cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Voa Amharic

መረጃዎችን ለመላክ @Voa_News_Amharic_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
16 531
مشترکین
+1824 ساعت
+847 روز
+80830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በጅጅጋ እየመከሩ ነው የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ የኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ የውሃ ሚኒስትሮች ጂግጂጋ መግባታቸው ተገለጸ። ሚኒስትሮቹ ጂግጂጋ የገቡት በቀጠናው ሀገራት መካከል የሚኖሩ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ ድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሃ አጠቃቀም ላይ ለመምከር መሆኑ ተጠቁሟል። የቀጠናው ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተጨማሪ የዩኒሴፍ የአለም ባንክና ሌሎች አጋር ድርጅቶች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል። ሚኒስትሮቹ ጅግጂጋ ሲደርሱ የሶማሌ ብሔራዊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ መሀመድ በጅጅጋ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
ትምህርት ሚኒስቴር ለስድስት ተጨማሪ የምርምር ጆርናሎችን እውቅና ሰጥቷል። ሚኒስቴሩ በ2012 ዓ.ም ለሦስት ዓመት የሚቆይ እውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎችን እንዲሁም ሌሎች ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ለማግኘት ያመለከቱ በድምሩ 35 የአገር ውስጥ ጆርናሎች ላይ ፍተሻ ሲያካሒድ መቆየቱን አስታውሷል። በዚህም በ2012 ዓ.ም እውቅና አግኝተው ከነበሩ ጆርናሎች መካከል አስራ አንድ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም ካመለከቱ ጆርናሎች መካከል ስድስት (ከታች ከቁጥር 12-17 የተገለፁት) በድምሩ አስራ ሰባት የምርምር ጆርናሎች መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል። ለጆርናሎቹ የተሰጠው እውቅና ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመት የሚቆይ ነው ተብሏል። 1. Bahir Dar Joumal of Education 2. East African Journal of Sciences 3. East African Journal of Social Sciences and Humanities 4. Ethiopian Journal of Agriculture Sciences 5. Ethiopian Journal of Education 6. Ethiopian Journal of Social Sciences and Language Studies 7. Ethiopian Journal of the Social Sciences and Humanities 8. Haramaya Law Review 9. Jimma University Law Journal 10. Journal of Ethiopian Studies 11. Oromia Law Journal 12. Ethiopian Association of Civil Engineers Journal 13. Ethiopian Journal of Business and Economics 14. Ethiopian Journal of Business Management and Economics 15. Ethiopian Journal of Development Research 16. Ethiopian Journal of Higher Education 17. Journal of Indigenous Knowledge and Development Studies https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
ሃማስ የተኩስ አቁም ሃሳብ እንደሚቀበል አስታወቀ ሃማስ ለኳታርና ለግብፅ ሸምጋዮች አዲስ የጋዛን የተኩስ አቁም እና ከእስራኤል ጋር ታጋቾችን የመልቀቅ የስምምነት ሃሳብ መቀበሉን አስታውቋል። የፍልስጤም የድርድር ልዑክ ባለስልጣናት "ኳሱ አሁን በእስራኤል እግር ላይ ናት" ብለዋል። የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃማስ የተቀበለው ሀሳብ “ከእስራኤል መሰረታዊ መስፈርቶች የራቀ ነው” ነገር ግን ድርድሩ ይቀጥላል ብለዋል። ቀደም ሲል እስራኤል ፍልስጤማውያን የከተማዋን ክፍል ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀች በኋላ በራፋህ ላይ የአየር ድብደባ አድርጋለች።በደቡብ ከተማ በሃማስ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሚችል ለረጅም ጊዜ እስራኤል ስታስፈራራ ቆይታለች። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በድርጊቱ ተጎድተዋል ተብሎ የታመነ ሲሆን በርካቶችም ሰኞ ዕለት በተሽከርካሪዎች እና በአህያ ጋሪ ላይ ሆነው ከመኖሪያ ቀዬያቸው ሲሰደዱ ታይተዋል። የሐማስ ባለስልጣናት የእስራኤል የአየር ጥቃትን ተከትሎ የራፋህ ምሥራቃዊ አካባቢዎችን ዜጎች ለቀው እንዲውጡ የተሰጠው ትዕዛዝ አደገኛ የውጥረት መባባስ ያስከትላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት ለሳምንታት የፈጀው ውጊያ ቆም ብሎ በሃማስ የተያዙ በርካታ የእስራኤል ታጋቾችን ማስፈታት ያለመ ነው።ሰኞ ማምሻውን የሃማስ የፖለቲካ መሪው እስማኤል ሃኒዬ ለኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የግብፅ የስለላ ሃላፊ “የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ ያቀረቡትን ሀሳብ ማፅደቃቸውን” የሚገልጽ መግለጫ አውጥተዋል። ሀማስ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ ጎጂ የሆነ እንቅስቃሴን ለዘለአለም ለማስቆም መስማማቱን ስለ ድርድሩ የሚያውቁ ከፍተኛ የፍልስጤም ባለስልጣን ተናግረዋል። ምንም እንኳን ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጥም ይህ ንግግር ሃማስ የትጥቅ ትግሉን ሊያጠናቅቅ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል። እያንዳንዱ ሂደት ለ 42 ቀናት የሚቆይ የሁለት-ደረጃ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሷል። የመጀመሪያው ምዕራፍ በእስር ላይ የሚገኙትን ሴት የእስራኤል ወታደሮች ከእስር መልቀቅን ይመለከታል። አንድ ሴት እስራኤላዊ ወታደር ከእስር ስትለቀቅ በአፀፋው በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ 50 ፍልስጤማውያን እስረኞች የዕድሜ ልክ እስራት የተበየነባቸውን ጨምሮ ይለቀቃሉ። በዚህ ጊዜ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ውስጥ ይቆያሉ። ነገር ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሥራ ላይ በዋለ በ11 ቀናት ውስጥ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የሚገኙትን ወታደራዊ ተቋማትን ማፍረስ ትጀምራለች በሚል ስምምነቱ ላይ ተገልጿል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
አቶ በረከት ስምኦን ከሀገር መውጣታቸው ተሰማ የቀድሞ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩትና ከወራት በፊት ከእስር የተፈቱት አቶ በረከት ስምኦን አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 ዳላስ ኤርፖርት በወዳጆቻቸው አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል።አቶ በረከት በምን ጉዳይ ከሀገር እንደወጡ ለጊዜው አልታወቀም። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድ "ተገቢ ያልኾነ ወሳኔ አሳልፎ ሕልውናዬን አደጋ ላይ ጥሏል በማለት ሰሞኑን ከሷል። ፓርቲው ይህን ያለው፣ ፓርቲው "የመሰረዝ ዕጣ ፋንታ" ሊገጥመው እንደሚችል  ቦርዱ ማስጠንቀቁን ተከትሎ ነው። ፓርቲው የወሰደውን 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የድጎማ ገንዘብ እንዳላወራረደ የገለጠው ቦርዱ፣ አንዳንድ የፓርቲው አመራሮች የስም ማጥፋት መረጃ አሠራጭተውብኛል ብሏል። በፓርቲው እና በቦርዱ መካከል ውዝግብ የተቀሰቀሰው፣ ፓርቲው በዲሲፕሊን ቀደም ሲል የታገዱ አመራሮች የዋና ጽሕፈት ቤቱን ቁልፍ ሰብረው ሲገቡ ምርጫ ቦርድ ርምጃ አልወሰደም ብሎ ከከሰሰ በኋላ ነው። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
እስራኤል አልጀዚራን ዘጋች፤ ጣቢያው ድንገተኛ ብርበራ ተደርጎበታል! እስራኤል የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘጋች። ጣቢያውን የዘጋችው ''የሐማስ አፈ ቀላጤ ሆኗል'' በሚል ክስ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ “የእስራኤል ካቢኔ ጣቢያው እንዲዘጋ ወስኗል” ብለዋል። ይህን ተከትሎ ፖሊስ በጣቢያው ቢሮ ኢየሩሳሌም፣ አምባሳደር ሆቴል ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ብርበራ አድርጓል።እስራኤል “አልጀዚራ ለብሔራዊ ደኅንነቴ ሥጋት ነው” ማለቷን ጣቢያው፣ “ቀሽም ነገር ግን አደገኛ ዉሸት” ሲል አጣጥሎታል።ጣቢያው በሕግ መብቱን እንደሚያስከብር ዝቷል። የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በድንገተኛ ወረራው አንዳንድ ቁሳቁሶች ተወስደዋል ብለዋል።በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የኤክስ ገጽ በተለጠፈ ተንቀሳቃሽ ምሥል ፖሊሶች ወደ ሆቴሉ ገብተው ሲበረብሩ ያሳያል።የቢቢሲ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው አቅንተው የነበረ ቢሆንም ወደ ውስጥ እንዳይገቡ፣ ክስተቱንም እንዳይቀርጹ ተከልክለዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው የእስራኤል ሳተላይት አገልግሎት አልጀዚራ ይታይበት በነበረ ምሥል አሁን የጽሑፍ መልእክት ብቻ እየታየ ይገኛል፤ መልእክቱም “መንግሥት በወሰነው መሠረት በእስራኤል የአልጀዚራ ሥርጭት እንዲቆም ተደርጓል” የሚል ነው።አልጀዚራ በሳተላይት ይታገድ እንጂ አሁንም በእስራኤል በፌስቡክ እየታየ ነው። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ኢሰማኮ አስታወቀ! የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብለዋል። ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ ግብር እንዲቀነስ ላቀረብነዉ ጥያቄ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ብሏል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተደነገገ ቢሆንም የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ በሚንስትሮች ምክር ቤት ባለመውጣቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያልተገባ መሆኑን ነዉ ማህበሩ ያስታወቀው። በጦርነት ዘላቂ መፍትሒ ስለማይመጣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና ጦርነት ቆሞ በዉይይት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች በድርድር እንዲፈቱ የጠየቀው ኢሰማኮ ለጉዳዩ አፅንኦት ይሰጠዉ ብሏል በመግለጫው። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ትንሣኤ ሎተሪ ወጥቷል። የ2016 የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የወጣ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የአንደኛ ዕጣ ቁጥር 1407747 ሆኖ ወጥቷል። 5 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የሁለተኛው የዕጣ ቁጥር ደግሞ 0179265 ሆኖ ወጥቷል። የ2.5 ሚሊዮን ብሩ የሶስተኛው ዕጣ ቁጥር 2160591 እንዲሁም የ1.5 ሚሊዮን ብር የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0165786 ሆኖ ወጥቷል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
በአማራ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መጠለያ ካምፕ ላይ ጥቃት በመፈፀሙ የሱዳን ስደተኞች ለቀው ለመውጣት ተገደዋል ተብሏል በአማራ ክልል በሚገኝ ኩመር ተብሎ በሚጠራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መጠለያ ካምፕ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት የሱዳን ስደተኞች ለቀው ለመውጣት መገደዳቸው ተጠቆመ። የታጠቁ ሀይሎች በመጠለያ ካምፑ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚያደርሱ፣ ዘረፋ እንደሚፈጽሙ ከመንግስታቱ ድርጅት እና ከሶስት ስደተኞች ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። “ወደ እዚህ መጠለያ ከመጣንበት ያለፈው አመት ሰኔ ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጸምብናል፣ እንታገታለን፣ እንገደላለን፣ ከአሁን በኋላ እዚህ መቆየት አንችልም፤ ጦርነት ቢኖርም ወደ ሀገራችን እንመለሳለን” ሲል አንድ ስደተኛ በስልክ እንደነገረው ሮይተርስ በዘገባው አካቷል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...
ሀማስ በከረም ሻሎም በፈፀመው የሮኬት ጥቃት ሶስት የእስራኤል ወታደሮች ተገደሉ ሃማስ ሮኬቶችን መተኮሱን ተከትሎ እስራኤል የከረም ሻሎምን የጋዛን መሻገሪያ መስመርን ዘግታለች። እስራኤል በጥቃቱ ሶስት ወታደሮቿ መግደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን አስታውቃለች። መሻገሪያው የምግብ እና የህክምና አቅርቦቶችን ጨምሮ ሰብአዊ ርዳታ ለማግኘት ወደ ጋዛ ከሚገቡት ጥቂት መንገዶች መካከል አንዱ ነው። በግብፅ የሚገኙ ሸምጋዮች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማስፈን እና በሃማስ የተያዙ ታጋቾችን ለማስፈታት ያለመ የሁለት ቀናት ውይይት ላይ በሚገኙበት ወቅት ጥቃቱ ተፈፅሟል። ሃማስ በመግለጫው እንዳስታወቀው የመጨረሻው ዙር ድርድር እሁድ መጠናቀቁን እና የልኡካን ቡድኑ ከካይሮ ወደ ኳታር በማቅናት ከቡድኑ አመራሮች ጋር ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አስታውቋል። በሽምግልና ጥረቶች ላይ የተሳተፉት የአሜሪካው የስለላ ተቋም የሲአይኤ ሃላፊ ዊልያም በርንስም ከግብፅ ዋና ከተማ ለቀው በዶሃ ውይይት ማድረጋቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል። የእርቅ ንድፈ ሀሳቡ የእስራኤል ታጋቾች ሲፈቱ ለ40 ቀናት ያህል ውጊያው እንዲቆምና በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ በርካታ የፍልስጤም እስረኞችን መፍታትን ያካትታል ተብሎ ይታመናል። ሃማስ አሁን የቀረበውን ሃሳብ “በአዎንታዊ መልኩ” ተመልክቻለሁ ብሏል፣ ነገር ግን ዋናው ነጥብ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዘላቂ ነው ወይስ ጊዜያዊ ይሆናል የሚለው ነው ብላል። ቡድኑ የትኛውም ስምምነት ጦርነቱን ለማቆም የተለየ ቁርጠኝነት እንደሚያደርግ አጥብቆ እየተናገረ ቢሆንም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን እሁድ እለት የነበረውን ድርድር አልተቀበሉትም። የእስራኤል መንግስት ይህንን የሃማስን ጥያቄ መቀበል አይችልም ሲሉ አክለዋል። የሃማስ ብርጌዶች ከጋሻቸው ወጥተው ጋዛን እንደገና የተቆጣጠሩበት ፣ ወታደራዊ መሠረተ ልማታቸውን መልሰው የገነቡበትን ሁኔታ ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም ሲሉ ተደምጠዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጦርነቱን እንዳያቆሙ በቀኝ ዘመም ኃይሎች በተለይ ወደ ራፋህ ሙሉ በሙሉ እግረኛ ጦር እንዲገባ እየተጠየቁ ይገኛል። በዚህ በኩል ደግሞ የታጋች ቤተሰቦች ግጭቱ ቆሞ ታጋቾች ከጋዛ ሰርጥ እንዲለቀቁ እየተጠየቀ ይገኛል። በጥቅምት 7 በሃማስ ታግተው ከነበሩት 252 ታጋቾች መካከል 128ቱ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከነሱ መካከል ቢያንስ 34ቱ ሞተዋል ተብሎ ይታመናል። የሐማስ ታጣቂ ክንፍ የሆነው አልቃሳም ብርጌድ በከረም ሻሎም ማቋረጫ ላይ አዲስ ጥቃት መፈፀሙን ያረጋገጠ ሲሆን፥ በአጭር ርቀት ሮኬቶች የእስራኤል ወታደሮችን ኢላማ አድርጓል። የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ ማቋረጫ አካባቢ ከከረም ሻሎም 3.6 ኪሜ ርቆ ከሚገኘው አካባቢ 10 ሚሳይሎች መተኮሳቸውን አስታውቋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
نمایش همه...