 2️⃣:-  እነዚን ቁልፎች ማለትም Volume up , Home key , power በተኑን ስልኩ እስኪከፈት ድረስ በአንድ ላይ ይጫኗቸው (ይሄ ለ samsung ሲሆን ለ huawei ደግሞ power በተኑን እና volume up እንጫናለን ስልኮት ሲከፍት power በተኑን ይልቀቁት ። 3️⃣:- ከዛም የተለያዩ ኦፕሽኖች ይመጡሎታል። 4️⃣:-volume በተንን ወደ ስር እና ወደ ላይ  እና power button click ለማድረግ እየተጠቀምን "Restore factory defaults" ወይም "Delete all user data" አልያም wipe factory reset የሚለውን እንመርጣለን። ቀጥሎ yes all የሚለውን ከተጫንን በኋላ ፕሮሰሱን ይጨርሳል። 5️⃣:-ከዛም "Reboot system now" የሚለውን ይምረጡ። 6️⃣:- ከዛም ስልኮት Reboot አድርጎ እስኪጨርስ ይጠብቁ። ስልኮት እንደ አዲስ ይከፍታል። ▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ      ❖ Contact      ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።                📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!! ━━━━━━━━━━━━━━━ t.me/TechnologyMasterPages ━━━━━━━━━━━━━━━ ▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬

Repost from Sharp Swords 2
⑤Power Supply Unit 〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመ
⑤Power Supply Unit 〰〰〰〰〰〰〰〰 ❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡