Change your Life
رفتن به کانال در Telegram
- We need Positivity + Hard work... Join our group @BurukLight
نمایش بیشتر2 782
مشترکین
+124 ساعت
+57 روز
-630 روز
آرشیو پست ها
2 782
ተስፉ የማይቆርጥን ሰው ልታሸንፈው አትችልም።ማን እንደተናገረው ባላቅም በርግጥ እውነት ነው።
ሽንፈት ተስፉ በማይቆርጥ ሰው ላይ አይሰራም።
2 782
ታውቃላችሁ በአለም ላይ ከ90% በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደሃ መሆናቸውን የሚገርመው የተቀሩት 10% የማይሞሉ ሰዎች ደግሞ የአለማችን ከግማሽ በላይ ሃብት የእነሱ ነው።
መቼስ የሆነ እነሱ የገባቸው እኛ ያልገባን ነገር እንዳለ ግልጽ ነው
መማር ብቻ ሀብታም ቢያረግ የተማረ ሁሉ ሚሊየነር በሆነ ነበር
ጥሩ ፣ ደግ ሰው መሆን ብቻውን ሃብታም ሚያደርግ ቢሆን አብዛኛው ለሰው የሚራራና የሚያስብ ደሃ ባልሆነ ነበር
አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር መስጠት ከቻላችሁ ለሱ ተገቢ ክፍያ መጠየቅ የሃብት መጀመርያ ነው።
ዋጋ ያለው ለሰዎች ምትሰጡት ነገር ምን አላችሁ? 🤔
2 782
አእምሮህ ልክ እንደማሽን ነው መልካም ነገር ከመገብከው መልካም ህይወት ይሰጥሃል ፣
መጥፎ ነገር ከመገብከው መጥፎ ህይወት ይሰጥሃል።
ቆሻሻ አእምሮህ ውስጥ ጨምረህ ፣ ድንቅ መልካም አስደሳች ህይወት ትጠብቃለህ?
የምታየውን የምትሰማውን የምታነበውን የምታስበውን ሰው አይመርጥልህም።
ምርጫው ያንተ ነው
2 782
መልስ ያጣኸው ጥያቄህ ላይ ስህተት ስላለ ነው።
ለትክክለኛ ጥያቄ ሁሌም መልስ አለ።
ጥራት ያለው ግልጽ ጥያቄ በራሱ የመልሱ 50% ነው።
2 782
ብዙ ሰዎች Motivation መጀመርያ እንደሚመጣ ያስባሉ። አይመጣም።
Motivation የሚመጣው የመጀመርያውን እርምጃ ስትራመድ ነው እንጂ ተኝተህ አይደለም።
2 782
አዲስ ነገር ማድረግ የፍርሃት ስሜት ይፈጥራል። ያ ተፈጥሮ ነው።
ከፍርሃት በላይ መሆን ግን ክህሎት ነው።
ክህሎት ደግሞ በድግግሞች የሚገነባ ነው።
ስለዚህ ፍርሃትን ለማሸነፍ የሚያስፈራህን ደግመህ ደጋግመህ ማድረግ ነው።
2 782
ህይወትን እንድትቆጣጠር የሚረዱህ 3 ነገሮች:
1. የምታስባቸውን ሃሳቦች
2. ጓደኞችህን መምረጥ
3. የምታየውን / የምትሰማውን መምረጥ
የህይወትህ መሪ መሆን የምትችለው አንተን influence ሊያደርጉ የሚችሉትን ነገሮች በመምረጥ ነው።
ከሶስቱ የትኛው በእናንተ ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው?
2 782
ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ ግን በቀን ለ3/4 ሰአት TikTok ታያለህ።
TikTok Scroll ማድረግ ስኬታማ የሚያደርግህ ይመስልሃል?
ከዛሬ ጀምረህ ወደ ምትፈልገው ህይወት የሚመራህን ነገር ማድረግ ጀምር።
2 782
የነገሮች ጊዜ መውሰድ!?
መማር ጊዜ ይወስዳል
ማንበብ ጊዜ ይወስዳል
TikTok ማየት ጊዜ ይወስዳል
መዝናናት ጊዜ ይወስዳል
መተኛት ግዜ ይወስዳል
መስራት ጊዜ ይወስዳል
ሁሉም ነገር ጊዜ/እድሜ በተባለ ነገር ውስጥ ይጠቃለላል።
ሁሉንም በጊዜው እንደማድረግ የሚያስደስት ነገር የለም።
በማንበብ ስአት ማንበብ ፣ በመዝናናት ስአት መዝናናት ፣ በመተኛት ስአት መተኛት በስራ ሰዓት መስራት...
ህይወት የሚመስቃቀለው ማድረግ ያለብንን ነገር ማድረግ ባለብን ሰአት ካላደረግን ነው።
በወጣትነታችን ካልሰራን ፣ ካልተዝናናንም ይቆጨናል።
አንድ ጥያቄ በአዕምሮአችሁ ያዙ በዚህ ሰአት በዚህ እድሜዬ ማድረግ ያለብኝ ምንድነው?መልሱ መዝናናት ከሆነ ተዝናኑ ፣ መስራት ከሆነ ስሩ ፣ መተኛት ከሆነም ተኙ😊 መማር ከሆነ ተማሩ ፣ ማግባት ከሆነ አግቡ... ማንኛውም ነገር ጊዜ ይወስዳልና ሁሉን በጊዜው አድርጉ።
2 782
ስሜት በራሱ መጥፎም ጥሩም አይደለም የምንተረጉምበት መንገድ ነው ያን የሚወስነው።አንዳንድ ሰዎችን ፍርሃት ወደኋላ ሲያስቀራቸው አንዳንዶችን ወደፊት ይገፉቸዋል ፣ አንዳንዶች ንዴት ሲሰማቸው ለመረጋጋት መጠጥ ይጠጣሉ (ያጨሳሉ) ብልሆች ሲናደዱ ያንን ንዴት ይዘው ፣ ይሰራሉ ይጥራሉ በጣም ስለተናደዱ እስኪያሳኩ አያርፉም። ሲደብረው የሚተኛ እንዳለ ወደ ስራ ወደ ንባብ ወደ ስፖርት የሚገባም አለ። የሚሰማችሁ ስሜት መጥፎም/ጥሩም ሃይል ነው ወደምትፈልጉት ነገር ላይ አውሉት።
2 782
Your brain becomes its environment. Change the environment, and habits follow automatically.
2 782
አስተማሪ ሞልቷል ተማሪ ጠፉ እንጂ።
ሰዎች ያስተምራሉ ፣ ተፈጥሮ ያስተምራል ፣ ክስተቶች ያስተምሩናል ፣ ህይወት ያስተምረናል ፣ ጊዜ አስተማሪ ነው ፣ መጽሃፍም ያስተምራል ፣ ሰባኪያን ያስተምራሉ...
የሚጠይቅ የሚማርና የሚያደርግ ግን የለም።
3ቱን ማድረግ የቻለ ያሸንፉል።
2 782
Feeling happy all the time is not good for us. As humans, we need both happiness and sadness to live in this world. They preach that we should always be happy, but that’s not how we are built to feel only positive emotions. When you’re sad, be sad; when you’re angry, be angry; when you’re happy, be happy :)
2 782
ሁሌም ፈተና አለ ሰራችሁም ፈተና አለ ተቀመጣችሁም ፈተና አለ።
የምትፈልጉትን ለማሳካት ብዙ ፈተና ታልፉላችሁ ፣ ብዙ ልፉት አለ ፤ ምን አለፋኝ ብላችሁም ብትቀመጡ ለመኖር ለመብላትም መልፉት አለባችሁ።
ለትልቅ ህይወት ስትሰሩም ፈተና የማይቀር ከሆነ ለትንሽ ነገርም እንደዛው ከሆነ ከሰራችሁ ከደከማችሁ አይቀር ለምን ለትልቁ አትሰሩም?።
ብትሰሩ ብትለወጡ ጊዜያችሁን ብትጠቀሙም ሰዎች ያወሩባችኋል ተለወጠ ፣ ኮራ ፣ ለምን እንዲ ሆነ ይላሉ ፣ ብትቀመጡም ባትለወጡ አይሰራም ሰነፍ ነው ፣ ደሃ ነው ይላሉ... ብትሰሩም ለትልቅ ነገር ፤ ባትሰሩም ፈተና አለ።
እንዴት ነው ወደፊት ትዳር ምን ታስባለህ ስለው?
"እመነኩሳለሁ ካልክም ፈተና ነው አገባለሁ ካልክም ፈተና ነው።"
ብሏል አንድ ዲያቆን ጓደኛዬ😁
ህይወት ላይ ሰራችሁም ተቀመጣችሁም ፣ ሰነፍ ሆናችሁም ጎበዝ ፣ ሃብታም ሆናችሁም ድሃ ፈተና /ልፉት በህይወት አለ።
ዋጋ ላለው ነገር መፈተን ግን የተሻለ ነው።
2 782
ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ሳይቀር ይዋሹና ያንን ውሸት ያምኑታል እንደነዚ አይነት ሰዎች ምንም ያህል ብታስረዷቸው እውነቱን ከማወቅ ውሸቱን ማመንን ይመርጣሉ።
እንደዚህ አይነት ሰዎች እውነቱን እንዲረዱ በገፋችኋቸው ቁጥር እየጠሏችሁ ይመጣሉ። ምክንያቱም እውነቱ ማወቅ ድክመታቸውን ማወቅ ፣ ስህተታቸውን ማመንን ይጠይቃል ያን ደግሞ አይፈልጉም።
የትኛውንም አሳማኝ ሃሳብ ብታነሱ ፣ ብትከራከሩ አይሰሙም ደረቅ ናቸው።
ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ከመከራከር ይልቅ ትክክል ነህ / ትክክል ነሽ ብሎ ማለፍ የተሻለ ነው።
- Buruk
2 782
ኢትዮጲያን ካለን ባህል የማደንቀው የቀብር ስነስርዓታችንን ነው።
እናት አባቶቻችን አለማዊ ትምህርት ሳይማሩ ያላቸው መረዳት ይገርመኛል...
ለቅሶ ላይ ሃዘን መካፈል መቅረት የሌለበት ባህላችን ነው።
ነጮች ይህ ባህል የላቸውም ቀብረው ወደ ስራ ብዙም አይለቀስም እስከ ሰልስት ማጽናናት ጊዜ እንደማባከን ነው የሚመለከቱጥ 7 ሰአት ቀብረው 7፡30 ሁሉም ወደ ስራ ነው። (እሱም ሰው ከመጣ ነው)
የሟች ቤተሰብ ለብቻው ሃዘኑን ይሸከማል እስከ ሳምንት ወይ ሰልስት ማጽናናት የለም አሁን ላይ ግን ይህ የኛ ባህል ከሳይኮሎጂ አንጻር ተቀባይነት ያለውና አስፈላጊ እንደሆነ ተረጋግጧል።
የሰውን ሃዘን መጋራት የዛን ሰው ሃዘን ያቀላል አብሮ ማልቀስ ፣ አብሮ መሳቅ ፣ አብሮ መቅበር..ኢትዮጲያዊያንን እንዳደንቅ የሚያደርገኝ ነገር ነው። እኛ ሰዎች ለብቻችን እንድንኖር አልተፈጠርንም በመሐበር እንድንኖር እንጂ።
እድርና እቁብም እኛ የምንታወቅበት ባህላችን ነው። አሁን ላይ ዘመናዊነት ሲመጣ ይህም እንዳይቀር እሰጋለሁ።
እናት አባቶቻችን "ያልተማሩ" ምሁር እንደነበሩ ጥርጥር የለውም።
🇪🇹 Ethiopian ✓
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
