cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ወይ ጉድ👀 thoughts🗣

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
492
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

join አርጉና አሪፍ አሪፍ ፊልሞችን ተመልከቱ #share #share
نمایش همه...
نمایش همه...
✨SIRAK VIDEO✨

HD Hollywood BoxOffice movies, HD Tv Series, Translated English-India-China-Tv Series. Plus Computer Apps, Games, Maintenance and Other Computer Services. Address : 0911-007061

‹‹አዎ ኤሊያስን ያጠቁትም እሷን ለማስወገድ እቤቷ ድረስ የሚገድላት ሰው የላኩት ሌሎች የኮሚቴ አባላት ናቸው ፡፡በተለይ ሼክ ጠሀ እና አቶ ከፍያለው?አዎ እነሱ ናቸው ወንጀላቸውን ለማዳፈን ከፕሮፌሰሩ ጀርባ ገዳይ እስኮድ ያሰማሩት"ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች። "ግን የቤቴን መክፈቻ ቁልፍ ፕሮፌሰሩ ብቻ ነው ያለው እሱ ካልሰጣቸው ማን ሊሰጣቸው ይችላል?››አስጠሊታ ስሜት የሚያጭር ጥያቄ በምናቧ ተሠነቀበረ..ነው ወይስ ትናንት አባቴ ሞቶል ብሎ ድንገት ስራውን ጥሎ ወደክፍለሀገር የሄደው የቤቷ ዘበኛ ስራ ይሆን ."አዎ ወይ ዘበኛውን በብር ኃይል አታለውት እንዲተባበራቸው አድርገዋል…ወይ ደግሞ ከፕሮፈሰሩ ቁልፉን ሰርቀውት ይሆናል...አዎ እንደዛ ነው የሚሆነው"እርግጠኛ ሆነች። ስልኳን አነሳችና ደወለችለት ፡፡ዘጠኝ ሰዓት እየተቃረበ ነው፡፡በሁለት ጥሪ ተነሳ፡፡ "ፕሮፌሰር እንዴት ነህ?" "ደህና ነኝ …ምነው ደህና አይደለሽም እንዴ?" ‹‹ሰላም ነኝ›› ‹‹የት ነሽ?" "እንዴት የት ነሽ እቤቴ ነኛ"ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡ ‹‹እቤት የት..ማለቴ እንዴት...?"የሚርገበገብ የተሰባሀረ እና ድንብርብሩ የወጣ ድምፅ "እንዴት ማለት..?." "ማለቴ በዚህ ሰአት በሰላም ልትደውይልኝ አትችይም ብዬ ነው ፡፡ሰዓቱን አይተሽዋል...?ምነው አመመሽ እንዴ?" ልንገረው አልንገረው ...አለበት ?የለበትም ? ከፍተኛ ሙግት ከራሷ ጋር ገጠመች፡፡ "አረ አናግሪኝ...ካልሆነ ልምጣ እንዴ?" "የት" "እንዴት የት? እቤቴ ነኝ አላልሺኝም እንዴ?" "አይ እቤት አይደለሁም..." "አረ ግራ አታጋቢኝ ?የሆንሺውን ነገር ነገሪኝ" ‹‹መቼስ ያን የሚያህል ሰውዬ በዚህ መጠን አያስመስልም››አለችና እውነቱን መናገር ጀመረ… ‹‹የሆኑ ሰዎች ሊያጠቁኝ እቤቴ ድረስ መጥተው ነበር...›› "በፈጣሪ ሊያጠቁኝ ማለት ?›› ይቀጥላል...... #share #share #share ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 @yetedeberut @yetedeberut
نمایش همه...
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች›› ምዕራፍ አንድ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ //// ከለሊቱ 8.15 ሞባይሏ ተንጣረረ… በግማሽ መንቃት ተንጠራርታ አጠፋችውና ወደእንቅልፏ ተመለሠች።ከ3 ደቂቃ ብኃላ የቤቷን መደበኛ ስልክ አንቃጨለ...ድምፁ እየሠመጠችበት ካለ የእንቅልፍ ማዕበል ዳግመኛ መንጭቆ አወጣት :: እያጎረመረመች ተነሳችና በዳበሳ መብራቱን አበራችው።እና መቆም በተሳናቸው እግሮቾ እየተንገዳገደች ስልኩ ወዳለበት ቦታ ሄደችና እጀታውን አንስታ ጆሮዋ ላይ ለጠፈች። ‹‹ሄሎ...ማን ል...በል?" "ዶ/ር አምልጪ...ሊ...ገድ..ሉሽ ...እየ...መጡ ..ነው" ጭል ጭል እያለች ልጥፋ አልጥፋ በማለት ከንፋስ ጋር ትግል እንደገጠመች ቁራጭ ሻማ ለህይወቱ የሚታገል የተቆራረጠ እና እጅጉን የተዳከመ የወንድ ድምፅ..ማንነቱን ወዲያው አወቀችው፡፡ "ኤልያስ..?" "እባ...ክሽ ፍጠ..ኚ" ‹‹ኤልያስ አንተ ደህና ነህ..?ጎድተውሀል እንዴ?"መልስ ሳይሆን የእቃ መንጓጓትና ድምፅ ነው የተሠማት ..ያንን ተከትሎ ከውጭ ተንጋግቶ የሚገባ ሚመስል የእግር ኮቴ፤ ጩኸትና ጫጫታ ጆሮዋ ላይ ለጥፋ በያዘችው ስልክ ውስጥ እየተሰማት ነው፡፡ ‹‹አባዬ ..ምንድነው…?….ቶሎ በሉ አንብላንስ ጋር ደውሉ…››ብዙ ብዙ ድምፅ እየተደራረበ ወደ ጆሮዋ ይገባል፡፡ ‹‹ሄሎ ኤልያስ...ሄሎ አናግረኝ…ሌላ ሰው አለ..ባካችሁ አነጋግሩኝ" ስልኩ አልተዘጋም…ረዘም ላለ ደቂቃ ብትታገስም የሚያናግራት ሰውም አላገኘችም፡፡ ተስፋ ቆርጣ ስልኩን ዘጋችው..የእንቅልፍ ስሜት ተሟጦ ከውስጧ በኖ ስለጠፋ ፍፅም ንቁ ሆናለች።ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው። "ምንድነው የተፈጠረው?"….ቢጃማዋን አውልቃ ሌላ ልብስ እየለበሰች መልስ የማታገኝላቸውን ጥያቄዎችን እየጠየቀች ነው። "ግድያን ምን አመጣው? " የሆነ የመንጎጎት ድምፅ ከውጭ የሠማች መሠላት "ቀስ ብላ ወደመስኮት ተጠጋችና መጋረጃውን በጥቂቱ ገለጥ አድርጋ አይኖቾን ወደውጭ አጨነቆረች።ምንም የሚታያት የተለየ ነገር የለም። "ውይ ከፍራቻዬ የተነሳ በሀሳቤ የፈጠርኩት ነገር ነው"አለችና ዝግጅቷን ቀጠለች..በለበሰችው ልብስ ላይ ረዘም ያለ ብኒ ቀለም ያለው ባለኮፍያ ኮፓርት ደረበች...ኮመዲኖዎን ከፈተችና ውስጡ የነበረውን ብር በማውጣት ወደ ቦርሳዎ ከተተች።መታወቂያ እና ፓስፓርቷን፤ ኤት.ኤም ካርዶን መረጃ የምታከማችበትን 64 ጂቢ ፍላሽ ያዘችና እቤቷን ወደኃላም ሳታይ ግቢዎንም ለቃ ወጣች። የተረገመ አጋጣሚ መኪናዋ ግቢዋ ውስጥ የለችም፡፡ የተወሰነ ያልተለመደ ድምጽ ስላሰማቻት ማታ ወደቤት ስትገባ ነበር ደንበኞቾ የሆኑ ጋራዥ ጋር ጎራ ብላ ለጥዋት እንዲያደርሱላት ጥላላቸው በኮንትራት ታኪሲ ወደቤቷ የገባችው…..ስለዚህ አሁን ያላት ምርጫ በእግር ማምለጥ ነው፡፡ ከቤቷ የውጨኛው በር 20 ሜትር ሳትርቅ ከሩቅ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ሰማች፡፡ በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነች...፡፡ዘላ ከመንገድ ወጣችና በጨለማ የተጋረደ መሸሸጊያ በመፈለግ እራሷን አጣጥፍ በመወሸቅ የሚሆነውን ለማየት እይታዋን ወደመንገድ አስተካከለች ።አልተሳሳተችም አንድ የቀብር አስፈፃሚዎች ድርጅት ንብረት የምትመስል ጥቁር ጨለማ ሚኒባስ እየተክለፈለፈች መጣችና ከእሷ ቤት በራፍ ጋር ስትደርስ ቀጥ ብላ ቆመች። ወዲያው የኃላው በራፍ ተንሸራቶ ተከፈተና ሶስት የሆሊውድ አክሽን ፊልም ላይ የሚተውኑ ሚመስሉ የተወጣጠሩ ወጠምሻ ሰዎች ድብ ድብ እያሉ ወረድ።. "እኚ ሁሉ ለአንድ ሴት ?"ስትል በውስጧ ጠየቀች "አሁን በዚህ ሰውነታቸው ይሄን በአደገኛ ሽቦ የታጠረ ግዙፍ ግንብ አጥር እንዴት አድርገው ዘለው ሊገቡ ነው?›› እያለች ስታሰላስል ይግረምሽ ብለው ቀጥታ እንደቤቱ አባወራ ወደበራፍ ተጉዘው በተዝናና ሁኔታ ቁልፍ ከኪሳቸው አውጥተው በመክፈት ወደውስጥ ሲገብ ባለማመን ተመለከተች።ይሄ እንዴት ሆነ የቤቷ ቁልፍ እሷና ፕሮፌሰሩ ጋር ነበር ያለው፡፡ከዛን በላይ በዛ አካባቢ መቆየት እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ነው ብላ ስላመነች ሚኒባሱ ውስጥ የቀረው ሹፌር እንዳያያት ተጠንቅቃ ከተወሸቀችበት ወጥታ ጥግ ጥጉን እየታከከች ከሰፈሯ ርቃ ወጣች። አሁን ካለችበት መኖሪያ ቤቷ ከሚገኝበት ወሎ ሰፈር ወደብዙ አቅጣጫ ሚወስዱ መንገዶች አሉ..ወደቦሌ መሄድ ትችላለች….በአቋራጭ ወደላንቻ መሄድ ትችላለች..እሷ ግን የያዘችው ወደጎተራ የሚመራውን መስመር ነው….…ጎተራ ማሳለጫው ጋር ስትደርስ ለተወሰነ ደቂቃ ቆመችና ለሰከንድ አሰላሰለች …ከፊት ለፊቷ ሌላ ሶስት ምርጫ አጋጠማት ፡፡ወደግራዋ ታጥፋ ወደ ሳሪስ መሄድ ወደ ቀኞ ታጥፋ ወደ ላንቻና ስቴዲዬም መጎዝ ወይም የፊት ለፊቱን አስፓልት ይዛ ወደቄራ መሸምጠጥ…. ያለምንም ደጋፊ ምክንያት የፊት ለፊቱን መርጣ ጉዞዋን ቀጠለች…...አስር ደቂቃ ከተጓዘች ቡኃላ ከሰፈሯ በጣም መራቋንና አዳኞቾም በቀላሉ ሊያገኞት በሚችሉባት አቅጣጫና ስፍራ ላይ አለመሆኗን ስትረዳ እራሷን ገታ ተረጋግታ ማሰብ ጀመረች ፡፡ ‹‹ከኃላ ከሚያሳድደኝ ሞት ሳመልጥ ፊት ለፊቴ ያልታሰበበት ሞት እንዳይገጥመኝ"አለችና ዙሪያዎን አማተረች….…ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣ ድምፅ እንኳን አይሰማትም ወይም ከመሸታ ቤት ወጥቶ ወደቤቱ እየተወለጋገደ ሚሄድ ሰካራም በስፍራው አይታይም……ብቻ የተወሰኑ መቶ ሜትሮች ወደፊት ጠጋ ብሎ የቄራው አጥር አካባቢ የሚልከሰከሱ የተወሰኑ ውሾች ይታዬታል..በተረፈ አካባቢው ፍፅም ጭር ብሏል... መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው… ከፊት ለፊቷ በአንድ ሜትር ርቀት የትራፊክ መብራት አለ……ትንሽ ሳብ ብሎ ወደሚታየው የባስ ፌርማታ አመራችና ጥጎን ይዛ ቁጭ አለች። ‹‹ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ ላመልክት?›› የሚል ሀሳብ መጣላት፡፡ግን ነገሩ ፖሊስ ጆሮ አንዴ ከገባ ወደኃላ የሚመለስ ነገር አይኖርም…ሄዶ ሄዶ ወንጀሉ በግለሰቦች ደረጃ ታጥሮ አይቀርም ወደ ሆስፒታላቸውም መዛመቱ አይቀርም…ያ ሆስፒታል ደግሞ የእሷም ሀብት ነው……ጠቅላላ ልፋቷንና ህልሞን ያዘለ ተቋም ነው….የእሱ መውደም እሷንም ቀጥታ ያወድማታል….ይሄንን ሁሉ በታትና አሰበችና ‹‹የነገሩን ጭራ በደንብ ሳልይዝ ለጊዜውም ቢሆን ፖሊስ ጋ አልሄድም ››ብላ ሀሳቧን ሰረዘችው፡፡ ‹‹እሺ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ..?››በቀጣይ እራሷን የጠየቀችው ጥያቄ ነው፡፡አሁን ምን ላድርግ..?ማን ጋር ልደውል?ስትል ፕሮፌሰሩ ወደ አእምሮዋ መጣ፡፡ …እዚህ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩ አለበት?"ስትል ህሊናን አዙሮ የሚደፋ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች። ኘሮፌሰር ማለት የስራ ባለደረባዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የረጅም ጊዜ የቅርብ ጓደኛዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የሶስት አመት ፍቅረኛዋ ነው...ኘሮፌሰር ማለት ከአራት ወራት ብኃላ ልታገባው ሽር ጉድ ያለችለት ያለ የወደፊት ባሏ እና የልጇቾ አባት ለመሆን ጫፍ ላይ ያለ ሰው ነው.... ፕሮፌሰር ብዙ የውጭና የሀገር ውስጥ ዪኒቨርሲቲዎች ለሁለት አስር አመታት ያስተማረ በአለም አቀፍ የምርምር ጆርናሎች አያሌ የጥናት ስራዎቹን ያሳተመ የአደባባይ ምሁር ነው.....በዚህ ላይ ሀገሪቱ ከለቻቸው ከአንድ እጣት ከማይበልጡ የልብ ቀዶ ህክምና ሀኪሞች አንዱ ነው፡፡ታዲያ እንዴት ነው ይሄ ሰው የእሷን የትሙት በቃ ውሳኔ ከሌሎች ገዳይና ማጅራት መቺዎቾ ጋር በማበር ሊፈርም የሚችለው?እሷ ስለሆነች አይደለም ሌላ ማንስ ቢሆን እንዴት እንዲህ ያደርጋል? ይሄ ሰው እኮ ለእንስሳት ነፍስ ሁሉ አንጀቱ ከመንሰፍሰፍ የተነሳ ቬጂቴሪያል የሆነ ሰው ነው?..ምንም ሊዋጥላት አልቻለም፡፡
نمایش همه...
ሰላም እንዴት ናቹ በነገሮች ባለመመቻቸት ምክንያት ስለጠፋን ይቅርታ እየጠየቅን በቅርቡ ተከታታይ እና ቆንጆ ታሪክ ልናቀርብላቹ ተዘጋጅተናል።እስከዛው ግን ቻናሉን ሼር እያረጋቹ እንድትጠብቁን እንጠይቃለን። #share #share #share https://t.me/yetedeberut
نمایش همه...
#ሙሉ የቤተሰብህን አባላት ከTelegram ላይ ከ ቦለክ በዋላ when ur Bio says:Family is everything 👀 @yetedeberut
نمایش همه...
🌚ሌሊት ነው በግምት 11:30 አካባቢ ተኝቻለው😴፣ለስራ ለመንቃት እየታገልኩ ነው፣ ድምጻቸውን የሰማውት ፣ከግቢ አልፈው ፣የተኛውበትን ክፍል አካባቢ በቅርብ ርቀት ድምጽ ሰምቼ ነበር። #እንደነቃው፣ አንዱ ሊያጠቃኝ ወደ እኔ እየመጣ እንደሆነ አየሁት ፣ራሴን ከመከላከል ውጪ አማራጭ የለኝም፣ በፍጥነት ቀደምኩት። ሁለተኛው እላዬ ላይ ዘሎ ተከመረ፣ ሁሉም ነገር ለማመን በሚያስቸግር ፍጥነት ነበር እየሆነ ያለው #ፈላው_ወንድሜ👶 ነቅቶ ፣ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓግቷል፣ በስተመጨረሻ ሁለተኛውንም ጠብቄ መታውት፣ እጄ በደም ተጨማልቆ ነበር። ሁለቱም ተዘርረዋል ፣በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አላወኩም፣ አንዱ ሲንቀሳቀስ አየሁት ድጋሚ በንዴት በጣም መታውት፣ ዝዝዝዝ እያሉ ከእንቅልፌ የቀሰቀሱኝ ሁለት ቢንቢዎችን ከለሊቱ 11:40 የገደልኩበት አገዳደል ነበር #ታላቅ_ገድል☺️ @yetedeberut @yetedeberut
نمایش همه...
〰〰15 አስቂኝ የንግድ ስሞች〰〰 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 1.እኔ እና ወንድሜ እንክፈተው አንክፈተው ተባብለን የከፈትነው ወርቅ ቤት።😂 2.ሰው መግደል ብርቅ ነው እንዴ ሽምግልና ስራዎች😂 3.ስዋሬዝ ስጋ ቤት🤣 4.ራዕይ ተገልፆልኝ የበረገድኩት እርጎ ቤት🤣 5.ካመሻችሁ ታድራላችሁ ይርጋአለም ፔንስዮን🤣 6.ሸዋ ዳቦ ምን ያደርጋል ጮርናቄ ቤት😂 7.አማርና ፊልም ጠላሁ ቪዲዮ ቤት😂 8.እህቴ ከጅዳ በላከችው ገንዘብ የከፈትኩት ሻይ ቤት🤣 9.ብንወፍር እንከሳለን በርገር ቤት🤣 10.ሾጥ ከሆኑ በማሳጅ እናስተካክላለን ማሳጅ ቤት😂 11.ጋዝ ለምኔ አጣና እና ከሰል ቤት😂 12.ቀድማችሁ ብትነግሩኝ መንግስተ ሰማያት ትገባላችሁ የሬሳ ሳጥን ቤት🤣 13.ብትጣሉ እናፋታለን ትፅደግ ቬሎ ቤት😂 14.በፍቅሩ ገዳይ አስጎብኚ ድርጅት🤣 15.ፓርላማ ለምኔ ይድነቃቸው የስብሰባ አዳራሽ አከራይ @yetedeberut
نمایش همه...
የ30 አመቱ ሰውዬ ከጎንህ ቁጭ ብሎ አስኮርጀኝ ሲልህ... ኢሳት እያየህ ከምትንዘላዘል አታጠናም ነበር🫥 @yetedeberut
نمایش همه...
ቢዚ ነው ለመባል ቆይታቹ ምትመልሱ ሰዎች ግን ፈጣሪ ይይላቹ😏 @yetedeberut
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.