fa
Feedback
Change your Life

Change your Life

رفتن به کانال در Telegram

- We need Positivity + Hard work... Join our group @BurukLight

نمایش بیشتر
2 777
مشترکین
+124 ساعت
+27 روز
-730 روز
آرشیو پست ها
ሰው ሊሞትለት የሚችል አላማ ከሌለው ለመኖር ይቸገራል።
- Buruk

የምንቆጣጠረው ነገር ላይ ብቻ ማተኮር። በዚህ ዘመን ልንቆጣጠረው በማንችለው ልንለውጠው ፣ ልናሻሽለው በማንችለው ነገር ላይ መጨነቅ የተለመደ እየሆነ መጥቷል። በፊት የዛሬ ምናልባት 10 እና 20 አመት ሰዎችን የሚያሳስባቸው አባወራዎችን የሚያስጨንቃቸው እንዴት ቤተሰቤን ላስተዳድር ነበር። እንዴት ለልጄ ልብስ ልግዛ ፣ ትምህርት ላስተምር.. እናቶች የሚጨነቁትም ለልጆቻቸው ነው ጥሩ ለማብላት ፣ ለማሳደግ ልጆች ከፍ ሲሉ እንዴት ቤተስቤን ልጡር ነበር ሃሳብና እቅዳቸው። አሁን በዚህ ዘመን ግን ሰዎች በሚያሳስበው ትተው በማያሳስበው ነገር ሲጠመዱና ሲጨነቁ 'የተመለከታቹ ይመስለኛል። "ትልቅ ሰዎች" 'ሚባሉት ሳይቀር ሀሳባቸው ትውልድ መቅረጽ ሳይሆን view, share እና like አገኝ ይሆን ሆኗል። ወጣቶችም ላሳደጋቸውን ቤተሰብ ውለታ ለመክፈል ከመጨነቅ ይልቅ አርሰናል vs ዩናይትድ ወይስ ሲቲ ነው የሚያስጨንቃቸው። በTiktok ባዩት ነገር ተጠምደዋል እንትና ይችላል ፣ እንትና ነው ጥፉተኛ ፣ እንትና ግን ትክክል ነች... ብዙ እንተናዎች... ስለ ሰው ህይወት ማውራት ፣ ማውራት... እኛ ምን እናድርግ አይደለም ወይይታቸው እንዴት ራሳችንን ከድህነት እናውጣ አደለም። ሲገናኙ እንዴት እኛ አንድ ላይ ቢዝነስ እንፍጠር አይደለም ሃሳብና ጭንቀታቸው። መለወጥ የምንችለውን የራሳችንን ህይወትና የቤተሰባችንን ሕይወት ማሰብ ትተን። ልንለውጠው ስለማንችለው ስለ ሰው ህይወት ፣ ስለእስራኤል (አሜሪካ) እና ኢራን ጦርነት ማውራት ላይ ተጠምደናል። ጦርነቱ የኛን ህይወት ይነካል? አዎ! ግን ብዙ ስላወራን የተወደደው ነዳጅ ይቀንሳል? No! አይቀንስም። ልንለውጠው ልንቀይረው ካልቻልን አንድ ነገር የእኛን ጊዜ ፣ ጉልበት እና ትኩረት ልንሰጠው ይገባልን??? አለም እየሄደችበት ያለው አንዱ አደገኛ መንገድ የሚያገባንን የራሳችንን ህይወት ትተን በማያገቡን ነገሮች እንድንጠመድ ማድረግ ነው። - Buruk

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!✨🕌✨

መጥፎ ሰዎች 😈 አንዳንድ ሰዎች በመጥፎ ባህርያቸው የእናንተን መልካም ምግባር ለመቀየር ሊፈትኗችሁ ይችላሉ። ባጎረሳችሁ ይነክሷችኋል። ለእነሱ መልካም ለማድረግ ስትደክሙ ፣ ስማችሁን በመጥፎ ያነሳሉ። ትንሽ ቆሞ ብላችሁ ስታስቡት🤔 'ምን አገባኝ? እኔ አልጎዳ ፣ የራሳቸው ጉዳይ!' ልትሉና የእናንተን መልካም ስብዕና ልትተዉ ትችላላችሁ። ያ መሆን ግን የለበትም። የእናንተ መልካም ምግባር በሰው መልካም/መጥፎ ምግባር ላይ መመስረት የለበትም። የራሳችሁን ህይወት/ ስነምግባር ራሳችሁ ወስኑ በሰዎች ይወሰን ዘንድ አትፍቀዱ። .

Action takers always win! They beat thinkers, planners, and smarter people - Always!

አለማቆም! መታገስ ኋላ መቅረት አይደለም። ጉዞህን ቀጥል አታቁም። ትንሽ ትግስት ትልቅ ዋጋ ታሰጣለች። መብራትን የፈጠረው Thomas Edison 1000ጊዜ ነው የሞከረው ይባላል አንድ አምፖል 💡 ለማብራት። 999 ጊዜ ታግሶ ሞክሮ አንድ ተጨማሪ ጊዜ ሳይሞክር ቢያቆም ኑሮ ዛሬ ስሙን ባላነሳን ነበር። አለማቆም እስከ መጨረሻው መታገስ የምንፈልገው ለማግኛት መላበስ ያለብን ጠባይ ነው።

ህግ እውነቱን ለመናገር እላይ ያሉት ታች ያሉት ወደላይ እንዲወጡ አይፈልጉም። ይህንን አለም ሚነዳው Greed ስግብግብነት ነው። ህጉን ሚሰሩት ከላይ ያሉት ማለትም ስልጣን ላይ ያሉ ገንዘብ ያላቸው ዝና ስኬት ተከታይ ያፈሩ ናቸው። ህጉንም ሲያወጡ አብዛኛውን ማህበረሰብ ለመጥቀም ሳይሆን ጥቂቶቹን (ራሳቸውን) ለመጥቀም ነው። ይህንን ስትረዱ የአለም ስርዓት አንድ ነገር ላይ ብቻ ያተኩራል። "ተራው" ማህበረስብ ጉልበቱ ፣ ጌዜው ፣ ነፃነቱ ፣ ገንዘቡን "መንጠቅ" ከዛ ለጥቂቶች የእነሱን ጉልበት ፣ ጊዜ ፣ ነፃነት ፣ ገንዘብ መገበር። ከበፊትም ጀምሮ እንዲ ነበር ፣ አሁንም እንዲ ነው ፣ ምናልባት ወደፊትም። ህግ ለተራው ማህበረሰብ እና ከላይ ላሉት እኩል እይሰራም።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! 🕊️✨ ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ። መልካም የትንሳኤ በዓል! @Buruk
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! 🕊️✨ ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ። መልካም የትንሳኤ በዓል! @Buruk_Light

የሰው ልጅ: ሲኖርህ ከፍ ያረግሀል ፣ ስታጣ ደግሞ ያጣጥልሀል አንተ በሁለቱም ጊዜ ዝም ብለህ ስራህን ስራ!

ተስፉ መቁረጥ ምርጫ ውስጥ እንደሌለ ብነግራችሁስ?! አንዳንዴ ተስፉ ብቆርጥስ ምን አደከመኝ። ምከርኩ ሞከርኩ አልተሳካም። ለፉው ጣርኩ አልሆነም። እንዴት ሊሳካ ይችላል? እውቀት የለኝ ገንዘብ የለኝ ዘመድ የለኝ የሚያግዘኝ ሰው የለኝ መራስ መተማ የለኝ ዝነኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ለመሆን ፣ በ YouTube, TikTok, Online ገንዘብ ለመስራት ሞከርኩ ፣ ቤተሰቦቼን ለመለወጥ ሞከርኩ... በአጠቃላይ ይህን ሞከርኩ ያን ሞከርኩ የምፈልገውን ውጤት ማግኘት ግን አልቻልኩም። ስለዚህ "ተስፉ ቆርጫለሁ።" ለማይሳካ ነገር ምን አለፋኝ ፣ እድሌ ነው በቃ ፣ የሚሳካ አይመስለኝም.. እንደዚ አይነት ስሜት ሊሰማችሁ እና እንደዚህ ልታስቡ ትችላላችሁ። የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው። ግን እውነታው ተስፉ መቁረጥ ወይም ማቆም የህይወት ምርጫ ውስጥ የለም። ምሳሌ ልስጣችሁ: አንድ ሰው ምርጫ ላስመርጣችሁ ቢልና ምቶዱትን ምግብ ለምሳሌ ሥጋ 🥩 ቢያቀርብ ከዛ ደግሞ ድንጋይ 🪨 አቅርቦ መርጣችሁ ብሉ ቢላችሉ። ምን ይሰማችኋል? ያመዋል እንዴ?😳 አትሉም ምክንያቱም እንዴት ምርጫ የማይሆን ነገር ያስመርጠኛል ብላችሁ። በጥያቄው ተገርማችሁ ያስመረጥከኝ አስመሰልከው እኮ ድንጋይ እኮ ምርጫ አየይደለም። ያቀረብክልኝ ሥጋ ብቻ ነው ሌላ ምርጫ የለኝም ትሉታላችሁ። ለምን? ምክንያቱም አእምሮአችሁ ምርጫ አይደለም ብሎ ስለሚያምን። በርግጥም ምርጫ አይደለም። በህይወትም እንደዛ ነው ተስፉ መቁረጥን እንደ ምርጫ ማየት ስታቆሙ ፣ ምንም ነገር የማያስቆመው ሰው ትሆናላችሁ። ህይወት የሰጠችን ብቸኛው ምርጫ ተስፉ ሳይቆርጡ መቀጠል ነው። እንስሳት ተስፉ አይቆርጡም ማደን የሚችል ያድናል ፣ መሮጥ የሚችል ይሮጣል ፣ መዋኘት የሚችል ይዋኛል። መዋኘት ደከመኝ ብላ 🐟አሳ ከባህር ትወጣለች? አትወጣም ምክንያቱም ትሞታለች ሰውም ተስፉ ሲቆርጥ መሞት ይጀምራል። ዛፍ ምን ያህል ርዝመት የሚያድግ ይመስላችኋል? መልስ: እስከሚችለው ድረስ! 🌳🌲🌴ሁሉም እንደ አቅሙ እስከሚችለው ድረስ ያድጋል። ተስፉ አትቁረጡ በርቱ አልላችሁም ምላችሁ ተስፉ መቁረጥ የሚለውን ቃል ራሱ ከአዕምሮአችሁ አጥፉት። ተስፉ መቁረጥ የሚባል ነገር እንደሌለ ስትገነዘቡ ያላችሁ ብቸኛ ምርጫ ጠንካራ ሆኖ በጽናት መቀጠል ነው።

ትኩረት! 👀 ትኩረትህን ትኩረት ከሚሰርቁ ነገሮች ካልጠበክ.. የምትፈልገውን ህይወት ለመኖር ትታገላለህ ብቻ አይደለም የ'ማትፈልገውን ህይወት ትኖራለ በዚያም አያበቃም... ጌዜህ ይባክንና አንድ ቀን በ40,50 ወይ 60 አመትህ ላይ በባከነው ጌዜህ ትጸጸታለህ! ግን አሁን ትኩረትህን ከጠበክ -> ጊዜህን ትጠቀማለህ -> ጊዜህን ከተጠቀምክ -> ...የምትፈልገውን ህይወት ትኖራለ ብቻ ሳይሆን ዞር ብለህ የምትጸጸትበት ታሪክ አይኖርም። በርግጥም ያሰብከው ይሳካል ፣ ሆኖም ባይሳካ እንኳን ያባከንከው ጊዜ ከሌለ... "በጊዜዬ ባለኝ እውቀት ፣ በቻልኩት መንገድ ሞክሬአለሁ" የሚል ስሜት ይኖርሃል። ነገ ላለመጸጸት ዛሬ: ✅መስራት የምትችለውን ስራ ፣ ✅ማንበብ ከቻልክ አንብብ ፣ ✅መጻፍ ከቻልክ መጽሃፍ ጾፍ ፣ ✅መተወን ከቻልክ ተውን ፣ ✅መስራት የምትቸለዉን ሁሉንም ✅በጊዜህ ስራ ምክንያቱም
ያን ማድረግ እችል ነበር እኮ😔
የሚል ስሜት ከባዱ ጸጸት ነው። ትኩረትህን በመጠበቅ ነገህን የተሻለ ማድረግ ትችላለህ።
ምርጫው ግን ያንተ ነው!

3ቱ ግብህን ሳታሳካ እንድቷቋርጥ የሚያደርጉህ ምክንያቶች 1ኛ ግቡ ላይ ብቻ ማተኮር። ግብ ማውጣት መልካም ሆኖ ሳለ ግቡ የሚሳካው ግን ግብ ስላወጣህ አይደለም። ግብህ የሚሳካው ግብህን የሚያሳካ ልማድ ስትፈጥር ነው። ስለዚህ ማተኮር ያለብህ ልማድህ ላይ ነው። ልማድህን ስትቀይር ግብህ ይሳካል። በወር 1ሺ ብር መቆጠብ ከፈለክ ትኩረትህ መሆን ያለበት 1ሺ ብሩ ላይ ሳይሆን በቀን 35 ብር ብቻ መቆጠብህን ማረጋገጥ ብቻ ነው። በየቀኑ እንደዛ ከቆጠብክ በወር 1000ብር መቆጠብህ ማየይቀር ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች ሳያሳኩ የሚያቋርጡት ግባቸው ጋር የሚያደርስ ልማድ ስለሌላቸው ነው። ስለዚህ ግባችሁን ለማሳካት ውጤታማ የሚያደርጋችሁን ልማድ መገንባት አለባችሁ። ልማድ እንዴት ይገነባል የሚለውን ሌላጊዜ እናየዋለን። 2ኛ ፍርሃት ሰዎች ብወድቅስ ፣ ሰው ምን ይለኛል የሚል ፍርሃት የሚፈልጉትን ሳያሳኩ እንዲያቋርጡ ያደርጋቸዋል። ሰው ምን ይለኛል ብላችሁ ስንት ነገር ልታደርኩ ብላችሁ ተዋችሁት? በሰዎች ለመተቸት ካልፈቀዳችሁ ትልቅ ስኬት ላይ ለመድረስ ትቸገራላችሁ። ፍርሃታችሁን ስትጋፈጡት የሚያስቆማችሁ ነገር አይኖርም። 3ኛ ትዕግስት ማጣት። የምታደርገውን በጽናት ብትቀጥል ይሳካልህ ነበር። ብዙ ጊዜ ስለማትታገስ ብቻ ነው እንጂ የምትፈልገውን ውጤት ያላገኘኸው የምትሰራው ትክክል ስለኣልሆነ አይደለም። ዛሬ ስፖርት ጀምረህ በሳምንት ለውጥ ካላየህ ታቆማለህ ፣ ማንበብ ጀምርምህ አንድ መጽሃፍ ሳትጨርስ ቁምነገር የለውም ብለህ ትተወዋለህ። 📖 ማጥናት ጀምረህ በመጀመርያው 30 ደቂቃ ስላልገባህ ከባድ ነው አይገባኝም ብለህ ታቆማለህ። Social Media ላይ ይዘት እፈጥራለው ብለህ 3 video ሰርተህ view , like የለውም ብለህ ታቆማለህ። የምትሰራውን በጽናት ብትቀጥል ውጤት ታገኝ ነበር። ምንድነው የጎደለኝ ካልክ ምናልባት ትዕግስት ሊሆን ይችላል መልሱ። ሰዎች ጀምረው የሚያቋርጡበት 3ኛው ምክንያት ትዕግስት ማጣት ነው። ----------+++++++------+++++--------- በእናንተን ህይወት ከእነዚህ ከ3ቱ የቱ ነው ጀምራችሁ እንድታቆሙ ያደረጋችሁ? ሌላም ካለ ከስር ኮመንት ላይ ለሌሎች ሃሳባችሁን አጋሩ👇

3ቱ ጀምረህ ሳታሳካ ምታቆምበት ጥልቅ ውስጣዊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ይህንን ነገር አሳካለሁ ብለ ትጀመርና ብዙ ጊዜ ሳታሳካው በመሃል ታቆማለህ ፣ ድጋሜ ሌላ ግብ ታወጣና በዚህ አመት የተለየ ይሆናል ብለህ ትጀምራለህ አሁንም መሃል ላይ ታቆማለህ።
ችግሩ ከግቡ 🎯 አይደለም።
ደጋግመህ ሳታሳካ ምታቋርጠው በእነዚህ 3 ውስጣዊ ምክንያቶች ነው... በቀጣይ Post 3ቱ ግብህን ሳታሳካ እንድቷቋርጥ ያደርጉህን ነገሮች በዝርዝር እንመለከታቸዋለን... እነዚህን ምክንያቶች ለማወቅ like👍

photo content

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ደሃ መሆናችሁ ራሱ ሃብታም እንዳትሆኑ አስሮ የያዛችሁ ነገር ነው። ብዙዎቻችን ሃሳብ አለን እውቀት አለን ይህን ባደርግ እንላለን ግን ሁሌ ሃሳባችንን ወደ ተግባር ልንቀይር ስንል የሆነ በገንዘብ ብቻ የሚፈታ ወይም ገንዘብ ቢኖረን በቀላሉ ምናልፈው ፈተና ይገጥመናል። ድህነታችን ራሱ ደሃ ሆነን እንድንቀር ወጥመድ ይሆንብናል። አንዴ ደህና ገንዘብ መስራት ስንጀምር ግን ብዙ መንገዶች ይከፈቱልናል። ገንዘብ ብዙ በሮችን ይከፍታል። ሀብታም መሆን ከባድ የሆነው ሀብታም መሆን በራሱ ከባድ ሆኖ ሳይሆን ከድህነት መውጣት ስለሚከብድ ነው። አንድ የሃብታም ልጅ ምንም ከቤተሰብ ገንዘብ ሳይሰጠው ሃብታም መሆን ይችላል ምክንያቱም እሱ ከድህነት መውጣት የለበትም ሃብታም ለመሆን። ጥሩ ትምህርት ፣ ጥሩ ስልክ ፣ ጥሩ ላፕቶፕ ፣ ከባለሃብቶች ጋር ጥሩ ግንኙነት ስላለው በቀላሉ ሚሊዮኖችን መስራት ይችላል። (ገንዘብ ባይኖረውም ሃብታም ስለነበር) አንድ የደሃ ልጅ ግን እንደሱ እኩል ቢጀምር ከባድ ይሆንበታል ምክንያቱም ድህነት ራሱ ማነቆ ነው ። ጥሩ ትምህርት ቤት አይማርም ፣ ጎበዝ ለመሆን ይቸገራል አስጠኚ አይቀጠርለትም ፣ ከባለሃብቶች ጋር ግንኙነት አይኖረውም። ፣ ስልክ ቢኖረውም ፣ ላፕቶፕ አይኖረውም ፣ wifi , internet ማግኘት ካርድ መሙላት ራሱ ከባድ ይሆንበታል። ሁለቱን ልጆች ብንመለከት ሁለቱም ምንም ገንዘብ አይኖራቸውም ይሆናል። ግን የጀመሩት እኩል አይደለም። እንደምንም ያለንን አቅም ተጠቅመን አንዴ ከድሃነት ከወጣን ከዛ በኋላ ያንን ማስቀጠል ቀላል ነው። ስለዚህ የመጀመርያዋ ደረጃ እስክንወጣ ብቻ ነው የሚያደክመው። ሁሌ ህይወት እንደዚህ ከባድ እንደሆነ አይቀጥልም ለ1/2 አመት ጠንክረን መሥራት ብቻ ነው ከኛ የሚጠበቀው። የመጀመርያዋን ደረጃ መውጣት ከባድ ቢሆንም ከዛ በኋላ ያለው ግን ቀላል ነው። ስለዚህ አሁን ጠንክረን ፣ በማስተዋል ሰርተን የመጀመርያዋን ደረጃ ብቻ እንውጣ ሌላው ቀላል ነው።

from my experience ሀብታሞች ይበልጥ ሀብታም ለመሆን ፤ ደሀዎች ሀብታም ለመሆን ከሚሰሩት በላይ ይሰራሉ። Amezing!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏

ውጫዊው አለም በአንተ ህይወት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንዳለውና ስኬታማ እንዳትሆን እንቅፉት እንደሆነብህ ይበልጥ ባመንክ ቁጥር ፣ ይበልጥ ገቢህን የሚወስነው አንተ ሳትሆን አለቃህ እንደሆነ ባመንክ ቁጥር ፣ መንግስት ፣ ሰው ፣ ፖለቲካው አንተን አስሮ እንደያዘህ ባመንክ ቁጥር ይበልጥ ደካማና ተጽዕኖ መፍጠር የማይችል ሰው ትሆናለህ።
Your Enemy Is Victim Mentality.
- Buruk

አንድ እርምጃ🚶‍♂ በመጀመርያ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመድ ፣ መጨረሻው ምንም ግልጽ ባይሆንልህ ፣ እንዴት ግብህ ጋር መድረስ እንደምትችል ቁልጭ ያለ መንገድ ባይታይህም። ግልጽ የሆነልህን አንድ እርምጃ ብቻ ተራመድ። ህይወት ልክ እንደ ጉም😶‍🌫 ናት አንዳንዴ የመንገዱ መጀመርያ እንጂ መጨረሻው አይታይም በተራመድክ ቁጥር ግን ቀጣዩን መንገድ ታያለህ ዝም ብለህ መጓዝህን ስትቀጥል... መጨረሻው (ግብህ) ጋር ትደርሳለህ።
መንገዱ ትክክል ይሁን እንጂ ፣ መጨረሻውን ማየት አይጠበቅብህም።
- Buruk