cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

CNN News አማርኛ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 620
مشترکین
-224 ساعت
+87 روز
+1130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።   የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ምን አሉ ? ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል። ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል። " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል። የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦ ° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ ° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል። " እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል። " የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል። ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል። ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል። " በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል። ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።
نمایش همه...
00:21
Video unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ሸዋ በርካታ ቁጥር ያላቸው አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች በኦነግ ‹‹ሸኔ›› ታፈነው መወሰዳቸው ተሰማ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገርበ ጉራቻ ከተማ፤ ቅዳሜ ዕለት ሰኔ 10/2015 ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከባድ መኪና እና የሕዝብ ትራንሰፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በማገት በርካታ አሸከርካሪዎችንና ተሳፋሪዎች አፍነው መወሰዳቸውን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች። ለእገታ የተዳረጉት የኹሉም ተሽከርካሪዎች አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እና ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ጉዞ በማድረግ ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል። በዕለቱም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን ከገርበ ጉራቻ ከተማ ወጣ ብሎ ልዩ ሥሙ ኡላ በተባለ ቦታ መንገድ በመዝጋት መኪኖቹን ካስቆመ በኋላ፤ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎችን ወስዶ ከስፍራው መሰወሩን ነው ነዋሪዎች የተናገሩት፡፡ ነዋሪዎቹ አክለውም፤ ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው በተደጋጋሚ መሰል ተግባራትን ማድረጉ የተለመደ ቢሆንም፣ የአሁኑ ለየት የሚያደርገው በቁጥር ብዙ የሆኑ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱ እና ሌላ ጊዜ ሌሊት ላይ የሚያደርገውን ተግባር በቀን መፈጸሙ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ የአገር መከላከያ ሰራዊት ካምፕ በኩዩ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ “ከበላይ አካል ትዕዛዝ አልተቀበልንም” በማለት ሰዎቹን ሊታደጓቸው አለመቻላቸው ነው የተገለጸው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ሳምንት በፊት በፊቼ ከተማ መውጫ ላይ በተለምዶ ገንደ ጉዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በቅርብ ርቀት ላይ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ ታፍነው መውሰዳቸው ተነግሯል። የአካባቢው ማህበረሰብ በታጣቂ ቡድኑ በተደጋጋሚ በሚደርስበት ጥቃት የስነልቦና ድቀት እንዲሁም በሰው ሕይወትና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገደ ነውም ብለዋል። በታገቱ ሹፌሮች ቁጣ፣ በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ከደብረ ማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ ከረፋድ ጀምሮ ዝግ መሆኑ አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል። የታገቱ አሽከርካሪዎችን ለመልቀቅ አጋቾች ለአንድ ሰው ከ500 ሺሕ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እየጠየቁ መሆኑም ተነግሯል። አዲስ ማለዳ ከአሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብታደርግም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል። #አዲስ_ማለዳ @cnn_amharic1 @cnn_amharic1
نمایش همه...
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ከግንቦት 5-7 ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ እና የሰርግ ስነስርዓትን ታድመው ይመጡ የነበሩትን ጨምሮ አጠቃላይ 40 ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን አነጋግሮ አሻም ቲቪ ዘግቧል። ከዚህ ቀደም ብሎ ግንቦት 4 በፋኖ ሀይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደነበር ተገልጿል። የአካባቢው ነዋሪዎች በስጋት ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ባህርዳር እና ወደ ገጠራማ አካባቢዎች መሰደዳቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ም/ሰብሳቢ አቶ እእድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በአካባቢው ውጊያ እንደነበር ገልፀው ነገርግን አንድም ንፁሃን አልሞቱም ሲሉ ለጣቢያው መናገራቸውን ሸገር ተመልክቷል። @cnn_amharic1 @cnn_amharic1
نمایش همه...
በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ ይሆናሉ ተባለ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ እንደሚሆን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ገልጸዋል።     በኢትዮጵያ 71 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም የሚፈጠረው የስራ እድል ግን ከ50 በመቶ በታች መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ወንድማገኝ ታዬ ለአራዳ ገልጸዋል።     በዚህም በየዓመቱ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ዜጋ ስራ አጥ እንደሚሆን የሴንትራል ስታቲስቲክስ ዳታ ጥናት ያመላክታል ነው ያሉት ባለሙያው።     የህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር አለመመጣጠን፣ ከማምረቻው ዘርፍ ይልቅ የአገልግሎት ዘርፉ መስፋፋትና የሚቀጥረው ሰው አነስተኛ መሆን የራሱ ድርሻ እንዳለውም ጠቅሰዋል።     በተጨማሪም ከሚፈጠር የስራ እድል ውስጥ 80 በመቶው በመንግስት በኩል መሆኑም ለዚህ የራሱ ድርሻ አለው ነው ያሉት።     ይህን ለመቅረፍም የግሉ ዘርፍ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በስፋት መስራት እንዳለባቸው ባለሙያው አስገንዝበዋል።     ከዚህ ባለፈም የመስራት ባህልን ማሳደግ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና መሰል የመፍትሄ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል። Arada
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
US Inflation Rate (I:USIR) US Inflation Rate is at 3.36%, compared to 3.48% last month and 4.93% last year. This is higher than the long term average of 3.28%.
نمایش همه...
نمایش همه...
Israel's First Reaction On Ireland And Norway Over Recognition Of Palestinian State

Norway's announcement of recognizing a Palestinian state comes amidst escalating tensions in Gaza and mounting pressure for a two-state solution.