cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Enzi primary, secondary and preparatory school

We will strive to have well educated, broad-minded, patriotic, curios, visionary and self motivated human resource.

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
712
مشترکین
+224 ساعت
+77 روز
+2830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
🕺❤🕺የኢንዚ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች ቀንን ምክንያት በማድረግ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም ዕለተ ቅዳሜ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ እስከ 6:30 ድረስ በባምቡ ፓራዳይዝ ሆቴል #VIP አዳራሽ ውስጥ በሚኖረን ቆይታ የት/ቤቱን 11ኛ ዓመት ምስረታ እና የ5ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻችንን ምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። 🕺🤳🕺ስለሆነም የት/ቤታችን ተማሪዎች ወላጆች እና ጥሪ የሚደረግላችሁ አካላትን ጨምሮ መላው የት/ቤቱ ማህበረሰብ የዚህ ደማቅ ፕሮግራም ታዳሚ እንድትሆኑ እየገለጽን ወላጆችና አሳዳጊዎች በእለቱ የቀጣይ 2017 ዓ/ም መማር ማስተማርን አስመልክቶ ውይይት በማድረግና ስምምነቶች ላይ የሚደረስባቸውን መሪ እቅዶችን በመገምገም ውሳኔዎችን ስለሚያሳልፉ በተደረገላችሁ ጥሪያችን መሰረት እንድትገኙልን በማለት በክብር ጠርተንዎታል። 🕺🤳🕺ኢንዚ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት!!
نمایش همه...
🕺🤳አስቸኳይ መረጃ:- 🤳🕺የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ በርካታ ተማሪዎች በሀሰተኛ የት/ት ማስረጃ በማቅረብና አንዳንዶችም ማስረጃ ለማቅረብ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ምክንያት ከኦንላይን ፎርም በፊት በተሰጣቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ስለማይችሉ እና ከመደበኛው ት/ት ገበታ ላይ  ራሳቸውን በማግለል የተሰናበቱ መኖራቸው ይታወቃል። 🤳🕺🤳ይሁን እንጅ ከላይ በተጠቀሱት ውስጥበተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ እንዳለፉና ት/ቤታችን ማስረጃችንን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም በማለት ራሳቸውን ሲሸውዱ ከቆዩት መካከል ተማሪ ሊያ ጀሰን ክሊራንስ ማቅረብ ባለመቻሏ እና ለመፈተንም የሚያስችል ማስረጃ ባለማቅረቧ ምክንያት ት/ቤቱና አጣሪ ቡድኑ ከዚህ በታች ያለውን ውሳኔ ማለትም:- #ተማሪዋ ማስረጃዋን ባለማቅረቧ ምክንያትና ከዚህ በፊት ስትማርበት በነበረችበት ት/ቤትና ርዕሰ መምህር በኩል በስልክ ባደረሱን መረጃ መሰረት ተማሪዋ የ11ኛ ክፍል ደጋሚ ተማሪ እንደነበረች በተገለጸው መሰረት: # በት/ቤታችንም በኩል ሸኝ አመጣለሁ በቀጠሮ ልመዝገብ በማለት ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ተመዝግባ ስትማር ብትቆይም ማስረጃ እንድታቀርብና ሞደል ፈተናዋንም ሆነ መደበኛውን ሀገር አቀፍ ፈተና እንድትፈተን ይደረጋል የሚል አስተያየት ቢሰጣትም ነገሩን ቸል በማለትና የለመደችውን የማጭበርበር ሂደት ስለቀጠለችበት የት/ቤቱ አጣሪ ቡድንም ማስረጃዋን እንድታቀርብ የመጨረሻ አማራጩን ተጠቅሞ እንድገለጽላት እና ማቅረብ ካልቻለች ግን በማህበራዊ ሚድያ በኩል ተማሪዋ ፈተና ላይ መቀመጥ እንደማትችልና እንድትሰናበት በማለት ውሳኔ አሳልፏል። 🤳🕺🤳ስለሆነም ተማሪ ሊያ ጀሰን የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል #ኢንትራንስ #የማትፈተን መሆኗን እየገለጽን ወላጆች ወይም አሳዳጊዎችም በጉዳዩ ዙሪያ የሚሉት አስተያየት ካለም ት/ቤቱ የሚቀበልና ቀጣዩንም ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን።
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦን-ላይን የሚፈተኑ ተማሪዎች ሞዴል ፈተና በአሶሳ ዩኒቨርስቲ እየወሰዱ ነው ………… ………… ………… ………… …… ……… (ሰኔ 24/2016 ዓ.ም አሶሳ) የቤኒሻንጉል - ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦን-ላይን ለሚፈተኑ ተማሪዎች ሞዴል ፈተና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ሞዴል ፈተናው ለዋናው ፈተና ተማሪዎችን የሚያዘጋጅና ከወዲሁ ተማሪዎቹ እንዲለማመዱ ዝግጁ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ሲሉ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ-ትምህርትና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊው አቶ መሀመድ ኡስማን ገልጸዋል፡፡ ምክትል ቢሮ ሃላፊውና የቢሮው ባለሙያዎችም ተፈታኝ ተማሪዎችን በመዘዋወር የተመለከቷቸው ሲሆን ቀሪ ስራዎችንም ከሚመለከታቸው የዩኒቨርስው ተጠሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በኦን ላይን ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 1,011 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሲሆኑ 593 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ቢሮው በትስስር ገጹ ላይ ያሳወቀውን የፈተና ድስፕሊን ተማሪዎች እንዲጠብቁና የሚመለከታቸው አካላትም ይህኑ እንዲያስተገብሩ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ መሀመድ ኡስማን አሳስበዋል፡፡ ዘገባው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው፡፡
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም እንዴት ናችው ውድ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች! የሞደል ፈተና ሚሰጠው ነገ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ/ም ከሰዓት ፈረቃ መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ተማሪ ለፈተና አገልግሎት የሚጠቀማቸው ቁሶች ማለትም:- #የተሟላ የት/ቤት ደንብ ልብስ /ዩንፎርም #መንነታችሁን የሚገልጽ የት/ቤት መታወቂያ እና #ID Card መያዝ ግዴታ ሲሆን ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እየገለጽን ምናልባት ሞባይልና የተለያዩ ጌጣጌጥ መሰል ምስሎችን በመያዝ ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ በመምጣት የተያዘ ተማሪ ላይ በሚፈጠረው መጉላላት ት/ቤቱም ሆነ ሌላ አካል ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ:- #በአሶሳ ዩንቨርስቲ ሚሰጠውን ሞደል ፈተና አለመውሰድ ከመደበኛው ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ እንዳትቀመጡ ምክንያት ይሆናል። #ኢንዚ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
نمایش همه...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት:- የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች (ዩኒቨርስቲዎች) ይዘው መግባት በጥብቅ የተከለከሉትን በውል ማወቅና መተግበር እንዳለባቸው ቢሮው ከወዲሁ ያሳስባል፡፡ መረጃዎችን በተለመደው አግባብ ለሌሎችም እንዲደርስ (ሼር) ያጋሩልን፡፡ የሁሉም ወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ብሎም የተማሪ ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ጣቢያ ከመምጣታቸው በፊት ችግር እንዳይገጥማቸው ግንዛቤ የመስጠትና የማገዝ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ምንጭ #BGEB#
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🤳💄💪አስቸኳይ መረጃ:- ለኢንዚ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ:-  🤳💄💪በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በይነ መረብ የOnline ፈተና ለምትወስዱት ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት ይረዳችሁ ዘንድ መንግስት የመለማመጃ ሞዴል ፈተና አዘጋጅቷል፤ ስለሆነም:- 🤳💄💪የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ሰኔ 24/10/2016 ዓ/ም ጀምሮ ጠዋት ከ3:00-6:00 ሰዓት ለማህበራዊ ሳይንስ ከ9:00-12:00 ለተፈጥሮ ሣይንስ በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በመገኘት እንድትፈተኑ እና በቂ ልምምድ እንድታደርጉ እና ሞደል ፈተናውን በብቃት እንድትወስዱ በማለት እናሣስባለን።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
❤ሰኔ 20/2016 ዓ/ም:- #የ2016 ዓ/ም የኢንዚ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት #ከሰኔ 17-20/2016 ዓ/ም ድረስ የ2ኛ ወሰነ ት/ት #የተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተና #በሰላም ተጀምሮ #በሰላም ተጠናቀቀ። #የትምህርት ዘመኑን የተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተና #ከጅምሩ እስከ ማጠናቀቅ ድረስ #ፍጹም ሰላማዊና #ድስፕሊን በተሞላበት አግባብ #ማጠናቀቅ በመቻላችንና ውድ ተማሪዎችና መምህራንን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካሎቻችን ለፈተናው መሳካት የበኩላችሁን ላበረከታችሁ በጎ ተጽእኖ በት/ቤቱ ስም እናመሰግናለን። #ኢንዚ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት!!
نمایش همه...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የፈተና ዲሲፕሊን መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የፈተና ዲሲፕሊን መመሪያ ያለው ሲሆን አጠቃላይ ዓላማውም በበየነ መረብ የፈተና ሂደት የሚሳተፉ ተፈታኞች የፈተና ህግጋትን አክብረው እንዲፈተኑ በማድረግ ፍትሃዊነት፣ ታማኝነት እና ወጥነት ያለው አሰራር መዘርጋት ነው። በዚሁ መመሪያ ላይ በተማሪዎች በኩል የሚታዩ የዲሲፕሊን ጥሰቶችና የሚወሰዱ እርምጃዎች የተጠቀሱ ሲሆን በሚከተለው መልኩ ተቀምጠዋል፡፡ .በፈተና ጥፋቶች ውስጥ የተማሪዎች ተሳትፎ፣ የስርቆት ይዘቶችና የማዕቀብ ሁኔታዎች ፡- • አንቀጽ 1፡ ዕጩ ተፈታኝ ተማሪ አልኮል ጠጥቶ ሰክሮ ወደ ፈተና ግቢ መግባት፤ እየተሰጠ ያለውን ፈተና መፈተን አይችልም፣ • አንቀፅ 2፡ የፈተና ፈታኙ ግዴታውን ሲወጣ ማስፈራራት፤ እየተሰጠ ያለውን ፈተና መፈተን አይችልም። • አንቀፅ 3፡ ባልተፈቀደለት የፈተና ማዕከል መገልገያዎች ወይም ንብረቶች ውስጥ መገኘት/መግባት፤ የሚሰጠውን ፈተና መፈተን አይችልም፣ • አንቀጽ 4፡ የመታወቂያ ካርድን በአጋጣሚ ወይም በግዴለሽነት መጣል፤ የሚሰጠውን ፈተና መፈተን አይችልም፣ • አንቀፅ 5፡ ተፈታኞች ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያን ለማሳየትም ሆነ ለማስፈተሽ ፈቃደኛ ያልሆነ ተግባራትን በሚፈጽሙ፣በፈተና አስተዳዳሪዎች ሲጠየቁ ፍቃደኛ ካልሆነ ፈተናውን እንዳይፈተኑ ይከለከላሉ፣ • አንቀፅ 6፡ የፊት መሸፈኛን ገልጦ የአንድን ሰው ፊት ለሴት ፈታኝ ወይም ለማንኛውም ሴት የፈተና ተቆጣጣሪ እና በወንድ ፈታሽ ወይም ለፈተና ጣቢያ ኋላፊው/አስተዳዳሪው የፈተና በር ላይ የተሸፈነውን የተፈታኝ ተማሪ ፊት ማንነት እንዲያውቅ አለመፍቀድ/ፈቃደኛ አለመሆን ፈተናውን እንዳይፈተን ይከለከልና በህግ ከለላ ስር ሆኖ የወንጀል ምርመራ ይደረግበታል፣ • አንቀጽ 7፡ ከተፈቀደው ጊዜ ውጪ ወደ ፈተና ክፍል ዘግይቶ መግባት (20 ደቂቃ ፈተና ከጀመረ በኋላ) እየተሰጠ ያለውን ፈተና እንዳይፈተን ይከለከላል፣ • አንቀጽ 8፡ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት (30 ደቂቃ) ከፈተና ክፍል ቀደም ብሎ መውጣት እስከሚፈለገው ጊዜ ድረስ እንዲቆይ ይደረግና ክፍል ውስጥ ለመቆየት ፈቃደኛ ካልሆነ ፈተናው ይሰረዛል፣ • አንቀጽ 9፡ ራስን በልብስ፣ በፀጉር አሠራር፣ በጭምብል እና/ወይም በሌላ በማንኛውም መልኩ ሌሎችን በሚያታልል ወይም በሚያስደነግጥ መልኩ ማንነቱን በትክክል ያልገለጠ፣ ፈተናውን መፈተን አይችልም፣ • አንቀጽ 10፡ ፈተናውን ብቻ ካነበበ በኋላ እንደታመመ በማስመሰል ከፈተና ክፍል መውጣት እየተሰጠ ያለውን ፈተና አይወስድም ፣ በፀጥታ አካላት ከላለ ስር ይቆይና ምርመራ ይደረግበታል፣ • አንቀጽ 11፡ ሆን ብሎ ፈተና ተሰርቋል ወይም ለአንድ ተማሪ የሚሰጠው ፈተና በሚወስዱ ተማሪዎች ላይ ሽብር ለመፍጠር መሞከር፣ ፈተናውን አይፈተንም፣ በተጨማሪም ሌሎች ቀሪ ፈተናዎችም ካሉ አይፈተንም፣ • አንቀጽ 12፡ አንድ ሰው ካልተፈቀደለት በስተቀር ፈተና እንዲፈተን ያልተመደበበት ክፍል ውስጥ በመግባት ፈተና መፈተን ፈተናውን እንዳይፈተን መከልከል አለበት፤ በተጨማሪም በህግ ከላላ ስር ይቆይና ምርመራ ይካሄድበታል። • አንቀጽ 13፡ ጊዜው ካለፈ በኋላ ፈተና መፃፍ ማቆም ባለመቻሉ የቃል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤ ካልታረመ የፈተና ወረቀቱን እንዳይያዝ ፈታኙ መምህር በልዩ ሁኔታ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ምልክት ያደርግበታል፣ • አንቀጽ 14፡ ወደ ፈተና ክፍል ሲገባ ለመፈተሽ ፈቃደኛ አለመሆን እየተሰ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.