cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የፍቅር ታሪክ❤❤❤😜😜

🌷🌷ከረፈደ እዉነተኛ ልብ የሚነካ የፍቅር ታሪክ 🌷❤️❤ 🌷 🌷ክፍል አንድ 🌷❤❤️ 🌷🌷ክፍል ሁለት 🌷❤️❤️ 🌷🌷ክፍል ሦስት🌷❤️❤️ 🌷🌷ክፍል አራት🌷❤❤ 🌷,,,,,,,,,,ሁሉንም በአንድ,,,,,, 🌷 👉 t.me/Yefikr_tark👈

نمایش بیشتر
أثيوبيا12 804امهری9 277دسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
208
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
+230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

zena Manchester United
نمایش همه...
3
​​#የመጨረሻ ክፍል# https://youtu.be/Bq3JUnFpN24 ድንገት መካከላቸው ወጣ ገባ ስትል የነበረች አንዲት መኪና አቅጣጫ ቀይራ ከመሀላቸው ስትወጣ ሚኪ ዞሮ መኪናዋን የሚያሽከረክረው መሳይ መሆኑን ሲመለከት በድንጋጤ እየጮኽ ፅናት መንገድ መንገድ ዘግታ እንድታስቆመው አደረገ። መሳይም በሁኔታው እየተደነባበረ ከመኪናው ወርዶ ሮጦ ከመጣው ሚኪ ጋር ተቃቀፈ። ተያይዘው ወደ አንድ ሆቴል በማምራት እንዴት ነገሮች ተቀይረው ለዚህ እንደበቃ እየጠየቀው በመሀል የፅናት ስልክ ጠራ ። ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ተመለከተችው። ፊቷ ተለዋወጠ። " ይኼ የማያፍር ሰይጣን ደግሞ ስልኬ ይደውላል እንዴ!" ብላ ስልኩን በመዝጋት በንዴት ስትንጨረጨር ከመሳይ ጋር የጀመረውን ጫወታ አቋርጦ••• hi"ማነው ፅኑዬ? " ያ ብሩክ ተብየው ነዋ!" "ተይው አትበሳጪ ስራው ካንቺ በላይ እኔን ማበሳጨት እንደነበረበት አውቃለሁ። ግን ደነዘዝኩ ባንዱ ጉዳት የተሰበረው ልብሽ ሳይጠገን በጉዳት ላይ ጉዳት ሲደራረብብሽ የመበሳጨትም አቅም ያጥርሽና ትደነዝዣለሽ። እንደ ብሩኬ አይነት ሰዎች ብዙ ናቸው። ሲበዛ እራስ ወዳዴች ከመሆናቸው የተነሳ አንቺ ችግር ውስጥ ስትገቢ ከዛ ችግር እንድትወጪ ከመርዳት ይልቅ -በችግርሽ -በእጦትሽ -በስጋት እና በፍርሀትሽ ሁሉ ተጠቅመው አንቺን እንዴት አድርገው ለፍላጎትና ለጥቅማቸው መሳካት እንደሚጠቀምቡሽ ነው የሚያስቡት። ብሩኬም እንደዚሁ ነው ያደረገው። በምኞት ላይ በፈፀምኩት ክህደትና በደል ከባድ ፀፀት ውስጥ መውደቄን በፀፀት ውስጥ ባገረሸው ፍቅሯ መጎዳቴንና የትም አለች ቢሉኝ እሷን ለማግኘት የማልወጣው ተራራ የማልፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ሲረዳ ሰው ቢሆን ኖሮ አጠገቤ ሆኖ ጉዳቴን በተጎዳ። ፍቅሬን ምኞቴን ፀፀቴን እንዳገኛት ከጎኔ ሆኖ በደከመ። ግን እሱ ሰው ቢሆንም እንደሰው እየኖረ አልነበረምና የኔን መጥፎ አጋጣሚ እራሱን ጠቅሞ እኔን ለመጉዳት ተጠቀመበት አንድ ያለችኝ መፅናኛ እህቴን አንቺን ሊያሳጣኝ ተሯሯጠ። ፈጣሪም ሩጫውን ገታው። ሀሳቡ ሳይሳካ መንገድ ላይ አስቀረው። የኔ ምኞት ግን ጠፍታ አትቀርም!" አለና እንባ ያቀረሩ አይኖቹን ጨምቆ አቀረቀረ። መሳይ ሚኪ ያወራውን ሲሰማ በተቀመጠበት ልቡ መምታት ያቆመች መሰለው ምድርና ሰማዩ ተገለባበጠበት። በዛች ቅፅበት ምን እንደሚያወራ ፣ምን እንደሚል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ተሳነው!። ምኞት ታየችው የሚያጣት ሚኪ የሚወስድበት መሰለው። ብድግ ብሎ ወደ ሽንት ቤት ለመሄድ አሰበና ጭንቅላቱ ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት፣ፍጭት እና ጩኸት ገና ከወንበሩ ሲነሳ አዙሮ የሚደፋው መሰለውና መነሳቱን አልደፈረም። እዛው በተቀመጠበት በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ እሱም እንደሚኪ አቀረቀረ። መሀላቸው ቁጭ ያለችው ፅናት ብሩክ ሲደውል የተንቀለቀለው ንዴቷ ጠፍቶ በረዶ ሆነች። የሁለቱንም ስሜት በየተራ እየተመለከተች ነበርና ሚኪ ባውራው ነገር መሳይ ለእብደት የዳረገውን ያለፈ መጥፎ የፍቅር ሂወቱን አስቦ የተረበሸ መሰላት ። "እባክህ ሚኪ እንደዚህ አትሁን እሱንም ረበሽከው እኮ! እባክህ ተረጋጋ!" ብላው ደሞ ወደ መሳይ ዞራ "ድንገት አግኝተንህ ማሰብ የማትፈልገውን መጥፎ ትዝታህን ስለቀሰቀስንብህ ይቅርታ እባክህ አትረበሽ። መሳይ ለፅናት መልስም አልሰጣትም። ቀናም አላለም። ግራ ሲገባት ወደ ሚኪ ተጠግታ ገና ሚኪዬ ብሏ እንደተጣራች ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ድፍት ያለውን መሳይን እየተመለከተ••• "ከሁሉም ነገር በፊት ትልቅ ይቅርታ እጠይቅሀለሁ መሳይ ወንድሜ! ይቅርታ የምጠይቅህ ግን ዛሬ ስለረበሽኩ ሳይሆን ለቆየ በደሌ ነው። በደሌ ምን እንደሆነና ለምን ይቅር በለኝ እንዳልኩህ ኑዛዜየን ስጨርስ ትረዳዋለህ። "አዋ ዛሬ ትክክለኛው ቀን ነው ከዚህ በፊት ብዙ ግዜ አግኝቼህ ሊሆን ይችላል። ፍቅርህን ናርዶስን ከማጣትህ በፊትም እሷን አጥተህ ልክ እኔ ዛሬ ቀን እንደጨለመብኝ በቀን ጨለማ ተውጠኽም እንዳገኘሁኽ አስታውሳለሁ። ግን መጎዳትህን አየሁ እንጂ ጉዳትህን አልተጎዳሁትም ነበር። በፍቅር ህመም ክፉኛ መታመምህን ተመለከትኩ እንጂ ህመምህን አልታመምኩትም ነበር። ካጠገብህ ዘወር ስል እረሳዋለሁ። ያንተ እንደዛ መሆን አይገባኝም፣ አያስጨንቀኝም፣ አይቆረቁረኝም። ዛሬ ግን ሕመምኽን ታምሜዋለሁና ጉዳትህን ተጎድቼዋለሁና ልክ እንዳየሁኽ ስላንተና ስለናርዶስ የማውቀውን ሚስጥር ሳልነግርህ ማለፍ አልቻልኩም። አቃተኝ። ሚኪ ስለፍቅረኛው ናርዶስ እኔ የማላውቀውን ሚስጥር ይነግረኛል ብሎ አልጠበቀምና ስለምኞት እያሰበ እሱን ከማድመጥ ውጪ ቀናም አላለም። "መሳይ ወላጅ አባትህ ጓደኛዬ ነው እሱን ይቅር የማለት እና ያለማለት ያንተ ፋንታ ነው ለኔ ግን ሁለቱም ጓደኛቼ አንድ አይነት ሰይጣኖች ናቸው አባትህ እና ብሩኬ!" አለ። እኼን ግዜ እንኳንስ የመሳይ የፅናት የልብ ትርታ እጥፍ ሆነ ሚኪ ምን ሊያወራ ነው ብላ ሁሉ ነገሯ ስራ ፈትቶ ሚኪ ላይ ተተከለች። መሳይ "ይኼ ሰው ደሞ ምን ሊያሰማኝ ነው ፈጣሪዬ እባክህ የምችልበትን አቅም ስጠኝ። አለ አንገቱን እንደደፋ ፍርሀት ከላይ እስከታች እየናጠው። ሚኪ ቀጠለ••• " አባትህ ከናርዶስ ጋር የነበረኽን የፍቅር ግኑኝነት በጭራሽ አይፈልገውም ነበር። ይኽን አንተም ታውቀዋለኽ። ናርዶስን ያልፈለጋት ያጠፋችው ወይ ያጎደለችው ነገር ስለነበር አይደለም። ጥፋቷም ጉድለቷም ድሃ መኾኗ : ከድሃ ቤተሰብ መፈጠሯ ብቻ ነበር። በአባትህ አይን ይቺ ያንተ ድሃዋ ናርዶስ እሱ ሊድርህ ለፈለገው ሰው እንዳይድርኽ መዃል የገባች የፍላጎቱ ፀር የእቅዱ ጠንቅ ነበረች። ይሄን ግዜ መሳይ ካቀረቀረበት ቀና እለና ሚኪ ላይ አፈጠጠበት ። አይኖቹ ደም ለብሰዋል። ፅናት መሳይን ስትመለከተው ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው እየተፋጩ ነው። ፈራች መሳይ እብደቱ የጀመረው መሰላት "ሚኪ አብደሃል ምንድን ነው የምታወራው ተነስ በቃ እንሂድ !" አለች ብድግ ብላ ቀና ብሎ እየተመለከታት"የትም አልሄድምም! አላበድኩምም! ያበድኩት ይሄን እውነት እያወቅኩ ሳልቃወም እውነቱን ደብቄ ለመሳይ እብደት ተባባሪ የሆንኩ እለት ነበር ፅናቴ ። እባክሽ አታቋርጭኝ! "ቀጠለ••• " እናም ይቺን የእቅዱ ጠንቅ የሆነችውን ናርዶስን በዘበኝነት ተቀጥረው እየሰሩ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆነው ባሳደጓት በአባቷ መጣባት። ለአቧታ ያላትን ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ለሚያጥሯት ናርዶስ ! አባቷን በሸረበው ተንኮል ወንጀል ውስጥ መግባታቸውን መስማት ከባድ ነበር። አባቷ እስር ቤት ገብተው እንዲማቅቁ የማትፈልግ ከሆነ አንተን እስከመጨረሻው ትታ እሱ ወደ ሚላት ቦታ ጨርቄን ማቄን ሳትል መሄድ እንዳለባት ሲጠይቃት ምርጫ አልነበራትምና ተስማማች። " መሳይ በዛን ግዜ የነበረው የአባቱ ሁኔታ በሙሉ ፊቱ ተደቀነበት ከእናቱ ሞት ቡሀላ የህይወቱን መራር ለቅሶ እያለቀሰ " እባክህ ወዴት እንደወሰዳት የት እንዳስቀመጣት ንገረኝ ሚኪ!" ፅናትም ሚኪም አብረውት አነቡ። ሚኪ ብድግ ብሎ ወደ መሳይ በመሄድ "እራስህን አረጋጋ መሳይ ወንድሜ ከዚህ ሰአት ቡኻላ በፈለግከው ሰአት ያንተ ናርዶስ ወዳለችበት ልወስድህ ዝግጁ ነኝ!! አንድ ቀን እንዲህ በአጋጣሚ እኔንም የኔ ምኞት ወዳለችበት ቦታ የሚወስደኝ ሰው ይልክልኝ ይሆናል ፈጣሪ !!" አለው። መሳይ ውስጡ ያለውን የተደበላለቀ ስሜት መረዳት ከበደው ተነስቶ ሚኪን አቅፎት ለሰከንዶች ቆየና ለቆት ወደ ሆቴሉ መታጠቢያ ቤት አመራ ። መታጠቢያ ቤት ገብቶ እራሱን
نمایش همه...

​​😘ምኞት😘 🔥ክፍል 48 https://youtu.be/Bq3JUnFpN24 "ተርፏል ብዙ አልተጎዳም መሰለኝ እናውጣው እስቲ በዛ በኩል ክፈቱት ኑ እባካችሁ እንፍጠን!" አለ ብሩክ መኪና ጋር ቀድሞ የደረሰው ሰው ከፊት በተጨራመተው መኪናው ውስጥ ፊቱ በደም የተጨማለቀውን ብሩክን ለማዳን አልከፈት ያለውን በር ለመክፈት እየታገለ። "ኧረ ተው እባካችሁ ትራፊክ ሳይመጣ መነካካቱ ጥሩ አይመስለኝም አለች አንዲት ሴትዬ ወደመኪናው እየተጠጋች ። አንድ አጠገባ የነበረ ሰው ብሽቅ ብሎ " እኔኮ እማይገባኝ ትራፊክ እስኪመጣ ውስጥ ያለው ሰው ደሙ ፈሶ ይሙት ነው እምትይው? ጥፋተኛው እንደሆነ ከውኻላ መጥቶ የገጨው እራሱ እንደሆነ ይታወቃል! ደሞ ባይታወቅስ አንድ አደጋ ሲደርስ ትራፊክ እስኪመጣ ፖሊስ እስኪመጣ እያልን ባደጋ የተጎዳው ሰው እስኪሞት መጠበቁ ተገቢ ነው? ፈጣሪ ምናልባት በኛ ምክንያት ዳን ብሎት ቢሆንስ የኛ እንቢተኝነት ምን እሚሉት ነው? ተጠያቂነትን ለመሸሽ በሰው ስቃይና ነብስ መፍረድ ሰው ከሆነ ፍጡር አይጠበቅም። " እሱስ ልክ ነው አለች ሴትዮዋ የሰውየው ብስጭት አስደንግጧት። ብሩክን ከመኪኖው ውስጥ ተጋግዘው አወጡት። ግንባሩ አከባቢ በፍንጥርጣሪ ከመፈንከቱና ከጉልበቱ በታች መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ ውጪ ብዙ የሚያሰጋ ጉዳት አልደረሰበትም። "ፈጣሪ ይመስገን ኧረ ምንም አልተጎዳም ቀበቶ ማሰሩ በጀው!" አለ ከመሀላቸው አንደኛው። ማን እንደደወለ ባይታወቅም ከደቂቃዎች ቡኻላ አንድ አንፑላንስ እያቃንጨለች ቦታው ደረሰች አፋፍሰው አስገቡት አንድ የብሩክን ሞባይል እና የኪስ ዋሌት የያዘ ግለሰብ አብሮት ወደ ሆስፒታል ሄደ። ብሩኬ ከሌላ መኪና ጋር በተላተመበት ተመሰሳይ ሰአት ላይ በሀዋሳ ሁለት ወይን እስከወገባቸው የያዙ ብርጭቆዎች እርስ በርስ ተላተሙ። ምኛት እና መሳይ ሀዋሳ ከደረሱ ቡሀላ ስለምንም ጉዳይ ሳያወሩ መዝናናትና መዝናናት ላይ ብቻ በማተኮር ታስራ እንደተለቀቀች ጥጃ በሀዋሳ ምድር ሲቦርቁ ሲሽከረከሩ ሲስቁ ሲበሻሸቁ ዋሉ። ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከባቢ አልጋ ወደያዙበት ሄቴል አምርተው እራት በልተው ከጨረሱ ቡሀላ የብሩኬ መኪና ስትጋጭ እነሱ ለፍቅራቸው ወይን የተቀዳበት ብርጭቋቸውን አጋጩ። መሳይ ጎንጨት አለና ውስጡ ሲከነክነው የነበረውን ነገር አነሳ "የፍቅር ታሪክሽን እንጂ ፍቅረኛሽ ስለነበረው ሰው ማንነት እኮ አልነገርሽኝም አላት ። እሄን ርእስ እንደጦር በፍርሀት ስትጠብቀው ነበርና ደነገጠች ፍርሀቱን የጫሩባት ሁለት ምክንያቶች ነበሯት ። አንደኛው የርእሱ መነሳት ወደ ነበሩበት ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዳይከታቸው መፍራቷ ሲሆን ሁለተኛው ስጓቷ ደግሞ ሚኪ በመጀመሪያው አዲስ አበባ በመጣችበት ቀን በቤቱ መታደስ ሰበብ ወደዛ ኮንዶሚንየም ሲያመጣት ኮንዶሚንየሙን የተከራዩት እሱና ሌሎች ጓደኛቹ በጋራ ሆነው እንደነበር ነግሯታል ። መሳይን ወደዛ ኮንደሚንየም ያመጣው ደሞ አባቱ ነው። አባትየው ከተከራዮቹ አንድ ከሆነ ደሞ ከሚኪ ጋር ይተዋወቃሉ ማለት ነው ። የመሳይ አባትና ሚኪ ከተዋወቁ ደግሞ መሳይ ሚኪን ሊያውቀው ይችላል እኼንን ስታስብ ለምን እንደሆነ ለራሳም ባይገባትም እዛ ኮንደሚንየም ውስጥ አምጥቶ የጣላት ፍቅረኛዋ ሚኪ መሆኑን ለመሳይ መናገሩ አስፈራት። ግን እስከመቼ? ትንሽ ተቁነጠነጠችና እሄውልህ መስዬ••• አሁን ለግዜው አንተም ከናርዶስ አለም እኔም የኔ ከነበረው ሰው አለም ወጥተን በራሳችን አለም ውስጥ የምናሳልፍበት ግዜ ቢሆን አይሻልም መስዬ እስከመጨረሻው ባንድ ግዜ አውጥተን መጣል ባንችልም እስቲ ትንሽ ግዜ አንተን ለአመት እኔን ለወራት ሲያስጨንቁን የነበሩትን ሀሳቦች ፊት እንንሳቸው!? አለችው " ግድ የለሽም ምኛትዬ በሙሉ ልብ ወደራሳችን አለም ለመግባት መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ስላሉ ነው ቀለል አርጊው እና ንገሪኝ እባክሽ ?"አላት። አቦ ያበጠው ይፈንዳ ምን አስጨነቀኝሳ አለች በውስጧ ወድያው ሚኪ •••ማለት ሚክያስ ይባላል ።ለብዙ አመት ከሀገር ውጪ ቆይቶ በቅርብ ግዜ ነው ወደ የመጣው ስትለው ••• መሳይ አፉን ተሻግሮ ጉሮሮው ላይ ደርሶ የነበረው ወይን ትን ብሎት ሊወጣ ሲል እንደምንም አከሸፈው ። ደነገጠ ሚኪን በደንብ ያውቀዋል ከአባቱ ጋር በእድሜ የማይደራረሱ ሚኪ ገና በጎልማሳዎቹ እድሜ ውስጥ ያለ ሰው ቢሆንም ከአባትየው ጋር ጓደኛ ነው እቤታቸው ብዙ ግዜ ይመጣል ከሱም ጋር በጣም ይግባባሉ ። ምን እንዳስደነገጠው አሰበ እቺን ልጅ እየወደድኳት ነው መሰለኝ ፈጣሪዬ ባክህ ዳግም ለጉዳት አታጋልጠኝ አለ በውስጡ። ዝምታው ያስፈራት ምኛት ምነው ዝም አልክ መስ ታውቀዋለህ እንዴ? አለችው "ኧረ በጭራሽ አላውቀውም ያስጨነኩሽ መሎኝ ነው ዝም ያልኩት ብሎ መልሶ ፀጥ አለ። ዝምታ በመሀላቸው ሰፈነ ተያዩ መሳይ ከዝምታው መሀል ድንገት ያልታሰበ እና ቦንብ የሆነ ጥያቄ አስወነጨፈ። "ምኛትዬ" ወዬ መስ ምነው ? " ሚኪ እንደው ምናልባት ባንቺ ላይ ያደረገው ነገር ስተት እንደነበር ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ይቅርታውን ተቀብለሽ ታርቀሽው አብረሽው ትኖሪያለሽ... ይቀጥላል.. https://youtu.be/Bq3JUnFpN24
نمایش همه...

​​​😘ም........ኞ........ት😘 🍃🙇🔥ክፍል 44🍃🙇🌸💞 እንዳሰበችው መሳይ አንዲት ጉርድ ፎቶ በእጁ ይዞ ደረቱ ላይ ልጥፍ እንዳረጋት እንቅልፍ ጥሎታል። ቀስ ብላ ፍራሹን ከተሻገረች ቡሀላ ወደ መደበቂያ ዕቃ ቤቷ ከመግባቷ በፊት መሳይ ይዞ የተኛው ፎቶ የኖርዶስ ሊሆን እንደሚችል ስለገመተች ማየት ፈለገች ደሞ እንዳይነቃ ፈራች። ድምፅ ላለማሰማት እየተጠነቀቀች በቀስታ ፍራሹ ላይ በርከክ አለችና ከእጁ ላይ የፎቶዋን ጫፍ ይዛ ጎተት ስታደርጋት ለቀቀላት ወድያው ገልብጣ ስትመለከተው እንደጠረጠረችው የኖርዶስ ፎቶ ነበር " እውነትም ቆንጆ ነሽ ናርዶስ ግን ከኔ አትበልጭም አደል? አለች ፎቶው ላይ እንዳፈጠጠች ፈገግ ብላ ዘወር ስትል ከፍራሹ አጠገብ የመሳይ የኪስ ዋሌት መሬት ወድቋል። ተጨማሪ ፎቶ ሊኖር እንደሚችል ስለገመተች አንስታ በመክፈት ስትመለከት ኖርዶስ በዋሌት መጠን እና በጉርድ የተነሳቻቸው ዘጠኝ ፎቶዋች አገኘች አንዱን ገልበጥ ስታደርገው "የኔ ናርዶስ መጣሽም ቀረሽም እስከምሞት አፈቅርሻለሁ ያንቺው እብድ አፍቃሪ መሳይ ይላል። ሌሎቹንም በየተራ እየገለበጠች ጀርባቸውን ስትመለከት አንድ ሌላ ፌቶ ላይ የተፃፈው••• ላንቺ ተፈጥሪያለሁ በምድር ሂወቴ አንቺን አፍቅሪያለሁ ባንቺ እራሴን ጠልቻለሁ ባንቺ አብጃለሁ በልቤ እንደያዝኩሽ ወደ መቃብር እወርዳለሁ ይላል ። ሚኪ ትዝ አላት እምባዋ ከሁለት አይኖቿ ቁልቁል መውረድ ጀመረ። ሚኪ መቀሌ ደርሶ "መጥቻለሁ ምኞትዬ ያለሽበትን ንገሪኝ እና ልምጣ እባክሽ የኔ ስስት ብሎ መልክት ላከ ። ብሩኬ የሚኪን መልክት ቢመለከቱውም መልስ አልሰጠውም ዝም አለው ሚኪ መልክት ደጋግሞ ቢልክም መልስ ስላላገኘ በጭንቀትና በብስጭት ለሰዓታት ከቆየ ቡሀላ " እባክሽ ስስቴ ልታገኝኝ ካልፈለግሽ ወደ መጣሁበት ልመለስ ቁርጡን ንገሪኝ" ብሎ ሲፅፍ ተመልሶ ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው ብሎ የደነገጠው ብሩክ አሰብ አደረገና መልክቱ በደረሰው በምኞት ስም በከፈተው የፌስ ቡክ አካውንት "ሚኪ እንደዛ ገፍትረህ የጣልከኝን ሴት እኔን ፍለጋ መቀሌ መምጣትህን በምን ልመን? ብሎ ላከለት። እሱ ከሆነ ችግሩ የኔ ስስት ኦን ላይን ሆነሽ ትንሽ ጠብቂኝ ብሎ ወድያው በአከባቢው ወደ ነበረው ሰመዓታት አውልት በማቅናት አከባቢውን በደንብ በሚያሳይ ሁኔታ እራሱን አስገብቶ እየቀረፀ ቀጥታ ቪድዬ እንድትመለከትና እንድታምነው ለማድረግ ሞከረ ። ብሩክ ቪድዬውን እየተመለከተ እስኪበቃው ከሳቀ ቡሀላ ••• " በል ፈተናውን አልፈኻል እኔ ያለሁት መቀሌ ሳይሆን ጎንደር ነው። የእውነት እየፈለከኝ እንደሆነ ማወቅ ነበረብኝ። የእውነት እምትፈልገኝ እምታፈቅረኝ ከሆነ ጎንደር ና" ብሎ ላከለት ሚኪ ጎንደር የደረሰው ምንም እንቅልፍ የሚባል ነገር ባይኑ ሳይዞር ነበር ። ከጎንደር የመጨረሻ ፈተናውን አልፈሀል አዳማ ና የእውነት ከአዳማ ተያይዘን ነው ወደ አዲስ አበባ የምንሄደው በሚል ሰበብ ወደ አዳማ እንዲመጣ ካደረገው ቡሀላ አዳማ መጥቼለሁ ምኞቴ ብሎ ሲልክ ••• በዛው የምኞት ፌስ ቡክ አካውን ባክህ ነቀምቴ ነኝ ብሎ ሲልክለት እንደእብድ አደረገው እጅጉን የመታከት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ ገባ ብቻውን እያወራ በእግሩ ብዙ ተጓዘ ። እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ምኞት በጤናዋ እያረገችው ነው ብሎ መቀበል አልቻለም። ድንገት አእምሮው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ብቻውን በየመንገዱ ያስለፈልፈው ጀመር ። ከፀቦች ሁሉ ክፉ ወደሆነው ፀብ ውስጥ ከተተው። ከራሱ ጋር ፀብ ፈጠረ ሚኪ አንድ ሰው ሆኖ እያለ በምኞት ጉዳይ ላይ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ሙግት ገጠመ ••• "ይቺ ልጅ እማ እሄን ሁሉ ነገር የምታረገው በጤናዋ አይደለም አብዳለች አልያም እብደት ጀማምሯታል" የሚል አስቀያሚ ሀሳብ ድንገት ሹክ ሲልበት ሳያስበው ጆሮው ላይ ጥይት የተተኮሰበት ያክል ነበር መሀል መንገድ ላይ እርምጃውን በመግታት ደርቆ የቀረው። "ኧረ በፍፁም እሄ የኔ ሀሳብ የወለደው እንጂ እሷ ጤነኛ ነች በማለት ለራሱ ሀሳብ እራሱ ምላሽ ሰጠ" " እስቲ አስበው ተመልሳ የምትገባበት ቤት የለላትን ልጁ በወላጆቿ ሞት በሀዘን የቆሰለው አእምሬዋ ሳያገግም አምጥተህ እዛ ኦና ኮንደሚንየም ውስጥ ስትወረውራት ባታብድ ነበር ሚገርመው አንተ ከሀዲ ነህ ተቀበል! ያለው መሰለው ከዚህ ውስጡ ተፈጥሮ ጎራ ለይቶ ከሚፋጨው ሀሳብ ወዴት ሮጦ እንደሚያመልጠው ግራ ገባው ። ሰው ሲሞግተን፣ ፣ የሚረብሸንን ሀሳብ እያነሳ ሲያስጨንቀን ፣ እንዲህ ሆኖ ቢሆንስ እያለ በስጋት ሲንጠን ሰውየውን እንሸሸው ከሱ ጋር ማውራት እናቆም አልያም እሱ በተገኘበት ቦታ አንገኝ ይሆናል ። ልባችን ህሊናችንና አእምሮአችን በሀሳብ ተከፋፍለው መስማማት ሲሳናቸው በውስጣችን ለሰው የማይሰማ ጦርነትና ጩኸት ሲፈጠር ምን መሸሻ አለን ሰው ከራሱ ወዴት ይሸሻል?ሰው ከራሱ ወዴት ሮጦ ያመልጣል ? ሚኪም መሸሸጊያ ያሳጣው የሀሳብ ማእበል ሲንጠው ከመናጥ ውጪ ማምለጫ አልነበረውም ። ሞባይሉን አወጣና ፌስቡክ ከፍቶ መልዕክት መፃፍ ጀመረ መልክቱን ቀለል አድርጎ ለመጀመር አሰበ•• "ምኞቴ እየተበቀልሽኝ ባልሆነ ከበደሌ አንፃር ምንም ቢደርስብኝ ምንም ብሆን ቅጣቴን ለመቀበል ዝግጁ ብሆንም ይቅርታ የማያጥበው የበደል እድፍ የለምና ይቅርታ ከጠየኩሽ ቡሀላ እሄን ያክል በኔ ላይ የጨከነ ልብ ከየት አገኘሽ ምኛትዬ ? አሁንስ ፈራሁ የምትይኝ እና እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ሌላ ነገር እንዳስብ አደረገኝና ፈራሁ ምኛትዬ። እኔ ምንም ልሁን እሄን ሁሉ ነገር የምታደርጊው በንፁህ እና በጤነኛ አእምሮሽ ከሆነ ይሁን ግድ የለም የኔ ድካም ተኝቼ ስነሳ ይጠፋል ፈጣሪዬን አደራ እምለው በኔ ምክንያት ተኝተሽ ስትነሺ የማይጠፋ የማይተው የአእምሮ በሽታ ጥዬብሽ እንዳይሆን ፈራሁ አምጥቼ ስጥልሽ በደሌን መቋቋም አቅቶሽ ተሸንፈሽ እንዳይሆን ሰጋሁ ምኞትዬ ። ሁሉም ቀርቶብኝ ጤነኛ መሆንሽን ብቻ አረጋግጭልኝ ስስቴ ቀውስሻል እያልኩሽ አይደለም ነብሴ ሰላምና እረፍት እንድታገኝ ደና መሆንሽን ብቻ ንገሪኝ ምንም አልሆንኩም ሰላም ነኝ ግን ላገኝህ አልፈልግም ብቻ በይኝ የኔ ፍቅር እባክሽ!"ብሎ መልዕክት ላከ.... ይቀጥላል https://youtu.be/Bq3JUnFpN24
نمایش همه...

​​😘ምኞት😘 ⚛ክፍል 47 https://youtu.be/Bq3JUnFpN24 ሚኪ ከአዳማ እንደመጣ ወደ ቤቱ ሳይገባ ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ስልኩን አጥፍቶ ሲጠጣ አመሸ ። ከምሽቱ ሶስት ስአት አከባቢ ሞቅ እንዳለው ስልኩን አውጥቶ በመክፈት ፅናት ላይ ደወለ። በብሩክ አማካሪበት በቀየረው አዲሱ ሲም ካርድ ነበርና የደወለው ፅናት አላነሳችውም። "እባክሽ አንሺው ፅናቴ ዛሬ ታስፈልጊኛለሽ እኔ ያንቺው ወንድም ሚኪ ፅናቴ እህቴ ከጎኔ ሆና አይዞህ እንድትለኝ እሻለሁ ከፍቶኛል ፅናቴ ከፍቶኛል! አለም በሙሉ የጠላኝ ይመስለኛል? ቢሆንም አንቺ ምንም ጥሩ ባልሆን እንደማትጨክኝብኝ አውቃለሁ።" ብሎ መልክት ላከላት። ፅናት መልክቱን አንብባ መልሳ ለመደወል ሰከንዶች ብቻ ነበሩ ያስፈለጓት። "ሚኪዬ በህይወት አለህ ግን ቆይ ምን አድርጌህ ነው ይሄን ያክል ቀን ስልክህን አጥፍተህ የጠፋኽብኝ••• አንቺ ደሞ ምን ታጠፊያለሽ ህይወቴ በሙሉ በጥፋት እና በፀፀት የታጠርኩት እኔ ምንም አላጠፋሽም ፅናቴ ግን ልክ ነሽ ጠፍቻለሁ በዚህ ሰአት እንኳን አንቺን ለምን እንደጠፋሁ አስረድቼ የማሳምንበት የተፈጠረውን ነገር አምኜ መቀበል ያቃተኝ ደካማ ሰው ሆኛለሁና ጥዬቄሽ ሳይሆን ድጋፍሽ ብቻ ነው የሚያስፈልገኝ ፅኑዬ ባንቺ ውስጥ የድሮውን ሚኪ ማየት እፈልጋለሁ ሚኪ ጠፍቶብኛል ፅናቴ! ሚኪን አጥቼዋለሁ። ቅጣቴ በዛና የድሮውን ደስተኛ እና ሳቂታዉን ሚኪ አጥፍቶ ሌላ ሰው አደረገኝ ። ይሄንን ሚኪ አላውቀውም ፅናት እህቴ እባክሽ ወደራሴ እንድመለስ እርጅኝ•••" እሺ ሚኪዬ እባክህ ከዚህ በላይ ያንተን ጉዳት የመስማት አቅሙም የለኝም አሁኑኑ እመጣለሁ የት እንዳለህ ንገረኝ!" ሚኪ እና ፅናት ሲያወሩ ጆሮዋን ደቅና ስታዳምጥ የነበረችው ሰራተኛ ስልኳን ወዳስቀመጠችበት ክፍሏ ተንደረደረች። እነፅናት ቤት ውስጥ ካሉት ሶስት ቋሚ ሰራተኛች መሀል አንዷ ስትሆን ብርኬ አጥምዶ በመተዋወቅ በገንዘብ ሀይል የፅኑን እንቅስቃሴ እየተከታተለች መረጃ እንድታቀብለው በገዛ ቤታቸው ቃል አቀባይ አድርጎ የሾማት ተባባሪው ነች። ስልኳን አንስታ ደወለች ። የብርኬ ስልክ በሚጠጣበት ግሮሰሪ ውስጥ ስታቃጭል ድምጿን ግሮሰሪው ውስጥ የተለቀቀው ሙዚቃ ቢውጠውም ብርሃኗን አይቶ አነሳት ••• "ሄሎ አዲስ ነገር አለ እንዴ? በደንብ እንጂ ልትወጣ እየለባበሰችልህ ነው! ወዴት እንደምትሄድ አጣርተሻል? ወደ ሚኪ! ሚኪ! መጣ እንዴ ?ብሎ ጮኸና ብርጭቆው ውስጥ ያለውን ውስኪ ጨለጠው። በምንድን ነው የምትሄደው ግቢ ውስጥ መኪናዋ አለ እንዴ? ምናልባት የጋሽዬን ይዛ ከወጣች እንጂ የሷን ወንድሟ የሱ ገራዥ ስለገባች ይዞባት ወጥቷል።አለችው ቃል አቀባይ የሆነችው የፅናት የቤት ሰራተኛ። " በይ አሁኑኑ ከቻልሽ የመኪናውን ጎማ አተንፍሺው ካልሆነ•••ብቻ እሷ ቶሎ እንዳትወጣ የሆነ ነገር አድርጊ ብሎ መልሼ ደውላለሁ ከስልክሽ እንዳትርቂ ብሎ ስልኩን በመዝጋት እንዴት ሳይነግረኝ መጣ ብሎ እየተብከነከነ ወደ ሚኪ ደወለ።ሚኪ ስልኩ ሲጠራ ገና እንደተመለከተው••• "አቦ ወደዛ ተፋታኝ አንተ ምክረ ደረቅ የሆንክ ሰውዬ እስካሁን ባንተ ምክር ሄጄ የቀናኝ ነገር የለም! አሁን ለምን እንዲህ አታረግም? እንዲህ ማድረግ እኮ አልነበረብህም እያለ ቁስሌን የሚያመረቅዝ ሳይሆን ቁስሌን የሚያክም የሚያድን ሱው ነው ማግኘት የምፈልገው ወደ እራሴ እስክመለስ ተወኝ አትደውልብኝ !" አለ ስልኩን ሳያነሳው በብስጭት እጁን እያወናጨፈ ። ብሩኬ ሚኪ ስልኩን ባለማንሳት በገነ! ተቁነጠነጠ። ወደ ፅናት ስልክ ደወለ ። እሷም አታነሳም። በንዴት እየተወናጨፈ ግሮሰሪው አካባቢ ወዳቆማት መኪናው ገባ። ትንሽ እንደሄደ ወደ ሰራተኛዋ ደወለ••• አነሳች። 'ወጣች እንዴ? ኧረ አልወጣችም። እንዴት እስካሁን ለባብሳ አልጨረሰችም ወይስ እንዳልኩሽ ጎማውን አስተነፈሽላት። እእእ ጋሽዬ ሲገቡ የመኪናውን ቁልፍ የት እንዳስቀመጡት አይቼ ስለነበር አንስቼ የወደቀ እንዲመስል ወደ አንድ ጥግ አሽቀነጠርኩላት። ይኸው ቤት ውስጥ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች እየተመነቃቀረች በመፈልግ ላይ ነች። አይ አንቺ ስማርት (smart) እኮ ነሽ ። በቃ ቀረብ ስል ሚስኮል አረግልሻለሁ ያኔ ቁልፉን አገኘሁልሽ ብለሽ ትሰጫታለሽ ሌላው ደግሞ ባለፈው የተነጋገርነውን እቅድ ሁለትን ነገ እንጀምራለን ምን ማረግ እንዳለብሽ የነገርኩሽን አረሳሽውም አደል? አረሳሁትም። እስቲ ንገሪኝ? እንዴ የሱ ምኞት የላከችለት ደብዳቤ ላይ ሊያገኛት የሚችልበትን ስልክ አስቀምጣ እንደነበር ብሩኬ ስለማይመቸው ደብዳቤውን ላንተ እንድትሰጥህ ለፅናት ሲሰጣት ስልኩ የተፃፈበትን ሌላኛውን ገፅ በማውጣት አጣሁት እራስህ ስጠው ብላ ለብሩኬ እንደምትመልስለት ከወንድሟ ስትማከር መስማቴን ። ከዛ ምኞት ጋር ደውለው ስራ እናስገባሽ ብለው በወንድሟ ሀሳብ አመንጪነት ፅናትና እና ወንድሟ አንድ ክፍል ውስጥ አግተው እንዳስቀመጧት ምግብ የማደርስላት እኔ እንደሆንኩና ታሪኳን ስታጫውተኝ አሳዝናኝ ለሱ እንደደወልኩለት የዚህ ሴራ ዋና ተግባሪ የፅናት ወንድም እንደሆነ ከነገርከኝ ታሪክ እያጣቀስኩ እግተዋለው" በቃ የኔ ቆንጆ ነብሴን አስደሰትሻት በቃ አሁን ትንሽ ቆይቼ ሚስኮል ሳረግ ቁልፉን ስጫት።ካካካካ። ቻው ቻው።" እነፅናት ሰፈር ደርሶ የመኪናውን መብራት አጠፋፍቶ አንድ ጥግ አቆመና ለሰራተኛዋ ሚስ ኮል አደረገላት። ወድያው ቀልፉን አገኘሁት ብላ ስትሰጣት ከእጇ ላይ መንትፋ ሮጠች ። በሰከንዶች ውስጥ የነፅናት የውጪ በር ወደ ጎን ተንሸራቶ ተበረገደ። የአባቷን ቪ ስምንት(V-8) መኪና ከግቢ ይዛ በመውጣት ቁልቁል ተፈተለከች። ብሩኬ የያዛትን ቪትስ(vitz) አስነስቶ የፅኑን መኪና እንድትከተል ሲያስጨንቃት ሳቋ መጣባት ሲበዛባት ተናደደች የምታወጣው ድምፅ ያቅሜን እየሄድኩ ነው እንግዲህ ከዚህ በላይ ልፈንዳልህ እንዴ? የሚል መልክት ያዘለ ይመስላል። በቅርብ ርቀት እንዳይከተላት በመሀል እየገቡ እንቅፋት የሚሆኑበትን እየተሳደበ እሱም እየተሰደበ ስቴድየም አከባቢ ሲደርሱ በሱና በፅናት መኪና መካከል ከአራት ያላነሱ መኪናዎች አሉ። ቀና ብሎ ከፊት ለፊቱ ያለውን የትራፊክ መብራት ደቂቃ ሲመለከተው ቆሌው ተገፈፈ። የትራፊክ መብራቱ ፅናትን ካሳለፈ ቡኻላ እሱን ካስቆመው ፅናት ልታመልጠው ነው። ያ ከሆነ ደግሞ ምን ያኽል እንደሚበሳጭና ምን አይነት አዳር እንደሚያድር ያውቀዋል። አይሆንም•••ይሄንም እያለ እየቶሽለከለከ ከአቅማ በላይ ጋለባት ፅኑ የትራፊክ መብራቱን አለፈች ። ከፅኑ ጀርባ ያለው ሌላኛው መኪና እንዳለፈ ደቂቃው አበቃ። ቀዩ መብራት ቦግ አለ። ከብሩክ ፊት የነበረው መኪና ለማለፍ ከነበረው ፍጥነት ባንዴ ሲጢጢጢ አርጎ ፍሬን በመያዝ ቀጥ አለ። ብሩኬ ከዋላ መጥቶ ተላተመ። በአከባቢው የነበሩ እግረኞች እየጮሁ ወደ ብሩኬ መኪና ተሯሯጡ። ከጀርባዋ ምን እንደተፈጠረ ያላወቀችው ፅናት ለሚኪ ለመድረስ ከአከባቢው ተሰወረች.......... ይቀጥላል.... https://youtu.be/Bq3JUnFpN24
نمایش همه...

​​😘ምኞት😘 💟ክፍል 49 https://youtu.be/Bq3JUnFpN24 "ምኞትዬ" ወዬ መስ ምነው ? "ሚኪ እንደው ምናልባት ባንቺ ላይ ያደረገው ነገር ስተት እንደነበር ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ይቅርታውን ተቀብለሽ ታርቀሽው አብረሽው ትኖሪያለሽ?••• አይጠይቀኝም! ምክንያቱም ይቅርታ የሚጠይቀውን ስህተትን ተሳስቶ የፈፀመ ብቻ ነው። ሚኪ ደሞ ለሱ ትክክል የሆነውን ነገር አስቦና ወስኖ ስላደረገ በምን ምክንያት ?ዛሬ ምን ተገኝቶ ይቅርታ ይጠይቀኛል! መልሷ ያልተዋጠለት መሳይ " ምኞትዬ ሰው በመጀመሪያ ለራሱ ትክክል ነው ስህተት መፈፀሙን የሚያምነው ስህተት እንደነበር መቀበል ሲፈልግ አልያም ስህተት እንደነበር ሲረዳ ነው ። ትናንት ትክክል መስሎን የሰራነው ወይም የወሰነው ውሳኔ ከቆይታ ቡሀላ ትክክል እንድዳልነበርን ሲገለጥልን ከአንዳንዶቻችን በስተቀር ስተት እንደሰራን ከተረዳንበት ቅፅበት አንስቶ የህሊና እረፍት እናጣለን ስህተቱን ወደ ዃላ ሄደን ማስተካከል ባይሆነልንም በኛ ስህተት የተጎዳ ሰው ካለ ያንን ሰው አግኝተን ይቅርታ እስከምንጠይቀው እንቅልፍ የማይወስደን ብዙዎች ነን!" አላትና ምላሿን መጠባበቅ ጀመረ•••ብታድያ ዛሬ ላይ ትክክል እንዳልነበረ ገብቶት የሚጠይቀኝ ይቅርታ ትክክል እንዳልነበረ ማመኑን እንጂ ታርቆኝ ከኔ ጋር አብሮ የመኖር ፍላጎት እንዳለው አያመለክትም እኮ። አየህ መስዬ የጥፋተኝነት ስሜት እና አብሮ የመሆን ፍላጎት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ለዚህ ነው አንዳንድ ፍቅረኛሞች ሀምሳ ግዜ እየተጣሉ ሀምሳ ግዜ ይቅርታ እየተባባሉ የሚታረቁት። ይቅርታ አብዛኛውን ግዜ ያለፈን ስህተት የማመን ጉዳይ እንጂ መጪውን ህይወት ለማቅናት በፍቅር እና በደስታ ተሳስቦ ለመኖር የመወሰን ወይም የመለወጥ ጉዳይን ያካተተ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ይቅርታዎች ስላለፈው ጉዳይ እንጂ ስለመጪው ህይወት የመወሰን አቅማቸው ምንም ነው። ያንን የመወሰን ሙሉ አቅም ያለው እውነተኛ ፍቅር ብቻ ነው ስለዚህ ሚኪ እኔ ላይ የፈፀመው በደል አላስቀምጥ ሲለው ከህሊና ወቀሳ ለመዳን ይቅርታ ጠየቀኝ ማለት ከኔ ጋር ታርቆ ደስተኛ አርጎኝ ለመኖር የሚያስችል ፍቅር በውስጡ መኖሩን አረጋገጠልኝ ማለት አይደለም። አለችው። መሳይ ምኞት ለነገሮች ያላት ጠለቅ ያለ ምልከታ ከገመተው በላይ ሆነበትና ታድያ ምን ብሎ ቢጠይቃት ነው ይቅርታው በፍቅር አብሮ የመኖር ዋስትናንም የሚያካትተው እያለ ሲያሰላስል••• እሱ ዝም በማለቱ ምኞት ግዜ አገኘች። እሷም በተራዋ የመልስ ምት የሚሆን ሚሳኤል የሆነ ጥያቄ ወደ መሳይ አስወነጨፈች••• ናርዶስ ጥላህ ለመጥፋቷ በቂ ምክንያት ይዛ ዛሬ ብትመጣ ይቅር ብለሀት አብረህ ለመኖር የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግኻል?መስዬ? አለችው••• በመሳይ በኩል ትንፋሽ ጠፋ። ይኸውልህ መስዬ መልሱን ስለማውቀው አትንገረኝ እስካሁን እየሆነ ያለው ነገር እኔ ወይም አንተ ቀድመን ያቀድነው ሳይሆን መሆን ያለበት ነው እየሆነ ያለው ስለዚህ መሆን ያለበትን ነገር ለነገ እንተወው። ኑሮ ወይም ህይወትን በእቅድ ለመምራት ይቻል ይሆናል ፍቅርን ግን በእቅድና ቀድሞ በተናገረው መንገድ የመራ ሰው የለም ፍቅር ስሜት ነውና በእቅድ አይመራም ። እኔ አንተን ከሚኪ ፍቅር መሸሸግያ ላደርግህ አልፈልግም! አንተም የናርዶስን ፍቅር በኔ ውስጥ እንድትደበቀው አልፈልግም። ግን እኮ እኔ እየወደድኩሽ ነው ምኞቴ? አላት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ። ግን መቸኮል የለብንማ መስዬ!! ውስጣችን ማለት የኔም ያንተም ልብ ያልደመሰሰው ፍቅር አለ። ግኑኝነታችን የእውነት እንዲሆን አሁን ባለንበት ከነገሮች ነፃ በሆነ እና መተሳሰብ በሞላበት ፍቅራችን ትንሽ እንቆይ ግን መስዬ እንዳትናደድብኝ! ካንተ የተደበቀ ምክንያት ኖሮኝ ሳይሆን ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው እባክህን ግዜ ስጠኝ ! አለችው። ላንቺ ያለኝን ሁሉንም ስሜት አልነግርሽም አንቺ ዝግጁ እስከምትሆኚ ብቻዬን አጣጥመዋለሁ ። እንዳልሽውም አንዱን ስሜት ለመሸሽ ዘለን ገብተን ዘለን የምንወጣበት የወረት ፍቅር እንዲሆን እኔም አልፈልግም። ነገር ግን የኔ ብትሆኝም ባትሆኝም እንደነብሴ ከምወዳት ታናሽ እህቴ ከራሴ አስቀድሜ የማይሽ! ተጎድቼ ባስደስትሽ ቅር የማይለኝ! በስስት እና በናፍቆት የምጠብቅሽ ዳግም ለመኖሬ ምክንያት እንድትሆኚ መርጦ የላከሽ የፈጣሪ ስጦታዬ እንደሆንሽ እወቂ! ብሏት ቀና ሲል የሱ ብቻ ሳይሆኑ የሷም አይኖች በእምባ መሞላታቸውን አስተዋለ ተያዩ እንባ ባጠለሉ አይኖቻችው ዝም ብለው ተያዩ " ግን አሁንም የመጀመሪያው ጥያቄዬ አልተመለሰልኝም አጠር አድርገሽ እንድትመልሽልኝ ጥያቄዬን አስተካክዬ በድጋሚ እጠይቅሻለሁ•• ሚኪ ካንቺ ጋር በፍቅር ለመኖር ፍላጎት እንዳለው አረጋግጦ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ትቀበይዋለሽ?ምላሽሽ ምን ይሆናል? መልሼልሀለሁ። አለችው። አልመለሽልኝም ምኞቴ አላት። አቦ ተወኛ አንተ ደረቅ የሆንክ ነገር አለችው። ተሳሳቁ እንባ ካዘሉ አይኖች ስር የፈለቀ ንፁህ የፍቅር ሳቅ። ተነስቶ እንባዋን ጠረገና ጉንጯን ሳማት ። ተያይዘው ጎን ለጎን ወደያዟቸው ክፍሎች አመሩ። ሁለቱም ቁልፎቻቸውን እበሩ ቀዳዳ ውስጥ አስገብተው በሩን ከመክፈታቸው በፊት ተያዩ ። ደና እደር መስ። አለችው። ደና እደሪ ምኞቴ አላት ቁልፉን ዘወሩት። በሩን ከፍተው ከመግባታቸውበፊት በድጋሚ "ደና እደሪ መልካም እንቅልፍ አላት። አሜን ብላው ወደ ክፍሏ ገባች። ትንሽ ቆመና እሱም ወደ ክፍሉ ገባ ። አንቺ ትችይ ይሆናል እኔ ግን አልችልም ምኞት አለ አልጋው ላይ ተደፍቶ። መሳይ በቀላሉ ፍቅር የሚያጠቃው አይነት ሰው ነው ምኞት በዚች አጭር ግዜ ውስጥ ውስጡ ገብታ ልትነግስ ተደላድላ ለመቀመጥ የሚሆናትን የልቡን ዙፋን ለመቆጣጠር ልቡ ላይ ተሰንቅራ የቆየችውን ናርዶስን ጠራርጋ ለማስወጣት ናርዶስ በመሳይ ልብ ለመንገሷ ፣ ለመፈቀራ ፣ በናርዶስ ለመሸነፉ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙሉ በተሻለ ኹኔታ እየተካቻቸው መኾኑን ሲረዳ ልቡ ፈራ። " ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው" ያለችው ነገር ደጋግሞ ያቃጭልበታል እኔኮ ተጥጄ በፍቅርሽ መሞቅ ጀምሬአለሁ ምኞቴ ! አለ ጮክ ብሎ ምኞት አጠገቡ የለችምና አልሰማችውም። ምኞትን አዲስ አበባ ይዟት መመለስ ፈራ ወዴት ወስጄ ልደብቅሽ ወዴት ይዤሽ ልሽሽ ምኞቴ ?ይዘሀት ጥፋ ጥፋ አለው ከዛ በፊት ግን ነገውኑ ምኞትን እዛው ሀዋሳ እንድትሆን በማድረግ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የሚኪን ሁኔታ ማጣራት ። ሚኪን አጋጣሚ እንዳገኘው መስሎ አግኝቶት ስሜቱን መረዳት ፈለገ ። በዚህ ሁኔታ እዚህ መቆየት አልፈልግም ነገውኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሼ ሚኪን አገኘዋለሁ አለ... የመጨረሻው ክፍል 500 ላይክ ከሞላ አውን ይለቀቃል
نمایش همه...

​​​😘ምኞት😘 💟ክፍል 46😘😘 እኔ.....በአንቺ ምክንያት የዳንኩት መሳይ ነኝ አንቺ ማነሽ? ሲላት ያየችው እና የሰማችው ነገር በህልሟ እንጂ እሷ ለወራት በኖረችበት በተረሳው በዛ ኮንደሚንየም እቃ ቤት ውስጥ ከተኛችበት ፍራሽ አጠገብ የተቀመጠው እብዱ መሳይ መሆኑን ማመን ተሳናት በማይክሮ ሰከንዶች ውስጥ ጭንቅላቷ ውስጥ ብዙ ጥያቄዋች ተፈጠሩባት። በፍርሀት ቀና ለማለት አቅም ብታጣም እንደምንም በጀርባዋ ከተንጋለለችበት ፍራሽ ቀና ብላ ግድግዳውን ተጠግታ በመቀመጥ በፍርሀት እና በዝምታ የመሳይን አይኖች ስትመለከት••• "አይዞሽ አትደንግጪ አትፍሪኝም እኔ አንቺን የሚጎዳ እጅም ልብም የለኝም። የዳንኩት ለዚህ የበቃሁትኮ ባንቺ ነው። አንቺ በህልሜ የምትመጭዋ የኔዋ ናርዶስ እንዳልሆንሽ የገባኝ ያንቀን ከዚህ አባቴ እና እህቴ በግዱ ይዘውኝ የኼዱ እለት ለሊት ነው። ያን ቀን ለሊት ናርዶስ ጥላኝ ከመሄዷ ከቀናት በፊት ለብሳው የነበረውን የምወድላትን ልብሷን ለብሳው መጣች። ስትመጣ ደስ አለኝ ግን ወድያው ደስታዬ ወደ ሀዘንና ወደ ጭንቀት ተቀየረ ምክንያቱም ያቺ ናርዶስ አንቺ ያስለመድሽኝን ነገር ሳታደርልኝ ተመልሳ መሄድ ጀመረች ። እንዳንቺ መድሀኒቴን አላዋጠችኝም፣ እንዳንቺ ፀጉሬን እየደባበሰች አላስተኛችኝም። እንደልማዷ የማትያዝ የማትጨበጥ መንፈስ ሆና ስታሰቃየኝ ቆይታ ልትሄድ ስትነሳ እባክሽ መድሀኒቴን ሳታውጪኝ አትሂጅብኝ እባክሽ! እያልኩ ስጮህ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ያኔ ሁሉም ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እዚህ እያለሁ ናርዶስ የመሰለችኝ ከዚችኛዋ ጋር አንድ ይሁኑ ይለያዩ ተምታታብኝ። ወደ ቀልቤ ለመመለስ ሞከርኩና ሳሰላስል አንቺና የኔዋ ናርዶስ ብትመሳሰሉም አንድ አይነት ወይም አንድ ሴት ሳትሆኑ ሁለት የተለያያችሁ ሴቶች መሆናችሁ ገባኝ። ይሄ ሲገባኝ ሌላ ግራ የሚያጋባኝ ጥያቄ ውስጤ ተነሳ እዛ ኮንደሚንየም ማታ ማታ የምትመጣውና ናርዶስን ስትመስለኝ የቆየችው ሴት ማነች? እዚስ ምን ትሰራለች ? ጭንቅላቴ ጋለ። ለዚህ ጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ ለደቂቃዎች ስቆይ ተለወጥኩ ማንም መውጣቴን ሳያውቅ በዛ ፅልመት ባልገፈፈለት ውድቅት ለሊት ከግቢ ወጥቼ እግሬ ወደመራኝ መጓዝ ጀመርኩ። ከአዲስ አበባ ወጣሁ በደብረብርሀን መስመር ዋናውን አስፖልት ይዤ መጓዜን የማውቀው ነገር አልነበረም ነበር ። ለስምንት ሰዓታት ያክል ከተጓዝኩ ቡሀላ ወደ እመቤታችን ወደ "ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት" ፀበል በቤት መኪናቸው ሲጓዙ የነበሩ የቤተሰብ አባላት ከዋላኣ ሲመለከቱኝ አረማመዴ መድከሜን አሳወቃቸው መሰል ••• አጠገቤ እንደደረሱ መኪናውን በማቆም ወዴት እንደምሄድ ጠይቀውኝ መልሴን ሳይጠብቁ እነሱ ወደ ሰሚነሽ ማርያም ፀበል እየኼዱ እንደሆነና ወደዛው ከሆንኩ አብሪያቸው መሄድ እንደምችል ሲነግሩኝ ጥሪው የሷ ነበርና አዎ ወደዛው ነው የምሄደው ከማለት ውጪ ሌላ ነገር ከአንደበቴ ማውጣት አልቻልኩም። ይሄን እንዳልኩ የመኪናውን በር ከፈቱልኝ አብሪያቸው ሄድኩ ሲጠመቁ ተጠመኩ የመኪናው ብቻ ሳይሆን የተዘጋው የጭንቅላቴ በርም ተከፈተ። አባቴ እዚህ ቤት አምጥቶ የጣለኝ ልበጎ መሆኑን ያወኩት እዛ ለሶስት ቀን ብቻ ቆይቼ የድሮውን መሳይ ሳገኘው ነው። ሁሉም ነገር ተቀይሮ የድሮውን መሳይ ብሆንም ኖርዶሴን ማፍቀሬ እና መናፈቄ ግን ዛሬም ህያው ነው። ጨርቁን ጥሎ የለየለት እብድ ስላልነበርኩ ያለፈው ነገር በከፊልም ቢሆን ትዝ ይለኛል። አንቺ ትዝ አልሽኝ በናርዶስ ቅዥት ከእንቅልፌ ስነቃ ስላንቺ ለተፈጠረብኝ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከሰዎቹ ጋር አብሬ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለስኩ ወደቤት ሳልሄድ ቀጥታ ወደዚህ መጣሁ አዝነሽ እንድታስገቢኝ እብዱን መሳይ መምሰል እንዳለብኝ አሰብኩ። ስመጣ በሩ ዝግ የሆነው እቤት ስላልሆንሽ መስሎኝ እስክትመጪ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ስጠባበቅ በመሀል ሽንት ቤት ገብተሽ ስትወጪ ስለሰማሁ ውስጥ እንደሆንሽ ተረዳሁ። አንቺን የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ። መስኮትሽ ስር ሆኜ እንደ እብድ መለፍለፍ ጀመርኩ። የጠበኩት ሆነ። በሩን ከፈትሽልኝ። ገባሁ ።እብዱን መሳይ እንደመሰልኩ ማንነትሽን ለማጣራት ብሞክርም አልቻልኩም ምክንያቱም••• - ከማንም ጋር አታወሪም፣ከማንም ጋር አትደዋወይም፣ቀኑን ሙሉ በተዘጋ ቤት ሊያውም በቤቱ አንድ ቆሻሻ ክፍል ውስጥ ነው እምትውይው፣ እኔን ካስተኛሽኝ ቡሀላ ስታለቅሺ ሰምቼሻለሁ። እንቅልፍ አጣሁ። በለሊት ተነስቼ እዚህ ክፍል በመግባት እስክትነቂ መጠባበቅ ጀመርኩ። እባክሽ ድጋሚ ከማበዴ በፊት ማን እንደሆንሽና ለምን በዚህ እድሜሽ እሄን የመሰለ ውበት ይዘሽ እዚህ ቤት ውስጥ ሊያውም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንድደምትኖሪ ንገሪኝ እባክሽ?" ከምኞት አይኖች የሚረግፈው እንባ ማቆሚያ አልነበረውም ታሪኳን በአጭሩና በሚያሳዝን ሁኔታ ነገረችው። "አይዞሽ ሁሉም አልፋል አሸንፈነዋል ከእንግዲህ ምንም ችግር አታይም ከጎንሽ ነኝ!" እያለ እንባዋን ከጉንጮቿ እየጠረገ የሱ ጉንጮች በእንባ ራሱ። ከዚህ ቤት ዛሬውኑ ይዤሽ እወጣለሁ ቤት እከራይልሻለሁ እቤት ደርሼ እስክመጣ ጠብቂኝ ብሏት ከወጣ ቡሀላ ሲመለስ የሚያጣት የምትጠፋበት መሰለውና ፈራ። ተመለሰ።" ፈራሁ አንቺም እንደናርዶሴ ጥለሽኝ የምትጠፊ መሰለኝ እባክሽ አብረን እንሂድ ሲላት ስሜቱ ከባድ ነበርና ሁለቱንም በእንባ አራጫቸው ተያይዘው አነቡ ።ተቃቅፈው አለቀሱ። እንደምትጠብቀው በእናቷ ስም ቃል ገብታለት ወደቤት ኼዶ ተመልሳሶ ሲመጣ ስላገኛት ደስታው ወደር አልነበረውም። መኪና ይዞ ነበርና የመጣው "ከእንግዲህ ወደዚህ ሲኦል ወደ ሆነ ቤት አትመለሽም በጣም የሚያስፈልጉሽን ያዢ ። አላት። ዳግም ላይመለሱ ከዛ ኮንደሚንየም ተያይዘው ወጡ ። " ጥሩ ቤት እንዲፈልግልኝ ላንድ በቅርብ ለማውቀው ደላላ ነግሬዋለሁ እስከዛው ላንድ ሶስት ቀን ከከተማ ወጣ ብለን እንቆያለን አላት። መስማማቷን ፈገግታ ባደመቀው ፍቷ ገለጠችለት። ከመሄዳቸው በፊት ወደ አንድ ዘመናዊ የሴቶች ልብስ መሸጫ ጎራ ብለው በምርጫዋ ሻንጣ ሙሉ ልብስ ገዛላት ። ምኞት ደመቀች ።ልክ እንደፅጌሬዳ ዳግም አበበች ። ያ የድሮው ውብ ማንነቷ የተመለሰ መሰላት ። መሳይ እየነዳ ምኞት አጠገቡ ጋቢና ውስጥ ተቀምጣ ፈንዲሻ እየበላች ወደ ሀዋሳ ነጎዱ......... ይቀጥላል.... https://youtu.be/Bq3JUnFpN24
نمایش همه...

​​😘ምኞት😘 🔰ክፍል 45🍃🥀 ምኞት ከዋሌቱ ያወጣችውን ፎቶ ወደ ዋሌቱ መልሳ ከመሳይ እጅ ላይ የወሰደቻትን የናርዶስን ጉርድ ፎቶ ደግሞ ከተኛው መሳይ አጠገብ እዛው ፍራሹ ላይ አስቀምጣለት ወደ መደበቂያዋ ወደ እቃ ቤቷ በመግባት መሳይ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ሰርታ ለመጨረስ ስለፈለገች ምግቧን ቶሎ ቶሎ መስራት ጀመረች። ከቀኑ 11:30 ሆኗል ። መሳይ ግን እስካሁን አልነቃም። "እሄ ልጅ ግን በሰላም ነው ሀይ ምነው እንቅልፍ አበዛ?"አለች መሳይ ሳይነቃ ረዘም ላለ ሰአት በመተኛቱ ሀሳብ ገብቷት። ስለሱ እያሰበች ጋደም ባለችበት እሷንም እንቅልፍ ይዟት ሄደ። ማታ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ቡሀላ ዙርያ ገባው ፀጥታ እየሰፈነበት ሲመጣ የመሳይና የራድዮኑ ድምፅ ይበልጥ ጎልቶ መሰማት ስለጀመረ ምኞትን ከእንቅልፏ ቀሰቀሳት። ተነስታ ቁጭ አለችና የመሳይን ወሬ ማዳመጥ ጀመረች። መሳይ አጠገቡ ያለ ከሚመስለውና ለሱ ብቻ ከሚታየው መንፈስ ጋር ናርዶስ ዛሬ ትመጣለች አትመጣም በሚል ሞቅ ያለ ክርክር ውስጥ ነው። አሳዝኗት ተነስታ የዕቃቤቱን በር በቀስታ ከፈተችና በድፍረት ቀጥ ብላ መሳይ ወዳለበት አመራች። መሳይ ልክ እንዳያት ወደ ጎን ዘወር አለና " አየኻት የኔን ንግስት አንተ ግልፍጥ ትመጣለች አላልኩህም "አለው።መጠጋት ብትፈራም ሁኔታው እና ስፍስፍ ማለቱ ምኞትን በሱ ላይ ለመጨከን አቅም አሳጥቷታል ። ትንሽ አጨዋውታው መዳኒቱን ካዋጠችው ቡሀላ እስኪተኛ አብራው ቆየችና ሲተኛ ገብታ ያቋረጠችውን እንቅልፍ ቀጠለች። የመሳይ እህት ትንቢት እና አባቷ በጥዋት ነበር መሳይ እና ምኞት ሳይወዱ ሳይፈቅዱ ወደተጣሉበት ኮንደሚንየም የመጡት። አንድ ሌላ ሰው አብሯቸው አለ። በሩን ከፍተው ሲገቡ ምኞት በርግጋ ተነሳች ። ትንቢት ወንድሟ መሳይን ልትቀሰቅሰው ወደተኛበት ስትጠጋ አባቷ " እንዳይረብሸን በተኛበት ብትወጋው አይሻልም ዶክተር?" አለ አጠገቡ ወደ አለው ሰው እየተመለከተ። አባ! እንደዛማ አይሆንም ።አይረብሽም። ቆይ ልቀስቅሰ። አለችና ዶክተሩ መሳይ በተኛበት እንዲወጋው ስላልፈለገች በፍጥነት ትከሻውን ይዛ እያወዛወዘች ቀሰቀሰችው። መሳይ ከእንቅልፉ እንደነቃ ቀና ብሎ ተቀመጠና ሶስቱንም በየተራ ተመለክቷቸው ••• "ወደዛ ኖርዶስ ወደ ሌለችበት ኦና ቤታችሁ ልትወስዱኝ ከሆነ የመጣችሁት አልሄድም! ተውኝ በቃ! እህቴ ይዘሻቸው ውጪ!እዚህ እኮ ናርዶስ ትመጣለች ማታም መጥታ ነበር። ዛሬም እንደምትመጣ ነግራኛለች። ሂዱ እዛ አስቀያሚ ቤታችሁ ውስጥ እናንተው ኑሩበት ። ፍቅር የሌለበት ቤት ውስጥ መኖር አልፈልግም! ፍቅሬ ዛሬ ማታ ትመጣለች መጥታ እንዳታጣኝ ይዘሽልኝ ውጪ እህት አለም•••እያለ ሲጮህ ዶክተሩ ጠጋ ብሎ መርፌውን ክንድ ላይ ወጋው። መሳይም ዝም አለ። ምኞት አንጀቷ ተንሰፈሰፈ ቆማ ማዳመጥ አቃታት። ሁለት እጆቿን ሆዷ ላይ አነባብራ እግሮቿ ላይ ቁጢጥ ለማለት ስታጎነብስ አይኖቿ ላይ የተንጠለጠሉት የእንባ ዘለላዎች ቁልቁል እየተወረወሩ ወለሉ ላይ ሲበተኑ አየቻቸው። እባትየው ከተወጋ ቡሀላ የተዝለፈለፈውን መሳይ ደገፍ አድርጎ ይዞት ሲወጣ ትንቢትና ዶክተር ተብየው ከውዃላ ተከተሉት። ቤቱ ጭር አለ ምኞት ሌላ አዲስ የብቸኝነት ስሜት ወረራት ።ቤቱ አስጠላት። ለሶስት ቀን በድብርት ውስጥ ሆና ነበር ያሳለፈችው ልክ በአራተኛው ቀን ቀኑን ሙሉ ስትተኛ ውላ ስትነቃ መሽቷል ዝናቡ ችፍ ችፍ ይላል ። ከቆይታ ቡሀላ ዝናቡ ለቀቅ እንዳደረገው ከኮንደሚንየሙ በረንዳ ላይ የሆነ የታፈነና የሚልጎመጎም የሰው ድምፅ የሰማች መሰላት። መጀመርያ ጆሬዬ ነው ባላ አለፈችው። እየቆየ እየቆየ ሲደጋገም ግን ፍርሀት ወረራት። በረንዳው ላይ ካለው ከዎናው የመብራት ቆጣሪ በተጨማሪ እሳ ክፍል ውስጥ ባለው የመብራት መቆጣጠሪያ (ብሬከር) የቤቱን መብራት በሙሉ ተራ በተራ ቃ፣ቃ፣ቃ እያደረገች አጠፋችው። የቤቱ መብራት መጥፋቱን ያስተዋለው በረንዳ ላይ የተቀመጠው ሰው••• " ናርዶስዬ ሳትመጣ መብራቱን አጠፉት እንኳን ደስ አለህ !" በማለት ሲጮህ መሳይ መሆኑን አወቀች። እራሱ ነው ! ጠፍቶ መሆን አለበት የመጣው! ግን እንዴት አወቀው ቤቱን? እያለች መብራቱን ሳታበራ ሻማ ለኩሳ ሳሎን መሀል ላይ አደረገችና በሩን ከፍታለት ከበሩ ጀርባ ቆመች ። ልክ ነበረች ።መሳይ ነው። በሩ መከፈቱን ሲሰማ ብድግ ብሎ ዝናብ ባበሰበሰው ልብሱ ውስጥ በብርድ እየተንቀጠቀጠ ሳሎን ውስጥ ወዳለው ፍራሽ ሲያመራ ከጀርባ በሻማው ብርሀን እያየችው ነበር። መሳይ ጠፍቶ ነበር የመጣው ስለዚህ የት እንዳለ የማታውቀው እህቱ ትንቢት ምግብ ይዛለት ልትመጣ አትችልም ። ምኞት ቀን በጭራሽ አትታየውም። እሱም ቀን ቀን ትመጣለች ብሎ አይጠብቅም። ማታ ማታ አብራው ታመሻለች ሲተኛ ከሰራችው ምግብ ላይ ነገ ቀን የሚበላውን አጠገቡ አስቀምጣለት ወደ መደበቂያ ክፍሏ ገብታ ትትኛለች። ከቀናቶች ቡሀላ ምኞት እንደልማዷ መሳይን እስኪተኛ እንደናርዶስ ሆና አውርታው ሲተኛ ነገ ሲነቃ የሚበላውን ምግብ አጠገቡ አስቀምጣለት ወደ ክፍሏ ገብታ ተኛች። ጠዋት ስትነቃ ግን እንደሁሌው በዛች መደበቂያ እቃ ቤቷ ውስጥ ብቻዋን አልነበረችም። ፍራሿ አጠገብ ተቀምጦ ቁልቁል ሲመለከታት እንዳየችው በተኛችበት ውሃ ሆነች። "እኔ •••እኔ•••እኔ ባንቺ ምክንያት የዳንኩት መሳይ ነኝ። አንቺ ማነሽ ?!" አላት... ይቀጥላል... https://youtu.be/Bq3JUnFpN24 5ክፍሎች ብቻ ነው የቀረን ❤️እንቀጥላለን Share ያድርጉ
نمایش همه...

​😘ምኞት😘 👁ክፍል 37🙇 ከአሁን ከአሁን ዘሎ አነቀኝ ብላ ባለችበት ደርቃ ቀረች። እንኳንስ መሳይ የለየለት ጤነኛውም ቢሆን መብራት ጠፍቶ ሲመጣ ድንገት ብቻውን የነበረበት ቤት ውስጥ አንድ ቆንጆ ሴት ሳሎን መሀል ላይ ተገትራ ቢያጋጥመው ደንግጦ ወደ የሚያምንበት አቤት ማለቱ የማይቀር ነው። ሳሎን መሀል ላይ አንደ እንጨት ደርቃ የቆመችውን ምኞት ሲመለከታት ሁሌም በህልሙም በእውኑም በሀሳብም በአካልም እየመጣች የምታሰቃየው ጥላው የሄደችው ፍቅረኛው ዛሬም ስለመምጣቷ ባይጠራጠርም ከተወሰነ ነገር ውጪ የመልኳ መቀያየር ግራ ያጋባው ይመስላል። ምኞት አሁን ላይ መልኳም ሰውነታም እንደበፊቱ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ እንደነበረው አይደለም እጅግ ተለውጣለች መብላት መተኛቱ ከአዲስ አበባ ቅዝቃዜ ጋር ተስማምቷታል የበፊቱ አስደናቂ ውበቷ ቀስ በቀስ መመለስ ጀምራል። አንድ እለት በመስታወት ፊቷን እያየች ከዛ ከደርጉ አውሬ ጋር ከመኖር የማይሻል የለም አሁን ይሄም ኑሮ ሆኖ ነው መልኬ የተመለሰው ይገርማል አለች ለራሷ እራሷን ፈገግ ብላ በመስታወት ውስጥ እያየችው። ዛሬ ደሞ እብዱ መሳይ ፊት ተገትራ አይን አይኑን ታየዋለች " መብራቱ ዛሬ እኔን ሊያዋርድ ካልሆነ በቀር እስቲ ጠፍቶ ሳያድር መጥቶ ያውቃል ይገርማል"።ትላለች አይኗን ከመሳይ ላይ ሳትነቅል። ፍቅረኛው እንደልማዷ ልታሰቃየው እንደመጣች ቢገምትም።ለደቂቃዎች ግራ በመጋባት ስሜት ሲመለከታት ከቆየ ቡሀላ ከተቀመጠበት ብድግ ሲል የምኞት የልብ ምት እጥፍ ሆነ። ቅፅበታዊ የማምለጫ ሀሳብ ብልጭታዎች በየተራና ከብርሀን በፈጠነ ፍጥነት አእምሮዋ ውስጥ ይሰገሰጉ ጀመር። "እሩጭ በሩን ከፈችና ብን ብለሽ አምልጭ። "ወደ ውጪ ከመሮጥ እቃ ቤት ገብተሽ ብዘጊ ይሻልሻል። የትም ብትገቢ ተከትሎ ያንቅሻል። ወይኔ ጉዴ ያንን ቻይናዊ ማጅራቱን ብላ የጣለችበትን ዱላ የት እንዳለ ለማስታወስ ሞከረች። ውይ ምኞት ሞኝ ነሽ እብዶች እኮ ባላቸው ጉልበት ላይ እላያቸው ላይ የሰፈረው የጋኔኑ ወይም የሰይጣኑም ጉልበት ስለሚጨመርላቸው ብትመችውም ተነስቶ ለማነቅ ጉልበት አያጣም። ምኞት አእምሮዋ ውስጥ ቶሎ ቶሎ የሚቀያየሩት ፍርሀት የወለዳቸው ሀሳቦች ፍርሀቷን ከነበረበት እጥፍ አደረጉት ጉልበቷ ተብረከረከ። ያሰበችውን አንዱንም ሳታደርግ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ እሱ ተነስቶ እንደቆመ ሳይንቀሳቀስ በስስትና በሚያሳዝን አይታ ይመለከታት ጀመር። ፊቱ ላይ የምታየው የስስት እና የፍቅር አስተያየት ብሎም ከንፈሮቹ መናገር ማውራት እየፈለጉ ቃላት ለማውጣት ከብዷቸው ሲንቀጠቀጡ መመልከቷ ምን አስቦ ምን ፈልጎ እንደሆነ ለመረዳት እንድትፈልግ ቢያስገድዳት ይበልጥ ግራ የመጋባቱና የፍርሀቱ ስሜት ተደበላልቆ ብዥ አረገባት። ከቆመበት አንድ እርምጃ ወደ ምኞት ሲጠጋ እሷ በተመሳሳይ በአንድ እርምጃ ሸሸችው ። እንደምትሸሸው ሲረዳ ... "እባክሽ ፍቅሬ ፣ የኔ እመቤት ፣የኔ ጤንነት፣የኔ ፀሀይ፣የኔ ንጋት፣የኔ ብርታት፣፣የኔ ርሀብ፣የኔ ጥማት፣ የኔ እብደት፣የኔ ሳቅና ፍካት... እባክሽን ዛሬም እንደሁሌው ሳታናግሪኝ እንዳትሄጂ። ሳታወሪኝ ተመልሰሽ አትጥፊብኝ እባክሽ። ደሞ የኔ ፍቅር ዛሬ ልዩ ሆነሻል ጭራሽ እኮ ሌላ ሰው መሰልሽ። እርግጠኛ ነኝ ጥለሽኝ የሄድሽው ወደ አሜርካ መሆን አለበት። ወይ ይቺ አሜርካ ፊትሽን ማሳመራ ይሁን ፣ የቆዳሽን ቀለም መቀየሯ ይሁን፣ አፍንጫሽን መገተሯ ይሁን፣ አይንሽን ማሳመሯ ይሁን ጭራሽ ቁመትም መጨመር ጀመረች አይ አንቺ አሜርካ ለንቺ ምን ይሳንሻል። ምኞት ለመሳይ ፍቅኛው በመንፈስ የመጣች እንደመሰለው ሲገባት ልቧ በሀዘን ተሰበረ።አይኖቿ በእንባ ተሞሉ። በነኛ ውብ አይኖቿ የተንቸረፈፈውን እንባ መሳይ እንዳያይ አቀረቀረች ። አይንሽንም፣መልክሽንም፣ቁመትሽንም ይቀይሩት ብቻ አንቺ እመሪልኝ እና ደስ ይበልሽ ግን እነዚህ አሜርካኖችን አምነሽ ሁሉ ነገርሽን አትስጫቸው ጥሩ ነው ያሉሽንም ሁሉ አትመኛቸው ነገ በነካ እጃቸው ፆታሽንም እንቀይር ከማለት አይመለሱም።ካስቸገሩሽ ጥለሻቸው እኔጋ ነይ እሺ። አላት በመሀል ዝም ስላለ ቀና ብላ አየችው እያለቀሰች መሆኑን ተመለከተ ፊቱ ወዳያው በሀዘን ተዋጠና እምባው ከሷ በላይ መውረድ ጀመረ... ይቀጥላል....
نمایش همه...
​😘ም..............ኞ...............ት😘 💞ክፍል 40💞 የመጣችው?" አለች እጅን ከአንግቷ ለማስለቀቅ እየተጣጣረች። ድጋሚ እቅፉን እያጠበቀ "ናርዶሴ ነቻ እህት አለም የማታው እማ ልዩ ነበር እንደ ሌላ ግዜው ታይታ ጥፍት ያለችብኝ መሰለሽ ብዙ ሰአት እኮ ከኔ ጋር ነበረች እንቅልፍ ባይወስደኝ እርግጠኛ ነኝ ለምን ለምን ጥላኝ እንደሄደች ልታወራኝ ፈልጋ ነበር በጣም ነው ደስ ያለኝ እህቴ ።"እያለ ትንቢት ትንፋሽ እስኪያጥራት አንገታን አጥብቆ እንዳቀፈ አወዛወዛት።ምኞት እቃ ቤት ሆና የምትሰማው ነገር ከራሷ አሳዛኝ ታሪክ በላይ ስለሆነባት እያለቀሰች" ፈጣሪዬ ለምን እዚህ ነገር ውስጥ ከተትከኝ ለምን" ለምን?እኔ በፍቅር ተጎዳሁ ተገፋሁ እያልኩ ሳማርርህ በፍቅር ተጎድቶ እራሱን የጣለውን ይሄን አሳዛኝ ወጣት እዚህ ጉያዬ ድረስ ያመጣክብኝ ከኔም የባሰ እንዳለ እንድረዳና እንድፅናና ወይስ በፍቅር የቆሰለ ልቧን እየነካካ እሷም አብራው ትበድ ይለይላት ብለህ ነው። ፈጣሪዬ ግራገባኝ እሄ ነገር አጋጣሚ ነው ብዬ ማለፍ ከበደኝ ለምን?ለምን?ሁለት የተገፋን ሰዎችን በአንድ ቦታ ሰብስበህ አንዳችን አንዳችንን ማፅናናት በማንችልበት ሁኔታ እርስ በርስ እንድንላቀስ ፈረድክብን። ፍቅርን የተማርነው ካንተ ሆኖ ሳለ በሰው ላይ ክፋትን የሚያደርጉ ይደሰቱ ዘንድ ፈቅደህ ሰው በወደድን ሰው ባፈቀርን የመከዳት መራራ ፅዋ እንድንቀምስ ሂወታችንን በለቅሶ እና በሀዘን እንድናሳልፍ ፈረድክብን ። ያፈቀረ ሰው ምን ይሆን ሀጥያቱ?ዝም አትበለኝ እባክህ መልስህን መጠበቅ ደከመኝ አምላኬ እባክህ ንገረኝ ይቺ አለም የማን ነች? የኩፉዋች፣ የሸረኛች እና የካሀዲዋች? ወይስ ወይስ የቅን ልቦች? ፈጣሪዬ እኔ የምፈልገውን ሳይሆን ህይወት የሰጠችኝን ተቀብዬ ከሰው እንዳልተፈጠርኩ ከሰው ተገልዬ ተስፋ የቆረጠ ልቤን የተቀበረ ፍቅሬን ከተኛበት የሚቀሰቅስ ሁኔታ ውስጥ ለምን ከተትከኝ ?ወላጆቼን ነጠክከኝ እሱም ሳይበቃ ለምን የምድር ሂወቴን አከበድከው አምላኬ ? እኔም እንደሁሉም ባንተ ፍቃድ አይደል እንዴ እዚህ አለም ላይ የተፈጠርኩት ለምን እኔ ላይ ? ለምን ስቃዬን አበዛከው ?ለምን ለምን ንገረኝ ዝም አትበል ንገረኝ መቼ ነው ሚያበቃው ንገረኝ ንገረኝ ንገረኝ!!!" እያለች ጮኸች አለቀሰች። በዚህ ሰአት እጅግ መራር የሀዘን ስሜት ውስጥ ነበረችና ድንገት በእጆቻ ከታፈነው አፏ ውስጥ አፈትልኮ የወጣ በሲቃ የታጀበ ፍጨት የሚመስል ቀጭን ድምፅ በመሳይ እቅፍ ባለችው ትንቢት ጆሮ ውስጥ በጣም በስሱ አቃጨለባት። ትንቢይ ድንገት ሹክ ብሎ ያስበረገጋትን ድምፅ ለማረጋገጥ ስለፈለገች "እሺ ቆይ እስቲ አንድ ግዜ ወንድሜ"አለችና እጁን ከአንገቷ ላይ እንደምንም አስለቅቃ ተነስታ ወደ መውጫው በር አመራች። በሩን ከፍታ ወደ በረንዳው ወጣች ። ዝር የሚልም ሰው የለም።ግራ ገባት ተመለሰችና "ቁርስ ብላና ታወራኛለህ" አለችው እና ቁርሱን አቀረበችለት ።መሳይ መልስ ሳይሰጣት ቁርሱን መብላት ጀመረ። "እኔም እንደሱ መቃዥት ጀመርኩ?ወይስ ጆሮዬ ነው ? ድምፅ እማ ሰምቻለሁ!በትክክል የሆነ ደስ እማይል የሚረብሽ ድምፅ ሰምቻለሁ" አለች ለራሷ።መሳይ ፍቅረኛውን እንዳያት ሲነግራት ደስታው ከሌላ ግዜው ላቅ ያለ መሆኑ ቢያስገርማትም በህልሙ አይቷት አልያም እንደለማዱ እየቃዥ ነው ብላ ደምድማለች። እንደተወዘጋገበች ተነሳችና ወደ መኝታ ቤት ገብታ አየት አትጋ ወጣችና ቀጥታ ወደ ሽንት ቤቱ አመራች የሆነ ድምፅ የሰማሁ መስሎኝ ነበር ከጎረቤት ነው እንዳልል ተዘጋግቷል አለች ጮክ ብላ።ምኞት ሰማቻት ትንቢት ወደ ሽንት ቤት ስትገባ ከመቅፅበት ከፍራሿ ለይ ተፈናጥራ በመነሳት መሬት ለይ በመቀመጫዋ ዝርፍጥ ብላ ተቀመጠችና መሀል ላይ እንደ መከለያ ባቆመችው አሮጌ የማይሰራ ፍሪጅ ላይ ወገባን በማስደገፍ ሁለት እግሮቻን ዘርግታ በሩን ለመዝጋት የምትጠቀምበት ግማሽ ቀረጢት ሲሚንቶ ላይ በማድረግ ወደ በሩ አጥብቃ ያዘችው።ትንቢት ሽንት ቤት ገብታ እንደወጣች ሽንት ቤቱ በር ላይ ቆም አለችና ከእቃ ቤቱ በር ጋር ተፋጠጠች። ግጥም ተደርጎ ቢዘጋም ከውጪ ሰረገላም ይሁን ተቀርቃሪ አልያም ተንጠልጣይ ቁልፍ የለውም ። ጠጋ አለችና ገፋ አደረገችው ዝግ ነው ሀይል ጨምራ ገፋችው አይነቃነቅም "ከውስጥ በምን ዘጉት" ግራ ገባት እቃ ቤቱ በውጪ የመስታወት መስኮት እንዳለው እንዳየች ትዝ አላት። በቃ ቤቱ መስኮት ወደ ውስጥ ለመመልከት ወደ በረንዳው ወጣች.................... ይቀጥላል..... https://t.me/SALMULD
نمایش همه...