cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

نمایش بیشتر
أثيوبيا9 113امهری8 199دسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
447
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

እስልምና ግን ውበቱ‼ ================ በየትኛው የዓለማችን ክፍል ላይ አዛን ከሰማን ሳናመነታ ወደዛ መስጅድ እንሄዳለን፣ በእኩል እንቅስቃሴ ወደ አንድ ቂብላ እንሰግዳለን፣ ሙስሊም ሁሉ ወንድማችን ነው፣ የጋራ መመሪያ ቁርኣንና ሐዲሥ አለን፣ አንድ አምላክ ብቻ እናመልካለን… እኛ ማነን? በ"ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ ሙሐመድ ረሱሉ-ል'ሏህ" ገመድ የተሳሰርን ሙስሊሞች ነን‼ ከየትኛውም ዓለም ና፣ ከየትኛውም ቤተሰብ ተገኝ፣ ድሃም ሁን ባለሃብት፣ ባለ ስልጣንም ሁን መደበኛ ህዝብ፣ አካል ጉዳተኛም ሁን ጤነኛ… ያለ ምንም ልዩነት የምትሰግደው በተመሳሳይ ረድፍ (ሶፍ) ላይ ነው፣ የምትሰግደውም ለአንድ አምላክ ብቻ ነው። ድሆችና አካል ጉዳተኞች ወደ ኋለኛው ሶፍ ሁኑ አይባልም። እንዳውም ለነዚህ ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ እንድናደርግ ታዘናል። ምን ያምር ዲን‼ እስልምናችን ኩራታችን! ከጌታችን የተቸረን በዋጋ የማይተመን ልዩ ስጦታችን! ሙስሊሞች አድርጎ እንጂ አይግደለን! || https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

#እርሳስ፦ በጣም ይቅርታ... . #ላጵስ፦ ለምኑ? ምንም ያጠፋኸው ስህተት እኮ የለም . #እርሳስ፦ ይቅርታ!! በጣም ጎድቼሀለው ሁሌ እኔ በተሳሳትኩ ጊዜ እኔን ለማረም ስታጠፋኝ አንተ ደግሞ እያነስክ እየመጣህ ነው . #ላጵስ፦ አዎ ትክክል ነህ..ግን አስቤውም አላውቅም ተመልከት...እኔ ይህንን የማደርገው አንተን ለመርዳት ነው አንተን ከስህተትህ ለማረም ነው በርግጥ አንድ ቀን እንደምጠፋ አስባለሁ....በእውነቱ በስራዬ በጣም ደስተኛ ነኝ ስለዚህ...አትዘን ያንተን ሀዘን ማየት አልፈልግም . "የአንተ/ቺ እናት እና አባት ማለት ላጵስ ናቸው እኛ ልጆቻቸው ደግሞ እርሳስ ነን ሁሌም ስናጠፋ እኛን ሲያርሙን እኛ ደግሞ ምክራቸውን ወደ ጎን ከተውን ልባቸውን በቀላሉ እየጎዳን የኛን ጥሩ ነገር ሳያዩ እድሚያቸው ሊያልፍ ይችላል ስለዚህ እኛም የዋሉልን ውለታ ስላለ እሱን ለመክፈል መዘጋጀት ይጠበቅብናል . #ለቤተሰቦቻችን_ረጅም_እድሜ ፈጣሪ ይስጥልን https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

ሁሌም ግርም የሚለኝ የጌታዬ ቃል‼ «وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ» «አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡» [ኢብራሂም: 42] ይዘገያል እንጂ በዳዮች የእጃቸውን ማግኘታቸው አይቀርም። Tit for Tat‼
نمایش همه...
እናትህን አደራ.mp34.76 MB
ጃፓኖች ማጽዳት ይችላሉ‼ =================== ✍ እኩይ ተልዕኮ አንግበው የመጡትን ጀርመናዊያን ኃፍረት አከናንባ የመለሰችልን በአላህ ፈቃድ ጃፓን ናት። መጀመሪያ ራሷ አሸንፋ፣ ቀጥላም የአሸናፊ ተሸናፊ እንዲሆኑ አድርጋ! ጃፓኖች የተቀመጡበትን የስቴዲየምና የመላበሻ ክፍል ተሸንፈውም ያጸዳሉ ሲባል ተገርመን ነበር። ለካ የሰው ቆሻሻም ማጽዳት ይችላሉ። በ8 ቢሊዮን ህዝብ ኃፍረት ሳይሰማቸው ለግብረ ሰዶማውያን ድምፅ ሲሆኑ የነበሩት ጀርመኖች፤ ዋንጫውን ቢያነሱ ኖሮ imagine የዛ ቀን ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ! ገና የመጀመሪያ ጫዎታቸውን ሲጀምሩ ታፍነናል ብለው ተቃውሞ የጀመሩ፤ ትንሽ ቢሳካላቸውማ…! ልክ እንደነርሱ ስትቅነዘነዝ የነበረችው ዴንማርክም በጊዜ መሸኘቷ የሙፍሲዶችን ጀንበር በጊዜ አጥልቋታል። እነዚህ እኩያን ኦዚል የሚባለውን ሙስሊም ተጫዋች ያገለሉት ለቻይና /ኡጙር/ ሙስሊሞች ድምፅ በመሆኑና ለፍልስጤም በማሰቡ ነበር። የእውነት ለሰው መብት ተቆርቋሪ ቢሆኑ ከግብረ ሰዶማውያን ይልቅ የንጹሐን እልቂትና ጭቆና ባንገበገባቸው ነበር። ሰማያዊውን የጌታችንን ህግጋት የሚጣረስ በሙሉ በዳይ ነው። እነዚህ ከበዳይም በላይ ትውልድ አምካኝ በዳይ ናቸው። እነሆ፦ (فَقُطِعَ دَابِرُ الْقَوْمِ الَّذِينَ ظَلَمُوا ۚ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ) (የእነዚያም የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ፡፡ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይገባው፡፡) [አል-አንዓም: 45] በነገራችን ላይ ጃፓን ውስጥ ብዛታቸው ትንሽ ቢሆንም አቅም ያላቸው ሙስሊሞች አሉ። FYI "Sony" ቴሌቪዥን የነሱ ነው፣ "Hitachi" ፍሪጅ የነሱ እጅ ያረፈበት ነው፣ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን ዓለማችንን ያጥለቀለቀው "Toyota" መኪና የነሱ ጥበብ ውጤት ነው፣ "Nikon" እና "Canon" ካሜራዎች የነሱ አሻራዎች ናቸው፣ "Toshiba" ላፕቶፕ የነሱ ነው፣ "Mazda", "Lexus", "Mitsubishi", "Honda", "Nissan", "Isuzu", "Suzuki" ምናምን የምንላቸው መኪናዎች የተፈበረኩት በነሱ ነው። ከምንም በላይ የናቋቸውን ግብረ ሰዶማውያን ማጽዳታቸው ያስመሰግናቸዋል። || https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

ጓደኛዋን «እስቲ ባሌን ፈትኚልኝ?» አለቻት። "እሺ!" ብላ ፈተነችላት። ባልየውም ፈተናውን በጥሩ ውጤት አልፎ ጓደኛዋን ሁለተኛ አገባት። አንዳንዴ ሪዝቅ ከየትና እንደት እንደሚመጣ አታውቅም¡ (ግን አንዳንድ ሴቶች ባላችሁን አላምነው ስትሉ በሌላ አካውንት ሌላ ሰው አስመስላችሁ ወይም በጓደኛችሁ ለምን ትፈትኑታላችሁ¿) https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

መልካም ሚስት.......! ብዙ አይነት እድለኛ ሰዎች ቢኖሩም ለኔ ግን መልካም ሚስት እንዳለችው ሰው የታደለ የለም ። ከላይ ከአሏህ የተፃፈች መልካም ሚስት ካለችህ  በየትኛውም  ሁኔታ ላይ  ሁነህ እንኳ ሙሉ ሰው ነህ ። የሂወት  ውጣ ውረድ  እና ጉድለት ላንተ ምንም ናቸው ። ወጥተህ እስክትገባ በናፍቆት የምትጠብቅህ  ከውጭ ስትመጣ ደሞ በስስት እያየች ስቃ የምትቀበልህ  ስትናገር የምትረዳህ መልካም ሚስት ስትኖርህ  ችግርህ ድሎት ፣መድከምህ እረፍት፣ መክሰርህ ትርፍ ፣ ማጣትህ ማግኛት፣ ብሶትህ ደሞ  ደስታ ነው። ▸ በቃ መልካም ሚስት ጎንህ ካለች  ከቤት ውጭ ስቱል እንኳ የሚያጋጥሙህን ጥሩ ያልሆኑ አጋጣሚወችን በቅፅበት ረስተህ  ወደ አዲስ የእፎይታ ስሜት ውስጥ ለመግባት  ፊቷን ማየት ብቻ በቂህ ነው። ▸መልካም ሚስት ማለት በሂወትህ  ትልቅ ዋጋ ከምሰጣቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን ልጅ  ትወልድልህና  አይንህን ባይንህ ታሳይሀለች።  አለፍ ሲል ደሞ የወለደችልህን ልጆች በመልካም ባህሪዎቿ  እየኮተኮተች በፍቅር አሳድጋ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰቡን  የሚያከብሩ ከመሆንም በላይ ለእስልምነታቸው፣ ለተውሒዳቸው ፣ለሱናቸው የስምህ_መጠሪያ  የሚሆኑ ጥሩ ልጆች ባለቤት  ታደርግሀለች። መልካመሰ ሚስት ቤተሰቦችህን እና ጓደኞችህን ስለምትወድልህ  ከነሱ ጋር በቂ የሆነ ሰአት  ለመስጠትም ሆነ  ማደረግ ያለብህን ለማድረግ ስለማትቸገረ  የቤተሰብህን ሀቅ_በመጠበቅ በኩል አትዘናጋም። መልካም ሚስት ማህበራዊ ህይወት ላይ ያለህ ተሳትፎም አይቆረፍድብህም  እሷ ከምሰጥህ ፍቅር እና ደስታ በመነሳት በምትኩ አንተ የልጆችህን እና የሷን ሀቅ ለመጠበቅ ብለህ በምታደርጋቸው  የመልካም ነገር_ሩጫወች ከፈጣሪህ ዘንድ  ትልቅ ደረጃ ታሰጥሀለች። መልካም ሚስት የእናት፣የአባትህን፣የእህት፣ወንድምህን  ቦታ ሳይቀር ተክታ በመያዝ ብቻዋን ሁና  ነገር ግን  ባለ ሙሉ ቤተሰብ እንደሆንክ እንዲሰማህ ታደርግሀለች። መልካም ሚስት ካለችህ ሁለም ነገር አለህ  የመልካም ሚስት ደረጃዋ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚወራ እና ተቆነሰጥሮ  የሚያልቅ  ነገር  አይደለም።   ለዛም ነውኮ.... መልካም ከፈጣሪ የምትሰጥ ልዩ ሰው ናት የሚባለው ።  ወንዶች መልካም "ባል" አድርጎን  መልካም ሚስት ይሰጠን ዘንድ እንማፀን። ሴቶች ደሞ  "ሚስት" ብቻ ሳይሆን መልካም_ሚስት  ሁናችሁ  "መልካም ባል" ታገኙ  ዘንድ ምኞቴ ነው።  https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

Photo unavailableShow in Telegram
በዱዓእ ነው ቤተሰብ‼ እስኪ እነዛን «ዐረብ ሩዝ እንጂ ኳስ አይመለከተውም!» ሲሉ የነበሩትን የኛ ሃገር ኩክኒያሞች ጥሩልኝ! ኳታር የተሸነፈችው መድረኩን በቁርኣን ስለከፈተች ነው ያሉት ደናቁራን፤ «ላ ኢላሃ ኢለልሏህ ሙሐመድ ረሱልሏህ» የሚል ሰንደቅ ያላት ሃገር፤ ለዋንጫው የምትጠበቅን፣ ቁጥር አንድ ጎበዝ ተጫዋችና ቡድን ያላትን ሃገር በሚገርም ብቃት ስታሸነፍ ምን ይሉን ይሆን! እንዳውም ዋንጫው ለሳዑዲ ነው የሚገባው! አላህ ይርዳቸው። Viva Saudi‼ || https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
🌺አቤት ማማራቸው🌺 እንደው ጉድ ያሰኘው ይሄ ውበታቸው እነሱን ለማየት ሰዎች ጉጉታቸው 'አቤት ብዛታቸው ጥቁር ነው ልብሳቸው ጥግ ጥጉን ይዘው ሲሄዱ ላያቸው እነዚህ እንስቶች አቤት ማማራቸው ማለቱ ስሰማ እኔም ወደድኳቸው ከላይም እስከታች አሸፋፈናቸው ሲሄዱ በመንገድ አረማመዳቸው ድምፅም አይሰማ ላነጋገራቸው የሰለፍይ ሴቶች አቤት ማማራቸው ምን ይሆን ሚስጥሩ የመሸፈናቸው በሐያእ በአዳብ የመራመዳቸው ሲያወሩ ድምፅን ዝቅ ማድረጋቸው ብለው ተገረሙ ሰዋች ሲያዩዋቸው ሚስጥሩ ወዲህ ነው እኔ ልንገራችሁ በነዚህ እንስቶች ለተገረማችሁ የአላህን ትዛዝ የነብዩን ሱና በነዚያ ቀደምቶች በሰለፎች ፋና ሆኖ ነው ኑሮቸው እንዲህ የተቃና በልባቸው ሰርፆ የአላህ ፍራቻ የነብዩን ሱና ይዘው በክራንቻ ግባቸው ሆኖ ነው ሁሌም ጀነት ብቻ ለዚህ ነው ያማሩት የሌላቸው አቻ እህቴ ካማረሽ ክብርት መሆንን ወንድሜም ከፈለክ ንግስት ማግባትን በሐያእ ተክነሽ ልበሽው ሒጃቡን  አንተም አስለብሳት ለውዷ እህትህ ስታገባም ምረጥ ባለ ዲንዋን ብለህ አባዬም አስለብስ ያንተው ውድ ልጅህ ጥብቅም እንድትሆን ስምህ ልታስጠራህ እንልበስ ባንድነት ሒጃቡን በጋራ በሱሪ በሚን እንዳንሆን ፋራ በኒቃብ በጅልባብ ይሁን ጉዞኣችን ለዱንያም ሰላም ላኸራም ቤታችን። --------🍃🌺🌺🍃----------- https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

# አይገልፃትም! ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፍጥረታት በሙሉ: ባ'ንድ ላይ ከትመዉ ሚዛኑን ቢሞሉ:: ማጋደሉ አይቀርም እስዋ ስትመጣ: እንኩዋንስ ገላዋ ትንፋሹዋ ሲወጣ:: የፍቅርዋ ወላፈን የመዉደድዋ ሺታ: ህመም ይፈዉሳል ያክማል በሽታ:: አይንዋ ከአይኔ አርፎ ስትመለከተኝ: በእጅዋ ገላየን ስትደባብሰኝ:: የፍቅርዋ ሀያልነት የመዉደድዋ ዝና: ተወርቶ የማያልቅ የማይጎድፍ ልቅና:: ለስዋ ተሰጥትዋታል ከታላቁ ጌታ: እናት የክብር ቃል እናት የፍቅር ሺታ! https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta
نمایش همه...
۞ዳዕዋ ~ ሰለፍያ۞

ይህ ግሩፕ የሰለፍዬች ደዕዋ ማሰራጫ የተቀጠፉ ዉሸቶችን በያን ማድረጊያ ኪታቦች ሪከርዶች ጥያቄወች በሀበሻ ምድር የሚለቀቅበት ግሩፕ ነው 🖥️ በ Telegram~Channel ➡

https://t.me/DaewaSelefyaBeAkesta

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.