cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መጽሐፍተ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ መገኛ ቻናል ሲሆን እናንተ መጽሐፍቶቹን እንድትጠቀሙበት ታስቦ የተዘጋጀ ስለሆን እባክዎ ይጠቀሙብት ።በተጨማሪም ከተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸው መጻሕፍት ትጠቀሙበት ዘንድ እናቀርባለን፡እንዲሁም አባሎቻችን እና ተጠቃሚው ይሰፋ ዘንድ ለሰዎች share በማድረግ እንተባበር። @Eotcpdf @Eotcpdf

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
740مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ማኅበራትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ
نمایش همه...
ዮሴፍ(የኀብከ) በቀለ, [5/9/2022 1:21 AM] በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል (ሉቃ 1፡14)›› ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡
نمایش همه...
ዮሴፍ(የኀብከ) በቀለ, [5/9/2022 1:21 AM] ልደታ ለማርያም፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡ የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ መዝ 86፡1-7 እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/›› በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ ‹‹የተቀደሱ ተራሮች›› ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን ‹‹የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡›› ብላ ታስተምራለች፡፡ ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ ኢሳ 11፡1 ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት ‹‹ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/›› በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ›› በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ ‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ (መዝ 131፡13)›› የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡ ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ መኃ 4፡8 በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/›› በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ ‹‹….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡›› በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ) በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም ‹‹ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ›› /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ ‹‹ሄኤሜን››አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)
نمایش همه...
ዮሴፍ(የኀብከ) በቀለ, [5/9/2022 1:21 AM] ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም ‹‹ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡›› ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው:: ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም) በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና ‹‹እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም ‹‹ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው:፡ የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ) ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት ‹‹ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡›› በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ ‹‹እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ›› በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ) የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ 1፡19)፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡” (መሓልይ 4፡7-16) በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡ ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ) የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት ‹‹ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ›› እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን ‹‹ማርያም›› ብለው ሰይመዋታል፡፡ የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም 5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ (ዘፍ. 3፡20) ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ (ዮሐ. 19፡26) ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡
نمایش همه...
መጋቢት ፲ በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው።
نمایش همه...
Repost from Adebabay Media
ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አድዋ ድል እንኳን ለታላቁ ሰማዕት የኢትዮጵያ ገበዝ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችኹ!!! ልመናው ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ በዕውነት ለዘለዓለሙ ይደረግልንና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገው ተአምር ይኽ ነው፡፡ በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 1854 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በ26 ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ፡፡ ከዚኽም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ "ሀገሬ ኢትዮጵያን እወዳለኹ የሚል ኢትዮጵያዊ ኹሉ ባስቸኳይ ይነሣ መስቀለ ሞቱንም ተሸክሞ ይከተለኝ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር ወሰን አልፎ ሀገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት መጥቷልና" ሲሉ ዓዋጅ አስነገሩ፡፡ ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ በጋሻቸው እምብርት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮቹን አዘዟቸው። መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደኾነ አስቀድሞ ያውቁ ነበርና፡፡ ከዚያም ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃዎች አንዷ የምትኾን አድዋ ከምትባል አገር ደረሱ፡፡ የሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲኹም ከቀሳውስቱና ከመነኮሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዙ፡፡ በዚኽም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኮሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ። ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ፡፡ ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ የካቲት 22 ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ የጦር ልብሳቸውን ለብሰው ከሠራዊታቸው ጋር ወደ ጦር ግንባር ኼዱ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝተው ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጦርነቱን ጀመሩ፡፡ የንጉሡ የሣህለ ማርያም ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት አድረው ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመኼድ እጅግ በሚያስደንቅ አነጋገራቸው ኃይለ ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኙ ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ይሰጡ ነበር፡፡ በዕውነትም ለተመለከታቸው ኹሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ይመስሉ ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሳቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር፡፡ የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ፤ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነት መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፉት ነበር፡፡ መጽሐፍ ሹመቱን ሽልማቱን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና፡፡ በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ በጦርነቱ መካከል ሳሉ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲኹም የአክሱም መነኮሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምሕላ ያደርሱ ነበር፡፡ ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አልተለዩም ነበር፡፡ የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር፡፡ በዚኽም ዕለት ይኸውም የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ኾነ። በዚኽም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ። ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚኽም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ፡፡ ከዚኽም የነጎድጓድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ኾነ። ለመዋጋትም አልቻሉም፤ ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረስ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በዓየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ "የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲኽ ማን ያድነናል?" አሉ። ምድር ጠበበቻቸው በዚኽም ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው፡፡ የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታች ኼደች፡፡ ከዚኽም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም ምኒልክ በእግዚአብሔር ኃይልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጁ፡፡ ስለዚኽም በዳዊት የምስጋና ቃል "የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔርን ባለ ዘመኔ አመሰግነዋለኹ፤ ለፈጣሪዬም እዘምራለኹ" አለ። ሕዝቡም ኹሉ "በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመሰግነዋለን፤ የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና ፤ ሠራዊቱንም ኹሉ በምድር ላይ በትኗልና!" እያሉ አመሰገኑ፡፡ በፈጣሪያቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁት፡፡ የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያዊያን ፊት ተዋረዱ። ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም፡፡ በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያኽል ዓረፈች፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክም ከዓድዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠሩ። ስሟንም "ገነተ ጽጌ" ብለው ሰየሟት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ኹሉ ይረዳቸው ነበርና፡፡ ልመናው ክብሩ በእኛ ለዘለዓለሙ በዕውነት ይደርብን!!! ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን። ተአምረ ቅዱስ ጊዮርጊስ
نمایش همه...
+++ ማሰብና ማድረግ እኩል ናቸው? +++ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የኖሩ እጅግ ለእምነታቸው የሚቀኑ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ነበሩ። ታዲያ በአንድ ወቅት ኃጢአትን በማሰብ እና በማድረግ መካከል ስላለው ልዩነት አንሥተው ይከራከሩ ጀመር። ብዙዎቹም "ማሰብና ማድረግ ምንም ልዩነት የላቸውም" የሚል የሚል አቋም ነበራቸው። በስተመጨረሻም ይህን ጥያቄ እንዲመልስላቸው ወደ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይዘው ቀረቡ። ቅዱሱ በምሳሌ ሊያስተምራቸው ስለ ፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ምንም ምግብ ሳይቀምሱ ቆይተው ማታ ለእራት እርሱ ዘንድ እንዲመጡ ጠራቸው። በቤቱም ለዓይን ያማረ ለመብላት ደስ የሚያሰኝ ፈታኝ ማዕድ እንዲያዘጋጁ ለአርድእቱ ተናገረ። እነርሱም እንዳላቸው አዘጋጁ። እንግዶቹም በመጡ ጊዜ በየቦታቸው ተቀመጡ። የተዘጋጀውም መዓድ ከፊት ቀረበ። የምግቡ መዓዛ የምግብ ፍላጎት የሚከፍት ብቻ ሳይሆን የሰዎቹን ረሃብ የሚያባብስም ጭምር ነበር። ከዚያም ቅዱስ ዮሐንስ በቤቱ የሚያገለግለውን ዲያቆን ከመዝሙራት እያወጣ እንዲያነብ አዘዘው። ዲያቆኑም ረዘም ላሉ ሰዓታት ማንበቡን ቀጠለ። እንግዶቹ ግን ከመጎምዠት ብዛት በአፎቻቸው ምራቅ ሞላ። ጸሎቱ አልቆ እስኪመገቡ መቆየት ጣር ሆነባቸው። አሁን ጸሎቱ ተጠናቋል። ይሁን እንጂ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን እንግዶቹን ለመዓዱ እንዲቀመጡ በመጋበዝ ፈንታ "በቃ ወደየቤታችሁ በሰላም ግቡ" ብሎ አሰናበታቸው። ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡት እንግዶችም ደነገጡ። ይህን ያየው ቅዱሱ "ምነው ግራ የገባችሁ ትመስላላችሁ? ምግቡን በደንብ አላያችሁትም? ልትበሉስ እጅግ ተመኝታችሁ አልነበረም?" ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም "አዎን" አሉት። አፈወርቅም "ጥሩ፤ እንግዲያውስ እንደ በላችሁ ይቆጠራላ" ቢላቸው ሁሉም ፈገግ አሉ። በዚህ ጨዋታ መካከል የእነዚያ ክርስቲያኖች ጥያቄ በሚገባ ተመለሰላቸው። ክፉን ነገር በማሰብና በማድረግ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ክርስትና ሐሳብ እና ሥራን መቀደስ ነው። ነገር ግን የሐሳብ ንጽሕና ባይኖርህ "ማሰብ ከማድረግ ጋር እኩል አይደል!" ብለህ በኅሊናህ የቋጠርከውን ክፋት ለማድረግ ራስህን አታደፋፍር። ያሰብከውን እስካልፈጸምህ ድረስ አሁንም ከኃጢአት ወጥመድ የማምለጥ እድሉ በእጅህ ነው። "ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት" ዘፍ 4፥7 ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected]
نمایش همه...
"#በእመቤታችን_ዕረፍት_ጊዜ " እመቤታችን በዚህ ምድር ላይ የኖረችው እድሜ 64 ዓመት ነው፡፡ መላው ዘመኗም ሲሰላ እንዲህ ነው ፡ ☞ ጌታን ሳትጸንስ 15 ዓመት ይህ ማለት 3 ዓመት ከእናት ከአባቷ ቤት 12 አመት በቤተ መቅደስ ☞ ጌታን ጸንሳ ሳለች 9 ወር ከ 5 ቀን ☞ ጌታን ከወለደች በኋላ 33 ዐመት ከ 3ወር ☞ ጌታ ካረገ በኋላ 15 ዓመት ጠቅላላ ሲደመር ☞ 3 + 12+ 9ወር + 33 ዓመት ከሶስት ወር + 15 ( ጌታ ካረገ በኋላ ) = 64 ዓመት እመቤታችን በአጸደ ስጋ ሳለች መላእክት በክንፎቻቸው ተሸክመው ወስደው ዐለመ ነፍሳትን አስጎብኚተዋታል፡፡ በገነት የሚኖሩ ነፍሳትንም "ዛቲ ይእቲ ሕይወትክሙ ኪያሃ ሰብሑ" ሕይወታችሁ እርሷ ናትና እርሷን አመስግኑ ብለው ሰጧቸው እነርሱም ከአዳም ጀምሮ እስከዚያችኛዋ ቀን የሞቱ ሰዎች ነፍሳት ይህን ዝማሬ እየተቀባበሉ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን በምድር ላይ የኖረችው ጥቂት ዘመን ቢሆንም አመታቱ በመከራ የተፈፀሙ ናቸው ከዚህ የመከራ ዓለም ሊያሳርፋት ልጇ በግርማ መለኮት በይባቤ መላእክት ወረደ እመቤታችን የእረፍቷን ዜና የሰማችው በቤተ ዮሐንስ እያለች ነበር፡፡ ስለ ክብሯ ሊቀበላት የወረደው ጌታ ሐዋርያትን ከየአህጉረ ስብከታቸው በፈጣን ደመና ሰበሰባቸው ፡፡፡ እመቤታችንን እንዲሰናበቷት አዘዛቸው ከዚህ በኋላ በአጸደ ስጋ አይገናኙምና ሁሉም ደቀ መዛሙርት ዝቅ ዝቅ እያሉ ተሰናበቷት ፣ በረከቷን ተቀበሏት ፣ ወደ ፈጣሪ እንድታሳስብላቸው አደራ አሏት ፡፡ ከዚህ በኋላ እነ ቅዱስ ዳዊት "ወትቀውም ንግሥት እያሉ" እነ ሰሎሞን " ንዒ ርግብየ " እያሏት ሌሎችም ነቢያት እያወደሷት ፣ የሰማይ መላእክት ማንም ሊሰማው በማይችለው የምስጋና ቃል እየጠሯት ሳሉ በልጇ ቅድስት ነፍሷ ከቅድስት ሥጋዋ ተለይታ በዛሬው ዕለት ጥር 21/49 ዓ.ም በተወደደ ልጇ እቅፍ አርፋለች ፡፡ የእመቤታችን እረፍት ጌታ የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጅ ተድላ ስጋዋን ስለማይሻ ነው ፡፡ እመቤታችን በስጋዋ ብታርፍም ከመ ትንሣኤ ወልዳ ተነስታለች፡፡ እመቤታችን ሆይ ንጽህት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን አሜን ፡፡ እንኳን አደረሰን ዲ/ን አለልኝ
نمایش همه...
ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሊባቡር ከ 1️⃣9️⃣6️⃣0️⃣➖ 2️⃣0️⃣1️⃣4️⃣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከአባታቸው ከአቶ ወልደ አምላክ ሁንዴና ከእናታቸው ወ/ሮ በላይነሽ በዲየ በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር፤ በፍቼ ዞን በሙከጡሪ ወረዳ በበቾ ፋኒሊ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደሴ በሚባል ቦታ በ1960 ዓ/ም ተወለዱ፡፡ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም የጀመሩት ብፁዕነታቸው፤ በገዳሙ ከሚገኘው አንጋፋው የመምህር ገብረ ማርያም ንባብ ቤት መሠረታዊ የግእዝ ንባብ፣ በደብረ ጽጌ ገዳም ከመምህር ልዑል ቅዳሴ ቤት ገብተው የግብረ ዲቁና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በተጨማሪም፡- ከየኔታ መርዓዊ ዜና ከቃል ትምህርት ጀምረው እስከ ዐቢይ ምዕራፍ ያለውን በማጠናቀቅ ጾመ ድጓና ድጓ የተማሩ ሲሆን፤ ከመምህር ወልደ ገብርኤል ዝማሬ መዋሥዕት እንዲሁም ከአቋቋሙ መምህር ከየኔታ በትረ ማርያም ክብረ በዓል፣ መዝሙርና አርባዕት፣ ወርኃ በዓልና መኃትው፣ ስብሐተ ነግህና ኪዳን ሰላም፣ ቅንዋትና አርያም በድጋሚ ዝማሬ መዋሥዕት በሚገባ ተምረው አጠናቅቀው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከመምህር ምሕረተ ሥላሴ የቅኔ ጉባኤ ቤት ቅኔ ተምረው የተቀኙ ሲሆን፤ በድጋሚ ከመምህር አምዴ ጉባኤ ቤት ገብተው ለሁለተኛ ጊዜ ቅኔ ተቀኝተው አገባቡን ቀጽለዋል፡፡ በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም በመምህር ገብረ ኢየሱስ ስም በተቋቋመው የብሉያትና ሐዲሳት ትርጓሜ አዳሪ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት፤ በብሉይ ክፍል ገብተው ለስምንት ዓመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ምክትል መምህር ሆነው አስተምረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ለመንፈሳዊ ትምህርት ካላቸው ፍቅር ብሉይ ኪዳኑን እያስተማሩ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜንና መጽሐፍተ ሊቃውንት በዚሁ በገዳሙ ተምረው ተመርቀዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል መዐርገ ዲቁናን በደብረ ጽጌ ገዳም የተቀበሉ ሲሆን፤ የአበውን ፍኖት በመከተል በታኅሣሥ 24 ቀን 1996 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን በመፈጸም በ1997 ዓ.ም. በጊዜው የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መዐርገ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው መንፈሳዊ ትምህርት ለመቅሰም ከነበራቸው ትጋት ባልተናነሰ መልኩ በአገልግሎታቸውም እጅግ ትጉህ፣ ምስጉንና ሰፊ አስተዋጽዖ ያበረከቱ አባት ነበሩ፡፡ ከሰጡት አገልግሎት ጥቂቱን ስንመለከት፡- በፍቼ ሀገረ ስብከት በስብከተ ወንጌልና በትምህርት ክፍል ሓላፊነት፤ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ካሉ የአብነት ጉባኤ ቤቶች ለተወጣጡ ከ300 ያላነሡ ደቀ መዛሙርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ተከታታይ ሥልጠና ሰጥተዋል፤ በመንፈሳዊ የትምህርት መስክ ያላቸውን መክሊት ከግንዛቤ በማስገባት በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው እንዲያስተምሩ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፤ የደብረ ሊባኖስ አባቶችና ደቀ መዛሙርት በገዳሙ እንዲቆዩላቸው በጠየቁት መሠረት በገዳሙ ቆይተው በመምህራቸው በመምህር ጥበቡ አስናቀ እግር ተተክተው ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በዋና መምህርነት አስተምረዋል፡፡ የብፁዕ አቡነ ሚካኤልን አገልግሎት፣ የትምህርት ዝግጅትና መንፈሳዊ ሕይወት ተመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረገው ምልአተ ጉባኤ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከተ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው እንዲሠሩ መርጧቸው ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ/ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሌሎች 14 አባቶች ጋር ሥርዓተ ሢመታቸው ተከናውኗል፡፡ ብፁዕነታቸው በአገልግሎታቸው ትጉህ፣ ለመንጋቸው እጅግ የሚጨነቁና በተመደቡበት የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ለስማቸው ሐውልት ሆነው የሚመሰክሩ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል፦ በሀገረ ስብከቱ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩ አብያተ ከርስቲያናትን በማሳደስ ለአገልግሎት ምቹ ያደረጉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ማኅበረ ምእመናንን እና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር 14 የሚደርሱ የታላላቅ ካቴድራሎችና አድባራት ህንጻ ቤተ ክርስቲያንን አሳንጸዋል። በሀገረ ስብከቱ በነበረው የአብያተ ክርስቲያናት በየሥፍራው አለመኖር ምእመናን የመካነ መቃብር እጦትን ጨምሮ መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማግኘት መቸገራቸውን የተረዱት ብጹዕነታቸው፤ ችግሩ ባለባቸው አካባቢዎች 22 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል በሀገረ ስብከቱ የሚገኙትን የአብያተ ክርስቲያናት ብዛት ወደ 373 አሳድገዋል። ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ ያለውን የአገልጋይ ካህናት እጥረት እና የስብከተ ወንጌል ውሱን ተደራሽነትን መቅረፍን ዐቢይ ዓላማ በማድረግ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር በመቱ ፈለገ ሕይወት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም እና ካህናት ማሰልጠኛ ማዕከል የአብነት ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ከየወረዳው የተወጣጡ 46 ደቀ መዛሙርት እንዲማሩ አድርገዋል። በሀገረ ስብከቱ ላሉ ምእመናን ወንጌልን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው (አፋን ኦሮሞ) ተደራሽ ለማድረግ አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን የተረዱት እኚህ ደገኛ አባት፤ የካህናት ማሰልጠኛዎች እንዲጠናከሩ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መሠረት ጥለዋል። ከካህናት ማሰልጠኛው በተጨማሪ ሀገረ ስብከቱን በገቢ ለማጠናከር ግምቱ ከሰማንያ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዘመናዊ ባለ 5 ፎቅ ሁለገብ ሕንጻ በማስገንባት ላይ ነበሩ። ብጹዕ አቡነ ሚካኤል የመጻሕፍት ሊቅ በመሆናቸውና በትምህርት መስፋፋት ላይ በርትተው መሥራትን የሚመርጡ ስለነበሩ የካህናት ማሠልጠኛውን ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለማሳደግ የሕንጻ ግንባታን አስጀምረዋል። ምእመናን በመንፈሳዊና በአስኳላ ትምህርት በሁለት በኩል የተሳሉ ሰይፍ እንዲሆኑ በማሰብም የአጸደ ሕጻናት እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በማሳነጽ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል አድርገዋል። የሀገረ ስብከቱን ገቢ ለማሳደግ በመቱ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ሕንጻዎችን በማስገንባት የቤተ ከርስቲያን መገለጫዋ የሆነውን የአካባቢ ጥበቃ በገቢ ማስገኛ አማራጭ እንደሚሆን በማቀድ የመናፈሻ ሥፍራዎችን በመቱ ከተማ በማደራጀት ተፈጥሮአዊ ሀብትን የማስጠበቅ ሥራን ሠርተዋል። ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠማት የሰላም እጦት ወቅት በሀገረ ስብከታቸው ባሉ አድባራትና ገዳማት ጸሎተ ምሕላ እንዲደርስ በማድረግ የሰላም ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ሲጸልዩ ቆይተዋል። ዝም ብለው የሠሩት ሥራቸው ብዙ የሚናገርላቸው፣ እጅግ መንፈሳዊና ተሐራሚ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን መክሊት በብዙ አትርፈው በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ/ም በ54 ዓመታቸው በዕረፍተ ሥጋ ተለይተውናል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም ጥር 16 ቀን 2014 ዓ/ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሓላፊዎችና ምእመናን በተገኙበት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተከናውኗል።
نمایش همه...